tgindex
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

Статистика
Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
9
Всего постов
32
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
52 108
+34 за 3 дн.
Сутки
+10
+0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
8 043
29 постов
Вовлечённость
15,4%
к подписчикам
Постов в день
1,3
всего 32
Упоминаний
7
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
5 621
1/48двое суток
6 441
1/72трое суток
6 947

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14 авг.3 526333

    https://www.youtube.com/live/oZKKNnnNbhQ?si=-s5m9FiqPUi58_hp

  • 13 авг.5 098344

    https://www.youtube.com/live/MkfCVeKsQKo?si=mgI6Hmew63xKIQei

  • 13 авг.4 919235

    • #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ "#ቀኖና ቤተ ክርስቲያን " በሚል ርእስ በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር ከሆኑት ከመዝገበ ጥበብ ልሳነ ወርቅ ዋሴ ጋር የተደረጉ ጥያቄና መልስ ይዛለች ። ሐመር መጽሔት #፴፫ ኛ ዓመት ቁጥር ፰ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ ! Magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል

  • 13 авг.5 1292911

    የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በማስጠበቅ ሥርዓቷን ለትውልድ እናስተላልፍ !(መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን ) የነሐሴ ወር ሐመር #መጽሔት #በውስጧ ምን ይዛለች ? የነሐሴ ወር ፳፻፲፰ ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን "#የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በማስጠበቅ ሥርዓቷን ለትውልድ እናስተላልፍ ! . ›› በሚል ርእስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለደነገገችው ሥርዓቶች ሁሉ ተገዥ በመሆን መጽናት እንደሚገባ ታስነብባለች። #ዐውደ ስብከት ሥር” በመጣህበት መንገድ በዚያ አትመለስ " በሚል ዐቢይ ርእስ ትምህርት ይዛለች፡፡ #በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር” ሱባኤ" በሚል ርእስ ሱባኤ ለምን እንደምንገባ? መቼ ሱባኤ መግባት እንደአለብን ፤ሱባኤ የምንገባው እንዴት ነው?የሚል ጹሑፍ በትምህርተ ሃይማኖት ይዛለች። #ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “#የቤተ ክርስቲያንን የስብከተ ወንጌል ስምሪት በዘመናዊ አሠራር መቃኘት " በሚል ርእስ ስብከተ ወንጌል ስምሪት ላይ የሚታዩ ዐቢይ ችግሮችና ውስንነቶችን ከመፍትሔ ጋር ይዛለች ። "#ክርስትና በማኀበራዊ ኑሮ፦ " #ያለኝን እሰጥሃለሁ "በሚል መነሻነት ችግሩን መረዳት ፤ያለንን ማወቅ ና በሌለን ነገር መጨነቅ እንደማይገባን ልንፈታው በማንችለው ችግር መጨነቅ እንደሌለብን በሰፊው ያሳያል ። • #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ታሪክ "ክፍል ፩ ስለ አመሠራረቱና ሌሎችም ጉዳዩች ላይ ሰፊ ትምህርት ይሰጣል ። • #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን "ከአንድ ምእተ ዓመት አርምሞ እሰከ ዘመናዊ የልህቀት ማእከልነት" የደብረታቦር መድኃኔዓለም የ4ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት ሁለንተናዊ አገልግሎትና ስኬቶች ፣የልማት ርእይና የወደፊት ዕቅዶች ታስነብባለች። #በኪነ ጥበብ ዐምድ #በርናባስ "በሚል ርእስ ታስነብባለች

  • 12 авг.6 338616

    видео или голосовое, без подписи

  • 11 авг.7 1249

    видео или голосовое, без подписи

  • 11 авг.7 1007710

    ዜና ገዳማት ወር በገባ የመጀመሪያው ማክሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ 3ኛ ወለል ሰዓት ᎓- 11᎓30-1᎓30

  • 10 авг.8 972555

    https://youtu.be/WM8tmVbLYuI

  • 10 авг.7 248605

    «እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰታ   ጾም በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚተላለፈውን ልዩ የመንፈሳዊ መርሐ ግብር፣ ትርጓሜ፣ ቅዳሴ እና ትምህርተ ወንጌል በቀጥታ ስርጭት እንድትከታተሉ በአክብሮት እንጠይቃለን ። ሰዓት፦ ዛሬ ከቀኑ 5፡00 ጀምሮ ቦታ፦ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚተላለፍበት፦ የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን (YouTube Live) ዛሬ ይጠብቁን!»

  • 8 авг.8 556618

    አንድ የፊኒሺንግ ዕቃ ትውልድ  ለሚታነጽበት የማኅበረ ቅዱሳን የልህቀት ማእከል ድጋፍ እናድርግ✝️✝️ ድጋፍ ለማድረግ  1.በንግድ ባንክ 1000003780717 2.በአሐዱ ባንክ 0003488710901 3.በአቢሲኒያ ባንክ 4753388 4.በአዋሽ ባንክ 01320021428400 5.በወጋገን ባንክ 0057130830101 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://forms.gle/E87npdh8XnWWN3vV7

  • 8 авг.9 410578

    видео или голосовое, без подписи

  • 7 авг.11,1 тыс19846

    እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ አደረሰን

  • 7 авг.8 050677

    📚 መማር እንሻለን! በተለያዩ ማኅበራዊ ቀውሶች ምክንያት የትምህርት መሣሪያ አጥተው የትምህርት ገበታቸው የተቋረጠባቸውን ሕፃናት በጋራ እንደግፍ። 🔹 የአንድ ተማሪ ሙሉ ወጪ፦ 3,300 ብር 🔹 እርሶ የሚችሉትን፦ "አንድ ደብተርም ቢሆን ዋጋ አለው!" 💰 በገንዘብ ለመርዳት፦ • ንግድ ባንክ፡ 1000309803648 • አሐዱ ባንክ፡ 0025393810901 • አቢሲኒያ ባንክ፡ 23375458 • አዋሽ ባንክ 01329817420400 • ወጋገን ባንክ፡ 083731610101   🎁 በዓይነት ለመስጠት፦ አምስት ኪሎ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ 1ኛ ወለል 📅 ጊዜ፦ ከነሐሴ 1 - ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት

  • 6 авг.11,3 тыс11341

    የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል። ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን አስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ አድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ አላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔር ትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በአጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብር አዞናል ከቅዱሳን ፍጥረታት መካከል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም አብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብራት እዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በአጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢአታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት አውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር አባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ነው።

  • 6 авг.9 00538

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.10,1 тыс4339

    ቅዱስ ፓትርያርኩ ጾመ ፍልሰታ ለማርያምን ምክንያት አድርገው መልእክት አስተላለፉ። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፣ አሜን በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺህ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም አደረሰን አደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን አካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ አካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን አካላት ግንኙነት በአካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ አይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከአካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ አንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር አምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤

  • 6 авг.8 236376

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.8 7716114

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 авг.10,7 тыс1248

    ሻሸመኔ ማእከል 25 ተተኪ ሰባክያንን አሠልጥኖ አስመረቀ ሐምሌ ፳፰/፳፻፲፰ ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማእከል በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሥር ከሚገኙ ልዩ ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ 25 ሠልጣኞች ሲሰጥ የቆየውን የ1ኛ ዙር የተተኪ ሰባክያን አሠልጥኖ አስመርቋል። ሥልጠናው ከሐምሌ 13 እስከ ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ሳምንታት በሻሸመኔ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ሠልጣኞች በቆይታቸው የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ታሪክ መሠረት ያደረጉ ትምህርቶችን ሲከታተሉ ቆይተዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን ቀሲስ መዝገቡ ቸኮል፣ የማእከሉ የሥራ ኃላፊዎችና አባላት፣ አሠልጣኝ መምህራን እንዲሁም ምእመናን ተገኝተዋል። በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የማእከሉ ዋና ጸሓፊ ዲያቆን ወንድሙ ገብሬ የሥልጠናውን አጠቃላይ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። በዕለቱ የተገኙት የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት የቅርሳቅርስ ክፍል ኀላፊ መልአከ ሰላም ቀሲስ ወልደ ኪዳን ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባር በመቀየር ቤተ ክርስቲያንን በፍቅርና በትሕትና እንዲያገለግሉ አደራ ብለዋል። በመጨረሻም ማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማእከል በቀጣይም ተተኪ አገልጋዮችን ለማፍራት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

  • 4 авг.10,3 тыс2

    видео или голосовое, без подписи