- Последний пост
- 16:43
- Последнее чтение
- ещё не заходили
- Постов за неделю
- 38
- Всего постов
- 38
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 33
- 1/48двое суток
- 37
- 1/72трое суток
- 40
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አብን በምክክሩ ሂደት ላይ የደረሰበትን ድምዳሜ እንደማይቀበለው ገለጸ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ በምክክሩ ሂደት ላይ "ከተራ የአሠራር ግድፈት" የዘለሉ "ተደጋጋሚ እና የተደራጁ ጥፋቶች ተፈጽመዋል" ሲል ያቀረበውን ክስ ውድቅ አደረገ። አብን ቅዳሜ ነሐሴ 092018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በሀገራዊ ምክክሩ "ገዢው አካል መዋቅራዊ ጥሰቶችን" እንደፈጸመ በመጥቀስ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ "የከተማዋ ነዋሪዎች ድምፅ እና ፍላጎት በአግባቡ ሳይወከል" ታልፏል ብሎ ነበር። ፓርቲው በዚሁ መግለጫው ላይ ሂደቱ ውስጥ ታይተዋል ያላቸውን "አግላይ እና አፋኝ አካሄዶች" በተመለከተ ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በደብዳቤ አቤቱታ ማቅረቡን ገልጿል። ይህንን የአብን መግለጫ በሚመለከት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሰኞ ነሐሴ 112018 ዓ.ም. በሰጠው ምላሽ የምክክር ሂደቱ "አካታች እና አሳታፊ አይደለም የሚለውን የአብን አቋም ኮሚሽኑ ተገቢውን ምርመራ እና ማጣራት" ማድረጉን ገልጿል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
በሁለቱ የኢሕአፓ ፖለቲከኞች እና በጠበቃ አበራ ላይ "ታጣቂዎችን ሲያደራጁ ነበሩ" የሚል ተጨማሪ ውንጀላ ቀረበ በሽብር የተጠረጠሩት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ፖለቲከኞች አበበ አካሉ እና ይሳቅ ወልዳይ እንዲሁም በጠበቃ አበራ ንጉሥ፣ ከ "ፅምዶ" እና ሌሎች ታጣቂዎች ጋር አላቸው ከተባለው ግንኙነት በተጨማሪ በዘይሴ ብሔረሰብ ውስጥ "ታጣቂ ኃይሎችን ሲያደራጁ" እንደነበር በማስረጃ ስለማረጋገጡ ፖሊስ ገለፀ። ፖሊስ ይህን ያለው፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ለችሎት ባቀረበው ማመልከቻ ላይ ነው። የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሰኞ ነሐሴ 112018 ዓ.ም ለዋለው ችሎት ባቀረበው በዚሁ ማመልከቻው ላይ፣ በፍርድ ቤቱ በተሰጠው የ12 ቀናት የምርመራ ጊዜ ውስጥ አከናወንኳቸው ያላቸውን ተግባራት በዝርዝር ሪፖርት አድርጓል። ተጠርጣሪዎቹ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ ዙሪያ በሚገኘው የዘይሴ ብሔረሰብ ውስጥ "ታጣቂ ኃይሎችን ሲያደራጁ የነበሩ መሆኑን በማስረጃ የማረጋገጥ ሥራ ሠርተናል" ሲል ፖሊስ በሪፖርቱ አመልክቷል። በተጨማሪም፣ እስከተያዙበት ቀን ድረስ "ጫካ ያሉ ፀረ-ሰላም ኃይሎች" ካላቸው አካላት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በስልክ ሲገናኙ እንደነበር ጠቅሷል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
የቀድሞው የሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ አዛዥ የአማራ ክልል ፖሊስን እንዲመሩ ተሾሙ የቀድሞው የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አሚሶም) አዛዥ ሌተናንት ጄነራል ጥጋቡ ይልማ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ። ላለፈው አንድ ዓመት ከአምስት ወራት ገደማ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው የሰሩት ዶር ዘላለም መንግሥቴ ወደ ቀድሞ ኃላፊነታቸው እንደተመለሱ ተገልጿል። አዲሱን አዛዥ ሌተናንት ጄነራል ጥጋቡ የሾሙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ መሆናቸውን የክልሉ ፖሊስ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል። ላለፉት ሦስት ዓመታት ግጭት ውስጥ ያለውን የአማራ ክልል የፖሊስ ኃይል የመምራት ኃላፊነትን የተረከቡት ሌተናንት ጄነራል ጥጋቡ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከ40 ዓመት በላይ ልምድ ያላቸው ወታደራዊ መኮንን ናቸው። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
የኢንስታግራም እና ፌስቡክን ገጽታ እስከወዲያኛው ሊለውጥ የሚችለው የፍርድ ቤት ክስ ሜታ ታዳጊዎችን ለአደጋ ከማጋለጥ ጋር የተያያዙ ተከታታይ ክሶች ቀርበውበታል። የኩባንያው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች የታዳጊዎችን ደኅንነት አልጠበቁም በሚል ከቀረቡት ክሶች አንዱ ነገ ማክሰኞ በፍርድ ቤት ይታያል። ከሕዝብ በተውጣጡ ፍርድ ሰጪዎች (ጁሪ) የሚታየው ክስ ሜታ ከገጠሙት ፈተናዎች ትልቁ እንደሚሆን ተገልጿል። ክሱ የተመሠረተው በአውሮፓውያኑ 2023 ሲሆን፤ ከሳሾቹ ካሊፎርኒያ እና ኒው ዮርክን ጨምሮ 30 የአሜሪካ ግዛቶች ናቸው። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
የኢንስታግራም እና ፌስቡክን ገጽታ እስከወዲያኛው ሊለውጥ የሚችለው የፍርድ ቤት ክስ ሜታ ታዳጊዎችን ለአደጋ ከማጋለጥ ጋር የተያያዙ ተከታታይ ክሶች ቀርበውበታል። የኩባንያው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች የታዳጊዎችን ደኅንነት አልጠበቁም በሚል ከቀረቡት ክሶች አንዱ ነገ ማክሰኞ በፍርድ ቤት ይታያል። ከሕዝብ በተውጣጡ ፍርድ ሰጪዎች (ጁሪ) የሚታየው ክስ ሜታ ከገጠሙት ፈተናዎች ትልቁ እንደሚሆን ተገልጿል። ክሱ የተመሠረተው በአውሮፓውያኑ 2023 ሲሆን፤ ከሳሾቹ ካሊፎርኒያ እና ኒው ዮርክን ጨምሮ 30 የአሜሪካ ግዛቶች ናቸው። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
"ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው" አራት የዘመነ ሕዳሴ ሥዕሎች ከጣልያን ሙዝየም ተሰረቁ በአውሮፓ በጥበብ እና ባህል አብዮት በሚታወቀው ሬነሳንስ ዘመን የተሠሩ አራት "ትልቅ ዋጋ ያላቸው" ሥዕሎች ሲሲሊ ከሚገኝ ሙዝየም መሰረቃቸውን የአገሪቱ የባህል ሚኒስትር አስታወቁ። አሌሳንድሮ ጉይሊ እንደተናገሩት ማርያምን ከክርስቶስ ጋር የሚያሳይ ሥዕልን ጨምሮ አራት የሥነ ጥበብ ሥራዎች ተሰርቀዋል። በጣልያናዊው አንቶኔሎ ደ ሜሲና የተሰሩት ሥዕሎች ከሙዝየም የተዘረፉት፣ ያለፈው ቅዳሜ ምሽት ነው። ሌቦቹ የደኅንነት መቆጣጠሪያ ደውል ሳይሰማ በምን መንገድ ወደ ሙዝየሙ መግባት እንደቻሉ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ይገኛል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
"የመጨረሻ ዓመቴ ሊሆን ይችላል" - ሮናልዶ ጫማ ሊሰቅል እንደሚችል ጠቆመ አንጸባራቂ የእግር ኳስ ዓመታትን ያሳለፈው ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ይህ የውድድር ዘመን በተጫዋችነት የሚቀጥልበት የመጨረሻው ዓመት ሊሆን እንደሚችል ጠቆመ። ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ከረጅም ጊዜ አጋሩ ጆርጂና ሮድሪጌዝ ጋር ጋብቻ የፈጸመው የ41 ዓመቱ ሮናልዶ፣ የወደፊት ሕይወቱን ቤተሰቡ ላይ ያተኮረ ለማረድግ እያሰበ መሆኑን ገልጿል። የአምስት ባሎንዶር እና አምስት የቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ሮናልዶ፣ በእንግሊዝ፣ ስፔን፣ ጣሊያን እና ሳውዲ ዓረቢያ ሊጎች ዋንጫ ማንሳት ችሏል። በወንዶች ዓለም አቀፍ እግር ኳስ የምንግዜውም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። የፖርቹጋሉ አምበል አራት ዓመታትን ካሳለፈበት የሳውዲ ፕሮ ሊግ ቻምፒዮኑ አል ናስር ጋር የተፈራረመው ውል ሊጠናቀቅ የአንድ ዓመት ጊዜ ይቀረዋል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
ትራምፕ በኢራን ጦርነት ለመሳተፍ ፈቃደኛ ካልሆነችው ደቡብ ኮሪያ ጋር የሚደረገው ወታደራዊ ልምምድ እንደሚቀንስ ተናገሩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ባላቸው "መልካም ግንኙነት" ምክንያት ከደቡብ ኮሪያ ጋር የሚያደርጉትን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ "በከፍተኛ መጠን እንደሚቀንሱ" አስታወቁ። ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ እንደገለጹት፣ ደቡብ ኮሪያ ኢራንን "ከኒውክሌር ነጻ በማድረግ" እንቅስቃሴ ውስጥ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልሆነችም። "እነዚህ ወታደራዊ ልምምዶች ዋጋቸው ውድ ነው። አብዛኛውን ወጪ የምትሸፍነው ደግሞ እንደተለመደው አሜሪካ ናት። ፈጽሞ የማያስፈልግ እና ነውጠኛ መሆኑን መልዕክት ያስተላልፋል" ብለዋል። ደቡብ ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው ወታደራዊ ልምምድ "በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት" እንደሚቀጥል ገልጻለች። ሰሜን ኮሪያ ግን እስካሁን አስተያየት አልሰጠችም። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
ባለ ፓስፖርት አይጦች እና ስለ ቲቢ የሚመራመሩት ኢትዮጵያዊ አይጦቹ፤ የሳምባ በሽታ (ቲቢ) ያለባቸውን ሰዎች ለመለየት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ናሙናዎች አነፍንፈው በጠረን ለይተዋል። ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው እንዳይያዙ ታድገዋል። አይጦቹ፤ የጦርነት አውድማዎችን አነፍንፈው በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር መሬትን ከተቀበሩ ፈንጂዎች ነጻ አውጥተዋል። ሂሮራትስ () ተብለው ነው የሚጠሩት። በሳይንሳዊ ስማቸው ልንላቸው እንችላለን። አፍሪካን ጃይን ትፖችድ ራትስ ( ) በሚለው መጠሪያቸውም ይታወቃሉ። ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት በብዛት ይኖራሉ። በኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ተራራማ አካባቢዎች እንዲሁም በማዕከላዊ አፍሪካ በቀላሉ ይገኛሉ። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
ሞሮኮ የስፔን ግዛት ወደሆነችው ሲዩታ ሊሻገሩ የነበሩ በርካታ ስደተኞችን ያዘች የሞሮኮ ባለሥልጣናት በሰሜን አፍሪካ ወደምትገኘው የስፔን ራስ ገዝ ግዛት ሲዩታ ሊሻገሩ የነበሩ በርካታ ስደተኞችን መያዛቸው ተገለጸ። ወደ ሲዩታ እየተጓዙ የነበሩ ከ100 በላይ ሰዎች፣ በፍኒዴቅ ከተማ መያዛቸውን የስፔን መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም የሞሮኮ የደኅንነት ምንጮችን የጠቀሰው ሮይተርስ ዘግበዋል። ከሞሮኮ የተነሱ 78,000 ገደማ ስደተኞች ወደ ሲዩታ መግባታቸው ውዝግብ ያስነሳው ከሳምንታት በፊት ነበር። ከስደተኞቹ መካከል 100 ያህሉ መሞታቸው ይታወሳል። በወቅቱ ሲዩታ ከገቡት ስደተኞች ውስጥ አብዛኞቹ ወደ ሞሮኮ መመለሳቸው ተገልጿል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ "መዋቅራዊ ጥሰቶች" እና "አንድ ወገን ብቻውን የሚወስንበት እንቅስቃሴ" ታይቷል ሲል ከሰሰ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ "ከተራ የአሠራር ግድፈት" የዘለሉ "ተደጋጋሚ እና የተደራጁ ጥፋቶች ተፈጽመዋል" ሲል ከሰሰ። "ገዢው አካል መዋቅራዊ ጥሰቶችን" እንደፈጸመ በማንሳት የከሰሰው አብን፣ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ "የከተማዋ ነዋሪዎች ድምፅ እና ፍላጎት በአግባቡ ሳይወከል" መታለፉን ገልጿል። አንድ ወር በሞላው የአገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ካሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው አብን ይህንን ክስ ያቀረበው ቅዳሜ ነሐሴ 092018 ዓ.ም ምሽት ባወጣው መግለጫ ነው። ፓርቲው፣ በምክክር ሂደቱ ታይተዋል ያላቸውን "መዋቅራዊ ግድፈቶች" እና "የመርህ ጥሰቶችን" በጥልቀት መገምገሙን አስታውቋል። ፓርቲው "በሂደቱ ውስጥ የታየው ሁኔታ ከተራ የአሠራር ግድፈት ወይም ከመደበኛ የፓለቲካ ልዩነት የዘለለ ሆኖ አግኝተነዋል" ሲል በግምገማ የደረሰበትን ድምዳሜ ገልጿል። በሂደቱ ላይ የተፈጸሙት "ተደጋጋሚ እና የተደራጁ ጥፋቶች" የሀገራዊ ምክክሩን "ተዓማኒነት፣ አካታችነት፣ ገለልተኝነት እና ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚስገቡ" እንደሆኑም ገልጿል። አብን ምክክሩ ላይ ለታዩት "መዋቅራዊ ጥሰቶች፣ ጫናዎች እና ወገንተኛ አካሄዶች" ተጠያቂ ያደረገው "ገዢውን አካል" ነው። "መንግሥታዊ መዋቅሮችን የአንድን ቡድን ፍላጎት ማስፈጸሚያነት የማዋል ጥረት እንደሚደረግ በስፋት አስተውለናል" ሲል በመግለጫው አስፍሯል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር በይፋ ጦርነትን የሚቋጭ ንግግር እንዲደረግ ጠየቀች የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ሊ ጄ ሚዩንግ ከጎረቤታቸው ሰሜን ኮሪያ ጋር ለመወያየት ጥያቄ አቀረቡ። ውይይቱ በሁለቱ አገራት መካከል በተወሰነ ደረጃ ያለውን ጦርነት በይፋ ለማቆም ያለመ መሆኑንም አስታውቀዋል። በሁለቱ አገራት መካከል ባለው ከወታደራዊ ቀጣና ውጪ የሆነ ድንበር ላይ ግጭት እንዳይነሳ "ዘርፈ ብዙ የደኅንነት ሥርዓት" ለመዘርጋትም ሐሳብ አቅርበዋል። በተጨማሪም የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር ፍላጎት ለመግታት ተግባራዊ መደረግ የሚችሉ መንገዶች ላይ መመካከር እንደሚያስፈልግም ጠቅሰዋል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
"በ40 ዓመቴ የካስትሮ እውነተኛ ልጅ ሆንኩ"፡ አመጸኛዋ የፊደል ካስትሮ ልጅ አሊና ፈርናንዴዝ ልጅ ሳለች ፊደል ካስትሮ በተደጋጋሚ ያለችበት ድረስ እየሄዱ ይጠይቋት ነበር። በልጅነቷ ኩባን ለ50 ዓመታት ያህል በፍጹም አምባገነንነት፣ በጠንካራ ክንዶቹ ሥር በማድረግ ያስተዳደሩት ሰው ወላጅ አባቷ እንደሆነ አታውቅም ነበር። ካስትሮ እና ናቲ ፈርናንዴዝ ከጋብቻ ውጪ በነበራቸው ግንኙነት ነበር አሊና በአውሮፓውያኑ 1956 የተወለደችው። እናቷ በዋና ከተማዋ ሃቫና የምትኖር ከናጠጠ ሃብታም ቤተሰብ የዘር ግንዷ የሚመዘዝ ቆንጆ ነበረች። ካስትሮ ደግሞ በወቅቱ ከሽምቅ ተዋጊዎች ንቅናቄ መሪዎች አንዱ ነበር። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች በኤአይ ላይ ያላቸውን አቋም ደጋግመው የሚያጋሩት ለምንድን ነው የቅርብ ጊዜ ክስተት የሆነው የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በሁለት የተለያዩ ጎራዎች ማከራከሩን እንደቀጠለ ነው። በአንድ በኩል የፈጠራ አቅምን ያዳክማል፣ ሥራን ያሳጣል በሚል አሉታዊ ጎኑ እንደሚያመዝን የሚከራከሩ እንዳሉ ሁሉ በሌላ በኩል ደግሞ ለችግሮች መፍትሔ ይሰጣል በሚል በበጎ የተቀበሉት አሉ። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ቴክኖሎጂው እየተስፋፋ እና እየተበራከተ መጥቷል። የቴክኖሎጂ አለቆችም ማኒፌስቶዎቻቸውን በማጋራት ስለቴክኖሎጂው እየሰበኩ ነው። ባለፈው ሳምንት ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ዋትስአፕ እና ትሬድስን የሚያስተዳድረው ሜታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ " ዘ ፊዩቸር ኢዝ ፎር ኤቭሪዋን" በሚል ርዕስ 6 ሺህ 500 ቃላት ያሉት ግልጽ ደብዳቤ አጋርተዋል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
ቢቢሲ ለቀረበበት የ10 ቢሊዮን ዶላር ክስ የትራምፕ ቤተሰቦች በምስክርነት እንዲቀርቡ ጠየቀ ቢቢሲ ዶናልድ ትራምፕ የመሰረቱበትን የ10 ቢሊዮን ዶላር የስም ማጥፋት ክስ ለመከላከል የትራምፕ ቤተሰብ አባላት ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና ምስክርነት እንዲሰጡ ፍርድ ቤቱ እንዲያዝ ጠየቀ። የፍርድ ቤት ሰነዶች እንደሚያሳዩት የቢቢሲ ጠበቆች ባለፈው ግንቦት ወር ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየርን፣ ኢቫንካ ትራምፕን እና ጃሬድ ኩሽነርን ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና ማስረጃ እንዲሰጡ ለማድረግ ሞክረው ነበር። ፕሬዚዳንት ትራምፕ የ2021ዱ የካፒቶል ሂል አመፅ ላይ የተሰራጨ ንግግራቸው የተለያየ ክፍልን ፓናሮማ ዘጋቢ ፊልም ወጥ አስመስሎ በማቅረቡ ቢቢሲን ከስሰዋል። ቢቢሲ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ንግግር ለተቀናበረበት መንገድ ይቅርታ ጠይቆ የስም ማጥፋት ግን አይደለም ሲል አስተባብሏል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
በፈረንሳይ ከ15 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች የተጣለው የማኅበራዊ ሚዲያ ክልከላ በፍርድ ቤት ታገደ የፈረንሳይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ላይ የተጣለውን የማኅበራዊ ሚዲያ እገዳ "ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ይጥሳል" ሲል ውድቅ አደረገ። የአገሪቱ ሕግ አውጭዎች ባለፈው ሐምሌ ወር ነበር ማኅበራዊ ሚዲያ በሕፃናት የአዕምሮ ጤና ላይ ጎጂ ተፅዕኖ ያስከትላል የሚሉ ስጋቶች መነሳታቸውን ተከትሎ ለሕጉ ድጋፋቸውን የሰጡት። ይህም ፈረንሳይ ታዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ በመከልከል የመጀመሪያዋ አውሮፓዊት አገር እንድትሆን አድርጓት ነበር። ሆኖም አርብ ዕለት የሕገ መንግሥታዊ ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከመስከረም ጀምሮ ደረጃ በደረጃ እንደሚተገበር ቃል የገቡለትን እገዳ ውድቅ አድርጎታል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
ከሌላ ጥናታዊ ጹሑፍ ኮርጀዋል በሚል ተከስሰው የነበሩት የካምብሪጅ ፕሮፌሰር ሞተው ተገኙ ጥናታዊ ጽሑፋቸውን ከሌላ ሰው ኮርጀዋል ተብለው ተከስሰው የነበሩት የቀድሞው የካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ጄሰን አርዴይ ሞተው ተገኙ። አርብ ከሰዓት በደቡባዊ ለንደን ባተርሲያ ወደሚገኝ መኖሪያ ቤት የደረሱት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች "ራሳቸውን ስተው" እንዳገኟቸው አስታውቀዋል። አርዴይ ከካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ የለቀቁት ከሌላ ሰው ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ ሰርቀዋል የሚል ውንጀላ ከቀረበባቸው እና የተወሰኑ ስኬቶቻቸው ላይ ጥያቄ ከቀረበባቸው በኋላ ባለፈው ሳምንት ነበር። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
"አያቴ እኔ ሳላውቅ ልጄን አስገረዘቻት" ባለፈው ሳምንት ኮሎምቢያ በላቲን አሜሪካ ግርዛትን ሕገ ወጥ ያደረገች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። ይህም ትልቅ ድል መሆኑን የመብት ተሟጋቾች እየገለጹ ነው። በምሥጢር የሚከናወነው እና እጅግ አደገኛ የሆነው ግርዛትን በሕግ ለማሳገድ ለዓመታት ትግል ተደርጓል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
ለሽብር ተከሳሾች የቀረበውን "የይቅርታ ሰነድ" ካልፈረሙት መካከል የሆነው የካናዳ ዜግነት ያለው እሱባለው ማነው ለምንስ አልፈረመም ይቅርታ ጠይቀው ከእስር እንዲለቀቁ ፊርማቸውን የሚያኖሩበት "የይቅርታ ሰነድ" ከቀረበላቸው ከ300 የሚልቁ የሽብር ተከሳሾች ውስጥ የካናዳ ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ይገኛል። ካናዳዊው እሱባለው በለጠ ብርሃኔ፣ በአማራ ክልል ካለው ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ለተከሰሱ እስረኞች የቀረበውን "ይቅርታ መጠየቂያ ሰነድ" አንፈርምም ማለታቸው ከተረጋገጠ 30 ተጠርጣሪዎች አንዱ ነው። በካናዳ የቶሮንቶ ፒርሰን አየር ማረፊያ "ከፍተኛ የአውሮፕላን ጥገና ባለሞያ" ሆኖ ሲሠራ የነበረው እሱባለው በለጠ፣ መስከረም 242018 ዓ.ም ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው። የእሱባለውን የክስ ሂደት በተመለከተ ለቢቢሲ ማብራሪያ የሰጡት ጠበቃው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ፣ እሱባለው ወደ ኢትዮጵያ የሄደው ጳጉሜ 32017 ዓ.ም. እንደነበረ ተናግረዋል። ወደ ትውልድ አገሩ የሄደበትም ምክንያትም የወላጅ እናቱን ህልፈተ-ሕይወት ተከትሎ ለለቅሶ እንደነበረ ነው የጠቀሱት። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA
በእስራኤል ሠፋሪዎች በተከበበ መንደር ውስጥ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ቤታቸውን ለቅቀው እንዲወጡ ተነገራቸው እስራኤል በኃይል በያዘችው ዌስት ባንክ በምትገኝ አንዲት መንደር ውስጥ የሚገኙ በርካታ የፍልስጤም ቤተሰቦች፣ እስራኤላውያን ሠፋሪዎችን ለማስወጣት በተደረገ ዘመቻ ወቅት ንብረቶቻቸውን ለቅቀው እንዲወጡ ታዘዙ። ሠፋሪዎቹ ከእሁድ ጀምሮ በመንደሩ ባሉ ሦስት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን የከበቡ ሲሆን የኤሌክትሪክ እና የውሃ አቅርቦታቸውንም አቋርጠው ነበር። የቁስራ ከንቲባ አብዱል አዚም ዋዲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት መንደራቸው ዝግ ወታደራዊ ቀጠና ተብሎ ታውጇል፤ የእስራኤል ኃይሎችም አንዳንዶቹን የተለቀቁትን የፍልስጤም ቤቶች እንደ ወታደራዊ ሰፈራ እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ። የእስራኤል ወታደሮች ዓላማው "ነዋሪዎችን መጠበቅ" ነው ብለዋል። አንድ የእስራኤል ቃል አቀባይ የሠፋሪዎቹ እርምጃ "አስጸያፊ" እና "ተቀባይነት የሌለው" መሆኑን ገልጸው መንግሥት ምርመራ እንደሚያደርግ እና ድርጊቱን የፈፀሙትን በቁጥጥር ስር እንደሚያውል ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወቅታዊ መረጃ @BBCAMARGNA