tgindex
ደብረ ዘይት ሚዲያ

ደብረ ዘይት ሚዲያ

Статистика

ቤተክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ።

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 026
0 за 2 дн.
Сутки
+1
+0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
441
21 постов
Вовлечённость
21,8%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
188
1/48двое суток
215
1/72трое суток
232

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • “ኢሰማዕነ ወኢርኢነ ወኢነገሩነ አበዚነ ከመቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌከ~~ያላንተ ሌላ አምላክ እንዳለ አባቶቻችን አልነገሩንም፤ እኛም አላየንም አልሰማንም።” (መጽሐፈ ሰዓታት)

  • በሕይወቴ ብዙ ሰዎች ጎድተውኝ አልፈዋል የሚገርመው ግን ዛሬም ሰውን ማመን አልተውኩም

  • ብሒለ አበው ኃጢአትን አለ መሥራት እጅግ መልካም ነው ። ብትሠራ ግን ንስሐን ባትቃወም ጥሩ ነው ንስሐ ከገባህ ደግሞ ወደ ኃጢአት ባትመለስ የተሻለ ነው ወደ ኃጢአት ካልተመለሰክ ደግሞ ይህን ያደረገልህ አምላክ ማመስገን መልካም ነው ቅዱስ ባስልዮስ ነፍስ የሌለው ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ፀሎትን የማታደርግ ነፍስ ሒይወት የላትም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የማይፀልይ ሰው ቅፅር የሌላትን ሀገር ይመስላል ያን ማንም እንዲዘርፈው እርሱም የተሰጠውን ፀጋ ያጣል ማር ይስሐቅ ፀሎት ለማድረግ ወደ እግዚአብሔር ስትቀቡ ራሳችሁን እንደ አንድ አነስተኛ ጉንዳን እንደ አንድ በምድር ላይ እንደ ሚሳብ አነስተኛ ፍጥረት እንደ አንድ ደቃቅ አልቅትና እንደ አንድ ተብተባ ህፃን ቁጠር ማር ይስሐቅ መከራን በመከራነቱ ሳይሆን በመካሪነቱ ውደደው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሔር ሆይ አትተወኝ በፊትህ መልካም የሆነ ምንም ምግባር የለኝም ነገር ግን ስለ ቸርነትህ ስትል መልካምን ነገር እንዴት እንደ ምጀምረው ግለጥልኝ አባ አርሳንዮስ ዲያቆን ሳሙኤል ተመጌን ነሀሴ 3/2014 ዓ/ም ቡሌ ሆራ (ሀ/ማረያም አድራሻዎቻችን Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :- ዩቱብ https://www.youtube.com/@12Samual ቴሌግራም https://t.me/tsidq ቲክ ቶክ https://vm.tiktok.com/Z

  • ምክረ አበው የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።(መጽሐፈ ምክር) "አንደበቱን ከቧልት ያየውን ሚስጥር ከመናገር የሚከለክል ሰው ልቦናውን ከኅልዮ ኃጢአት ያርቀዋል ።(አረጋዊ መንፈሳዊ) ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እዳታጣ " (ማር ይስሃቅ) ‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ እንጦንስ/ ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል።›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/ ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/ ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ መቃርስ/ ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ አርሳንዮስ/ ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ እንድርያስ/ ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።›› /አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን/ ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/ ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/ ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።›› /ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ/ ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።›› /ቅዱስ እንጦስ/ አድራሻዎቻችን Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :- ዩቱብ https://www.youtube.com/@12Samual ቴሌግራም https://t.me/tsidq ቲክ ቶክ https://vm.tiktok.com/Z

  • የሰው ሥጋ እንደ ምን ከምድር አፈር ሊፈጠር ቻለ ከምድር አፈር ሸክላ ጡብ እንስራ ወይም ይህን የመሰለ ይገኛል እንጂ እንደ ምን የሰው ሥጋ ሊገኝ ይችላል አጥንት ነርቭ ደም ቅዳና ደም መልስ ቧንቧ  ስብ ቆዳ ጥፍር ፀጉር እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች እንደ ምን ከአንድ ምንጭ ማለትም ከምድር አፈር ሊፈጠሩ ቻሉ ሊቁ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ኦሪት ዘፍጥረት በተረጎመበት ድርሳኑ በአግራሞት የተናገረው

  • መጻሕፍትን በተሻለ መንገድ ለማንበብ እነዚህን መንገዶች ተከተሉ :- 📖 የሚስባችሁን መጽሐፍ ብቻ ምረጡ በግዴታ የማትወዱትን መጽሐፍ አትጀምሩ ። ታሪክ ፣ ስነ-ልቦና ፣ ንግድ ፣ ሃይማኖት ወይም ሌላ የሚስባችሁን ብቻ መርጣችሁ አንብቡ ። 📖 በትንሽ በትንሹ ጀምሩ በቀን ከ 5 –10 ገጽ ብታነቡ በቀጣይ ቀናት ደግሞ በእጥፍ በእጥፍ እያሳደጋችሁ ማንበብ ። በአንድ ቀን ብዙ ለማንበብ ብላችሁ ራሳችሁን አታጨናንቁ :: 📖 ምን ለማለት ፈልጎ ነው በሉ:- ማንበብ ስትጀምሩ ሐሳባችሁን "ደራሲው ምን ሊነግረኝ ፈልጎ ነው? " ፣ "ይህ ለሕይወቴ ምን ያስተምረኛል?" ብላችሁ አስቡ ። 📖 የገባችሁን ነገር ጻፉት :- የወደዳችሁትን ሐሳብ ፣ አዲስ ቃላት ወይም ትምህርት በማስታወሻ ደብተር ላይ መዝግቡት ። 📖 በየቀኑ የተወሰነ ሰዓት መድቡ :- ለምሳሌ ጠዋት 15 ደቂቃ ወይም ከመኝታ በፊት 20 ደቂቃ ። 📖 በእርጋታ አንብቡ :- በፍጥነት አንብቦ መጨረስ ሳይሆን በእርጋታ መረዳት ዋናውና መሰረታዊ ነገር ነው :: በፍጥነት አንብቦ ከማለፍ ይልቅ አንዱን ገጽ አንብቦ ለመረዳት 20 ደቂቃ ቢፈጅብህ ይሻላል :: ጃዕፈር መጻሕፍት ! የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን ! ( ምክሩን ከወደዳችሁት ለሌሎችም እንዲደርስ ለወዳጅ ዘመድዎ አጋሩልን )

  • በሥጋ ስለ ወለደችኝ እናቴ ሰዎች ከነገሩኝና ከሚነግሩኝ ውጪ ፎቶዋን እንኳን ለማየት አለ መታደሌ ብቻ ሳይሆን ስለ አሟሟተዋና ሌሎች ነገሮች ባሰብኩ ቁጥር ሁሌ ልቤ ይደማል በሕይወቴ ጎደሎነትም ይሰማኛል ግን ደግነቱ ከመስቀል ስር እግዚአብሔር ሥጦታ አድርጎ የሰጠኝ እናት ስላለችኝ በእርሷ እፅናናለሁ

  • አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ ሉቃ 23÷42

  • ሰላም ቤተሰብ በኢፖክሲ ስራ ብቅ ብለናል። ማንኛውንም አይነት የኢፖክሲ ስራዎችን ማለትም የግርግዳ ፌቶ ፤ ሰዓት ፤ ምስሎች ፤ coffee and dinning table፤ በሞልድ የሚሰሩ የቤት መገልገያዎች እንዲሁም ረከቦት በፈለጋቹት አይነት ይዘትና ቅርፅ በተጨማሪም ረከቦት እና ማዕድ ስር የሚነጠፉ ሱፍራ(ምንጣፍ) በትዕዛዝ እሰራለው። ማዘዝ የምትፈልጉ +251925503019 Elsabeth Demelash ደውሉልኝ

  • видео или голосовое, без подписи

  • በቡርኪና ፋሶ የሸሪዓ ህግ ፈጽሞ አይኖርም እኛ የምንፈልገው የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን እንጂ የሸሪዓ ምሁራንን አይደለም" — የቡርኪና ፋሶው መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ የቡርኪና ፋሶ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ካፕቴን ኢብራሂም ትራኦሬ፣ ሐሙስ ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ያስተላለፉትን ጠንከር ያለ ንግግር ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲጂታሉ ዓለም እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆነዋል። ፕሬዝዳንቱ በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ የያጋ (Yagha) ክልል ተወካዮችን ባናገሩበት ወቅት፣ ትኩረታቸውን ሀገሪቱ ባሏት ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች—ማለትም በሃይማኖት እና በትምህርት ፖሊሲ ላይ አድርገዋል። ኢብራሂም ትራኦሬ በመግለጫቸው መንግስታቸው ለሃይማኖት ብዝሃነት ፍጹም ታማኝ መሆኑንና ማንኛውንም አይነት እምነት በዜጎች ላይ በሃይል የመጫን ፍላጎት እንደሌለው አስምረውበታል። "እኔ እስላም ነኝ ነገር ግን በቡርኪና ፋሶ ያለ ማንኛውም ዜጋ የመረጠውን ሃይማኖት የመከተል ሙሉ መብት አለው። እዚህ ሀገር ውስጥ በጭራሽ የሸሪዓ ህግ አይኖርም" ሲሉ ለስብሰባው ታዳሚዎች ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም በሀገሪቱ አሁን ያለው የትምህርት ስርዓት ውጤት እና ሀገሪቱ ከምትፈልገው ተጨባጭ ልማት ጋር አለመጣጣሙን ጠቁመዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ፣ በርካታ ወጣቶች ተግባራዊ ባልሆኑ ረቂቅ ቲዎሪዎች፣ በተለይም በሃይማኖታዊ ትምህርቶች ላይ ብቻ ጊዜያቸውን እያባከኑ ይገኛሉ። በመሆኑም የሀገሪቱ የትምህርት ፖሊሲ ሙሉ በሙሉ ወደ STEM (ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ስታቲስቲክስ/ሂሳብ) እንደሚያደላና ትኩረቱ ዘመናዊ የልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት እንደሚሆን ገልጸዋል። ሀገራችንን ለመገንባት በቴክኖሎጂ እውቀት የዳበሩ ሰዎችን ነው የምንፈልገው እንጂ የሸሪዓ ምሁራንን አይደለም ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ይህ የትራኦሬ ንግግር በተለይም ለአፍሪካ አህጉር እድገት የትምህርት ስርዓት ማሻሻያ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር አስፈላጊ መሆኑን በሚያውቁ ወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን እያገኘ ይገኛል።

  • +++ የዕለት እንጀራችንን ስንቀበል የአደራውንም መስጠት አንዘንጋ +++ በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ ‹ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው› ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት :- ‹እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን አድራሹ ሰው ረስቶኛል!› መጻሕፍት እንደሚያስተምሩን "የዕለት እንጀራችንን ስጠን" የሚለው ጸሎት ለመነኮሳት ሲሆን "ለዕለት"፣ በዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሲሆን ደግሞ "ለዓመት" የሚሆን እንጀራ ስጠን ማለት ነው። ታዲያ ለምን አንዳንዶች ከዓመት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ ያጣሉ ? መቼም ‹ለሰው ፊት የማያዳላ› እግዚአብሔር "አድልዎ ቢኖርበት ነው" ብለን የድፍረት ቃል በእርሱ ላይ አንናገርም።(ሐዋ 10፡34) ይህ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙ ሰዎች ምንም የሌላቸውን እንዲረዱ እና መግቦት የባሕርይው የሆነውን አምላካቸውን በጸጋ እንዲመስሉት ነው። በዚሁም ላይ በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን የመተዛዘንና የፍቅር ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡ ‹የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ› ብለን የለመንነው አምላክ ከዓመት እንጀራችን በላይ አትርፎ የሚሰጠን፣ የሚበቃንን ያህል ተመግበን በቀረው ለሌሎች አድራሽ መልእክተኞች እንድንሆን ነው። ስለዚህ ይህን የተጣለብንን አምላካዊ አደራ ባለመወጣት ድሆችን አንበድል፤ ተማርረው ከፈጣሪያቸውም ጋር እንዲጣሉ አናድርጋቸው። የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Share ያድርጉ ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :- ዩቱብ https://www.youtube.com/@12Samual ቴሌግራም https://t.me/tsidq ቲክ ቶክ https://vm.tiktok.com/

  • ወዳጄ አፈር አፈር ነው ፣ አጽምም አጽም ነው፡፡ የነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጽም ግን ሙት የሚያስነሣ አጽም ነው፡፡ ‘’እግዚአብሔር የጻድቃንን አጥንት ይጠብቃል ፤ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም’ ተብሎ የተጻፈለት አጽም ነው፡፡ /መዝ 34፡20/ ለዚህ ነው ከሀገር ሀገር ተጉዘን መቃብራቸውን ለመሳለም የምንተጋው:: በአንድ ወቅት ሰዎች የአንድን ሰው አስከሬን በቃሬዛ ሊቀብሩ ተሸክመው ሔዱ፡፡ ወደ ቀብሩ ሲደርሱ ግን አደጋ ጣዮች ወደ ሥፍራው እንደመጡ አዩ፡፡ ‘የሞተን እንቀብራለን ብለንማ አብረን አንቀበርም’ ብለው በቃሬዛ የያዙትን አስከሬን አሽቀንጥረው ጣሉና እግሬ አውጪኝ አሉ፡፡ የተወረወረውን ሟች ለካስ የጣሉት በነቢዩ ኤልሳዕ መቃብር ላይ ነበር፡፡ ሟች የነቢዩ አጽም ያረፈበትን መቃብር ሲነካ ወዲያውኑ ከሞት ተነሣ፡፡ ምናልባትም በእኔ ግምት እሱም አሁን አጥቶ ያገኛትን ነፍሱን ከአደጋ ጣዮች ለማዳን ሮጦ ይሆናል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን የጻድቁ ኤልሳዕ አጽም ሙቱን አስነሥቷል፡፡ እሱ ሞቶ እንዴት ሙት ያስነሣል? የጠፋ ሻማ ሌላውን መለኮስ ይችላል ወይ? ካላችሁ እንግዲህ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ ነው ምን እናድርገው? /2ነገሥ 13፡21/ ይህ ነቢዩ ኤልሳዕ ታሪክ የቅዱሳን አጽም ሙት የማስነሣት ኃይል እንዳለው ሲያስረዳን በሌላ በኩል ነቢዩ ኤልሳዕ በሞቱ ሕይወትን የሰጠን የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ይኖራል፡፡ የቅዱሳን አጽም ሙት የሚያስነሣ ከሆነ ታዲያ ምነው ከጻድቃን አጠገብ የተቀበሩ ሁሉ ለምን አይነሡም? የሚል የዋህ ይኖራል፡፡ ወዳጄ መቼም ጻድቃን አሉ ተብሎ ሞት አይቀርም፡፡ ለክብራቸው መግለጫ የተፈጸመ ተአምር ነገርኩህ እንጂ ጻድቃን የተፈጥሮን ሕግ አዛብተው የሞተን ሁሉ እያስነሡ ትውልድ ያስጨንቃሉ ማለት አይደለም፡፡ እንደዚያ ቢሆን መቼም መሞቱ የሚፈለግ አጠፋምና ሲሞት እንዳይነሣ ጻድቃን የሌሉበት መቃብር እንፈልግ ይባል ነበር:: የሁሉ አስነሽ ክርስቶስ እንኩዋን በምድር በተመላለሰ ጊዜም እችላለሁ ብሎ የሞቱን ሁሉ አስነሥቶ ምድርን አላወከም፡፡ የግድ ሙት ካልተነሣ ካልከኝ ግን በል አሁኑኑ ተነሥና ወደ ሰማዕታትና ወደ ጻድቃን መቃብር ሒድ፡፡ በኃጢአት የሞተ ሕሊናህን በንስሓ ያስነሡልሃል፡፡‘ "እግዚአብሔር እኛን ወደ ቅድስና ሕይወት ለመምራት የሠጠን ቃሉን ሲሆን ሁለተኛው የቅዱሳንን አጽም ነው’ የሚለው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ቅዱሳን መቃብር እንዲህ ይላል፦ ‘‘ከየትኛውም ሥፍራ ይልቅ የሰማዕታት መቃብር የሚገኝበትን ይህንን ሥፍራ እወደዋለሁ ፡፡ ወደዚህ ሥፍራ የምመጣው ምዕመናን ለበዓል ሲሰበሰቡ ብቻ አይደለም፡፡ ለብዙ ጊዜ እመጣለሁ፡፡ ብቻዬን መጥቼም ጠቃሚ ሃሳቦችን አገኛለሁ፡፡ በዚህኛው ሕይወት አንዳችም ቋሚ ነገር እንደሌለ ፣ ደስታውንም ኀዘኑንም እንደምናልፈው ይታየኛል፡፡ በእነዚህ ነገሮች ላይ በፍጹም ደስታ ውስጥ ሆኜ ስመሰጥ ዓይኖቼ ወደ መቃብሮቹ ትክ ብለው ይመለከታሉ፡፡ ነፍሴ ደግሞ ወደ ሞቱት ሰማዕታትና አሁን እየኖሩበት ወዳለው የበረከት ሕይወት እያየች ከፍ ከፍ ትላለች’’ / On the blessed babylas ii / Encomium of the Holy great Martyr Drosida 1/ በሉ እንግዲህ በቀጣዩ ሰንበት በትሕትና ትምህርት ቤት እንገናኝ:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ታኅሣሥ 22/ 2012 ዓ ም አዲስ አበባ የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Share ያድርጉ ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :- ዩቱብ https://www.youtube.com/@12Samual ቴሌግራም https://t.me/tsidq ቲክ ቶክ https://vm.tiktok.com/Z

  • + የትሕትና ትምህርት ቤት + በዲያቆን ሄኖክ ሐይሌ በዕረፍት ጊዜያችን የምንሔድባቸው ቦታዎች እንደየዝንባሌያችን የተለያዩ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ትክክለኛ ዕረፍት የምናገኝባቸው መንፈስ የሚያረጋጉ ቦታዎች ሲሆኑ አንዳንድ ሰው ደግሞ ዕረፍት የሚነሡና ራሳቸውም ዕረፍት የሚፈልጉ ቦታዎችን ለዕረፍት ጊዜ ማሳለፊያነት ሊመርጥ ይችላል፡፡ ከወራት በፊት በአንድ አጋጣሚ የተገኘሁበትንና ከዚያን ቀን ጀምሮ ሳሰላስለው የከረምሁትን የዕረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ቦታ ላስተዋውቃችሁ፡፡ ይህ ሥፍራ ከማሳረፍ አልፎ ወደ ጥልቅ ጸጥታና ራስን መመርመር የሚመራ ቦታ ነው፡፡ እንደ ቤተ መጻሕፍት ‘ጸጥታ ይከበር’ የሚል ጽሑፍ ባይኖርበትም ፍጹም ጸጥታ የሰፈነበት ሥፍራ ነው፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ፣ አረጋውያን ፣ ሕጻናት ፣ ንግግር አዋቂዎች ፣ ባለ ሥልጣናት ፣ ወታደሮች በአንድ ላይ የሚገኙበት ሥፍራ ቢሆንም አንድም ጫጫታ የማይሰማበት ፍጹም የዕረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ሥፍራ ነው - የመቃብር ቦታ! መቼም የዕረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ያልሁት መቃብር ሥፍራ መሆኑን የሚያነብ ሰው ‘አዪ እኔ ደግሞ ደህና ነገር መስሎኝ ፤ እሱንማ በቁሜ ለምን እሔዳለሁ አንደኛዬን እደርስበት የለ? ስንት መዝናኛ እያለ መቃብር ምን አስኬደኝ? መቃብር ቦታ ዕረፍት አገኛለሁ ብዬ መጋኛ ቢያጠናፍረኝስ? ጉንዳን መጫወቻ ቢያደርገኝስ?’’ የሚል አይጠፋም፡፡ በጣም ጥቂቶች ካልሆኑ በቀር አብዛኞቹ የሀገራችን የመቃብር ሥፍራዎችም ብዙም በንጽሕና ያልተያዙ መሆናቸውን በማሰብም ቢሆን ይህንን ዕቅድ ውድቅ የሚያደርግም አይጠፋም፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን በሕይወት ላለ ሰው ሁሉ እጅግ ድንቅ የዕረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ሥፍራ ቢኖር የመቃብር ቦታ ነው፡፡ ለሃይማኖተኞች የጥልቅ ተመሥጦ ፣ ለፍልስፍና ተማሪዎች ቤተ መጻሕፍት ፣ ለሥነ ጽሑፍ ሙያተኞች የድርሰት መፍለቂያ የሆነ የሕይወት ትርጉም የሚጎላበት ውስጥን ጸጥ የሚያደርግ ሥፍራ የመቃብር ቦታ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ወደ መቃብር ሥፍራ የምንሔደው ወዳጅ ዘመድ ለመቅበርና ሐውልት ለመመረቅ ሲሆን ሔደንም በፍጥነት ከዚያ ሥፍራ ለመውጣት እንቻኮላለን፡፡ ቀጠሮ ይዘን ግን ወደ መቃብር ሥፍራ አንሔድም፡፡ ሆኖም ቀን በንጽሕና ተይዞ ሰዎች ሊያርፉበት : ተማሪዎች ሊያጠኑበት : ነፋስ ሊቀበሉበትና መናፈሻ ሊያደርጉት የሚገባ በከተማ ጽዳትና ውበት ፕሮጀክት ውስጥ መካተት የሚገባው እጅግ ሰላማዊ ሥፍራ መቃብር ነው:: የመቃብር ሥፍራ መግቢያው በር ቢኖረውና የእንኳን ደህና መጡ መልእክት እንዲህ ተብሎ ቢጻፍ ጥሩ ነበር፦ ‘’ወደ ትሕትና ትምህርት ቤት እንኳን ደህና መጡ!’’ ‘‘ደሃና ሀብታምን አንድ ወደሚያደርገው ሥፍራ እንኳን ደህና መጡ!’’ ‘‘ብዙ መልከ መልካሞች እንደ ሣር ወደ ደረቁበት ሥፍራ እንኳን ደህና መጡ! ‘‘ብዙ ኃያላን ወደ ወደቁበት ፣ ብዙ ተናጋሪዎች ጸጥ ወዳሉበት ሥፍራ እንኳን ደህና መጡ!’’ ወዘተ የመቃብር ሥፍራን ‘የትሕትና ትምህርት ቤት’ ብሎ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል ፦ ‘ወደ መቃብር ሥፍራ በመመልከት ብዙ መንፈሳዊ ጥቅሞችን እናገኛለን፡፡ በዚህ እይታ ምክንያት ንዝህላልና ቸልተኛ የሆነች ነፍሳችን ወደ ትሕትናና ጸጸት ትመለሳለች ፤ ትጉሕና ፈጣሪዋን የምትሻ ነፍስ ደግሞ የበለጠ የምትተጋና መሻትዋ የሚጨምር ትሆናለች፡፡ በድህነት የሚሰቃይ ሰው ወደ መቃብር ሲመለከት ይጽናናል፡፡በሀብቱ የሚኮራ ሰው ደግሞ ትሑት ይሆናል፡፡ መቃብሮችን ማየት ማንኛውንም ሰው ሳይፈልግ እንኳን ስለራሱ ሞት እንዲመራመር ያደርገዋል፡፡ ደስታንም ሆነ ኀዘንን ዘላቂ አድርጎ እንዳይመለከት ያደርገዋል፡፡ወደ መቃብሮች መመልከት ወደድንም ጠላንም ለራሳችን ፍጻሜ እንድንዘጋጅ ይገፋፋናል’’ {Encomium of the Holy great Martyr Drosida 1} በእርግጥም ወደ መቃብር ሥፍራ የመጣህ እንደሆነ ሳታስበው ውስጥህ ጸጥ ይላል፡፡ ስለ ሕይወት ፍልስፍና ውስጥ ትገባለህ ፤ ‘መጨረሻዬ ይሄ ነው ለካ? ለዚህ ነው እንዲህ የምጨነቀው?’ ብለህ ራስህን ትታዘባለህ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ይላል ፦ ‘በሥጋ እስካለን ድረስ እስቲ ወደ መቃብሮች ሥፍራ እንሒድ፡፡ ከንቱ ሃሳቦቻችን ሁሉ መዳረሻቸው የት እንደሆነ ሔደን እንመልከት፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምን እንደምንሆን እስቲ ሔደን እንመልከት፡፡ አንታለል ይልቅስ ፍጻሜያችን እንዴት እንደሆነ እንመልከት፡፡ የት እንደሚያበቃልን አይተን ራሳችንን እናስተካክል’’ /On Patience and On Not weeping bitterly over the dead. Pg 60/ ምድር ላይ ለሥልጣን የሚፋጩ ፣ ለስንዝር መሬት የሚጋጩ ፣ ለዝና ለሀብት ብለው በባልንጀራቸው ላይ ግፍ የሚሠሩ ወይም ግፍ ተሠራብኝ ብለው የሚማረሩ ሁሉ መጨረሻቸው መቃብር ነው፡፡ እንደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ባሉ መቃብራት ብትሔዱ ከሞት ቢነሡ ዱላ የሚማዘዙ ጠላቶች በአንድ ቅጽር ተኝተዋል፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ ይገልጻቸዋል፦ ‘ፖለቲካዊ ሥልጣን የነበራቸው ሰዎች የትኞቹ ናቸው? ወደር ያልተገኘላቸው አንደበተ ርቱዐን ተናጋሪዎችስ ወዴት አሉ? የጦር መሪዎች ፣ ሀገረ ገዢዎችና ፣ አምባገነኖች ወዴት ናቸው? ሁሉም ወደ ትቢያ ተለወጡ አይደለምን? የሕይወት ዘመናቸው ማስታወሻ የአጥንቶቻቸው ቅሪተ አካል አይደለምን? ጎንበስ በሉና መቃብሮችን ፈትሹ ፣ ማን ጌታ ማን ባሪያ ፣ ማን ደሃ ማን ሀብታም ፣ እንደሆነ ለመለየት ሞክሩ፡፡ ከቻላችሁ ምርኮኛና እስረኛውን ከንጉሡ ፣ ኃያሉን ከደካማው ፣ ውቡን ከመልከ ጥፉው ለይታችሁ አውጡ፡፡ የሁላችንም ተፈጥሮ መጨረሻ አንድ መሆኑን ስታስቡ ያን ጊዜ መመካትና መታበያችሁ ይቆማል’ St Basil the great On Guard Thyself 5 የመቃብር ሥፍራ ለሚጎበኘው ሰው የትዕቢት ማስተንፈሻ የትሕትና ትምህርት ቤት ነው፡፡ ‘‘አንተ ሰው ሆይ ስለምን ተኮፍሰሃል? ስለምንስ በራስህ ትኩራራለህ? ወደ መቃብር አብረን እንሒድና ምሥጢራትን እንመልከት፡፡ ምንም ያህል ጠቢብና አዋቂ ብትሆንም ወደ መቃብር እንሒድና እንጎብኝ! በዚያም የትኛው ሬሳ ንጉሥ ፣ የትኛው ተራ ዜጋ ፤ የትኛው የመኳንንት ወገን ፣ የትኛው ባሪያ ፣ የትኛው አዋቂ ፣ የትኛው አላዋቂ እንደሆነ ለይተህ ታሳየኛለህ!’’ ይላል አፈወርቅ /On Repentance Homily 9/ እርግጥ ነው ውዳሴ ከንቱ ሞተውም የማይለቃቸው ሰዎች ከቤታቸው የሚበልጥ መቃብር ሊያሠሩ ይችላሉ፡፡ ውስጡ ተከፍቶ ቢታይ ግን አፈር ይሆናሉ፡፡ በእውቀት ፣ በሀብት ፣ በዘር ፣ በነገድ ለምንመካ ሰዎች ሁሉ መቃብር ሁላችንን አንድ ያደርገናል፡፡ በብሔር ተከፋፍለህ ይህ መሬት የእኛ ነው ብለህ ስትጣላ ብትውል መቃብር ግን ብሔር ሳትለይ ትውጥሃለች፡፡ ምስጦችም ወገን ሳይለዩ ይበሉሃል፡፡ ለእነርሱ ዘርህ ፣ እውቀትህ ፣ ሀብትህ ፣ ውበትህ አይታያቸውም፡፡ አፈር አፈር ነው፡፡ ከመቃብር ሁሉ የሚበልጠው ትልቁ መቃብር ግን የቅዱሳንና የሰማዕታት መቃብር ነው፡፡ በምድር የከበሩ ፣ ብዙ ዝናና ስም ያላቸው ሰዎች መቃብራቸው ብዙ አበባ ይቀመጥለታል ፣ ሰው ፎቶ ያነሣዋል ከዛ ግን አያልፍም፡፡ የቅዱሳን ሰዎች መቃብር ግን እጅግ የከበረ ነው፡፡ ለዚህ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሰው ‘በሞትሁ ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው በተቀበረበት መቃብር ቅበሩኝ አጥንቶቼንም በአጥንቶቹ አጠገብ አኑሩ’ ብሎ የተናዘዘው፡፡ /1ነገሥ 13፡31/

  • “አንኳኩቼ አላገኘሁም” አትበል፡፡ ብቻ የለመንከው፣ ደጅ የጠናኸው አንተ የምትወደው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚወድልህ ይሁን፡፡ ወደ እግዚአብሔር የተዘረጋ እጅ ፈጽሞ ባዶውን አይመለስም፡፡ ስለዚህ ራስህን፣ ልመናህን ምን ዓይነት እንደሆነ ፈትሽ እንጂ አንኳኩቼ አላገኘሁም አትበል፡፡ እንኳንስ ንጹሐ ባሕርይ የሆነው እግዚአብሔር ክፋት የሚስማማው ምድራዊ አባትም ለልጁ ጀሮውን አይደፍንም፡፡ አስቀድሞ ሕያዊት ነፍስን “እፍ” ብሎ እንዲሁ የሰጠን ጌታ፣ ኋላም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጁን ሳይራራ ከሰጠን እንደምን በዚህ ይታማል? እንደምንስ አይሰጠንም እንላለን? /ሮሜ.8፥32/፡፡ ልጁን የሰጠው እኮ ጭራሽ “ስጠን” ብለው ላልለመኑ አሕዛብም ጭምር ነው፡፡ ታድያ እንዲህ የምንለምን እኛማ እንዴት አብልጦ አይሰጠንም? የሚበልጠውን ሰጥቶን ሳለስ እንደምን ትንሹን አይሰጠንም እንላለን? ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀውን ሳናደርግ “እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማም” የሚል የሰነፎች አባባል የምንናገር አንሁን፡፡ ጆሮን የፈጠረ ይሰማል!” ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ https://t.me/tsidq

  • አንድ ሰዉ እጁን ወደ እግዚአብሔር አነሳና ጌታሆይ ‎ተመልከት እጇቼ ንፁሆች ናቸዉ  :: ‎አልሰረኩም ፤አልገደልኩም  አለ ‎እግዚአብሔርም አዎ ልጄ እጇችህ ንፁሆች ናቸዉ ‎ምንም ሀጢአት አልሰሩም  ነገር ግን ባዶ ናቸዉ ‎አልሰረቅህም ነገር ግን አልመፀወትክም ‎አልገደልክም ነገር ግን የተቸገር አረዳህም አለዉ :: ‎እናም እግዚአብሔር ‎ከኛ የሚፈልገዉ  መጥፎ ነገር አለማድረጋችንን ብቻ ሳይሆን ‎መልካም ነገር ማደረጋችንንም ይፈልጋል :: ‎እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው። ‎የያዕቆብ መልእክት 4 : 17 ‎ ‎ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :- ‎ዩቱብ ‎https://www.youtube.com/@12Samual ‎ ‎ቴሌግራም ‎https://t.me/tsidq ‎ ‎ቲክ ቶክ ‎https://vm.tiktok.com/Z ‎

  • ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም ! | በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር! "ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ብትሄድ እኮ ድካምህ ይቀንስልህ አልነበር?" ሲል ጠየቀው:: ሕጻኑም ሲመልስ እንዲህ አለ:- "ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም" አለው:: ያን ጊዜ ጥያቄውን ያቀረበው ወታደር ራሱን መቆጣጠር አልቻለም ... ስሜቱ በጣም ተነካ ... ዓይኖቹ በዕንባ ታጠቡ:: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጃፓን ይህ ምስል ... የወንድማማችነት፣ የአንድነት ተምሳሌት ሆነ:: እናም ... የሕይወት መርሃችን እንዲህ ቢሆንስ:- ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም ! እህቴ ናት እኔን አትከብደኝም ! ወንድምህ ቢወድቅ አንሳው ! እህትህ ብትደክም ከጉኗ ቁም ! ወንድምህ ቢስት በየውሃት መንፈስ አቅናው ! እህትህ ስህተት ብትሰራ ይቅርታህን አትንፈጋት ።

  • ወንድምህን_አትናቀው" ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል ። "እንዴት"? ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ሆኗልና። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እሱን ናቅከው ማለት ክርስቶስን ናቅከው ማለት ነው። ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም ። ስለዚህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ ። ከቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ) ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :- ዩቱብ https://www.youtube.com/@12Samual ቴሌግራም https://t.me/tsidq ቲክ ቶክ https://vm.tiktok.com/Z

  • ከእለታት ባንዱ ቀን አንድ ታዳጊ አባቱን “የህይወት ዋጋው ስንት ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡ አባትም መልስ በመስጠት ፈንታ ልጁን እንዲህ ሲል አዘዘው፡፡ “እንካ ይህንን የድንጋይ ቁራጭ...ወደ ገበያ ውሰደው"ሰዎችም ዋጋውን ከጠየቁህ በጣቶችህ ሁለት ቁጥርን ብቻ አሳያቸው እንጂ ምንም አትናገር” አለው፡፡ ልጁም ድንጋዩን ወሰደ፡፡ ወጥቶም በገበያ መሃል ቆመ፡፡ አንዲት ሴትም መጣች፡፡ “ይህ ድንጋይ ዋጋው ስንት ነው? ብትሸጥልኝ ወስጄ ግቢዬ ውስጥ አስቀምጠዋለሁ” አለችው፡፡ ልጁም እንደታዘዘው ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳያት፡፡እሷም አለች "ሁለት ብር? እወስደዋለሁ!!” ልጁም ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ በገበያ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡ አባትየውም አለው “አሁን ደግሞ ድንጋዩን ይዘህ ወደ ሙዚየም ሂድ ዋጋውን ሲጠይቁህም ሁለት ጣቶችህን አሳይ” ልጁም ወደ ሙዚየም ወጣ፡፡ ገዢም መጥቶ ዋጋ በጠየቀው ጊዜ ሁለት ጣቶቹን አሳየው፡፡ ገዢውም “ሁለት መቶ ብር? እወስደዋለሁ!” አለው፡፡ ልጁም በድንጋጤ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡ አባትየውም ተናገረ፡፡ “አሁን ደግሞ በመጨረሻ ድንጋዩን ይዘህ ወደ የከበሩ ማዕድናት መሸጫ ሂድ ለባለቤቱም አሳየው” አለው፡፡ ልጁም ሄደ ለሱቁም ባለቤት አሳየው፡፡ የሱቁ ባለቤት በመገረም “ይህ እኮ ዓለም ላይ እጅግ ውድ ከሆኑ የከበሩ ድንጋዮች አንዱ ነው” አለ፡፡ “ከየት አገኘኸው? ስንትስ ትሸጠዋለህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳየ፡፡የሱቁም ባለቤት አለ.... “ይህንን ድንጋይ በሁለት መቶ ሺህ ብር እወስደዋለሁ፡፡” ልጁም በመገረም እየሮጠ ወደ ቤቱ ተመልሶ ያጋጠመውን ለአባቱ ነገረው፡፡አባትየውም “ልጄ አሁን የህይወትህ ዋጋ ተገልጦልሃል” አለው፡፡አየህ የመጣህበት ቦታ፣ ዘርህ፣ ሃይማኖትህ፣ የቤተሰቦችህ ሃብት፣ የተወለድክበት ቦታ ልዩነት አይፈጥርም፡፡ ዋናው ራስህን የምታስቀምጥበት ቦታ፣ ራስህን የምታገኝበት የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ልዩነቱ ያለው ራስህን ለመሸከም በምትመርጥበት መንገድ ነው፡፡ ህይወትህን ሙሉ የሁለት ብር ድንጋይ ዋጋ ስትሰጠው ኖረህ ይሆናል፡፡ ህይወትህን ሙሉ የኖርከው ዋጋህ ሁለት ብር ብቻ እንደሆነ በሚያስቡ ሰዎች ተከበህ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ውድ የሆነ የከበረ ድንጋይ በውስጡ ይዟል፡፡"

  • видео или голосовое, без подписи

ደብረ ዘይት ሚዲያ — tgindex