tgindex
አልያብ ቲዩብ - Alyab Tube™️

አልያብ ቲዩብ - Alyab Tube™️

Статистика

🚶‍♀️እንኳን ደህና መጣችሁ 👋 ✨በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን፨ 👉መዝሙር እና የመዝሙር ግጥሞች 👉ኦርቶዶክሳዊት ትምህርቶች እና ጥያቄዋች 👉ስብከት 👉የእለቱን ስንክሳር እና 👉የቤተክርስቲያን ስዕላት ✨የሚለቀቅበት መንፈሳዊ ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
7
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 181
−4 за 4 дн.
Сутки
−1
−0,08%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
189
25 постов
Вовлечённость
16,0%
к подписчикам
Постов в день
1,0
всего 25
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
73
1/48двое суток
83
1/72трое суток
90

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • 13 авг.851из Mekrez_media

    ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፯/7 🌥 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ​በዚች ቀን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ጻድቁ ኢያቄም ተልኮ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስ ያበሠረበትና ቅድስት ሐና የፀነሰችበት ቀን ነው። እንዲሁም የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ "አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ የመሰከረበት መታሰቢያ በዓል ነው። 🌟 ​ጻድቁ ኢያቄምና ባለቤቱ ቅድስት ሐና ልጅ አጥተው በስደትና በጽኑ ጸሎት ይኖሩ ነበር፤ ልጅ ቢሰጣቸውም ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ተሳሉ። ቅዱስ ገብርኤልም ለኢያቄም ተገልጦ የዓለም ሁሉ መመኪያ የምትሆን፣ ለዓለም ድኅነትን የምታመጣ ሴት ልጅ እንደሚያገኙ አበሠረው። ቅድስት ሐናም በዚች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችንን ፀነሰች።🥰 ​በዚችም ቀን ጌታችን በፊልጶስ ቂሣርያ ደቀ መዛሙርቱን "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ፣ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ "አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ" ብሎ መሰከረ። ​ጌታችንም የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖት አድንቆ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ሰጠው፤ የሐዋርያት ሁሉ አለቃና የቤተ ክርስቲያን መሠረት አደረገው። ከእርሱም የክህነትና የሹመት ሁሉ መሠረት ተተከለ። 🌥​"ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ኢያቄምና ሐና፣ በሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም ጸሎት ይማረን፤ በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።" ​ ምንጭ፦ መፅሐፈ ሚስጥር✍️ ​"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" (የቅዱሳንን ዜና/ታሪክ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄     ❤ React ያድርጉ የእመቤታችንን የፅንሷን ብስራትና የታላቁን ሐዋርያ የቅዱስ ጴጥሮስን የእምነት ምስክርነት ታሪክ Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ልደት✍️

  • 13 авг.7913из Mekrez_media

    እንኳን አደረሳችሁ🤗    ነሐሴ  ➐ ጽንሰታ)ለማርያም ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል። ስለ ምን ነው ቢሉ ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው። አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ። "ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ።" "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው።" (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4) ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል። የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ በሕጉ ጸንተው በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር። ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር። ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ። እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም። የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው። አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች። "እንስሳትና አራዊትን እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች። ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ። ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ። በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ በማኅጸኗ ስትደርስ አየ። እርሷ ደግሞ የኢያቄም በትር አብቦ አፍርቶ ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች። ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ። በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች። "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ" "ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ። (ቅዳሴ ማርያም) ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!    REACT❤ ያድርጉ ልደት✍️

  • 12 авг.834из Mekrez_media

    ✨ ዛሬ ክርስቶስን አተረፍን ወይስ...... ❓ የትም ቦታ ክርስቶስን የማታተርፉበት ከሆነ ትታችሁት ዉጡ የትም ቦታ ክርስቶስን የማታገኙበት ከሆነ ጥንቅር ብሎ ይቅር መድሀኒአለምን የማታገኙበት ቦታ የከሰርንበት ንግድ ነዉ ! ከክስረት መድሀኒአለም ይጠብቀን 🙏 አባ ገብረኪዳን    ❤ React ያድርጉ | 📢 ሼር ያድርጉ

  • 12 авг.922из Mekrez_media

    ❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥 አምላኬ ሆይ ሀብት ስጠኝ፤ ጌታ ሆይ ገንዘብን ስጠኝ፤ አምላኬ ሆይ ምግብ ስጠኝ አትበሉ። ጌታ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ያውቃል። መጽሐፍም እንዲህ ይላል "ነገር፡ግን፥አስቀድማችኹ፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ጽድቁንም፡ፈልጉ፥ይህም፡ዅሉ፡ይጨመርላችዃል" 🙌 ልደት🤗 ❤ React ያድርጉ | 📢 ሼር ያድርጉ

  • 11 авг.108из Mekrez_media

    ✨ እግዚአብሔር በጣም ቸር ነው የጠየቅነውን በሙሉ አልሰጠንም። የጠየቅነውን ሁሉ ሰጥቶን ቢሆን ኖሮ ምንአልባት ዛሬን አናይም ነበር። እስቲ ወደኋላ ዘወር ብላችሁ የጠየቃችሁትን ነገር ግን ያልሰጣችሁን አስቡ🙌 ልደት✍️ ❤ React ያድርጉ | 📢 ሼር ያድርጉ

  • 11 авг.11511из Mekrez_media

    ለችግራችን ብቻ ስንጠራው ያልታዘበንን እና እኛን ከመርዳት ፈቅ ያላለን አምላክ እናመስግን🙏 ተመስገን         ያልተውከን...❤️‍🩹 ልደት✍️ ❤ React ያድርጉ | 📢 ሼር ያድርጉ

  • ♡ የድንግል ትህትና ♡ በድንግል ትህትና አለምተደነቀ /2/ እዉነተኛ መጠጥ ከሆዷ ፈለቀ /2/ ሰዉ የሚድንበት ሮማንና ገዉዝ /2/ ከሆዷ ፈለቀ እንደ ምንጭ እንደወንዝ /2/ ፀጋን ስላደላት የመዉለድ ስጦታ/2/ በፍቅር ሳበችው የፍጥረቱን ጌታ /2/ ሰማያዊዉ አምላክ ከእርሷ ሥጋንነሳ /2/ ፀሐይ ስለወጣ ቀረልን አበሣ /2/ እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ሥንከብር /2/ ታላላቅ አንስቶች እናቶች ቢባሉም /2/ አምላክን በመዉለድ እርሷን አያህሉም /2/ እስኪ ተመልከቱት ይህንን ደስታ ይህን ታላቅ ነገር ወልድን በመዉለዷ በፀጋ ሥንከብር /2/ ታላላቅ አንስቶች እናቶች ቢባሉም /2/ አምላክን በመዉለድ ድንግልን አይቀድሙም /2/ እግዚአብሔር ምድርን አየና በመላ /2/ ማርያምን አገኛት ከቤተ-መቅደሱ ከቤቱ ተጥላ ከመላዕክቱ ጋር እየተጫወተች /2/ የሰማዩን መና እየተመገበች /2/    ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈       @AlyabTube021    ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

  • 10 авг.1161из Mekrez_media

    ✨ የሰውን ልጅ ትህትናዉ መሰላል ሆኖ ወደ ሰማይ ያወጣዋል። (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ) ልደት✍️ ❤ React ያድርጉ | 📢 ሼር ያድርጉ

  • 10 авг.13232из Mekrez_media

    ✨ ነገ ምን ይዞ እንደሚመጣ ባለዉቅም ነገን የያዘዉን እግዚአብሔርን አዉቀዋለሁ አምነዋለሁ ! 🤗 ልደት ✍️ ❤ React ያድርጉ | 📢 ሼር ያድርጉ

  • በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላል አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ #ሼር ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈        @Alyabtube021     ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

  • 10 авг.1 28415

    በዓለም ላይ ያለውን ነገር ሁሉ ብታገኝ ነፍስህ ግን ሰላም ካጣች ምን ይጠቅምሀል?እውነተኛ ሰላም የሚገኘው ከእግዚአብሔር ጋር በመታረቅ ብቻ ነው።              ሊቁ  አውግስጢኖስ

  • ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘሰኑይ #ሼር ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈        @Alyabtube021     ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

  • 9 авг.1475из Mekrez_media

    ሲነጋ በነፍስ አባቱ ፊት በንስሐ ለመቅረብ አቅዶ ተኛ ሲነቃም ራሱን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ቆሞ አገኘው...🥹     ዛሬን ለንስሐ እንጠቀም፤ ያለን እሱ ነውና🙌           ሁላችንንም ከዚህ ይሰውረን🙏 ልደት ነኝ😴

  • 7 авг.186из Mekrez_media

    ✨''በከንቱ ጊዜህን አታጥፋ እያንዳንዱ ሰከንድ ወደ ዘለአለም የምትቀርብበት እርምጃ ነዉና ''🤔 ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ልደት✍️

  • 7 авг.1979из Mekrez_media

    ✨እንኳን ለ2018 የፍልሰታ ፆም በሰላም✍️ አደረሳችሁ ❤️🥰 ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን 🙏 ልደት✍️

  • 6 авг.18272из yene_mezmur27

    ይቅርታ ! ከፆመ ፍልሰታ በፊት እያወኩ በድፍረት ሳላውቅም በስህተት ያስቀየምኩህኳቹ የማውቃቹንም ሆነ የማላውቃችሁ በሙሉ በእግዚአብሔር ስም ይቅርታ እጠይቃችኋለሁ።🙏7 እናንተም ይህን ሼር በማድረግ የምታውቋቸውንም የማታውቋቸውንም ሰዎች ይቅርታ በመጠየቅ ፆመ ፍልሰታን በይቅርታ በንፁህ ልብ እንጀምር እላለሁ!!!

  • 6 авг.193из Mekrez_media

    без подписи

  • 6 авг.17741из Mekrez_media

    ✨ ጌታ ሆይ .. 🌥 መከራ ባገኝኝ ጊዜ እግዚአብሔር ትቶኛል ብዬ ተስፋ እንዳልቆርጥ ያገኝኝ ፈተና ለበጎ እንደሆነ መረዳት የሚችል ፅኑ ልቦና ስጠኝ 🙏 ዲ/ን ልደት✍️