tgindex
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች

Статистика

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Последний пост
7 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
am
Категория
Instagram
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
2 861
−4 за 2 дн.
Сутки
−4
−0,14%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
817
21 постов
Вовлечённость
28,6%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
307
1/48двое суток
351
1/72трое суток
379

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 7 авг.347154

    🌾✞ #ጾመ_ፍልሰታ ✞🌾 ✅✞ "ፍልሰታ" የሚለው ቃል "ፈለሰ፣ ተሰደደ፣ ተጓዘ" ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን እመቤታችንም ከጌቴ ሴማኒ ወደ ገነት መፍለሷን በኃላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረችበት መነሳቷን ለማመልከት አስቀድሞ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት "ተንሥእ እግዚኦ ውስተ እረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ"(አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም) መዝ ፻፴፩፥፲ በማለት ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የእመቤታችንን ምልጃዋን ትንሣኤዋን አስቀድሞ በትንቢቱ ተናግሮ ነበር። t.me/EOTC2921 ✅✞ የፍልሰታ ጾምም ሁሌ በየአመቱ ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን ይሆናል። በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ጥር ፳፩ ቀን አርፋ በ፷፬ ዓመት እድሜዋ በ፵፱ ዓ/ም አይሁድ ለምቀኝነት አያርፋም ነበርና ቀድሞ ልጅዋን ተነሣ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል አሁን ደግሞ እሷን ተነሣች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን? "ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ"(ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው) ብለው ተነሱ። ከመካከላቸውም አንድ ታውፋንያ የሚባል ጎበዝ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ የአልጋውን ሸንኮር መያዣ ሲይዝ ቅዱስ ገብርኤል በእሳት ሰይፍ እጆቹን ቆረጣቸው። እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ። ታውፋንያም ወደ ሐዋርያት ዞሮ በድያለሁ ይቅር በሉኝ ብሎ ቢማፀን፤ የምሕረት እናት የሆነች እመቤታችን አይኖቹዋን ገልጣ ቅዱስ ጴጥሮስን እጆቹን መልስለት ብላው እጆቹንም እንደ ነበሩ መልሶለት ተፈውሷል። ✅✞ ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ። ከዚያም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡ ወዲያውኑ የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ የቅድስት ድንግል የከበረ ሥጋዋን በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በመቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡ ኋላም በጌታ ፈቃድ ከተቀሩት ሐዋርያት ጋር ተገናኘ። ሐዋርያትም የእመቤታችንን ነገር እንደምን እንደኾነ ሲጠይቁት ርሱም በገነት ያየውን ነገር ነገራቸው፤ ሐዋርያትም ይኽነን ታላቅ ምስጢር ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በአረፈች በስምንተኛው ወር ነሐሴ ፩ ሱባኤ ጀመሩ ነሐሴ ፲፬ ቀን በኹለተኛው ሱባኤ ጌታ የእናቱን ሥጋ አምጥቶ ሰጥቷቸው በምኅላና በደስታ በጌቴሴማኒ አሳረፋት። ✅✞ ከዚህም በኃላ በሦስተኛው ቀን ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ በተወደደች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ምድርን ይጠሯት ዘንድ አዘዛቸው እነርሱም ምድርን “ይኤዝዘኪ እግዚእነ ከመ ታውጽኢ ሥጋሃ ለእሙ ቅድስት” (ጌታችን የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ ያዝሻል) አሏት፤ ያን ጊዜ ልጇ “ንዒ ኀቤየ ወላዲትየ ከመ አዕርጊ ውስተ መንግሥተ ሰማያት”(ወደ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ እናቴ ወደኔ ነዪ) አላት፤ በልጇም ሥልጣን የቅድስት ድንግል ማርያም ነፍሷና ሥጋዋ ተዋሐዱ፤ በነሐሴ ፲፮ ዕለትም እመቤታችን ከሞት ተነሣች፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ከሰማይ በታላቅ ግርማ ወረዱ፤ ነቢዩ ዳዊትም "ንግሥቲቱ ወርቀ ዘቦ ግምጃ ደርባ ደራርባ በቀኝኽ ትቆማለች" እያለ ይዘምርላት ነበር፤ አየሩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመላ፤ እጅግ የሚያስደንቅ መዐዛ አካባቢን ዐወደው። በታላቅ ክብርም በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ፤ ጥሪው ከሰዱቃውያን ትውልዱ ሕንዳዊ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ ሰማዩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመልቶ የአምላክ እናት በክብር ስታርግ ተመለከተ፤ ያን ጊዜ ነገሩ ረቆበት ምን ይኾን እያለ ሲል ቅዱሳን መላእክት የእመቤታችን ዕርገት እንደኾነና እጅ እንዲነሣ ነገሩት፡፡ ቅዱስ ቶማስም ትንሣኤዋን ከእርሱ ሰውራ ያደረገች መሥሎት፤ “ከቶ ምን አርጌ ይኾን፤ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ ቀረኊ ዛሬ ደግሞ የርሷን ትንሣኤ ሳላይ ልቅር?” ብሎ ከደመና ተወርውሮ ሊወድቅ ወደደ። http://t.me/EOTC2921 ✅✞ እመቤታችንም “አይዞኽ አትዘን እነሱ ሞቴን አይተዋል እንጂ ዕርገቴን አላዩም። አኹንም እመቤታችን ተነሣች፤ ዐረገች ብለኽ ንገራቸው” ብላ ለቀሩት ሐዋርያት ምልክት የሚሆን ሰበን ወይም መግነዟን ሰጥታው ተለያዩ። እርሱም በደስታ ተመልቶ ሐዋርያት ያሉበት በመኼድ የእመቤታችን ነገር እንደምን ኾነ ብሎ ጠየቃቸው፤ እመቤታችን ሞተች ቀበርናት አሉት፤ “መቼ ሞተች?” አላቸው በጥር አሉት፤ “መቼ ቀበራችኋት?” አላቸው በነሐሴ አሉ፤ ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይኽ ነገር እንዴት ይኾናል? አላቸው፤ ቅዱስ ጴጥሮስም ቶማስን ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ አላምን ብለኽ የጌታን ጐን የዳሰሰ እጅኽ ተቃጥሎ ነበር፤ አኹን ደግሞ እኛ ብንነግርኽ አላምን ትላለኽ ብሎ፤ መቆፈሪያ ይዞ ኼዶ ይቆፍር ጀመር፤ እርሱም የያዘውን ይዟልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፤ ቈፍረው ሲያጧት ደነገጡ፤ ቶማስም አይዟችኊ አትደንግጡ እመቤታችን እኮ በመላእክት ምስጋና ወደ ሰማይ አረገች ብሎ ሰበኑን አሳያቸው፤ እነርሱም ለበረከት ሰበኑን ተካፍለውታል፡፡ ዛሬም ሐዋርያዊት የኾነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ይኽነን በማሰብ ዛሬም ቀዳሽ ዲያቆኑ ከመስቀል ሥር ከመፆሩ ጋር የሚይዘው መቀነት መሳይ ጨርቅ የእመቤታችን የሰበኗ ወይም የመግነዝዋ ምሳሌ ነው። ✅✞ ከዚህም በኃላ በዓመቱ ሁሉም ሐዋርያት ተሰባስበው ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በድጋሚ ሱባኤ ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፬ ቢጾሙ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ነፍሷን ከስጋዋ አዋህዶ ትንሣኤዋንም ዕርገቷንም አሳይቷቸዋል። ክብር ይግባውና ጌታችን በደመና ነጥቆ ወስዶ ሥርዓተ ቊርባንን ፈጽሞላቸው፤ ስለ እናቱ ዕርገት በዓለሙ ኹሉ ዙረው እንዲያስተምሩ አዝዟቸዋል፡፡ እነርሱም ዓለምን ዞረው ወንጌልን ሲያስተምሩ የእመቤታችንን ትንሣኤና ዕርገትም ሰብከዋል አስተምረዋል፡፡ እኛም ከበረከቷ ለመሳተፍ በመላው ዓለም የምንገኝ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆንን ሁሉ ከሕፃን እስከ አዋቂ ድረስ በፍቅርና በዕምነት የምንጾመው የሱባዔ ጾም ነው። ✅✞ እመቤታችን ከእናቷ ማሕፀን ዠምራ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች አዳማዊ ኀጢአት ያላገኛት፣ ኀጢአት አልባ የኾነች እንዲያውም አዳምና ሔዋን ከእርግማን በፊት ከነበራቸው ንጽሕና የበለጠ ንጽሕናን ገንዘብ ያደረገች ስትኾን ክብር ይግባውና አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽነን ንጹሕ ሥጋዋንና ነፍሷን በመንሣት በተዋሐደው ሥጋ በመስቀል ተሰቅሎ፤ ሦስት መዓልትና ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ፤ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትንና ኀጢአትን ድል ነሥቷልና፤ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን ተነሥታለች። "በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝ ትቆማለች።"(መዝ ፵፬፥፱)፡፡ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

  • без подписи

  • 31 мая1 220151

    без подписи

  • 31 мая1 100131

    🌾 መቼ ይሆን? 🌾 አምላኬ ሆይ አባቴ ሆይ እረኛዬ የማትረሳ የማት'ተወኝ ጌታዬ አንተ ቅዱስ ቤትህ ቅዱስ ስምህ አዳኝ የሚፈውስ የመሸብኝ ካንተ ርቄ የነጋብኝ በኔው ስቄ ባንተው ስራ ታየውብህ ተከበርኩኝ ሰፋውብህ ከፍ አረከኝ ኮራሁብህ እየኝማ አባቴ ሆይ ተመልከተኝ ወዳጄ ሆይ ፈካ ብዬ ተጠቅልዬ በነጠላ ከልለኸው ጉድፍ መልኬ እንዳይጎላ ካንተ ውጪ የዋልኩበት አንተን ትቼ ያደርኩበት ባይመችም አለሁ እዛው መቼ ይሆን የምትመጣው? ዛሬ ይሆን የምትመጣው? ለስጋ ሀሳብ እየተጋው ውስጤን ነፍሴን እንደጎዳው ማታ ይሆን የምትመጣው? እየሰከርኩ እየጠጣሁ? መሸታ ቤት እያነጋሁ በራቀ ድምፅ በቄሱ ድምፅ ሳህታቱን ኪዳንህን ገድላትህን እየሰማሁ በሙዚቃ ጭፈራዬን እያስነካሁ ያኔ ይሆን የምትመጣው ? መቼ ይሆን የምትመጣው? ማታ መቼም ባትመጣ በባለ 50ም  ባትመጣ ቅዳሜ ቀን ባትመጣ ካንተ ስርቅ ባትመጣ አታየኝም ታጣኛለህ ሳትለየኝ ትሄዳለህ ሌላ ሆኜ ታልፈኛለህ የሞኝ ሀሳብ የምመኘው ሀጥያቴን እንደመተው ካንተም ከኔም እንድሆነው በኩዳዴ በፆሙ ና አርብ እና ሮብ ወይ በገና ባስራ ስድስት በነሀሴ ወይም እሁድ በቅዳሴ ማታ አዳሬን እየወቀስኩ ፊትህ ቆሜ እያለቀስኩ ለንሰሀ እንደበቃሁ ለማስቀደስ እንደገባሁ ያን ግዜ ና ቤትህ አግኘኝ እንዳልወጣ ቤትህ አስቀረኝ ታምሚያለሁ አንተ አክመኝ ልብ ስጠኝ አንተን ልበል ያንተው ሆኜ ባንተ ልማል ልታዘዝህ ቤትህ ልዋል:: ከቤቱ አያርቀን በምህረቱ ይመልከተን🙏 ✍️ ቸርነት ፍቃዱ

  • 12 апр.1 4903

    без подписи

  • 12 апр.1 27381

    🌺በስመአብ🌺 🌺 ወወልድ 🌺 🌺ወመንፈስ ቅዱስ🌺 🌺 🌺 🌺አሃዱ🌺 🌺አምላክ🌺 🌺አሜን🌺 ✍✞“#ክርስቶስ_ተንሥአ_እሙታን” (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) ✍✞“#በዐቢይ_ኀይል_ወሥልጣን” (በገናና ኀይልና ሥልጣን) ✍✞“#ዐሠሮ_ለሰይጣን” (ሰይጣንን ዐሰረው) ✍✞“#አግአዞ_ለአዳም” (አዳምን ነጻ አወጣው) ✍✞“#ሰላም” (ፍቅር አንድነት ሆነ) ✍✞“#እምይእዜሰ” (ከእንግዲህስ) ✍✞“#ኮነ” (ሆነ) ✍✞“#ፍሥሐ_ወሰላም” (ደስታ ሰላም) ✝አሜን እንኳን አደረሳችሁ✝ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #ሕያውን_ከሙታን_መካከል_ስለ_ምን_ትፈልጋላችሁ_ተነሥቶአል_እንጂ_በዚኽ_የለም፡፡ሉቃ 24፡5 •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #በመስቀሉ_ደም_ሰላምን_አደረገ_በሰማያትም_ላሉት_እርቅን_ሰላምን_አደረገላቸው፡፡ ቆላ፡1÷19 •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #ለኃጢአት_ሞትን_ለፅድቅ_እንድንኖር_እርሱ_ራሱ_በሥጋዉ_ኃጢያታችንን_በእንጨት_ላይ_ተሸከመ_በመገረፉ_ቁስል_ተፈወሳችሁ_እንደ_በጎች_ትቅበዘበዙ_ነበረና_አሁን_ግን_ወደ_ነፍሳችሁ_እረኛና_ጠባቂ_ተመልሳችሃል። 2ኛ ጴጥ 2÷24 •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #የመሰቀሉ_ቃል_ለምጠፉት_ሞኝነት_ለእኛ_ለምድን_ግን_የእግዚአብሔር_ኃይል_ነው፡፡ 1ኛ ቆሮ፡1÷18 •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #ከጌታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ_መስቀል_በቀር_ሌላ_ትምክህት_ከእኔ_ይራቅ፡፡ገላ፡6÷14 •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• 💐ሰላም💐 💐ለአንተ💐 💐ይሁን💐 💐ውድ የተዋህዶ ልጆች💐 🌹እንኳን🌹 🌹ለብርሃነ🌹 🌹 🌹 🌹 🌹ትንሳኤው🌹 🌹 🌹 🌹በፍቅር🌹 🌹በሰላምና🌹 🌹በጤና🌹 🌹 🌹 🌹አደረሳችሁ🌹 🌹 አደረሰን🌹 🌹 🌹 🌹መልካም🌹 🌹የትንሳኤ🌹 🌹 በአል🌹 🌹ይሁንላችሁ🌹 ✞ 🌹አ🌹 ✞አሜን✞🌹ሜ🌹✞አሜን✞ 🌹ን🌹 ✞ ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

  • #ሕያውን_ከሙታን_መካከል_ስለ_ምን_ትፈልጋላችሁ__ተነሥቶአል_እንጂ_በዚኽ_የለም (ሉቃ 24፡5)" •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ♥ ይህ የትንሣኤ በዓል ሞት የተሸነፈበት፣ መቃብር የተረታበት፣ ሕይወት ያገኘንበት ታላቅ በዓል ነውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ በሞቱ ሞትን ድል መንሣቱን፣ ሙስና መቃብር መጥፋቱን፣ ዓለም በብርሃን መመላቱን ትመሰክራለች፡፡ ♥ ክብር ይግባውና ለአዳም በሰጠው ተስፋ መሠረት ወልደ እግዚአብሔር ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ተወልዶ በሚያስተምርበትም ጊዜ 3 ቀንና 3 ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ እንደሚነሣ ያስተምር ነበር፡፡ ጥቅሶቹም፦ (ማቴ 12:40፤ ሉቃ 9:21፤ ዮሐ 2:19) ♥ የዚኽም አቈጣጠር ሁለት ዐይነት ነው የመጀመሪያው “መዓልት ይስሕቦ ለሌሊት ወሌሊት ይስሕቦ ለመዓልት” (ቀን ሌሊትን ሌሊት ቀንና ይስባል) በሚለው የአቈጣጠር ዘዴ ጌታ ቅድስት ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ዐርብ በሠርክ ወደ መቃብር ስለወረደ ዐርብ እንደ አንድ ቀን ሲቈጠር፤ ቅዳሜ ያው አንድ ቀን፣ እሑድ ደግሞ መንፈቀ ሌሊት ስለተነሣ እሑድ እንደ አንድ ቀን ይቈጠራል። ♥ ሌላው አቈጣጠር ደግሞ ዕለት የሚለው ፍቺ አንድ እጅ ብርሃን አንድ እጅ ጨለማን ያካተተ ነው፤ ሰለዚህ በዚህ ተመርጒዘን ካየነው ► የስቅለት ዕለት ዐርብ ከጠዋት እስከ ስድስት ሰዓት ብርሃን ስለሆነ አንድ እጅ ብርሃን ► ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ስለኾነ አንድ እጅ ጨለማ ► በሠርክ ደግሞ ብርሃን ሆኗል አንድ እጅ ብርሃን ► ቅዳሜ ደግሞ ሙሉ ቀን ሙሉ ሌሊት ስለሆነ አንድ እጅ ብርሃን አንድ እጅ ጨለማ ► ጌታ የተነሣው እሑድ ሌሊት ስለሆነ አንድ እጅ ጨለማ ነበር፡፡ ስለዚህ ሦስት እጅ ብርሃን ሦስት እጅ ጨለማ 3 መዓልት 3 ሌሊት ተብሏል፡፡ ♥ ጌታችን ለምን ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐደረ ቢሉ? ሀ) 1) አዳምን 2) ሔዋንን 3) ሕፃናቱን እንዳደነ ለማስረዳት 3 ዕለት ዐደረ ለ) 1) ለሥጋችን 2) ለነፍሳችን 3) ለደመ ነፍሳችን እንደካሰልን ለማስረዳት ሐ) የሰው 3 ጠላቶች ይኸውም 1) ሞት 2) ፍዳ 3) ኀጢአትን እንዳጠፋ ለማጠየቅ ነው ♥ ክብር ይግባውና ትንሣኤና ሕይወት የኾነው አምላካችን ክርስቶስ ሞትን ድል ነሥቶ በድንቅ ምስጢር መቃብሩ እንደተዘጋ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል እሑድ በመንፈቀ ሌሊት ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ያን ጊዜ ዓለም በብርሃን ተዋጠ፡፡ ♥ የፅንሰቱና የልደቱ ምስጢር ከትንሣኤው ምስጢር ጋር ይስማማል፤ ይኸውም በፅንሰቱና በልደቱ የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያምን ማኅተመ ድንግልና ሳይከፍት እንደተፀነሰና ሳይከፍት እንደተወለደ ሁሉ አሁንም በተዘጋ በተገጠመ መቃብር በድንክ አምላካዊ ጥበብ ረቂቅ ዘእምረቂቅ የሆነው አምላክ ተነሣ፡፡ ♥ ለዚህ ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዐተ ቅዳሴዋ ላይ “ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን በመንክር ኪን” (ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሣልፎ የሚኖረውን በድንቅ አምላካዊ ሥራ ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ጌታችንን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በበፍታ ገነዙት) በማለት ለልጆቿ የትንሣኤውን ታላቅነት እየመሠከረች “ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ” (ትንሣኤህን ለምናምን ለእኛ ብርሃንህን ላክልን ወደኛ) እያለች በፍጹም ደስታ ትዘምራለች፡፡ ♥ዕለተ እሑድ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ የተነሣባት ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት እናከብራታለን፤ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ የዕለተ ዐርቡን የመከራ እና የዕለተ እሑድን የደስታ ቀን እንዲኽ ያነጻጸረውን እነሆ ብያችለኊ፡- ✍ ከትላንትና ወዲያ አይሁድ እየተዘባበቱበት “ራስኽን አድን” ይሉት ነበር (ማቴ ፳፯፥፵)፤ ዛሬ ግን ርሱ ጥሎት የተነሣበትን መቃብር መላእክት እየሳሙት ነው፤ ትናንት ሞቶ በመቃብር በተቀበረ ሰው ልማድ በታተመ መቃብር በዝምታ ነበር፤ ዛሬ ግን ሕያው ኾኖ ለሙታንም ሕይወትን በመስጠት ኹሉንም ወደ ሕይወት አስነሣቸው። ♥ ከትናንትና ወዲያ ጦር፣ ኾምጣጤ እና ኀሞት እሾኽ እንዲኹም ስቅለት ነበር፤ ዛሬ ግን መላእክት በክብር እና በደስታ ዘመሩለት፤ ከትናንትና ወዲያ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የእግዚአብሔር ልጅ ነፍሱን በአባቱ እጅ አደራ ሰጠ (ሉቃ ፳፫፥፵፮)፤ ዛሬ ግን ኹሉንም የማዘዝ ሥልጣን ያለው ርሱ ነፍሱን ከሥጋው ጋር አዋሐዳት። ♥ ትላንት የመሰቀያውን መስቀል አቆመ፤ ዛሬ ግን ጥንካሬ፣ የሙታን ትንሣኤና ኀይል ኾነ፤ ከትናንት ወዲያ ስምዖን አላውቀውም በማለት በተደጋጋሚ ካደው (ማቴ ፳፯፥፸)፤ ዛሬ ግን ሞትን ድል ነሥቶ በመነሣቱ መቃብሩን ለማየት ሲሮጥ ኼደ (ዮሐ ፳፥፬)፤ የዕለተ ዐርብ መከራው ለሐዋርያት ጉባኤ መሸመቂያ አዘጋጀ፤ እሑድ ግን ዐዲስ ራእይና ደስታ ኾነ። ♥ ትናንት ንጉሡ በመቃብር ተኝቶ ነበር፤ ዛሬ ግን ወይኑ እንደተወው ኀያል ተነሣ (መዝ ፸፯፥፷፭)፤ ባላፈው ቀን ቅዱሳት አንስት በመከራ እና በለቅሶ ውስጥ ነበሩ (ሉቃ ፳፫፥፳፯)፤ ዛሬ ግን ርሱን እንደ አትክልተኛ አይተውት ታላቅ ደስታ ሐሴትን አደረጉ፤ በዐሳዛኙ ሰንበት ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ርሱ በኩረ ሙታን ከሙታን መኻከል ነበር፤ እሑድ ግን በመላእክት ጉባኤ ታጀበ (ማር ፲፮፥፭)። ♥ በዕለተ ዐርብ የሐዋርያት ጉባኤ በሐዘን ተበተነ፤ ዛሬ ግን ትንሣኤውን በመደነቅ ለማየት የደቀ መዛሙርት ጉባኤ ወጥተው ነበር፤ በሌላኛው ቀን ሽሽት፣ በመበታተንና ራሳቸውን መደበቅ ነበረባቸው፤ ዛሬ ግን ለመሮጥ፣ በአንድ ላይ ለመሰብሰብ እና የምሥራቹን ለማምጣት ቻሉ፡፡ ♥ ትናንት እረኛው ተመትቶ የርሱም ጠቦቶች ተበታትነው ነበር (ዘካ ፲፫፥፯፤ ማቴ ፳፮፥፴፩)፤ ዛሬ ደግሞ ተኲላዎቹ ፈረጠጡ፤ መንጋዎቹ በደስታ ተመሉ፤ ትናንት ይሁዳ ገንዘብ ተቀበለ፤ ቀያፋ ምክር ሲሰጥ ሃናም ሲያወግዝ ተሰማ፤ ጸሓፍት በሁካታ ውስጥ ነበሩ፤ ጲላጦስ ተቀምጧል፤ ጌታችንም ምሰሶውን ይዞ ቆሟል፤ ስምዖን ክዷል፤ እንድርያስ ሸሽቷል፤ ዮሐንስ ርቀቱን ጠብቋል፤ ፊሊጶስ አይታይም፤ ማቴዎስ ተደብቋል፤ በርተሎሜዎስ ጸጒረ ልውጥ ኾኗል፤ ቀነናዊው ተርበትብቷል፤ ኹሉም በያለበት ተበትኗል (ማቴ ፳፯፥፭-፵፭)። ♥ ዛሬ ግን ቀያፋ ኀፍረት ተከናንቧል፤ ሃና ግራ መጋባት ውስጥ ገብቷል፤ ይሁዳም ብሩን በትኖ ራሱን ዐንቋል (ማቴ ፳፯፥፭)፤ ጸሓፍትም መናገር ተስኗቸዋል፤ የምኲራብ አለቆች በኀፍረት ራሳቸውን ሸፍነዋል፤ ሌዋውያን ርስ በርሳቸው እየተወቃቀሱ ነው፤ ጲላጦስ ተደንቋል፤ የዚኽ ኹሉ ጠንሳሾች ከነጭራሹ በቦታው የሉም፤ የተኲላ መንጋዎች ተበትነዋል። ♥ እረኛው ከበጉ ጋር ይነጋገራል፤ መንጋዎቹን ሲሰበስባቸው መዐዛውን ሳቡት፤ ማርያም ተደስታለች (ማር ፲፮፥፩)፤ ሰሎሜም በኀሤት ተመልታለች፤ ማርታ መልካም ዜና ይዛለች፤ ዮሐና የሰላም ዜና ታመጣለች (ሉቃ ፳፬፥፲)፤ ደቀ መዛሙርት ራሳቸውን ገልጠዋል፤ ሐዋርያት ከተደበቁባቸው ቦታዎች ወጥተዋል፤ ስምዖንና ዮሐንስ ወደ መቃብሩ ሮጠዋል፤ ማቴዎስና በርቶሎሜዎስ ጭንቀታቸውን ረስተዋል፤ እንድርያስና ያዕቆብ በደስታ ውስጥ ናቸው፤ ቶማስ ተናዝዟል፤ ፊሊጶስ ምስጋናን አቅርቧል። ✍ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ✞ ዘማቴዎስ። "ጊዜ ተሰዓቱ ሰዓት ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ።" ✞ ዘማርቆስ። "ጊዜ ተሰዓቱ ሰዓት ገዓር ኢየሱስ በቃሉ ወወፅአት መንፈሱ ሶቤሃ።" ✞ ዘሉቃስ። "ጊዜ ተሰዓቱ ሰዓት ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅፀነ ነፍሶ ሶቤሃ።" ✞ ዘዮሐንስ። "ጊዜ ተሰዓቱ ሰዓት አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኵሉ።"

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи