Afar Mass Media Agency (AFMMA)
СтатистикаThis channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA). AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
- Последний пост
- 5 мая
- Последнее чтение
- ещё не заходили
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 36
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ሚያዝያ 27 የታሪክ ማኅደር ተገልጦ የሚነበብበት የትላንት ትዝታ ብቻ አይደለም፤ ሚያዝያ 27 ለእኛ የታሪክ ማኅደር ተገልጦ የሚነበብበት የትላንት ትዝታ ብቻ አይደለም፤ የአርበኞች አባቶቻችንን እና እናቶቻችንን የድል መንፈስ እንደ ብዕር በመጠቀም አዲስ የታሪክ ምዕራፍ መጻፍ የጀመርንበት የትንሣኤ ጉዟችን መነሻ መሠረት ነው! ሚያዝያ 27 የነፃነት ማስታወሻ ብቻ ሳይሆን፣ ወጣቱ ትውልድ ሀገሩን በክብር ለመረከብ ላቡን የሚያፈስበትና ያለውን የሚሰጥበት የቁርጠኝነት ቀን ነው!። ከ85 ዓመታት በፊት አባቶቻችን በደምና በአጥንታቸው ሀገርን ጠብቀው የማቆየት ታሪካዊ ግዴታቸውን በድል ተወጥተዋል። ዛሬ የታሪኩ ምዕራፍ ተቀይሮ ተረኝነቱ የእኛ ሆኗል፤ እነርሱ በነፃነት ያቆዩልንን ሀገር እኛ በዕውቀታችን፣ በላባችንና በሥራችን የመገንባት የዘመኑ አርበኝነት አደራ አለብን። አባቶች በጠመንጃ ሀገር ጠበቁ፤ እኛ በቴክኖሎጂ ሀገር እንገነባለን። አባቶች ዳር ድንበር አስከበሩ፤ እኛ ድህነትን አሸንፈን ብልጽግናን እናረጋግጣለን። አባቶች ለነፃነት ወደቁ፤ እኛ ለታላቅነት እንቆማለን። ይህ የትውልድ ቅብብል ነው ። ያለ አባቶች ጥበቃ ዛሬ የምንገነባት ሀገር ባልኖረች ነበር፤ ያለ እኛ ግንባታም አባቶች የጠበቋት ሀገር ትርጉም ያለው ሕይወት ለዜጎቿ መስጠት አትችልም። በመሆኑም ትናንት በጀግንነት የተረከብናትን ሀገር፣ ዛሬ በሥልጣኔ አንጸን ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ የሞራል ዕዳ፣ የሀገር አደራ አለብን። ለዚህም ነው ኢትዮጵያዊያን ከስንዴ ልመና ለመላቀቅ ወገባችንን አጥብቀን፣ ማረሻችንን ጨብጠን የተነሳነው፣ ለዚህ ነው አለም እኪደመም ተደምረን 48 ቢሊዮን ችግኝ የተከለነወ፣ ለዚህ ነው ከመቀነታችን ፈትተን፣ ከጉርሳችን ቀንሰን ህዳሴያችንን እውን ያደረግነው፣ ለዚህ ነው የዘመናት የጉስቁልና ምልክት የነበሩ ያረጁ ከተሞቻችንን ለመለወጥ እያመመን የበረታነው፣ ለዚህ ነው የከረሙ ስብራቶቻችንን ለመጠገን እንመካከር ያለነው፣ ለዚህ ነው ዙሪያው ተቸንክሮብን እስከመቼ እንኖራለን ያልነው! ለዚህ ነው የታዳሽ ሀይል መሠረት ለመጣል እየተጋን ያለነው ፣ ለዚህ ነው የአፍሪካ ትልቁን የአቬሽን ማዕከል እየገነባን ያለነው አደራ ስላለብን፣ ሀገርን በላብ የማሻገር አደራ! በመሆኑም በዚህ ታሪካዊ ቀን፣ እያንዳንዱ ዜጋ በተሰማራበት የሥራ መስክ ሁሉ ለሀገሩ ጡብ የሚደረድር የራሱ ዘመን አርበኛ መሆን ይጠበቅበታል። ዛሬ እኛ የምናከናውናቸው የልማት ሥራዎች፣ የምናሳየው ጽኑ አንድነትና ዳር የምናደርሳቸው ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ሀገርን ጠብቀው ላቆዩን አባቶች የምንሰጠው ትልቁ የክብር መግለጫና የታሪክ ምላሻችን ነው።" ክብር ሀገርን ጠብቀው ላቆዩን አባቶች! በትጋት ሀገርን ለሚገነቡ ልጆች! ኢትዮጵያ በላባችን ታላቅ ትሆናለች! ሚያዝያ 27/2018
без подписи
без подписи
без подписи
እንኳን ለ85ኛው የጀግኖች አርበኞች በዓል አደረሳችሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዝያ 27 ቀን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አርበኞች የፋሽስትን ወረራ የቀለበሱበትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ያስከበሩበት በዓል ነው። አርበኝነት ማለት ለሀገር ያለ ዋጋ የሚከፈል ከራስ ወዳድነት የነጻ መሥዋዕትነት ነው። ዓላማውም ሀገርንና ሕዝብን ብቻ ማዕከል ያደረገ ነው። ለግል ወይም ለቡድን በተለየ የሚገኝ ነገር የለውም። ለሀገር ከሚገኘው ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና ክብር ከሚደርስ የዜጋ ድርሻ በቀር። እናትና አባት አርበኞች ከፋሺስት ጋር የተዋጉት ለሀገር እና ለወገን ብለው ነው። በግል ጥቅም ለማግኘትማ ከአርበኝነት ይልቅ ባንዳነት አቋራጭ ነበር። ግን አላደረጉትም። የአርበኝነት ትግሉ ከሦስት ጠላቶች ጋር የተደረገ ነበር። ከራስ ፍላጎት፣ ከባንዳና ከወራሪ ፋሺስት ጋር። አርበኝነት የራስን ጥቅም ለሀገር ጥቅም ሲባል መተው ነው። አርበኝነት የግል ክብርን፣ የግል ሥልጣንን እና የግል ጥቅምን መሠዋት ነው። ይሄንን ለመቀበል ከጠላት በፊት ራስን ማሸነፍ ይጠይቃል። ባንዳዎች ማለት ራሳቸውን ማሸነፍ ያቃታቸው ናቸው። የግል ጥቅምንና ክብርን ማሸነፍ ሲያቅታቸው የሀገራቸውን ክብርና ጥቅም ይሸጣሉ። ባንዳነት ማለት ሀገርን ለራስ ጥቅም በመሸጥ የሚከናነቡት የውርደት ካባ ነው። አርበኞች ከባንዳዎች ጋር ታግለዋል። ባንዳዎች በአንድ በኩል ሀገራችሁን ሽጣችሁ እንደኛ በግል ተጠቀሙ ይሏቸዋል። በሌላ በኩል መንገድ እየመሩ ወራሪውን ያመጡባቸዋል። ያም አልሆን ሲላቸው ሕዝቡን በሐሰተኛ ወሬ ልቡን ይሰልቡባቸዋል። ዛሬም ሦስቱም ጠላቶች አሉ። መልክና ስም ብቻ ቀይረዋል። በሌላም በኩል ዛሬም በየመስኩ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን አርበኞች አሉ። የኢትዮጵያ ብልጽግና እንዲሳካ ብሔራዊ አርበኞችን ይፈልጋል። የራስ ፍላጎትን፣ ባንዳነትን እና ወራሪን እምቢ የሚል አርበኝነት። የኢንዱስትሪ አርበኞች፣ የግብርና አርበኞች፣ የጸጥታ አርበኞች፣ የፖለቲካ አርበኞች፣ የንግድ አርበኞች፣ የዲፕሎማሲ አርበኞች፣ የመንግሥት አገልጋይ አርበኞች፣ የሕክምና አርበኞች፣ የትምህርት አርበኞች፣ ወዘተ. ያስፈልጉናል። ይሄንን በዓል የምናከብረው የየራሳችንን የአርበኝነት ደረጃ በመገምገም ነው። ለኢትዮጵያ ምን ያህል አርበኞች ነን? ዛሬም የግል ፍላጎት የሚያሸንፋቸው ደካሞች አሉ። ሀገርን አፍርሰው የግል ቤት መሥራት የሚመኙ። ትልቁን መርከብ አፍርሰው ትንንሽ ታንኳዎችን ለመሸጥ የሚመኙ። ለቅንጥብጣቢ ነገር ውርደትን ለመሸከም የማይሰቀቁ። ዛሬም ወራሪዎች አሉ። በአካል ሀገርን ለመውረር ካሰፈሰፉት በተጨማሪ ድህነት፣ ኋላቀርነትና ሌብነት የሚባሉ እንደ ሰርዶ ሀገርን ወርረው ሽባ የሚያደርጉ ጠላቶች አሉ። ሀገርን ለባዳ ከሚሸጡት ባንዳዎች እኩል፣ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የሚሸጡ ባንዳዎች አሉ። አገልግሎትንና የሕዝብን ሀብት የሚሸቅጡ ባንዳዎች አሉ። ብሔራዊ አርበኝነት ማለት እነዚህን ሦስት ጠላቶች ታግሎ ማሸነፍ ማለት ነው። ዛሬ የምናየውን የኢትዮጵያ ለውጥና ዕድገት ማስመዝገብ የተቻለው ብሔራዊ አርበኞች በየአካባቢው በመኖራቸው ነው። ብሔራዊ አርበኞች ሦስቱን ጠላቶች እያሸነፉ ቢሆንም ገና ሙሉ በሙሉ ድልን አልተቀዳጁም። ድሉ እንደ ሚያዝያ 27 የሚታወጀው ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌትስትሆን ነው። ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ከሚገኙ ኃያል ሀገሮች አንዷ ስትሆን ነው። ይሄንን ድል እውን ለማድረግ ኢትዮጵያን የሚወዱ የኢትዮጵያ አርበኞች ሁሉ እንዲነሡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ። ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ
без подписи
без подписи