CHRISTIAN INSIGHT
описание
ይህ ድህረ-ገፅ በምድር ስንኖር ለሚያጋጥሙን ፈተናዎች መፅሐፍ ቅዱስን መሰረት በማድረግ ስለመፍትሄዎቹ የምናወጋበት ፤ እንዲሁም በምድር ላይ ስንኖር እንደ ክርስቲያን ስኬታማ ኑሮ መኖር ስላለብን ስለ-ስኬታማነትና ስለ-ስኬት መንገድ እናወጋለን። በዚህ መድረክ አስፈላጊ የሆነ ነገር ሁሉ ስለሚዳሰስ ይከታተሉ።
247
подписчиков
Охват к подписчикам
81,0%
ERR
Реакции к просмотрам
2,35%
94 на 20 постов
Пересылки к просмотрам
0,20%
8
Постов в день
0,0
всего 20
Где отзываются чаще
доля реакций к просмотрам- 29 июл.በሕይወትህ ውስጥ አንዳንዴ በሮች የሚዘጋጉት ጥፋት ደርሶብህ ሳይሆን፣ ከዛ በላይ ለሆነ ትልቅ መንገድ ስለተመረጥክ ሊሆን ይችላል። መጠበቅን እንደ ቅጣት ሳይሆን እንደ ዝግጅት ጊዜ ቁጠረው። በጸጥታ ውስጥ የሚደረግ እድገት ሁልጊዜም ዘላቂ ነው። @Christian_Insight @Christian_Insight10,53%
- 30 авг. 2025 г.🌸 - ከህይወት ትዝብት - 🌸 🍀 ፍቅር ለማይገባው ፡ ፍቅርህን ንግግርህ ለማይገባው ፡ ቃላትህን አትስጥ። 🍀 የምታደርገውን የትኛውንም ነገር ስታደርግ ከቁም ነገር ለሚቆጥርና ዋጋህን ተገንዝቦ value ለሚሰጥ ሰው አድርገው። 🍀 አየህ ለስጋ በሊታ እንስሳ ሳር አይሰጥም ፣ ሳር ለሚበላ እንስሳም ስጋ አይሰጥም ለሁሉም የራሱ ስርዓት አለው። ያንን ስርዓት ለመበጠስ መጣር ከተፈጥሮ ህግ ጋር መጣረስ ነው። ፍቅርህንና ቃልህን ለሚገባው ብቻ ስጥ.! @Christian_Insight @Christian_Insight4,29%
- 17 нояб.ከገበያው ውጡ ያላችሁበት ገበያ ምን የሚሸጥበት እንደሆነ ስለማታውቁ አብዛኞቻችሁ ያላችሁበት ገበያ ለእናንተ የሚመጥን አይደለም። አያችሁ ይሁዳ መገኘት በሌለበት ገበያ ተገኝቶ ነው ክርስቶስን ሽጦ የወጣው። መሸጡ የማይገባ እንደሆነ ተረድቶ ለመመለስ እና ክርስቶስን ለማስመለስ ቢመለስም እሺ ብለው አልመለሱለትም ነበር። እናንተስ የትኛው ገበያ ውስጥ ነው ያላችሁት ? ምናልባት ክርስቶስ የሚሸጥበት ገበያ ቢሆንስ ? አሁን አንድ ነገር አድርጉ ያላችሁበትን ገበያ ተመልከቱ። ምድር ክርስቶስን ለሚሸጥ ትልቅ ጥቅምና ቦታ ትሰጣለች። ምናልባት የተሰጠን ትልቅ ቦታ የተሰጠን ክርስቶስን በዚያ ቦታ ላይ አስጥሎን ቢሆንስ ? ክርስቶስ የሚሸጥበት ገበያ በተለምዶ የሚሞቅና የሚደራ ነው። ለመሳተፍም መነሳሳትን ይፈጥራል። ገበያው ምናልባት የምንሰራው ስራ ፡ የምንውላቸው ሰዎች ፡ የምንገባበት ቤት ፡ የምንውልበት ቦታ ፡ የምንወዳቸው ሰዎች even ቤተሰቦቻችን ሊሆኑ ይችላሉና በደንብ ተመልከቱአቸው። ክርስቶስ የሚሸጥበት ገበያ መገኘትና በግብይቱ መሳተፍ የሚቀበሩበትን ጉድጓድ እንደ መቆፈር ነው። @Christian_Insight @Christian_Insight3,98%
- 23 авг. 2025 г.ምንም አትሆኑም "የሕልውናችን መሠረት እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰው የሕይወታችንን መብራት፤ ለማብራትም ሆነ ለማጨለምም ድርሻ የለውም። የእኔ ሕይወትና የእኔ ጉዳይ በእግዚአብሔር እጅ ነው ብለን በእምነት መኖር ይገባናል።" እምነት ከእውቀትና ፍርሃት በላይ ኃያል ነው። ለዚሁ ነው እግዚአብሔር ከምናውቀው ይልቅ እንድናምነው አጥብቆ የሚፈልገው። ስለ ህይወታችን ከሰው ይልቅ እግዚአብሔርን እንመነው። @Christian_Insight @Christian_Insight3,76%
- 28 окт.🍀 ይህ ይህወት እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠን ነው። 🍀 የሕይወት ዋጋዋ ስንት ነው ? ዋጋው ያኖረን ቸርነቱ ነው። እስትንፋሳችን በአፍንጫችን ላይ የተንጠለጠለች ፣ ለመሄድ የተዘጋጀች ናት። እስትንፋሳችንን በአፍንጫችን ያሳደረልን ፣ ያዋለልን ጌታ ቸር ነው። ይህን ቸርነቱን ማጣጣም ፣ ማመስገን ፣ መመስከር ይገባል። 🍀 በእግዚአብሔር የሚታመን ሰው ምስጉን ነው። @Christian_Insight @Christian_Insight3,55%
- 30 окт.በእግዚአብሔር የታመነችን ፣ ስንፍናን የናቀች አይኖቿን ከሁኔታዎች እና ከከበቧት ችግሮቿ አንስታ ወደ አምላኳ ያደረገችን ሴት ማንም እንደፈለገ አይሰብራትም እንዳሻዉም አያታልላትም ምክንያቱም እግዚአብሔር ለመንገዷ መሪ ለእግሮቿ መብራት ለልቧም ብልሀት እና ሞገስ ነዉ። @Christian_Insight @Christian_Insight3,37%
- 29 окт.ሰው ካከበረው እግዚአብሔር ያከበረው እጅጉን ይበልጣል፤ ሰዎች በሁኔታዎች ይቀየራሉ፣ እንዳስቀመጥክ ላታገኛቸው ትችላለህ። የሰው ልጅ ሸምበቆ ነው ተደግፈኸው የሆነ ቀን ሊቀነጠስ ይችላል። ሙሉ እምነትህን እግዚአብሔር ላይ ብቻ አድርገው! እግዚአብሔር አያሳፍርህም። ሞገስና ጌጥ ፡ ክብርና ዝና ፡ መካሪና ወዳጅ ፡ አጋዥና መሪ ፡ እናትና አባት ፡ ጓደኛና አድማጭ ይሆንልሃል ❤ @Christian_Insight @Christian_Insight3,28%
- 2 сент. 2025 г.ቶሎ ቶሎ ውለዱ 🍀 ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው። ለመሳቅ ፡ ለማልቀስ ፡ ለመውጣት ፡ ለመግባት እንዲሁም ለመውለድም ጊዜ አለው። 🍀 አንድ ነገር ጊዜ አለው ማለት ያንን ነገር ለማድረግ ምርጡ ጊዜ እሱ ነው ማለት ሲሆን ፡ ያ ጊዜ ሳይመጣም ሆነ ካለፈ በኋላ ያንን ነገር ማድረግ አንችልም። 🍀 ለምሳሌ ለመውለድ ጊዜ አለው ከሆነ እድሜ በላይ እና ከሆነ እድሜ በታች ነው መውለድ የሚቻለው። ከዚያ የጊዜ ማዕቀፍ ውጪ መውለድ አይቻለም። 🍀 በህይወት ላይም ጊዜ የሚባል ነገር አለ። ከእናት ማህፀን የሚወለደውን ልጅ ራዕይ ወይም አላማ ነው እንበለውና አጠር ያለ ነገር ልበላችሁ። የወጣትነት እድሜ ራዕይና አላማችንን መውለጃ ምርጡ ጊዜ ነው። እሄንን ጊዜ ተጠቅመን በውስጣችን የሚመላለሰውን ራዕይ መውለድ አለብን። 🍀 ይህ ባይሆን ግን መውለድ ፈልገን እንኳን መውለድ የማንችልበት ጊዜ ይመጣል። በተወለዱ ራዕዮች ስንቀና እንኖራለን። ስለዚህ ባላችሁ በዚህ ጊዜ ቶሎ ቶሎ ውለዱና ተገላገሉ። እኛም እንኳን ጌታ ረዳችሁ ለማለት ቸኩለናል። የተወደዳችሁ ናችሁ ❤ @Christian_Insight @Christian_Insight3,14%
- 31 авг. 2025 г.🌸 ሥር የሰደዱ ዛፎች ነፋስን ይቋቋማሉ ፣ ወደ ታች የጠለቁ መሠረቶች ብዙ ፎቅ ይሸከማሉ ። 🌸 ሰውም በሳል ሲሆን በፈተና ይጸናል ፣ ፈተናና ነፋስ ያልፋሉና ። ነፋሱ ዘንበል ቢያደርግህም እንዲሰብርህ መፍቀድ የለብህም ። 🌸 ብዙ ጫናዎችን ለመሸከም እውቀትና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ ። ከአገሬ በቀር አገር የለም ፣ ከእናቴ በቀር እናት የለም ፣ ከእኔ በቀር ሰው የለም ፣ ከእገሌ በቀር አገልጋይ የለም አትበል። 🌸 ጨርሶ መናገር ለዚህ ዓለም ነዋሪ ትዝብት ያተርፍለታል ። በክረምት ለመዝራት ዝናቡን የተሰቀቁ የአጨዳ ዘመን የላቸውም ። ሌላው ሲያለቅስ የሳቁ በኀዘናቸው አጋር አያገኙም። 🌸 ካልገዛ በቀር ስጦታውን የሚያቃልል የእግዚአብሔርና የሰው ወዳጅ መሆን አይችልም ። ፍላጎት መልካም ነው ፣ ከልክ ያለፈ መሻት ግን በቀን ሰላም ፣ በሌሊት እንቅልፍ የሚነሣ ነው ። @Christian_Insight @Christian_Insight3,05%
- 2 сент. 2025 г.እራቁታችንን መጥተናል እራቁታችንን እንመለሳለን። @Christian_Insight @Christian_Insight2,82%
- 24 авг. 2025 г."ያጠለቅነው ጫማ ባዶ እግራችንን፣ የለበስነው ልብስ ዕራቁት መወለዳችንን ካስረሳን ሞኝ ነን። በባዶነት ጀምረን በባዶነት በምንጨርስባት ዓለም ሁሉ የእኔ ካልሆነ ብለን አንታክት። በድብቅ እየወደቅን በገሀድ የወደቁት ላይ አንዘባበት። ትምህርታችን ያልተማሩትን ካልረዳ አለማወቅ ነው። የእኛን ትምህርት ዋጋ ያለው ያደረገው ያልተማሩት ናቸው። ጨለማን የማያስወግድ ብርሃን ራሱ ጨለማ ነው። ፍላጎታችንን ባለማወቅ የሰውን ድንበር አንግፋ። በክብር ለመኖር ልክን ማወቅ መሠረት ነው። ሐሰትን ከፈጠራት ያሰራጫት የከፋ ነውና የማናውቀውንም የምናውቀውንም ከመናገራችን በፊት እናስተውል።" @Christian_Insight @Christian_Insight2,60%
- 4 сент. 2025 г.በኢየሱስ... "ህይወት ትርጉም የሚያገኘው በእየሱስ ውስጥ ራሳችንን ማየት ስንጀምር ነው። የተፈጠርንለትን ዓላማ ማግኘት የምንችለው ወደ እየሱስ በመንፈስ ቅዱስ መቅረብ ስንጀምር ነው። ፀሎት እኛ ጋር ድርግት ሳይሆን ህይወት (life style) መሆን ሲጀምር ስጦታውን ትተን ሰጭውን ራሱን መፈለግ ስንጀምር ያኔ የህይወታችንን ዓላማ ማግኘት እንጀምራለን። መንፈስ ቅዱስ አባትሽ ነው የሩቅ ሰው አታድርጊው ይወድሻል ዕለት ዕለት ሊያወራሽ ይፈልጋል። እውነት ነው እሱ አብሮን እየኖረ ነው እሱ አብሮሽ እየኖረ ነው ማለት ግን አንቺ አብረሽው እየኖርሽ ነው ማለት አይደለም ቅረቢው አውሪው ይህንን ካደረግሽ እርግጠኛ ነኝ ዳግመኛ ህይወት ይደብራል የሚል ቃል ከአንደበትሽ አይወጣም ።" @Christian_Insight @Christian_Insight2,59%