tgindex
ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት

ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት

Статистика

በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። የቴሌግራም ቻናል:-  @Finote_Wongel የቴሌግራም ግሩፕ:- @FinoteWongel27 የቲክቶክ ገፅ:- https://www.tiktok.com/@finotewongel27 Youtube:- https://www.youtube.com/@Finote_Wongel ©ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
669
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
259
22 постов
Вовлечённость
38,7%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
151
1/48двое суток
173
1/72трое суток
186

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ❤️ ነሐሴ (7) ቀን ❤️ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን!                 ✝️ ✝️ ✝️ 📖 የእመቤታችን የፅንሰት አጭር ታሪክ ጻድቁ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና በ እግዚአብሔር ፊት በቅንነትና በደግነት የሚኖሩ እውነተኛ አማኞች ነበሩ። ነገር ግን በጋብቻ ዘመናቸው ልጅ ባለመውለዳቸው ምክንያት እጅግ ያዝኑ ነበር። በወቅቱ የነበሩ የእስራኤል ልጆችም “ልጅ ያልወለደ ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው” እያሉ ያቃልሏቸውና ይነቅፏቸው ነበር። ቅዱሳኑ ግን በሰው ነቀፌታ ተስፋ ሳይቆርጡ፣ “የአባቶቻችን የእስራኤል አምላክ ሆይ! ለአይናችን ማረፊያ፣ ለልባችን ተስፋ የሚሆን ፍሬ ስጠን” እያሉ ዘወትር በጾምና በጸሎት ወደ አምላክ ይለምኑ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ቅድስት ሐና በቤቷ አትክልት ስፍራ ሳለች፣ አንዲት ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት ተመለከተች። በዚያን ጊዜ ልቧ ተነክቶ፦ “አቤቱ ጌታዬ! ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ፣ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ?” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች። ከዚህ በኋላ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ወደ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ዘንድ በመሄድ ታላቅ ስዕለት ተሳሉ፦ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን እንዲያገለግል፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ውኃ ቀድታ፣ መሶበ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ እናደርጋለን” አሉ፤ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስም ጸሎታቸውን አሳርጎ ባረካቸው። ሐምሌ 30 ቀን ቅዱሳኑ አስደናቂ ራእይ አዩ፦ ጻድቁ ኢያቄም፦ “ሰባት ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው፣ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” አለ። ቅድስት ሐና፦ “እኔም ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ፣ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ” አለችው። ይህንን ራእይ ካዩ በኋላ “ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን” ብለው ዕለቱን አልጋና ምንጣፍ ለይተው ለሰባት ቀን ያህል በጸሎት ተለይተው ሰነበቱ። በሰባተኛው ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለጻድቁ ኢያቄም በተራራ ላይ ሲጸልይ በተገለጸለት ጊዜ፦ “ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች፤ ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን፣ ለብዙዎች የሕይወት ብርሃንና ድኅነት የምትሆን ሴት ልጅ ትወልድልሃለች” ሲል አበሰረው። መልአኩ ለቅድስት ሐናም ተገልጦ የጌታን ፈቃድ ነገራት። በብስራተ መልአክና በፈቃደ እግዚአብሔር፣ እሁድ ዕለት በነሐሴ 7 ቀን ከሰው ሁሉ የበለጠች፣ ከመላእክትም የከበረች፣ የዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነችው አምላክን የምትወልደው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማኅፀነ ሐና ተፀነሰች።                      ✝️ ✝️ ✝️ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና በረከት፣ የቅዱስ ኢያቄምና የቅድስት ሐና ጸሎት አይለየን።🙏 ⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨ የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wonge

  • አሁንም የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆችና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማኅበሮች ሆይ ይኽቺን የተባረከችና የተመረጠች ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናመስግናቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግልን የተባረከችዋን ፍሬ ያፈራችበትን ንጽሕት የምትኾን የሩካቤያቸው ዕለት እንደምን ያለች ዕለት ናት ከይሁዳ ወገን ለኾነችው ንጽሕት ርግብ መፀነስ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ የጾታዊ ተዋሕዷቸው ቀን ይኽቺ እንዴት ያለች የተመረጠች ቀን ናት፤ ለንጉሥ ማደሪያ አዳራሽ መመሥረት የተደረገባት (የኾነባት) የደስታ ቀን እንዴት ያላት ቀን ናት። (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ አርጋኖን ዘረቡዕ)

  • без подписи

  • без подписи

  • "እግዚአብሔር በተነሣ ጊዜ ምን አደርጋለሁ ? በጎበኘኝ ጊዜ ምን እመልስለታለሁ ?"   ኢዮብ 31÷14 ⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨ የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wonge

  • የምስራች የምስራች የምስራች ዜና ዘማሪት ሃና ኃይለ መስቀል ለቅኖች ምስጋና ይገባል ከሁሉ አስቀድሞ ሁሉን ላደረገ ሲሰጥ የማይሰስት ሰጥቶ የማይነጥፍበት ሁሉ በርሱ ለእርሱ የሆነለት አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ስላደረገልን መልካም ነገር ሁሉ ስሙ ለዘለአለሙ የተመሰገነና ከፍ ከፍ  ያለ ይሁንልን!!! ከሐምሌ 19/2018 ዓ/ም ጀምሮ  በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ትምህርት ልዩ ልዩ ሚዲያዎችና በቅን እህት በወንድሞቻችን የግል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በቅዱስ ገብርኤል አመታዊ የንግስ ክብረ በዓልና በተለያዩ በአሰላ ከተማ አድባራት አውደምህረቶች ላይ በዚህ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት የሰንበት ትምህርት ቤታችን አገልጋይ የሆነችው እህታችን ዘማሪት ሰርክአዲስ( ሃና )ኃይለ መስቀል በመተንፈሻ አካሏ በደረሰባት የጤና እክል ምክንያት ጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባደረገችው ምርመራ የልብ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለባት ስለተነገራት ህክምናውን በታዝማ ሆስፒታል ለመፈጸም ደግሞ 1,300,000.00 (አንድ ሚሊየን ሶስት መቶ ሺህ ብር) መጠየቋን ጠቅሰን መላ ኢትዮጵያውያን ለእህታችን ማሳከሚያ የሚሆን እጅ እንድትዘረጉልን ጠይቀን እናንተም ደግ ኢትዮጵያዊያን ከጉለታችሁም ላይ ቢሆን የምትችሉትን ሁሉ እንዳደረጋችሁልን ይታወቃል ለዚህም ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን መድኃኔዓለም ከክፉ ነገር ሁሉ እንዲጠብቃችሁ ጸሎታችን ነው። ስለሆነም እግዚአብሔር አምላካችን የእናንተን ጸሎት ተቀብሎ እስካሁን በሰበሰብነው ብር ላይ ሞልቶ የሚያሳክም ወዳጅ ዘመድ ስለተገኘ አሁን በዚህ ሳምንት ውስጥ ወደ ህክምና ለመሄድ ዝግጅቷን ስለጨረሰች ሁላችሁም ህክምናው በተሰካ ሁኔታ ተሰርቶላት በሙሉ ጤናዋ ጠብቆ ፍጻሜዋን እንዲያሳምርላት በጸሎት እንድታስቧት ስንል በአክብሮት እናሳስባለን። የአሰላ ደ/መ/ መ/ዓ/ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ትምህርት ቤት ⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨ የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wonge

  • без подписи

  • без подписи

  • ⛪️ሀሁ ብዬ⛪️ ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ                                            በአቦጊዳ አፌን የፈታውብሽ በመልእክት መንፈሴ ተደሰተ በዳዊቱ ብዙ ነው በረከቱ (2) ተዋህዶ ኧኸ ሀይማኖቴ የእውቀት ምንጭ ኧኸ መሰረቴ አለኝ ትዝታ ከዛፉ ስር 2 የኛ የኔታ ዱላ በትር 2 ሀሁ ብዬ ስጮህ         ሀ ድምፄን እያሰማው      ሁ አንዷን ቃል ስገድፋት    ሂ የኔታን አስቆጣው        ሃ ሀ ማለት እግዚህ ነው   ሄ እያሉ ሲቀኙ               ህ የኔታን አንደበት           ሆ ማር ይንጠፍጠፍበት   ሆ ⛪️አዝ አቦጊዳ ብዬ መልእክተን ሳልወጣ 2 የኔታ ደከሙ እንቅልፋቸው መጣ 2 ፊደል ገበታዬን            ሀ ግዕዝ ጥያት ከመሬት            ሁ ካዕብ አቧራዬን ማቡነን          ሂ  ሣልስ ያዝኩኝ መላፋት           ሃ ራብዕ ሲነቁ የኔታ                  ሄ ኃምስ ልምጯን አነሱ             ሆ ሳብዕ ቁጣ ቃል አሰሙ          ሀ ግዕዝ ⛪️አዝ ተማሪ እና ውሻ ሁል ጊዜ አይስማሙ 2 እስከ እድሜ ልካቸው አሉ እንደ ተዳሙ 2 አቆፋዳ አንግቦ            ሀ ገመሎውን ለብሶ         ሁ በእንተ ስሟ ሲል          ሂ ድምፁን አለስልሶ        ሃ አንዲት እፍኝ ጥሬ        ሄ የቁራሽ እንጀራ           ህ ውሻ ሲያባርረው         ሆ አይ ያለው መከራ        ሆ ⛪️አዝ አለኝ ትዝታ ቅኔ ቤት 2 በእንተ ስሟ ለማርያም ማለት 2 የዜማው መለኪያ         ሀ ጭረት ምልክቱ            ሁ እዝልና ግዕዙ               ሂ ቅናቱ ድፋቱ                 ሃ ጣቢዘር ጥሬዘር          ሄ ደግሞም ቅኔ ቤት       ህ አገባብ ሚስጥሩ         ሆ ሰባት ስምንት ቤት       ሆ ⛪️አዝ አለኝ ትዝታ ከመቅደሱ 2 ሌሊቱን ሙሉ ማወደሱ 2 መፃሃፍን ዘርግቶ         ሀ ከጉባኤ ውሎ             ሁ መሪ ዜማ አጥንቶ        ሂ ስምአኒ ብሎ              ሃ ተፈስሂ እያልን             ሄ እሱን ስደረድር           ህ ሳዜመው ይነጋል        ሆ ቅኔ ስደረድር             ሆ ⛪️አዝ አለኝ ትዝታ ከጎጆዬ 2 ተሰቅላ አቆፋዳዬ 2 ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ በአቦጊዳ አፌን የፈታውብሽ በመልእክተ መንፈሴ ተደሰተ በዳዊቱ ብዙ ነው በረከቱ ⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️ ⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨ የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wonge

  • "ከእንቅልፌ ስነቃ ፈጥኜ ወደ አንተ አንጋጥጣለሁ አቤቱ የሰው ሁሉ ወዳጅ የሆንክ ጌታ በአንተ ፍቅርና ደግነት ወደ አንተ ለመጸለይና መንፈሳዊን ሥራ ለመሥራት እጥራለሁ።በሁሉም ጊዜ በማንኛውም ነገር እርዳኝ ከማንኛውም ከዓለም ክፋ ሥራና ከዲያብሎስ ጥቃት ሁሉ አውጣኝ ፤ወደ ዘላለማዊዉ መንግሥትህ ምራኝ ።አቤቱ ፈጣሪዬ አንተ የማንኛውም መልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ነህና ፤ተስፋዬ ሁሉ በአንተ ላይ ነው።አቤቱ ለአንተ ምስጋና አቀርባለሁ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።"            ጸሎተ አባ መቃርዮስ

  • ኑ አብረን እንጓዝ! ወደ ታላቁ ገዳም ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም

  • 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 📚#በእንተ_ፍልሰታ_ለማርያም#📚 #ቅዳሴ_ማርያም #አባ_ሕርያቆስ_ስለ_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም የድንግልን ክብሯን ልዕልናዋን ገናንነቷን እናገራለሁ። ሦስት ጐሥዐ ተናግሮ ነበርና ለዚያ አርእስት ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዐብየኪ ብሎ የሚያመጣ ነውና ለዚያ አርእስት ነው፤ ይህም አይደለም አርእስት ተቀዳደመ ለመጀመሪያው አርእስት አርቆ ሰጥቶ ለመጨረሻው አርእስት አቅርቦ አይሰጥም ብሎ መጽአ ኀቤኪ ቃል እንዘ ኢይትፈለጥ ብሎ የሚያመጣ ነውና፤ ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ፤ ወአየድዕ ውዳሴሃ፤ ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ ብሎ ሦስት ጊዜ መላልሶ ተናገረ፤ ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ ኦድንግል ምልዕተ ውዳሴ፤ ኦ ድንግል አኮ ዘተአምሪ ርስሐተ የሚል ነውና፡፡ አንድም አባቷ ዳዊት ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል፤ መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፤ እስመ ኀረያ እግዚአብሔር ለጽዮን ብሎ ሦስት ጊዜ መላልሶ አመስግኗታል። 🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜ ⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨ የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wongel

  • እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ "የምግባራት ኹሉ እናታቸው ጾም ደረሰች፤ ጸሎትና ምጽዋትም ልጆችዋ ናቸው፤ ሦስቱም ሀገራቸው አንድ ነው። እናት እና አባታቸውም አንድ ናቸው።"          🌹የርቱዓ ሃይማኖት ደራሲ 🌹

  • ጾመ ፍልሰታ በነገረ ማርያም መጽሐፍ ተጽፎ እንደምናገኘው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥር 21 ቀን  ከዚህ ዓለም ድካም ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ሊቀብሯት ወደ ጌቴሴማኒ ሥጋዋን ይዘዋት ሲሔዱ አይሁድ “እንደ ልጇ ተነሣች፤ ዐረገች እያሉ እንዳያውኩን በእሳት እናቃጥላት” ብለው በዓመጽ ተነሡ፡፡ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊም አጎበሩን ይዞ ሥጋዋን ሊያወርድ ሲል የእግዚአብሔር መልአክ ሁለት እጆቹን ቀጥቶታል፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ጨምሮ እመቤታችንን በደመና ነጥቆ ወደ ገነት ወስዶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጣት፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም እመቤታችን ያለችበት ቦታ እንዲገለጥላቸው ባረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ጀመሩ እመቤታችን ካረፈችበት ቀን ከጥር ወር ጀምሮ እስከ ነሐሴ ድረስ ጥያቄያቸውንና ጸሎታቸውን ባያቋርጡም ከሰው ተለይተው ሱባዔ ገብተው ጾም ጸሎት የጀመሩት ግን ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ነው፡፡ ሁለት ሱባዔ ካደረሱ በኋላም የነገሩትን የማይረሳ፣ የለመኑትን የማይነሳ እግዚአብሔር አምላካችን ጸሎታቸውን ሰምቶ የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው በክብር ገንዘው በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል፡፡ በሦስተኛው ቀንም እንደ ልጇ እንደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይታ ተነሥታለች “ከመ ትንሣኤ ወልዳ፤ እንደ ልጇ ትንሣኤ” ያሰኘውም ይህ ታሪክ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ሲሰብክ ቆይቶ ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ እመቤታችን ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ወደ ሰማይ ስታርግ አገኛት፡፡ በዚህ ጊዜ “ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ፤ ዛሬ ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁን?” ብሎ ትንሣኤዋን ባለማየቱ ኀዘን ስለ ተሰማው ከደመናው ይወድቅ ዘንድ ወደደ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” እንዲል፡፡ እመቤታችንም “አይዞህ አትዘን፤ ባልንጀሮችህ ሐዋርያት ያላዩትን ትንሣኤዬን አንተ አይተሃል” ብላ ከሙታን ተለይታ መነሣቷንና ማረጓን እንዲነግራቸው አዝዛ የያዘቸውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው፡፡ እርሱም ትዕዛዟን ተቀብሎ በክብር ከተሰናበታት በኋላ ወደ ሐዋርያት ሔዶ እንዳልሰማ እንዳላየ መስሎ “የእመቤታችን ነገር እንደምን ኾነ?” አላቸው፡፡ እነርሱም “አግኝተን ቀበርናት” ሲሉት “ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴት ይኾናል?” አላቸው፡፡  በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ከዚህ በፊት የክርስቶስን ትንሣኤ መጠራጠሩን ጠቅሶ እየገሠጸ ስለ እመቤታችን መቀበር እነርሱ የሚነግሩትን ኹሉ መቀበል እንደሚገባው ለቅዱስ ቶማስ አስረዳው፡፡ ቅዱስ ቶማስም የያዘውን ያውቃልና ጸጥ ብሎ ሲሰማው ቆየ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ተቈጥቶ የእመቤታችንን ክቡር ሥጋ ለቅዱስ ቶማስ ለማሳየት ሔዶ መቃብሯን ቢከፍት የእመቤታችንን ሥጋ ሊያገኘው አልቻለም በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ደንግጦ ቆመ ቅዱስ ቶማስም “አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ስታርግ አግኝቻታለሁ” ብሎ የሰጠችውን ሰበን ለሐዋርያት ሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም በእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት እየተደሰቱ ሰበኑን ለበረከት ተካፍለውታል፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስተምሩን በቅዳሴ ጊዜ ሠራዒ ዲያቆኑ በሚይዘው መስቀል ላይ የሚታሠረው መቀነት መሰል ልብስ፤ እንደዚሁም አባቶች ካህናት በመስቀላቸው ላይ የሚያደርጉት ቀጭን ልብስና በራሳቸው የሚጠመጥሙት ነጭ ሻሽ የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው፡፡ በዓመቱ ቅዱሳን ሐዋርያት “ቶማስ የእመቤታችን ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አይቶ እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን?” ብለው ከየሀገረ ስብከታቸው ተሰባስበው ጌታችን ሥጋዋን እንዲሰጣቸው በጠየቁበት በዚሁ ወቅት ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምረው ሱባዔ ቢይዙ ጌታችን ልመናቸውን ተቀብሎ ነሐሴ 16 ቀን እመቤታችንን መንበር፤ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፤ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ  አቍርቧቸዋል፡፡ እነርሱም እመቤታችንን በዓይናቸው ከማየት ባሻገር አብረው ሥጋውን ደሙን ተቀብለዋል /ትርጓሜ ውዳሴ ማርያም/፡፡ ይህንን ትምህርት መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከነሐሴ 1-16 ያለው ሁለት ሱባዔ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ኾኖ በምእመናን ዘንድ መጾም እንደሚገባው ሥርዓት ሠርተውልናል /ፍት.ነገ.አን.15/፡፡ ይህ ጾምም “ጾመ ማርያም (የማርያም ጾም)” ወይም “ጾመ ፍልሰታ ለማርያም (የማርያም የፍልሰቷ ጾም)” እየተባለ ይጠራል፡፡ ‹ፍልሰት› የሚለው ቃልም “ፈለሰ ሔደ፤ ተሰደደ” ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ትርጕሙም ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር መሔድን ያመለክታል፡፡ ‹ፍልሰታ ለማርያም› ሲልም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ካረፈች በኋላ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መወሰዷን የሚያስረዳ መልእክት አለው፡፡ በጾመ ፍልሰታ በቤተ ክርስቲያናችን በየቀኑ በማኅሌቱ፣ በሰዓታቱና በቅዳሴው በሚደርሰው ቃለ እግዚአብሔር ነገረ ማርያም ማለትም የእመቤታችን ከመጸነሷ ጀምሮ እስከ ዕርገቷ ድረስ ያለው ታሪኳ፣ ለአምላክ ማደሪያነት መመረጧ፣ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ክብሯ፣ ርኅርራኄዋ፣ ደግነቷ፣ አማላጅነቷ፣ ሰውን ወዳድነቷ በስፋት ይነገራል፡፡ እመቤታችንን ከሚያወድሱ ድርሳናት መካከልም በተለይ ምሥጢረ ሥላሴን፣ ምሥጢረ ሥጋዌንና ነገረ ድኅነትን ከነገረ ማርያም ጋር በማዛመድ የሚያትተው ቅዳሴ ማርያም፤ እንደዚሁም ነገረ ድኅነትን ከምሥጢረ ሥጋዌ (ከነገረ ክርስቶስ) እና ከነገረ ማርያም ጋር በማመሣጠር የሚያትተው ውዳሴ ማርያምም በስፋት ይጸለያል፤ ይቀደሳል፤ ይተረጐማል፡፡ በሰንበታት የሚዘመሩ መዝሙራት፤ በየዕለቱ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለተዋሕዶ በእግዚአብሔር መመረጧን፣ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን፣ ክብሯን፣ ቅድስናዋን፣ ንጽሕናዋን የሚያወሱ ናቸው፡፡ በጾመ ፍልሰታ ባሕታውያን ብቻ ሳይኾኑ ዓለማውያንም በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእመቤታችን አማላጅነት የሰይጣንን ፈተና ድል ለማድረግ እንዲቻላቸው ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በየገዳማቱና በየአብያተ ክርስቲያናቱ በዓት አዘጋጅተው፣ ሱባዔ ገብተው፣ ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው አስገዝተው ይጾማሉ፤ ይጸልያሉ  እንደዚሁም ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበላሉ፡፡ እኛም የእመቤታችንን ዕረፍትና ትንሣኤ በማሰብ ከልጇ ከወዳጇ የሚገኘውን ጸጋና በረከት ተስፋ በማድረግ የአባቶቻችንንና የእናቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በየዓመቱ ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን፤ የምንችል ደግሞ አስቀድሰን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንቀበላለን በተጨማሪም ይህ ጾም ለእመቤታችን ያለንን ፍቅርም የምንገልጽበት ወቅት ነው፡፡ በተለይ ኦርቶዶክሳውያን ሕጻናት በአብዛኛው ትምህርተ ወንጌል የሚማሩት፤ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የሚቀበሉት በዚህ በጾመ ፍልሰታ ነው በጾመ ፍልሰታ ሳምንታት በጌታችን፣ በእመቤታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት ስም በቤተ ክርስቲያን ተሰባስበን ቅዱሳት መጻሕፍትን ከመማር ባሻገር ብንጾም፣ ብንጸልይ፣ ብናስቀድስ፤ እንደዚሁም ሥጋውን ደሙን ብንቀበል በበረከት ላይ በረከትን፤ በጸጋ ላይ ጸጋን እናገኛለን በኋላም ሰማያዊውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ እንችላለን ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግልማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና በረከት አይለየን፡፡ በረከት እና ምሕረትን ከእግዚአብሔር ዘንድ የምንቀበልበት  ጾም ያድርግልን

  • “​በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሰራለሁ።’’          ✍️ዘፍጥረት 39፥9

  • "እግዚአብሔር ትቶኛል" አንዳንድ ሰዎች እጅግ የጠለቀ ኀዘንና መቆርቆር ውስጥ ሲገቡ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ረስቶኛል” ብለው ሲያማርሩ እሰማቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ነቢዩ እንዲህ ከሚሉ ሰዎች ጋር ክርክር አለው፡፡ “በውኑ ሴት ከማኅፀኗ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃኗን ትረሳ ትችላለችን?” በማለትም ይጠይቃቸዋል (ኢሳ.49፡14)፡፡ ይህም ማለት ሴቷ ከማኅፀኗ የተወለደው ልጇን ልትረሳ ዘንድ እንደማይቻላት እግዚአብሔርም ሰውን ይረሳ ዘንድ ባሕርይ አይደለም እያላቸው ነው፡፡ ነቢዩ ይህን ምሳሌና ማነጻጸርያ አንሥቶ ክርክር መግጠም የፈለገው እያንዳንዷ እናት ለልጇ ያላትን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቅ ነው፡፡ ኾኖም ይህን ያህል የምናንቆለጳጵሰው የእናት ፍቅር ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ለዚህም ነው “አዎን እርሷ ትረሳ ይኾናል፤ እኔ ግን አልረሳሽም… ይላል እግዚአብሔር” በማለት የሚቀጥለው፡፡ እንግዲህ የአምላካችን ፍቅር እንደምን የበዛ እንደ ኾነ ታስተውላላችሁን? እንግዲያውስ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “አባት ለልጆቹ እንዲያዝን እንዲራራ እንደዚህም ኹሉ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ለሚያመልኩት ይራራለቸዋል” ብሎ እንደተናገረ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ትቶኛል” የሚል ማንም አይገኝ (መዝ.102፡13)፡፡ ጆሮን የፈጠረ እርሱ ይሰማል፤ ዐይንን የፈጠረ እርሱ ያያል፡፡ እግዚአብሔር በእጁ መዳፍ የቀረጻቸው ልጆቹን አይረሳም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨ የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wongel

  • ''መድኃኔዓለም ሆይ እኛን ስለማዳን መከራን ለመቀበል ዘንበል ላለው ርዕስኽና ስዕርተ ርዕስኽ ሰላም እላለኹ ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ ከሰማየ ሰማያት ወርደኽ ከድንግል ማርያም ተወልደኽ በሥጋ ብእሲ በሕጻን አርአያ በተገለጽክበት ወራት እናታችን ሔዋንን ያሳተ ከይሲ ዲያቢሎስ ፈራ ደነገጠ በኃዘንና በልቅሶም ተዋጠ''             ''መልክአ መድኃኔዓለም'' ⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨ የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wongel

  • አስቸኳይ የእርዳታ ተማፅዕኖ😭😭 "እነሆ አገልጋይን ማዳን አገልግሎትን ማዳን ነው" 🙏🙏🙏አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ🙏🙏🙏 በመላው ዓለም የምትገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ ከታች በምስሉ የምትመለከቷት እህታችን ዘማሪት ሰርክ አዲስ ኃ/መስቀል (ዘማሪት ሐና) ትባላለች። በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴደራል ፍኖተ ወንጌል ስንበት ት/ቤት አገልጋይ ስትሆን ባጋጠማት ከፍተኛ የልብ ሕመም ምክንያት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክትትል ስታደርግ የቆየች ቢሆንም አሁን ላይ ህክምናው ከአቅም በላይ በመሆኑ ምክንያት ለቀዶ ጥገና ከ 1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ስለተጠየቅን ይህችን ዘማሪት እህታችንን በማሳከም ወደ አገልግሎት እንመልሳት ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ከታች ባሉት አካውንቶች የቻላቹህትን የአቅማቹን አግዙን🙏🙏 👉 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ(CBE) 1000783587487 👉አቢሲኒያ ባንክ(BOA)  13339538 👇👇👇👇👇 ለበለጠ መረጃ                              👉09 23 31 40 15                            👉09 12 62 12 20 ⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨ የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wongel

  • без подписи

  • " እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።"             ዕብራውያን 6:10 🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓 🎓🎓🎓 እንኳን ደስ አላችሁ🎓🎓🎓 🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓   በቀን 25/11/2018  ዓ.ም የሰንበት ት/ት ቤታችን እንቁ  አገልጋይ የሆኑት መዘ/ት ይዲዲያ ዮሐንስ እና መዘ/ት ጫልቱ ቶሎሳ በከተማችን ከሚገኘው dream land  ኮሌጅ ተመርቀዋል። ውድ እህቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ መልካም የስራና የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላችሁ  የፍኖተ ወንጌል ሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ ወንድም እሕቶቻቹ  እንመኝላቹሀለን። ⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨⚡️✨ የቴሌግራም ቻናል:-  T.me/Finote_Wongel