መካነ አእምሮ የአንድምታ ት/ት ቤት⛪️
Статистика👉የዚህ ግሩፕ አላማ የእግዚአብሔር ቃል የሚነገርበት :የሐዲስ ኪዳን ትምህርት እና የተለያዩ መጻሕፍት የሚተረጎሙበት: ወንጌል: ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ: የክብረ በዓላት ይዘት ትምህርተ ሃይማኖት: ትምህረተ ኅቡዓት :ቅዳሴ:መጽሐፈ መነኮሳት :አንድምታ ይተረጎምበታል በዚ የቴሌግራም ቻናል። በመጋቤ ሐዲስ መ/ር ፀዳሉ ስንሻው እና በሌሎች መምህራን:ይሰጥበታል .. #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘለዓለም ትኑር::
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 34
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 109
- 1/48двое суток
- 124
- 1/72трое суток
- 134
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
ፅንሰታ ለማርያም ነሐሴ 7 በዚህች ዕለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተጸነሰች የእመቤታችን ወላጆችዋ ኢያቄም እና ሃና ይባላሉ እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ ኃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ ፦ ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:፡ ሐናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋየምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግዕዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ! ብላ ምርር ብላ አለቀሰች። እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን ፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ። ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ብሎ አሳረገላቸው። ከዚያም ቅድስት ቡርክት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ፦ ኢያቄም 7ቱሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት ሃናም እኔም አየሁ አለችው:ምን አየሽ ቢላት:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ። ይህንን ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው:: እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም ፤ ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሔዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን ? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሐና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች ። የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃዋ በረከቷ ይድረሰን🙏
‹‹አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ፡፡ መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት። ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት፡፡ ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው፡፡ ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ። ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት ‹‹በዚህ ቄስ መገደል እኮ ሕዝቡ ተደስቷል›› አለኝ፡፡ ‹‹እንዴት?›› ብለው ‹‹አላየህም ሲያጨበጭብ?›› አለኝ፡፡ ‹‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል›› አልኩት፡፡ ‹‹እንዴት?›› ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት፡፡" አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ በቦታው ሆነው የተከታተሉት ሙሴ ፓይላክን የተባሉ ግለሰብ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ለጳውሎስ ኞኞ ከነገሩት የተወሰደ፡፡ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ/ም
የጻድቁ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏 በበረሀ የሚጮኽ የፍጹም ባህታዊ ድምጽ 🙏 በሉቃስ 1÷14 እንደተጻፈው ቅዱስ ገብርኤልና አባቱ ትንቢት የተናገሩለት፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ያገለገለ፤ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፤ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ፤ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ ነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ። ዮሐንስ ማለት እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው፡፡ ካህኑ ቅዱስ ዘካርያስና ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ በመፈጸም ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ፡፡ ኤልሳቤጥም መካን ነበረች ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ዘወትር ይማጸኑት ነበር። ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን በማሳረግ ላይ ሳለም የእግዚአብሔር መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ጸሎቱ እንደ ተሰማ ነገረው፡፡ ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ እንደምትወልድ፣ ስሙንም ዮሐንስ እንደሚለው፤ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላበት ነገረው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም መልአኩን “እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ?” አለው፡፡ መልአኩም “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ እነሆም በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ ይህ ነገር እስከሚኾን ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም” አለው፡፡ የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሔደ፤ ከሁለት ቀን በኋላም አረጋዊቷ ቅድስት ኤልሳቤጥ ፀነሰች፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥም በመካንነቷ ከሰዎች የሚደርስባት ሽሙጥ ተወግዷላታልና “እግዚአብሔር በዚህ ወራት ከሰው ስድቤን ያርቅ ዘንድ እንዲህ አደረገልኝ” ስትል ለአምስት ወራት ተሸሸገች፡፡ ጌታችን ሊወለድ ስድስት ወራት ሲቀረው፣ ሰኔ 30 ቀን ንዑድ፣ ክቡር የሆነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ፡፡ አንደበቱ ተይዞ የነበረው ካህኑ ዘካርያም ስሙ “ዮሐንስ” ይባል ብሎ ሲጽፍ አፉ ተከፈተ፤ አንደበቱም ተፈታ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶም የቅዱስ ዮሐንስን ነቢይነትና አጥማቂነት ተናገሯል፡፡ በዚህም ምክንያት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በበረሀ የሚጮኽ የአዋጅ ነጋሪው ቃል ተብሎ ይገለጻል፡፡የገዳማዊ ሕይወት ምሣሌ የሆነውን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ስናስብ የገዳማውያንን ጸጋ፣ ገዳማውያንን መደገፍና፣ በዓታቸውንም ማጽናት ምን ያህል ግዙፍ የበረከት ሥራ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ አምላክ ነው። እግዚአብሔር በሰው ውስጥ ያለውን ሁሉን ያውቃል ይህ አምላካዊ ባሕርይ ነው። ኢየሱስም በሰው አካል የተገለጠ እግዚአብሔር ነውና ሁሉን አዋቂ ነው። “ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።” — ዮሐንስ 2፥24-25
#እንኳን_አደረሳችሁ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ቅጽል ስሞች👇 • መልአከ ምሕረት • መልአከ ሰላም • መልአከ ኃይል • መልአከ ምክር • መልአከ ኪዳን • መልአከ መዊዕ • መልአከ ሕይወት • መልአከ አድኅኖ • መጋቤ ብሉይ እስራኤል ዘሥጋን • የመራቸውና የጠበቃቸው • ባህር የከፈለላቸው • ጠላት ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያጠፋላቸው • በአምላኩ ፈቃድ መና ከሰማይ ያወረደላቸው • በለዓም እንዳይረግማቸው ሰይፉን መዞ መርገማቸውን የመለሰላቸው • ለመራገም የሄደውን እንዲመርቃቸው ያደረገው ....በዚህም መጋቤ ብሉይ ተብሎ የተጠራው • የባህራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረው • የቅድስት አፎምያን ፈታኝ በሥልጣን የረገጠው ... መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው!!! ቅዱስ ያሬድ "አስተምሕር ለነ ሰአልናከ በዐሠርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ " ብሎ እንደለመነው.... እኛም እስራኤል ዘነፍስ በቅዱስ ያሬድ ቃል ♥ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ!♥ ተማጽነንሃል! በአሥራ አራቱ ምልጃዎችህ ማልድልን" እንደ አምላክህ በሆነው ርኅሩህነትህ ከፈጣሪያችን ጋር አስታርቀን ክፉውን ሁሉ በምልጃህ ተቋቋምልን በጠላቶቻችን የተጻፈብንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት ቀይርልን በልዩ ልዩ ደዌ የሚፈትኑንን አጋንንትን ከአምላክህ በተሰጠህ ሥልጣን እርገጥልን .. እያልን እንለምነዋለን! የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ ሁላችንንም በያለንበት ይጠብቀን!
🔥 ጰራቅሊጦስ፦ የእሳት ላንቃና የቤተክርስቲያን ልደት ዛሬ "ጰራቅሊጦስ" ነው፤ ጌታችን "አጽናኝ እልክላችኋለሁ" ያለው ተስፋ በሐዋርያቱ ላይ የወረደበት ዕለት። 📍 የጰራቅሊጦስ ትርጉም "ጰራቅሊጦስ" የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "አጽናኝ"፣ "ረዳት" ፣ "መካሪ" ወይም "ጠበቃ" ማለት ነው። አባቶች እንደሚሉት፣ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ የተባለው፦ ሐዘናቸውን ስለሚያርቅ (አጽናኝ)፣ ደካማነታቸውን ስለሚያበረታ (ረዳት)፣ ምስጢርን ስለሚገልጥላቸው (መካሪ) እና በከሳሻቸው በሰይጣን ፊት ስለሚቆምላቸው (ጠበቃ) ነው። 📍 የ50ው ቀን ምስጢር (በዓለ ኀምሳ) ለምን 50 ቀን ሆነ? አባቶች እንዳስተማሩን፣ በእርጅና ዘመን ሙሴ በ50ኛው ቀን ከሲና ተራራ የድንጋይ ጽላት ሕግን ተቀብሎ ነበር። ዛሬ በጸጋው ዘመን ደግሞ፣ በ50ኛው ቀን የሥጋ ጽላት በሆነው በሐዋርያት ልብ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ሕግ ተጻፈ። ጌታችን ከትንሣኤ በኋላ 40 ቀን በምድር ቆይቶ ካረገ በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱ 10 ቀን በአንድ ልብ ሆነው ሲጸልዩ ቆይተው በ50ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው። 📍 እንደ እሳት ላንቃና እንደ ነፋስ ድምፅ መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ በሁለት ምልክቶች ተገለጠ፦ እንደ ኃይለኛ ነፋስ፦ ነፋስ የማይታይ ግን የሚሰማ ኃይል እንደሆነ፣ መንፈስ ቅዱስም የማይታይ ግን ዓለምን የሚለውጥ ኃይል መሆኑን ለማሳየት ነው። * እንደ እሳት ላንቃ፦ እሳት ዝገትን እንደሚያጠፋ፣ መንፈስ ቅዱስም የሐዋርያትን የፍርሃትና የድንቁርና ዝገት አጥፍቶ በልባቸው ፍቅርን ለማቀጣጠል ነው። አባቶች "እሳቱ አቃጣይ ሳይሆን አብሪ ነበረ" ይላሉ። 📍 የቋንቋዎች መገለጥ (የባቤል መፍረስ) በጥንት ዘመን በባቤል ሰዎች በትዕቢት ተነስተው ቋንቋቸው ተደባልቆና ተበታትኖ ነበር። ዛሬ በጰራቅሊጦስ ዕለት ግን፣ መንፈስ ቅዱስ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን ለሐዋርያት ሰጣቸው። አባቶች "መበታተን ያመጣው ቋንቋ ዛሬ ዓለምን በአንድ ወንጌል ለመሰብሰብ አንድነት ሆነ" ይላሉ። ሐዋርያቱ ባልተማሩት ቋንቋ ሁሉ መናገር ጀመሩ፤ ዓለምም ተደነቀች። 📍 የቤተክርስቲያን ልደት ቤተክርስቲያን በዕለተ ዓርብ በጌታ ጎን በተከፈተው ደም ተመሠረተች፤ ዛሬ በጰራቅሊጦስ ዕለት ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተወለደች (ሥራ ጀመረች)። ሐዋርያት ከፍርሃት ወጥተው አደባባይ በመቆም ሰበኩ፤ በአንድ ቀን ሦስት ሺህ ሰዎች አመኑ። ጰራቅሊጦስ የክርስቲያን ጉዞ የኃይል መጀመሪያ ነው። 📍 ማጠቃለያ፦ በዓለ ኀምሳ የደስታችን ማሳረጊያ ሳይሆን የቅድስና ሕይወታችን መጀመሪያ ነው። ዛሬ ራሳችንን እንጠይቅ፦ "የመንፈስ ቅዱስ እሳት በልባችን ይነድዳል? ወይስ በዓለማዊ ጭንቀት ጠፍቷል?" ጌታ ሆይ! በሐዋርያቱ ላይ ያወረድከውን መንፈስ ቅዱስን ዛሬም በእኛ ላይ ላክ፤ ልባችንን አንጻው፣ ሕይወታችንንም በመለኮታዊ ፍቅርህ አቃጥለው። "ወረደ መንፈስ ቅዱስ ላዕለ ሐዋርያት፤ ከመ እሳት ላንቃ" መንፈስ ቅዱስ እንደ እሳት ላንቃ በሐዋርያት ላይ ወረደ።)
без подписи
💢ሦስተኛ :-ሌላውመንፈስ ቅዱስ ወይም ጰራቅሊጦስ መጽንኢ ነው ያፀናል፡፡ ደቀመዛሙርቱ ፈሪዎች ነበሩ ድፍረት አልነበራቸውም ፅናት ሊሰጣቸው፣ድፍረት ሊሰጣቸው ማንንም ሳይፈሩ፣ሳያፍሩ ወንጌልን በኃይል እንዲሰብኩ፣በድፍረት እንዲሰብኩ የሚያደርግ፣የሚያፀናው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፀጋ በሰማይ ወረደ፡፡ አፀናቸው፣ ድፍረት ሰጣቸው ዛሬም ፍርሀትን አርቆ ድፍረቱን እግዚአብሔር አምላክ ያድለን፡፡ ፃድቃንን፣ሰማዕታት፣ሐዋርያት ግርፋቱን፣ስቅላቱን መከራውን ሳይፈሩ በድፍረት አስተምረዋል፣መስክረዋል፣ለምን መንፈስ ቅዱስ ስላፀናቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሀይል መንፈስ ነው፤መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ ነበር ያላቸውና የሐዋርያት ሥራ 1፡8 ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ በነሱ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ተላበሱ በኃይል ወንጌልን ሰበኩ፣በኃይል አስተማሩ በማባባል አይደለም እውነቱን እየተናገሩ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ አንድ ጊዜ በሰበከው 3000 ሰዎች አሳመነ ክብር ምስጋና ይግባው ለአምላካችን፡፡ 💢ሰለ ጰራቅሊጦስ በሊቃውንት አንደበት ምን ይላሉ? አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በበዓለ ኀምሳ ምንባብ ላይ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ስለተባለበትና ተስፋ በተሰጣቸው በኀምሳኛው ቀን ወርዶ ስለ ሠራው ሥራ እንዲህ በማለት ያብራራል። ‹‹ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢተሰምየ ጰራቅሊጦስሃ ዘእንበለ አመ ይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ እፌኑ ለክሙ ካልአ ጰራቅሊጦስሃ። ጰራቅሊጦስ ብሂል ናዛዚ ብሂል በነገረ ጽርዕ ……መንፈስ ቅዱስም ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሌላውን አጽናኝ እልክላችኋለሁ›› ከማለቱ በፊት ጰራቅሊጦስ አልተባለም ጰራቅሊጦስ ማለት በጽርዕ ቋንቋ አጽናኝ ማለት ነው ስለምን አጽናኝ ተባለ ደቀ መዛሙርቱ ወልድ ካረገበት ቀን ጀምሮ ጰራቅሊጦስ እስከ ወረደበት ቀን ድረስ ያለቅሱ ነበረና ስለዚህም ወልድ መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አለው። የስሙ ትርጓሜ ግን አስቀድመን እንደተናገርነው አጽናኝ ማለት ነው። (ዮሐ. ፲፬፥፲፭) በዓለ ጰራቅሊጦስ የሚከበረው ርደተ መንፈስ ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመሆኑ ምክንያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል ነው፤ በዕለቱም ኢየሩሳሌም በተባለችው ቤተክርስቲያን ስለመጽናት፤ ከግለኝነት ይልቅ መንፈሳዊ አንድነትን ስለማስቀደም እና ስለመጸለይ እንማራለን ብርሀን ምሥጢር ገለጠላቸው 💢ወገኖቼ አስተውሉ? በሰው ልጆች ኃጢያት፣በደል፣ጥፋት ምክንያት ቋንቋ ተደባለቀ በሰናዖር ምድር ላይ መግባባት አልተቻለምን ነበር ከዛ በፊት ግና በአንድ ቋንቋ ነበር የሚግባቡት በኃጢአት ምክንያት ተከፋፍሎ የነበረ ቋንቋ ደግሞ አሁን እግዚአብሔር መንፍስ ቅዱስ ሁሉ አንድ ለማድረግ ለአባቶቻችን ለቅዱሳን ሐዋርያት ቋንቋ፣ልሣን፣አንደበት ገለጠላቸው አለሙን ሁሉ በቋንቋው እንዲያስተምሩ አደረጋቸው ዛሬ ታድያ አሁን የተፈጠረ ይመስል ቋንቋ መገዳደያለ :የመለያያ አድርጎናል በተለይ ኢትዮጵያውያን በበዓለ ጳራቅሊጦስ ዘዳግም ቋንቋ በፀጋ የተሰጠበት ቀን ነው የቤተክርስቲያን ልደትም ናት የበዓላት ሁሉ እመቤት ይላታል ዮሐንስ አፈወርቂ ቋንቋ መነካከሻ፣መለያያ፣መጣያ አይደለም ከእግዚአብሔር የሰጠን ፀጋ ነው በፍቅር፣በሰላም እንድንግባባበት፣የምንስማማበት ነው፡፡ ቋንቋችን ቢለያይም ሁላችን አንድ ነን የአዳም ልጆች ብቻ አይደለም በተለይ ክርስቲያኖች ዳግም ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የተወለድንበት ነው ሰው ሁሉ በቋንቋ ምክንያት ልንጣላ፣ልንከፋፈል አይገባንም፡፡ እግዚአብሔር አምላክ አሁንም በቋንቋ ምክንያት ለምንጣላው፣ለምንነካከሰው ይሄንን የፍቅር ምሥጢር ገልፆ በሰላም እንድንኖር ይርዳን፡፡ ከሰዓት አኳያ ሌሎቹን ጠቆም ላድርጋችሁ 💢 ጰራቅሊጦስ ወይም መንፈስ ቅዱስ መንጽሒ ነው ያነፃልና? ከበደላችን አንፅቶናል፣ ከርኩሰታችን ቀድሶናል እነሆ አዳም እና እኛ ልጆቹ ከብልየት ኃጢያት የታደስነው፣በአእምሮ የጎለበትነው፣የኃጢአታችንን ስርየት ያገኘነው በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ነው፡፡ ከታጠብን በኃላ የቆሸሽን፣ከተቀደስን በኃላ የረከስን አለንና አምላካችን አሁንም እንደገና ሁላችንንም ከበደል እድፍ እና ጉድፍ ይጠበን፣ያንፃን መንፈስ ቅዱስ የወረደው ሊያነፃን ነውና፡፡ 💢ሦስተኛ :-ሌላውመንፈስ ቅዱስ ወይም ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ነው ያፀናልና፡፡ ደቀመዛሙርቱ ፈሪዎች ነበሩ ድፍረት አልነበራቸውም ፅናት ሊሰጣቸው፣ድፍረት ሊሰጣቸው ማንንም ሳይፈሩ፣ሳያፍሩ ወንጌልን በኃይል እንዲሰብኩ፣በድፍረት እንዲሰብኩ የሚያደርግ፣የሚያፀናው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፀጋ በሰማይ ወረደ፡፡ አፀናቸው፣ ድፍረት ሰጣቸው ዛሬም ፍርሀትን አርቆ ድፍረቱን እግዚአብሔር አምላክ ያድለን፡፡ ፃድቃንን፣ሰማዕታት፣ሐዋርያት ግርፋቱን፣ስቅላቱን መከራውን ሳይፈሩ በድፍረት አስተምረዋል፣መስክረዋል፣ለምን መንፈስ ቅዱስ ስላፀናቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሀይል መንፈስ ነው፤መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ ነበር ያላቸውና የሐዋርያት ሥራ 1፡8 ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ በነሱ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ተላበሱ በኃይል ወንጌልን ሰበኩ፣በኃይል አስተማሩ በማባባል አይደለም እውነቱን እየተናገሩ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ አንድ ጊዜ በሰበከው 3000 ሰዎች አሳመነ ክብር ምስጋና ይግባው ለአምላካችን፡፡ 💢አራተኛው:- ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ ቀድሞ በንፋስ አምሳል መንፈስ ቅዱስ ብዙ ተአምራት አድርጓልና 💢ለምሳሌ ያህል:-የእግዚአብሔር መንፈስ በዉኃ ላይ ሰፍሮ ነበር ዘፍ 1:2 በዉኃይ ላይ መስፈፉ በጸጋ መንፈስ ቅዱስ በዉኃ (በጥምቀት) ለዘመነ ሐዲስ ሰዎች የሚስጥ መሆኑን ለማሳየት ነበር። ነፋስ ድምጽ አለው ድምጹን ትሰማለህ መልኩም ግን አይታይም መንፈስ ቅዱስም ምሥጢር ሲገልጥ ቋንቋ ስያናገር እንጂ የመንፈስ ቅዱስ መልክ አይታይምና 💢 ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ 2እኛ ጼጥሮስ 1:21 ለምሳሌ ያህል ቅድስት ኤልሳቤጥ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? ሰዎች ሲናገሩ ይታያሉ እንጂ የምያናግራቸው ግን መንፍስ ቅዱስ ነው። 💢ሌላው በንፋስ መምሰሉ ንፋስ ከየት ተነስቶ እንደሚመጣ ወዴየትም አንደሚገባ አይታወቅም የመንፈስ ቅዱስም ባሕርይ አይታወቅም አይመረመርም መንፈስ ቅዱስ በቦታ አይወሰንም ዮሐ 14:17 💢ንፋስ ምርቱን ከገለባው ይለያል ገለባውን (እብቁን)ይወስዳል ይበትናል። ዐዉሎ ነፋስም እንደ እብቅ ጠረጋቸው (ኢሳ 40:24) መንፈስ ቅዱስም ጻድቃን ከኃጢአተኞች ለይቶ ይቀድሳችዋል (1እኛ ጴጥ 1:1 መንፈስ ቅዱስ በርናባስ እና ጳውሎስ እንደ ጠራቸው አንደ ቀደሳቸው እኛም እንዲቀድሰን መንፈስ ቅዱስ ወርዷል ። 💢ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል አሜን። @አዘጋጅ Yonas Zedebreyidras
➢ የስብከቱርዕስ:-በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው ሐሥ 2:4 ➢የትምሕርቱ ዓላማ:- የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከተቀበልን ብኋላ የምናገኘው ጸጋ ማስረዳት ነው። ➢መግብያ (ጸሎት:ሰላምታ:ማብራሪያ :ማሳሰብያ) ▶ጸሎት:-ይትባረክ አምላከ አበዊነ ለዘአብጸሐነ እሰከ ዛቲ ሰዓት እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ በዚህ ዓለም ስንኖር በበደልና በኃጢአት ወድቀን እንዳንቀር ደካሞች ነንና መንግስትህን እንወርስ ዘንድ በመንፈስ ረድኤት ጠብቀህ በቤትህ ጸንተን እንኖር ዘንድ እንለምንሃለን ። ◆ የተከበራቹ አዕይተ እግዚአብሔር አባቶች ካህናት መምህራን እግዚአብሔር የምትወዱት ይልቁንም እግዚአብሔር የሚወዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ምዕመናን ወምዕመናት እንዲሁም ሕጻናት በልዑል እግዚአብሔር ስም ሰላም እላችኋለሁ እንደምን ሰነበታችሁ እንደምን ዋላችሁ ? አሜን በባሕሪው ሞት በመንግሥቱ ሽረት የሌለበት ቅደመ አለም የነበረ አለምን የፈጠረ አለምን አሳልፎ የሚኖር የአባቶቻችን አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር በሀብቱ ሰቦ በረድኤቱ አቅርቦ እሰከዚህች ሰዓት ስላደረሰ ስሙ ዘወትር የተመሰገነ ይሁን አሜን ። የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ የድኅነታችን ምክያት ናትና: ክብርና ዉዳሴ ይድረሳት እንዲሁም የመላእክት ጠባቂነት የቅዱሳን ተራዳኢነት አይለየን አሜን። ▶ማሳሰቢያ :- ሁላችንም በተረጋጋ መንፈስ ተቀምጠን በጽሞና እንድንከታተል አምላክን ይርዳን። ➢በርዕሱ ላይ እንደተገለጸው በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው የሐዋ2:4 ትንሳዔውን ባከበርን በ50ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ የወረደበትን በዓለ ጰራቅሊጦስ እናከብራለን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ማነው?፣ ለምንድን ነው የወረደው?፣ መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ አባቶቻችን ሐዋርያት ምን አገኙ እኛስ ምን አገኘን በዓሉን ስናከብርስ እኛ ምን ልናደርግ ይገባናል ጰራቅሊጦስ ምንድነው የሚለው በትንሹ እንመለከታለን? በመጽሐፍ ቅዱስ ሰለ መንፈስን ቅዱስ በብዙ ቦታ ተገልጾ ይገኛል ለምሳሌ ያህል በትንቢተ ኢሳያስ 51:12 የማጽናናችሁ እኔ ነኝ እንዳለው በነብዩ አድሮ ክርስቶስ ፥ የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ትፈራ ዘንድ አንተ ማን ነህ? መንፈስ ቅዱስ በግሪኩ ጰራቅልጦስ ይለዋል ጰራቅልጦስ ማለት ናዛዚ ማለት ነው፤ አፅናኝ፣አረጋጊ ማለት ነው፡፡ ▶መንፈስ ቅዱስ ለምን ወረደ ስንል? ሊያፅናናን ወረደ፣ ሊያረጋጋን ወረደ፣ በተለይም እረኛቸውን ላጡት በጎች ሰብሳቢና አፅናኝ ሊሆን ወረደ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት አምላካችን መድኃኒታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቶ በክብር እንደሚያርግ ሲነግራቸው ጊዜ ልባቸው በሀዘን ተሞልቶ ነበር፡፡ ተጨንቀው፣ታውከው ነበር፡፡ ለዚህ ነው እንዲህ እያለ ያፅናናቸው፡- በዮሐንስ ወንጌል 16፡7 ʽʽእኔ ብሄድ ይሻላችኋል እኔ ባልሄድ አፅናኚ ወደ እናንተ አይመጣም እና እኔ ብሄድ ግን አፅናኙን ወደ እናንተ እልክላችኋለው ነበር ያላቸው ፡ የተጨነቁትን ሊያረጋጋ፣ያዘኑትን ሊያፅናና፣ለታወኩት ፀጥታን ሰላምን ሊሰጣቸውየ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፀጋ ወረደ። ▶የተነገረው ትንቢት እንዲፈፀም ከሰማየ ሰማያት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፀጋ ወረደ፡፡ በነቢዩ ኢዩኤል ላይ አድሮ አምላካችን እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሯል ትንቢተ ኢዩኤል 2፡28 ʽʽ ስለዚህ እንደዚህ ይሆናል መንፈሴን በስጋ ለባሹ ሁሉ ላይ አፈሳለው፡፡ʼʼ ብሎ አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለቃሉ ታማኝ ነው እና ይህ ትንቢት እንዲፈፀም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፀጋ ከሰማይ ወረደ፡፡ ▶ሌላው የአምላካችን መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በነሱ በፀጋ ባደረ ጊዜ ተፅናኑ፣ተረጋጉ፣ከእነርሱ አልፈው ተርፈው ዓለምንም አፅናኑ፤ዓለምንም አረጋጉ፡፡ የሚያፅናና ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ፡፡ የተጨነቀውን ዓለም፣ የታወከውን ዓለም በተሰጣቸው መንፈስ ቅዱስ ፀጋ አለም አፅናኑ፣ አፅናኝ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ ▶የሰው ልጅ በተለያዩ ጭንቀቶች በእራሱ ላይ እርምጃ ይወስዳል በሽጉጥ እራሱን የሚገል አለ? ገንዘብብቻውንችግር አይፈታምና እውቀት ብቻውን ከጭንቀት አያርቅም ስልጣን ብቻውን ምንም አያደርግምና የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ያፅናናል፣ያረጋጋል፡፡ በትንቢተ ኢሳይያስ 51፡12 ʽለዚ ነው የማፅናናችሁ እኔ ነኝ ያለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደ አፅናኙ መንፈስ ቅዱስ ነው እኛ ሰዎች ግን የጤና ጉዳይ፣የትዳር ጉዳይ፣የቤ/ክ ጉዳይ የሚያስጨንቀን በውስጥም በውጭም የሀገር ጉዳይ የሚያስጨንቀን ብዙ አለ የሰላም ጉዳይ የሚያስጨንቀን እንደዚህ እየተበላላን፣እየተነካከስን፣ሰላም አጥተን ወንድም ወንድሙን ሲገድለው አይተናል በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ ሁሉ ያስጨንቀናል በእውነቱ ክርስቲያኖች ፡አንዳንዶቻችን በገዛ ሀገራችን ስደተኛ እስከመሆን ደርሰናል፡፡ የሚያፅናናን፣ የሚያረጋጋን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ አሁንም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፀጋው ለሁላችንንም መረጋጋቱን፣መፅናናቱን፣ሰላሙን ያድለን? ▶ሁለተኛ፡- እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፀጋ ለምን ወረደ ስንል በፀጋ የወረደበት ምክንያት ምሥጢር ሊገልጥ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ወይም ጰራቅሊጦስን ከሣቴ፤ምሥጢር ገላጭ ማለት ነው፡፡ ለደቀመዛሙርቱ ምሥጢር ሊገልጥ ከሰማይ በፀጋ ወረደ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሏቸው ነበር ለደቀመዛሙርቱ በዮሐንስ ወንጌል 16፡12-15 ጀምሮ መመልከት ይቻላል
без подписи
☁️ ዕርገት፦ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ወደ ቀደመ ክብሩ የተመለሰበት ዕለት እኔ ያ ደመና ነኝ—የክብርን ጌታ ተቀብዬ ከደቀ መዛሙርቱ ዓይን የሰወርኩ። ዛሬ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሰማይና ምድር ተገናኙ። ጌታዬ ወደ ሰማይ የወጣው መሬታዊውን ሥጋችንን ሰማያዊ ሊያደርገው፣ የጠፋውን ክብራችንን ሊመልሰው ነው። 📍 የ40ው ቀናት ትምህርትና ፍጻሜ ጌታችን ከትንሣኤ በኋላ ለ40 ቀናት በምድር መቆየቱ ለብዙ ምስጢር ነው። አባቶች እንደሚሉት፣ ሙሴ ሕጉን ለመቀበል 40 ቀን እንደቆየ፣ ጌታም አዲሱን የጸጋ ሕግና የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ለሐዋርያት ለማስተማር 40 ቀን ቆየ። ዕርገት የዚህ ትምህርት ማኅተም ነው። ጌታችን በሥጋ ተገልጦ የማስተማሩ ሥራ አብቅቶ፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በምስጢር የሚመራበት አዲስ ምዕራፍ ተጀመረ። 📍 "እጆቹን አንስቶ ባረካቸው" (የበረከት ዕርገት) ጌታችን ወደ ሰማይ ሲወጣ የመጨረሻው ሥራው "መባረክ" ነበረ። አባቶች "እጆቹን አንስቶ እየባረካቸው ሳለ ከእነርሱ ተለየ" (ሉቃ. 24:51) የሚለውን ሲተረጉሙ፦ "ያ በኃጢአት ምክንያት ተዘግቶ የነበረው የበረከት ደጅ ዛሬ ተከፈተ" ይላሉ። ጌታችን ወደ ሰማይ የወጣው በረከቱን በምድር ላይ ትቶ ነው። ዛሬም ቤተክርስቲያን የምትኖረው በዚያ በዕርገቱ ዕለት በፈሰሰው መለኮታዊ ምርቃት ነው። 📍 የሥጋችን ወደ ሰማይ መግባት (የክብር ዕርገት) የዕርገት ትልቁ ምስጢር ከድንግል ማርያም የነሳው መሬታዊ ሥጋ ዛሬ በኪሩቤልና በሱራፌል ትከሻ ላይ ካለው ዙፋን በላይ ከፍ ማለቱ ነው። አባቶች "አዳም ሆይ! ተመልከት፤ ያ በመርገም ምክንያት ወደ መሬት ወርዶ የነበረው ሥጋህ ዛሬ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ" ይላሉ። ዕርገት የሰው ልጅ ተፈጥሮ ካረጀበት የኃጢአት ጉድጓድ ወጥቶ ወደ ዘላለም ክብር የገባበት ዕለት ነው። 📍 "ስፍራ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ" (የተስፋ ዕርገት) ደቀ መዛሙርቱ ጌታቸው ሲለይ አዝነው ነበር። እርሱ ግን "ባለሁበት እናንተም እንድትኖሩ ስፍራ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ" አላቸው። ዕርገት ለእኛ ትልቅ ተስፋ ነው። ጌታችን ወደ ሰማይ የገባው ለብቻው ለመኖር ሳይሆን፣ ለእኛ መንገድ ሊቀድልንና ማደሪያ ሊያዘጋጅልን ነው። ዛሬ ዕርገትን ስናስብ፣ ትክክለኛው ቤታችን ምድር ሳይሆን ሰማይ መሆኑን እናረጋግጣለን። 📍 የዳግም ምጽአት ዋስትና ጌታችን ሲያርግ ሁለት መላእክት በነጭ ልብስ ተገልጠው ለሐዋርያቱ እንዲህ አሉ፦ "ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ፣ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል" (ሐዋ. 1:11)። ዕርገት የዳግም ምጽአቱ ማረጋገጫ ነው። ዛሬ በክብር የሄደው ጌታ፣ ነገ ደግሞ በክብር ሊፈርድና ቅዱሳኑን ሊወስድ ይመጣል። 📍 ማጠቃለያ፦ ዕርገት የድል ቀን ነው። ጌታችን ሰማይንና ምድርን አስታረቀ፤ ሥጋችንን ከሰማያዊ መላእክት ጋር ቀላቀለ። ዛሬ በዕርገት ዕለት ራሳችንን እንጠይቅ፦ "ልባችን ከምድራዊ ጭንቀት ወጥቶ ወደ ሰማያዊው ክብር አርጓልን?" ጌታ ሆይ! አንተ ወደ ሰማይ እንደወጣህ፣ የእኛንም ሕሊና ከምድር ትቢያ አንስተህ ወደ ሰማያዊው ሰላምህ አሳርግልን።
እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ወርኀዊ በአል አደረሳችሁ። ቅድስት አርሴማ የጎርጎርዮስ ዘአርማንያ እህት ናት። ንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ ቆንጆ ሴት ፈልጋችሁ ስዕሏን ስላችሁ አምጡልኝ ብሎ ሰራዊቱን በየአገሩ ሰደደ። ቅድስት አርሴማን በሮም አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ከሰባ አንድ ደናግል ጋር አገኟት ሥዕሏን ስለው ለዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት መልካም ብላቴና አግኝታችሁልኟል ሂዳችሁ አምጡልኝ አላቸው። እሷም በመንፈስ ቅዱስ አውቃ አርማንያ ወረደች ይህን ሰምቶ ለንጉሡ ለድርጣድስ አስፈልገህ ላክልኝ ብሎ ላከበት ንጉሡ ድርጣድስም አስፈልጎ አገኛት። የቅድስት አርሴማን ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ አጋታን አባብላ እሽ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም አይሆንም ያልሁ እንደሆነ ጸብ አጸናለሁ ብላ እሽ አለችው እሷን ግን እንዲህ አለቻ ይህ ርኩስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተይ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው። ንጉሡም ወደ እልፍኝ ሊያስገባት ተነስቶ አርሴማን ያዛት በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ቀላቀለችው ንጉሥ ነውና ቢያፍር በሰይፍ አስመታት ከዚህም አያይዞም ሰባ አንዱንም በሰይፍ አስመትቷቸዋል። የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ አማላጅነት ከእርሷ ጋር ሰማዕትነትን ከተቀበሉ ቅዱሳት በረከት ያድለን።
ቅዳሜ፦በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ቅዱሳት አንስት ይባላል። ጌታ መያዙና መሞቱ እርግጥ ከሆነ በኋላ ትንሣኤውን ለማየት ከጓጉት ውስጥ ሴቶች ተጠቃሽ ናቸው። "…በዚህ ዕለት ሴቶች የአይሁድን ማስፈራሪያ ንቀው የክርስቶስን አካል ሽቱ ለመቀባት ፍርሀታቸውን በክርስቶስ ፍቅር ለውጠው ጨለማ ሳያግዳቸው በጋለ ፍቅር አካሉን መፈለጋቸው ወደ መቃብሩም ሲመላለሱ ማደራቸው ማርያምም ትንሣኤውን ቀድማ ስለማየቷ ሴቶችም የመላእክትን ራእይ ስለ ማየታቸው ቤተክርስቲያን የምታስተምርበት ዕለት ነው። ማቴ 28 ፥1-15፣ ማር 16፥1-8 ሉቃ 24፥1-12 ዮሐ 20፥1-18 "…በሐዲስ ኪዳን የሴቶች ተሳትፎ እጅግ ሰፊ ነው። ጌታ ከመረጣቸው 120 ቤተሰቦች መካከል 36ቱ ቅዱሳት አንስት ናቸው። ጌታ በዋለበት ውለው በአደረበት አድረው ያገለገሉትም ሴቶችም ናቸው። ባለሽቱዋ ማርያምና የይሁዳ እናትን ጨምሮ ብዙዎቹ ጌታ በንስሐ ጠርቶ ያቀረባቸው ናቸው። ሴቶች ቃሉን ለመማርም ትጉሃን ነበሩ። ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም። ሉቃ 10፥42 የሚል ምስክርነት የተሰጠውም ለሐዲስ ኪዳን ሴቶች ነው። ከልብ ስለሰሙት ሞቱ ላይ ቆመው ትንሣኤውን ናፈቁ። “…መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ።…እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም።…ፈጥናችሁም ሂዱና፦ ከሙታን ተነሣ…ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው።" ማቴ 28፥1-7 ተብለው ትንሣኤውን ያበሠሩን ሴቶች ናቸው። ከቅዱሳት አንስት ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን! ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም።
ለዚህ ነው። የዘር አብነት እንዳለ ማስረጃውም በሰሎሞን መጽሐፍ ቃለ ጠቢብ የሚልና ቃለ ጥበብ የሚል መገኘቱ ነው። በሌሎችም ይህንን የመሰለ ይገኛል። "የትርጓሜ ውበት" ከሚባለው መጽሐፌ በጥልቀት በመጽሐፍ ስለሚወጣ ሰፊውን ጉዳይ ከዚያ ይጠብቁ። 🌴፳. አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ውጭ ሀገር በአኃት አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ የሚኖር ሆኖ በእነዚያ አብያተ ክርስቲያናት የሚፈጸሙ ሥርዓቶች (ቁርባን ፣ ጥምቀት፣ ወዘተ) ላይ መሳተፍ ይችላል? መልስ፦ አዎ ይችላል። አኃት አብያተ ክርስቲያን ምንም እንኳ በአንዳንድ የቀኖና አሰጣጥና የሥርዓት አፈጻጸም የተለያየን ብንሆንም በዶግማ ወይም በመሠረተ እምነት አንድ ነንና። ከጥያቄ 21 እስከ ጥያቄ 60 ያሉትን ደግሞ ለነገ እመልሳለሁ። ከ60-100 ያሉትን እሑድ እመልሳለሁ። © በትረ ማርያም አበባው
መልስ፦ በምሥጢረ ሥላሴ ሦስቱ አካላት ተገነዛዝበው ይኖራሉ እንጂ ያለተገናዝቦ በራሳቸው ብቻ አይኖርም። መንፈስ ቅዱስም በአብ ልብነት ሳያስብ በወልድ ቃልነት ሳይናገር በሕይወትነቱ ብቻ መኖር አይችልም። አብም በወልድ ቃልነት ሳይናገር በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት ሕያው ሳይሆን በልብነቱ ብቻ መኖር አይችልም። ወልድም በአብ ልብነት ሳያስብ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ሕያው ሳይሆን በቃልነቱ ብቻ መኖር አይችልም። መገነዛዘባቸው ባሕርያዊ ስለሆነ በዘመን ብዛት የሚለወጥ ወይም ሊጠፋ የሚችል አይደለም። 🌴፲፭. በቅረቡ በአንድ ቦታ ቅዳሴ እያስቀደስኩ ካህናት ሥጋ ወደሙን ሲከለክሉ አየሁ ስጠይቃቸው የማናውቀውና ወጣት ከሆነ ወይም ከሆነች አናቆርብም አሉኝ። ልጂቱን ለምን ከለከላችኋት ስላቸው እናውቃታለን እሷ ሥጋ ወደሙን መቀበል አትችልም አሉኝ ለምን ስላቸው ኃጢአተኛ ናት እናውቃታለን አሉ። ንሥሓ ገብታ እንደሆነስ ስላቸው አይቻልም እያወቅን አንስጥም አሉኝ። ሥጋውን ደሙን አትከልክሉ እሚል መጽሐፋ አምጣ አሉኝ። መልሱ እንዴት ነው? መልስ፦ ማንኛውም ሰው ኃጢአት ሊሠራ ይችላል። ቢሆንም ግን ንስሓ ገብቶ ሥጋውን ደሙን ይቀበላል። ስለዚህ ንስሓ የገባን ሰው ከቁርባን መከልከል አይገባም። ምናልባት የከለከሉት ሰው ያለንስሓ እንዲሁ እቀበላለሁ ብሎ አስቦ ከሆነ መከልከላቸው መልካም ነው። ሳይገባው ቢቀበል ይጎዳበታልና (1ኛ ቆሮ.11፥29)። ንስሓ የገባውን ሰው አልቀበልም አላቆርብም ብሎ የከለከለ ካህን ካለ ግን ይሻር ተብሏል። "ኃጥኡን አልቀበልም የሚል ኤጲስ ቆጶስ ቄስ ቢኖር ይሻር" ተብሏል (ፍት.ነገ.5)። 🌴፲፮. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋው አላዋቂ ነው ማለት እንችላለን ወይ? መልስ፦ ቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋው አላዋቂ ነው የሚል ተጽፎ እስካሁን አላገኘሁም። በተፈጥሮም ቢሆን እግዚአብሔር ለሰው ልጅ አዋቂነትን ሰጥቶ ፈጥሮታል እንጂ አለማወቅን ሰጠው አልተባለም። ስለዚህ እንኳንስ ክርስቶስ ማንኛውም ሰው በሥጋው አዋቂ ነው። የሰው ልጆች ዕውቀት ግን ከሰው ሰው ይለያያል። ዕውቀታቸው የጸጋ ስለሆነ ማለት ነው። ክርስቶስ ግን ራሱ የባሕርይ አምላክ ስለሆነ በዕውቀቱ መከፈል የለበትም (የማያውቀው ዕውቀት) የለም። 🌴፲፯. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ በሥጋው መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ ይባልለታል ወይ? አያይዘው ክርስቶስ ለራሱ ቆርቦ እንዳቆረባቸው ይነገራል። የመቁረቡ ጥቅሙ ምንድን ነው? መልስ፦ አዎ ክርስቶስ ሥጋዉን ደሙን ቀምሶ እንዳቀመሳቸው በትርጓሜ ተገልጿል (ማቴ.26፥26 ትርጓሜ)። እርሱ ራሱ መቅመሱ ለአርአያነት ነው እንጂ እርሱ ራሱ የሚጠቀምበት ሆኖ አይደለም። በዮርዳኖስ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ ተብሎም ተጽፏል (ሃይ.አበ.79፥61)። በጥምቀት መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ ማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ አምላክነቱን መግለጡን ያመለክታል። መንፈስ ቅዱስን የባሕርይ ሕይወቱ ያደረገው ሥጋ ቃልን በተዋሐደ ጊዜ በማሕፀን ነው። እኛ በስሙ አምነን ስንጠመቅ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን እንደምንቀበል ለማሳወቅ በዮርዳኖስ ለአርአያነት መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ። መቀበሉ ግን እርሱ እጠቀም ብሎ ወይም የተጠቀመበት ሆኖ አይደለም። በጥምቀቱ እኛን አከበረበት እንጂ እርሱ አልከበረበትም። መንፈስ ቅዱስን በዮርዳኖስ በአምሳለ ርግብ በመቀበሉም እኛን አከበረበት እንጂ እርሱ አልከበረበትም። "ተጠምቀ በዮርዳኖስ ወኢተጠምቀ ከመ ይኩን ንጹሐ፤ ለራሱ እጠቀም ብሎ አልተጠመቀም" እንዲል (ሃይ.አበ.117፥5)። 🌴፲፰. በቅድስት ሥላሴ አስተምህሮ መሠረት ኩነት አካላዊ ነው ወይስ ባሕርያዊ? ከዚሁ ጋር ተያይዞ አብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ልባቸው ከተባለ፣ ወልድ የአብ የመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ከተባለ፣ መንፈስ ቅዱስ የአብ የወልድ ሕይወታቸው ከተባለ ፍጹም አካል የላቸውም አንዱ ለአንዱ የአካሉን ጉድለት የሚሞላለት ነው አያሰኝም? መልስ፦ ኩነት ከአካል ያልተለየ ስለሆነ አካላዊ ይባላል። ራሱ አካል ግን አይደለም። ኩነት የሚባለው መሆን ሲሆን የአካል መሠረት በመገናዘብ ባሕርይ የሚባል ነው። አብ ራሱ ልብ ሆኖ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ልባቸው ነው። ወልድ ራሱ ቃል ሆኖ የአብ የመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው። መንፈስ ቅዱስ ራሱ ሕይወት ሆኖ የአብ የወልድ ሕይወታቸው ነው (ሃይ.አበ.40፥8)። ልብነት፣ ቃልነት፣ እስትንፋስነት ግን ኩነታት ስለሆኑ አካላዊ ናቸው እንጂ አካላት አይደሉም። ስለዚህ አካላት በኩነታት ስለተገነዛዘቡ ፍጹምነታቸውን አጠያያቂ አያደርገውም። ሕጸጹ ቢጎላም ለምሳሌ አንድ ሰው በጽጌረዳ አበባ መካከል ሲያልፍ የጽጌረዳ አበባው መዓዛ ይሸተዋል። ሰውየው መዓዛውን ስላሸተተ ለሰውየው የጨመረለት ወይም ጎዶሎውን የሞላለት አካላዊ ነገር የለም። ጽጌረዳውም መዓዛውን ሰው ስላሸተተው ከአካሉ አይጎድልም። ሁለቱም በየአካላቸው ፍጹማን ሆነው ይኖራሉ እንጂ። ስለዚህ በከዊን መገነዛዘባቸው ፍጹምነታቸውን ጥያቄ ውስጥ አያስገባውም። 🌴፲፱. አንድምታ ትርጓሜ መጻሕፍት ላይ ምንም እንኳ የእግዚአብሔር ቃላት በብዙ ምስጢራት ሊተረጎሙ እንደሚችሉ የታወቀ ቢሆንም ትርጓሜያቸው አንድ ብቻ ብያኔ የሆኑ በተለይ ታሪካዊ ሁነቶች ላይ እርስ በእርሳቸው የሚቃረኑ የሚመስሉ አንድምታዎች አሉ። ለምሳሌ የማቴዎስ ወንጌል ትርጓሜ ላይ የዮሐንስ ምግቡ አንበጣ የሚለውን "አንቦጣ የሚባል ቅጠል" አንድም "በቁሙ አንበጣ" ይላል። ሰብአ-ሰገል የገበሩት እጅ መንሻ እንዴት ከእነርሱ እንደደረሰ አንድ ብያኔ ከመስጠት ይልቅ list of hypothesis ማስቀመጥ አለ። መዝሙረ ዳዊት ላይ "ዳዊት ይህን የተናገረበት ጊዜ አልታወቀም አንድም ታውቋል" የሚሉ አገላለጾች ብዙ መጻሕፍት ላይ አሉ። ሊቃውንቱ በእግዚአብሔር ተመርተው ከተረጎሟቸው እንዴት መላምታዊ የሚመስሉ አተረጓጎሞች ተጻፉ? መልስ፦ የትርጓሜ ስልቱን በመጽሐፍ መልኩ በጥልቀት እያዘጋጀሁት ስለሆነ ጥልቅ ጉዳዩን በዚያ የምገልጸው ይሆናል። ከትርጓሜ ስልቶች አንዱ ታሪክ ነው። ታሪክ ሲተረክ ደግሞ ሁሉም በየደረሰበት መረጃ ይናገራል። መተርጉማኑም በጉዳዩ ዙሪያ ልዩ ልዩ ሊቃውንት የተናገሯቸውን መሠረት አድርገው የሁሉንም ሐሳብ አንድ በአንድ እየገለጹ እገሌ እንዲህ ይላል፣ እገሌ ደግሞ እንዲህ ይላል እያሉ የተቀመጡትን ሐሳቦች ያስቀምጣሉ። ሙሉ ማስረጃ የተገኘለትን ጉዳይ "ይህስ አይደለም እንዲህ ነው" ብለው ደምድመው ይናገራሉ። ማስረጃ የሌለውን ጉዳይ ግን የሁለቱንም ሐሳብ አቅርበው ለጥናት ክፍት አድርገው ይተውታል። የዶግማ ሐተታዎች ግን አይለወጡም። ታሪክን፣ ቀኖናን መሠረት ያደረጉ ሐተታዎች ግን እንደዘመኑ ሊታተቱ ይችላሉ። መተርጉማን ከእነርሱ በፊት የተጻፉ ጽሑፎችን፣ በዘመናቸው የሚባሉ አባባሎችን ተጠቅመዋል። እግዚአብሔር ገልጾላቸው የጻፉ መተርጉማን ይኖራሉ፣ በአንጻሩ የቀደሙ አባቶች የጻፏቸውን ጽሑፎች በማደራጀት የጻፉም ይኖራሉ። ስለዚህ ትርጓሜውን ራሱ መመርመር ይገባል። ሌላው አብነት የሚባል አለ። ይህ አብነት የዘርና የትርጓሜ ተብሎ በሁለት ይከፈላል። በዘር አብነት የዮሐንስን ምግብ አንበጣ ያለውን እንቦጣ ብለው የጻፉ ስለነበሩ የእነርሱን ሐሳብ ለማስቀመጥ የበረሃ ማር ብለውታል። ዮሐንስ የበረሃ ማርንም ይበላ ስለነበር ሐተታው መልካም ነው። መደበኛው ግን ዮሐንስ መጥምቅ አንበጣ ይበላ ነበር የሚለው ነው። ወንጌል የምግብ ሕግ አይደለችምና አንድም ለንጹሓን ሁሉ ንጹሕ ነውና ተብሎ በሐተታ የታተተ
🌴፱. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው ለምልአተ ኃጢአት ነው ወይስ ለጥንተ አብሶ? መልስ፦ ክርስቶስ ተሰቅሎ ያዳነን በሁለቱም ምክንያት ለሁለቱም ምክንያት ነው። ለጥንተ አብሶም ለምልአተ ኃጢአትም ነው። በጥንተ አብሶ ብቻ ቢሆን ኖሮ አዳምንና ሔዋንን ብቻ ለማዳን መጣ ባሉት ነበርና። ወልደ እግዚአብሔር ሰው የሆነው ግን ሰው ሁሉ በኃጢአት ተዘፍቆ ይኖር (ምልአተ ኃጢአት) ስለነበር ሰውን ሁሉ ለማዳንም ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዕብራውያንን በተረጎመበት ድርሳኑ "ሶበሰ መጽአ በጥንተ አብሶ እምኢኮነ ሞቱ ለቤዛ ብዙኃን" እንዲል (ድርሳን 17)። 🌴፲. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብላለች ወይስ አልተቀበለችም? ከተቀበለች የልጇን ሥጋ መብላት አይሆንም ወይ? ካልተቀበለች በራስዋ ድናለች ወይ? መልስ፦ በትውፊት በውዳሴ ማርያም ትርጓሜያችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደቆረበች ተገልጿል። ልጇ ሰው ብቻ አይደለም። አምላክም ሰውም የሆነ አንድ ነው እንጂ። የልጇ ሥጋ እንደሌላው ሰው ሥጋ አይደለም። በተዋሕዶተ መለኮት የከበረ የሚያድን የሚፈውስና ዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚያጎናጽፍ ነው እንጂ። ስለዚህ የልጇን ሥጋ ብትበላውም በጸጋ ላይ ጸጋን ይጨምርላታል እንጂ ምንም ችግር የለውም። ምልእተ ጸጋ አይደለችም ወይ የምን ጸጋ ነው ይጨመርላታል የሚባለው የሚል ካለ ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከፍጡራን ሁሉ በላይ ጸጋ ያላት መሆኗን ለመግለጽ ምልእተ ጸጋ አልናት እንጂ ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት ጸጋን የማትቀበል ናት ማለታችን አይደለም። በማይቋረጥ ጸጋ (ተወስኮ ዘነሣእያን) ከሁሉ በላይ ሆና ትኖራለች እንጂ። ተወስኮ ዘነሣእያን ደግሞ አይቆምም፣ አይገታም፣ አያቋርጥምና (ድር.ዮሐ.አፈ.1 ትርጓሜ)። እንዲሁም "ወኢይጸራዕ ውሒዙ እምተወስኮ፤ ጸጋው ከመሰጠት አያቋርጥም። እስመ ተወስኮሰ ዘነሣእያን ይእቲ" እንዲል (አረ.መን.33)። ድንግል ማርያም ምልእተ ጸጋ መባሏ አንጻራዊ ነው እንጂ ከዚህ በኋላ ጸጋ የማያስፈልጋት ከባሕርይ አምላክነት የደረሰች ናት ለማለት አይደለም። 🌴፲፩. እግዚአብሔር ወልድ በእመቤታችን ማሕፀን አደረ ወይስ ተዋሐደ? ተዋሐደ ካልን እመቤታችን አምላክ አትባልም ወይ? መልስ፦ ከዚህ ላይ ምሥጢረ ሥጋዌን በጥቂቱም ቢሆን መረዳት ይገባናል። እግዚአብሔር ወልድ በድንግል ማርያም ማሕፀን አደረ ስንል ምን ማለታችን ነው? የሚለውን ማወቅ ያስፈልጋል። ወልደ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም የነሣውን ሥጋ ተዋሐደ እንጂ ራሷን ድንግል ማርያምን የተዋሐደ አይደለም። ስለዚህ ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ አትባልም። ቅድስተ ቅዱሳን በመሆኗ ግን የጸጋ አምላክ ትባላለች። 🌴፲፪. ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ይባላል ወይስ አይባልም? መልስ፦ ይባላል። በዚህ ዙሪያ ቅዱሳን ሊቃውንት ቃል በቃል የተናገሩትን በቅደም ተከተል ከሃይማኖተ አበው እንመልከት። ቅዱስ ባስልዮስ "ይብል ዘንተ በእንተ ልደቱ በሥጋ ከመ ውእቱ ፍጡር ወግቡር፤ ቃል የተዋሐደው ሥጋ ፍጡር እንደመሆኑ መጠን በሥጋ ስለተወለደው ልደት ይህን ተናገረ.....ይደሉ ይትበሀል ዝንቱ ትርጓሜ በእንተ ትስብእቱ ለመድኅን እስመ ፍጡር ውእቱ፤ ትስብእት የተፈጠረ ነውና ይህ መድኅን ሰው ስለመሆኑ ይነገራል" ብሏል (ሃይ.አበ.32፥13-18)። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ "ወዓዲመ ይትበሀል ፍጡረ በእንተ ዘኮነ ሥጋ ወኀደረ ላዕሌነ፤ ወዲህም ሰው ስለሆነ የእኛን ባሕርይ ስለተዋሐደ ፍጡር ይባላል" ብሏል (ሃይ.አበ.35፥6)። ቅዱስ አቡሊዲስ "መለኮትሰ ኢፍጡር ውእቱ፤ መለኮት ያልተፈጠረ ነው። ወሥጋሰ ፍጡር ውእቱ፤ ሥጋ ግን የተፈጠረ ነው...ወኢንሬስዮ ለመለኮት ፍጡረ ወኢግቡረ፤ መለኮትን የተፈጠረ ነው አንልም። ወዓዲ ኢንሬስዮ ለሥጋ ኢፍጡረ፤ ዳግመኛም ሥጋን ያልተፈጠረ ነው አንልም" ይላል (ሃይ.አበ.39፥25-27፤ ሃይ.አበ.40፥23)። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "እስመ ትስብእቱ ፍጡር ውእቱ፤ የተዋሐደው ሥጋ ፍጡር ነውና" ብሏል (ሃይ.አበ.63፥28)። ቅዱስ ኤጲፋንዮስ "እስመ ሶበ ተሰምየ ፍጡረ በእንተ ትስብእቱ ዓዲ ተሰምየ አንቀጸ፤ ሰው ስለሆነ ፍጡር ቢባል ወዲህም በኵር ተባለ" ይላል (ሃይ.አበ.56፥22)። ቅዱስ ቄርሎስ "ወኢይትበሀል ከመ ሥጋ ተመይጠ ኀበ ህላዌ መለኮት፤ ሥጋ መለኮት ወደ መሆን ተለወጠ ሊሉ አይገባም። ወኢቃል ተመይጠ ኀበ ህላዌ ትስብእት፤ ቃልም ሥጋን ወደ መሆን ተለወጠ ሊሉ አይገባም። እስመ ሥጋ ፍጡር ወግቡር ውእቱ፤ ሥጋ ፍጡር ነውና" ብሏል (ሃይ.አበ.78፥30)። ቅዱስ ቴዎዶስዮስ "ወሶበ ትሰምዕ ከመ ውእቱ ፍጡር ኢተኀሊ ግሙራ ከመ ዝንቱ ይትበሀል በእንተ ቃል ከመ እግዚአብሔር ፈጠሮ በከመ ይቤ አርዮስ ርጉም፤ ፍጡር እንደተባለ ብትሰማ የተረገመ አርዮስ እንደተናገረው ስለቃል የተነገረ አይምሰልህ። አላ ይትበሀል በእንተ ሥጋ ከመ ውእቱ ፍጡር፤ ፍጡር እንደሆነ ስለሥጋ ይነገራል እንጂ። ወውእቱ ዘሐነፀ ሎቱ መቅደሰ እምድንግል ንጽሕት ማርያም፤ ለራሱ ከእመቤታችን ነፍስን ሥጋን ፈጥሮ የተዋሐደ እርሱ ነው" ይላል (ሃይ.አበ.83፥14)። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወሰብእ እንዳልነው ሁሉ ፍጡር ወፈጣሪ እንለዋለን። "ውእቱሰ ፍጡር ወፈጣሪ ውእቱ" እንዲል (ሃይ.አበ.124፥18)። የሃይማኖተ አበው የትርጓሜ መጻሕፍት ፍጡር የሚለውን ቃል በቃል ሲያስቀምጡት ወደ አማርኛ የተረጎሙ ሊቃውንት ደግሞ አንዳንድ ቦታ ሰው እያሉ ተርጉመውታል። ሁለቱም ግን ሐሳቡ አንድ ነው። የሁለቱንም ሐሳብ በደንብ የሚገልጸው "እስመ ሰብእሰ ፍጡር ውእቱ"የሚለው ቃል ነው (ሃይ.አበ.124፥26)። ከላይ ለማሳያ ያህል ጥቂቶቹን ጠቀስን እንጂ ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር እንደሚባል ከአራቱ ጉባኤያት በተጨማሪ በርካታ መጻሕፍት ላይ ይገኛል። ፍሬ ነገሩ የክርስቶስ ሥጋ ቅድመ ዓለም የነበረ ሳይሆን የተፈጠረ መሆኑን የሚገልጽ ነው። ፍጡር ማለት የተፈጠረ ማለት ነውና። አንዳንዶች ባለማወቅ ተዋሕዶው ፍጡርነቱን አጥፍቶታል ብለው ሰውነቱን ዘንግተው አምላክ ብቻ (ዕሩቅ ቃል) ለማድረግ ይጥራሉ። ነገር ግን ተዋሕዶው በተዓቅቦ ስለሆነ መጠፋፋት የለበትም። "ኢያፍለሰ ፈጣሪ መለኮቶ ለከዊነ ፍጡር፤ ፈጣሪ ባሕርዩን ፍጡር ወደ መሆን አልለወጠውም። ወኢደምሰሰ ትስብእቶ ፍጡረ ለከዊነ ፈጣሪ፤ የተፈጠረ ሥጋንም ፈጣሪ ወደ መሆን አልለወጠውም" እንዲል (ሃይ.አበ.36፥24)። 🌴፲፫. መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት ሲወርድ ለእመቤታችን ወርዷል ወይስ አልወረደም? ወርዷል ካላችሁ እመቤታችን መጀመሪያ መንፈስ ቅዱስ አላደረባትም ወይ? መልስ፦ መንፈስ ቅዱስ ለእመቤታችንም ወርዷል ከሐዋርያት ጋር ነበረችና (የሐዋ. ሥራ 1፥14)። ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቶ አያልቅም። ስለዚህ ምንም እንኳ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቀድሞም ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ያደረባት የነበረች ቢሆንም በነበራት ሀብት ላይ እግዚአብሔር ባወቀ ተጨማሪ ሀብት ተሰጥቷታል ማለት ነው። 🌴፲፬. መንፈስ ቅዱስ ሕይወት ነው ከተባለ አንዱ ያለ አንዱ መኖር አይችልም ወይ?
የጥያቄዎች መልስ (ከጥያቄ 1 እስከ 20) 🌴፩. በሥርዓተ ቤተክርስቲያን የሚጋቡ ሙሽሮች በሚቆርቡበት ዋዜማ ወንዱ በዝንየት ቢመታ፣ ሴቷ ደግሞ ያልተጠበቀ ወር አበባዋ ቢከሠት በነጋታው የሚደረገው የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት ምን ይደረጋል? መልስ፦ ጋብቻ የሚፈጸመው በቍርባን ነው። ሴት ደግሞ በወር አበባዋ ጊዜ መቍረብ አትችልም (ፍት.ነገ.3)። በዘመነ ወንጌል እንጂ ደም አበባ ነው ብሎ ደፍሮ ከቤተክርስቲያን ያገባ ካህን ቢኖር ከሹመቱ ይሻር ተብሏልና (ፍት.ነገ.24፤ አቡሊዲስ 18)። ወንዱም ዘሌዋ.15፥16 ላይ እንደተገለጸው ዝንየት ቢያገኘው በብሉይ ኪዳን ከርኵሰት ይቆጠርበት ነበር። በሐዲስ ግን እንደ የወር አበባ ርኩስ ባይባልም ዕለቱን ከመቍረብ ይከለከላል። [ብዙ ድግስ ተደግሶ ድግሱ ይበላሽብን የለምን የሚል ሰው ሊኖር ይችላል፤ ነገር ግን ቍርባኑን ለሌላ ጊዜ አድርጎ የድግሱን ነገር ደግሞ ከንስሓ አባት ጋር መመካከር ይቻላል የሚል አስተያየት አለኝ]። 🌴፪. ሕፃናት ልጆችን ያስቆረቡ ባልና ሚስት ከስንት ቀን በኋላ ነው መተዋወቅ የሚችሉት ወይስ እነርሱ እስካልቆረቡ ድረስ ችግር የለውም? መልስ፦ ልጃቸውን ክርስትና የሚያስነሡ እናትና አባት ክርስትና ከመነሣቱ ከሁለት ቀን በፊት እና ክርስትና ከተነሣ በኋላ እስከ ሁለት ቀን ከሩካቤ መከልከል ይገባቸዋል። ይህም ስለክብረ መንፈስ ቅዱስ ነው። "ወካልኡ እምነ ተራክቦተ ወላድያኒሁ ለዘነሥእዎ በጥምቀት ክርስትና፤ ጸጋ ክብር በሚያሰጥ በጥምቀት ክርስትና ያነሡትን ሰው አባት እናት ከመገናኘት መጽሐፍ መምህራን ከለከሉ። እመኒ በመዓልት ወእመኒ በሌሊት በእንተ ክብረ መንፈስ ቅዱስ" እንዲል (ፍት.ነገ.24)። 🌴፫. በምሥጢረ ሥላሴ ወላዲ ባሕርይ ተወላዲ ባሕርይ ሠራፂ ባሕርይ ማለት ይቻላል? መልስ፦ በእርግጥ ባሕርይ የሚለው ቃል ባለብዙ ትርጉም ስለሆነ ጠያቂው በየትኛው ትርጉም እንደጠየቀ መረዳት አልቻልኩም። ብዙ ጊዜ ግን ባሕርይ የሚባለው የሦስቱ አካላት በአንድነት መገናዘብ ስለሆነ ጥያቄው በዚህ ከሆነ ልመልስ። የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ አንድ ነው። በባሕርይ አንድ ስለሆኑ በዚህ አንድ ባሕርይ ግብር ሦስቱም ይጠሩበታል። ለምሳሌ አብ ፈጣሪ እንደተባለ ወልድም ፈጣሪ ይባላል መንፈስ ቅዱስም ፈጣሪ ይባላል። ምክንያቱም ፈጣሪነት የባሕርይ ግብር ነውና። ወላዲ ባሕርይ ካልን ሦስቱንም አካላት ወላድያን፣ ተወላዲ ባሕርይ ካልን ሦስቱንም ተወላድያን፣ ሠራፂ ባሕርይ ካልን ሦስቱንም አካላት ሠራፅያን ስለሚያሰኝ አያስኬድም። ወላዲነት ሦስቱ አንድ በሚሆኑበት ለመለኮት የሚነገር ሳይሆን በተለየ አካሉ ለአብ የሚነገር ነው። ተወላዲነትም ለወልድ የሚነገር ነው፣ ሠራፂነትም ለመንፈስ ቅዱስ የሚነገር ነው። በአፍኣዊ ግብረ ባሕርይ ለምሳሌ ለእኛ ለምእመናን አባት ወይም ወላዲ በመባል ግን ሦስቱም ይጠሩበታል። "ወላዲ ውእቱ መንፈስከ፤ ሕይወትህ መንፈስ ቅዱስ ወላዲ ነው" እንዲል (አረ.መን.35)። ክርስቶስንም አቡነ ዘበሰማያት፣ አበ ዓለም ሐዲስ እንደምንለው ማለት ነው። 🌴፬. ወንጌላዊ አካላት በሚጠሩበት በአካል ስም ወልድ ሰው ሆነ አላለም ነገር ግን በኩነት በሚለይበት በባሕርይ አንድ በሚሆንበት ቃል ሥጋ ሆነ ነው ያለው ይላል። በባሕርይ አንድ ከሆኑ ሦስቱም ሰው ሆኑ አያሰኝም? መልስ፦ አያሰኝም። ምክንያቱም ባሕርይ ወይም መለኮት የሚባለው የሦስቱ አካላት መገናዘብ ነው። "ዘውእቱ አሐዱ ብርሃን ዘይሠርቅ እምኔሁ ሥላሴ፤ ሦስትነት ከእርሱ የሚገኝ አንድ ብርሃን ነው። አንድም ዘይሠርቅ እምኔሁ ለሥላሴ፤ ከሦስትነት የሚገኝ አንድ ብርሃን ነው" ይላል (ሃይ.አበ.11፥9)። ከሦስትነት የሚገኝ አንድ ብርሃን የሚለው አገላለጽ የሦስቱን አካላት ኩነታት መገናዘብ ያመለክታል። ባሕርይ አንድ ቢባልም ሦስት ከዊን እንዳለው ለመግለጽ ደግሞ ሦስትነት ከእርሱ የሚገኝ አንድ ብርሃን ተብሏል። ስለዚህ ባሕርይ በቃልነት ከዊኑ ሰው ሆነ እንጂ በልብነት ከዊኑ ወይም በእስትንፋስነት ከዊኑ ሰው አልሆነምና ሦስቱም ሰው ሆኑ አያሰኝም። "በእንተ ተዋሕዶተ መለኮት ዘንትናገር በዝየ ዘህልው በወልድ ወአኮ በእንተ አብ ወመንፈስ ቅዱስ፤ መለኮት ከትስብእት ጋር ተዋሐደ ብለን የምንናገርለት በወልድ ያለ ነው ስለአብ ስለመንፈስ ቅዱስ አይደለም" እንዲል (ሃይ.አበ.11፥3)። 🌴፭. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መንፈስ ቅዱስ አነጻት ወይስ ጠበቃት? መልስ፦ መጻሕፍት አንጽሓ፣ ዐቀባ እየተባለ ተገልጿል የሁለቱም ምሥጢር ግን አንድ ነው። ቅዱስ ያሬድ "አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ" ብሏል። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስም "መንፈስ ቅዱስ ቀደሰ ወአንጽሐ ሥጋሃ ለማርያም፤ የድንግልን ሥጋ አጸና አነጻ" ብሏል (ሃይ.አበ.36፥19)። ይህም ከሰው ሁሉ ልጆች ይልቅ ደግ መሆኗን በመለኮታዊ ዕውቀቱ አስቀድሞ አውቆ ከማሕፀን ጀምሮ ንጹሕ አድርጎ እንደፈጠራት ያመለክታል። አነጻት ማለቱ ከጽንስ ጀምሮ ነው እንጂ ቀድሞ ንጽሕት ሳትሆን ቀርታ በኋላ አነጻት ማለት አይደለም። ጠበቃት [ዐቀባ] የሚለውም ከማሕፀን ጀምሮ በንጽሕና እንደጠበቃት ያመለክታል። "መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እምከርሠ እማ" እንዲል (ውዳ.ማር.ዘረቡ.ትር.) 🌴፮. እመቤታችን የክርስቶስ የጸጋ እናቱ ወይስ የባሕርይ እናቱ ናት? መልስ፦ ባሕርይ ባለብዙ ትርጉም ነው። ባሕርይ መገኛ ተብሎ የሚተረጎምበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ የሰው ልጅ ከአራቱ ባሕርያት የተፈጠረ ነው ሲል ባሕርያት ያላቸው እሳትን፣ መሬትን፣ ነፋስን፣ ውሃን ነው። በዚህ ጊዜ ባሕርይ መገኛ ማለት ነው። በዚህ አግባብ ካየነው ክርስቶስ በሥጋ ከድንግል ማርያም የተወለደ (የተገኘ) ስለሆነ ድንግል ማርያም የባሕርይ እናቱ ትባላለች። በመለኮቱ ከአብ የተወለደ (የተገኘ) በመሆኑ በመለኮቱ የአብ የባሕርይ ልጁ ይባላል። ወልድ ከአብ ተገኘ እያሉ መጻሕፍት ሲናገሩ መገኘቱ (ተረክቦው) አባት ቀድሞ ልጅ ሳይከተል ወይም መቀዳደም ሳይኖር ነው። ከድንግል ማርያም ተወለደ ስንል ግን በሥጋ ስለሆነ በሥጋ ደግሞ ድንግል ማርያም ትቀድማለች። ዮሐንስ መጥምቅም "ይመጽእ እምድኅሬየ ብእሲ ዘሀሎ እምቅድሜየ" ብሏል (ዮሐ.1፥15)። እምድኅሬየ ማለቱ በሥጋ ይቀድመዋልና ነው። 🌴፯. ማቴ.1፥18 በመንፈስ ቅዱስ ግብር ፀንሳ ተገኘች ሲል የመንፈስ ቅዱስ ግብር ምንድን ነው? መልስ፦ ምንም እንኳ የተፈጥሮ ሕግን የሠራም ራሱ እግዚአብሔር ቢሆንም ከተለመደው የተፈጥሮ ሕግ ከፍ ያሉ ጉዳዮችን ደግሞ በተለየ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ (ግብረ መንፈስ ቅዱስ) እያለ ይጠራቸዋል። የመንፈስ ቅዱስ ሥራ እያለ ለይቶ መንፈስ ቅዱስን ይጥራው እንጂ በአምላካዊ ሥራ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ስለሆኑ የአብ ሥራ (ግብረ አብ)፣ የወልድ ሥራ (ግብረ ወልድ) ቢልም አንድ ነው። ስለዚህ ከዚህ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ያለው ከተፈጥሮ ሕግ በላይ ስለሆነ ያለወንድ ዘር መፅነስን፣ ያለሩካቤ መፅነስን ነው። 🌴፰. በአብ መሠረትነት ስንል ለምስጢረ ሥላሴ ምን ማለት ነው? መልስ፦ አብ መገኛ መሆኑን ለመግለጽ መሠረት ተብሏል። የሀገራችን ሊቃውንት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ፣ አለቃ ኅሩይና ሌሎችም መገኛነቱን ለመግለጽ በአብ መሠረትነት እያሉ ይገልጻሉ። ይህ መሠረትነት ወይም መገኛነት ግን መበላለጥን አያሳይም። በምሳሌ ዘየሐጽጽ ሙቀትና ብርሃን ከፀሐይ ክበብ ይገኛሉ። ከፀሐይ ክበብ ይገኛሉ ብንልም ሙቀትና ብርሃን ከክበብ የተለዩበትና ክበብ ኖሮ እነርሱ ያልነበሩበት ጊዜ ግን የለም።
በደንብ ይጠየቅ። ከ250 በላይ ጥያቄዎች ተጠይቀዋል። ማናቸውም ሃይማኖታዊ ጥያቄ ያለው ይጠይቅ እስከ ጰራቅሊጦስ የፈለጋችሁን መጠየቅ ትችላላችሁ። ስትጠይቁ ጥያቄውን ግልጽ አድርጉት የጠየቃችሁበትን መጽሐፍ ምዕራፍና ቁጥር ወይም ገጽ አስቀምጡ © በትረ ማርያም አበባው
🌴፴፬. ከጥምቀት በፊት የሞቱ ሕፃናት ለምሳሌ 40 ቀን ወይም 80 ቀን ያልሞላቸው ሕፃናት መንግሥተ ሰማያት ይገባሉ? ሌላው የዘር ኃጢአት በክርስቶስ ተሽሯል ተብሏል። ነገር ግን ያልተጠመቁ ሕፃናት የዘር ኃጢአት አለባቸው የሚል መጽሐፍ አንብቤ ነበር እና ግራ ተጋባሁ። የዘር ኃጢአት ምንድን ነው? ሌላው ሕፃናቱን ከ40 እና 80 ቀን በፊት ማጥመቅ ይቻላል ወይ? መልስ፦ 🌴፴፭. በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ምን ያህል ነው? ለምሳሌ የሆነ ነገር ከተፈጠረ መጥፎም ይሁን በጎ እግዚአብሔር እንዳደረገው በምን እናውቃለን? እግዚአብሔር የሠራው እስከ ምጽአት የሚሠራ ሲስተም ነው ወይስ እሱ ነው አሁንም የሚሠራው? መልስ፦ 🌴፴፮. ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ያረገው በግዘፍ አካል (በሥጋ) ነው? ከአካል ህልውና አንጻር፣ ከግብር አንጻር፣ ከኩነት አንጻር ድኀረ ዕርገትን አብራሩልኝ? መልስ፦ 🌴፴፯. በዚህ ወቅት ማለትም በበዓለ ኀምሳ ንስሓ መግባት ይቻላል? መልስ፦ 🌴፴፰. "ሰላም ለኪ እመቤቴ ኪዳነ ምህረት ሆይ! ሰላምታ ላንቺ ይገባል፥ አለኝታ ተስፋ አንቺ ነሽና ሰላምታ ላንቺ ይገባል፥ ኃጥአንን አማልደሽ ለምታጸድቂ ላንቺ ሰላምታ ይገባል፥ ከዘጠናው በጎች ተለይቶ የጠፋ በግ አዳምን የምትፈልጊ ለአንቺ ሰላምታ ይገባል" ይላል። እና [ማቴ.18፥11-13] ካለው ጋር አይጋጭብንም? መልስ፦ 🌴፴፱. በዳግም ምጽአት የሰዉ ልጅ የሆነ ሁሉ ለፍርድ ይቆማልን? እንደዚህ ከሆነ ማመን አለማመን ሳይሆን የሚጠየቁትን 6ቱ የወንጌል ቃል የፈጸመ ሁሉስ በቀኝ ይቆማል ወይ? መልስ፦ 🌴፵. በቅዱሳን ገድል፣ ድርሳንና ሌሎችም መጻሕፍት ሙሉ በሙሉ የመቀበል ግዴታ አለብን ወይ? ካለብንስ በውስጥ ቤተክርስቲያንን የማይመጥኑ ጽሑፎች በውስጥ አሉ። ለምሳሌ በገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ (ከምዕራፍ 26-28) አንድ አንድ ገድል ላይ 26 ላይ ከደብረ ሊባኖስ ዕትም ላይ 28 አለና። የብሔር ጥለቻ የሚመስሉ ነገሮች ይታያሉ። ለአገዉ ሕዝቡ ሳይገባው ነው 333 ዓመት የገዛዉ ይላል። ስለዚህ ባይገባስ ለምን ቤተክርስቲያን ታቦት ቀርጻ ቅዱስ ላሊበላ ብላ ሥራዉን ታከብራለች? ይህ እንዴት ይታያል? በዚሁ ጋር ተያይዞ በአቡነ መብዓ ጽዮን ገድልም አገው ህዝብ ድባን የሚባል ጣዖት አምላኪ ነበር ይላል። ይህ ደሞ ትክክል አይደለም። ለምን ቢባል በቋንቋቸዉ ድባን ማለት እግዚአብሔር ነዉ አሁንም ቢሆን እየጠሩት የሚገኙት አጠቃቀም ነው። ስለዚህ ይህን እንዴት ማስታረቅ ይቻላል? መልስ፦ 🌴፵፩. አዋልድ መጻሕፍትን ከትክክለኛ ቦታ መቀዳተቸዉን በምን ማረጋገጥ እንችላለን? ኀላፊነቱስ የማን ነው? መልስ፦ 🌴፵፪. አጋንንት ከረአይት የተገኙ ናቸው ይላል ኩፋሌ አንድምታ። 90 እጁ ሲዘጋባቸው 10 እጅ ሰውን እንዲያሳስቱ እግዚአብሔር ፈቀደላቸው የሚለው ማጥፋት እየቻለ እንድንሳሳት ለምን ፈቀደላቸው? መልስ፦ 🌴፵፫. ጥሬ ስጋ መብላት ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም? መልስ፦ 🌴፵፬. የስቅለት ዕለት ቀኑን ሙሉ ግበረ ሕማማትን የሚያክል መጽሐፍ ሲነበብ ውሎ አንድ የበራ ጧፍ መቋሚያ ላይ አስረው በመርገም መድመደም ወፍኖቶሙሰ ለኃጥአን ትጠፍእ ብሎ ማጠናቀቅ አያስነቅፍም? መልስ፦ 🌴፵፭. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች አገልጋዮች ትላልቅ በሚባሉ ሰዎች የሚጸለዩ ጸሎቶች ቱላዳን፣ ባርቶስ፣ መልክአ ራጉኤል ባለጠልሰም እየተባሉ የሚጠሩ መጻሕፍት እውነተኛ የጸሎት መጻሕፍት ናቸው ማለት እንችላለን? መልስ፦ 🌴፵፮. የእስራኤል ልጆች መሰብሰብ (The Gathering of Israel)። በኢሳ.11፥12 ላይ መሲሑ የተበተኑትን የእስራኤልን ልጆች ከዓለም ዳርቻ እንደሚሰበስብ ተጽፏል። ኢየሱስ ሲመጣ ግን አይሁድ ይበልጥ ተበተኑ እንጂ አልተሰበሰቡም። ይህ ትንቢት እንዴት ተፈጸመ ትላላችሁ? መልስ፦ 🌴፵፯. የመቅደሱ መታደስ (Rebuilding the Temple)። በሕዝ.37፥26-28 መሠረት መሲሑ መቅደሱን ለዘላለም በመካከላቸው እንደሚተክል ይናገራል። ኢየሱስ በመጣ በ70 ዓ.ም. ግን የነበረው መቅደስ ፈረሰ። ይህ ከትንቢቱ ጋር እንዴት ይስማማል? መልስ፦ 🌴፵፰. ዓለም አቀፍ ሰላም (Universal World Peace)። በኢሳ.2፥4 ላይ መሲሑ ሲመጣ ሕዝቦች ሰይፋቸውን ማረሻ ለማድረግ እንደሚቀጠቅጡና ጦርነት እንደማይኖር ይናገራል። ነገር ግን ባለፉት 2,000 ዓመታት ዓለም በጦርነት ተሞልታለች። ይህንን እንዴት ታዩታላችሁ? መልስ፦ 🌴፵፱. የአሕዛብ ሁሉ አንድነት (All Nations Acknowledge One God)። በዘካ.14፥9 እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እንደሚነግሥና ስሙም አንድ እንደሚሆን ይናገራል። ዛሬ ግን ዓለም በብዙ ሃይማኖቶች ተከፋፍላለች። ይህ ትንቢት በኢየሱስ በኩል ተፈጽሟል ለማለት ይቻላል? መልስ፦ 🌴፶. የዘር ሐረግ እና የድንግል መውለድ (The Lineage of David)። መሲሑ የዳዊት ዘር መሆን ያለበት በአባት በኩል እንደሆነ የአይሁድ ሕግ ይናገራል። ኢየሱስ ግን ከድንግል ከተወለደ (ያለ ምድራዊ አባት)፣ እንዴት የዳዊት የሥጋ ዘር ሊባል ይችላል? ዮሴፍ አሳዳጊው እንጂ የወለደው ካልሆነ የዘር ሐረጉ እንዴት ይተላለፋል? ዘኍ. 1፥18። መልስ፦ 🌴፶፩. በወላጆች ንስሓ አባት ልጅ መቀጠል አለበት ወይስ የራሱን አባት መያዝ አለበት? መያዝ ካለበት ከዕድሜም ሆነ ሌላ መስፈርት ካለ መቼ ነው የራሱን አባት መያዝ ያለበት? መልስ፦ 🌴፶፪. አዳም በገነት የነበረው ነጻ ፍቃድና ከጥፋት በኋላ ያለው ነጻ ፍቃድ ይለያያል? ነጻ ሆኖ ከተፈጠረ ለምን ይቀጣል? መልስ፦ 🌴፶፫. ሙዚቃ ሁሉ ኃጢአት ነው ወይ? መጽሐፍ ቅዱስ ዘፈንና ዘፋኝነትን ሲቃወም ምን ዓይነት ዘፈንን ነው የሚለው ጥያቄ አይሆንም? እዚሁ ጋር ተያይዞ ሌላኛው ደግሞ ያው ብዙ ጊዜ እንደሚነሳው በግሪኩ "ከመጠን ያለፈና ሥርዓት የሌለው ጭፈራ/ግብዣ" የሚለው በአማርኛው የተተረጎመው ግን "ዘፋኝነት" ይላል እሱስ እንዴት ይታያል? መልስ፦ 🌴፶፬. ኃጢአትም ጽድቅም ያልሆነ ነገር አለ ወይ? ለምሳሌ አንድ ክርስቲያን ከእርሱ የሚጠበቁ ነገሮችን የሚያደርገብትን ሰዓት በማይጋፋ መልኩ (የጸሎት ጊዜውን ወይም ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ያለበትን ሰዓት) ስፖርት ቢሠራ፣ ልብወለድ ቢያነብ፣ ኳስ ቢጫወት ወይም ፊልም ቢያይ (ከመንፈሳዊው ጋር የማይጋጭ ግን ዓለማዊ የሆነ) ችግር አለው? መልስ፦ 🌴፶፭. በምሴተ ኀሙስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ከሐዋርያት ጋር ነበረች ወይስ አልነበረችም? በዚያ ዕለትስ ሥጋውን ደሙን ተቀብላለች ወይ? መልስ፦ 🌴፶፮. የእመቤታችን ትንሣኤ እንዴት ነበር? ማለት ለምሳሌ አልአዛር መግነዝ ተፈቶለት በር ተከፍቶለት ነው ። የእመቤታችንስ? መልስ፦ 🌴፶፯. እመቤታችን አዳም በገነት ይዞት የነበረውን ሥጋ ንጽሕና ነው በምድር የያዘችው? እኛስ ከትንሣኤ በኋላ ያለ ያለን ሥጋ አዳም በገነት በነበረ ጊዜ የያዘውን ነው የምንይዘው? መልስ፦ 🌴፶፰. "ወደ አባቴ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ" ሲል እንልና ወደ አባቴ አለ - የባሕርይ አባቱ ስለሆነ ወደ አባታችሁ አለ የጸጋ አባታችን ነውና። ካልን በኋላ ወደ አምላኬ - የሚለውን "ሰው ስለሆነ፥ በሥጋ ይፈጥረዋልና" ብለን እናልፈዋለን። አብ (አምላኬ የተባለው አካል) ለክርስቶስ የባሕርይ አምላኩ ነው? ለእኛስ እግዚአብሔር የምን አምላካችን ነው የባሕርይ ወይስ የጸጋ? መልስ፦