tgindex
ኤሊሲያ

ስነ-ጽሑፍ የነፍስ ምግብ ነው ✍️ የሀሳብ ፍሰቶች፣ የስሜት መግለጫዎች እና ግሩም የሆኑ ስነ-ጽሑፋዊ ስራዎች የሚቀርቡበት አዲስ መድረክ ✨ እንኳን ደህና መጡ! ቃላትን ልብዎ ድረስ እንሸኛለን..😊

Последний пост
8 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
209
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
161
19 постов
Вовлечённость
77,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
117
1/48двое суток
134
1/72трое суток
144

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የልጅነትን ንጹሕ ዓለም ስናስብአዋቂዎች ከጠፋብን እውነት ጋር እንገናኛለን። አንድ ሕፃን ምስጢር አያውቅም፤ ከታመመ ይናገራል እንጂ ተደብቆ አያለቅስም፤ ችግሮቹንም በሰዎች ፊት በግልጽ ያሳያል። ስለ መጪው ጊዜ ጨርሶ ሳይጨነቅ፣ አሁን ያለውን ሰዓት በሙሉ ኃይሉ ይኖርበታል። ለነገ ምግብ ሳያስቀር፣ ነገም እንደሚመገብ ባለው የጸና ተስፋ ይኖራል፤ በሚገርም ሁኔታም ይሳካለታል።​ ልጆች ነገሮችን ለዘላለም ይዞ የመቆየት ስግብግብነት የለባቸውም። መጫወቻ ገዝተው ያጠፉታል፤ የአሸዋ ግንብ ሠርተው በራሳቸው እጅ ይፈርሱታል ይህም «ምንም ነገር ለዘላለም አይኖርም» የሚለውን ታላቅ የሕይወት ትምህርት ይሰጡናል። ከዚህም በላይ ሕፃናት ራስ ወዳድ አይደሉም፤ የሰውን ጥቅም ከራሳቸው ጋር አያመዛዝኑም፤ ለዚህም ነው በቀላሉ የሚታለሉት። ሆኖም፣ ከሁሉም በላይ ልጆች በትንሽ ነገር ሊደሰቱ የሚችሉ እጅግ ንጹሖች ፍጥረታት ናቸው።

  • እዚህ ቻናል ውስጥ ገብታችሁ ለምታገኙት እውቀት እኔ ተጠያቂ አይደለሁም!! https://t.me/Evangadi21

  • ሌሊት ሲወርድ ሁሉም ይተኛሉ እኔ ግን ከራሴ ጋር እወያያለሁ ያልተነገሩ ህመሞች..... ያልተፈጸሙ ህልሞች እና ነገ የሚሻል እንደሚሆን ያለኝ ተስፋ... ማንም አያየውም ግን በውስጤ የሚደረገው ትግል ትልቅ ነው ምክንያቱም አንዳንድ ድሎች ከሌሎች ፊት አይታዩም በዝምታ ውስጥ ይወለዳሉ።

  • መልካም ነገር ሰርተህ ወንዝ ውስጥ ጣለው : አንድ ቀን በርሀ ላይ ታገኘዋለህ

  • ምን ስጦታ ልስጣት ብዬ ብዙ ተጨነኩ 🤔 ላንቺ የሚሆን ምንም ላገኝ አልቻልኩም 😞 ሻኪሶ ወርቅ ተይዞ ይኬዳል? 🤔 ...ለውቂያኖሶ ውሀ ይሰጣል? 💧 ያሰብኩት ስጦታ ሁሉ በርበሬ ይዞ ማረቆ እንደ መሄድ ሆነብኝ.. ቅጠል ለዛፍ እንደመስጠት ልቤን ወይም ፍሴን ብሰጥሽም ጥቅም የለውም 🥀 ሁለቱንም ይዘሻቸዋል..... ስለዚህ ፍቅሬ መስታወት ይዤልሽ መጥቻለሁ ❤️ ራስሽን እያየሽ ሀልጊዜ አስታውሽኝ 😊

  • ወንድ ልጅ የውበት ሳሎን ገብቶ ፊቱን አቮካዶ ተቀብቶ፣ በፎጣ ጭንቅላቱን ተጠቅሎ፣ 🤔 እግሩን እና እጁን ማስታጠቢያ ውስጥ ተዘፍቶ ቸከሶቹ እያገላበጡ እግሩን በብሩሽ እያጠቡት እና ጥፍሩን በሞረድ እየገዘዙለት እንደማየት እመነኝ ቀንህን የሚጦልብ ምንም ነገር የለም! 🤷‍♂️ . . ደግሞ እኮ "በቧንቧ ውሃ ፊቴን አልታጠብም!፣ አለርጂ አለብኝ! "Yes" ውሃ አምጠልኝ!" ምናምን እያለም ይጨመላለቃል! 😂🛁🚿

  • ‹‹Some rise by sin, and some by virtue fall.›› - ‹‹አንዳንዶች በኩነኔያቸው ጀገኑ፤ ሌሎች ስለበጎነታቸው ተነወሩ፡፡›› William Shakespeare (Theatre - Measure for Measure)

  • እሱ:- ይህ ሁሉ ናፍቆት ለምንድን ነው? እሷ፦ ምክንያቱም አንተን ማሰብ ራሴን እንደማሰብ ነው... እሱ፦ ግን በአካል የለሁም እሷ፦ አካልማ የስሜት እስር ቤት ነው...ፍቅር ግን ነፃነት ነው..እዚህ የሌለህበትን ቦታ በውስጤ ላንተ ባዘጋጀሁት ስፍራ እየተመላለስኩ እኖራለሁ.. ናፍቆት እኮ መገናኘት መሻት አይደለም፣ በአንድ ነፍስ ውስጥ መዋሃድ እንጂ

  • ስለአንድ ፡ሀብታም ፡ገንዘብ ፡ሞልቶት ፡የተረፈው ሰው ፡ነው። እድሜውን ፡የፈጀው፡ ገንዘብ በመሰብሰብ፡ ነበር። ሰው፡ አያምንም። ሁሉንም ይጠራጠራል። በዚህ፡ የተነሳ፡ ብቸኛ ፡ሆኖ፡ ሲኖር አንድ ፡ቀን ፡የልብ ፡ጓደኛ፡ ያገኛል። ይህ ፡ጓደኛው ፍጹም፡ ሰው፡ ነበር ፡ታዲያ ፡ሰውዬው፡ ጓደኛው የነገረውን፡ ሁሉ፡ ይሰማል ፣ ይቀበላል ፣ ይፈጽማል።   ቀንም፡ ሆነ ፡ማታ ፡ሌሊትም፡ ሆነ ጧት፡ አይለያዩም ፤ ፍጹም ፡አይለያዪም... ከጊዜ: በኋላ :ያሰው :ገንዘቡ :ያልቅበትና :እጦት አፋፍ: ላይ: ይደርሳል። ጓደኛው የሚሰጠውን ምክር መስማት ፣ መቀበል ፣ መፈጸም ያቆማል።  ቀስ በቀስ እየተራራቁ ይሄዱና ከናካቴው ይረሳሳሉ። ጓደኛው ጨርሶ ይጠፋል።  ያ ሰው ይጸጸታል። ጸጸቱ ግን ሊመልሰው አልቻለም...... "ወይኔ ጓዴ ! ወይኔ ጓዴ ! ጓዴን ገደልኩት ! በገዛ እጄ ገደልኩት !" እያለ ሲጮህ ሂዶ ለፖሊሶች እጁን ይሰጣል:: << ፖሊሶቹ ተጣድፈው 'ሬሳውን አሳየን ፤ ወንጀሉን የፈጸምክበትን ቦታ አሳየን' ሲሉት ፤ ደጋግሞ 'ይሄውና' እያለ ራሱን ያሳያቸው ነበር። ምርመራው ይቀጥላል ይፋፋማል። በየቀኑ ያንኑ ጥያቄ ይጠይቁታል።  እሱም ይሄውና እያለ ይመልሳል።  ከስንት ምርመራ በኋላ በመጨረሻ ህሊናውን የሳተ መሆኑን ይገነዘቡና ወደ አማኑኤል ይልኩታል።  ከጓደኛው ጋር እንደተለያዩ ይቀራሉ።>> አበራ የድርሰቱን ፍሬ ነገር እንደገባው ለማሳየት እሺ እንደሚል ሰው ራሱን ነቀነቀና << ጓደኛው የሰውዬው ህሊና መሆኑ ነው አይደለም?>>  ሲል ለማረጋገጥ ጠየቀው። << ነው >> << ህሊናና ሰው የተራራቁበት ዘመን መሆኑን ለማስታወስ ነው?>> <<ይሆን ይሆናል!>> በአሉ ግርማ✍

  • በቀን : ወይ : በሌሊት በጾም : በቅበላ የበላ  : ይኖራል፥ ይብላኝ : ለተበላ ጋጋሪው : ቢራቀቅ፥ ቢሰወር : ምጣዱ የለት : እንጀራ : ነው፤ አንደኛው: ሰው : ላንዱ :: [ ገ ጣ ሚ : በ ው ቀ ቱ : ስ ዩ ም ]

  • የደከመ ገድሎ ፉከራ ምንድነው ቀን የጣለው‘ለታ እሱም እንደኔ ነው። የት ነበር የማቀው ይሄን ስንኝ?  ልጅቷ እያንጎራጎረች አለፈችኝ። ድምፅዋ የሚያላዝን ያህል ለጆሮ ደስ አይልም።  ዞሬ አየኋት። ክፉኛ ገላመጠችኝ። በግርምት ፈገግ አልኩ። የተከሰከሰ ፊት ቅጭም አድርጋ አሳይታኝ መንገዷን ቀጠለች። ወደፊት መራመዴን ቀጠልኩ። ሃሳቤ ግን ያለፍኳትን ልጅ ያስባል። ምን ይሆን ይሄን ስንኝ ያስመረጣት? የእጅጋየሁ "አቦ ሸማኔ" ውስጥ ያለ ስንኝ እንደነበር ዘግይቶ ትዝ ብሎኛል። ምናልባት  ስለሰማኋት ምቾት አልሰጣትም። ምስጢሯን ድንገት የደረስኩበት ያህል ደብሯታል፣ ፈገግ ማለቴ ተጨምሮበት  በቁስሏ ከሚደሰቱት አንደ አንዱ ሆኜ ታይቻት ይሆን? ምን ሆና ይሆን?  ቀጣዩን ስንኝ ስሰማት ካቆመችበት አንጓ ላይ ማንጎራጎር ያዝኩ " እርም የእናቴን ስጋ እምልልሃለሁ ፍቅርን ካልሰጠኸኝ እሞትብሃለሁ" የገዛ ሃሳቧ መሰለኝ። አዘንኩላት። ቀጥ ያለ መንገድ ጨርሼ ከመታጠፌ በፊት ደመነፍሴ አንገቴን ወደኋላ እንዲዞር አደረገው።  ድንገት አይን ለአይን በድጋሚ ተገጣጠምን። በተመሳሳይ መምረር ውስጥ እንደምትገኝ ፊቷ ይናገራል። በድጋሚ ፈገግ አላልኩም። መንገዴን ቀጠልኩ። --- ህይወታችን ልክ እንዲህ ነው። ሁላችንም እልፍ ጊዜ ተላልፈናል። በስሜት፣ በአውድ፣ በልቡና፣በሃሳብ፣ በገቢር…  እልፍ ጊዜ በሕይወት መንገድ ላይ ተላልፈናል። Surafel ayele

  • ለአንዱ በመንፈስ የጥበብን ቃል መናገር ይሰጠዋል፤ ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ የዕውቀትን ቃል መናገር ይሰጠዋል፤ https://t.me/kewenet

  • ሰሞኑን ልጅ ልጅ...ብቻ ልል እችላለሁ😁 የልጅነት ትዝታዎቻችን በሳይኮሎጂ መነፅር ​ሰላም! እንደ አንድ የሳይኮሎጂ ተማሪ እና የትምህርት ባለሙያ ስለ ልጅነት ትዝታዎቻችን አንድ ነገር ላካፍላችሁ። ​ድሮ ልጅ እያለን የምንጫወታቸው ጨዋታዎች እነ፡- 🎶 ኧረ አምሳለ... 🎶 እቴ እሜቴ የሎሚ ሽታ... 🎶 ልጅ ለመፈለግ መጥተናል... 🎶 አሌ ቡሌ... 🎶 መሀረቤን ያያችሁ...ብዙ ብዙ ​እና እንደ "በዚያ በበጋ" ወይም "ገበሬው እርሻ አለው" ያሉ መዝሙሮቻችን መቼም አይረሱም! ​እነዚህ ጨዋታዎችና መዝሙሮች በዘመናዊ የሳይኮሎጂ መርሆዎች ሲታዩ ለልጆች አካላዊ (physical developement) አእምሯዊ (cognitive development) እና ስሜታዊ እድገት (emotional development) ወሳኝ የሆኑ የመማሪያ ሜዳዎች ነበሩ። በግሌ እነዚህ ጨዋታዎች ለልጆች እጅግ ጤናማ እንደነበሩ አምናለሁ ምክንያቱም ልጆች በማህበራዊ ግንኙነት በቋንቋ እና በቡድን ስራ እንዲያድጉ ያደርጓቸው ነበር ( Long Live Dr. Mitku )እዚ ነገር ላይ ብዙ ለመናገር ይቻላል። ነገር ግን የእነዚህን ጨዋታዎች ግጥምና Social Development ላይ ያለውን ነገር ጠልቆ ማየት ያስፈልጋቸዋል ባይ ነኝ ዛሬ ባለውለታ የቴክኖሎጂ ዘመን ከነሱ የተሻለ አማራጭ አለ ይመስለኛል የድሮ ጨዋታዎቻችንን እንደ ትዝታ እንድናወራው ሊሆን ነው ምክንያቱ ደግሞ ከመነሻቸው ጥቂት ስህተቶች መኖራቸው ሊሆን ይችላል ስማችሁን mention ሳላረግ ​የራሳችሁን ሃሳብ እና የልጅነት ትዝታችሁን እንዲሁም አያስፈልጉም ነበር የምትሏቸው ጨዋታዊ ግጥሞች ካሉ ሀሳባችሁን ብታካፍሉኝ ደስ ይለኛል ....

  • ክረምቱን ከእህቴ ልጆች ጋር እያሳለፍኩ ነው አንድ ጥያቄ ተፈጠረብኝ ቆይ ካሁን ጊዜ ልጆች ጋር ያለያየን የዘመን ነው ወይስ የጋራ ጀነቲክ አለ?

  • አንድ መንገደኛ እጅግ ጥቅጥቅ ባለና መንገድ በማይታወቅበት ትልቅ ጫካ ውስጥ ብቻውን እየተጓዘ ነበር። በእጁ ላይ ሁለት ነገሮችን ይዟል፦ አንደኛው በከፍተኛ ድምፅ የሚጮህ ሰዓት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ምንም ድምፅ የሌለው ኮምፓስ ነበር። ​መንገደኛው ጫካው ውስጥ ሲጓዝ፤ የሰዓቱ ቲክ... ቲክ... ቲክ... የሚል ድምፅ እጅግ ይረብሸው ጀመር። ሰዓቱ "ቶሎ በል፤ ጊዜህ እያለቀ ነው። ፀሐይ ልትጠልቅ ነው። አዘግይተሃል" እያለ የሚጮህበት ይመስለዋል። በዚህ የሰዓቱ ጩኸት የተደናገጠው መንገደኛ፤ መድረሻውን ሳያረጋግጥ በጭንቀትና በከፍተኛ ፍጥነት ጫካው ውስጥ መሮጥ ጀመረ። በሮጠ ቁጥር ግን የበለጠ እየጠፋና እየደከመ መጣ። ​በመጨረሻም ዝልፍልፍ ብሎ ዛፍ ሥር ሲወድቅ፤ ቀኝ እጁ ላይ የያዘውን ጸጥተኛ ኮምፓስ ተመለከተ። ኮምፓሱ ምንም አይጮህም፤ አያስጨንቅም። ነገር ግን ቀስ ብሎ ትክክለኛውን የሰሜን አቅጣጫ (True North) ብቻ ያሳያል። መንገደኛውም የሰዓቱን ጩኸት ትቶ፤ ኮምፓሱ ወደሳየው አቅጣጫ በዝግታና በእርጋታ መራመድ ሲጀምር፤ ከጫካው በሰላም ወጥቶ መድረሻው ገባ። ​እናም እኔ እያልኩህ ያለሁት፤ በሕይወታችንና በቢዝነስ ዓለማችን ውስጥ ብዙዎቻችን የምንመራው በሰዓቱ ጩኸት ነው። ☑️ ጓደኞቼ ቤት ሠሩ፤ እኔ ግን ገና ነኝ፤ ☑️ የዕድሜ እኩዮቼ ተሸለሙ፤ እኔ ግን ወደ ኋላ ቀረሁ፤ ☑️ ወሩ ሊያልቅ ነው ግን በቂ ሽያጭ አላመጣሁም... እያልን በማኅበራዊ ሚዲያና በሰዎች የጩኸት ድምፅ (ሰዓት) ተደናግጠን ያለ አቅጣጫ እንሮጣለን። ​ነገር ግን በሕይወትህ ውስጥ ከ"ፍጥነትህ" ይልቅ "አቅጣጫህ" እጅግ በጣም ወሳኝ ነው። ያለ አቅጣጫ (ያለ ዕቅድና ያለ ዕውቀት) በፍጥነት መሮጥ፤ ቶሎ ከመጥፋት ውጪ ሌላ ትርጉም የለውም። በሪል እስቴት ሽያጭም ሆነ በማንኛውም ስኬት ውስጥ ትልቁ ነገር፤ የራስህን ኮምፓስ (ራዕይህን፣ የሥራ ስነ-ምግባርህን እና እውነተኛ የደንበኛ ትስስርህን) ይዘህ በትክክለኛ መንገድ ላይ መገኘትህ ነው። ​ትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ከሆንክ፤ በዝግታም ቢሆን መድረስህ አይቀርም። ዛሬ ሐሙስ ነው። የሌሎችን የሩጫ ፍጥነት እያየህ አትደናገጥ። የሰዓቱን ጩኸት አጥፋውና ከኮምፓስህ (ዓላማህ) ወደሳየህ የትኩረት አቅጣጫ በእርጋታ ተጓዝ። ​ትልቁ ስህተት ትክክል ባልሆነ መንገድ ላይ በፍጥነት መሮጥ ነው። ፍጥነትህን አቁመህ አቅጣጫህን አስተካክል። ​የሌሎችን ሰዓት እያየህ የራስህን ሰላም አታጣ፤ ትክክለኛ አቅጣጫ ይዘህ በእርጋታ የሚደረግ ጉዞ፤ ሁልጊዜም በድል ያበቃል።

  • እኔ ምለው 🤓 ኤርታሌ ላይ ውስጥ ውሃ ቢደፋበት ሙቀቱ የሚቀንስ አይመስላችሁም 🤔

  • ኤሊሲያ pinned «ይህቺን ወግ እዩአትማ ትወዷታላችሁ ​ሶስት ቀኔ ነው ከተኛሁ። ድፍን ሰባ ሁለት ሰዓት! ጓደኞቼ የሰው ልጅ ስንት ቀን ያለ እንቅልፍ እንደሚኖር እያሰቡ እየተጨነቁ ነው። ያመጡልኝንም የእንቅልፍ ክኒን ሆነ ሌሎች የመፍትሔ አማራጮች ለመቀበል ፈቃደኛ አይደለሁም። ​ምክንያቱን ሲጠይቁኝ "ምናለ እናንተ እንኳን ብቻዬን ብትተውኝ" እላለሁ። "ሌላ የሚያስቸግርህ ሰው አለ እንዴ?" የሚለው ጥያቄ ይከተላል። የጭቅጭቅ…»

  • ይህቺን ወግ እዩአትማ ትወዷታላችሁ ​ሶስት ቀኔ ነው ከተኛሁ። ድፍን ሰባ ሁለት ሰዓት! ጓደኞቼ የሰው ልጅ ስንት ቀን ያለ እንቅልፍ እንደሚኖር እያሰቡ እየተጨነቁ ነው። ያመጡልኝንም የእንቅልፍ ክኒን ሆነ ሌሎች የመፍትሔ አማራጮች ለመቀበል ፈቃደኛ አይደለሁም። ​ምክንያቱን ሲጠይቁኝ "ምናለ እናንተ እንኳን ብቻዬን ብትተውኝ" እላለሁ። "ሌላ የሚያስቸግርህ ሰው አለ እንዴ?" የሚለው ጥያቄ ይከተላል። የጭቅጭቅ ክበብ ውስጥ ገብታችሁ ታውቃላችሁ? እንደዛ የሚሆነው ከሁለት አንዳችሁ የምትደብቁት እውነት ሲኖር ነው። 🤔 ​ስምንተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ይመስለኛል። ሁሌ ስፖርት ፔሬድ ስንወጣ የሆነ በግምት ሀያ ስድስት አመት የሚሆነው ወጣት ከዛፍ ስር ቁጭ ብሎ እኔን ብቻ ያየኛል... ወይም ይመስለኛል። ሲደጋገም እያናደደኝ መጣ። ያለኝ አማራጭ ማናገር ነው ብዬ የሆነ ቀን ከውስጥ ቱታ ሳልለብስ መጣሁ። 🏃‍♂️ ​ስፖርት መምህሬ ከጠበቅኩት በላይ ተናደዱ። "ባለፈው ሚኒሚዲያ ላይ ያቀርብከው ወግ ተመችቶኛል ብዬ ብስኩት ስለጋበዝኩህ ንቀኸኝ ነዋ?" ብለው አፈጠጡብኝ። ያልጠበቅኩት መልስ ስለሆነ ከንቀት ጋር የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ ላስረዳ ብሞክርም "ወደፈለግከው መሄድ ትችላለህ... ከአሁን በኋላ በኔ ክላስ እንዳትገባ" ብለው ጀርባቸውን ሰጡኝ። የበለጠ ተናደድኩ። ስዞር ወጣቱ እያየኝ እየሳቀ ነው። 😮 ​"ችግርህ ምንድን ነው?" አልኩት ከአጠገቡ እንደደረስኩ። ​"‘ብስኩት ስለጋበዝኩህ ነው የናቅከኝ’ አለህ?!" አለኝ ምንም ሳይገርመው። ​"ምናገባህ! ለምን የራስህን ኑሮ አትኖርም" ​"እየኖርኩ ነው... ይልቅ አንድ ነገር ልንገርህ!" ​"ልንገረኝ የፈለግከው ነገር እንዳለ ታስታውቃለህ... እኔ ግን መስማት አልፈልግም!" ​"ታውቃለህ? ከውስጥ ቱታ ሳትለብስ የመጣኸው አንተ ብቻ እንዳልሆንክ? ሌሎቹ በኔ ክላስ እንዳትገቡ አልተባሉም። አንተን ግን ስለሚያደንቁህ እንደሌላው ተማሪ የመሳሳት ፈቃድ የለህም።" ​"መስማት አልፈልግም እያልኩህ ለምንድን ነው የምታወራኝ?" ​"መስማት ካልፈለግክ ለምን አትሄድም ታዲያ?" ​ዝም አልኩ። ዝም ማለቴን አይቶ ቀጠለ። "ይሄ ነገር ወደፊትም ይቀጥላል። ወግ ግጥም የምትለውን ነገር ትተህ ኑሮህን ብትኖር ይሻልሃል" ⏳ ​ከንዴቴ እና ከግራ መጋባቴ ላይ ሳቄ ተጨምሮ ያወዛውዘኝ ጀመር። "ማን ነኝ አልክ አንተ" አልኩት ቢጨንቀኝ! ​"ከአስር አመት በፊት እዚህ እማር ነበር። እንዳንተ ወግም ግጥምም ለማቅረብ አይደክመኝም። የሰው ሙገሳ እና አክብሮት ሱሴ ነው።" ቁጭ አልኩ። የማውቀው ስሜት ስለሆነ ቆሜ መስማት አቃተኝ። 😔 ​"ህይወት ሲጀመር ግን ቀስ እያልኩ ወደኋላ ቀረሁ። ድሮ ያለፍኩት ቁጥቋጦ ቀስ እያለ ሲያልፈኝ ታወቀኝ። ወደኋላ እየሄድኩ እንደሆነ ያወቅኩት የሚራመደው ብቻ ሳይሆን የቆመውም ሲያልፈኝ ነው።" ​"ከኔ ህይወት ጋር ምን ያገናኛዋል?" የአልፈራሁ ለመምሰል ሞከርኩ። የግንባሬ ጫፍ ብቅ ያለውን ላብ በዩኒፎርሜ ጠረግኩ። ​"በአንተ ውስጥ ልጅነቴን ስላየሁ ነው። ከጠቀመህ የምልህን ስማኝ! እንደኔ ለፍተህ ለፍተህ ወደጀመርክበት መመለስ ካልፈለግክ ከዚህ ልክፍት ራቅ። አትቅጨምጭም። 'this is not a great place for someone who likes books'" 📚 ​"ምንድን ነው ችግሩ! ልሞክረውና ከሆነ ይሆናል። ካልሆነ ይቀራል... ሌላ ነገር እሰራለሁ" ​"ከዚህ እድሜህ ጀምሮ ራስህን ያዘጋጀኸው ለዚህ ነው። እንዴት ነው ድንገት ተነስተህ ሌሎቹን የምትመስለው። በጊዜ ሲስተማቸው ውስጥ ገብተህ ካልተገራህ ማንም ሊጋልብህ አይችልም። ካልተጋለብክ ሳር አታገኝም። እንዲህ ነው ይሄ አለም የሚሰራው!" ​ሀይለ ቃል ልናገረው ብዬ እንደከፋው ስለገባኝ አሳዘነኝና ተውኩት። "ያው ሁሉም ሰው አንድ አይነት ነው ማለት ይከብዳል! እኔ ፈጣን ተማሪ ነኝ! ይሄን ለቅቄ ሌላ ነገር መልመድ እችላለሁ። አንተም ቢሆን ቁዘማውን ትተህ አማራጭ ብትፈልግ ጥሩ ነው" ​"ነፋስ የነካው ፕላስተር ነው የምትሆነው。ይዘህ አትይዝም... ለቀህ አትለቅም። በጊዜ አካሄድህን ካላስተካከልክ ወደኋላ መመለሻ መንገድ የለም" 💨 ​"እውነቱን ለመናገር በህይወቴ እንዳንተ ጨለምተኛ ሰው አይቼ የማውቅ አይመስለኝም!" ​"ገና ህይወትህ ስላልተጀመረ ነው" አለና ከተቀመጠበት ተነሳ። "ከፈለግከኝ ታች ሰፈር ነው የምኖረው መጥተህ ብትፈልገኝ ማወቅ የምትፈልገውን ሁሉ እነግርሃለሁ" ብሎኝ ሄደ። ​እንደማልሄድ እርግጠኛ ነበርኩ። በሶስተኛው ቀን ግን ራሴን ሰፈራቸው ውስጥ ገብቼ ስፈልገው አገኘሁት። የጠበቀኝ ድንኳኑ ነበር። ለሰው እንደዛ አዝኞ ማወቄ ትዝ አይለኝም። ባላገኘሁት አልኩ! 🏕️ ​መቃብሩ ላይ አበባ ላስቀምጥ ሶስት ዘለላ ቀንጥሼ ወሰድኩለት። አዲስ የተሰራ መቃብር ውስጥ በፀጥታ ተኝቷል። እንደዚህ አርፎ የሚያውቅ አይመስልም። አበባውን አስቀመጥኩ። መቃብሩ ላይ የተጻፈው ጽሑፍ "ሞተ ሳይሆን ተሸርፎ አለቀ በሉ" ይላል። 🪦 ​እንባዬን ላቆመው አልቻልኩም። "ምን አይነት ዥልጥ ነው?"..."ምናለ እንዲህ ጨለምተኛ ባይሆን?"..."ምናለ እንዲህ ድራማቲክ ባይሆን?"..."ወይ ምናለ እኔ ሳላወቀው ቀርቼ ቢሆን".... ስንቱን አሰብኩት። በእንባ እየታጠብኩ ቀጥ ብዬ መቃብሩ ላይ ያለውን ፎቶ ሳየው ለመጀመሪያ ጊዜ ፂም አልባ ፊቱን አየሁት። እሱም አፈጠጠብኝ። በዚህ ደረጃ እኔን መምሰሉ አስደነገጠኝና ወደኋላ ማፈግፈግ ጀመርኩ። መቃብሩ ላይ ያለው ስምም የራሴው ነው። ልቤ የጎን አጥንቴን በርቅሳ ለመውጣት ያህል እየተነሳች ትፈርጣለች። ሁለመናዬን መሸከም አቃተኝ። ተርበተበትኩ። ወደኋላ ሳፈገፍግ ድንጋይ ጠለፈኝ እና የተቋጠረ ውሃ ላይ ወደቅኩ። 😭 ​ከእንቅልፌ ስነቃ ጓደኞቼ በጆክ ውሃ ይዘው ፊቴ ላይ እያርከፈከፉብኝ ነበር። ሁሉም ደንግጠዋል። ለካስ የበላሁት ራት ላይ የእንቅልፍ መድኃኒት አድርገውበት ኖሮ ሳላስበው ተኝቼ ኖሯል። ይሄ ሁሉ ቅዠት ነበር። 🛌 ​"አንተ ማነው በህልምህ እየመጣ እንደዚህ የሚያስቃዥህ?" አሉኝ ሁሉም በጭንቀት! ​"እኔ እንጃ! ሰሞኑን የድሮው እኔና የወደፊቱ እኔ አዕምሮዬ ውስጥ እየተገናኙ የሆነ ነገር እያሴሩብኝ ነው..." አልኩ ቁና ቁና እየተነፈስኩ。 ​ካልኩት በኋላ ፊታቸው ላይ የነበረውን ድንጋጤ አይቼ ነው የተናገርኩትን ነገር ያስተዋልኩት። በላብ እና በውሃ የተጠመቀ ሰውነቴን በፎጣ እየጠረግኩ ፈገግ ካልኩ በኋላ "አምናችሁኝ እንዳይሆን... ኧረ ስቀልድ ነው!" አልኩ። እየቀለድኩ መሆኔን ማመን ቀለላቸው መሰለኝ ሁሉም ሳቁልኝ። 😂 ​እኔ ግን የተፈጠረው ምን እንደሆነ ለማጣራት ተደላድዬ ተቀመጥኩ። "ብኖር ያን ፂማም ልጅ ብሞት ተሸናፊ.. መሆን ነው የኔ ዕጣ፤ ሀዘኔ ቅጣ..... ከአዕምሮዬ አልወጣ!" እያልኩ ለራሴ ሙሾ አወረድኩ። ​ተረኛው ተፍ ተፍ ብሎ የሰራውን ቁርስ አቀረበ። "አልበላም ሀዘን ላይ ነኝ" ልላቸው ነበር! "ማን ሞተ?" ብለው ቢጠይቁኝ ማን እላለሁ ብዬ እየመረረኝ በላሁት። 🍽️😊 ​@ሚካኤል አዝማራው

  • የ Paulo Coelho ድንቅ የህይወት ታሪክ ​ሶስት ጊዜ ወደ አእምሮ ህክምና ሆስፒታል ተሰዶ የነበረው ያ ሰው በኋላ ላይ በዓለም ላይ ካሉ ከፍተኛ ሽያጭ ካላቸው ደራሲያን አንዱ ለመሆን በቅቷል። የእሱ በጣም ተወዳጅ መጽሐፍ ከ150 ሚሊዮን በላይ ኮፒዎች የተሸጠ ሲሆን ከ80 በላይ ወደሚሆኑ ቋንቋዎች ተተርጉሟል። ​ከጠረጴዛ ጋር አስረው የኤሌክትሪክ ለቀቁበት። እሱ ግን ብቸኛ ወንጀሉ ከህግ ባለሙያነት ይልቅ ደራሲ መሆን የፈለገ ታዳጊ ወጣት መሆኑ ብቻ ነበር። የተደናገጡት ወላጆቹ የእሱ የፈጠራ አስተሳሰብ የእብደት ምልክት መስሏቸው ሶስት ጊዜ ወደ አእምሮ ህክምና ተቋም ወሰዱት። ​ነገር ግን ከዓመታት በኋላ ያው ሰው ተቀምጦ በአስራ አራት ቀናት ውስጥ ብቻ ዓለምን የሚቀይር መጽሐፍ ጻፈ። ​ስሙ Paulo Cielho ይባላል የእሱ ታሪክ ደግሞ በጣም ጨካኝ ተቺዎቻችን ስለወደፊት ህይወታችን ሙሉ በሙሉ እንደሚሳሳቱ ያረጋግጣል። ​በ1988 ፓውሎ በበረሃ ውስጥ ህልሙን ስለሚያሳድድ እረኛ ብላቴና የሚተርክ ቀለል ያለ ድንቅ ታሪክ ላይ ነፍሱን ዘራበት። መጽሐፉንም The Alchemist አለው። መጽሐፉ ልዩ መሆኑን ቢያውቅም የህትመት ዓለም ግን ምንም ደንታ አልነበረውም። ​መጽሐፉን ለመጀመሪያ ጊዜ ያተመው የህትመት ድርጅት መጽሐፉ በየመደርደሪያው ላይ አቧራ ሲለቅም ተመለከተ። ሽያጩ በጣም ደካማ በመሆኑ ምክንያት በይፋ እጃቸውን በማጠብ ከራሳቸው ላይ አሳልፈው መብቱን መልሰው ሰጡት። ​መጽሐፉ ሙሉ በሙሉ እንደከሸፈ ነገሩት። ሌላ ማንኛውም ሰው ቢሆን ኖሮ በዚያው ተስፋ ይቆርጥ ነበር። ከሁሉም በላይ ደግሞ ባለሙያዎቹ ተናግረዋልና። ነገር ግን ፓውሎ እውነተኛውን የኤሌክትሪክ ንዝረት ህክምና ተቋቁሞ ያለፈ ሰው በመሆኑ የውድቅት ደብዳቤ እንዲያቆመው አልፈቀደም። ​"አንድን ነገር ከልብህ ስትፈልገው ዓለም ተፈጥሮ ሁሉ ያንን ነገር እንድታገኝ ያሴራል" በሚለው የመጽሐፉ ዋና መልዕክት ላይ ጽኑ እምነት ነበረው። ​ተስፋ ለመቁረጥ ፈቃደኛ አልነበረም። ፓውሎ ሌላ ዕድል የሚሰጠው ሁለተኛ አሳታሚ አገኘ ከዚያም አንድ አስደናቂ ነገር ተከሰተ። ስኬቱ ግን በትልቅ እና ውድ በሆነ የገበያ ማስታወቂያ የመጣ አልነበረም። መጽሐፉ ቀስ በቀስ ልክ እንደ ሹክሹክታ እያደገ ሄደ። ​አንድ ሰው አነበበው በልቡ ውስጥ ለውጥ ተሰማው ከዚያም ለጓደኛው አስተላለፈው። ያ ጓደኛ ደግሞ ለሌላው ሰጠው። ​ብዙም ሳይቆይ ያ ሹክሹክታ ወደ ነጎድጓድ ተቀየረ። ​መጽሐፉ ከብራዚል ጎዳናዎች ተነስቶ ወደ መላው ዓለም ተጓዘ። ዛሬ ዘ አልኬሚስት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በጣም ስኬታማ ከሆኑ መጽሐፍት አንዱ ነው። ከ150 ሚሊዮን በላይ ዕትሞች የተሸጠ ሲሆን ከ80 በላይ ወደሚሆኑ ቋንቋዎች ተተርጉሟል። ​አሁን ላይ በጣም ተደማጭነት ካላቸው የዓለም መሪዎች ጠረጴዛ ላይ እስከ ምስኪን ተማሪዎች ቦርሳ ውስጥ ይገኛል። ​ፓውሎ ወላጆቹን ሰምቶ ቢሆን ኖሮ ህይወቱን ደስተኛ ያልሆነ የህግ ባለሙያ ሆኖ ያሳልፍ ነበር። የመጀመሪያውን አሳታሚ ሰምቶ ቢሆን ኖሮ ደግሞ ይህ ድንቅ ስራው ለዘላለም ጠፍቶ ይቀራል ነበር። እሱ ግን በምትኩ የውስጥ ድምፁን ማመንን መረጠ። ​በህይወት ውስጥ ብቸኛው እውነተኛ ውድቀት ጉዞውን ለመጀመር ፈቃደኛ አለመሆን ወይም አንድ ሰው አይሆንም ባለህ ቅጽበት ተስፋ መቁረጥ መሆኑን ለዓለም አሳይቷል።

  • ዲቃላ ብላኝ ነው የልጅነት ቁስሌን የነካችው ፤ የአባቴን ብልግና ነው እናቴ እና እኔ ላይ የዶለችው ፤ እንዴት ሰው ቁስሉን ይሰደባል ብዬ ከተውኳት በኋላ... ሰው ማንነቱ የሚገለጥበት ሲናደድ ነው ፤ ብስለቱ የሚለካው ድንበሬ ተረገጠብኝ ፣ ተጣሰብኝ ብሎ በሚወስደው እርምጃ ነው ። ስትናደድ ያሳየችው ፣ የወነጨፈችው ስድብ አቅሟ ነው ብዬ ከተውኳት በኋላ... ሊያስማሙን የዳከሩትን ሽማግሌዎች አሻፈረኝ አልኳቸው ፣ ቆረጥኩኝ ደግሞም ቆራጥ ነኝ። ባለጌ ምን ያደርግልኛል ካልኩ ፣ ከተዘባነንኩ ብዙ ጊዜ ከተቆጠረ በኋላ... ታናሽ ወንድሟን አገኘሁት ፤ ተጠመጠመብኝ ፤ ከእህቱ ጋ ይደረብ ይሆናል ብዬ ነበር ፤ እሱ ግን እንደ ድሮ ነው። ጥምጥም አለብኝ ፤ ንፁህነቱን ቀናሁበት። ካልቸኮልክ እንጫወት ብዬ ቅርባችን ወዳ'ለ ሬስቶራንት ወሰድኩት ። ተጨዋወትን ፤ በጨዋታችን መሃል ጄሩ ደህና ናት ስለው "ደህና ናት " ተጣልታችኋል አይደል?" አለኝ አይ አልተጣላንም ስራ በዝቶብኝ ስለማንገናኝ እንጂ ስለው ። "አይ ቢኒ" አለኝ። "በተጣላቹ በነጋታው ነው ሁላችንም ያወቅነው ። ያንተ ስም እኮ እኛ ቤት ጄሩ በየምክንያቱ ፣ በየቦታው ነው የምታስገባው ፤ ጄሩ እኮ ልታጣጥልህ ጀምራ አሞግሳህ ነው ጨዋታዋን የምትዘጋው። እናቴ ጤናዋ ሁላ ታውኮ ነበር ፤ የእናቴ ህልም እና ፀሎቷ ላይ ሳይቀር ነበርክ ፤ ጄሩ የማትነግራት ነገር አልነበረም። ጓደኞቿ እቤት ሲመጡ ያንተ ጉዳይ አገራዊ ጉዳይ ይሆናል ። ቤታችን ስንት ሳምንት ድብርት እንደተጫነው አልገባህም ፤ አንተ ፍቅረኛህን ነው የተውክ የመሰለህ ፤ ከጄሪ ጋ በሁላችንም ጭንቅላት ተጋብታቹ ነበር ። መተውህ ብቻ አልነበረም የጎዳት ጥፋተኛ እንደሆነች አሳምነሃት ነበር የተውካት ፤ መተውህን ያገዘፈው ቤቷ ፣ ስራ ቦታዋ ፣ ወዳጆቿ ጋ ስምህን ስታነሳ ስለምትውል ማጣፍያው ተምታታባት ። ያላለቀ ነገር ሰው ልቦና ውስጥ ከገነባን በኋላ ሲመሰቃቀል መሰናዳቱ ከባድ ነው ፤ ትግሉ ከውጪም ፣ ከውስጥም ስለሚሆን" አለኝ ። ታላቅነት መለኪያ የምድር ቆይታ እንዳልሆነ መሰከረብኝ ፤ በእኔ መታበይ ምክንያት ስንት ሰው ድብርት ውስጥ ናጥኩ ። ፍቅር አይታገስም ? ምን አለ ፍቅሯ ስጋ ለብሶ ሲማፀነኝ ብላላ ኖሮ ! ፍቅር እና ይቅርባይነት መነጣጠል ይቻላቸዋል? ይቅር በይኝ እስኪ? Adahanom mitiku