tgindex
"ኦርቶዶክሳዊ ህይወት (Orthodox Life)

"ኦርቶዶክሳዊ ህይወት (Orthodox Life)

Статистика
@Gabrielson_19английский

““አቤቱ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ።” — መዝሙር 9፥1 Face book➥ https://www.facebook.com/share/1A9Keo2sQ4/ Telegram ➥ https://t.me/Gabrielson_19 Threads ➥ https://www.threads.com/@ashu_gabrielson

Последний пост
17:58
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
15
Всего постов
37
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
669
−2 за 3 дн.
Сутки
−1
−0,15%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
91
33 постов
Вовлечённость
13,6%
к подписчикам
Постов в день
2,1
всего 37
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
81
1/48двое суток
92
1/72трое суток
100

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ‹‹ነሐሴ 7›› በዚህች ዕለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተፀነሰች። ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱና የመጀመሪያው መታሰቢያ ነው። የእመቤታችን ወላጆች ቅዱሳን ኢያቄምና ሃና ይባላሉ። እነዚህ ቅዱሳን በትዳር አንድ ሆነው ሲኖሩ ልጅ አልነበራቸውም። ስለዚህም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሄደው በታላቅ ሐዘን እግዚአብሔርን ይለምኑ ነበር። ኢያቄም፦ «አቤቱ ጌታዬ፣ ጸሎቴን ስማኝ፤ ለዓይኔ ማረፊያና ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ልጅ ስጠኝ» ብሎ ለመነ። ሃናም፦ «አቤቱ ጌታዬ፣ ስማኝ፤ የማኅፀኔን ፍሬ ስጠኝ፤ የተባረከች ሴት ልጅ ከሰጠኸኝ ለአንተ አገልግሎት እሰጣታለሁ» ብላ በልቧ አጥብቃ ጸለየች። ከዚያም ሃና ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ፣ «ለዚህች እንስሳ ልጆችን የሰጠህ አምላክ ሆይ፣ ምነው ለእኔ ልጅ ነሳኸኝ?» ብላ በሐዘን አለቀሰች። ኢያቄምና ሃናም ወደ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ሄደው፣ እግዚአብሔር ልጅ ቢሰጣቸው ለቤተ እግዚአብሔር እንደሚሰጡት ስዕለት ገቡ። ዘካርያስም፦ «እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ፤ ስዕለታችሁንም ይቀበልላችሁ» ብሎ አሳረገላቸው። በዚያም ሌሊት ሁለቱም ድንቅ ራእይ አዩ። ኢያቄም ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይ የወረደ ነጭ ወፍ በራሱ ላይ ሲቀመጥ አየ። ሃናም ነጭ ርግብ መጥታ በራሷ ላይ ወርዳ ወደ ማኅፀኗ ስትገባ እንዳየች ነገረችው። ይህንን ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ቀን ነበር። በኋላም በፈቃደ እግዚአብሔር የሚመጣውን ተስፋ በመጠባበቅ ለሰባት ቀናት በየብቻቸው ቆዩ። በሰባተኛው ቀን፣ ነሐሴ 7 ቀን፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ እና በመልአክ ብሥራት፣ ከሰው የበለጠች፣ ከመላእክትም የከበረች ቅድስት ድንግል ማርያም ተፀነሰች። የእመቤታችን መፀነስ የድኅነታችን ታላቅ ተስፋ መጀመሪያ ነው። እርሷም ከዚያ በኋላ የዓለምን መድኃኒት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ወልዳለችና። ምልጃዋና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን! https://t.me/Gabrielson_19

  • "ነገ ነሐሴ 7 ፀንሰታ ለማርያም እንኳን ለእናታችን ለድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ምልጃ በረከቷ አይለየን🙏⛪❤ https://t.me/Gabrielson_19

  • በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ 'ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው' ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 'እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን አድራሹ ሰው ረስቶኛል!' መጻሕፍት እንደሚያስተምሩን "የዕለት እንጀራችንን ስጠን" የሚለው ጸሎት ለመነኮሳት ሲሆን "ለዕለት"፣ በዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሲሆን ደግሞ "ለዓመት" የሚሆን እንጀራ ስጠን ማለት ነው። ታዲያ ለምን አንዳንዶች ከዓመት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ ያጣሉ ? መቼም 'ለሰው ፊት የማያዳላ' እግዚአብሔር "አድልዎ ቢኖርበት ነው" ብለን የድፍረት ቃል በእርሱ ላይ አንናገርም። (ሐዋ 10፥34) ይህ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙ ሰዎች ምንም የሌላቸውን እንዲረዱ እና መግቦት የባሕርይው የሆነውን አምላካቸውን በጸጋ እንዲመስሉት ነው። በዚሁም ላይ በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን የመተዛዘንና የፍቅር ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡ 'የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ' ብለን የለመንነው አምላክ ከዓመት እንጀራችን በላይ አትርፎ የሚሰጠን፣ የሚበቃንን ያህል ተመግበን በቀረው ለሌሎች አድራሽ መልእክተኞች እንድንሆን ነው። ስለዚህ ይህን የተጣለብንን አምላካዊ አደራ ባለመወጣት ድሆችን አንበድል፤ ተማርረው ከፈጣሪያቸውም ጋር እንዲጣሉ አናድርጋቸው። (ዲያቆን አቤል ካሳሁን) https://t.me/Gabrielson_19

  • በድካምህ አትዘናጋ! ሰውነት ደካማ ነው። የሆነ ጊዜ ሃይሉን ያጣል፣ የቀደመ ተነሳሽነቱ ይመክናል፣ እንደ በፊቱ መነቃቃትና ጠንክሮ መስራት ይሳነዋል። ይሔ ተፈጥሮ ነውና ምንም ብታደርግ ልትቀይረው አትችልም። ነገር ግን መቀየር የምትችለው አንድ ነገር ይኖራል እርሱም በሁነቱ መዘናጋት ማቆም ነው። ለድካምህ እጅ አትስጥ፣ በድብርት አትሸበር፣ በዝለት ውስጥህን አታውክ። ምርጫው የአንተ ነው። ማንም የማይደክም የለም ድካሙን ውጦ፣ ዝለቱን ችሎ፣ ድብርቱን ጥሎ የሚያልፍ ግን በጣም ጥቂት ነው። ወደኋላ መመለስ፣ ራስን ማደስ፣ ስሜትን ማስተካከል የብስለት እንጂ የሞኝነት ምልክት አይደለም። በደከመህ ሰዓት ራስህን ጫና ውስጥ አትክተት ፋታ ውሰድ፣ ራስህን ዳግም አንፅ እንደገናም ወደ ጀመርከው መንገድ ተመለስ። ሁሌም የሚከተሉህ ነገሮች አሉ። እነርሱም የሚረብሹህ ነገሮች ናቸው። አያስፈልጉህም ነገር ግን እንደሚያስፈልጉህ ሌት ከቀን ይከተሉሃል፤ አይጠቅሙህም ነገር ግን ሁሌም እንደሚጠቅሙህ እንድታምን ያደርጉሃል። በሂደት ስሜትህን ያውኩታል፣ ተነሳሽነትህን ይገድሉታል፣ የሃሳብ ውቂያኖስ ውስጥ ይከቱሃል፣ ድካምና ዝለት እንዲቆጣጠሩህ ያደርጉሃል። አዎ! ጀግናዬ..! በድካምህ አትዘናጋ፣ ለዝለትህ አትበገር። ሲመጣ ዘላለም የሚደክምህ ይመስልሃል፣ ስትገናኙ እንደሚቆጣጠርህ ሊያሳይህ ይጥራል። በእርግጥ ግን ያላንተ ፍቃድ እርሱ ምንም አቅም የለውም። የሆነ ጊዜ ሊሰብርህ ይችላል ነገር ግን ሁሌም ሊሰብርህ አይችልም፤ የሆነ ጊዜ ስሜትህን ሊያውከው ይችላል ነገር ግን ሁሌም ሊያውከው አይችልም። ለቀጣዩ ከፍታህ አሁን ዝቅ ማለትህን አትፍራ። ነገሮች በትናንቱ መንገድ አይቀጥሉም። ማግኘት ማጣት፣ መውደቅ መነሳት፣ ማትረፍ መክሰር ያለና የሚኖር ነገር ነው። ተሰብሮ መቅረትን በፍጹም ምርጫህ አታድርግ፣ ለውጣውረዱ መሸነፍን መቼም ምርጫህ አታድርግ። ብርቱ ጦረኞች ተዋግተው እስኪያሸንፉ አያቆሙም፤ ጠንካራ ሰራተኞች የሚፈልጉትን እስኪያገኙ ወደኋላ አይመለሱም። ያንተ ጦርነት ከህይወት ፈተና ጋር ነው፤ ያንተ ግብግብ ከስሜት ውጣውረድህ ጋር ነው። ሳታሸንፍ የሚያቆም ጥረት አይኖርም፤ አላማህን ሳታሳካ የሚታጠፍ እጅ የለም። ፍረሃት ሊያስርህ ቢፈልግ አሻፈረኝ ትለዋለህ፣ ጭንቀት አቅም ሊያሳጣህ ቢሞክር አቅምህን ታሳየዋለህ። አዎ! ከጫናዎች ብዛት ትወድቅ ይሆናል ነገር ግን ዳግም ትነሳለህ፣ በድካምህ ምክንያት ስሜትህ ይረበሽ ይሆናል ነገር ግን እነደገና ወደ ትክክለኛው መንገድ ታገኘዋለህ። ያንተን ምርጫ ብዙዎች አይመርጡትም ምክንያቱም ምርጫህ እጅግ ከባድ ነውና፤ ባንተ መንገድ ብዙዎች አይጓዙበትም ምክንያቱም ምቾት የለውምና። ዝቅ መደረግ ብርቅህ አይደለም፤ በሰዎች እይታ ትንሽ መምሰል አዲስህ አይደለም። የግል ህይወትህ ተቆጣጣሪ አንተ ነህ። ዓለም ቢያብርብህ፣ ሰው ሁሉ በተቃራኒህ ቢቆም ከእውነተኛው ማንነትህ ጋር ከተሰለፍክ ማንም ሊያንቀሳቅስህ አይችልም። አቅም አለህና አቅምህን አውጥተህ ተጠቀም፤ ችሎታው አለህና ለውጤት አብቃው። አውቀቱ አለህ እርሱንም ከጊዜያዊ ሙቀት በላይ ለዘላቂው ውጤት ተጠቀመው። ብዙ ሰው የማያየውን በውስጥህ መመልከት ትችላለህ፣ ብዙዎች የተሰናከሉበት ጊዜያዊ ድካምና ድብርት አያቆምህም። አንተ ስትበረታ ፈተናው ጉልበት ያጣል፣ አንተ ስራህን ስትመርጥ የናቁህ ያፍራሉ። ስራህን ወጥረህ ስራ፣ ለምርጫህ እንደምትገባ አስመስክር፣ እንቅፋቶችህን ሁሉ ጥለህ ማለፍ እንደምትችል አሳይ። ወደ ቅዳሴ 😊 https://t.me/Gabrielson_19

  • ........ እኅቴ ዲያቆን ስላገባሽ ራስሽ ላይ የምትጨምሪው ጽድቅ የለም። አንቺ ዲያቆን ብታገቢ ምእመን ካገባችዋ የበለጠ ክብርን የምትቀዳጂ መስሎሽ ከኾነ ተሳስተሻል። "ዲያቆን ማግባት ጽድቅ ይጨምራል" የሚል ዲያቆን ካገኘሽ ሚስት የጠረረበት ሊኾን ይችላል። ካህን ከምእመኑ በተሻለ ሰፊ የኾነ የአገልግሎት ድርሻ አለው። ነገር ግን እግዚአብሔር ፊት ባላቸው ክብር ከኾነ ምእመኑ ካህኑን በልጦ ሊገኝም ላይገኝም ይችላል። ሥልጣነ ክህነት የሌላቸው እልፍ አእላፍ ወትእልፊት የሚኾኑ ቅዱሳኖች አሉን {ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ቅዱስ መርቆሬዎስ... ኹሉ ሥልጣነ ክህነት የላቸውም}። የቤተ ክርስቲያኒቱ ኅልውና እንዲቀጥል ሥልጣነ ክህነት ግድ ስለኾነ ካህናት ያስፈልጉናል። ግን ለዚህ ዐይነቱ ነገር አይደለም። እኅቴ ዲያቆን ስላላገባሽ ያጣሽው ነገር የለም። አይዞሽ። ዲያቆናት ከሳትኩ አረሙኝ 😊 https://t.me/Gabrielson_19

  • አስቸጋሪ ጊዜን ያሳለፉ ሰዎች የዝምተኛነታቸውን ጥንካሬ ፈጽሞ አቅልለህ አትመልከተው። ያሳለፉትን ትግል በቃላት ላይገልጹት ይችላሉ፤ ነገር ግን የደረሰባቸው እያንዳንዱ ጠባሳ ጠንካራና ጽኑ አድርጓቸዋል። ሕይወት ሊሰብራቸው ሲሞክር በጽናት መቆምን፣ የሚመራቸው ሰው ባይኖርም ወደፊት መራመድን፣ እንዲሁም በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ጊዜያትም እንኳ ተስፋ አለመቁረጥን ተምረዋል። ​​ዝምታቸው የደካማነት ምልክት አይደለም፤ ይልቁንም ህመምን የተቋቋመ፣ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ራሱን የገነባ እና ከእያንዳንዱ ፈተና ከበፊቱ በበለጠ ጥንካሬ የወጣ ሰው ጥበብ ነው። ብዙውን ጊዜ እጅግ ጠንካራ ልብ ያላቸው ሰዎች ብዙ መከራን ያሳለፉ፣ ሆኖም ግን እያንዳንዱን ቀን በፍቅር፣ በርህራሄ እና በድፍረት ለመኖር የሚመርጡ ናቸው። https://t.me/Gabrielson_19

  • + ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል + ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል::  ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ  ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!" ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::  ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5) ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር:: ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር:: ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም:: "በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23) እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ:: ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን? ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል:: እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል  የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው:: የዐቢይ ጾም የወንጌል ምንባብ ስለ ዲያቢሎስ ፈተና ሦስቱ ወንጌላት የተናገሩትን ስናስተውል ሦስት ዓይነት ጥቅሶች እናገኛለን:: አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። (ሉቃ 4:2) በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ (ማር 1:13) የሚሉት ቃላት ጌታችን ዐርባውንም ቀን መፈተኑን ያሳያሉ:: አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ እንዲህ አለው (ማቴ 4:2) የሚለው ደግሞ ከጾሙ በኁዋላ የቀረቡለትን ሦስት ፈተናዎች የሚያሳይ ነው:: ሦስተኛው ጥቅስ ደግሞ ከተፈተነ በኁዋላ ያለው ሲሆን ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ። (ሉቃ 4:13) ይላል:: ዲያቢሎስ ፈተናውን ቢጨርስም የሚተወው ለጊዜው እንጂ መፈተኑን አያቆምም::  የዲያቢሎስ ፈተና ስልቱ ይቀያየራል እንጂ ይቀጥላል:: ዐቢይ ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በዐቢይ ጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: ከነስሙ ሁዳዴ (ሰፊ እርሻዬ) የምንለው ይህ ጾም ለነፍሳችን ብዙ ዘር የምንዘራበት አጋንንት መድረሻ የሚያጡበት ጾም ነው:: በዐቢይ ጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በዐቢይ ጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም:: ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የካቲት 15 2012 ዓ ም ዝዋይ ኢትዮጵያ Deacon Henok Haile https://t.me/Gabrielson_19

  • የአንቺን ቁመት፣ ወርድ፣ ርዝመትና ጥልቀት ማን ዲካውን ያገኘዋል። እንደኛው በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት እንዳንወስንሽ ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ ለሚባልለት ምሉዕ በኩለሄ እግዚአብሔር ማደሪያ ኾነሽዋል። ሊቃውንቱ መግለጫ ቢያጡ ዳግማዊት ሰማይ ይሉሻል። የሰማዮች ሰማይ የማይወስኑት ግን አንቺን መቅደስ አድርጎሻልና ይኽም አይመጥንሽም። ከሰማዮች ትሰፊያለሽ፣ ከውቅያኖሶችም ትጠልቂያለሽ፣ እንደ ጽርሐ አርያም ትርቂያለሽ። እመቤታችን በእውነት ትለያለሽ!!! https://t.me/Gabrielson_19 አማላጅቱ ሆይ እንወድሻለን።

  • ~ሚስትህን ፍታት!~ ✍️.የጽሑፌ ዓላማ በጾመ ፍስለታ ባል ሚስቱን እንዲፈታ ሚስትም ባሏን እንድትፈታ ባልና ሚስት በጭቅጭቅ ከሚኖሩ እንዲፋቱ የሚል ነው። ለምን? ካላችሁኝ ሙሉውን አንብባችሁ በዓላማ ሞግቱኝ። ✍️. ​ትዳር ማለት የሴትና የወንድ ተራ ህብረት ወይም የውል ስምምነት በሁለቱ ፈቃድ የሚመሰረትና የሚፈርስ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው። 👏 ትዳር የሁለት ነፍሳት አንድ መሆን ነው።አንድነቱም የፍቅር፣ የክብር፣ የነፃነት ፣ የጋራ እድገት፣የገራ ሀሳብና ኑሮን የመጋራትና በነገር ሁሉ ከሁለት አንድ የመሆን ምሥጢር ነው። ✍️ ትዳር የተመሰረተው ሰውን ከአካላዊና መንፈሳዊ ባዶነት ለማውጣት («ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም» - ዘፍ 2፥18)የሚለውን ቃል ለመፈጸም ነው። 👏፣ትዳር ሁለቱ ሰዎች(ባልና ሚስት) እርስ በርስ እየተደጋገፉ ወደ ተሻለ እድገትና ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲደርሱ የሚያደርግ ጥበብና ምሥጢር ነው። ✍️የትዳር መሰረታዊው ዓላማና ጥቅም በፍቅር የተሞላ ሕይወትን መመስረትና መምራት፣ የሰላም ወደብ መሆንና የትውልድ ማስቀጠያ መንገድም መሆን ነው። 👏​በትዳር ውስጥ እንዴት መኖር ይገባል ካላችሀኝ? በመከባበር፣ በመደጋገፍ፣ እና የራስን እየረሱ ለሌላው(ባል ለሚስቱ ሚስትም ለባሏ) መስዋዕት በመሆን ነው። ✍️ፍቅር ስሜት ብቻ ሳይሆን በየቀኑ የሚደረግ ንቁ ውሳኔ ነው። ሚስትህን ልታኖራት፣ ልታከብራት፣ የነፍሷን ጥያቄ ልትመልስላት የዘወትር ህልሟን ልታደርግላት ይገባል።አንቺም ባልሽን እንደዚሁ! ​👏እንዲህ ካልኖርክና ካላኖርካት... ሚስትህ ላይ «የነገር ቋንጣ የምትሰቅል» ከሆነ፣ ሁልጊዜ በትንሽ ትልቁ የምትነዛነዛት፣ የምትጨቃጨቃት፣ ሰላሟን የምትነሳት ከሆነ—ፍታት! ✍️ ​አዎ፣ ፍታት! ፍታት ስልህ ግን ከሕግ ቤት ሂደህ የጋብቻ ወረቀቱን በጣጥሰው የተክሊልህንና የቁርባንህንም ምሥጢር አዋርደው እያልኩህ አይደለም። «ፍታት» ስልህ፦ 👏​❶.በውስጥህ የቋጠርካትን የቂም ቋጠሮ ፍታት! በየቀኑ የተከማቸውን የቆየ ቁስል፣ ያለፈ ጥፋትን እና የውስጥ ጥላቻን ልብህ ውስጥ ከታሰረበት የጨለማ ክፍል ፈትተህ አውጣው። ቂም ባለበት ቦታ ፍቅር ማደር አይችልም እያልኩህ ነው። ✍️❷.​ከጥላቻና ከፉክክር ቀጠሮህ ፍታት! ትዳር የጦር ሜዳ ወይም ማን አሸነፈ የሚባልበት የመድረክ ውድድር አይደለም። ከእሷ ጋር የምታደርገውን የፍጥጫ፣ የብልጫ እና የፉክክር መንፈስ ፈትተህ ጣለው። እሷ ስትሸነፍ አንተ አታሸንፍም፤ አንተም ስትሸነፍ እርሷ አታሸንፍም፤በሁለታችሁ መካከል መሸናነፍ የለም።ለመሸናነፍ ካሰባችሁ ታስራችኋልና ተፋቱ እያልኩህ ነው። 👏❸.​ከቁጣህና ከንዝንዝህ ሰንሰለት ፍታት! በየቀኑ የምትረጫትን የምላስህን መርዝ፣ የቃል ወቀሳና የጭቅጭቅ ድብደባ ፈትተህ አየር ላይ በትነው።ተወው እያልኩህ ነው። ✍️ ➍. ከራስ ወዳድነትህ ፍታት! «እኔ ብቻ ላሸንፍ፣ የእኔ ቃል ብቻ ይደመጥ አትበላት!» ዛሬውኑ የትዕቢትን ገመድ በጥሰህ ጣለው እያልኩህ ነው። ​👏.የተቀደሰው መጽሐፍ ቅዱስ << ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልንም አይቆጥርም» (1ኛ ቆሮ 13፥4-5)።እንደሚለው ብቻ ለመኖር ሞክር እያልኩህ ነው። ✍️ ወዳጄ ነጻነት የሚጀምረው አእምሮን ከውስጥ እስራት ነፃ በማውጣት ነውና በውስጥህ ከቋጠርከው ቋጠሮ በፍታት ሚስትህን ከአንተ ነጻ አውጣት። 👏 በትዳርህ ውስጥ ሰላም፣ ፍቅርና ክብር መስጠት ካልቻልክ በቅድሚያ በውስጥህ ከያዝከው መጥፎ ባህሪ፣ ጥላቻ፣ ቂምና ጭቅጭቅ ሚስትህን ፍታት! ✍️.እነዚህን ሁሉ አሉታዊ ነገሮች ከውጥህ ስትፈታ፣ ያን ጊዜ ትዳርህ ከእስር ቤትነት ወደ ቅዱስ ማደሪያነት ይለወጣል።ስለዚህ ሚስትህን ፍታት! 👏 ካልሆነ ግን በአንድ ቤት እየኖራችሁ የነፍስ እስረኞች ሆናችሁ ከመቃጠል ይሻላችኋልና፣ የያዝከውን የጨለማውን ማንነትህን አሁኑኑ ፍታው! ✍️.ሚስትህን ፍታት ያልኩህ ከጨለማው ማንነትህ ነውና ዛሬውኑ ከእስራቷ ፈተሀት ያኔ በእጮኝነትህ ወደ አሳየሀትና ወደ አጓጓሀት ብርሃናዊው ሕይወት መልሳት። 👏ሴቷም እሕቴ ባልሽን ከጨለማው እስራትሽ ፍችው።ፍታት ፍችው ተፋቱ! ✍️👏ከተሳሳትኩ እታረማለሁ እኔ በግሌ በጾመ ፍልሰታ ኑ ሚስታችንን እንፍታ ኑ እንፋታ ብያለሁ እናንተስ? https://t.me/Gabrielson_19

  • видео или голосовое, без подписи

  • 🌹#በዓታ ለማርያም ማለት🌹 ✞ 📌#እመቤታችን የብጸሐት ልጅ ናት ( የስለት ልጅ) 3 ዓመት ሲሆናት አፍዋ እህል ሳይለምድ ሆድዋ ስው ሳይውድ ብለው እናት አባትዋ ውስደው ለቤተ እግዚአብሔር ስጡዋት ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ይባላል ✞ የእመቤታችን መልኳ እንደ ፅሀይ ሲያበራ አይቶ ይእችን የመስለች ውብ ብላቴና ተረክቤ እንደምን አድርጌ አኖራታለው ብሉ ደውል አስምቶ ካህናትን ስብስቦ የምግቧን ነግር ሲማከሩ መልአኩ ቅዱስ ፋኖኤል ዕብስት ስማያዊ ጸዋ ስማያዊ ይዞ ከላይ እርቦ ታየ ሊቀ ካህናቱ ዛሬ ሀብቴን ክብሬን በስው መካከል ሊገልጥልኝ መስለኝ ብሎ ሊቀበል ቀርበ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀበት + ካህናቱም ሊቀበሉ ቀርቡ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው + እህሩገ እስራኤልም ቀርቡ መልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው + ሐና እያቄምም ሊቀበሉ ቀርቡመልአኩ ወደ ላይ ስቀቀባቸው ሐና ምን አልባት ለዚህች ብላቴና የውርደ መንፈስ ቅዱስ ሳይሆን አይቀርምና እስኪ ትተሻት ጥቂት እልፍ በይ አሏት ትታት ትንሽ እልፍ ብትል መልአኩ ውርዶ ግራክንፉን አንጥፋ ቀኝ ክንፈን አጉናጸፏ በቆመ ብዕሲ አድርጉ መግቧት አርጓል "ምግቧ ሰማያዊ ነው ሲል ነው " የምግቧ ነግር ከተያዘልን ይህችን ውብ ብላቴ ከስው ጋራ ምን ያጋፈታል ኖሮዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን ብለው ከቤተመቅደስ አግብተው አኖርዋት ሄደዋል እመቤታችንም መላእክት ሊቃነ መላዕክት አያጫውትዋት እያርጋጓት 12ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀምጠች ከእናት አባትዋቤት 3ዓመት በአጠቃላይ 15ዓመት ሲሆናት 🌿💖 አይሁዶች መቼም ለምቀኝነት አያርፉምና ይእች ብላቴና ለአቅመ ሔዋን ደርሳለች እሷን ያለ ጉልማሳ በቤተ መቅደሳችን አስገብተን ቤተ መቅደስሳችንን ታርክስብናለች እንዲያውም ጠረጠረናት ትውጣልን የጠየቀችሁን አድርግላት አሉት 🌿💖 ሊቀ ካህናቱም ዘካርያስ ከእመቤታችን ሄዶ ልጄ እንደምን ብለሽ መኖር ትውጃለሽ አላት እመቤታችንም ፍፃምተ ፈቃድ ፤ ትሁት ናትና እንግዲህ ከእግዚአብሔር በታች ያለከኝ አባት አንተ ነህ ውደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ አለችሁ 🌿💖 ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት ጌታ ስራውን ያለ ምክንያት አይስራውምና ከነገደ ይሁዳ ሚስቱ የሞተችበትን በትር ስብስበ በቀዳማይ ሰዓታት ሌሊት ይዘህ ገብተ ስትፀልይበት እደር ከዚያ ምልክት አሳይካለው ለዕዚያ ስው ስጣት አለው 🌿💖 ሊቀ ካህናቱም በትር ቢስበስብ 9መቶ 1985 በትር ሆነ ያንን በቀዳማይ ስዓት ሌሊት ይዙ ገብቶ ሲጸልይበት ቢያድር + በዮሴፍ በትር ላይ የሎሚ ቅጠል አብባ አፍርታ ታየች + እርግብም በዮሴፍ እራስ ላይ አርፈለች + እጣም ቢጥሉ ለዮሴፍ ደርስው በሦስት ምስክር ለዮሴፍ ደርስች ሱባዬ ገብተን የስጠንክን ሱባዬ ገብተን እስክንቀበልክ ድርስ ጠብቃት ተንከባከባት አሉት የዮሴፍም ይዟት ውደ ቤቱ ሄደ። ከቤቱ አኑሯት ዘመኑ የንግድ ውቅት ነበርና ወደ ንግድ ለመሄድ ዕለቱን ተሸኝቶ አድሯል ዮሴፍ ከ3ወር በሀላ ተመለስ ዮሐንስ የሚባል ፍላስፍ ወዳጅ ነበርው ሊጠይቀው መጣ ጥቂት ተጨዋወተው ሊሄድ ተነሳ ሊሽኘው ውጣ ዮሴፍ ይህች ብላቴና ፀንሳለች ከአንተ ነው ወይስ ከሌላ አለው በምን አውቀው ቢሉ በፈልስፈና የጌታስ ፀንስ በፈልስፈና አይታውቅም ብሎ ሴቶች ሲፀንሱ ከቀደመው ይልቅ መልካቸው ያምራል ጡታቸው ይጦቅራል ከንፈራቸው ይደርቃል በዚያ አውቆ። 🌿💖 ዮሴፍም አር እኔ እንኳን ግቢር ቀርቶ ሐልኦም አልውቅባትም አለው እንግዲያውስ ስስነች ተብላ እንዳትውገርብህ ገብተህ ጠይቀ ተረዳ አለው። ዮሴፍም ውደ ቤት ተመልሶ ድንግል ማርያምን የፀነሽው ከማን ነው ብሎ ጠየቃት ድንግልም ከመንፈስ ቅዱስ ነው አለችሁ ከዚህ በፈት እንዲህ ተደርጉ አያውቅም እና ነገሩ እርቀቀበት ቢርቀው ከደጅ ወድቆ ይኖር የነበር ደርቅ ግንድ አለ ይሀንን አለምልማ አብባ አፈርታ አሳይታዋለች 🌿💖 በዚያውስ ላይ ዐፁቅ በባህሪያቸው እንዲያብቡ ንቦችን እንዲራቡ የሚያደርግ ጌታ እኔንስ በእቱም ድንግልና ፀንሼ በህቱም ድንግልና እንድውልድ ቢያደርገኝ ይሳነዋል ትላለክ??? ብላ ነገሩን እንደዚህ አስርድታዋለች 🌿💖 ይህም አልቀርም ውድያው ለባህል የሚውጡበት ጊዜ ደርስ የሴፍም ትቺያት ብሄድ ያደርገውን አውቆ ትቷት መጣ ይሎኛል ይዥትም ብሄድ ሴስነች ብለው በድንጋይ ወግርወ በእሳት አቃጥለው ይገድሉብኛል ምን ይሻለኛል እያለ ይህን ሲያውጣ ሲያውርድ መላከ እግዚአብሔር በህልም ታየው ተነጋገርው ዮሴፍ ከእርሷ የሚወለደው የአብ አካለዊ ቃል በግብር መንፈስ ቅዱስ ነውና አይዞህ አትፈሪ ይዘሀት ውጣ አለው ይዝዋት ውጥቷል ነገሩም አልቀርም " 🌿💖 ማየ ዘለፈአጠጧት " ይህ በኦሪቱ ልማድ ነው ባልየው መንፍሳዊ ቅናት ተነሳስቶ ከሌላ ውንድ ደርሳለች ብሎ ሚስቱን የጠርጠራት እንደሆነ " አሪፀ ስግምን ውሃ በገንቦ አሲዞ እራሷን አከናንቦ ወደ ቤተ መቅደስ ይዟት ይሄዳል ሊቀ ካህናቱ ከምህዋሩ ለይ ሆኖ ክንብንብሽን ግለጭው ይላታ እንዲህ ይግለጥብኝ በይ ሲያስኛት ነው 🌿💖 ከኦሪቱ የሚደገም የሚነበብ የሚጸለይ አንዳንድ አለ ሊቀ ካህናቱ ያንን ደግሞ ህራር እጣኑን አመደ ምስዋቶን በጥብጦ ባልሽ የጠርጠርሽን አድርገሽ ስውርሽ እንደሆነ ስውነትሽ ይበጥ ፣  ጉንሽ ይላጥ ፣  አጥንትሽ ይርገፍ አላደርግሽው እንደሆነ በውንድ ልጅ ይታርቅሽ ብሎ ይስጣታል እርሷም አሜን ውአሜን ብላ ተቀብላ ትጠጣዋለች ። 🌿💖 እርግማኑ ይደርግብኝ ምርቃኑ ይደርግልኝ ስትል ነው ባልዋ የጠርጠራትን አድርጋ ስውራ እንደሆነ ውድያው ስውነቷ ያብጣል ፣ጉንዋ ይላጣል ፣አጥንቷም ይርግፈል ያላደርገችው እንደሆነ በውንድ ልጅ ይታርቃታል በዚያ ልማድ ነው 🌿💖 ለእመቤታችንም ቢያጠጥዋት ፈትዋ ከፀሐይ ስባት እጅ አብርቶ ተገኘ ታየ ከዚያ የተስበስ ህዝቡ ይህችን ብላቴ ባላደርገችው ነገር በከንቱ አምተናታል ብለው የተናገሩት ለእርሷ ስጥቶ ውይትፀርይ ብሉ ተናገር። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች እንዲህ ብላ ተናገርች መላኩ ቅዱስ ገብርኤል ከነገርኝ ነገር ቃል በቀር ሌላ እንደማላውቅ እግዚአብሔር ያውቃል ብላ ተናገርች ። ✞ ንፅህት ድንግል ማርያም አምላክን ለመውለድ የታመነች ናት ✞ አምላክን ለመውለድ የታመነች ድንግል ማርያም ብቻ ናት ✞ የስውን ልጅ ለማማለድ ድንግል ማርያም የታመነች ናት 🌿💖 ድንግል ሆይ !!! የማይውስነውን ውስንሽ የማይቻለውንን ቻልሽ ምንም ምንም ሊችለው የሌለውን ቻልሽ ምልዕተ ፀጋ ምልዕተ ክብር እመቤታችን የአብ አካላዊ ቃል ማደሪያው ድንግል እመቤታችን የማህፀኗ ፈሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለሙን ሁሉ አዳነ ከእኛ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን አጠፈ            🌿💖 እመቤቴ ማርያም ሆይ ዘር ያልወደቀባት ገበሬ ያልጣረባት የቅዱስ ቁርባንን አዝመራ ያፈራሽ ገራህት ሆይ፤ ከትጉሃን መላእክት ጋር ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡           🌿💖 ድንግል እመቤቴ ሆይ ብልህ አዋቂ የሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ያፈቅራል፤ ሰነፍ ልበ ቢስ ግን በከንቱ ይጠላሻል፤ ዳሩ ግን በመከረው የተንኮል ምክር ወጥመድ እሱ ራሱ ይጠመድ፡፡ 🌿💖 እመቤታችን ድንግል ማርያም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!! ድንግል ሆይ ከልጅሽ ከውዳጅሽ ከኢየሱስ ከክርስቶስ ለምኝልን ከሀጥያታችንን ያስተስርይልን ዘንድ  አሜን!!! https://t.me/Gabrielson_19 ወስብሓት ለእግዚአብሔርው ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር አሜን

"ኦርቶዶክሳዊ ህይወት (Orthodox Life) — tgindex