tgindex
የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ETHIOPIAN BLOOD & TISSUE BANK SERVICE

የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ETHIOPIAN BLOOD & TISSUE BANK SERVICE

Статистика

በቂ የሆነ የደምና የዓይን ብሌን ከበጎ ለጋሺ በማሰባሰብ ለህክምና ተቋም ማሰራጨት

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
35
Всего постов
56
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
741
−3 за 2 дн.
Сутки
−2
−0,27%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
90
40 постов
Вовлечённость
12,1%
к подписчикам
Постов в день
5,0
всего 56
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
96
1/48двое суток
110
1/72трое суток
118

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 🩸 አባክዎ የደም ልገሳ በማድረግ የሰውን ህይወት ይታደጉ! "ድልድይ ሆነን እናገለግላለን!" የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት በነገው ዕለት ቅዳሜ (09/12/2018 ዓ.ም) በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የልገሳ ጣቢያዎች ደም የመለገስ ጥሪ ያስተላልፋል። የእርስዎ የበጎ ፍቃድ የደም ልገሳ የ 3 ሰዎችን ህይወት የመታደግ ታላቅ ሀይል አለው! 🏥 ቋሚ የልገሳ ማዕከላት ቋሚ ማዕከል: ቀይ መስቀል ግቢ (ስታዲየም አካባቢ) ዋና መሥሪያ ቤት: የደም ባንክ ዋናው መሥሪያ ቤት (ጤና ሚኒስቴር ግቢ ) 📞 ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት: በነፃ የስልክ መስመር 80 40 ይደውሉ። 🌐 ድረ-ገጽ: ebtbs.gov.et ይምጡ፤ ደም ይለግሱ፣ ህይወት ያትርፉ!

  • 🩸 Please Donate Blood and Save a Life! "We Serve as a Bridge!" The Ethiopian Blood and Tissue Bank Service calls upon you to donate blood tomorrow, Saturday (09/12/2018 E.C.), at donation centers located across all sub-cities. Your voluntary blood donation has the power to save up to 3 lives! 🏥 Permanent Donation Centers Permanent Center: Red Cross Compound (around Stadium) Head Office: Blood Bank Head Office (around the Ministry of Health) 📞 For more information: Call the toll-free line at 80 40. 🌐 Website: ebtbs.gov.et Come, donate blood, and save lives!

  • ከ 60 በላይ ወጣቶች የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል ገቡ። * አዲስ አበባ — የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መድረክ ላይ፣ በርካታ ወጣቶች ከህይወት ህልፈታቸው በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል ገቡ። ወጣቶቹ በተዘጋጀው  የቃል ኪዳን ፎርም ላይ በመፈረም፣ ከሕልፈታቸው በኋላ ብሌናቸውን በመለገስ በጨለማ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻቸው ብርሃን ለመሆን ያሳዩት ቁርጠኝነት በጣም የሚበረታታ ተግባር መሆኑ በመድረኩ ላይ ተገልጿል። በመድረኩ ላይ ለወጣት በጎ ፈቃደኞች ገለፃ ያደረጉት ዶክተር አምሳለ ጌታቸው፤ስለ ዓይን ብሌን ጠባሳ መነሻ ምክንያቶች እና የመከላከያ መንገዶች፣ስለ ዓይን ብሌን አሰባሰብ ሂደቶች፣ እና ስለ ዓይን ባንክ ዋና ዋና ተግባራት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ዶክተር አምሳለ አክለውም፣ የወጣቶቹ የዓይን ብሌን ልገሳ ቃል ኪዳን እይታቸውን ላጡ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች አዲስ ተስፋ የሚያበስር ታላቅ ሰብዓዊ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በዕለቱ በተካሄደው መድረክ ላይ እማኝነቱን ያቀረበው ወጣት ፍሬው ሺበሺ፣ በጨለማ እና በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ለዓመታት ካሳለፈ በኋላ በበጎ ፈቃደኞች በተደረገ የሕይወት ዘመን ቃል ኪዳን አማካኝነት ዳግም ወደ ብርሃን መመለሱን ተናግሯል። ወጣት ፍሬው ይህ መልካም ተግባር ዛሬ ላይ እንደ አዲስ መኖር እንዲጀምር እንዳስቻለው በመግለፅ መሰል የበጎ ፍቃድ ተግባራትን በማስቀጠል የሺዎችን እይታ መመለስ  ታላቅ ሰብአዊነት ነው ብሎዋል። ከሕይወት ህልፈታቸው በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ የስምምነት ሰነድ የፈረሙት ወጣቶች በበኩላቸው፣ ውሳኔያቸው በድንገት የተወሰደ ሳይሆን የማህበረሰቡን ችግር በጥልቀት ከመመልከት እና ከጥልቅ ሰብዓዊ ስሜት በመነሳት የተደረገ ታላቅ የሕይወት ቃል ኪዳን መሆኑን አረጋግጠዋል።

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • https://www.facebook.com/100064325666044/posts/1533155188838655/?app=fbl

  • የእርስዎ ደም፣ የሌላ ሰው ተስፋ ነው።! ለህይወት አድን ጥሪ ምላሽ ይስጡ። * ነገ ዓርብ ነሃሴ 08 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ደምና ሕብረ ህዋስባንክ አገልግሎት አማካኝነት በሚዘጋጀው የደም ልገሳ መርሐግብር ላይ በመሳተፍ ህይወት ያድኑ! ያለዎትን ጥቂት ጊዜ ለልገሳ በማዋል የአንድ ሰው ሙሉ ህይወት መመለስ ይችላሉ። የት መለገስ እንደሚችሉ ከላይ ያለውን ዝርዝር ይመልከቱ! ቀኑን እና ቦታውን በማስታወስ፣ ጓደኞችዎን እና ቤተሰብዎን በመያዝ ይምጡና ደም ይለግሱ! የበለጠ መረጃ ለማግኘት በነፃ የስልክ መስመር 8040 ይደውሉ ወይም ድህረ ገጻችንን ebtbs.gov.et ይጎብኙ።

  • የሙሰሊም ተማሪዎች ሊግ አገር አቀፍ የደም ልገሳ ዘመቻ ሊያካሂድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለጸ፡፡ ****** አዲስ አበባ — የሙሰሊም ተማሪዎች ሊግ “ማነው በነቢዩ መሃመድ (ሰ.ዐ.ወ) ስም ደም ለመለገስ ፈቃደኛ የሆነው?” በሚል መርህ ቃል ከነሐሴ 21 ቀን እስከ ነሃሴ 24/20 18 ዓ.ም የሚካሄድ አገር አቀፍ የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ ዘመቻ ለማካሄድ ዝግጅቱን ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቁን አስታወቀ። ይህ አገር አቀፍ የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ ዘመቻ ለተከታታይ 4 ቀናት የሚካሄድ እና አዲስ አበባ፤አዳማ፤ጅማ፤ዲላ፤ድሬዳዋና ወልቂጤን ጨምሮ በመላው አገሪቱ ወደ 10 በሚጠጉ ከተሞች ውስጥ በስፋት እንደሚካሄድና 5ሺ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገልጿል። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ደምና ሕብረሕዋስ ባንኩ የደም ለጋሾች ዘርፍ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር መላሽ ገላው፣ የደም ልገሳ ሕይወትን የማዳን ፋይዳ እና ደም መለገስ ለለጋሹ የሚያስገኛቸውን የጤና ጥቅሞች አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ደም በመለገስ ብቻ በርካታ አደጋ ላይ ያሉ ወገኖችን ሕይወት መታደግ እንደሚቻልና ተግባሩ ከፍተኛ ሰብአዊ ዋጋ ያለው መሆኑ አመልክተዋል፡፡በተጨማሪም የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ ለለጋሹ አካላዊና ጤናማ ኑሮ ያለው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ዶ/ር መላሽ ገላው በሰጡት ማብራሪያ አንስተዋል። ሊጉ ሕብረተሰቡን ለማስተባበር እያከናወነ ያለው አገራዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው መሆኑን ያነሱት ዶ/ር መላሸ የበጎ አድራጊ ተማሪዎች ሊግ ይህንን መልካም ሥራ በአንድ ጊዜ ዘመቻ ብቻ ሳይወስነው በየሶስት ወሩ በቋሚነት ደም በመለገስ እንዲሁም ማህበረሰቡን በማስተባበር ረገድ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። በጤና ተቋማት ውስጥ የሚታየውን የደም እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ እንዲህ ዓይነት አገር አቀፍ እና ቋሚ የሆኑ የህዝብ ንቅናቄዎች ወሳኝ መሆናቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፣ የደምና ሕብረህዋስ ባንኩ ድጋፍ እና ትብብር ከሊጉ ጎን ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። የደም ልገሳው ዓላማ ለዓለማት ሁሉ እዝነት ተብለው ከሚገለፁት ነብዩ መሃመድ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ምድር መምጣት ጋር የሚታሰበውን ረቢዑል አወል ወር ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን እንዲሁም የደም ልገሳን የዚህ እዝነት ቀጥተኛና ተግባራዊ መገለጫ አድርገው እንደሚመለከቱ የዘመቻው አስተባባሪዎች ገልፀዋል፡፡ “በሀገራችን በሁሉም አካባቢዎች በሚገኙ የጤና ተቋማት ደም ለድንገተኛ ቀዶ ጥገና፤ በወሊድ ወቅት ለእናቶች፣ ለአደጋ ተጎጂዎች እና የካንሰር ታካሚዎች ሁሉ በበቂ ሁኔታ እንዲኖያ ያስፈልጋል ያሉት የሊጉ አስተባባሪዎች "አንድም እናት በደም እጥረት ችግር እንዳይገጥማት በተቀናጀ እና ሀገር አቀፍ በሆነ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባር ችግሩ ሊቀረፍ እንደሚችል እናምናለን።”ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታወቀዋል፡፡ የበጎ ፈቃድ ዘመቻው የብሔር፣ የቋንቋ እና የሃይማኖት ልዩነት ሳይለይ በሩ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ክፍት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን መላው ህብረተሰብ የዘመቻውን ሰብአዊ ዓላማ በመረዳት ከጎናቸው እንዲቆምና በንቃት በመሳተፍ የሰው ህይወት እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል።

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • "Blood Donation: The Gift of Life! Save human lives by donating blood at nearby donation sites during the blood donation program taking place on Thursday, August 13, 2026 (Nehase 7, 2018 E.C.). Donating blood means being able to save a precious human life! For more information: Toll-free line: 8040"

  • "የደም ልገሳ፡ የሕይወት ስጦታ!" * ሐሙስ 7/12/18 ዓ.ም በሚካሄደው የደም ልገሳ መርሃ-ግብር በአቅራቢያዎ በሚገኙ የልገሳ ቦታዎች በመገኘት ደም በመለገስ የሰዎችን ሕይወት ይታደጉ። ደም መለገስ ማለት ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት መታደግ መቻል ነው! ለተጨማሪ መረጃ፦ የነፃ የስልክ መስመር፦ 8040

  • በኦሮሚያ ክልል በ2018 በጀት ዓመት ከ130 ሺህ ዩኒት በላይ ደም ተሰበሰበ። * አዲስ አበባ — በኦሮሚያ ክልል በ2018 በጀት ዓመት 125 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ ፤ ከ130 ሺህ ዩኒት በላይ ደም መሰብሰብ መቻሉን የክልሉ ደም ባንኮች አስተባባሪ አቶ ጌቱ ገብሬ አስታወቁ። አስተባባሪው ለኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ የኮሙኒኬሽን ክፍል በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ ይህ ስኬት ሊገኝ የቻለው በጋራ ጥረትና ቅንጅት ነው። ለአፈጻጸሙ መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች፣ ለደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ፣ ለክልሉ ጤና ቢሮ፣  እንዲሁም ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የበጀት ዓመቱ አፈጻጸም ከእቅድ በላይ ቢሆንም፣ በክልሉ የሚገኙ የሕክምና ተቋማትን የደምና የደም ተዋጽኦ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማሟላት አሁንም ቢሆን ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ አቶ ጌቱ አስገንዝበዋል። በኦሮሚያ ክልል የበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ቢመጣም፣ ማኅበረሰቡ ደም መለገስን የዘወትር ባህሉ አድርጎ እንዲቀጥል በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫና የማኅበረሰብ ንቅናቄ ሥራዎች አሁንም በስፋት መሠራት እንዳለባቸው ገልጸዋል። በክልሉ የደም ባንኮችን ተደራሽነት ለማስፋት በተደረገው ጥረት፣ በ2018 በጀት ዓመት የደምቢዶሎ እና የያቤሎ ደም ባንኮች ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል። ይህም በክልሉ የሚገኙ የደም ባንኮችን ቁጥር ወደ 17 አሳድጎታል። በሌላ በኩል፣ በበጀት ዓመቱ በክልሉ ባሉ ደም ባንኮች መካከል በተደረገው የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አብዛኞቹ  ደም ባንኮች በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፤ የሸገር ደም ባንክ፤የጎባ ደም ባንክ እና የማያ ደም ባንክ በቅደም ተከተል ከ1-3ተኛ ደረጃ በመያዝ የላቀ አፈጻጸም በማሳየት እውቅና አግኝተዋል። በመጪው 2019 በጀት ዓመት ከ150 ሺህ ዩኒት በላይ ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስተባባሪው ገልፀው በተለይም በክረምቱ ወራት በተከናወነ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከእቅድ በላይ ደም መሰብሰብ መቻሉን አውስተዋል።በያዝነው በጀት ዓመትም ደህንነቱ የተጠበቀ ደም አቅርቦትን  ለማሳደግ ተጨማሪ ደም ባንኮችን ለማቋቋም እንደሚሠራም አስታውቀዋል። አቶ ጌቱ በመጨረሻም ደም በመለገስ የዜጎችን ሕይወት የታደጉ በጎ ፈቃደኞችን፣ በግብአት፣ በሎጀስቲክስ፣ በአቅም ግንባታና በክትትል ድጋፍ ላደረገው ለኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ እንዲሁም በበጀትና ሁለገብ ድጋፍ ለሚያደርገው ለክልሉ ጤና ቢሮና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ETHIOPIAN BLOOD & TISSUE BANK SERVICE — tgindex