- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 225
- 1/48двое суток
- 257
- 1/72трое суток
- 278
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ነሐሴ 14 እና 15 ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ
"መፍቀሬ ሰብእ አቅረበነ ኀቤሁ - ሰውን የሚወድ ሰው የሚወደው እርሱ ከአባቱ ጋራ አስታረቀን። " ከራድዮን የሚባል ፀዓዳ ዖፍ አለ ከነገሥታቱ ቤት ይኖራል። ሰው ሲታመም አምጥተው ከፊቱ ያኖሩታል። የሚሞት እንደሆነ ፊቱን ይመልስበታል የሚድን እንደሆነ ቀርቦ አፉን ከአፉ አድርጎ አስተንፋሱን ይቀበለዋል ነጭ የነበረው ይጠቁራል። ዋዕይ ፀሐይ ሲሻ ወደ ዓየር ይወጣል፤ ፫ት ሰዓት ዋዕየ ፀሐይ ተመቶ ወደ ባሕር ይወርዳል። ፫ት መዓልት ፫ት ሌሊት በከርሠ ባሕር አድሮ የ ቀደመ ጠጉሩን መልጦ ታድሶ ይወጣል። ዖፍ ፀዓዳ የተባለ ጌታ ነው ፀዓዳ በመለኮቱ እንዲለው። ድውይ የተባለ አዳም ነው ቀርቦ አስተንፋሱን እንደመቀበል ባሕርዩን ባሕርይ አድርጓል ደዌ በእስትንፋሱን ወደሱ እንደተመለሰ የአዳም ባሕርይ ባሕርይ ቢያደርግ በአዳም የተፈረደውን መከራ ተቀብሏል። ወቦአ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ውስተ ኩሉ ፀዋትወ መከራ እንተ ባቲ አመከረነ ጸላኢ እንዲል። ወደ አየር እንደ መውጣት ወደ መስቀል መውጣት ነው። ዋዕየ ፀሐይ ሲሰማው ወደ ባሕር እንደ መውረድ ወደ መቃብር መውረድ ነው። ፫ት መዓልት ፫ት ሌሊት በከርሠ ባሕር አድሮ የቀደመ ጠጉሩን መልጦ ታድሶ እንደ መውጣት ፫ት መዓልት ፫ት ሌሊት በከርሠ መቃብር ኑሮ ፭ ወገን ሁኖ ለመነሣቱ ምሳሌ። ሰውን የሚወድ ሰውም ከሚወደው ልጅሽ ድንግል እመቤታችን፤ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን። ከዓርብ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ የተወሰደ
መልሺው ስለእያንዳንዱ ነገር ከማመስገን ርቆ ዘወትር የሚያማርረውን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ትቶ በራሱ ሕግ የሚመራውን ቤቱ የሆነች ቤተክርስቲያንን ትቶ በባዕድ አገር የተሰደደውን ሕይወት የሚሆን መብል ትቶ ከሞት መዓድ የሚቋረሰውን ወዳጅ ዘመድ የሆነውን ልጅሽን ርቆ ወደ ጠላት የሔደውን እመብርሃን እመአምላክ እናታችን ከተቀደሰው ሁሉ ርቆ የሔደውን ልጅሽን መልሺው🙏 ✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨
+++ "እግዚአብሔር የጣላት እሳት" +++ በደብተራ ኦሪት በመሠዊያው ላይ የሚነደውና መሥዋዕቱ ይቃጠልበት የነበረው እሳት ከሰማይ የወረደ ነበር። ይህም እሳት ዘወትር እንዳይጠፋ የአሮን ልጆች (ካህናቱ) ማለዳ ማለዳ እንጨት እየጨመሩ እንዲያቀጣጥሉና እንዲያነዱት እግዚአብሔር አዝዟቸዋል።(ዘሌዋ 6፥12) ከማዕጠንት ጀምሮ እስከ እንስሳት በድንኳኑ የሚቀርቡ ማናቸውም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሁሉ የሚበሉት ከሰማይ በወረደው በዚህ "የእግዚአብሔር እሳት" ነው። ታዲያ ከእለታት በአንዱ ቀን የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እንዲህ አደረጉ። ለእግዚአብሔር የእጣን መሥዋዕት ማቅረብ ፈልገው ለየራሳው ጥናውን (ማዕጠንት) አነሡ። ነገር ግን በጥናው ውስጥ ያደረጉት ከሰማይ የወረደውን "የእግዚአብሔር እሳት" ሳይሆን፣ ከመንደር ጭረው ያመጡትን ወይም ራሳቸው ያቀጣጠሉትን "ሌላ እሳት" ነበር። በዚህም እግዚአብሔር ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት ስላቀረቡ አምላክ ተቆጣ። በፊቱም እሳት ወጥቶ እንዲበላቸው አደረገ። እነርሱም ወዲያው ሞቱ።(ዘሌ 10፥1-3) ሊቀ ካህናቱ አሮንን እየተከተሉ እንዲያገለግሉ የተመረጡት ሁለቱ ልጆቹ ገና አገልግሎታቸውን በቅጡ ሳይጀምሩ ተቀሰፋ። ለመሆኑ እነዚህ ሁለት የኦሪት ወጣት ካህናት የተቀጡበት "የሌላ እሳት" ታሪክ ለሐዲስ ኪዳኑ ዘመን ምን ምሳሌ ይኖረው ይሆን? እግዚአብሔር በኦሪቱ ድንኳን እሳትን እንዳወረደ፣ በሐዲስ ኪዳንም የሰውን ልጅ ለማዳን ከሰማይ ሲወርድ ይዞልን የመጣው እሳት አለ። "እሳተ አምጻእኩ ለብሔር፤ ወምንተ እፈቅድ ዘእንበለ አንድዶታ" - "በምድር ላይ እሳት ልጥል መጣሁ፥ አሁንም የነደደ ከሆነ ዘንድ ምን እፈልጋለሁ?" እንዳለን።(ሉቃ 12፥49) ይህ መድኃኒታችን በምድር ላይ የጣለው እሳት ምንድር ነው? አገልግሎቱስ እንዴት ነው? ጌታችን በምድር የጣላት እሳት "ወንጌል" ትባላለች። ሰው ሰውነቱን ንጹሕና የተቀደሰ ሕያውም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብባት "የእግዚአብሔር እሳት" ወንጌል ነች። ይህች ወንጌል ጌታ አንድ ጊዜ በምድር የጣላት፣ እኛ ደግሞ ለዘወትር እንዳትጠፉ የምናቀጣጥላትና የምናነዳት እሳት ነች። የማቀጣጠያው እንጨቶችም ቃለ እግዚአብሔርን መስማት እና ማንበብ ናቸው። ያለ ወንጌል እሳትነት ምንም መሥዋዕት እንድናቀርብ አልተፈቀደልንም። ነገር ግን እንደ አሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ ከመንደር ቆስቁሰን ወይም ራሳችን አቀጣጥለን የምናመጣቸው "ሌላ እሳት" የተባሉ ከንቱ ፍልስፍናዎችና እንግዳ ትምህርቶች የእግዚአብሔርን ቁጣ ይቀሰቅሱብናል። ዳግመኛም እሳት የተባለው በጥምቀት ጊዜ በሁላችንም ላይ የወረደው ጸጋ እግዚአብሔር ነው። ይህም ጸጋ ለመዳናችን ዓይነተኛ ሚና አለው። ይሁን እንጂ ልክ በደብተራ ኦሪት እንደ ወረደው እሳት ካልተንከባከብነው እና ካላቀጣጠልነው ሊዳፈን እና የሌለ ሊመስል ይችላል። ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስ "እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው...በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ሥጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ" በማለት የሚመክረው።(2ኛ ጢሞ 1፥6) እግዚአብሔር ለሰጠን ጸጋ ማቀጣጠያዎቹ ደግሞ ጾም፣ ጸሎትና መንፈሳዊ ትሩፋት ሁሉ ናቸው። እርሱ የሰጠህን የጸጋ እሳት ከማቀጣጠል ይልቅ "ሌላ እሳት" ላምጣ ያልህ ቀን ግን ታላቅ ጥፋት ያገኝሃል። ዲያቆን አቤል ካሳሁን abelzebahiran@gmail.com
ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል። መዝሙረ ዳዊት 119፥72
አቤቱ በዋጋ የገዛኸው የሰው ልጅ በነጻ ሲሞት ዝም አትበል ! መርጦ ሳይወለድ ተመርጦ ለተገደለው ጌታ ሆይ እዘን !
አዎን አቤቱ የሁሉ አምላክ ነህ። አዎን አቤቱ የሁሉ ንጉስ ነህ። አዎን አቤቱ ሁሉን የያዝክ ነህ። አዎን አቤቱ ሁሉን የምትገዛ ነህ። አዎን አቤቱ ሁሉን የምታድን ነህ። አዎን አቤቱ የሁሉ ገዥ ነህ። አዎን አቤቱ የሁሉ መድኃኒት ነህ። አዎን አቤቱ ሁሉን የምትመግብ ነህ። ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
"... ዓይነ ልቡናችንን ወዳንተ እናንጋጥጣለን ፤ ክሣደ ልቡናችንን ወዳንተ እናዘነብላለን ፤ ላንተ መገዛት ይገባል ፤ ለመንግሥትህም ምስጋና ይገባል ፤ ከሊቃነ መላዕክት ጋራ ንጹሕ እጣንን እናቀርብልሃለን ..." ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
ተጨልፎ እንደማያልቅ እንደ ውቅያኖስ ምስጋናዬ ምነው በሆነ! እንደማይደረስበት አድማስ እምነቴ ምነው በሰፋ! እንደማይቆጠር የጤፍ ዘር አምልኮዬ ምነው በበዛ! በነፍስ ግስጋሴ ሁልጊዜ ምነው በፈለኩህ! እባክህን አምላኬ አንተን እንዳየሁ ልቅር!
የማርያም ልጅ ነኝ ብለህ ፣ ወልድ በራስህ ተኮራህ ፤ አብ አይበልጥም ወይ አባትህ ፣ ተለማኝ እናትህ ። አንድ ያገራችን ባለቅኔ
“ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል” 1ኛ ቆሮ. 10:13
የምናሴ ጸሎት (፪ ዜና መዋዕል ፴፫ ፥ ፲፬-፳፮) ዓለምን ሁሉ የምትገዛ ፥ የአባቶቻችን የአብርሃምና የይስሐቅ የያዕቆብም የጻድቃን ልጆቻቸውም አምላክ ሆይ ፥ ሰማይንና ምድርን ከዓለሞቻቸው ጋር የፈጠርህ ፥ በቃልህ ትእዛዝ ባሕርን የገሠጽሃት ፥ ቀላዮችን የዘጋህ የሚያስፈራውንም የወሰንህ ፥ ይኸውም በተመሰገነው ስምህ ነው ፥ ኀይልህ ከመገለጡ የተነሣ ሁሉ የሚርድና የሚንቀጠቀጥ ፥ ለክብርህ ከፍተኛነት ፍጻሜ የለውምና ፥ የቁጣህም መቅሰፍት በኃጥአን ላይ ግሩም ነው። በትእዛዝህ ለሚሆነው ይቅርታ ስፍር ቍጥር የለውም ፤ ገናና እግዚአብሔር አንተ ብቻ ነህና ፥ ይቅር ባይ ፥ ከቁጣ የራቅህ ፥ ይቅርታህ የበዛ ፥ የሰውንም ኅጢአት የምታስተሰርይ አንተ ነህ። አሁንም አቤቱ ፥ የጻድቃን አምላካቸው አንተ ነህ። ንስሓን የፈጠርህ ለጻድቅ ሰው አይደለምና ፥ አንተን ላልበደሉ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም አይደለምና ፤ ነገር ግን የኔን የኃጥኡን ንስሓ ወደ ማየት ተመለስ። ቍጥሩ ከባሕር አሸዋ የሚበልጥ በደልን በድያለሁና ፥ ኀጢአቴም ብዙ ነውና ፤ ከበደሌም ብዛት የተነሣ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ አገባቤ አይደለም። ሰውነቴን ከኀጢአቴ አሳርፋት ዘንድ በብረት ቀፎ ደከምሁ ፤ በዚህም ደግሞ አላረፍሁም ፤ መዓትህን አነሣሥቻለሁና ፥ ከንቱውን ስመለከት የማይጠቅመኝንም ነገር ሳበዛ በፊትህ ክፉ ሥራን ሠርቻለሁና። አሁንም ቸርነትህን እየለመንሁ በልቤ ጉልበት እሰግዳለሁ። አቤቱ ፥ ጌታዬ ፥ ፈጽሜ በደልሁ ፤ ኀጢአቴንም አምናለሁ። አንተንም እማልዳለሁ ፤ እለምንህማለሁ ፤ ይቅር በለኝ ፤ አቤቱ ፥ ይቅር በለኝ ፤ ለኀጢአቴም አሳልፈህ አትስጠኝ። ለዘለዓለም ክፋቴን አትመልከትብኝ ፤ በምድር ጥልቀት አትበቀለኝ ፤ አቤቱ ፥ በንስሓ ለሚመለሱ ሰዎች ፥ አምላካቸው አንተ ነህና ፥ ቸርነትህ በኔ ላይ ይገለጥ ፤ መዳን የማይገባኝ ሲሆን በይቅርታህ ብዛት አዳንኸኝ። በየጊዜውና በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አመሰግንሃለሁ። የሰማያት ኀይል ሁሉ አንተን ያመሰግናሉና ፤ ለዘለዓለምም ምስጋና ለአንተ ይገባል ፤ አሜን።
የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እና ሥርዓት እንዴት አሁን ያለበትን ዓይነት ቅርጽ ሊይዝ ቻለ? በዚህ ሂደት ውስጥስ በቤተ ክርስቲያን የተካሄዱ ዓለማቀፉዊ ጉባኤያት (Ecumenical Councils) ድርሻቸው ምን ነበር? ይህን አጠር ባለ መንገድ ለመረዳት “ጉባኤ ኒቅያ” የተሰኘውን ሦስት ክፍሎች ያሉትን ተከታታይ ትምህርት ከማስታወሻ ጋር እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ። https://youtu.be/Epd_EC5diLI?si=JlViJ7yVxsPkpyHA
ሰፊው ዓለም የጠበባቸው ፣ ነግቶ ምሽት የሚመስላቸው ፣ በነፍስ ማዕበል የሚንገላቱ በልጅሽ ሰላም ይረፉ ። ቅድስት ሆይ ለምኚልን !
የመንገድህ ዋስትና እኔ ነኝ ። በበረሃ ልጥልህ ከቤት አላወጣሁህም። ስጸዳ እመጣለሁ ብለህ ከቤቴ አትራቅ ። ካልሞትህ በቀር ከቤቴ አትቅር። ጥያቄዎችህን ሳይሆን እኔን አስብ። የሁሉም ነገር መልስ በዓለም ላይ የለም። የሁሉም ነገር መልስ ግን እኔ ነኝ። አንድ ቃል ልንገርህ፡- ዋጋ ያለህ ፍጥረቴ ነህ።
📍መስቀል አደባባይ ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በብዙ ስለሚያተርፉ እንዳያመልጦ !
ባሪያህን አትለፈኝ... የአብርሃሙ ሥላሴ የአባታችን የቅዱስ አብርሃምን ድንቅ ታሪክ የሚያሳይ አዲስ ቪዲዮ አዘጋጅተንላችኋል። ጠላት ሰይጣን በአብርሃም መልካም ግብር ተቀንቶ ያደረገውን ተንኮል እና አብርሃም እንግዳ አጥቶ ማዘኑን ፣ በመጨረሻም የቅድስት ሥላሴን ቡራኬ ማግኘቱን እናያለን! ለመመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑ፡ !👉🏻link Youtube | Telegram | Instagram | Tiktok #አብርሃም #ቅድስት_ሥላሴ #የኦርቶዶክስ_ታሪክ #ኦርቶዶክስ #ተአምር #ሐምሌ7
እንኳን ለቅዱስ ጳውሎስ ወጴጥሮስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ! “የጳውሎስ የመጨረሻዋ ቀን” ተራኪ፡ ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን ቅዱስ ጳውሎስ፣ ገጽ፡ 409
“እኔ የኢየሱስን ማኅተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና” ገላ 6:17