tgindex
የበገና መዝሙር እና ቁጥር መገኛ

የበገና መዝሙር እና ቁጥር መገኛ

Статистика

የበገና መዝሙሮችና ቁጥሮቹን እንዴት ላግኝ?🤔 በገና ምንድነው?🤔 አገልግሎቱስ?🤔 ከበገና ደርዳሪ ምን ይጠበቃል?🤔 መንፈሳዊ ጥቅሙስ ምንድነው ?🤔 ሁሉኑም በአንድ ያገኛሉ ይቀላቀሉ።

Последний пост
29 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
13 441
−27 за 4 дн.
Сутки
−5
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
5 088
21 постов
Вовлечённость
37,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 405
1/48двое суток
1 610
1/72трое суток
1 736

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 29 июл.1 7229

    "ዛሬ ሐምሌ 22 መልአከ ብርሃናት ቅዱስ ዑራኤል ቅዳሴ ቤቱ ተከብሮ ይውላል ብርሃኑን ያብራልን🙏 ✥ቅዱስ ዑራኤል ከሊቀ መላእክት አንዱ ነው። መላእክት በስማቸው ቅጥያ ኤል የሚል ቃል አለ ይኸውም እግዚአብሔር ማለት ነው።  "ዑር" ማለት ብርሃን፤ "ኤል" ማለትም እግዚአብሔር ማለት ነው።ዑራኤል ማለት የብርሀን ጌታ፣ የብርሀን አምላክ ማለት ነው። ✥ የሰማይን ሚስጥር ለሄኖክ እውቀትን የገለጸለት መልአክ ነው። የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። መ.ሄኖክ 28፥13 ✔️በብርሃናት ሁሉ ሊቀ ብርሃናት ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ዑራኤል ነው። ✔️ቅዱስ  ዑራኤል በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ  ስለሆነ እርሱም መባርቅትን ለጥጋብና ለበረከት እንዲሁም ነጎድጓድን ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መ.ሄኖክ ፮፥፪ ➕ ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን  ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። ✥ቅዱስ ዑራኤል ልቡናን የሚያበራ እውቀትን የሚገልጽ ርሑሩህ መልአክ ነው። ቅዱስ ዑራኤል ለነብዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋአ ልቡናን አጠጥቶት ሰማያዊ ሚስጥራትን ገልፆለታል። ነብዩ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸውን መጻሕፍት ደርሷል። በሰዓታቱም "ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኤልያስ ወኤልሳዕ ነቢያተ እስራኤል ወምስለ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋዓ ልቡና ዘአስተዮ ዑርኤል፡፡" "ነይ ወደ እኛ ድንግል ሆይ ከእስራኤል ነብያት ከኤልያስና ከኤልሳ እንዲሁም ዑራኤል ጽዋ ልቡናን ካጠጣው ከእዝራ ሱቱኤል ጋር።" ✥ሌላኛው ቅዱስ ዑራኤል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእጸ መስቀል ላይ በቀራንዮ በአምስቱ ቅንዋት (ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ሮዳስ) ሲቸነከር ይህ ብርሃናዊ መልአክ ነው ከጎኑ የክርስቶስን ደም በጽዋ ቀድቶ በዓለም ሁሉ የረጨው። ✥እመቤታችን ወደ ግብፅ በተሰደደች ጊዜ በዚህ የጭንቅ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እየተራዳ መንገድን እየመራት በብርሃን ወደ ሀገረ ግብፅ ቀጥሎም ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም አስራት ወደ ሆነቻት ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራት መጥቷል። ማቴ 2÷13-15 ✥ሌላው የእውቀትን ብርሃን የገለጸላቸው የእውቀትን ጽዋ ያጠጣቸው ለሊቁ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነው። እኚም አባታችን በመልአኩ ተራዳኢነት ብዙ ድርሰቶችን ደርሰዋል። እመቤታችንም በምልጃዋ ቅዱስ ዑራኤል የእውቀትን ጽዋ ያጠጣቸው ዘንድ አድርጋለች። አባ ጊዮርጊስ እመቤታችንን ይወዷት ስለነበረ አርጋኖን ሌሎችንም ደርሰዋል። የሊቀ ብርሃናት ቅዱስ ዑራኤል በረከት ተራዳኢነት አይለየን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏

  • 29 июл.1 4473

    без подписи

  • 18 июн.7 5502

    ቅዱስ ሚካኤል መልካም ነገርን ሁሉ ያሰማን ሐሳባችንን ይሙላልን ከመከራ ከበሽታ ከጉስቁልና ይጠብቀን።

  • https://t.me/Ty1921/s/270

  • 15 июн.5 88510

    + የሰው ልጅ ቅድስተ ቅዱሳን + ነገር ግን እግዚአብሔር ከሰውነታችን ክፍሎች ኹሉ ለይቶ ልባችንን ብቻ ለራሱ እንዲሆን ለምን መረጠው ? "ልጆች ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ " ይላል ምሳ 23-26 እንዲሁም የመጀመርያው ትእዛዝ "አምላክህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ ውደድ " የሚል ነው ዘዳ 6-5 በእውነቱ ከሆነ እንደ ርኅራኄ የውሃት ምሕረትና ፍቅር ካሉ ስሜቶች አንጻር ከልብ ይልቅ ጥልቅ ነገር በሰው ዘንድ የለም ። ልብ የሰው ልጅ እጅግ ለስላሳና ቅን የኾኑ ስሜቶች ማዕከል ነው ። ኾኖም ግን እግዚአብሔር የሰው ልብ የሚፈልገው ለዚህ ብቻ አይደለም ። በልብ ውስጥ ከደግነት ከርኅራሄ ከምሕረት ወይም ከፍቅር በላይ የኾነ ሌላ ባሕርይ አለና። ይኽውም ልብ የሰው ልጅ ማንነት ምንጭ መኾኑና ዋና ባሕርያቱ ኹሉ ከእርሱ የሚመነጩ መኾኑ ነው ። ልብ የሰው ልጅ ቅድስተ ቅዱሳን ነው ። እግዚአብሔር በውስጡ ሊያድርበት ሚያበቃውም በዚህ ልዮ ባሕርዮ ምክንያት ነው ። አንድ ሰው እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ ወደደ ማለት በሙሉ ማንነቱ ወደደው ማለት ነው ። ራሱንም ያለ ምንም መከልከል ለእግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው ። አባ መቃርስ ልብ አዕምሮን ሕሊናን አሳብን እንደሚያካትት ይናገራል ። በዚህም እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ልብ እንዲፈልግና በፍቅሩም እንዲማርክ ያደረገውን ወሳኝ ምክንያት ይጠቁመናል ። እግዚአብሔር ስሜት በሚጎዳበት ወይም በሚዋረድበት ጊዜ ወዲያውኑ በሚጠፍው ስሜታዊ ፍቅር - ያ ፍቅር ምንም ያህል ከፍተኛ ቢኾንም አይደሰትም ። እግዚአብሔር የሚፈልገው የልብን ፍቅር ነው ። ይህም ማለት ሰው ራሱን (ኢጎውን) እና ማንነቱን ኹሉ አሳልፎ ሰጥቷል ማለት ነው ። ይህ ፍቅር በቁስል የሚቀሰቀስ በመከራ የሚነጥር (የሚሞረድ) እና በሞት ደግሞ ይበልጥ የሚፈጸም (ፍጹም የሚኾን) ፍቅር ነው ። ዠ ( ኦርቶዶክሳዊ የጸሎት ሕይወት "በአባ ማቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት" ትርጉም፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ ገጽ 248-249) ዲያቆን ፍጹም ከበደ @yedawit_begena

  • 6 июн.5 2114

    ይድረስ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት። /ይፍቱኝ አባቴ-ቡራኬዎም ይድረሰኝ/ ከአንድ የመንፈስ ልጅዎ የተጻፈ! +++++++++++++++++++++++++++++ ይህንን ለመጻፍ ስንት ቀናት አሰብሁ? ተጨነቅሁ? ለዚህም በአምላኬና በአምላክዎት ሥም እምላለሁ፡፡ ለምን ቢሉኝ መልሴ ይህ ነው፡፡ አባቶቻችንን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተናገርናቸው የጵጵስና ክብር እየቀነሰ፣ ክህነት አክብረው የሚኖሩትንም እያሸማቀቅናቸው ምልክት እያጣን ነው ብዬ ስለማምን ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ አንዱ የቤተ ክርስቲያን ጠላት አላማ ክብረ ክህነትን የሚያዋርድ ትውልድ መጥቶ እንዳንደማመጥና እንድንለያይ ማድረግ በመሆኑ ለእነሱ መሳሪያ ላለመሆን ነበር፡፡ ቅዱስነትዎ! ነገር ግን እኛ ልጆቻችሁ እናንተን ለመጠበቅ የምንደክመውን ያህል ለእኛ አስባችኋል ደክማችኋል ብዬ አላምንም፡፡ እናንተ ለእኛ የጽድቅ መንገድ ትሆናላችሁ ስንል መሰናክያ እንዳትሆኑብን እንጨነቃለን፡፡ አስቀድሜም ለምጽፈው ነገር ይቅርታን እየጠየቅሁ በድፍረት ሳይሆን በቁጭት መጻፌን እንዲረዱኝ እጠይቃለሁ፡፡ በዚች ቅድስት እያልን በምንጠራት ሀገር በኦርቶዶክሳውያን ላይ ላለፉት 50/60 ዓመታት የደረሰውን በደል ለእርስዎ መናገር ለቀባሪ ማርዳት ነው፡፡ እንኳን በእርስዎ 80 በተሻገረ እድሜ ይቅርና በእኛ በልጆችዎ እድሜ እንኳ እናይዋለን ብለን የማናስበውን እያየን ነው፡፡ እርስዎም ለዓመታት በየመድረኩ አልቅሰዋል። ቅዱስ አባታችን በዚህም ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ያለው ወጣት አንዴ በጦርነት ዜና፣ አንዴ በኑሮ ውድነት፣ አንዴ በዓለም አቀፍ ጫና ደቅቆ፣ ስነ ልቡናው ተሰልቦ፣ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ በመሆኑ እድሜውን ሳይኖረው በቁሙ እየሞተ ነው፡፡ በአጭሩ ዝለናል፡፡ ነገ የሌለው ሰው ሁነናል፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት ተገደንም ቢሆን ወደ ቅድሰት ቤተ ክርስቲያን እንሰበሰባለን፡፡ ወደ አባቶቻችን እንጠጋለን፡፡ ችግሩ ግን እርስዎም በተለያዩ ጊዜያት እንደሚናገሩት አባቶቻችን መጠጊያ ለመሆን ለምእመኑ አለመዘጋጀታችሁ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ወጣት የት ይሂድ? በዚህ ትውልድ መጥፋት አለመጠየቅ እንዴት ይቻላል? በእውነት ይህ ምእመን ምን ቢበድላችሁ ፊታችሁን አዞራችሁ? ለዚች ቤተ ክርስቲያንስ ከገንዘቡ ጀምሮ እስከሕይወቱ አልከፈለም? ምን አጉድሎ ምን ነስቷችሁ ይሆን? ቅዱስነትዎ ከሥልጣንዎ ከፍታ የተነሳ እርስዎን ጠየቅሁ እንጂ ብቸኛ ተጠያቂ ከማድረግ አይደለምና ይቅር ይበሉኝ! በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተስፋዬ እያለቀ ትልቅ እድል ግን እርስዎ ጋር አለ ብዬ ከማሰብ ነው፡፡ ሁሉንም አባቶች ብዬ ግን የምወቅስ ደፋር አይደለሁም፡፡ እነብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን፣ብፁዕ አቡነ ኤልያስ /ስዊድን/ እና ብፁዕ አቡነ ዮናስ /አፋር ሀገረ ስብከት/፣ አቡነ አትናትዮስን ፣አቡነ ቄርሎስ፣አቡነ ዘካርያስን፣ አቡነ እንድርያስን የመሳሰሉ እንባቸውና ሐዘናቸው በእግዚአብሔር ፊት ይደርሳል ብለን የምናምንባቸው አረጋውያን አባቶች አሉን፡፡ ዛሬም በየአሉበት ቡራኬያቸው ይድረሰን። ወደ ጽሑፌ ዋና ጉዳይ ልምጣ! ቅዱስነትዎ ምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የማን ነው? ቅዱስ ሲኖዶስ በሚመራው መዋቅር ተካቷል? ጠቅላይ ቤተክህነት ያውቀዋል? እዚያ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳዉያንስ አባት ነን ትላላችሁ? ለመሆኑ በአርሲ ክርስቲያኖች ጉዳይ ምን ያህል መረጃ አላችሁ? ኦርቶዶክሳውያን የነበሩባቸው ቀበሌዎች በፍጥነት እየጸዱ ባዶ የእርሻ መሬት መሆናቸውን፣ ባለፉት ዓመታት በመቶዎች መገደላቸውን፣ በሺህዎች መፈናቀላቸውን፣ አይዞህ ባይ አጥተውና ተስፋ ቆርጠው ሃይማኖታቸውን እንደሚቀይሩ፣ አብያተ ክረስቲያናት መንደዳቸውን፣ ምእመናን ታቦት ይዘው በየጫካው መሸሸጋቸውን ታውቃላችሁ? ይህን ስልዎት ልቤ እያዘነ ነው፡፡ እኔ አንድ ተራ ምእመን እንዲህ ማለት እንደሌለብኝ ይሰማኛል፡፡ ነገር ግን ልጁ የማይጠይቀው አባት አለን ብዬ አላምንም! ከዓመታት በፊት በጦርነቱ ወቅት “ ታፍኛለሁ ለልጆቼ ድምፅ መሆን አልቻልሁም” ብለው በአለም አቀፍ ሚዲያ በኩል ድምጽ ሁነዋል። ያኔ ያውም ምንም ማለት ዋጋ በሚያስከፍልበት ከባድ ጊዜ ላመኑበት አቋምዎ የቻሉትን አድርገዋል። ቅዱስ አባታችን ዛሬ ለአርሲ ክርስቲያኖችስ? 3/4 ዓመት ሙሉ በተገደሉ ቁጥር ሁለት ገጽ መግለጫ? ዛሬም መጽናናትን መመኘት? እነሱ እኮ ስደት ላይ ናቸው አባቴ!የእናንተን መግለጫ አይሰሙ አያነቡም። ለመንግስት እንዳይሉ መሞታቸውን እንኳ አልሰማሁም መረጃ የለኝም ላለ መንግስት? አባቴ ሥጋ ለባሽ ነዎትና ፈተናዎትን እረዳለሁ። የቅደስት ቤተ ክርስቲያን መሳሪያዋ ጸሎት መሆኑንም አውቃለሁ። ግን ቅዱስነትዎ እርስዎ ምእመን አይደሉም። ባለሥልጣን ነዎት። ምእመናንን ሊጠብቁ የተሰጠዎትን ሥልጣን ነው እንዲጠቀሙበት በልጅነት እየጠየቅሁ ያለሁት። እርስዎ በዓለም የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ቁጥር ሁለተኛ ከኦሬንታል ደግሞ በብዛት አንደኛ የሆነች ቤተ ክርስቲያን መሪ ነዎት። ይህ ለእርስዎ ትልቅ እድልም ጉልበትም ሊሆን ይገባል ብዬ አምናለሁ። ግብፅ፣ ቱርክ፣ሶሪያ ያየ ክርስቲያን እንዲህ ያለውን ጥቃት እንደቀላል አይቶ ሊተኛ አይችልም። በመግለጫዎ ለመንግስት የታሪክ ተጠያቂነት እንዳለበት እንዳሳወቁት ሁሉ አባቶቻችን ቀድማችሁ በመሰበራችሁና ምእመኑን አባት አልባ ለማድረግ በምትሄዱት መንገድ እናንተም ተጠያቂ አለመሆን አትችሉም። ይህን የምለው ለአርሲ ምእመናን በማሰብ ብቻ አይደለም ማእተቤ አንገቴ ላይ እስካለ ድረስ የነገ የእኔንም እጣ ፋንታ በመፍራት ነው። ተማፅኖዬ ለራሴ ነው። እናንተም እኛም አልቅሰን መፍትሔ አይመጣም። ቆም ብላችሁ አስቡና ድርሻችንን ስጡን ድርሻችሁን ውሰዱ። ስለሆነም ምኞቴ ከጸሎት ባሻገር 1- ፌዴራል መንግስት ጋር ገፍተው በመሄድ ምን እያሰበ እንደሆነ ጠይቀው ምላሹን ለመንፈስ ልጆችዎ ቢያሳውቁልን፣ 2- ለልጆቹ ግድያ ድምጽ ለመሆን ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጠርተው የኦርቶዶክሳውያንን መከራ ገለጻ ቢያደርጉልን፣ (ቢያንስ ዓለም መከራችንን ይወቀው) 3- ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ዓለምአቀፍ ተቋማት በደብዳቤ ቢያሳውቁልን፣ 4- ለተጎዱትና ለተፈናቀሉት ወገኖቻችን አስቸኳይ የሰብአዊና የመንፈሳዊ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዲያቋቁሙልን፣ ይህንን ለማድረግ ከልብዎ ፈቅደው ሲነሱ አላሠራ የሚሉ መካሪ መሳይ አባቶችን በይፋ ለምእመናን እንዲያሳውቁ እና አብረንዎት እንድንቆም እንዲፈቅዱልን እጠይቃለሁ። የዕድሜ መግፋትና የጤና ድካም ቢኖርብዎትም፣ እግዚአብሔር የሰጠዎትን መንፈሳዊ ሥልጣንና የአባትነት ክብር ዛሬም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጋር አለ። በተለያዩ የሕንጻ ምርቃት ባየዎትም ይህን ለማድረግ አይደክሙም ከማለት ነው። በዚህ ሂደት ቀድሞ ለመፍትሔ ያልሮጠ ሁሉ አሰራር እያለ ሕግና መመሪያ እንደሚጠቅስ ይታወቃል። ቤተ ክህነታችን በዚህ አይታማም። ሕግ ግን ከሰው ሕይወት አይበልጥም። ካህናት ያላችሁት ምእመናን ስላለን ነው። አባቴ በቀረችዎት እድሜ ይህን በማድረግዎ የሚመጣብዎት መከራ ቢኖር እንኳ ተጋፍጠው ለዚህ ትውልድ ቋሚ ምልክት እንዲሆኑን በልጅነት ዝቅ ብዬ እጠይቃለሁ። ቡራኬዎ ይድረሰኝ! የመንፈስ ልጅዎ ገበረ ጊዮርጊስ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

  • 6 июн.3 982

    ኮንሰርቱ አልተሰረዘም ‼️‼️ የተዋህዶ ወጣት አሁን ነው የሚለየው ከእምነትህ ከሐይማኖትህ መጠጥ እና ጭፈራ እንደማይበልጥብክ አውቃለሁ እውነት ለእምነትህ ቆራጥ ከሆንክ አንድም ኦርቶዶክሳዊ እዚህ ኮንሰርት እንዳይገኝ ዛሬ ኮንሰርት የገባ እውነት እውነት እላችኋለሁ አርሲ ላይ የፈሰሰው ደም ይፋረዳችኋል ለሁሉም ሼር ሼር ይደረግ

  • 2 июн.5 0591

    በኦሮምኛ ቋንቋ መንፈሳዊ መዝሙሮችእና ትምህርቶች የሚለቀቁበት ቻናል ከፈለጋችሁ ቶሎ ተቀላቀሉይ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/tawahiidoo Faaruu fi barnota ortodoksii tewaahidoo affaan oromootiin yoo barbadan dafaa kotaa 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/tawahiidoo

  • 2 июн.6 3889

    ☦️ጭንቀት ከምን ይመጣል❔ ❕ከአቡነ ሺኖዳ ትምህርቶች የተወሰደ ​ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ጭንቀት የሚመጣው ከቁሳዊ ችግሮች ይልቅ ከመንፈሳዊ ድካም እንደሆነ ያስተምራሉ። ዋና ዋናዎቹ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦ ​፩. የእምነት መጓደል፦ "ጭንቀት የሚጀምረው እግዚአብሔርን ከሥዕሉ ውስጥ ስናስወጣው ነው" ይላሉ። እግዚአብሔር ታሪካችንን እንደሚመራና ለእኛ እንደሚያስብ ስንረሳ፣ ነገን በራሳችን ትከሻ ላይ ለመሸከም እንሞክራለን፤ ያኔ ጭንቀት ይወለዳል። ​፪. ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር መፈለግ፦ ሰው ከቁጥጥሩ ውጭ የሆኑ ነገሮችን (የወደፊቱን፣ የሰዎችን ሐሳብ...) ለመቆጣጠር ሲታገል ይጨነቃል። አቡነ ሺኖዳ እንደሚሉት፦ "የማይቻለውን ነገር ለእግዚአብሔር መተው አለመቻል የጭንቀት ምንጭ ነው።" ​፫. ከመጠን ያለፈ የዓለም ፍቅር፦ ልባችን በምድራዊ ጥቅም፣ በዝና እና በሀብት ላይ እጅግ ሲጣበቅ፣ እነዚህን ነገሮች እንዳናጣ በመስጋት ዘወትር እንጨነቃለን። ​፬. የጸሎት ሕይወት መዳከም፦ ጸሎት የነፍስ ትንፋሽ ነው። ጭንቀት ማለት በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያልተወረወረ ከባድ ሸክም ነው። ​☑️መፍትሔው ምንድን ነው❔ ​አቡነ ሺኖዳ ለጭንቀት የሚሰጡት ታላቅ መድኃኒት "ለእግዚአብሔር መተው" የሚለውን ነው፦ ​"ልጄ ሆይ❕ አንተ ስለ ራስህ ከምትጨነቀው በላይ እግዚአብሔር ስለ አንተ ያስባል፤ ስለዚህ ጉዳይህን ሁሉ ለእርሱ ሰጥተህ በሰላም ውለህ እደር።"

  • 2 июн.3 4796

    “አንተ እራስህን ከሚታዩ ኃጢአቶች ለመጠበቅ ስትሞክር አምላክ ከማይታዩና ከህሊና በላይ ከሆኑት ይሰውርሃል።’’ ✍️አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

  • 21 мая5 1688

    የጌታችን ንዑሳት በዓላት የሚባሉትም ዘጠኝ ሲሆኑ እነርሱም ስብከት ፣ ብርሃን ፣ ኖላዊ ፣ በዓለ ጌና ፣ ግዝረት፣ ልደተ ስምዖን ፣ ቃና ዘገሊላ ፣ ደብረ ዘይትና መስቀል ናቸው፡፡ የጌታችን የከበረ የዕረገቱ ረድኤት በረከት ይደርብን! በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ላረገ አምላካችን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይሁን ከቸር አባቱ ከአብ ሕይወት ከሆነ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ለዘለዓለሙ አሜን! ስንክሳር ዘወርሃ ግንቦት

  • 21 мая5 5147

    ​​​​እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል በሰላም አደረሰን!!! ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፡፡›› መዝ 67(68)፡33፡፡ ‹‹ አምላክ በእልልታ፣ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ፡፡ ዘምሩ፣ ለአምላካችን ዘምሩ ፤ ዘምሩ ፣ ለንጉሣችን ዘምሩ፡፡ እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና ፤ በማስተዋል ዘምሩ፡፡ እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ ፤ እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል፡፡ ›› መዝ 47፡5-8፡፡ ‹‹ ነሆም አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፡፡ እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው፡፡ ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ፡፡ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፣ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ፡፡ ›› ሉቃ 23፡50-53፡፡ ‹‹ #ዕርገት ›› የሚለው ቃል ዐረገ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ‹‹ ከፍ ከፍ አለ ፣ ወደ ሰማይ ወጣ ›› ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ላይ ‹‹ በስምሽ በመለመን በመማጸን የሰው ልጆችን ጸሎት ያሳርጋሉ ›› እንዲል፡፡ እንዲሁም በእሁድ ውዳሴ ማርያም ላይ ‹‹ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያሳረገ›› እንዳለ፡፡ በተጨማሪም በራእይ 8፡4 ላይ ‹‹የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር በመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ›› በማለት ዐረገ የሚለውን ቃል በአማርኛ ‹‹ወጣ›› በማለት ይገልጸዋል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ሞቶ ድኅነትን ከፈፀመ በኋላ በሦስተኛው ቀን የሞትን መውጊያ ሰብሮ ተነሣ፡፡ ከዚህ በኋላ በሞቱ ቀቢጸ ተስፋ ይዟቸው የነበረውን ሐዋርያትና አርድዕትን በተደጋጋሚ ትንሣኤዉን በመግለጥ ያጽናናቸው ነበር፡፡ ጌታችን ከሞት ከተነሣ ከኋላ ለአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ኪዳንንና ትምሕርተ ሕቡዓትን በዝርዝር አስተምሯቸዋል፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ ጀምሮ እስከ 40 ቀን ድረስ ሐዋርያትን ፣ አርድዕትን በጠቅላላው 120ውን ቤተሰብ ሲያጽናና ቆይቶ ለቅዱስ ጴጥሮስ የፕርትክና (ታላቅ አባት የመሆን) ሥልጣንን ከሰጠው በኋላ 120ውን ቤተሰብ ወደ ደብረ ዘይት ይዞአቸው ወጣ፡፡ በዚያም ሳሉ ‹‹ኃይልን እስክትለብሱ ድርስ በኢየሩሳሌም ጸንታችሁ ቆዩ›› የሚለውን ታላቁን የዕርገት መልእክት አስተላልፎ ከምድር ከፍ አለ፡፡ በመላእክት ምስጋና ‹‹በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ›› እንዲል ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ከዐይናቸዉም ተሰወረ፣ ሐዋርያትም ወደላይ አንጋጠው አንገታቸውን አቅንተው ይመለከቱ ነበር፡፡ ሐዋ 1፡2፡፡ በዚህ ጊዜ ሁለቱ ብርሃናውያን መላእክት እንዲህ ሲሉ ተናገሯቸው ‹‹የገሊላ ሰዎች ሆይ! ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁ እንዲሁ ይመጣል፡፡›› ይህ ታላቅ የተስፋ ቃል የመላእክት ንግግር ከቅዱስ ዳዊት ትንቢት ጋር የተዛመደ ሲሆን የጌታችን ምጽአት በምሥራቅ በኩል እንደሚፈጸም ያሳያል፡፡ ሁለቱ መላእክት በንግግራቸው በዚህ ሲሄድ እንዳያችሁት በግርማ ደግሞ በዚህ ይመጣል ብለው ነበር፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ ›› መዝ 67(68)፡33 በማለት ይናገራል፡፡ በመሆኑም ጌታችን ያረገው በምሥራቅ ነው ፤ ደግሞ ለፍርድ የሚመጣው በምሥራቅ ነው ማለት ነው፡፡ የጌታችን ዕርገት ምሳሌ እና ትንቢት አለው፡፡ ምሳሌው እንደምን ነው ቢሉ የቅዱስ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀን አድሮ በሦስተኛው ቀን መውጣቱ ለትንሣኤው ምሳሌ እንደሆነ ሁሉ እንዲሁ የቅዱስ ኤልያስ ዕርገትም ለጌታችን ዕርገት ምሳሌ ነው፡፡ ልዩነቱ ግን ቅዱስ ኤልያስ በመላእክት እርዳታ በፈቃደ እግዚአብሔር ያረገ ሲሆን ጌታችን ግን በፈቃዱ በራሱ ኃይል ዐርጓል፡፡ ትንቢቱም ቅዱስ ዳዊት ‹‹ ወደ ሰማይ ላረገው ለእግዚአብሔር ዘምሩ ›› መዝ 67(68)፡33 ብሎ የተናገረው ነው፡፡ በተጨማሪም ‹‹ወደ ላይ ዐረግህ ምርኮን ማረክህ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ›› (መዝ 67፡18) የሚል እናገኛለን፡፡ በመጨረሻም የጌታችን ታላቁ የዕርገት መልእክት ‹‹ኃይልን እስክታገኙ በኢየሩሳሌም ጽኑ›› የሚለው ታላቅ መልእክት ነው፡፡ ጌታችን በኢሩሳሌም እንደተወለደ እንዳደገ እንዳስተማረ እንደተሰቀለ በቤተ ክርስቲያንም በቤተልሔም ሥጋው ደሙ የሚዘጋጅባት ቃሉ የሚነገርባት በቤተ መቅደስ ሥጋው የሚቆረስበት ደሙ የሚፈስባት ቦታ ናትና ኢየረሳሌም የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ስለሆነም ቅዱስን የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲሁም ጸጋ ለማግኘት በቤተ ክርስቲያን መጽናት እንደሚገባ በአጭር ዐረፍተ ነገር ያስተማረው ታላቅ በዓል ነው፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገቱን ከትንሣኤው አከታትሎ ወዲያውኑ አላደረገም ፣ ምክንያቱም ፈጽመው ክፋትን የተመሉ አይሁድና በኋላም የሚነሣ የረከሱ መናፍቃን ዕርገቱ ምትሐት ናት ብለው እንዳያስቡ ነው፡፡ ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ የደቀ መዛሙርቱን ተሸብሮ የነበረ ልቡናቸውን እያጽናና መነሣቱንም እያስረዳቸው ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀን ኖረ፡፡ ይህ የዕርገት በዓል ከጌታችን ዓበይት (ታላላቅ) በዓላት መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የጌታችንን የዕርገት በዓል ሁለት ጊዜ ታከብራለች፡፡ ይኸውም በመጀመሪያ ጌታችን ያረገበትን ጥንተ በዓሉን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የቀመር በዓል ነው፡፡ ዓመታዊ በዓላት ዓዋድያት (Movable Feasts) እና ዓዋድያት ያልሆኑ (Immovable Feasts) ተብለው በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡ ዓዋድያት (Movable Feasts) የሚባሉት በቅዱስ ዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት መባጃ ሐመርን ተከትለው ወደፊት ወደኋላ በመመላለስ በየዓመቱ በተለያየ ቀንና ወር የሚውሉት ናቸው፡፡ እነዚህም እንደ ስቅለት፣ ሕመማት፣ ትንሣኤ፣ ደብረ ዘይት ፣ ሆሣዕና ፣ ዕርገትና ጰራቅሊጦስ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ዋድያት ያልሆኑ (Immovable Feasts) የሚባሉት ደግሞ ሁልጊዜም በወር ውስጥ በሚገኝ በታወቀ ቀን ብቻ በቋሚነት የሚውሉት ናቸው፡፡ እነዚህም እንደ ፅንሰት (ትስብእት) ፣ ልደት ፣ ጥምቀት ፣ ደብረ ታቦር ፣ ቃና ዘገሊላ ፣ ዘመን መለወጫ ፣ መስቀል ፣ 33ቱ የእመቤታችን በዓላት ፣ የመላእክት ፣ የሰማዕታትና የቅዱሳን በዓላት ናቸው፡፡ የጌታችን ዓበይትና ንዑሳት በዓላት፡- ለመጀመሪያ ጊዜ የጌታችንን በዓላት ማክበር የጀመሩት የከበሩ ሐዋርያት ናቸው፡፡ ሠለስቱ ምእት ደግሞ ከ325 ዓ.ም ጀምረው በዓላቱ በቀኖና በሕግ እንዲከበሩ አዘዋል፡፡ ለዚኽም በፍትሐ ነገሥቱ ላይ የተጻፈውን በማስረጃነት ማየት እንችላለን፡፡ ‹‹እግዚአብሔር የጠመመውን እያቀናላቸው፣ የጎደለውን እየሞላላቸው የጌታን በዓላት ማክበር እንዲገባ 318 ሊቃውንት በጉባኤ ኒቅያ በእግዚአብሔር አጋዥነት የጌታችንን በዓላት ያከብሩ ዘንድ፣ ተአምራቱን ይገልጹ ዘንድ፣ ምስጋናውንም ይናገሩ ዘንድ አዘዙ ተናገሩ›› እንዲል፡፡ (ፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ፣ ገጽ 260) የጌታችን ዓበይት በዓላት ዘጠኝ ናቸው፡፡ እነዚህም፡- ፅንሰት (ትስብእት)፣ ልደት፣ ጥምቀት፣ ደብረ ታቦር፣ ሆሣዕና፣ ስቅለት፣ ትንሣኤ፣ ዕርገትና ጰራቅሊጦስ ናቸው፡፡

  • 20 мая3 352

    💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️ 💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️ 👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️ ⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️ 🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️ በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት                 👇👇👇      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel

  • 20 мая3 687

    🎉ከ17 ደቂቃ በኃላ ይጠፋል የ 200 ብር ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ! የንኤስ_አንበሳ የተባለው ማን ነው ?

  • 18 мая3 9334

    ግንቦት 12 እረፍቱ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ማን ነው? ልደቱና እድገቱ፦ ነገረ ታሪኩን የከተቡ መጻሕፍት እንደሚያስረዱት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተወለደው አንጾኪያ በምትባል ከተማ በ347 ዓ.ም. ነው፡፡ አንጾኪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐዋርያት ክርስቲያን ተብለው የተጠሩባት ከተማ ስትሆን የምትገኘውም በሮም ምሥራቃዊ ግዛት ነው፡፡ አንጾኪያ ለሮም ምሥራቃዊው ግዛት የት ከቊስጥንጥንያ ቀጥላ ሁለተኛዋ መናገሻ ከተማ ነበረች፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ወላጆች የአባቱ ስም ሲፋኒዶስ (ሴኩንዱስ) ሲሆን የእናቱ ስም ደግሞ አንቱዛ (አትናስያ) ነው:: አባቱ ሲፋኒዶስ የታወቀ አገረ ገዥ ነበረ፡፡ ሆኖም ግን ሚስቱ አትናስያ (አንቱዛ) ገና የሃያ ዓመት ወጣት እያለች ዮሐንስ አፈወርቅንና ታላቅ እኅቱን እንደ ወለዱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ከዚህም በኋላ ልጆችን የማሳደጉ ኃላፊነት በአትናስያ (አንቱዛ) ትክሻ ላይ ብቻ ወደቀ፡፡ አትናስያም ምንም እንኳ ባሏ ገና በለጋ ዕድሜዋ ትቷት ቢሞትም ሁለተኛ ላግባ ሳትል ልጆቿን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅንና እኅቱን በጥልቅ የክርስትና ሕይወት ትምህርት አሳደገቻቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተወለደበት ይህ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የትውልድ ሀገሩ በሆነችው በአንጾኪያ ብዙ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርታቸውን ለማስፋፋት እየተሯሯጡ የነበረበት ዘመን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እናቱ አትናስያ ጠንካራ ክርስቲያን ከመሆኗ የተነሣ ልጇ ከዘመኑ የኑፋቄ ትምህርት እንዲጠበቅ በሕይወትም በትምህርትም ተንከባክባ በመልካም አስተዳድግ አሳደገችው፡፡ የዕብራውያን መልእክትን የተረጎመውን ድርሳኑን የተረጐሙ አባቶቻችን በመልካም አስተዳድግ የማደጉን ነገር ሲናገሩ ''ወተሐፅነ በሠናይ ተሐፅኖ፤ በመልካም አስተዳድግ አደጉ በማለት ዜና ልኅቀቱን በተዋበ ቋንቋ ገልጸውታል፡፡ የትምህርት ዘመኑ፦ አትናስያ ልጇ ቅዱስ ዮሐንስን በመልካም አስተዳድግ አሳድጋዋለች ተብላ እንድትመስገን ከሚያደርጋት ነገር አንዱ ልጇ የሕፃንነት ዘመኑን በጊዜው ከነበሩት የታወቁ ትምህርት ቤቶች ገብቶ ዘመኑ የሚጠይቀውን ዓለማዊና መንፈሳዊ ትምህርት ተምሮ እንዲያድግ ማድረጓ ነው፡፡ ሊቁ በልጅነት ዘመኑ በወቅቱ ይሰጡ የነበሩትን ሁለት ታላላቅ ትምህርቶች ከሁለት ታላላቅ መምህራን ተምሯል፡፡ ይኸውም የፍልስፍና ትምህርትና የንግግር ክህሎት ነው፡፡ የፍልስፍና መምህሩ አንድሮጋቶስ ሲባል የንግግር ክህሎት መምህሩ ደግሞ ሊባንዮስ ይባላል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትምህርት ቤት ቆይታው የታወቀ ጎበዝ ተማሪም ነበር። ለጉብዝናውም የመምህሩ ምስክርነት ተጠቃሽ ነው፡፡ የንግግር ክህሎት መምህሩ ሊባንዮስ “ከአንተ በኋላ በአንተ ወንበር ማን ቢተካ ትፈልጋለህ?'' ተብሎ በተጠየቀ ጊዜ “ክርስቲያኖች ከእኛ ሰርቀው ባይወስዱብን ኑሮ የሚተካኝ ዮሐንስ ነበር” በማለት የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን የዕውቀት ከፍታ በመምህርነት አንደበቱ እንደመሰከረለት ታሪኩን የሰነዱ መምህራን ያስረዳሉ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትምህርት ቤት ቆይታው ጊዜ ከነበሩት የቅርብ ጋደኞቹ መካከል ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ አንዱ ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስ ከጓደኞቹ ሁሉ የተለየ ተወዳጅ ጓደኛው እንደ ነበር “ብዙ ቀና ልብ ያላቸውና እውነተኛ፣ የወዳጅነትን ሥርዓት የሚያውቁና ይህንንም በታማኝነት የሚያከብሩ ወዳጆች ነበሩኝ፡፡ ከእነዚህ ሁሉ በላይ ግን ከእኔ ጋር በነበረው ግንኙነት የሚበልጠው አንዱ (ባስልዮስ) ነበር። እነዚህ ወዳጆች ከሌላው ሰው ይልቅ ወዳጅነታቸው ከፍ ያለ እንደ ነበር ሁሉ እርሱም ከእነዚህ ወዳጆቼ መካከል ወዳጅነቱ እጅግ የላቀ ነበር፡ '' በማለት ይገልጸዋል፡፡ የእነዚህ የሁለቱ ሊቃውንት በአንድ ትምህርት ቤት በተመሳሳይ ፍላጎት ተመሳሳይ ትምህርት ተምረው ማደጋቸው በኋላ ለኖሩት ተመሳሳይ የሆነ የቅድስና ሕይወት መሠረት እንደ ነበረ አያጠራጥርም። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከትምህርት ቆይታው በኋላ ምን ዐይነት ሕይወት መኖር እንዳለበትም የወሰነው በትምህርት ቤት ቆይታው ከቅዱስ ባስልዮስ ጋር በጓደኝነት በቆየበት ጊዜ ነበር፡፡ ይህንንም ራሱ ሊቁ በእንተ ክህነት በሚል ርእስ ባዘጋጀው ሥራና ገብረ እግዚአብሔር ኪደ በተረጎመው መጽሐፍ ውስጥ “በምንማረው ትምህርት ብቻ ሳይሆን ትምህርታችንን ጨርሰን ከዚያ በኋላ ምን ዓይነት ሕይወት ሊኖረን እንደሚገባ ስንወስንም ውሳኔያችንና አሳባችን ተመሳሳይ ነበበማለት ገልጾታል፡፡ ቅድመ ምንኵስና በጥብቅና ሙያ ይቀጥላል......

  • 9 апр.9 39715

    የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ስያሜዎች ፬ ሐሙስ ጸሎተ ኀሙስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚሁ ዕለት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙንም ለሐዋርያት የሰጠበት ዕለት ነው፡፡ የአይሁድ ፋሲካ የነበረው ሐሙስ ነው፡፡ ከአይሁድ ጋራ በበዓል በጾም እንዳንገናኝ የኒቅያ ጉባኤ በድሜጥሮስ ቀመር፤ እንዲሁም የአውሻክር ሰዎች በአውሻህር፣ በባሕረ ሐሳብ በዚሁ ሁሉ ወስነውታል፡፡ "እመቦ ዘይጸውም ጾሞሙ ለአይሁድ ወያከብር በዓሎሙ ለአይሁድ ይሰደድ እምክርስቲያን" "የአይሁድ ጾማቸውን የሚጾም፣ በዓላቸውንም የሚያከብር ካለ? ከክርስቲያንነት ይወገድ /ይባረር/ ብሏል ሰለስቱ ምዕት በሃይማኖተ አበው" በዚሁ ዕለት በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 26፡26 እንደተገለጸው ጌታ ክቡር ሥጋውንና ደሙን ለሐዋርያት ሰጥቷል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ቁርባን የሚለው በዕለቱ ተለውጧል ወይ? ወይስ አልተለወጡም? በሌላ በኩል ጌታችን ለሐዋርያት የሰጣቸው "ሥጋዬ" ብሎ ሲሆን ይህ አማናዊ ነው ወይ? እንዴት ከመሰቀሉ በፊት "ሥጋዬ" ብሎ ሊሰጣቸው ቻለ? የሚሉ እንዳሉ ጥያቄ ሰምቼአለሁ፡፡ መልሱ ግልጽና አጭር ነው፡፡ ይኸውም አማናዊ ነው፡፡ ነገ በቀራንዮ የሚሰቀል "ዝውእቱ ሥጋየ ወዝውእቱ ደምየ" "ነገ በመስቀል የሚሰቀል ሥጋየ ይህ ነው፣ ነገ ኲናተ ሐራዊ የሚያፈሰው ደሜ ይህ ነው" ብሎ አክብሮ፣ ለውጦ ትኩስ ሥጋ፣ ትኩስ ደም አድርጎ ሰጣቸው፡፡ ስለፈሩ "ጥዒሞ አጥዓሞሙ" አይዟችሁ አትፍሩ ብሎ ቀምሶ ሰጣቸው፡፡ ጌታ ሳይቀበል አቀበሎአቸው ቢሆን ኖሮ፣ ዛሬ የሚቀድሰው ካህን አቀብየ ሳልቀበል ልውጣ ባለ ነበርና፣ ተቀብሎ ያቀብል ለማለት ለአብነት፣ የሠራው ሁሉ ለእኛ ነው፡፡ "እስመ አልቦ ነገር ዘይሰዓኖ" "ለእግዚአብሔርየሚሳነው የለም"፡፡ እግዚአብሔር ይህ ሥጋየ ነው ሲል ውሸት ነው አይባልም፡፡ የተናገረውን ሁሉ ማመን አለብን፣ ጥያቄው ሳይሰቀል ለምን ሥጋየ ነው አለ ነው፣ ነገር ግን ነገ የሚሰቀለው ሥጋዬ ይህ ነው ሲል ተለውጦ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ሆነ ማለቱ እንደሆነ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ ያ የዕለተ ሐሙስም ሆነ ዛሬ ካህናት የሚያቀርቡት መሥዋዕት አማናዊ ሥጋውና ደሙ ነው፡፡ ጠያቂዎቹ እንደምሳሌ አድርገው የሚያቀርቡት ጌታ ከመሰቀሉ በፊት ሥጋውና ደሙ ተበልቷል ወይስ አልተበላም እንዴት ጌታ ሳይሰቀል ሥጋው ተበላ የሚል ጥያቄ ነው፡፡ መልሱ፣ ነገ የሚሰቀለው ሥጋየ ይኸ ነው፣ ነገ የሚፈሰው ደሜ ይኸነው ሲል ቃሉ ለወጠው፤ ሥጋና ደሙ አደረገው፡፡ እኛ አምነን እንቀበላለን እንጂ አይደለም አይባልም፡፡ እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ አምነን መቀበል አለብን፡፡ እሱ ይህ ሥጋየ ነው ይህ ደሜ ነው እያለ አይደለም የሚል ካለ ሐሰተኛ ይሆናል፡፡ "እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር" እሩቅ ብእሲ ቢሆን ኖሮ አይሆንም ይባል ነበር፡፡ እግዚአብሔር ግን ያለው ሁሉ ይሆናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በዕለተ ሐሙስ ሐዋርያት የታጠቡት ኅፅበት ስለ ትሕትና ወይስ ስለ ጥምቀት የሚል ጥያቄ አለ፤ ይህም፡- ሐዋርያት የታጠቡት ጥምቀት ነው፡፡ "እመ ኢሐጸብኩከ እገሪከ አልብከ ክፍል ምሳሌየ" "ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም" ሲል መልሶለታል፡፡ ዮሐ. 13፡7 ዕድል ፈንታ የለህም ማለት ልጅነት አታገኝም ማለት ነው፡፡ ጥምቀት እንዳንል ካሣ አልተፈጸመም የሚል ሐሳብ ካለ አስቀድሞ አጥቦ ወዲያው ሥጋና ደሙን ሰጣቸው፡፡ ዛሬ መጀመሪያ ሕፃኑን እናጠምቀዋለን፤ ኋላ ሜሮን ተቀብቶ ሥጋውና ደሙን ይቀበላል፡፡ ይኸ "ተሰዕሎተ ቢንያም" የሚባል ጥሩ አድርጐ ጽፎታል፡፡ ስለዚህ ሐዋርያት መቼ ተጠመቁ ቢባል በሕጽበተ እግር ጊዜ ነው፡፡ ይህም "አልብከ ክፍል" "ዕድል ፈንታ የለህም" ባለው ይታወቃል፡፡ ለጊዜው ሐዋርያት ዕግራቸው ብቻ እንደታጠቡ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ግማሹ አካላቸው ታጥበውስ እንዴት ጥምቀት ሆኖ ሊቆጠር ቻለ ቢሉ? ያማ "ዘይውህጥ ርዕሶ" ብለው ሠለስቱ ምዕት የሕጻኑን ራስ በሚውጥ ባሕር ብቅ ጥልቅ ብቅ ጥልቅ አድርጉ ብለው በጥልቅ ባሕር፣ በማዕከላዊ ባሕር፣ በንዑስ ባሕር የተጠመቀ እንደ ሆነ ነው ብለው ጽፈው የለ፡፡ "ዘይውህጥ ርዕሶ" የሚጠመቀውን ሰው በፈሳሽ ወንዝ ብቅ ጥልቅ ብቅ ጥልቅ አድርገህ ታወጣዋለህ፡፡ ጴጥሮስ መላ አካላቴን እጠበኝ ባለበት ሰዓት ጌታ አይፈቀድልህም ያለው ይህ ለምንድነው ቢባል? እግሩን የታጠበ ሰው ሌላው ሊታጠብ አይፈልግም፡፡ አንዱ የሰውነት አካልህ ካጠብኩህ መላ ልጅነት ይሰጥሃል፡፡ ማለት ነውና በትልቁ ባሕር፣ በትንሹ ባሕር፣ በጳጳስ ቢጠመቁ አንድ ነው፡፡ "አሐቲ ጥምቀት" "አንዲት ጥምቀት" /ኤፌ. 4፡4/፡፡ አንዳንዴም ሐዋርያት የተጠመቁት በውሃ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ለዚያም እንደ ማስረጃ የሚጠቅሱት መጥምቁ ዮሐንስ በማቴዎስ ወንጌል የንስሐ ጥምቀት በሚያጠምቅበት ጊዜ "እኔ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳት ያጠምቃችኋል" ማቴ. 3፡11 ያለውን ይጠቅሳሉ፡፡ ለዚህ መልስ የሚሰጠን በግብረ ሐዋርያት ጴጥሮስ ሲናገር "ንስሐ ግቡ፣ ኃጢአታችሁም ይሠረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ የሚለው ነው፡፡ /የሐዋ. 2፡38/ ሐዋርያት ሲያጠምቁ ቋንቋ ይገለጽላቸው ነበር መንፈስ ቅዱስ ያድርባቸው ስለነበር ተጠቀሰ እንጂ የሐዋርያትን መጠመቅ አያስመለክትም፡፡ ከዚሁ ባልተለየ መልኩ አብሮ የሚታየው ኦሪት አለፈች፤ ወንጌል ተተካች የሚባለው መቼ ነው ቢሉ ከልደቱ እስከ ጥምቀቱ ከጥምቀቱ እስከ ዕለተ ሐሙስ ከዕለተ ሐሙስ እስከ ትንሣኤ ባለው ሰዓት ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ሲያስተምር እሷን ወደ ወንጌል እየሳበ ቆይቷል፡፡መስዋዕትዋን የሻረው በዕለተ ሐሙስ ነው፡፡ በግ ይሰዋ ነበር፤ ቀርቷል መስዋዕትዋን አሳለፈው፣ የበሉትን ምግብ ከሆዳቸው በግብር አምላካዊ አጥፍቶ አማናዊ ሥጋውን አማናዊ ደሙን ሰጣቸው፡፡ ሌላው በየስፍራው ሲያስተምር አሳልፎታል፡፡ ዐሠርቱ ቃላት ብቻ አላለፉም፡፡ ሌሎች ሥርዓቶች ግን አልፈዋል፡፡ የወንድምን ሚስት ማግባት ቀርቷል፡፡ የበግ፣ የላም፣ የዋኖስ የዕጉለር ግብ፣ መስዋዕትና ይህን የመሰለ ሁሉ ቀርቷል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ኦሪት ለምን አለፈች ይባላል? "ጌታ በወንጌል ኢመጻእኩ እስዓሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት አላ ከመእፈጽሞሙ" "ኦሪትንና ነቢያትን ሊሸራቸው አልመጣሁም፣ ልፈጽማቸው እንጂ" ብሎአልና አላለፈችም የሚሉ አሉ፡፡ "ኢመጻእኩ ከመእስዓሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት" ማለት፤ ኦሪት፣ ነቢያት የተናገሩትን ላስቀር አልመጣሁም፣ ይወርዳል ይወለዳል፣ ብለው የተናገሩትን ሁሉ ልፈጽም ነው የመጣሁ፣ ማለት እንጂ ኦሪት አላለፈችም ለማለት አይደለም፡፡ "የውጣ" የተባለው ዐሠርቱ ቃላት ነው፡፡ ይኸውም እነሱ አልተሻሩም፡፡ኦሪት አለፈች የሚያሰኘው በግ፣ ላም መሠዋት፣ የወንድም ሚስት ማግባት፣ እጃቸው እስኪላጥ መታጠብ፣ ይህን የመሳሰለ ሁሉ አልፏል፡፡ ከአሥሩ ቃላት በቀር ሁሉም አልፏል፡፡ ዐሠርቱ ቃላት ግን በወንጌል እንኳንስ ነፍስ መግደል፤ ወንድሙን የሰደበ ይፈረድበታል፡፡ ሲል ፈጽሞ እያበለጠው ሄደ፣ "አትዘሙ" ያለውን "ኲሉ ዘርእያ ለብእሲት ወፈተዋ ዘመወ"

  • 9 апр.6 5381

    ፀሎተ ሐሙስ

  • 4 апр.6 423

    https://t.me/tawahiidoo

  • 4 апр.5 84113

    ሠላምሽ ዛሬ ነው የሆሳእና መዝሙር

  • 4 апр.5 79842

    ሰላምሽ ዛሬ ነው (በበገና ትዝታ ቅኝት) 425 4233 212 24 233-3 21-1-11-1133 244 23-1-355 45-4-32  222     ሆሳዕና በአርያም  እያሉ ዘመሩ     ህፃናት በኢየሩሳሌም      24231-1 1-1231244        14-214- 225-5 5415         4225-54222-2 ሰላምሽ_ዛሬ_ነው ሰላምሽ ዛሬ ነው እየሩሳሌም ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/  ሆሣእና በአርያም እያሉ ዘመሩ  ሕፃናት በኢየሩሳሌም  አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2 / ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2 / የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/2/ @yedawit_begena