tgindex
ልቦና ቲዩብ ገፅ

ልቦና ቲዩብ ገፅ

Статистика

ይህ ትክክለኛ የልቦና ቲዩብ የቴሌግራም ቻናል ነው :: የመወያያ ግሩፕ @libonatubegroup መልዕክት ወይም ቪዲዮች ለመላክ :- @Libona27 የዩቱብ ቻናል:-https://youtube.com/channel/UCBtfy4U5ppRDW3is7xbnvzg የፌስቡክ ገፅ:-https://m.facebook.com/yabsramatiwoss/

Последний пост
19 мая 2025 г.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Видео
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 511
−4 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 964
20 постов
Вовлечённость
130,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • እንኳን ለምድራዊ መልአክ ቅዱስ ያሬድ በዓል በሰላም አደረሰን !

  • እግዚአብሔር ዐለም ቦታ ሆኖላቸው የሚኖሩበት፣ እነርሱም ዐለም ቦታ ሆነውት የሚኖርባቸው ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉ ፡፡ https://t.me/libonatube

  • ✞ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዓብይ ሀይል ወስልጣን አጋዕዞ ለአዳም አሰሮ ለሰይጣን ሰላም እሚዜሰ ኮነ ፍሰሀ ወሰላም....እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሠላም አደረሳችሁ !

  • 🔘እግዚአብሔር ይመስገን ሌላ ምን ይባላል ! ላለፉት ወራቶች የተጠለፈው የዩቱብ አካውንታችን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተመልሷል ፡፡ውድ ቤተሰቦቼ አሁን ያለንበት የሰሙነ ሕማማት ሳምንት የፆም ወቅት እንደመሆኑም ዝርዝር ነገሩን በአሁን ሰዓት ማቅረብ ተገቢ ነው ብዬ ስለማላስብ ከትንሳኤ በኋላ ሙሉ መረጃን ይዜላችሁ እንደምቀርብ እያሳወኩኝ እስከዛም ግን የዛሬ ሁለት ዓመት ያዘጋጀነውን ሕማማት የተሰኘውን ትረካ በዩቱባችን ላይ እየገባችሁ እያደመጣችሁ ትቆዩኝ ዘንድ እየጠየኩ ።እንዲሁም ዩቱብ አካውንታችን ላለፉት ወራት በሌላ ሰው እጅ ሌሎች የውጭ ቪዲዮች እየተለቀቁበት ስለነበር እንዲሁም ከዚህ ቀደም እኔ የሰራዋቸው ቪዲዮች ሙሉ ጠፍተው ስለነበር እየገባችሁ ሌሎችም አስተማሪ ቪዲዮች እየተመለከታችሁ ዩቱባችንን እንድታነቃቁልኝ ስል በትህትህና እጠይቃለው ፡፡ መልካም የበረከት ፆም ያድርግልን ለብርሀነ ትንሳዬውም በሰላም ያድርሰን ፡፡አሜን ፫ ያብስራ ማቴዎስ ▶️ልቦና ቲዩብ -https://youtube.com/@libonatubee?si=lbnXp0_kurklgdaB ▶️ሕማማት ትረካ -https://youtube.com/playlist?list=PLaHOIicdErt__MDtp8cKn7NXtKLKvQlmo&si=LfGQcuL8TiNEP66P

  • 'ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ከጸጋ የሚገኘውን ደስታ ከመከራ ጋራ፣ ከመከራ የሚገኘውን ኀዘን ከጸጋ ጋራ አንድ አድርጎታል፡፡' @libonatube

  • ዛሬጥር 10 የከተራ በአል ነው እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ከተራ ማለት? ከተራ ማለት "ከተረ" ከምለው ከግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ዙርያውን ከበበ፣ አጠረ፣ ገደበ ማለት ነው። #ከተራ ማለት ከተረ፣ አጠረ፣ ሰበሰበ ማለት ሲሆን ይኸውም ወራጁን ውሃ ሰብስቦ ወይም ገድበው በየሰበካው ተለይቶና ተከልሎ ለጥምቀት የምዘጋጁበት ዕለት ነው። >>ታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረዳቸው - ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን አስከትሎ ሊጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ የመወረዱ ምሳሌ ነው። ታቦታቱ የጌታችን ምሳሌዎች ናቸው። >>>ታቦታቱን ያከበሩ ካህናት የመጥምቁ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ምሳሌዎች ናቸው። ባህረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ምሳለ ነው። >>ታቦታቱን አጅበው የምሄዱ ምዕመናን ወደ መጥምቁ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ እየሄዱ ንሰሃ እየገቡ የንሰሃን ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩ የእኔሱ ምሳሌዎች ናቸው። መልካም የከተራ በዓል @libonatube

  • ጥር ፬ ለዘሰአለከ ሀቦ፤ ለሚለምንህ ሥጠው እንጂ አትከልክለው የሚለውን የወንጌል ትዕዛዝ አንተ ታወቃለህና ከፍ ያለች የከበረች በረከትህን እነሆ እኛ እንልጋለን፤ ባለፀጋ ዮሐንስ ሆይ! መስጠትን ችላ አትበለን፤ የድሆች ሕይወታቸው ልመና ነውና፡፡ (መልክአ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚህ) እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ዮሀንስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! @libonatube

  • እንኳን ለአምላካችን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ። በሀገር ውስጥም በውጭ ለምትኖሩ የልቦና ቤተሰቦች ሁሉ መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ።

  • ታህሳስ 24 የኢትዮጵያ ፀሐይ አባታችን ተክለሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው ። እንኳን ለፃድቁ አባታችን ለአቡነ ተክለሃይማኖት መታሰብያ በአል በሰላም አደረሳችሁ። +ቅዱስ አባት ሆይ የቅዱስ ወንጌል ፀሓፊዋና ሰባኪዋ ማርቆስ የተባልክ አንተ ተክለሃይማኖት ነህ አኮን፤ስለዚህ ስለ ንፁሕ ወርቅና ብርም ፈንታ አባት ሆይ የምስጋና እጅ መንሻ አቀርብልሃለሁ። +አባታችን ተክለሃይማኖት ሆይ የነፍስና የስጋ ሐኪም ሉቃስ የተባልክ እኔ አገልጋይህን ከበሽታዬ ከደዌዬ ፈዉሰኝ? መልክአ ተክለሃይማኖት @libonatube

  • እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!! " ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።"                 ዳን. ፱፥፳፩ /9፥21/ - በቅዱሱ መጽሐፍ ስማቸው ከገነነ የእግዚአብሔር መላእክት አንዱ ቅዱስ ገብርኤል ነው - የስሙም ትርጓሜ "ከእግዚአብሔር የሆነ አለቃ" ማለት እንደሆነ መጽሐፍት ይነግሩናል - ቅዱስ ገብርኤል ብሥራትን በማወጅ የሚታወቅ መልአክ ነውና የደስታና የብሥራት መልአክ ይባላል -የሰው ልጆችን መዳን ታላቁን የምሥራች ይዞ በመምጣቱና በሐዲስ ኪዳን ተደጋግሞ ስሙ በመጠቀሱ "መጋቤ ሐዲስ" ይባላል አምላካችን እግዚአብሔር መላእክቱን ልኮ የነደደብንን እሳት ያጥፋልን። የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አይለየን። @libonatube

  • ⛔️ውዶ ቤተሰቦቼ እንደምን ከረማችሁ ዩቱቤ ስለተጠለፈ መጥፎ ይዘት ያላቸው እኔን የማይወክሉ ነገሮች ሊለቀቁ ስለሚችሉ ከወዲሁ ከኔ እንዳልሆነ እንድታውቁልኝ ስል እወደላሁ ። ዩቱቡ የሚመለስበትን መንገድን ሁሉ እያደረኩ ነው ። አመሰግናለሁ !

  • ህዳር ፅዮን 21 እንኳን አደረሳችሁ በዚህች ቀን የእስራኤላውያን መመኪያ በእመቤታችን ስም የተሰየመችው ታቦተ ጽዮን ዳጐን በተባለው ጣኦት ላይ ኃይሏን ክብሯን የገለጸችበት ቀን ነው፤ ቤተክርስቲያን ጽዮን ማርያም ስትል ዕለቱን ታከብረዋለች። ታሪክ : - አክሱም ጽዮን እንደዛሬው ድርቅ ያለ መሬት አልነበረም ባህር ነበር እንጂ፤ አብርሃና አጽብሃ ለታቦተ ጽዮን ምን ዓይነት ቤተክርስቲያን ነው የምንሰራላት ቦታውስ የት ጋር ነው የሚሆነው እያሉ ሲጨነቁ ጌታችን ተገለጸላቸው ድንጋይ ላይ ቆሞም አዩት፤ ቤተክርስቲያኗን እዚህ ባህር ላይ ስሩት ስሟንም በእናቴ ስም ሰይሟት፤ ይላቸዋል ጌታ ሆይ ይህ እኮ ባህር ነው ይሉታል ቅዱስ ሚካኤልን ከገነት አፈር ይዞ እንዲመጣ ያደርገዋል ባህሩ ላይ ነሰነሰው ደረቀ የዛሬውንም ቅርጽ ያዘ ይላል ጌታችን የቆመበት የእግሩ ምልክት ዛሬም ድረስ ይታያል ፤ ምንጭ ድርሳነ ጽዮን፤ በድንኳን ቅርጽ የተሰራው ቤተክርስቲያን ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ያሳነጹት ሴቶችም ወንዶችም የሚገቡበት። በመሐል ታቦተ ጽዮን ያለችበት እቴጌ መነን ያሳነጹት ስመ ጥምቀታ ወለተ ጊዮርጊስ በስሩ የጥንቱ ቤተመቅደስ ፍርስራሽ ይታያል በአራት መአዘን ቅርጽ ያለው አፄ ፋሲለደስ ያሳነጹት ሴቶች የማይገቡበት ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ነው። ፅዮን ማርያም ባልንበት ፀሎት ልመናችንን ትስማን @libonatube

  • እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ በያለንበት አይለየን!! @Libonatube

  • <<<< ኅዳር ፮ >>>>> #ቊስቋም ማርያም እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ቊስቋም ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓሏ በሰላም አደረሳችሁ ። በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው ። ከግብጽ ሲመለሱ ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤ እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው ብትለው "ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ኢትዮጵያ ናት፤ በዚህች አገር ያሉ ሳይዩኝ ያመኑኛል፤ አስራት በኩራትሽ ትሁን ብሎ ሰጥቷታል፡፡ በኪደተ እግራቸውም ጣና ሐይቅን ፤ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ኡራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል፡፡ ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን:: @Libonatube

  • ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በግብጽ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሒድ አለ። እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ። -ማቴ 2:19-21

  • ሳይንቀሳቅስ፣ ጥረት ሳያደርግ፣ ሳይደክም፣ ሳይለፋ፣ ሳይራብ፣ ሳይጠማ፣ ራሱን ሳይገዛ ተኝቶና ተጎልቶ "እግዚአብሔር ያውቃል" የሚል ሰው ቀንደኛው አሿፊና ቦዘኔ ነው። //ዘአቡነዮሴፍ//

  • https://youtu.be/_9uKw8DtgUA?si=uyXoUo3fIXOiZhp-

  • በእርሱም_ቍስል_እኛ_ተፈወስን።”           ት/ኢሳይያስ ፶፫፥፭ እንኳን አደረሰን ጥቅምት ፳፯ (መድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል) እሱ ንፁህ፣ ነውር የሌለበት ስለኛ የደም ዋጋ የከፈለልን፣ ቸሩ መድኃኔዓለም ይክበር ይመስገልንል። #መድኃኔዓለም ጥቅምት 27 ቀን ቤተክርስቲያናችን የመድኃኔዓለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው አንዴ ብቻ ነው እርሱም መጋቢት 27 ቀን፤ ይህ ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡ ✝️ መድኃኒዓለም ሆይ እኛን ለማዳን መከራን ለመቀበል ዘንበል ላለው እራስህ ሰላም እላለሁ ✝️ የቅዱሳንን ጥሪ ለሚሰማ እዝንህና ድሆችን ለሚመለከቱ ዓይኖችህ ሰላም እላለሁ ✝️ ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ በመስቀል ላይ በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህንም በጦር በወጉህም ጊዜም አንዳችም  የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰም እስትንፋስህም  ሰላም እላለሁ ✝️ አቤቱ አምላኬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ልጆችህን ከመከራ ስጋ ወነፍስ ጠብቀን ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን። አሜን @libonatube @libonatubegroup

  • https://youtu.be/w8MAM7lcO5A?si=_0d6aH_odNPcJ1El

  • ''ጉዞ ወደ እግዚአብሔር '' በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ትርጉም :- ዲ/ን ግርማ ባቱ https://t.me/libonatube

ልቦና ቲዩብ ገፅ — tgindex