በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )
Статистикаዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው 1ጴጥሮስ 1:23-ፍጻሜ
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 463
- 1/48двое суток
- 530
- 1/72трое суток
- 572
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
09/12/2018 የዕለቱ የወንጌል ክፍል ዮሐንስ 10:1-22 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው። ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል። የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና። ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ምን እንደ ሆነ አላስተዋሉም። ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ። ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም። በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል። ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል። ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል። መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ። ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ። ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ። እንግዲህ ከዚህ ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ሆነ። ከእነርሱም ብዙዎች፦ “ጋኔን አለበት፡ አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ?” አሉ። ሌሎችም፦ “ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዕውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን?” አሉ..... ፊልጵስዩስ 1:12-24 2 ዮሐንስ 1:6-ፍጻሜ ሐዋ.ሥራ 15:9-25 ምስባክ መዝ 44:9 ወትቀውም ንግሥት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኅብርት ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ እዝነኪ ትርጉም ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ተሸፋፍና ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ
8/12/2018 ማቴዎስ 7:12-26 ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፥ ነቢያትም የሚያዝዙት ይህ ነውና። በጠባቢቱ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የምትወስድ ሰፊ በር፥ ሰፊ መንገድም አለችና፤ ወደ እርስዋም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው። "ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ፥ መንገድዋም ቀጭን ናትና፤ የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው። “የበግ ለምድ ለብሰው ወደ እናንተ ከሚመጡ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፤ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ናቸው። "ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾህ ወይን፥ ከአሜከላም በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ያፈራል፤ ክፉ ዛፍም ክፉ ፍሬን ያፈራል። መልካምም ዛፍ ክፉ ፍሬን ማፍራት፥ ክፉ ዛፍም መልካም ፍሬን ማፍራት አይችልም። "መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። “እንግዲህ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ ከሚያደርግ በቀር አቤቱ! አቤቱ! የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። «በዚያች ቀን ብዙዎች አቤቱ! አቤቱ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። ያንጊዜ ከቶ አላውቃችሁም፤ ዐመፅን የምታደርጉ ሁላችሁ ከእኔ ራቁ እላቸዋለሁ። ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ብልህ ሰውን ይመስላል። ዝናም ዘነመ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንም ቤት ገፉት፤ ነገር ግን አልወደቀም፤ በዐለት ላይ ተመሥርቶአልና....... ሮሜ 9:24-ፍጻሜ 1 ጴጥሮስ 4:12-ፍጻሜ ሐዋ.ሥራ 16:35-ፍጻሜ 👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ) ምስባክ መዝሙር 57:8-9 ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ ትርጉም እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላየኋትም እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይውጣችኋል
7/12/2018 ማቴዎስ 16:13-21 ጌታችን ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፥ “የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?” ብሎ ጠየቃቸው። "እነርሱም፥ “መጥምቁ ዮሐንስ ነው የሚሉ አሉ፤ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ፥ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ” አሉት። "እርሱም፥ “እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። "ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፥ “አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ” አለው። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ አንተ ብፁዕ ነህ፤ በሰማይ ያለው አባቴ ነው እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና። እኔም እልሃለሁ፤ አንተ ዐለት ነህ፤ በዚያች ዐለት ላይም ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ፤ የሲኦል በሮችም አይበረታቱባትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈታው በሰማይ የተፈታ ይሆናል።” ከዚህም በኋላ እርሱ ክርስቶስ፤ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይናገሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው... ዕብራውያን 9:1-11 1 ጴጥሮስ 2:6-18 ሐዋ.ሥራ 10:1-30 👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ) ምስባክ መዝሙር 93:12-13 ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚአ ወዘመርሀኮ ሕገከ ከመ ይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት ትርጉም አቤቱ አንተ የገሠጽኸው ሰው ብፁዕ ነው ሕግህንም ያስተማርኸው ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ
6/12/2018 ማርቆስ 16:9-19 በእሑድ ሰንበትም ማለዳ ተነሥቶ ሰባት አጋንንትን ላወጣላት ለማርያም መግደላዊት አስቀድሞ ታያት። እርስዋም ሄዳ ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ ነገረቻቸው። እነርሱ ግን ሕያው እንደ ሆነ፥ ለእርስዋም እንደ ተገለጠላት በሰሙ ጊዜ አላመንዋትም። "ከዚህም በኋላ፥ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ገጠር ሲሄዱ በሌላ መልክ ተገለጠላቸው። "እነርሱም ደግሞ ሄደው ለባልንጀሮቻቸው ነገሩ፤ አነርሱንም ቢሆን አላመኑአቸውም። "ከዚህም በኋላ፥ ደግሞ ዐሥራ አንዱ በማዕድ ተቀምጠው ሳለ ተገለጠላቸው፤ እንደ ተነሣ ያዩትን አላመኑአቸውምና ስለ ሃይማኖታቸው ጕድለት ገሠጻቸው፤ የልባቸውንም ጽናት ነቀፈ። እንዲህም አላቸው፥ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ለፍጥረትም ሁሉ ወንጌልን ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ” ይህችም ምልክት በስሜ የሚያምኑትን ትከተላቸዋለች፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋም ይናገራሉ። "እባቦችንም በእጃቸው ይይዛሉ፤ የሚጎዳቸውም ነገር የለም፤ የሚገድል መርዝ ቢጠጡም የሚጐዳቸው የለም፣ በድውያን ላይም እጃቸውን ይጭናሉ፤ ድውያኑም ይፈወሳሉ..... 1 ቆሮንጦስ 3:10-22 1 ጴጥሮስ 3:1-7 ሐዋ.ሥራ 16:13-19 👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ) አው ዘ፫፻ (ግሩም) ምስባክ መዝሙር 44:12-13 ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን ትርጉም የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ ለሐሴቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው
05/12/2018 ሉቃስ 15:1-11 ቀራጮችና ኀጢኣተኞችም ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። ጻፎችና ፈሪሳውያንም፥ “ይህስ ኀጢኣተኞችን ይቀበላል፤ አብሮአቸውም ይበላል” ብለው አንጐራጐሩ። 'እንዲህም ብሎ መሰለላቸው። “ከእናንተ መካከል መቶ በጎች ያሉት ሰው ቢኖር፥ ከእነርሱ አንዲቱ ብትጠፋው ዘጠና ዘጠኙን በምድረ በዳ ትቶ እስኪ ያገኛት ድረስ ይፈልጋት ዘንድ ወደ ጠፋችው ይሄድ የለምን? በአገኛትም ጊዜ ደስ ብሎት በትከሻው ላይ ይሸከማታል። ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ፥ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹን ጠርቶ፦ የጠፋችኝን በጌን አግኝቼአታለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል። እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኙ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በሰማያት ፍጹም ደስታ ይሆናል። "ዐሥር ድሪም ያላት ሴት ብትኖር፥ አንዲቱ ብትጠፋባት መብራት አብርታ በቤቷ ያለውን ሁሉ እየፈነቀለች እስክታገኛት ድረስ ተግታ ትፈልግ የለምን? 'ያገኘቻት እንደሆነ ወዳጆችዋንና ጎረቤቶችዋን ጠርታ የጠፋችብኝን ድሪሜን አግኝቼአታለሁና፥ ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች። እላችኋለሁ፣ እንዲሁ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት በሰማያት፥ ደስታ ይሆናል........ 2 ቆሮንጦስ 12:10-17 1 ዮሐንስ 5:14-ፍጻሜ ሐዋ.ሥራ 15:1-13 👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ አው ግሩም ምስባክ መዝሙር ፲፯ :፵፫ – ፵፬ ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ ትርጉም የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ የማላቀው ሕዝብም ይገዛልኛል በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ
ሕዝቅያስ ንጉሥ ወፊልጶስ ወአኃዊሁ ወማቴዎስ 4/12/2018 የዕለቱ የወንጌል ክፍል ሉቃስ 14:31-ፍጻሜ ወይም ሌላውን ንጉሥ በጦርነት ሊጋጠም የሚሄድ፥ ከሁለት እልፍ ጋር የሚመጣበትን በአንድ እልፍ ሊገናኝ የሚችል እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ የማያስብ ንጉሥ ማን ነው? ባይሆንስ ሌላው ገና ሩቅ ሳለ መልክተኞች ልኮ ዕርቅ ይለምናል። እንግዲህ እንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።” “ጨው መልካም ነው፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፈጣል? ለምድር ቢሆን ለፍግ መቈለያም ቢሆን አይረባም፤ ወደ ውጭ ይጥሉታል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።” ሮሜ 12:16-ፍጻሜ 1 ጴጥሮስ 5:6-12 ሐዋ.ሥራ 17:23-28 ምስባክ መዝሙር 20:1-2 እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ ትርጉም አቤቱ፥ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፤ በማዳንህ እጅግ ሐሤትን ያደርጋል። የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥
ዘሰንበተ ክርስቲያን ማቴዎስ 12:38-ፍጻሜ ያንጊዜም ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ወገን ሰዎች መጥተው፥ “መምህር ሆይ፥ ከአንተ ምልክት ልናይ እንወዳለን” አሉት። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ዐመፀኛዪቱና፤ አመንዝራዪቱ ትውልድ ምልክትን ትሻለች፤ ምልክት ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር አይሰጣትም። ዮናስ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በዓሣ አንበሪ ሆድ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በምድር ልብ ውስጥ ይኖራልና። የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ተነሥተው ይህችን ትውልድ ይፋረዱአታል በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆ፥ ከዮናስ የሚበልጥ በዚህ አለ። "ንግሥተ አዜብ በፍርድ ቀን ተነሥታ ከዚች ትውልድ ጋር ትፋረዳለች፥ የሰሎሞንን ጥበብ ትሰማ ዘንድ ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፣ እነሆ፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ በዚህ አለ። "ርኩስ መንፈስም ከሰው ከወጣ በኋላ፥ ዕረፍት ሲሻ ውኃ ወደሌለበት ምድረ በዳ ይዞራል፤ አያገኝምም። "ከዚህም በኋላ፥ እንግዲህስ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፤ በመጣም ጊዜ ባዶ ሆኖ፥ ተጠርጎና ተለስኖ ያገኘዋል። ከዚህም በኋላ ይሄዳል፤ ከእርሱም የሚከፉ ሌሎች ሰባት አጋንንትን ያመጣል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው የኋላ ኑሮው ከፊተኛው የከፋ ይሆናል፤ ለዚችም ክፉ ትውልድ እንዲሁ ይሆንባታል።” "ለሕዝቡም ይህን ሲነግራቸው፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊያነጋግሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። ከደቀ መዛሙርቱም አንዱ መጥቶ፥ “እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ከውጭ ቆመዋል፤ ሊያነጋግሩህም ይሻሉ” አለው። እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፥ “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” አለው። "እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ፥ “እነሆ፥ እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው። በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ወንድሜ፥ እኅቴ፥ እናቴም ነውና” አለ..... 1 ቆሮንጦስ 8:1-ፍጻሜ 1 ጴጥሮስ 4:1-6 ሐዋ፡ሥራ 26:1-29 ምስባክ መዝሙር ፹፮ : ፭ – ፮ እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ ወውእቱ ልዑል ሣረራ ትርጉም ሰው እናታችን ጽዮን ይላል በውስጥዋም ሰው ተወለደ እርሱ ራሱም ልዑል መሰረታት
2/12/2018 ዮሐንስ 8:1-12 ኢየሱስ ግን ወደ ደብረ ዘይት ሄደ። ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ። ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር። ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፦ “መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ?” አሉት። የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፦ “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት፡” አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፦ “አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት። እርስዋም፦ “ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ” አለች። ኢየሱስም፦ “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ፡” አላት። 1 ጢሞቴዎስ 2:8-ፍጻሜ 1 ጴጥሮስ 3:1-7 ሐዋ.ሥራ 16:13-19 👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ) ምስባክ መዝሙር 44:14-15 ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግለ ድኅሬሃ ወቢጸሂ ይወስዱ ለከ ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበሐሤት ትርጉም በዃላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ ባልንጀራዎቿንም ወዳንተ ያቀርባሉ በደስታና በሐሴት ይወስዷቸዋል
ወፌ ሰንብታ ሰንብታ መጣች በፍልሰታ
01/12/2018 ዮሐንስ 19:38-ፍጻሜ ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ። ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት። በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ። ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ አኖሩት........ 1 ጢሞቴዎስ 5:1-11 1 ዮሐንስ 5:1-6 ሐዋ.ሥራ 5 : 26-34 👉ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ አው ዘእግዝእትነ ምስባክ መዝሙር 118:47-48 ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኀፈር ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀርኩ ጥቀ ወአንሥእ ዕደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘአፈቀርኩ ትርጉም በነገሥታት ፊት ምስክርኽን እናገራለኹ አላፍርምም እጅግም በወደድዃቸው በትእዛዛትኽ ደስ ይለኛል እጆቼንም ወደ ወደድዃቸው ወደ ትእዛዛትኽ አነሣለኹ
30/11/2018 ማርቆስ 4:35-ፍጻሜ ያንጊዜም ሲመሽ ደቀ መዛሙርቱን፥ “ወደ ማዶ እንሻገር” አላቸው። ሕዝቡንም አሰናበተና በታንኳ ወሰዱት፤ ከእነርሱም ጋር ሌሎች ታንኳዎች ነበሩ። ጽኑ ዐውሎ ነፋስም ተነሣ፤ ከሞገዱም የተነሣ ውኃው ታንኳውን እስኪሞላው ድረስ ማዕበሉ ወደ ታንኳው ይገባ ነበር። እርሱ ግን በታንኳው በስተኋላ በኩል ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ ቀስቅሰውም፥ “መምህር ሆይ፥ ስንሞት አያሳዝንህምን?” አሉት ተነሥቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕርዋንም “ዝም በዪ፥ ጸጥ በዪ” አላት ፤ ነፋሱም ዝም አለ ፍጹም ጸጥታም ሆነ። “እንዲህም አላቸው፥ “እናንተ ደካሞች፤ ምን ያስፈራችኋል? እንዲህስ እምነት የላችሁም?” ታላቅ ፍርሀትንም ፈሩ፤ እርስ በርሳቸውም፥ “እንግዲህ ባሕርም፥ ነፋስም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ .... 1ቆሮንጦስ 2:1-9 2ጴጥሮስ 1:12-17 ሐዋ፡ሥራ 3:1-10 👉ቅዳሴ ዘሐዋርያት ምስባክ መዝሙር ፻፳፫ : ፬ – ፭ እምውኂዝ አምሠጠት ነፍስነ አምሠጠት ነፍስነ እማየ ሐከክ ይትባረክ እግዚአብሔር አምላክነ ዘኢያግብአነ ውስተ መሥገርተ ማዕገቶሙ ትርጉም ነፍሳችንም ከጐርፍ አመለጠች ነፍሳችን ከክርክር ውኃ አመለጠች ወደ ከባቢ ወጥመዳቸው ያላገባን እግዚአብሔር ይመስገን
29/11/2018 ሉቃስ 12:1-13 በዚያን ጊዜ የሕዝብ አእላፍ እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ተሰብስበው ሳሉ፥ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ “አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው። ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም። ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፥ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይሰበካል። ለእናንተም ለወዳጆቼ እላችኋለሁ፥ ሥጋን የሚገድሉትን በኋላም አንድ ስንኳ የሚበልጥ ሊያደርጉ የማይችሉትን አትፍሩ። እኔ ግን የምትፈሩትን አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ። አዎን እላችኋለሁ፥ እርሱን ፍሩ። አምስት ድንቢጦች በአሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ስንኳ በእግዚአብሔር ፊት አትረሳም። ነገር ግን የእናንተ የራሳችሁ ጠጕር ሁሉ እንኳ የተቈጠረ ነው፤ እንግዲያስ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች ትበልጣላችሁ።” “እላችሁማለሁ፥ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል፤ በሰውም ፊት የሚክደኝ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይካዳል። በሰው ልጅም ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ መንፈስ ቅዱስን የሚሰድብ ግን አይሰረይለትም። ወደ ምኵራቦችና ወደ መኳንንቶችም ወደ ገዢዎችም ሲጐትቱአችሁ፥ እንዴት ወይም ምን እንድትመልሱ ወይም እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ መንፈስ ቅዱስ በዚያች ሰዓት ልትናገሩ የሚገባችሁን ያስተምራችኋልና....... ገላትያ 3:15-ፍጻሜ 1 ዮሐንስ 4:9-18 ሐዋ.ሥራ 9:20-32 👉ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ (እምቅድመ ዓለም) ምስባክ መዝሙር 33:19-20 ወእምኵሉ ያድኅኖሙ እግዚአብሔር እግዚአብሔር የዐቅብ ኵሎ አዕፅምቲሆሙ ወኢይትቀጠቀጥ አሐዱ እምውስቴቶሙ ትርጉም እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል ከእነርሱም አንድ አይሰበርም
የዕወቀት ባለቤት ጥበብን የሚያናግር በጥልቅ ጨለማ ውስጥ ተሰውሮ የነበረውን የገለጽክልን የኃይልህን ከፍታ ለሚሰብኩ የደስታ ቃልን የምትሰጥ ። ቀድሞ ያሳድድ የነበረ ጳውሎስን በብዙ ቸርነትህ የጠራኸው የተመረጠ ዕቃም ያደረግኸው አንተ ነህ በዚህም ወደድኸው ሐዋርያ ይሆን ዘንድ የምትጠራ የመንግሥትህንም ወንጌል የሚያስተምር ይሆን ዘንድ። አምላካችን ክርስቶስ ሆይ ሰውን የምትወድ አንተ ነህ ። ቸር ሆይ ያለ ሥራ ዕውቀትን ካንተ የማይለይ ንጹሕ ሕሊናንም ስጠን ። ዛሬም ከርሱ ዘንድ በኛ ላይ የተነበበች ክብርት የምትሆን የትምህርትህን ልክ እናውቅ እናስተውል እንረዳም ዘንድ ። የሕይወት ራስ ሆይ አንተን እንደመሰለ እኛም እንደሱ በምግባር በሃይማኖት እሱን እንመስል ዘንድ የቢቃን አድርገን ። ቅዱስ ለሚሆን ለስምህ ምስጋና እናቀርብ ዘንድ ክቡር በሚሆን በመስቀልህም ሁልጊዜ እንመካ ዘንድ ። መንግሥት ያንተ ናትና ከሃሊነት ገናንነትና ሥልጣን ክብርምስጋናም ለዘለዓለሙ መጽሐፈ ቅዳሴ
28/11/2018 ማቴዎስ 19:1-23 ጌታችን ኢየሱስም ይህን ነገር ከፈጸመ በኋላ ከገሊላ ተነሥቶ ወደ ይሁዳ አውራጃ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ደረሰ። ብዙዎች በሽተኞችም ተከተሉት፤ በዚያም ፈወሳቸው። 'ፈሪሳውያንም ሊፈትኑት ወደ እርሱ መጥተው፥ “በማናቸውም በበደለችው ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ለሰው ይገባልን?” አሉት። እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “አላነበባችሁምን? በመጀመሪያ የፈጠራቸው እርሱ ወንድና ሴት አደረጋቸው።” እንዲህም አለ፥ “ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ሚስቱን ይከተላል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ። እንኪያስ ሁለት አይደሉም፤ አንድ አካል ናቸው እንጂ፤ እግዚአብሔርም አንድ ያደረገውን ሰው አይለይ።” እነርሱም፥ “እንኪያ የፍቺዋን ደብዳቤ ሰጥተው እንዲፈቱአት ሙሴ ለምን አዘዘ?” አሉት። እርሱም አላቸው፥ “ሙሴስ ስለ ልባችሁ ክፋት ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ፈቀደላችሁ፤ ቀድሞ ግን እንዲህ አልነበረም። "እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፤ የተፈታችውንም ያገባ ያመነዝራል።” ደቀ መዛሙርቱም፥ “የባልና የሚስት ሥርዐት እንዲህ ከሆነስ መጋባት መልካም አይደለም” አሉት። “እርሱም አላቸው፥ “ይህ ለተሰጠው ነው እንጂ ለሁሉ የሚቻል አይደለም። «ከእናታቸው ማኅፀን እንዲሁ የተወለዱ ጃንደረቦች አሉና፤ ሰዎች የሰለቡአቸውም ጃንደረቦች አሉ፤ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን ጃንደረባ ያደረጉ አሉ፤ መታገሥ የሚችል ግን ይታገሥ..... 1 ቆሮንጦስ 7:1-ፍጻሜ 1 ጴጥሮስ 3:1-8 ሐዋ፡ሥራ 7:1-9 👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ) ምስባክ መዝሙር 54:13-14 ወአንተሰ ብእሲ ዘከመ ነፍስየ ማእምርየ ወዐውቅየ ዘኅቡረ አስተጠዓምከ ሊተ መባልዕት ትርጉም አንተ ሰው አንተ ግን እንደ ነብሴ ነበርኽ ባልንጀራዬ የማውቅህ መብልን ከእኔ ጋር በአንድነት ያጣፈጥህ ነበርህ
ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥ ኃጢአተኛውን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ፡፡ ያዕቆብ 5:19-20
ዕብራውያን 2:17-18 ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው። እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።
27/11/2018 የዕለቱ የወንጌል ክፍል ዮሐንስ 10:34-ፍጻሜ ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ “እኔ፦ ‘አማልክት ናችሁ አልሁ፡’ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፡ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ ‘ትሳደባለህ፡’ ትሉታላችሁን? እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤ ባደርገው ግን፥ እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።” እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም ወጣ። ዮሐንስም በመጀመሪያ ያጠምቅበት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ እንደ ገና ሄደ በዚያም ኖረ። ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ መጥተው፦ “ዮሐንስ አንድ ምልክት ስንኳ አላደረገም፥ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነበረ፡” አሉ። በዚያም ብዙዎች በእርሱ አመኑ....... ዕብራውያን 5:7-ፍጻሜ 1 ዮሐንስ 5:16-ፍጻሜ ሐዋ.ሥራ 4:14-19 ምስባክ መዝሙር 88:18-19 ወቅዱሰ እስራኤል ንጉሥነ ውእተ ዓሚረ ተናገርኮሙ በራእይ ለደቂቅከ ወትቤ እሬሲ ረድኤት በላዕለ ኃይል
ዘሰንበተ ክርስቲያን ማቴዎስ 8:1-ፍጻሜ ከተራራም ሲወርድ ብዙ ሰዎች ተከተሉት። "እነሆ፥ አንድ ለምጻም ሰው መጥቶ፥ “አቤቱ! ከወደድህስ እኔን ማንጻት ይቻልሃል” እያለ ሰገደለት። 'እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈቅዳለሁ ንጻ” አለው፤ ያንጊዜም ከለምጹ ነጻ። 'ጌታችን ኢየሱስም፥ “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፣ ነገር ግን ሂድና ራስህን ለካህን አስመርምር፤ ምስክርም ሊሆንባቸው ሙሴ እንደ አዘዘ መባህን አቅርብ” አለው። ወደ ቅፍርናሆም በገባ ጊዜ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ መጥቶ፦ “አቤቱ! ልጄ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተጨነቀ በቤት ተኝቶአል” ብሎ ለመነው። ጌታችን ኢየሱስም “እኔ መጥቼ እፈውለዋለሁ” አለው። የመቶ አለቃውም መልሶ፥ “አቤቱ! አንተ ከቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም ነገር ግን በቃልህ እዘዝ፤ ልጄም ይድናል፤ "እኔም እኮ የምገዛ ሰው ነኝ፣ የማዝዛቸውም ጭፍሮች አሉኝ፤ ይህን ሂድ ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ና ብለው ይመጣል፤ አገልጋዬንም ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል” አለው። ጌታችን ኢየሱስም ሰምቶ አደነቀ፤ ለሚከተሉትም እንዲህ አለ፥ “እውነት እላችኋለሁ፤ በእስራኤል ሁሉ እንዲህያለ እምነት አላገኘሁም፣ “ነገር ግን እላችኋለሁ፦ ብዙ ዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፤ በመን ግሥተ ሰማያትም ከአብርሃምና ከይስሐቅ፥ ከያዕቆብም አጠገብ ይቀመጣሉ። “የመንግሥትን ልጆች ግን በውጭ ወደ አለ ጨለማ ይጥሏቸ ዋል፤ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆ ናል።” "ጌታችን ኢየሱስም የመቶ አለቃውን እንዲህ አለው፥ “እንግዲህ ሂድ እንደ እምነትህ ይሁንልህ።” ልጁም በዚያ ሰዓት ዳነ፤ መስፍኑም ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ልጁ ድኖ አገኘው። ጌታችን ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ የጴጥሮስን አማት በንዳድ ታማ ተኝታ አገኛት። እጅዋንም ይዞ ዳሰሳት፤ ንዳዱም ተዋት፤ ተነሥታም አገለገለቻቸው። "በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደሩባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ ኣጋንንትንም በቃሉ አወጣቸው። የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ። " ይህም ነቢዩ ኢሳይያስ፥ “ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ” ብሎ የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ነው። ጌታችን ኢየሱ ስም በዙሪያው የተሰበሰቡትን ብዙ ሰዎች በአየ ጊዜ ባሕሩን ተሻግረው እንዲሄዱ አዘዘ። “አንድ ጸሓፊ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “መም ህር፥ ወደምትሄድበት ሁሉ ልከተልህን?” አለው። ጌታችን ኢየሱስም፥ “ለቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፤ ለሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም” አለው። “ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን ልቅበር ፍቀድልኝ” አለው። ጌታችን ኢየሱስም፥ “አንተስ ተከተለኝ፤ ሙታኖቻቸውን ይቀብሩ ዘንድ ሙታንን ተዋቸው” አለው። ወደ ታንኳ በወጣ ጊዜም ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። እነሆም፥ የባሕሩ ማዕበል ታንኳውን እስኪደፍነው ድረስ በባሕሩ ውስጥ ታላቅ መናወጥ ሆነ፣ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው ቀሰቀሱትና፥ “አቤቱ! እንዳንሞት አድነን” አሉት። “እርሱም፡ “እናንተ እምነት የጐደላችሁ ምን ያስፈራችኋል?” አላቸው፤ ተነሥቶም ነፋሳትንና የባሕሩን ማዕበል ገሠጻቸው ታላቅ ጸጥታም ሆነ ሰዎችም፡ “ባሕርና ነፋሳትስ እንኳ የሚታዘዙለት ይህ ማነው?” እያሉ ተደነቁ። ወደ ማዶም ወደ ጌርጌሴኖን ሀገር በደረስ ጊዜ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ወጥተው ተቀበሉት፡ እነርሱም ማንም በዚያች መንገድ ማለፍ እስከማይችል ድረስ እጅግ ክፉዎች ነበሩ። ባዩት ጊዜም፥ “የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋርምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደ ዚህ መጣህን?” እያሉ ጮኹ። “ከዚያም ብዙ የእሪያ መንጋዎች ከእነርሱ ርቀው ተስማርተው ነበሩ። "እነዚያ አጋንንትም፥ “ካወጣኸንስ በእሪያዎቹ መንጋ ላይ እንድናድር ወደዚያ ስደደን” ብለው ለመኑት፡ እርሱም “ሂዱ” አላቸው። "ወጥተውም ሄዱ፤ በእሪያዎቹም ላይ አደሩ፡ የእሪያዎችም መንጋዎች ሁሉ ከአፋፉ እየሮጡ ወደ ባሕር ውስጥ ወደቁ፣ በውኃው ውስጥም ሞቱ። "እረኞችም ሸሹ፤ ወደ ከተማይቱም ገብተው ነገሩን ሁሉ፥ አጋንንትም ባደሩባቸው የሆነውን አወሩ። “እነሆ፥ በከተማዋ ያሉት ሁሉ ጌታችን ኢየሱስን ሊቀበሉት ወጡ፤ ባዩት ጊዜም ከሀገራቸው እንዲሄድ ለመኑት...... 2 ቆሮንጦስ 10:1-ፍጻሜ ያዕቆብ 3:1-9 ሐዋ፡ሥራ 28:17-ፍጻሜ 👉ቅዳሴ ዘእግዚእነ ምስባክ መዝ· ፷፬ : ፱ – ፲ ሐወጽካ ለምድር ወአርወይካ ወአብዛኅኮ ለብዕላ ፈለገ እግዚአብሔር ምሉዕ ማያት ትርጉም ምድርን ጐበኘሃት አረካሃትም፥ ብልጽግናዋንም እጅግ አበዛህ፤ የእግዚአብሔር ወንዝ ውኆችን የተመላ ነው
25/11/2018 ማርቆስ 13:5-14 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመር፦ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች፦ ‘እኔ ነኝ፡’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል። ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤ በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል..... 1 ቆሮንጦስ 2:1-ፍጻሜ ይሁዳ 1:11-17 ሐዋ፡ሥራ 26:6-12 👉ቅዳሴ ዘወልደ ነጐድጓድ ምስባክ መዝሙር 67:35 መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁ አምላከ እስራኤል ውእቱ ይሁብ ኀይለ ወጽንዐ ለሕዝቡ ወይትባረክ እግዚአብሔር ትርጉም እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው የእስራኤል አምላክ እርሱ ኀይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል እግዚአብሔርም ይመስገን
አባ ኖብ ፲ወ፱ወ፳ወ፬ ማኅበራነ ኖብ ወስምዖን ሊቀ ጳጳሳት 24/11/2018 ማቴዎስ 19:16-22 እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ፦ “መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ?” አለው። እርሱም፦ “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ፡” አለው። እርሱም፦ “የትኞችን?” አለው። ኢየሱስም፦ “አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ፡” አለው። ጐበዙም፦ “ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፥ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?” አለው። ኢየሱስም፦ “ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ፡” አለው.... 2 ቆሮንጦስ 7:8-11 1 ጴጥሮስ 5:1-6 ሐዋ.ሥራ 16:35-ፍጻሜ 👉ቅዳሴ ዘ፫፻ (ግሩም) ምስባክ መዝሙር 54:13-14 ማእምርየ ወዐውቅየ ዘኅቡረ አስተጠአምከ ሊተ መባልዕተ ወነሐውር ቤተ እግዚአብሔር በ፩ ልብ ትርጉም ባልንጀራዬና የማውቅህ መብልን ከእኔ ጋራ በአንድነት ያጣፈጥኽ በአንድ ልብ ወደ እግዚአብሔር ቤት ተራመድን