tgindex
ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

Статистика

ይህ የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት ቻናል ነው 👉👉ለጠቅላላ @weldwahid 👉👉ለአብነት እና ግእዝ ቋንቋ ትምህርት @weldwahidabinet 👉👉 ለቤተ መጻሕፍት አገልግሎት @Abaiyesuslib 👉👉ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @mels_asteyayet

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
25
Всего постов
31
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 091
−3 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
294
30 постов
Вовлечённость
14,1%
к подписчикам
Постов в день
3,6
всего 31
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
278
1/48двое суток
318
1/72трое суток
343

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • "እግዚአብሔር ይምረን ዘንድ በኛም ላይ ይቅር ይል ዘንድ ሹ ለምኑ ስለኛ ከቅዱሳን ጸሎትን ልመናንም ይቀበል ዘንድ ኹል ጊዜ ባማረ ነገር ቡሩክ ከሚኾን ምስጢር አንድነት እንድንቀበል የበቃን ያደርገን ዘንድ።"        ሥርዓተ ቅዳሴ

  • ‛‛ትዕግስት ማለት መከራን መሸከም ብቻ ሳይሆን፥ በመከራ ውስጥ ሆነው ለሚያሳድዱህ መጸለይ ነው።’’                         ✍️ቅዱስ ፖርፊሪዮስ

  • ‛‛ትዕግስት ማለት  ችግርን ዝም ብሎ መቀበል ብቻ ሳይሆን ችግር ውስጥም ሆኖም ፈገግ ማለት ነው።’’             ✍️ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰላልዊ

  • "ሁለትን ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ሳልሞትም አትከልክለኝ፤ ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው፤ ድኅነትንና ባለጠግነትን አትስጠኝ፤ ነገር ግን የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ" ምሳ 30÷7-8

  • "ጠላቴ ሆይ ብወድቅ እነሳለሁና በጨለማ ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሀን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልህ" ።                            ሚክያስ 7፥8

  • "ወደ ቤተ ክርስቲያን ስንመጣ እግዚአብሔር ደስ እንደሚያሰኘው ኾነን፤ በልባችን ቂም ጥላቻ ሳንይዝ፤" ወይም "እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል አንተም ይቅር በለን" የሚለውን ስንጸልይ ይህን ለጉዳታችን ሳናደርገው ልንመጣ ይገባናል (ማቴ.6፥12)፡፡ ይህ ኃይለ ቃል አስፈሪ ነውና፡፡ ይህን የሚጸልይ ሰውም ለእግዚአብሔር እንዲህ እያለው ነውና፡- “ጌታ ሆይ! እኔ ትቻለሁና አንተም ተውልኝ፡፡ እኔ ፈትቻለሁና አንተም ፍታኝ፡፡ እኔ ይቅር ብያለሁና አንተም ይቅር በለኝ፡፡ ባልንጀራዬን ይቅር ካላልሁት ግን አንተም ኃጢአቴን አትደምስስልኝ፡፡ እኔ በሰፈርኩት ቁና አንተም ደግሞ ስፈርብኝ።" ስለዚህ እነዚህን ነገሮች እንወቃቸውና ያቺን አስፈሪ ቀንና ያን ዘለዓለማዊ እሳት እናስታውስ፡፡ እነዚያን አስፈሪ ቅጣቶች በሕሊናችን ጓዳ በልቡናችን ሰሌዳ ላይ እናኑራቸውና ከሐስተኛ መንገዳችን ፍጹም እንመለስ፡፡ የዚህ ዓለም ትርኢት ከመኖር ወዳለመኖር ሲያልፍ ማንም ይኹን ማን ተጋድሎ (ንስሓ) መፈጸም የማንችልበት ጊዜ ይመጣልና፡፡ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው ዓለም ካለፈ በኋላ ማንም ምግባር ትሩፋት መሥራት አይቻለውምና፡፡ ይህ የተጋድሎ (የንስሓ) ሜዳ ካለፈ በኋላ ማንም የድል አክሊልን ለመቀዳጀት መጋደል አይቻለውምና፡፡ ያ ጊዜ የፍርድ ጊዜ ስለ ኾነ የንስሓ ጊዜ አሁን ነው። ያ ጊዜ አክሊላትን የመቀበል ጊዜ ስለ ኾነ የተጋድሎ ጊዜ አሁን ነው። ያ ጊዜ የዕረፍት ጊዜ ስለ ኾነ አሁን የድካም ጊዜ ነው። ያ ጊዜ ደመወዝ መቀበያ ጊዜ ስለ ኾነ አሁን የልፋት እና የጥረት ጊዜ ነው ። ስለዚህ ተነሥ፡፡ ተነሣና እነዚህን ኃይላተ ቃላት ስማቸው ብዬ እማልድሃለሁ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ንስሐና ምፅዋት

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ❤️ ነሐሴ (7) ቀን ❤️ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን!                 ✝️ ✝️ ✝️ 📖 የእመቤታችን የፅንሰት አጭር ታሪክ ጻድቁ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና በ እግዚአብሔር ፊት በቅንነትና በደግነት የሚኖሩ እውነተኛ አማኞች ነበሩ። ነገር ግን በጋብቻ ዘመናቸው ልጅ ባለመውለዳቸው ምክንያት እጅግ ያዝኑ ነበር። በወቅቱ የነበሩ የእስራኤል ልጆችም “ልጅ ያልወለደ ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው” እያሉ ያቃልሏቸውና ይነቅፏቸው ነበር። ቅዱሳኑ ግን በሰው ነቀፌታ ተስፋ ሳይቆርጡ፣ “የአባቶቻችን የእስራኤል አምላክ ሆይ! ለአይናችን ማረፊያ፣ ለልባችን ተስፋ የሚሆን ፍሬ ስጠን” እያሉ ዘወትር በጾምና በጸሎት ወደ አምላክ ይለምኑ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ቅድስት ሐና በቤቷ አትክልት ስፍራ ሳለች፣ አንዲት ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት ተመለከተች። በዚያን ጊዜ ልቧ ተነክቶ፦ “አቤቱ ጌታዬ! ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ፣ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ?” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች። ከዚህ በኋላ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ወደ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ዘንድ በመሄድ ታላቅ ስዕለት ተሳሉ፦ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን እንዲያገለግል፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ውኃ ቀድታ፣ መሶበ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ እናደርጋለን” አሉ፤ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስም ጸሎታቸውን አሳርጎ ባረካቸው። ሐምሌ 30 ቀን ቅዱሳኑ አስደናቂ ራእይ አዩ፦ ጻድቁ ኢያቄም፦ “ሰባት ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው፣ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” አለ። ቅድስት ሐና፦ “እኔም ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ፣ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ” አለችው። ይህንን ራእይ ካዩ በኋላ “ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን” ብለው ዕለቱን አልጋና ምንጣፍ ለይተው ለሰባት ቀን ያህል በጸሎት ተለይተው ሰነበቱ። በሰባተኛው ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለጻድቁ ኢያቄም በተራራ ላይ ሲጸልይ በተገለጸለት ጊዜ፦ “ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች፤ ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን፣ ለብዙዎች የሕይወት ብርሃንና ድኅነት የምትሆን ሴት ልጅ ትወልድልሃለች” ሲል አበሰረው። መልአኩ ለቅድስት ሐናም ተገልጦ የጌታን ፈቃድ ነገራት። በብስራተ መልአክና በፈቃደ እግዚአብሔር፣ እሁድ ዕለት በነሐሴ 7 ቀን ከሰው ሁሉ የበለጠች፣ ከመላእክትም የከበረች፣ የዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነችው አምላክን የምትወልደው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማኅፀነ ሐና ተፀነሰች።                      ✝️ ✝️ ✝️ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና በረከት፣ የቅዱስ ኢያቄምና የቅድስት ሐና ጸሎት አይለየን።🙏 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

  • አሁንም የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆችና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማኅበሮች ሆይ ይኽቺን የተባረከችና የተመረጠች ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናመስግናቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግልን የተባረከችዋን ፍሬ ያፈራችበትን ንጽሕት የምትኾን የሩካቤያቸው ዕለት እንደምን ያለች ዕለት ናት ከይሁዳ ወገን ለኾነችው ንጽሕት ርግብ መፀነስ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ የጾታዊ ተዋሕዷቸው ቀን ይኽቺ እንዴት ያለች የተመረጠች ቀን ናት፤ ለንጉሥ ማደሪያ አዳራሽ መመሥረት የተደረገባት (የኾነባት) የደስታ ቀን እንዴት ያላት ቀን ናት። (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ አርጋኖን ዘረቡዕ)

  • ሳምንታዊው የረቡዕ ጉባኤ "ሰዎች የሰው ልጅ ማን ይሉታል?" ክፍል -2 በ ዲ/ን ዳንኤል ታደለ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም

  • እግዚአብሔርን ምን ያስደስተዋል ?🤔 "አንድ ወንድም አባ መቃርስን  እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው" እግዚአብሔርን ምን ያስደስተዋል ሲል? "አባ መቃርስም እንዲህ ብሎ መለሰለት " እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው ዝምታና ንጹሕ ሐሳብ ነው፤ ሰው በምድር ሳለ ልቡ ከፈጣሪ ጋር መሆን አለበት።"                   "አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።" መዝ 51÷10😊 እግዚአብሔር ንጹሕ ልብ ይስጠን🙏

  • "እግዚአብሔር እንደሚያይህ፣ እንደሚያደምጥህና ስለአንተ በፍቅር እንደሚጨነቅ እመን። የአንተ ቲኒኒሽ ጉዳዮች በፍቅሩ ፊት ትልቅ ናቸው፥ አንተን ሚያሳስቡህ ትልልቅ ጉዳዮች ደግሞ በፍጹም ኃይሉ ፊት ከቶ ምንም አይደሉም።" ቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ፮ተኛ የተናገሩት

  • 🔔ምስባክ ዘነሐሴ ፮🔔 የዕለቱ ምንባባት ፩ ቆሮ ፫ ÷፲ -፳፪ ፩  ጴጥ፫ ÷፩ -፯ ሐዋ ፩፮÷ ፩፫-፩፱ የዕለቱ ወንጌል  ማር ፩፮÷፱  ፩፱ ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣለት ለመግደላዊት ማርያም ታየ እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም። ከዚህ በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ እነርሱም ሄደው ለሌሎች አወሩ እነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም። ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ  ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ። እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ያመነ የተጠመቀም ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል ያመኑትንም  እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ እባቦችን ይይዛሉ የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም እጃቸውን  በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ ። ቅዳሴ: ዘእግዝትነ አው ግሩሞ የዕለቱ ምስባክ ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ ኲሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን። መዝ ፵፬÷፩፪-፩፫ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨🍁🍁✨

  • ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media pinned a photo

  • "የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ቤት እግሩን ማራቅ ሲጀምር፣ ፍቅርም ከእርሱ ፈቀቅ ትላለች፤ ያን ጊዜ ከሚያየውና ከሚዳስሰው ሁሉ ጋር መጋጨት ይጀምራል። ግጭቱም ከሰዎች ጋር ብቻ አይደለም ከተፈጥሮ፣ ከአካባቢው፣ ከማኅበረሰቡና ከራሱ የሕሊና ሙግት ጋር እንጂ። ​ፍቅር በሌለበት ምድር ባዶነት ትነግሣለች፤ ፍቅር በሌለበት ልብ የውስጥ ሰላም አይገኝም። ፍቅር ከራቀ ደግሞ ሁሉ ነገር ድቅድቅ ጨለማ ይለብሳል። ​ስለሆነም የሰው ልጅ ሆይ! ሙሉ ፍቅርን ታገኝ ዘንድ ሁልጊዜም እግሮችህ ወደ አምላክህ ቤት ይፋጠኑ። ያኔ ለሕሊናህ ፍጹም ሰላምና ፍቅር ታገኛለህ፤ ያን ጊዜ ባዶነትህ ይሞላል፣ ጨለማህም በብርሃን ይተካል።"

  • "ስለ ሌላው ሰው ከመፍረድህ በፊት፣ በእርሱ ጫማ ውስጥ ገብተህ ለመራመድ ሞክር። ያኔ መፍረድ ትተህ መጸለይ ትጀምራለህ።" አባ ሙሴ ጸሊም

  • “​​​​​እያንዳንዱ የባለንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድ ስንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ።’’                  ✍️1ኛ ቆሮንቶስ 10፥24

  • ሳምንታዊው የረቡዕ ጉባኤ "ሰዎች የሰው ልጅ ማን ይሉታል?" ክፍል -1 የባለፈው ሳምንት ትምህርታችን በ ዲ/ን ዳንኤል ታደለ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

  • ​✨ የረቡዕ ጉባኤ ✨ ​ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና በሌሎች እምነቶች ያለው አስተምህሮ በስፋትና በጠለቀ ሁኔታ የሚዳሰስበት ትምህርት ተዘጋጅቷል። ​ለተከታታይ ሶስት ሳምንታት የሚሰጠው የዚህ ትምህርት ክፍል ፩ በዚህ ሳምንት ረቡዕ ይጀምራል! ​✨ መምህር፦ ዲ/ን ዳንኤል ታደሰ 📅 ቀን፦ ነሀሴ 6 ቀን  2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 12:30 - 1:30 📍 ቦታ፦ ወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ ​📖 “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” (ማቴ 16፥13)

  • "እግዚአብሔር በተነሣ ጊዜ ምን አደርጋለሁ ? በጎበኘኝ ጊዜ ምን እመልስለታለሁ ?"   ኢዮብ 31÷14

  • "አንተ ባትረዳኝስ ማን ይረዳኛል? አንተ ባትጠብቀኝስ ማን ይጠብቀኛል? የሰው ረድኤት ከንቱ ነውና።" ​አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (መጽሐፈ ሰዓታት)