ውሉደ ጥምቀት ዘገዳመ ኢየሱስ
Статистикаበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት በገዳመ ኢየሱስ ቤተ-ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል መነሻ በማድረግ የተቋቋመ ማህበር ነው
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 37
- 1/48двое суток
- 42
- 1/72трое суток
- 45
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
" ነሐሴ 7 ፀንሰታ ለማርያም እንኳን ለእናታችን ለድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ምልጃ በረከቷ አይለየን🙏⛪❤
*_<<7ቱ_ዕለታት_ለእመቤታችን_ምሳሌዋ_ናቸው>>_* *➕ በዕለተ እሁድ ትመሰላለች* - በዕለተ እሁድ አሥራወ ፍጥረታት አራቱ ባሕርያት ተገኝተዋል። ከሷም ዘኮነ ምክንያተ ፍጥረት በህላዌሁ እንዲለው አሥራወ ፍጥረት ጌታ ተገኝቷልና ። *➕ በዕለተ ሠኑይ ትመሰላለች* - በዕለተ ሠኑይ ከዚህ ምድር እስከ ብሩህ ሰማይ መልቶ የነበረውን ውሀ ከሶስት ከፍሎታል፣አንዱን እጅ ከላይ ሰቅሎታል ሐኖስ ነው አንዱን እጅ በዙሪያው ወስኖታል አንዱን እጅ አጽንቶ የብርሃን ማኅደር አርጎታል። ዕለቲቱ የሱዋ ጠፈር ከሱዋ የነሣው ሥጋ ብርሃን የጌታ ምሳሌ። *➕ በዕለተ ሠሉስ ትመስላለች* - በዕለተ ሠሉስ ለታብቀል ምድር ሐመልማለ ሣዕር ዘይዘራዕ በበዘርዑ ወበበዘመዱ በበአርአያሁ ወበአምሳሊሁ ባለ ጊዜ በእጅ የሚለቀሙ አትክልት በማጭድ የሚታጨዱ አዝርዕት በምሳር የሚቆረጡ ዕፀዋት ለሥጋውያን ምግብ የሚሆኑ ተገኝተዋል። የመንፈሳውያን ምግብ የሚሆን ጌታም ከሱዋ ተገኝቷልና ። *➕ በዕለተ ረቡዕ ትመሰላለች* - በዕለተ ረቡዕ በይቁሙ ብርሃናት በገጸ ማይ ካለ ጊዜ ለሥጋውያን ምግብ የሚሆኑ ፀሓይ ጨረቃ ከዋክብት ተገኝተዋል ። ለመንፈሳውያን ምግብ የሚሆን ጌታ ከሱዋ ተገኝቷልና ። *➕ በዕለተ ሐሙስ ትመሰላለች* - በዕለተ ሐሙስ ለታውጽዕ ባሕር ዘቦ መንፈሰ ሕይወት ባለ ጊዜ በልባቸው የሚሳው በእግራቸው የሚሽከረከሩ በክንፋቸው የሚበሩ በደመ ነፍስ ሕያዋን ሁነው የሚኖሩ ፍጥረታት ተገኝተዋል። በልባቸው የሚሳቡ የሰብአ ዓለም በእግራቸው የሚሽከረከሩ ከትሩፋት ወደ ትሩፋት የሚሄዱ የባሕታውያን በክንፋቸው የሚበሩ ተመስጦ ያላቸው የሰማዕታት ምሳሌ። ዕለቲቱ የሱዋ ባሕር የጥምቀት ምሳሌ ። - > ደመ ነፍስ ከሌላት ባሕር በደመ ነፍስ ሕያዋን የሚሆኑ ፍጥረታት እንደተገኙ ለምዕመናን የድኅነት ምክንያት የሚሆን ጌታ የሴቶች ልማድ ከሌለባት ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ለመገኘቱ ምሳሌ ነው። ➕ *በዕለተ ዓርብ ትመሰላለች* ከዕለተ ዓርብ በኵረ ፍጥረት አዳም ተገኝቷል ዳግማይ አዳም ጌታም ከሱዋ ተገኝቷልና ። ➕ *በዕለተ ቀዳሚት ትመሰላለች* በዕለተ ቀዳሚት ሥጋዊ ዕረፍት ተገኝቷል ወአእረፈ እግዚእነ እምኩሉ ግብሩ ዘአኃዘ ይግበር እንዲል ከሱዋም የመንፈሳውያን ዕረፍት ጌታ ተገኝቷልና ።
без подписи
"ይህች ለዘለዓለም ማረፈያዬ ናት ፡ መርጫታለሁ ና በዚህች አደራለሁ ፡፡ ባልቴቶችን እጅግ እባረካቸዋለሁ ድሆችዋንም እህል አጠግባቸዋለሁ #ካህናቷንም ድኀንነትን አለብሳቸዋለሁ ጻድቃኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋለ ፡፡ በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ ቀብቼ ላነግሥሁትም መብራት አዘጋጀለሁ ጣላቶቹንም እፍራትን አለብሳቸዋለሁ በእርሱም ቅድስነዬ ያፍራል" (መዝ 131 ÷14-18 )
እግዚአብሔር ወልድ ሰውን ማዳን በወደደ ጊዜ የመጣው በድንግል ማርያም በኩል ነው። እንግዲህ መድኀኒት የሆነው ጌታ በእርሷ በኩል ከመጣ መድኀኒት ፈላጊ የሆነ ሰው እርሷን ደጅ መጥናቱ ምን ይደንቃል? ኦ ድንግል ሰአሊ በእንቲኣነ። እንኳን አደረሳችሁ !!
“የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።” — ማቴዎስ 5፥4 ሰላም ሰላም እንደምን ቆያችሁ በቅድሚያ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እያልን የማህበራችሁ ኮሚቴ የሆኑት ማሙሽ ደሊል እና ሃብቱ ደሊል አባት ከዚ ዓለም ድካም ስላረፉ ለቅሶ እንድትደርሱ እና ነገ 17/11/2018 ከቀኑ 8:30 በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ግብሃተ መሬታቸው ስለሚፈፀም እንድትገኙ እናሳስባለን! ማህበራችን ውሉደ ጥምቀት በአቶ ደሊል ሞት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለወንድሞቻችን እና ለመላው ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል የአባታችንን ነፍስ በአፀደ ገነት ያሳርፍልን!!! አድራሻ :- ከብርሃና ሰላም ት/ቤት ፊት ለፊት ባለው ቅያስ ገባ ብሎ
ቅድስት ኪዳነ ምህረት እናቴ 16♥️🎚️ እመቤቴ ኪዳነምህረት ሆይ፤ በብርሃናዊው ኮከብ ለተመሰለው ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል፤ በጨለማ ለሚኖሩ ሕዝቦች ብርሃኑን አብርቶላቸዋልና፡፡ የቃል ኪዳኗ እመቤት ሆይ፡የአምላክ ቃል ኪዳኑ መዛግብት በዕለተ ዓርብ የተገኘው የደህንነታችን ተስፋ ያስገኘሽ ዕውነተኛ መዝገብ እኮ ነሽ፡፡ አባታችን ቀዳማዊ አዳም በጭንቅና በኃዘን ከገነት በተሰደደ ጊዜ ከልቦናው ኃዘን ተረጋግቶብሻልና፡፡ (መልክአ ኪዳነ ምህረት) ኪዳነ ምህረት እኛንም ከሀዘን ከመከራ ታውጣን🙏 ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ትሰውረን አሜን!!🙏
እግዚአብሔር የሚጠላቸው ሰባት ነገሮች። 1 ትዕቢተኛ ዓይን 2 ሐሰተኛ ምላስ 3 ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ 4 ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ 5 ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር 6 በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር 7 በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ። መጽሐፈ ምሳሌ 6፡16-19 ከሁሉም ደግሞ 7ተኛውን አብዝቶ ይጠላል።
እንደምን አደራችሁ የልኡል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንኳን ለፃድቁ አቡነ ኪሮስ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በዘመድ በወገን በገንዘብ በዕውቀት በውበትም እንዳንመካ ማሰተዋልን ይሰጠን የአባ ኪሮሰ አምላክ እግዚአብሔር በዓለም ፍቅር ተጠልፈን እንዳንወድቅ የአባ ኪሮሰ ምልጃ ፀሎት አይለየን! ለንሰሐ ያብቃን አሜን🥰❤️🩹🕯
*ሐምሌ_7_ልደቱ_ወዕረፍቱ_ለማርጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ* ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ አፈ በረከት የጋስጫው ኮከብ የቤተ ክርስቲያን መብራት አባ ጊዮርጊስ የደረሳቸው መጻሕፍት ኆኅተ ብርሃን መጽሐፈ አርጋኖን ወዳሴ መስቀል መጽሐፈ ብርሃን መጽሐፈ ሰዓታት ዘመዓልት ወዘሌሊት የቅዳሴ መጽሐፍ (መዓዛ ቅዳሴ) ጸሎተ ፈትቶ ውዳሴ ሐዋርያትና የሐዋርያት ማኅሌት መልክዓ ቊርባን እና የቍርባን ሥርዓት ፍካሬ ሃይማኖት መጽሐፈ ምሥጢር እንዚራ ስብሐት መሰንቆ መዝሙር ሕይወታ ለማርያም ተአምኆ ቅዱሳን ጸሎት ዘቤት ውስተ ቤት ውዳሴ ስብሐት ወሰላምታ ጸሎተ ማዕድ ቅዳሴ እግዚእ ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ውዳሴ ማርያም ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መዝሙረ ድንግል መልክዐ ውዳሴ ይዌድስዋ መላእክት (የሰዓታት ክፍል) መልክ0 ሥዕል ከበረከታቸው ያሳትፈን🤲
‹‹ሐምሌ 7›› አጋዕዝተ ዓለም ስላሴ በአብርሃም ቤት ተገኝተው ቤቱን የባረኩበት የአንድነታቸውንና ሶስትነታቸው ሚስጢር የገለጹበት ታላቅ በዓል ነው። በዚችም ቀን ልዩ የሆኑ ሦስቱ አካላት /ቅድስት ሥላሴ/ በኦሪት መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገቡ ያቀረበላቸውንም ተመገቡ፡፡ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት ለመረዳት በሥላሴ ፈቃድ መጻሕፍት እንዳስተማሩ ሊቃውንት እንደተረጉሙልን እንጂ ማንም በገዛ ፈቃዱ ተመራምሮ አይደርስበትም፡፡ የሐምሌ 7 ቀንም ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው ቸርነታቸውና ፍቅራቸውን የገለጹበት፣ ስለሆነ በዓሉን ስናዘክር ሥላሴን እናመሰግናለን፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ዕለት በአብርሃም ቤት እግዚአብሔር የተስተናገደበት፣ አንድነቱና ሦስትነቱ የተገለጠበት፣ አብርሃም እና ሣራ ካረጁ በኋላ ልጅ እንደሚወልዱ የተበሠረበት፣ ይሰሐቅንም እንደሚወልድ የተነገረበት ዕለት ነወ። ለአብርሃም ምሥጢሩን የገለጠ እግዘአብሔር ለሁላችን ይግለጥልን🙏
без подписи
без подписи
ዛሬ ሐምሌ 5 የብርሃናተ ዓለም የሐዋርያው ቅድስ ጴጥሮስ እና የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው፡፡ እንኳን አደረሳችሁ 🙏❤➴እንኳን ለአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ❤ ፃድቁ አባታችን ስደተኛ ልጆችህን በምልጃህ አስበን 🤲
⛪ እንደምን አደራችሁ ቤተሰቦቻችን "እግዚአብሔር ይመስገን በቸርነቱ ወርኅ ሠኔ ተፈፀመ ወርኅ ሐምሌን የበረከት የሰላም ወር ያድርግልን የሀገራችን የቤተክርስቲያን ሠላም ይመልስልን ቸሩ መድኃኔዓለም አሜን ። ልደታ ማርያም እናቴ ልደትሽ ልደታችን ነው ሀገራችንን ሰላም አድርጊልን ከኃጢዓት በቀር የልባችንን መሻት ፈፅሚልን በያለንበት አንቺ ጠብቂን አሜን🙏መልካም ቀን ይኹንልን በቀኝ ያውለን💜
🕊 🌺 🕊 [ 🕊 መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ 🕊 ] 🕊 🌺 🕊 እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። 🕊 💖 🕊 ❝ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። ❞ [ ሉቃ.፩፥፲፬ ] † የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ :- - በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ - በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት - በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ - እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ - የጌታችንን መንገድ የጠረገ - ጌታውን ያጠመቀና - ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው:: ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን :- ነቢይ : ሐዋርያ : ሰማዕት : ጻድቅ : ገዳማዊ : መጥምቀ መለኮት : ጸያሔ ፍኖት : ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች:: 🕊 ❝ በጣፋጭ አንደበቱ ወንጌልን የሚሰብክ ፣ ቀኙ የሚያቃጥል መለኮትን የዳሰሰች ፣ ጀርባው በግመል ጸጉር የተሸፈነ ፣ የዮሐንስን ደግነት ፈጽመን እንናገራለን። ❞ ❝ እውነት እላችኋለሁ ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፡፡ ❞ [ ማቴ.፲፩፥፲፩ ] 🕊 እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ስለወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
‹‹ሰኔ 30›› በዚህች ቀን የጌታን መንገድ ጠራጊው ፤ሐዋርያው ፤መጥምቁ ፤መምህሩ ፤ነብዩ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮሐንስ የልደት ቀኑ ነው። ጨካኝ ሄሮድስ የቤቴልሔም ህጻናትን ሲጨፈጭፍ መጥምቁ ዮሐንስ ከአናቱ ከቅድስት ኤልሳቤጥ ጋር ወደ ሲና በርሃ ተሰደደ። ኤልሳቤጥ በጣም አርጅታ ነበር ያን በርሃ ታዲያ እንዴት ቻለችው ያውም ልጅ አዝላ ልጅ ተሸክማ ረዳት ሳይኖራት ብቻዋን፤አባቱ ዘካርያስ በምኩራብ በመሰዊያው ፊት ልጅህን አምጣ ብለው አንገቱን ቆርጠው ገደሉት። ኤልሳቤጥም ሲና በርሃ ላይ ሞተች ህጻኑ ዮሐንስ ብቻውን ቀረ፤ የእናቱን በድነ ስጋ አቅፎ አለቀሰ፤ሁሉን ቻይ ሁሉን የሚያይ፤ ሁሉን የሚመረምር ጌታችን መድኀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን እናቴ ሆይ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ በበርሃ አርፋለች እንቀብራት ዘንድ እንሂድ አላት ደመና ጠቅሰው ዮሴፍና ሰሎሜን አስከትለው ሄደዋል ገንዘውም ቀብረዋታል። ከዚህ በኃላ እመቤታችን ልጄ ወዳጄ ሆይ ዮሐንስን ይዘነው እንሂድ አለችው የለም እናቴ ፤እርሱ እዚው ይቆያል መንገዴን ጠራጊ ነው፤ ኑሮው በዚሁ በርሃ ነው፤ጊዜው ሲደርስ ወደ ዮርዳኖስ ይመጣል ያጠምቀኝማል ያኔ አንድነቴ ሶስትነቴ ይገለጣል አላት፤ ትተውት ተመለሱ። ከመሞቱ በፊት እናቱ ያሰፋችለትን የግመል ቆዳ አገልድሞ አንቦጣ የሚባል ቅጠልና የበርሃ ማር እየበላ በበርሃ ኖረ 30 ዓመት ከ 6 ወር ሲሆነው፤ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ” እያለ ከበርሃ ወጣ ሉቃ 3፤3። የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ምልጃና በረከት ይደርብን
እኔ የምፈልገው የድንግል ማርያም ልጅ መሆን ነው ❤🙏 አባ ገብረ ኪዳን✝🥰 መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን ቤተሰብ በቀኝ ያውለን ከተናግሮ አናጋሪ ይሰውረን ክፉን በመልካም ይለውጥልን ደህና ዋሉ። 🦋
“የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።” — ማቴዎስ 5፥4 የሐዘን መግለጫ የወንድሞቻችን እና የማህበራችን የውሉደ ጥምቀት ዘገዳመ ኢየሱስ መንፈሳዊ ማህበር አገልጋይ እና ኮሚቴ ወንድወሰን ከበደ ወርቅነህ ከበደ እና ብሩክ ከበደ አባታቸው በዛሬው ዕለት ማለትም በ21/10/18 ስላረፉ በነገው ዕለት በ22/10/18 ምልዕልተ አድባራት ደብረ ቀራንዮ መዳኒዓለም ቤተክርስትያን በ8 ሰዓት ግብዓተ መሬታቸው ስለሚፈፀም ከ7:30 ጀምረን በቤታቸው አብረን በመገኘት ቤተሰቡን እናፅናና 🙏 ፈጣሪ ለቤተሰቡ ለወንድሞቻችን መፅናናትን ይስጥልን ነብሳቸውን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን አሜን !!!
ድንግልና እያላት እናት የሆነች፣ እናት ተብላ ተጠርታ ድንግልናዋ ያልጠፋባት ሴት በምድራችን ላይ አልነበረችም ወደ ፊትም ከቅድስተ ቅዱሳን ከድንግል ማርያም በስተቀር አትኖርም፡፡ ድንግልናን ከእናትነት እናትነትን ከድንግልና ይዛ የተገኘችና የዚህ ጸጋ (ሀብት) ብቸኛ ባለቤት የሆነችው እመቤታችን ብቻና ብቻ ናት፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን