tgindex

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

643
подписчиков
Охват к подписчикам
43,1%
ERR
Реакции к просмотрам
0,48%
34 на 27 постов
Пересылки к просмотрам
0,48%
34
Постов в день
0,0
всего 28

Где отзываются чаще

доля реакций к просмотрам
  • 1 авг."በጎ ልብ፤ ትንሽ ስጦታ፣ ግዙፍ ዓላማ!" ​በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህልን በማሳደግ የብዙዎችን ሕይወት በአንድ ላይ መቀየር እንችላለን! ​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ባዘጋጀው "የዲጂታል በጎነት" ፕሮጀክት አማካኝነት ማህበረሰባችንን ለመደገፍ የእርስዎ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ዋጋ አለው። ​የለውጡ አካል ለመሆን አሁኑኑ ይሳተፉ፣ ወደ 6400 "A" ብለው መልዕክት ይላኩ! መልካምነትዎን በዲጂታል መንገድ ያጋሩ! ​#ዲጂታልበጎነት #6400A #ኢትዮቴሌኮም #የበጎፈቃድአገልግሎት #አዲስአበባ #EthioTelecom #AddisAbaba3,05%
  • 4 авг.በቀን አንድ ብር ብቻ በመለገስ የሌሎችን ጉድለት መሙላት ይችላሉ! አሁኑኑ ወደ 6400 "A"ን በመላክ ደጋግ ልቦችን ይቀላቀሉ። መልካም ቀን ይሁንልዎት!2,56%
  • 16 июл. 2025 г.без подписи2,22%
  • 29 июл.የቅጥር ማስታወቂያ አአ ጤና ቢሮ ሐምሌ 22/2018 ዓም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ለኮልፌ አጠቃላይ ሆስፒታል በተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን በቋሚነትና በኮንትራት አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለኮንትራት ቅጥር ፈላጊዎች Contract Position የሚለውን ሊንክ በመጫን እንዲሁም ለቋሚ ቅጥር ፈላጊዎች Permanent Position የሚለውን ሊንክ በመጫን በስራቸው የተዘረዘሩ የስራ መደቦች ላይ በመመዝገብ ማመልከት የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ Contract Position (ለጊዜያዊ የስራ መደብ ) Permanent Position (ለቋሚ የስራ መደብ ) ማሳሰቢያ፡- ለጊዜያዊ የስራ መደብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከሀምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ እንዲሁም ለቋሚ የስራ መደብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከሀምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ ሆኖ ከጠዋቱ 2.30 እስከ ማታ 11.30 ብቻ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ በአንድ ኢሜል አድራሻ አንድ ጊዜ ብቻ ነው መመዝገብ የሚቻለው፡፡ ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑት። https://forms.gle/eNbU1f5HbPiPsDUQA1,75%
  • 17 мар.без подписи1,53%
  • 8 июл.በመዲናዋ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር 10 ሺህ በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት በሚበዛባቸው የመንግስት ተቋማት ይሰማራሉ። በከተማችን የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት በየጊዜው እያደጉ መምጣታቸውን የሚያሳይ "በጎነት በገልግሎት ሰጪ ተቋማት!" የተሰኘ የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር ተጀምሯል። ዛሬ በተካሄደው መድረክ፣ አገልግሎት በሚበዛባቸው የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ተሰማርተው ህዝባቸውን የሚያገለግሉ በጎ ፈቃደኞች የስራ ስምሪት ተሰጥቷቸዋል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ይመር ከበደ ለበጎ ፈቃደኞች የስራ መመሪያና አቅጣጫ ሰጥተዋል። ዋና ኮሚሽነሩ በንግግራቸው "በጎ ፈቃደኞች በሚሰማሩባቸው ተቋማት ሁሉ ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃድ መርሆዎችን በጥብቅ መከተል ይኖርባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግ የተቋማቱን የአሰራር እሴቶችና ስነ-ምግባር አክብሮ መስራት ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በበኩላቸው፣ በከተማዋ የበጎነት ባህል እንዲዳብርና የህብረተሰቡ የጋራ እሴት እንዲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘርፈ ብዙና አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። ይህ የዛሬው የስምሪት መርሃ-ግብርም የዚሁ ስኬታማ ጉዞ አካል መሆኑን ጠቁመዋል። የበጎ ፈቃደኞቹን የስራ አካባቢ ምቹ የማድረግና የመደገፍን አስፈላጊነት ያነሱት ደግሞ በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ የቢሮው አማካሪ አቶ አቡበክር ሀሽም ናቸው። አቶ አቡበክር በመንግስት ተቋማት ውስጥ ለሚሰማሩት ለእነዚህ በጎ ፈቃደኞች ተቋማቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ቀጣይነት ያለው ክትትል እንደሚያደርጉላቸው አረጋግጠዋል። ታዋቂው የስራ ፈጣሪና በጎ ፈቃደኛ ኢንጂነር ቢጄአይ ናይከር እና በመከላከያ ሰራዊትነት ለረዥም ጊዜ አገራቸውን ያገለገሉት 50 አለቃ ብርሃኑ አማረ በመድረኩ ተገኝተው ለበጎ ፈቃደኞቹ የረጅም ዘመን የስራ፣ የህይወትና የሀገር ፍቅር ልምዳቸውን አጋርተዋል። ታዋቂ ግለሰቦች ያጋሩት ልምድና የተሰጣቸው የስራ አቅጣጫ ወደ አገልግሎት ከመግባታቸው በፊት የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዳገዛቸውና መነሳሳት እንደፈጠረላቸው በጎ ፈቃደኞቹ ገልፀዋል። ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በዜጎች መካከል የመረዳዳትና አብሮነትን የማጠናከር ትልቅ አገራዊ ፋይዳ ይኖረዋል።1,26%
  • 25 маябез подписи0,71%
  • 25 июл.ኤካ ኮተቢው አጠቃላይ ሆስፒታል በክረምት በጎ ፈቃድ መርሀ ግብር ከ200 ሺህ በላይ ዜጎችን ነፃ የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ አደረገ። አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም በየካ ክፍለ ከተማ የሕክምና ወጪ መሸፈን ለሚቸገሩ በርካታ ነዋሪዎች እፎይታን ሲሰጥ የቆየውና ከ200 ሺህ በላይ ነፃ የሕክምና አገልግሎቶች የተሰጡበት የ11 ቀናት የበጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር ዛሬ ተጠናቋል። በጤና ሚኒስቴር፣ በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል እና በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትብብር የተዘጋጀው ይህ ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ የብዙዎችን የጤና ችግር በመቅረፍና ለዜጎች አስፈላጊውን የሕክምና ድጋፍ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገልጿል። በማጠናቀቂያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የሜዲካል ሴንተሮች መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢሊባቡር ቡኖ እንደተናገሩት፣ በዘንድሮው ዓመት ብቻ በመላ ሀገሪቱ ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የዚህ ነፃ የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ። የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር መገርሳ አለሙ በበኩላቸው፣ ባለፉት 11 ቀናት ለሕብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ለህክምናው መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ የጤና ባለሙያዎችና አጋር አካላት ምስጋና በማቅረብ መሰል ሰብዓዊ አገልግሎቶች ወደፊትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ኢምሮ፣ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የሕክምና ወጪ መሸፈን ለማይችሉ ወገኖች አገልግሎት ሲሰጥ ለቆየው ለኤካ ኮተቤ ሆስፒታልና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል። በዚህ የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ላይ እንደ ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር፣ ላንሴት ሆስፒታል እና ጂአይቪ ሆስፒታል ያሉ የግል ተቋማትም በመሳተፍ የዜጎችን ህይወት ለመታደግ በተደረገው ጥረት ድጋፍ አድርገዋል ሲል የዘገበው የካ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ነው።0,69%
  • 30 апр.без подписи0,62%
  • 18 июл.የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ስራዎች የለውጡ እሳቤ በተግባር የተገለጠባቸው መሆናቸው ተገለጸ። አዲስ አበባ| ሰኔ 11/2018 ዓ.ም ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ውጤቶች የለውጡ እሳቤ በተግባር የተገለጠባቸው ተግባራት መሆናቸውን የአዲስ አበባ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ ተናገሩ። ምክትል ኮሚሽነሯ ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያካሄደ በሚገኘው የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ ወቅት ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም እና ያለፉት 5 ዓመታት የስራ አፈፃጸም ግምገማ ከሰኔ 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የኮሚሽኑን የስራ አፈፃጸም አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ፤ ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት የህዝብ ተሳትፎን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ረገድ በርካታ ዘርፈ ብዙና ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራት ስኬታማ በሆነ መንገድ መከናወናቸውን አስገንዝበዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ቀዳሚ መሪነት የተጀመረው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት የመገንባት ስራ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ውስጥ ትልቅ እምርታ ማሳየቱን ምክትል ኮሚሽነሯ አብራርተዋል። ይህ የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ቀደም ሲል ከነበረበት የግለሰብ ቤቶች እድሳት ደረጃ በመውጣት፣ በአሁኑ ወቅት ሰፋፊ የሆኑ የ"በጎነት መንደር" ግንባታዎችን ወደ ማካሄድ መሸጋገሩንና በከፍተኛ ደረጃ መስፋቱን አስረድተዋል። ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት ውስጥ ብቻ በዚህ በጎ እሳቤ ተመርቶ በተከናወነ የተቀናጀ ስራ የዜጎችን ማኅበራዊ አኗኗር የሚመጥኑና የከተማዋን ገጽታ ያዘመኑ ከ46 ሺህ 441 በላይ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች መተላለፋቸውን ወ/ሮ ፀሐይ ገልጸዋል። አያይዘውም ይሄው አበረታች የበጎ ፈቃድ ስራ በሚቀጥለው የ2019 በጀት ዓመትም ከከተማዋ ሁለንተናዊ እድገትና ለውጥ ጋር ተመጋጋቢ በሆነ መንገድ፣ ይበልጥ በላቀ የሰው ተኮር እሳቤ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2 ሺህ 500 አዳዲስ መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችና ለችግረኛ ወገኖች ለመገንባት ታቅዶ ርብርብ እየተደረገበት እንደሚገኝና ስራዎችም በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በተቋሙ "በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የሚመሩት እነዚህ ማኅበራዊ አገልግሎቶች የነዋሪውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ያለሙ ናቸው። #በጎነት_ለአዲስ_አበባ_ከፍታ #የበጎ_ፈቃድ_አገልግሎት #humanitarian #አዲስ_አበባ #Ethiopia0,56%
  • 22 июн.በአዲስ አበባ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር 2,500 ቤቶች ሊገነቡ ነው። አዲስ አበባ| ሰኔ 15/2018 ዓ.ም፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተጀመረው የቤት ግንባታና የአካባቢ ማደስ ፕሮጀክት፥ የመንግስትን ፖለቲካዊ ቃል ኪዳን ወደ መሬት የመቀየር ስትራቴጂ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ። ከንቲባዋ "የመረጠንን ህዝብ የምናመሰግነው በቃላት ሳይሆን በተግባራዊ ምላሽ ነው" ያሉ ሲሆን፥ ይህም ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ ዳግም ኢትዮጵያን ለመምራት ተጨማሪ የአምስት ዓመት እምነት በተሰጠው ማግስት የተጀመረ መሆኑን ገልጸዋል። በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በከተማ ደረጃ 2,500 ቤቶችን ለመገንባት የታቀደ ሲሆን፥ የዚሁ አካል የሆነውና ከከንቲባ ፅህፈት ቤት በስተጀርባ የሚገነባው የ“አራዳ የበጎነት መንደር” ግንባታ በይፋ ተጀምሯል። ይህ ሜጋ ፕሮጀክት ባለ 9 ወለል 8 ዘመናዊ የመኖሪያ ህንፃዎችን እና ባለ 4 ወለል ሁለት የገበያ ማዕከላትን ያካተተ ሲሆን፥ ለዘመናት የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን በመቀየር ለሰው ልጆች ክብር የሚመጥን ዘመናዊ የጋራ መገልገያ፣ አረንጓዴ ስፍራና የስፖርት ሜዳዎችን ያካተተ መንደር እንደሚሆን ተገልጿል። ከቤት ግንባታው በተጨማሪ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ አካባቢን የማጽዳት፣ የጎርፍ መከላከያ ግንባታ፣ አቅም ለሌላቸው ማዕድ የማጋራት፣ የደም ልገሳ እና የነፃ ህክምና አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ከንቲባዋ አስታውቀዋል። በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ የተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እና የመንገድ ትራፊክ ማሳለጥ ስራዎችን በማከናወን ከተማዋን ለኑሮ ምቹ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቅሷል። ለዚህ ታላቅ ግንባታ ስኬት የከተማዋ ባለሀብቶች ፈጣን ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ በላይነህ ክንዴ እና ያደታ ጁነዲን እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ባለ 9 ወለል ህንፃ ለመገንባት ቃል ገብተዋል። በተመሳሳይ ቲኤንቲ ኮንስትራክሽን፣ ግራንድ ሌጋሲ ሃውስ፣ ኢቲ ኦንላይን፣ አብይ ማስረሻ፣ ዴማ ሪልስቴት፣ ቴምር ሪልስቴት፣ ስናፕ ትሬዲንግ፣ ጊፍት ሪልስቴት፣ መሃመድ አድናን እና አሚር በድሩ ቀሪዎቹን ህንፃዎች በጋራ ለመገንባት አጋርነታቸውን ማረጋገጣቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸው ምስጋና አቅርበዋል።0,49%
  • 14 сент. 2025 г.без подписи0,39%