tgindex
ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

Статистика
Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
18
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 920
−6 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
681
22 постов
Вовлечённость
13,8%
к подписчикам
Постов в день
2,6
всего 22
Упоминаний
3
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
628
1/48двое суток
719
1/72трое суток
776

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ✝️እነርሱም ይህን ሲሰሙ ‹‹ጊዜ ይተርጕመው ብለው›› ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ ለዘር ሊያበቃቸው ፈቅዷልና መካኗ ቴክታ ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ‹ሄኤሜን› አለቻት፡፡ ትርጕሙም ‹ስእለቴን (ምኞቴን) አገኘሁ› ማለት ነው፡፡ ✝️ ሄኤሜንም ለዓቅመ ሔዋን ስትደርስ ዴርዴን፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ ሐናን ወለዱ፡፡ ለሐናም ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ እነርሱም እንደ በጥሪቃና ቴክታ መካኖች ኾኑ፡፡ ✝️በእስራኤላውያን ባህል መካንነት የእርግማን ምልክት ተደርጎ ይቈጠር ነበርና ሐና እና ኢያቄም ብዙ ዘለፋና ሽሙጥ ይደርስባቸው ነበር፡፡ ✝️በአንድ ወቅት መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደስ ሔዱ፡፡ የዘመኑ ሊቀ ካህናት ሮቤል መካን መኾናቸውን ያውቅ ነበርና ‹‹እናንተማ ‹ብዙ ተባዙ› ብሎ እግዚአብሔር ለአዳም የነገረውን ቃል ያስቀረባችሁ ርጉማን አይደላችሁምን? እግዚአብሔር ቢጠላችሁ እንጂ ቢወዳችሁማ ልጅ ይሰጣችሁ አልነበረምን?›› ብሎ መሥዋዕታቸውን ሳይቀበላቸው ቀረ፡፡ ✝️አንድም ከአዕሩገ እስራኤል (ከአረጋውያን እስራኤላውያን) የተወለዱ ሰዎች የሚመገቡትን ተረፈ መሥዋዕት እንዳይመገቡ ከለከላቸው፡፡ በዚህ እያዘኑ ሲመለሱ ከመንገድ ላይ ከልጆቻቸው ጋር የሚጫወቱ ርግቦችንና አብበው ያፈሩ ዕፀዋትን ሐና ተመለከተች፡፡ እርሷም ‹‹ርግቦችን በባሕርያቸው መራባት እንዲችሉ፤ ዕፀዋትንም አብበው እንዲያፈሩ የምታደርግ ጌታ እኔን ለምን ልጅ ነሳኸኝ?›› ብላ አዘነች፡፡ ✝️ከቤታቸው ሲደርሱም ‹‹እግዚአብሔር ልጅ ቢሰጠን ወንድ ከኾነ ለቤተ እግዚአብሔር ምንጣፍ አንጣፊ፣ መጋረጃ ጋራጅ ኾኖ ሲያገለግል ይኑር፤ ሴት ብትኾንም መሶበ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ ስታገለግል ትኑር›› ብለው ተሳሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ሐምሌ ፴ ቀን ኹለቱም ራእይ አዩ፡፡ ሐና ‹‹በሕልሜ ፀምር (መጋረጃ) ሲያስታጥቁህ፤ በትርህ አፍርታ ፍጥረት ዅሉ ሲመገባት አየሁ›› ብላ ያየቸውን ራእይ ለኢያቄም ነገረችው፡፡ ✝️ኢያቄምም ‹‹ጸዓዳ ርግብ ሰባቱን ሰማያት ሰንጥቃ መጥታ በራስሽ ላይ ስታርፍ፣ በቀኝ ጆሮሽ ገብታ በማኅፀንሽ ስታድር አየሁ›› ብሎ ያየውን ራእይ ለሐና ነገራት፡፡ ወደ ሕልም ተርጓሚ ሔደው ትርጕሙን ሲጠይቁም ‹‹ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹አንተ አልፈታኸውም፤ ጊዜ ይፍታው›› ብለው ተመለሱ፡፡ በሌላ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ‹‹ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ›› ብሎ የሕልሙን ትርጕም ትክክለኛነት ነግሯቸዋል፡፡ ✝️ከዚህ በኋላ ብሉይ ኪዳን (ዓመተ ዓለም፣ ዓመተ ፍዳ) ተፈጽሞ የሐዲስ ኪዳን መግባት ሊበሠር፤ ጌታችንም ሊፀነስ ፲፬ ያህል ዓመታት ሲቀሩ በፈቃደ እግዚአብሔር ነሐሴ ፯ ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተፀንሳለች፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእናቷ በቅድስት ሐና ማኅፀን ሳለች ካደረገቻቸው ተአምራት መካከልም በርሴባ የምትባል ሴትን ዓይን ማብራቷ አንደኛው ነው፡፡ ይህቺ አንድ ዓይና ሴት (በርሴባ) ‹‹እግዚአብሔር በረድኤት ጐበኘሽ መሰለኝ፤ ጡቶችሽ ጠቁረዋል፤ ከንፈሮችሽ አረዋል›› ብላ የሐናን ማኅፀን በዳሰሰችበት እጇ ብታሻሸው ዓይኗ በርቶላታል፡፡ ✝️ይህንን አብነት አድርገውም እንደ እርሷ የሐናን ማኅፀን በመዳሰስ ብዙ ሕሙማን ከደዌያቸው ተፈውሰዋል፡፡ እንደዚሁም ሳምናስ የሚባል ልጅ በሞተ ጊዜ ሐና የአልጋውን ሸንኮር ይዛ ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት ከሞት ተነሥቶ ‹‹ሰላም ለኪ ኦ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ፤ ሰማይና ምድርን የፈጠረው አምላክ አያቱ ሐና ሆይ! ሰላም ላንቺ ይኹን! ሰላምታ ይገባሻል!›› በማለት ሕልም ተርጓሚ ያልፈታውን ራእይ በመተርጐም ከቅድስት ሐና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፤ ከእመቤታችን ደግሞ እውነተኛው ፀሐይ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንሚወለድ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ ✝️በአጠቃላይ ‹‹ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል …፤ ልዑል እግዚአብሔር ማደሪያውን መረጠ፤ አከበረ፤ ለየ፤ ቀደሰ …፤›› (መዝ. ፵፭፥፬) በማለት ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እንደ ተናገረው፣ አምላክን ለመውለድ የተመረጠችው ማኅደረ ማለኮት፤ የዓለሙን ቤዛ በመውለዷ ‹‹ቤዛዊተ ዓለም›› እየተባለች የምትጠራው፤ በአምላክ ሕሊና ታስባ ትኖር የነበረችው፤ የድኅነታችን ምክንያት የኾነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማኅፀን የተቋጠረችው (የተፀነሰችው) ነሐሴ ፯ ቀን ነው፡፡ ✝️ ፅንሰቷም እግዚአብሔር በባረከውና ባከበረው ቅዱስ ጋብቻ በተወሰኑት ወላጆቿ በቅዱስ ኢያቄምና በቅድስት ሐና ሥርዓት ያለው ግንኙነት ነው፡፡ ✝️ ‹‹ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ፤ ድንግል ሆይ በሥጋዊ ፈቃድ የተፀንሽ አይደለሽም፤ ሕጋዊ በኾነ ሥርዓት ከሐና እና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ፤›› እንዳሉ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም፡፡ ስለዚህም ‹‹ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ እስመ ወለድኪ ለነ መብልዐ ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ ሕይወት ዘበአማን፤ ማርያም ሆይ! እውነተኛውን ምግብ፣ እውነተኛውን መጠጥ አስገኝተሽልናልና እናከብርሻለን፤ እናገንሻለን፤›› በማለት አባ ሕርያቆስ እንዳመሰገኗት፣ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚሰጠውን፤ ከሞተ ሥጋ ከሞተ ነፍስ ማዳን የሚቻለውን፤ እውነተኛውን ምግበ ሥጋ ወነፍስ ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ ወለደችልን ‹‹እናታችን፣ እመቤታችን፣ አማላጃችን፣ የድኅነታችን ምክንያት፣ ወዘተ›› እያልን ቅድስት ድንግል ማርያምን እናከብራታለን፤ እናገናታለን፤ እናመሰግናታለን፡፡ ✝️ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከት አይለየን፡፡ እናቱን በአማላጅነት፤ ራሱን በቤዛነት ለሰጠን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር፣ ምስጋና ይድረሰው፡፡ ምንጭ፦ ማኅበረ ቅዱሳን ድህረ ገጽ

  • ፅንሰተ ማርያም ድንግል ዘወትር ሐሙስ፦ እናስተዋውቅዎ ✝️በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ ነሐሴ ሰባት ቀን ከሚዘከሩ በዓላት መካከል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፅንሰት አንደኛው ነው፡፡ በዓሉን ለመዘከር ያህልም የእመቤታችንን የመፀነስ ታሪክ በአጭሩ እናስታውሳችሁ፤ ✝️የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ አያቶች ቴክታ እና በጥሪቃ ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለ ጠጎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን መካኖች ነበሩ፡፡ ✝️ ዘራቸውን ባለመተካታቸውና ሀብታቸውን የሚወርስ ልጅ ባለማግኘታቸውም ያዝኑ፣ ይተክዙ ነበር፡፡ ✝️ ከዕለታት አንድ ቀን በጥሪቃ ሚስቱ ቴክታን ጠርቶ ‹‹አንቺ መካን፤ እኔ መካን፡፡ ይህ ዅሉ ገንዘብ ለማን ይኾናል?›› አላት፡፡ ቴክታም ‹‹እግዚአብሔር ከእኔ ልጅ ባይሰጥህ ከሌላ ይሰጥህ ይኾናል፡፡ ሌላ ሚስት አግብተህ ልጅ አትወልድምን?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ይህንስ እንዳላደርገው አምላከ እስራኤል ያውቃል›› አላት፡፡ ✝️ በዚህ አኳኋን እያዘኑ ሲኖሩ አንድ ቀን ነጭ እንቦሳ (ጥጃ) ከበረታቸው ስትወጣ፤ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ልጅ ስትደርስና ስድስተኛዪቱ እንቦሳም ጨረቃን፣ ጨረቃም ፀሐይን ስትወልድ ራእይ አዩ፡፡ ✝️ ራእያቸውን ለሕልም ተርጓሚ ሲነግሩም ‹‹የጨረቃዪቱ ትርጕም ከፍጡራን በላይ የምትኾን ልጅ እንደምታገኙ የሚያመለክት ነው፡፡ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጠልኝም፡፡ እንደ ነቢይ፣ እንደ ንጉሥ ያለ ይኾናል፤›› አላቸው፡፡

  • 13 авг.427из mkpublicrelation

    • #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ "#ቀኖና ቤተ ክርስቲያን " በሚል ርእስ በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር ከሆኑት ከመዝገበ ጥበብ ልሳነ ወርቅ ዋሴ ጋር የተደረጉ ጥያቄና መልስ ይዛለች ። ሐመር መጽሔት #፴፫ ኛ ዓመት ቁጥር ፰ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ ! Magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል

  • 13 авг.43912из mkpublicrelation

    የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በማስጠበቅ ሥርዓቷን ለትውልድ እናስተላልፍ !(መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን ) የነሐሴ ወር ሐመር #መጽሔት #በውስጧ ምን ይዛለች ? የነሐሴ ወር ፳፻፲፰ ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን "#የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በማስጠበቅ ሥርዓቷን ለትውልድ እናስተላልፍ ! . ›› በሚል ርእስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለደነገገችው ሥርዓቶች ሁሉ ተገዥ በመሆን መጽናት እንደሚገባ ታስነብባለች። #ዐውደ ስብከት ሥር” በመጣህበት መንገድ በዚያ አትመለስ " በሚል ዐቢይ ርእስ ትምህርት ይዛለች፡፡ #በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር” ሱባኤ" በሚል ርእስ ሱባኤ ለምን እንደምንገባ? መቼ ሱባኤ መግባት እንደአለብን ፤ሱባኤ የምንገባው እንዴት ነው?የሚል ጹሑፍ በትምህርተ ሃይማኖት ይዛለች። #ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “#የቤተ ክርስቲያንን የስብከተ ወንጌል ስምሪት በዘመናዊ አሠራር መቃኘት " በሚል ርእስ ስብከተ ወንጌል ስምሪት ላይ የሚታዩ ዐቢይ ችግሮችና ውስንነቶችን ከመፍትሔ ጋር ይዛለች ። "#ክርስትና በማኀበራዊ ኑሮ፦ " #ያለኝን እሰጥሃለሁ "በሚል መነሻነት ችግሩን መረዳት ፤ያለንን ማወቅ ና በሌለን ነገር መጨነቅ እንደማይገባን ልንፈታው በማንችለው ችግር መጨነቅ እንደሌለብን በሰፊው ያሳያል ። • #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ታሪክ "ክፍል ፩ ስለ አመሠራረቱና ሌሎችም ጉዳዩች ላይ ሰፊ ትምህርት ይሰጣል ። • #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን "ከአንድ ምእተ ዓመት አርምሞ እሰከ ዘመናዊ የልህቀት ማእከልነት" የደብረታቦር መድኃኔዓለም የ4ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት ሁለንተናዊ አገልግሎትና ስኬቶች ፣የልማት ርእይና የወደፊት ዕቅዶች ታስነብባለች። #በኪነ ጥበብ ዐምድ #በርናባስ "በሚል ርእስ ታስነብባለች

  • አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ አ.ያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው ። ይህ ጻድቅም ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር የእስራኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና ። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር ። ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ ። የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷ የሚበራላችውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ወለደቻት ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ኢያቄምና ሐና ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።

  • ቴሌግራም፦👇 https://t.me/MkAddisAbabaCenterMedia ፌስቡክ፦👇 https://www.facebook.com/MKidusanaddisababacenter ቲክቶክ:- 👇 tiktok.com/@mk.aa.maekel.media የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ።

  • 12 авг.576из mkpublicrelation

    видео или голосовое, без подписи

  • ብሒለ አበው ዘወትር ረቡዕ ጀግኖች ከሌሉ አገርም የለችም፡፡ አገርም ከሌለች ጀግኖች አይገኙም እስካለ አገር ነጻነት መሥዋዕት መሆን እንዳይረሳና እንዳይፈዝ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ትውልድ የማስተማር የማስጠናትና የመቀስቀስ ኃላፊነት አለባት፡፡  አቡነ ሺኖዳ ዓለም እኔን ሳትንቀኝ አስቀድሜ ንቄያታለሁ፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ሰው አገሩን ጥሎ በሔደ ጊዜ ሁሉ ያዝንለታል፤ ከርስቱ ከጉልት በተለየ ጊዜ ሁለ ይራሩለታል ያለቅሱ ለታል፤ ከመንግሥተ ሰማያት ከተድላ ፤ ከመዓዛ የተለየ ሰውማ ምን ያህል ልቅሶ ማልቀስ ምን ያህል ዕንባ ማፍሰስ ይገባው ይሆን፡፡ ጮኾ ያለቅስ ብዙ ዕንባ ያፈስ ዘንድ የሚገባው ምን ያህል ይሆን፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እውቀትህን ሰጠኸኝ ሕግህንም ይረዳኝ ዘንድ ላክህልኝ፡፡ ማር ይስሐቅ እነሆ የመዳኔን ምሥጢራዊ ተአምር ሊነጻጽር የሚችል አንዳችም ነገር የለም፡፡ ጥቂት የደመ መለኮት ጠብታዎች መላውን ዓለም ዳግመኛ በሐዲስ ተፈጥሮ ፈጥረዋልና፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ

  • አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ስድስት በዚች ቀን ከቂሳርያና ከቀጰዶቅያ አገር የከበረች ኢየሉጣ ምስክር ሁና ሞተች ። ይቺም ቅድስት ከወላጆቿ ብዙ ገንዘብን ወረሰች ከታጋዮችም አንዱ በግፍ በላይዋ ተነሥቶ ጥሪቷን ሁሉ ወንዶች ሴቶች ባሮቿንም ለዳኛ መማለጃ በመስጠት ነጠቃት ። ይህም ዐመፀኛ እንደምትከሰውና ሐሰቱንም እንደምትገልጥበት በአወቀ ጊዜ ወደ ቂሳርያው ገዢ ሒዶ ክርስቲያን እንደ ሆነች ወነጀላት ። በልቧም እንዲህ አለች የዚህ ዓለም ገንዘብ ኃላፊ ጠፊ አይደለምን እነሆ እርሱን ነጠቁኝ የሰማይ ድልብን ገንዘብ ካደረግሁ ማንም ከእኔ ነጥቆ ሊወስድብኝ አይችልም ። ያን ጊዜም ወደ መኰንኑ ቀረበች በፊቱም ቁማ እንዲህ አለች እኔ ክርስቲያዊት ነኝ ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ ። መኰንኑም ስምቶ ተቆጣ ወደ እሳትም ውስጥ እንዲወረውሩዋት አዘዘ ነፍሷንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች ። ነገር ግን እሳቱ አልነካትም ምንም ምን አላቃጠላትም ከውኃ ውስጥ እንደሚወጣም ከእሳት ውስጥ አወጧት ። ስለ ገንዘቧና ስለ ጥሪቷም የማያልፍ የሰማይ መንግሥትን ወረሰች ቅዱስ ባስልዮስም ብዙ ወድሷታል ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን ። አርኬ. ሰላም ለኢየሉጣ እንበይነ ምግባራ ሠናይ ። በውስተ እቶን ዘእብእዋ በውዴተ ብእሲ እኩይ ። እንዘ ኢሀሎ ላዕሌሃ አሠረ ዋዕይ ። ወጽአት እምእሳት ከመ ዘወጽአ እማይ ። አምሳለ ፍቱን ወርቅ ወብሩር ጽሩይ ።

  • በአነዲት ቀንም ወደ ጣዖቶቻቸው ቤት ገባ ያን ጊዜ ጣዖታቱን ከመቀመጫቸው ጣላቸው የአገር ሰዎችም በአዩ ጊዜ ቁጣን ተመልተው አብዝተው ደበደቡትና ከአገር አበረሩት በጥዋትም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲጸልይ አገኙት ። ሁለተኛም በገመድ አሥረው ወደ ከተማው ውጭ ጐትተው በላዩም አፈር ቆልለው እንዳይሞት ጥቂት መተንፈሻ ትተው አልፈው ከዚያ ሔዱ ። በእግዚአብሔርም ኃያል ተነሥቶ ሔደ ስለ መመለሳቸውም ሲጸልይ አገኙት በእንዲህ ያለ ሥራም እየተጋደለ ዐሥር ዓመት ኖረ ። የክብር ባለቤት እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አይቶ ወደ ቀናች ሃይማኖት ልባቸውን መለሰ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከታናናሾች እስከ ታላላቆች ድረስ ሁሉንም አጠመቃቸው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖትም ጸኑ ። ከዚህም በኋላ በሃይማኖታቸው መጽናታቸውን ባየ ጊዜ ከንቱ ውዳሴ እንዳያመጣበት ፈርቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ አገሪቱንም በመስቀል ምልክት አማተበባትና ማንም ሳያውቅ ወጥቶ ወደ ሌላ አገር ሔደ ። ሰይጣንም በሚያስፈራው በብዙ ሥራ ይፈታተነው ነበር ቅዱሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኃይል አሸነፈው ። ጽኑ በሆነ ተጋድሎም ኖረ ያለ ዕንባም ሰዓት አላለፈችውም በጥርሶቹም አልሳቀም በከንፈሮቹም ፈገግ አላለም ስጋውን ቅባት አልነካውም ስጋውንና ደሙን ከሚቀበልበት ጊዜ በቀር ፊቱንና እግሩን አልታጠበም ። እናትና አባቱ በስድስት ዓመቷ ትተዋት የሞቱ እኅት ነበረችው ስሟም ማርያ ይባላል ዘመዶቿም ወደ አብርሃም አምጥተዋት ፈሪሀ እግዚአብሔር ሃያ ዓመት ሆናት ድረስ ትሕትናንም እያስተማራት በእርሱ ዘንድ አደገች ። ከዚህም በኋላ ሰይጣን ቀንቶባት ከአንድ መነኩሴ ጋር አፋቀራት ድንግልናዋንም አጠፉች ልብሷንና አስኬማዋን ለውጣ ወደ ሌላ አገር ሔደች ። አባ አብርሃምም በዚያች ሌሊት ታላቅ ከይሲ ርግቢቱን ሲውጣትና ጥቂት ቆይቶ ከእግሩ በታች ሲተፋት ራእይን አየ በማግሥቱም ማርያ ከቦታዋ ታጣች አባ አብረሃምም ደነገጠ ወደ እግዚአብሔርም ከብዙ ዕንባ ጋር ጸለየ እርሷን ያገናኘው ዘንድ ። ከጥቂት ወራትም በኋላ እኅቱ ያለችበትን አባ አብርሃም ሰማ ሰዎችም እንዳያውቁት የምንኩስናውን ልብስ ለውጦ ፊቱንም ተከናንቦ የወታደር ልብስ ለብሶ በፈረስ ተቀምጦ ወዳአለችበት አገር ሔደ ከዚያም ደርሶ ማርያ ወዳለችበት ገባ የመሸተኛንም ልብስ ለብሳ በአያት ጊዜ እጅግ አዘነ ነገር ግን እንዳትሸሸው እንድታውቀው አልሆነም ። ከዚህም በኋላ ለሚያገለግላት አሽከር ከማርያ ጋር የሚደሰትበት መብልና መጠጥ እንዲያዘጋጅ የወርቅ ዲናር ሰጠው ለርካሽ ሥራ እንደሚፈልጓት ሰዎች ይመስላት ዘንድ ። ከራት በኋላም ወደ ውስጠኛው ቤት አስገባት በሩንም ዘጋ እጇንም ይዞ ራሱን ገለጠላት በአወቀችውም ጊዜ ደንግጣ እንደ በድን ሆነች ልጄ ሆይ አይዞሽ ከእግዚአብሔር በቀር ከኃጢአት ንጹሕ የሆነ የለም ነገር ግን ወደ ንስሐ ተመለሺ ወደቦታሽም ገብተሽ የቀድሞ ሥርዓትሽን ያዢ አላት እርሷም እሺ አለች ። በነጋም ጊዜም ወስዶ በፈረሱ አስቀመጣትና ደስ እያለው ተመለሰ እኅቱን ከሰይጣን እጅ ማርኳልና ወደቦታውም በደረሰ ጊዜ የቤቷን ደጅ ዘግቶላት ማቅ በመልበስ እየተጸጸተች የተጋድሎንም ሥራ እየተማረች በብርታቷና በተጋድሎዋ ያዩ ሁሉ እስቲአደንቁ ጸንታ ኖረች ። እግዚአብሔርም በዚህ ቅዱስ ሰው እጆች ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ አጋንንትን በማስወጣት በሽተኞችን በማዳን ከአንዲት ዓመትም በኋላ የማርያን ንስሓዋን አይቶ በሰባ ዘመኑ የተመሰገነ እግዚአብሔርን እያመሰገነ አረፈ ። ማርያ እኅቱም ከለቅሶ ጋር ትርጎምትን በማብዛት ቀንና ሌሊት እየተጋደለች ሌሎች አምስት ዓመታትን ኖረች ከዚያም በኋላ አረፈች ያዩዋትም በፊቷ ውስጥ ስለአለው ብርሃን እግዚአብሔርን አመሰገኑ ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በቅዱሳን በጸሎታቸው ይማረን ለዘለአለሙ አሜን ። አርኬ ሰላም ለአብርሃም ዘተሰደ ወተዘብጠ ። እምሕርትምና ወካህድ አረማውያነ እስከ ሜጠ ወነፍስ እኅቱ ፄዊዎ እምኣፈ ከይሲ መሠጠ ። እስመ ኢጸግበ እምተጋድሎ እስከ ዕድሜሁ ሰለጠ ። መዋዕለ ዓመታት ሮ ኮናሁ ኅዳጠ ።

  • አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሔሴ አምስት በዚች ቀን ሌላው አብርሃም አረፈ ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ባለጸጎች ናቸው በተግሣጽና ፈሪሃ እግዚአብሔርን በማስተማር አሳደጉት ። በአደገ ጊዜም ያለ ፈቃዱ አጋቡት እግዚአብሔርም ወደሚፈቅደው ይመራው ዘንድ ሲለምን ኖረ ። በሰባተኛውም ቀን በዐልጋው ላይ ሳለ የእግዚአብሔር ቸርነት አነሳሥቶት ከጫጉላ ቤቱ ወጣ ብርሃን እየመራው ሒዶ ባዶ ቤት አግኝቶ በውስጡ ገብቶ ኖረ ምግቡን ከሚቀበልባት ከጥቂት መስኮት በቀር መዝጊያ ሠርቶ ደጁን ዘጋ ። ዓለምን ከተወ በዓሥረኛው ዓመት አባትና እናቱ ብዙ ጥሪት ትተውለት ሞቱ እርሱ ግን ለድኆችና ለችግረኞች በትኖ በጾምና በጸሎት ተወስኖ እየተጋደለ ኖረ ከአንድ ዐጽፍና ሰሌን በቀር ምንም ምን ጥሪት አላኖረም እንዲህም ሆኖ ዐሥር ዓመት ተጋደለ ። እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አየ በአንዲት አገርም አረማውያን ነበሩ ከታናሾቻቸው እስከ ታላላቆቻቸው ወደ ሃይማኖት ሊመልሳቸው የሚችል የሌለ በአንዲት ቀንም አባ አብርሃምን ጳጳሱ አሰበው ብርታቱንና ብልህነቱንም አይቶ ቄስ እንዲሆንና እነዚያን አረማውያን እንዲመልሳቸው አስገደደው በግድ አስጨንቆም ቅስና ሾመው ። ወደዚያም ቦታ ደርሶ ቤተ ክርስቲያን ሠራ እነዚያን አረማውያን እርሱን ፈጣሪያቸውን ወደ ማወቅ ይመልሳቸው ዘንድ በውስጧ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ።

  • ፮.ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት፣አልባሳት፣ ከወርቅ፣ ከብር ፣ ከነሐስ፣ ከብረትና ከዕፅ የተቀረጹ መስቀሎችና ልዩ ልዩ ንዋያተ ቅድሳት ፣ የባህልና የወግ ዕቃዎች ለብል፣ ለዝገት፣ ለፍሳሽ፣ ለእሳትና ለመሳሰሉት አደጋዎች እንዳይጋለጡ ፦ ሀ) ለቅርሳ ቅርስ አጠባበቅ አመች የሆነ ዕቃ ቤት እንዲዘጋጅ ያደርጋል። ለ) ቅርሳ ቅርሱን በኀላፊነት የሚጠብቁ ሠራተኞችና አስገጎብኝዎች እንዲመደቡ ያደርጋል። ሐ) በየበጀት ዓመቱ መጨረሻና የቅርሳ ቅርስ ኀላፊ ዝውውር በሚደረግበት ጊዜ ሁሉ ማንኛውም ቅርስ እየተቆጠረና እየተመረመረ ውጤቱ ደረጃውን ጠብቆ እስከ መንበረ ፓትርያርክ ድረስ መግለጽ ግዴታው ይሆናል። መ) ከሀገር ውስጥና ከውጭ አገር ጎብኝዎች ሲመጡ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት በየጊዜው በሚሰጠው የአፈጻጸም መመሪያና የክፍያ ደረጃ መሠረት ከጎብኝዎች ገቢ እንዲገኝ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ። ሠ)  ከጎብኝዎች የሚገኘው ገቢ በሕጋዊ ካርኒ እየተመዘገበ ከቤተ ክርስቲያኑ ጠቅላላ ሒሳብ ጋር እንዲያዝ ያደርጋል። ፯.ለአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ንብረትና ታሪካዊ ቅርሳ ቅርስ ኀላፊ ሆኖ የሚመደበው ካህን የገንዘብ ጉድለት ያልተገኘበት፣ በንብረት ማባከንም ሆነ በሌላ ወንጀል  ተከሶ በጉባኤ ያልተወሰነበት፣ በፍርድ ቤት  ያልተፈረደበትና በቂ ተያዥ ያለው መሆኑን ያረጋግጣል። ፰. ረዘም ላሉ ዘመናት ያገለገሉ አልባሳት፣ ንዋያተ ቅድሳትና መጻሕፍት አገልግሎት ከመስጠት ነጻ ሆነው ዓይነታቸው ሳይለወጥ ጥገና እየተደረገላቸው በቅርስነት ተከብረው እንዲቀመጡ ያደርጋል። ፱. ሀ/ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅርሶች በልዩ ልዩ ምክንያት በውሰት እንዲወሰዱ በሚጠየቅበት ጊዜ በክፍሉ ሊቀ ጳጳስ ሰብሳቢነት በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ተወስኖና ተፈቅዶ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትም አውቆት የማስፈጸሚያ ትእዛዝ ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤው ሲያደርሰው ሕጋዊ በሆነ  ደረሰኝ አስፈርሞ  ለተወሰነ ጊዜ በትውስት እንዲሰጥና እንዲመለስ ያደርጋል። ለ/ ለሚመለከተው ባለስልጣን ማስታወሻ በማቅረብ ወደ ነበረበት ቦታ እስኪመለስ ድረስ እስከ መጨረሻው ተከታትሎ ያስፈጽማል። ፲. ጠቅላላ የቤተ ክርስቲያኑ  ንብረቶች በየዓመቱ መጨረሻ እየተቆጠሩና እየተመዘገቡ መያዛቸውንና በጥንቃቄ መቀመጣቸውን ያረጋግጣል ። ያሉትንና የሌሉትንም ለይቶ በመዘርዘር ለአጥቢያው ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ሪፖርት ያቀርባል ።  ፲፩. በዐጸደ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ጥንታዊና አገር በቀል ዕፅዋት ደኅንነታቸው ተጠብቆ እና እንክብካቤ እየተደረገላቸው እንዲያዙ ያደርጋል።

  • የንብረት፤የንዋየ ቅድሳትና የቅርሳ ቅርስ ክፍል ሥራና ኀላፊነት ዘወትር ሰኞ፦ቃለዓዋዲ ምን ይላል? ፩.ከታቦተ ሕጉ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳት፣አልባሳት፣መጻሕፍትና ልዩ ልዩ ንብረቶች ሁሉ ለዚሁ ሥራ ተመርጦ በተመደበ ካህን (ቄሰ ገበዝ ) በጥንቃቄ እንድመዘገቡ ያደርጋል ። ፪.  የሰበካ ጉባኤውን አላቂና ቋሚ እቃዎችን የሚንቀሳቀሱ እና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በየአይነታቸው ለይቶ ይመዘግባል። ፫. ወጪ ሆነው ለሥራ የሚሰጡትን ዕቃዎችና ንብረቶች በደረሰኝ ያስረክባል፤ ወጪ የተደረጉ ንብረቶችም ሥራ ላይ መዋላቸውንና መጠበቃቸውን ይቆጣጠራል፤ የሚመለሱትንም መርምሮ ይረከባል ። ፬. ለቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጣዊ አገልግሎት የሚያስፈልጉትን ሁሉ እንዲሟሉ ያስደርጋል። ፭.በቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ቅርሳ ቅርሶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን ጥበቃ ያደርጋል፤ለጎብኝዎችና ለታሪክ ጸሐፊዎችም ተለይተው እንዲታዩ አድርጎ ምቹ በሆነ ሥፍራ በጥንቃቄ ያዘጋጃል ።

  • 10 авг.602из mkpublicrelation

    https://youtu.be/WM8tmVbLYuI

  • ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሕዝቅያስ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬም የተናገውን እንዲነግሩትና ስለርሱና ስለ ሕዝቡ ይጸልይ ዘንድ ወደ ኢሳይያስ መልእክተኞችን ላከ ። ኢሳይያስም ከእግዚአብሔር ቃልን ተቀብሎ እንዲህ ብሎ መለሰለት ልብህን አጽና አትፍራ በዓለሙ ሁሉ እንደርሱ ያለ ያልተሰማ ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሥራ. በሰናክሬም ላይ ሊሠራ እግዚአብሔርአለውና ። ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር የላከው መልአክ መጥቶ ከፋርስ ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ የለኪሶም ሰዎች ሲነጋ በተነሡ ጊዜ የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ሁሉ አገኙ የተረፉትም ከንጉሣቸው ጋራ ሸሽተው ነነዌ አገር ገቡ ። ሰናክሬምም ሊጸልይ ወደጣዖቱ ቤት በገባ ጊዜ ልጆቹ አድራማሌክና ሶርሶርበሰይፍ መትተው ገደሉት ። ሕዝቅያስምከሰናክሬም እጅ ድኖ የተመሰገነ እግዚአብሔርን አመሰገነ ። በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ታመመ ለሞትም ደረሰ የአሞፅ ልጅ ኢሳይያስም ወደረሱ መጥቶ እግዚአብሔር እንዲህ አለ ትሞታለህ እንጂ አትድንምና ቤትህን ሥራ አለው ። ሕዝቅያስም ፊቱን ወደግድግዳው መልሶ ወደ እግዚአብሔር ለመነ እያመሰገነውም እንዲህ አለ አቤቱ በቀና ልቡና በዕውነት ሥራ በፊትህ ጸንቼ እንደኖርኩ ፈቃድህንም እንደፈጸምሁ አስብ ብሎ ሕዝቅያስ ፈጽሞ ጽኑዕ ልቅሶን አለቀሰ ። ኢሳይያስም ወደ መካከለኛው ዐፀድ ደረሰ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረው ሒደህ ለወገኖቼ ንጉሥ ለሕዝቅያስ ያባትህ የዳዊት ፈጣሪ እግዚአብሔር እንዲህ አለ በለው ። ጸሎትህን ሰማሁ ዕንባህንም አየሁ እነሆ እኔ አድንሃለሁ እስከ ሦስት ቀንም ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ ። በዘመኖችህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨምሬልሃለሁ ከፋርስ ንጉሥ እጅም አድንሃለሁ ይቺንም አገር ስለ እኔና ስለ ባለሟሌ ዳዊት አጽንቼ እጠብቃታለሁ ። ሕዝቅያስም ኢሳይያስን እንዲህ አለው እግዚአብሔር እንደሚያድነኝና እስከ ሦስት ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ለመውጣቴ ምልክቱ ምንድ ነው ። ኢሳይያስም እንዲህ አለው የተናገረውን ቃል ያደርግ ዘንድ ከእግዚአብሔር የተገኘ ምልክቱ ይህ ነው እነሆ ጥላው ወደ ዐሥረኛው እርከን ቢመለስ ምልክቱ ይህ ነው ። ሕዝቅያስም እንዲህ አይደለም የጥላው ወደ ዐሥረኛ እርከን መመለስ ቀላል ነው ። መመለስስ ከሆነ ፀሐይ ወደ ዐሥረኛው እርከን ይመለስ አለ ። ኢሳይያስም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ ፀሐይም ዐሥሩን እርከን ተመለሰ ። ሕዝቅያስንም የምድር ነገሥታት ሁሉ ፈሩት እጅ መንሻም አገቡለት የእግዚአብሔርኃይል ከእርሱ ጋራ እንዳለ አውቀዋልና ። በመንበረ መንግሥቱም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነግሦ ኖረ ። እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም አረፈ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን ። አርኬ ሰላም ለሕዝቅያስ ዘጸለየ በሕቱ ። ዘተወሰከ ዘመኑ ወፈድፈደ እምኁልቁ እመኒ ሶቢሃ ተዐየርዋ ለጽድቁ ። በእደ መልአክ ሠራዊተ ፋርስ ኅልቁ ወለመልአኮሙ ቀተልዎ ደቁ ።

  • አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ አራት በዚች ቀን ከዳዊት ዘር የሆነ የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ ንጉሥ አረፈ ። ከጻድቁ ንጉሥ ከዳዊት በኋላ እንደ ሕዝቅያስ ያለ በእስራኤል ውስጥ አልተሾመም ከዚህ ጻድቅ ንጉሥ በቀር ሁሉም ጣዖትን አምልከዋልና መሠዊያም ሠርተዋልና ። እርሱም በነገሠ ጊዜ ጣዖታትን ሰበረ መሠዊያቸውንም አፈረሰ ከነሐስ የተሠራውንም እባብ ቆራረጠ የእስራኤል ልጆች አምልከውት ነበርና እግዚአብሔርም ዘመነ መንግሥቱን እጅግ አሳመረለት በጎ ነገርንም ሁሉ ሰጠው ። ሕዝቅያስም በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዘመን የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ኢየሩሳሌምን ከበባት ይህም ሰናክሬም, በዘመኑ እንደርሱ ያለ የሌለ ኃይለኛ ብርቱ የምድር ነገሥታት ሁሉ የፈሩትና የታዘዙለት ነው ። ሕዝቅያስም ከእርሱ ግርማ የተነሣ ፈርቶ አገሩን እንዳያጠፋ ብዙ ወርቅና ብር እጅ መንሻ ላከለት ሰናክሬምም ደስ ብሎት ምንም ምን አልተቀበለም በእርሱ ላይና በልዑል እግዚአብሔር ላይተቆጥቶ እግዚአብሔር ከእኔ እጅ ሊያድናችሁ አይችልም በማለት የስድብን ቃል ላከ እንጂ ። ሁለተኛም በልዑል ስም ላይ ስድብና ቍጣ የተጻፈበትን ደብዳቤ ላከ ሕዝቅያስም በሰማ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ አለቀሰ ልብሱንም ቀዶ ማቅ ለበሰ እንዲህም ብሎ ጸለየ ። አቤቱ የእስራኤል አምላክበኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ አንተም ብቻህን በዓለም መንግሥታት ላይ ንጉሥ የሆንክአንተም ሰማይና ምድርን የፈጠርህ ልመናዬን አድምጥ ። ዐይኖችህን ገልጠህ ተመልከት ሕያው እግዚአብሔር አንተን እያቃለለ ሰናክሬም የላከውን ቃሉን ስማ ።

  • ጠርቶትም መጥቶ በፊቱ በቆመ ጊዜ ደም ከመግል ጋራ በእግሮቹ ላይ ሲፈስ አየ አበ ምኔቱንም እጅግ አስጨነቀው። ልብሶቹንም ገልጦ በሥጋው ውስጥ የገባውን ያንን ገመድ አየው አበ ምኔቱም በእርሱ ላይ ተቆጥቶ ይህን ታደርግ ዘንድ እንዴት ደፈርክ አለው በታላቅ ድካምም ያንን ገመድ ከሥጋው ውስጥ አወጡት ቍስሉም እስከሚድን መድኃኒት እያደረጉለት ኃምሳ ቀኖች ያህል ኖረ።  ከዚህም በኋላ አበ ምኔቱ እንዲህ አለው ልጄ ስምዖን ሆይ እንግዲህስ ወደ ፈለግኸው ቦታ ሒድ ከዚያም ወጥቶ ሔደ በደረቅ ጕድጓድ ውስጥም ገብቶ ከእባቦችና ከጊንጦች ጋራ ኖረ። ከዚህም በኋላ አገልጋዩ ስምዖንን ለምን ሰደድከው አሁንም ፈልገህ መልሰው በፍርድ ቀን እርሱ ከአንተ ይሻላልና ብሎ ሲገሥጸው አበ ምኔቱ ራእይን አየ። አባ ስምዖንንም ከገዳሙ ስለመውጣቱ ገሠጸው።  በነጋም ጊዜ አበ ምኔቱ ራእይን እንዳየ ስለ አባ ስምዖንም እንደገሠጸው ለመነኰሳቱ ነገራቸው ወንድሞችም ደንግጠው እጅግ አዘኑ እስከምታገኙትም ሔዳችሁ በቦታው ሁሉ ፈልጉት አላቸው ሔደውም ፈለጉት ግን አላገኙትም። ከዚህም በኋላ መብራትን አብርተው ወደ ጕድጓድ ውስጥ ገቡ ያለ መብልና መጠጥም ከእባቦችና ከጊንጦች ጋራ ተቀምጦ አዩት።  ገመድም አውረዱለትና ከዚያ አወጡት በፊቱም ሰግደው በአንተ ላይ ያደረግነውን በደላችንን ይቅር በለን አሉት እኔንም ስለ አሳዘንኳችሁ ይቅር በሉኝ አላቸው። ከዚህም በኋላ ወደ ገዳማቸው ወሰዱት በብዙ ገድልም ተጠምዶ ሲያገለግል ኖረ።  ከዚህም በኋላ ከዚያ ገዳም በሥውር ወጥቶ ወደ አንዲት ዐለት ቋጥኝ ደረሰ። በእርስዋም ላይ ሳያረፍና ሳይተኛ ስልሳ ቀን ቆመ። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ስለ ብዙ ሰዎች ድኅነት እግዚአብሔር እንደ ጠራው ነገረው። ከዚያም ሔዶ ቁመቱ ሠላሳ ክንድ የሚሆን የድንጋይ ምሰሶ አገኘ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ በሽተኞችንም እየፈወሰ ወደርሱ የሚመጡትንም እያስተማረ ዐሥራ ሁለት ዓመት በድንጋይ ምሰሶው ላይ ቆመ።  አባቱም ፍልጎት ነበር ግን ሳያየው ሞተ እናቱ ግን ወሬውን ሰምታ ከብዙ ዘመናት በኋላ ወደርሱ መጣች በድንጋይ ምሰሶውም ላይ ቁሞ አገኘችው አይታውም አለቀሰች ከድንጋይ ምሰሶውም በታች ተኛች። ቅዱስ ስምዖንም ጌታችን በጎ ነገርን ያደርግላት ዘንድ ስለርሷ ለመነ ያን ጊዜም እንደተኛች አረፈችና ከደንጊያው ምሰሶ በታች ቀበሩዋት።  ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ እግሩን መታው ከእግሩ ትል እየወደቀ በአንዲት እግሩ ብዙ ዓመታት ኖረ። ከዚህም በኋላ የሽፍቶች አለቃ ወደርሱ መጥቶ ንስሐ ገባ ጥቂት ቀኖችም ኑሮ አረፈ በጸሎቱም ሕይወትን ወረሰ። ወደርሱ ስለሚመጡ ብዙ ሕዝቦችም የውኃ ጥማት እንዳያስጨንቃቸው ወደ እግዚአብሔር ለምኖ ከድንጋይ ምሰሶው በታች ውኃን አፈለቀላቸው። ዳግመኛም ወደ ሌላ ምሰሶ ተዛወረ በእርሱም ላይ እየተጋደለ ሠላሳ ዓመት ኖረ። ብዙዎች አረማውያንንና ከሀድያንን ካስተማራቸውና ወደ ፈጠራቸው እግዚአብሔር ከመለሳቸው በኋላ ክብር ይግባውና ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔደ በሰላምም አርፎ የዘላለም ሕይወትን ወረሰ።  ከዚህም በኋላ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባ ስምዖን እንዳረፈ በሰማ ጊዜ ካህናትን ዲያቆናትንና የአገሩን መኳንንቶች ከእርሱ ጋራ ይዞ የቅዱስ አባ ስምዖን ሥጋው ወዳለበት ደረሰ በታላቅ ክብርም ተሸክመው እየዘመሩና እያመሰገኑ ወደ እስክንድርያ አድርሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከሥጋውም ድንቆችና ተአምራቶች ታላቅ ፈውስም ተገለጡ። ቴሌግራም፦👇 https://t.me/MkAddisAbabaCenterMedia ፌስቡክ፦👇 https://www.facebook.com/MKidusanaddisababacenter ቲክቶክ:- 👇 tiktok.com/@mk.aa.maekel.media የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ።

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ነሐሴ ሦስት በዚህች ቀን በገድል የተጠመደ መስተጋድል የከበረ አባ ስምዖን ዘዓምድ አረፈ። ለዚህም ቅዱስ ስድስት ዓመት በሆነው ጊዜ አባቱ የበጎቹ ጠባቂ አደረገው። ወደ ቤተ ክርስቲያንም በመሔድ ሁል ጊዜ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይሰማ ነበር የእግዚአብሔርም ቸርነት አነሳሥቶት ወደ አንድ ገዳም ሒዶ መነኰሰ ብዙ ዘመናትም በገድል ተጠምዶ ሲጋደልና ሰውነቱን ሲያስጨንቅ ኖረ።  ከዚህም በኋላ ገመዱ ሥጋውን ቆርጦ እስቲገባ ድረስ በወገቡ ላይ ገመድን አሠረ። ሥጋውም ተልቶ ከእርሱ ክፉ ሽታ ይወጣ ነበር ስለ ክፉ ሽታውም መነኰሳቱ አዘኑ ተጸየፉትም ወደ አበ ምኔቱም ተሰብስበው ይህን መነኰስ ስምዖንን ከእኛ ዘንድ ካላወጣኸው አለዚያ አንተን ትተን ወደሌላ እንሔዳለን አሉት እርሱም ምን አደረገ አላቸው እነርሱም ጥራውና አንተ ራስህ እይ አሉት።