"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel
описание
This is a channel dedicated to sharing Orthodox Christian teachings and programs. Among these are: ➯ Commemoration of the Saints (daily synaxarium), religious teachings, hymns, various Orthodox PDFs, current Orthodox Christian information, etc.
20 585
подписчиков
Охват к подписчикам
0,9%
ERR
Реакции к просмотрам
0,26%
52 на 49 постов
Пересылки к просмотрам
0,12%
23
Постов в день
0,3
всего 270
Где отзываются чаще
доля реакций к просмотрам- 21:11без подписи2,86%
- 28 июл.#አቡነ_ጴጥሮስ_ሰማዕት (ኢትዮጵያዊ) ➯ዳግመኛም በዚህች ዕለት ኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት አረፉ፡፡ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ በ1875 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት እንደሚሞቱ አስቀድመው መምህራቸው በትንቢት ነግረዋቸው ነበር፡፡ ‹‹አለቃ ተጠምቀ›› የተባሉ ቅድስናን ከሊቅነት ጋራ አስተባብረው የያዙ የቅኔ መምህራቸው አንድ ቀን አቡነ ጴጥሮስን ጠርተው «ኀይለ ማርያም አንተ ወደፊት ጳጳስ ትሆናለህ፤ በወቅቱም አረመኔ በዚህች ሀገር ይሠለጥናል፡፡ ታዲያ ያኔ አንተ ለነፍስህ ሳትሳቀቅ በሰማዕትነት እለፍ፤ ሰማዕትነት ክፍልህ ነው፣ አደራ›› ብለዋቸው ነበር፡፡ ይኸውም ትንቢት ደርሶ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት ለማረፍ በቅተዋል፡፡ ብፁዕ አባታችን የጵጵስና ስማቸውን ከማግኘታቸው በፊት መመህር ኀይለ ማርያም ይባሉ ነበር፡፡ በልጅነታቸው ወላጆቻቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ በሃይማኖትና በምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉ አድርገዋቸዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓተ ትምህርት ከንባብ እስከ ቅኔ ያሉትን ትምህርቶች በሚያስገርም ፍጥነት ከተማሩ በኋላ ወደ ቅኔው አውድማ ጎጃም በመሄድ በሸዋራ የቅኔ ትምህርታቸውን ፈጽመው መምህር ሆነዋል፡፡ የዜማውንም ትምህርት ወደ ጎንደር ሄደው ተምረዋል፡፡ በመቀጠልም ወሎ ቦሩ ሜዳ ላይ ወንበር ዘርግተው የመጻሕፍትን ምሥጢር ይመግቡ ወደነበሩት ወደ ሊቁ አካለ ወልድ ዘንድ በመሄድ ዋና ዋናዎቹን የመጻሕፍት ትርጓሜ ማለትም ብሉያትን፣ ሐዲሳትንና ሊቃውንትን በሚገባ አሒዱ፡፡ ከዚህ በኋላ በ1900 ዓ.ም ወሎ አምሐራ ሳይንት ሄደው በምስካበ ቅዱሳን ገዳም ገብተው ወንበር ዘርግተው ለ9 ዓመታት ቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ፡፡ በ1910 ዓ.ም ወደ ደብረ ሊባኖስ መጥተው ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጸሙ፡፡ ከዚያም መምህርነት ተሹመው ደብረ መንክራት ምሁር ኢየሱስ ገዳም ሄደው ለ6 ዓመታት ካስተማሩ በኋላ በ1916 ዓ.ም እንደገና በዝዋይ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም በመምህርነት ተሹመው ለ3 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በ1919 ዓ.ም ወደ አ.አ በመምጣት የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ መምህርና በቤተ መንግሥት የግርማዊ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ የንስሓ አባት ሆኑ፡፡ ➯ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በራሷ ተወላጅ ጳጳሳት ልጆቿ እንድትመራ ከ1600 ዓመታት በኋላ ስለተፈቀደላት ከዚህ በኋላ በሃይማኖታቸውና በስነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው አምስት ደጋግ አባቶች ሲመረጡ አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ነበሩ፡፡ በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የራሷን ጳጳስ ስትሾም አቡነ ጴጥሮስ ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም ጵጵስና ተሾሙ፡፡ ከዚህም በኋላ ብፁዕ አባታችን ‹‹አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቀ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዐ›› ተብለው በያኔው መንዝና ወሎ ሀገረ ስብከት ተሾሙ፡፡ ➯ብፁዕ አባታችንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንና ቅድስት ሀገራችን በጸሎታቸው፣ ሕዝቡን በትምህርታቸው እየጠበቁ በተጋድሎ እየኖሩ ሳለ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት በ1928 ዓ.ም በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን አውጆ ሕዝቡን በግፍ ይገድል ቤተ ክርስቲያንን ያቃጥል ጀመር፡፡ በየገዳማቱ እጅግ በርካታ ካህናትና መነኮሳት ተገደሉ፣ ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያን ቅርሶች ተዘረፉ፡፡ አቡነ ጴጥሮስም ይህንን ግፍ በማየታቸው ከሀገራችን አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎታቸው ሊዋጉት ተነሡ፡፡ አባታችን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ተከትለው ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ማይጨው ዘምተዋል፡፡ ፋሺስቱ በማይጨው በመርዝ የተደገፈ ጦርነት ከማድረጉ የተነሣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበታተንም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ወደ አ.አ የተመለሱት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው ለአገርና ለነፃነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሠላሌ አርበኞች በሚገባ አስተምረዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ ጫካዎች ውስጥ መሽጎ የነበረው የእነ ደጃዝማች አበራ ካሣ አርበኛ ጦር እና በሸንኮራ በኩል መሽጎ የነበረው የእነ ፍቅረ ማርያም አርበኛ ጦር እንደሁም በምዕራብ ይመራ ከነበረው የእነ ደጃዝማች አባ ነፍሶ ጦር ሦስቱም በአንድ ጊዜ ወደ መሐል አ.አ በመግት አ.አ ላይ መሽጎ የነበረውን ፋሽስትን ለመውጋት ታቅዶ የነበረው ዕቅድ በመረጃ ክፍተት ምክንያት ውጤታማ ሳይሆን ቀረ፡፡ በተለያየ ጊዜ መሐል አ.አ እየደረሱ ማለትም በመጀመሪያ የእነ ፍቅረ ማርያም አርበኛ ጦር ለብቻው በኮተቤ አድጎ የካ ሚካኤል ላይ ሲድርስ ተመቶ ተመለሰ፤ ይሄኛው እንዳለቀ ቀጥሎ የእነ አባ ነፍሶ ጦር በባቡር ጣቢያ መጣሁ ቢልም በጠላት ጦር ድካሚ ተመቶ ተመለሰ፤ መጨረሻ ላይ የእነ ደጃዝማች አበራ ካሣ አርበኛ ጦር በእንጦጦ በኩል ቢመጣም እርሱም በጠላት ጦር ተመቶ ተመለሰ፡፡ ➯በዚህ ዓይነት ሁኔታ ሦስቱም የአርበኞች ጦር በመረጃ ክፍተት ምክንያት እየተመታ ወደመጣበት ሲመለስ አቡነ ጴጥሮስ አብረው ከአርበኛው ጦር ጋር መመለሱን አልፈለጉትም ይልቁንም ‹‹ብችል ጠላት በኢትዮጵያውያን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በቅርብ ርቀት ሆኖ የሚመለከተውን ሕዝብ በማትጋት በጠላት ላይ እንዲነሣ አደርገዋለሁ ካልሆነም ደግሞ እዚሁ እሞታለሁ›› በማለት አባታችን ከአርበኞቹ ተነጥለው አ.አ ቀሩ፡፡ ይሁን እንጂ ጠላት በመላዋ ከተማ ያሰማራቸው ባንዳዎች አባታችንን እንዳሰቡት ሊያነቀሳቅሷቸው አልቻሉም ነበር፡፡ በመሆኑም አባታችን ‹‹የሀገሬን ሕዝብ ለጠላት እንዳይገዛ በአደባባይ አውግዤ ጠላትን ረግሜ በሰማዕትነት ባልፍ ይሻለኛል›› ብለው ራሳቸውን ለጠላት አሳልፈው ለመስጠት ወሰኑና የፋሺስት ኢጣሊያ እንደራሴ ለሆነው ለራስ ኀይሉ ሄደው እጃቸውን ሰጡት፡፡ እርሱም ብፁዕ አባታችንን ወስዶ ለግራዚያኒ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም አሳልፎ ሰጧቸው፡፡ ግራዚያኒም ግማሽ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዲገደሉ ወሰነባቸው፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በፈቃዳቸው እጃቸውን አሳልፈው ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ በጠላት የጥይት እሩምታ በሰማዕትነት እስካለፉበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሒደት ኮርየሬ ዴላሴራ የተባለው ጋዜጣ ወኪልና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው ፖጃሌ የተባለው ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ ሰኔ 15 ቀን 1936 ዓ.ም በአዲስ አበባ በነበረ ጊዜ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ የተሰጠውን ፍርድና የተፈጸመውን የግፍ ግድያ ባየውና በተመለከተው መንገድ እንደሚከተለው ጽፎ ነበር፡- ‹‹ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም አቡነ ጴጥሮስ ተይዘው ወደ ግራዚያኒ ቀረቡ፡፡ ➯በዚህ ጊዜ አቡነ ቄርሎስ የተባሉት ግብፃዊ ጳጳስ ቀርበው ‹ለእስክንድርያው መንበረ ፓትርያርክ ምክር ቤት ሳታሰማ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ እንዳች ነገር ማድረግ አይገባህም››› ሲሉ ለግራዚያኒ ነገሩት፡፡ አቡነ ቄርሎስ ይህን ማለታቸው በዲፕሎማቲክ ደረጃ ለዓለም ለማሰማትና የአቡነ ጴጥሮስን ሕይወት ለማትረፍ አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ግራዚያኒ የአቡነ ጴጥሮስ የሞት ፍርድ እንኳንስ እስከ ግብጽ ከአ.አ ውጭ እንኳ ከመሰማቱ በፊት በግማሽ ቀን እንዲፈጸም መመሪያ አስተላላፈ፡፡ ወደ ምሥራቅ አፍሪካው ዜና መዋዕል አዘጋጁ ወደ ፖጃሌ ዘገባ እንመለስና የአቡነ ጴጥሮስን መልካቸውንና ተክለ ቁመናቸውን እንዲህ በማለት ይገልጸዋል፡- ‹‹ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም፣ ፊታቸው ዘለግ ያለ፣ መልካቸው ጠየም ያለ፣ ዐዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድ የተሰየሙት.........2,35%
- 6 авг.#ዝክረ_ቅዱሳን_ነሃሴ_1/፩ እንኳን #ለቅድስት_ጾመ_ፍልሠታ_ለማርያም እና #ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! #ጾመ_ፍልሠታ_ለማርያም ➯ቸር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ…1,97%
- 6 авг.#ዝክረ_ቅዱሳን_ነሃሴ_1/፩ እንኳን #ለቅድስት_ጾመ_ፍልሠታ_ለማርያም እና #ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! #ጾመ_ፍልሠታ_ለማርያም ➯ቸር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ #ጽድቅ መድረስ አይቻልም:: ➯ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው:: ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 7 አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች:: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው:: ➯"ፈለሠ" - ሔደ: ተጉዋዘ እንደ ማለት ሲሆን " ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው:: እመ ብርሃን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም:: ➯ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና:: ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው:: ከ7ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት:: ➯ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ:: ➯የኔ ብጤ ደካማ ደግሞ ጠዋት ማታ ወደ ደጇ እየተመላለሰ "አደራሽን ድንግል" ይላታል:: ➯በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን:: ➯ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ልበለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን:: ➯ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን:: #ቅዱሳን_ዮሴፍና_ኒቆዲሞስ ➯እጅግ የተወደዱ: ሞገስ የሞላላቸውና ፈጣሪያቸውን በክብር ገንዘው የቀበሩ አባቶች ናቸው:: #ቅዱስ_ዮሴፍ_ዘአርማትያስ ➯ቅዱሱ በእሥራኤል ምድር ተወልዶ ያደገ: ኦሪትን የተማረ ባለጠጋ ሰው ነው:: የተማረ ደግ ሰው ነውና የክርስቶስን መምጣት በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ባገኘውም ጊዜ በአዳኝነቱ (በመሲህነቱ) አምኖ በስውር ተከታዩ ነበር:: #ቅዱስ_ኒቆዲሞስ ➯ወንጌል እንደሚነግረን ይህ ሰው የአይሁድ አለቃ: መምሕር: ዳኛ እና ሃብታም ሰው ነበር:: እነዚህ ሁሉ ማነቆዎች ግን እርሱን ከፈጣሪው ሊያስቀሩት አልቻሉም:: ሌሊት እየመጣ ከጌታችን እግር ይማር ዘንድም አድሎታል:: በመካከልም ከአይሁድ ጋር ብዙ ተጋጭቷል:: ➯ሁለቱ አባቶች መድኃኒታችን ስለ እኛ ሲል ሞቶ ባለበት ሰዓት ላይ በእርሱ የደረሰ ይደርስብናል ሳይሉ በድፍረት ሥጋውን ከዺላጦስ ተካሠው ለመኑ:: እንባቸው በፊታቸው እየወረደ ከመስቀል አውርደው በዮሴፍ በፍታና በኒቆዲሞስ ሽቱ ገነዙት:: እንዲህ እያሉ:- ➯"ሙታንን የምታስነሳ ጌታ አንተ ሞትክን?! ደካሞችን የምታጸና ቸር አንተ ደከምክን?!" በዚያች ሰዓት ጐልጐታ አካባቢ ዝማሬ መላእክትን እየሰሙ የክብር ባለቤትን ቀብረውታል:: ጌታችንም ከተነሳ በሁዋላ በንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ➯"እየሳማችሁ አክብራችሁ እንደ ገነዛችሁኝ እኔም በሰማይ በእንቁ ዙፋን ላይ አስቀምጣቹሃለሁ" ብሏቸዋል:: "አነ አብረክሙ ዲበ መንበረ ሶፎር" እንዲል:: ጻድቃን አበው ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በተረፈ ዘመናቸው ወንጌልን ሰብከው: ከአይሁድ መከራን ታግሰው: በበጐ ሽምግልና ዐርፈዋል:: #ቅዱስ_አቦሊ_ሰማዕት ➯ቅዱስ አቦሊ የሰማዕታቱ ቅዱስ ዮስጦስና ቅድስት ታውክልያ ልጅ ሲሆን በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ያበራ የቤተ ክርስቲያን ዕንቁ ሰማዕት ነው:: የሚገርመኝ ሦስቱ የግማሹ ዓለም አስተዳዳሪዎች ነበሩ:: ዮስጦስ ንጉሥ: ታውክልያ ንግሥት: አቦሊ ደግሞ ልዑል ነው:: ➯ነገር ግን ይህንን ክብራቸውን በክርስቶስ ፍቅር ጐን: ሚዛን ላይ ቢያኖሩት በጣም ቀሎ ታያቸው:: 3ቱም ከዙፋናቸው ወርደው: ወገባቸውንም ታጥቀው: ባሮቻቸው በነበሩ ሰዎች ስለ ክርስቶስ ብዙ ተንገላቱ:: መራራ ሞትንም ታገሱ:: ➯በተለይ ቅዱስ አቦሊ ከአንጾኪያ ወደ ግብጽ (ብስጣ) ይዘው አምጥተው ክርስትናውን እንዲተው ያላደረጉት የለም:: በቁሙ ቆዳውን ገፈው: በቆዳው አቅማዳ ሰፍተው: ያንንም አሸክመው: የተገፈፈ አካሉን ጨውና ኮምጣጤ እየቀቡ አዙረውታል:: ➯እርሱ ግን ጌታ በላከለት ድንቅ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ሁሉን ችሎታል:: በዘመኑ ብዙ ተአምራትን የሠራ ሲሆን አንድ ጊዜ ቤት ተንዶ 16 ሰዎች ቢያልቁ የተገፈፈ ቆዳውን እየጣለባቸው ተነስተዋል በተአምራቱና በተጋድሎውም ብዙ ሺህ አሕዛብን ለክርስትና: ብሎም ለሰማዕትነት አብቅቷል:: ➯እርሱም ከብዙ የመከራ ጊዜያት በሁዋላ በዚህች ቀን አንገቱን ተከልሏል ጌታችን "ዜናሕን የጻፈውን: ያነበበውንና የሰማውን ይቅር እለዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳንን ሰጥቶታል:: ➯ፈጣሪ ከጻድቃንና ሰማዕታት በረከትን አይለይብን:: ወርሐ ነሐሴንም ለበረከት ይቀድስልን:: ወስብሐት ለእግዚአብሔር @AndEmnet ነሃሴ ፩ ቀን1,75%
- 10 сент. 2025 г.без подписи0,89%
- 28 июл.#ቅዱስ_ለውንትዮስ (ስንክሳር) ➯በዚህችም ቀን ቅዱስ ለውንትዮስ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ቅዱስ ክርስቲያን ከሀድያን ከሆኑ ሠራዊት ጋር ይኖር ነበር ሀገሩም ጠራብሎስ ነው መልኩም ያማረ በገድሉም ፍጹም የሆነ ነበር። አምላክ ያስጻፋቸው መጻሕፍትንም ያነብ ነበር።ይልቁንም የዳዊትን መዝሙር ሁልጊዜ ያነብ ነበር። ባልንጀሮቹ ለሆኑ ወታደሮችም ያስተምራቸው ይመክራቸውም ነበር።እግዚአብሔርንም እንዲፈሩ ያስገነዝባቸው ነበር። የማይጠቅሙ የረከሱ የአማልክትንም ሸክም ከትከሻችሁ ጣሉ ይላቸው ነበር። ከስሕተትም ተመልሰው ክብር ይግባውና በጌታችን ያመኑ አሉ። ከእነርሱም ወደ መኰንኑ ሒደው ለውንትዮስ አማልክትን አቃለላቸው ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ የፈጠረ ክርስቶስ ነው ይላል ብለው የከሰሱት አሉ። መኰንኑም በሰማ ጊዜ ወደርሱ አስቀርቦ ጠየቀው እርሱ ግን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስን እንደሚያመልከው በመኰንኑ ፊት ታመነ ጳውሎስ ከፈጣሪዬ ከክርስቶስ ማን ይለየኛል እንዳለ ከታናሽነቴ ጀምሮ በፍጹም ልቡናዬ አመልከዋሁ ለእርሱም እሰግዳለሁ አለው። መኰንኑም እጆቹንና እግሮቹን አሥረው በወህኒ ቤት ውስጥ እንዲጥሉት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። በማግሥቱም መኰንኑ አቅርቦ እንዲህ አለው በምን ኃይል የንጉሥን ትእዛዝ ደፍረህ ትተላለፋለህ ሰዎችንም አማልክትን ከማምለክ በምን ኃይል ትመልሳቸዋለህ ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት። በእውነት ሰዎች ሁሉ ክብር ይግባውና ወደጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት እንዲገቡ እኔ እሻለሁ አንተም ስሕተትህን ትተህ ክብር ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስን ብታመልከው የረከሱ አማልክትንም ማምለክ ብትተው የዘለዓለም መንግሥትን በወረስህ ነበር። ➯ይህንንም በሰማ ጊዜ መኰንኑ እጅግ ተቆጣ ደሙ እንደ ውኃ እስኪፈስ ድረስም ይገርፉት ዘንድ አዘዘ እርሱም እግዚአብሔርን ፈጽሞ ያመሰግነው ጀመረ። ከወታደሮችም አንዱ አዘነለትና በጆሮው አሾከሾከ እኔ ስለአንተ አዝናለሁ ጉልምስናህንም ላድን እወዳለሁ አንተ ለአማልክትም እንደምትሠዋ ለመኰንኑ አንዲት ቃልን ብቻ ተናገር እኔም እዋስሃለሁ አለው። ቅዱሱም ሰይጣን ከኋላዬ ሒድ ብሎ ገሠጸው። መኰንኑም ጭካኔውን አይቶ ሥጋው እስከ ሚቆራረጥ ደሙም እንደ ውኃ በምድር ላይ እስኪፈስ ድረስ ሥቃዩን እጥፍ ድርብ አደረገበት። ከዚህም በኋላ በውኃ እንዲዘፍቁት በእግሩም እንዲጐትቱትና በወህኒ ቤት እንዲጥሉት አዘዘ በዚያም ነፍሱን አሳለፈ ገድሉንም ፈጸመ። የምታምን ሀብታም ሴት መጥታ ለወታደሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥታ የቅዱሱን ሥጋ ወሰደች በአማሩ ልብሶችም ገነዘችው የወርቅ ሣጥንም አሠርታ በውስጡ አኖረችው። ሥዕሉንም አሣለች በፊቱም ሁልጊዜ የሚያበራ ፋና አኖረች። ለዚችም ሴት ቅዱሱ ያደረገላት የድካም ዋጋዋ ሰኔ አንድ ቀን ተጽፎ አለ። ➯ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። #ስንክሳር ሐምሌ 22 እና #ከገድላት_አንደበት0,71%
- 25 июл.без подписи0,58%
- 18 июн.без подписи0,54%
- 29 нояб.без подписи0,50%
- 31 авг. 2025 г.без подписи0,49%
- 28 маябез подписи0,48%
- 15 нояб.без подписи0,38%