ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
Статистикаይህ ቻናል የምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ቶማስ መታሰቢያ የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት በቤተ ከርስቲያን ዙሪያ ማስተማሪያና ማወያያ ገጽ ነው።
- Последний пост
- 17:50
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 37
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 114
- 1/48двое суток
- 1 276
- 1/72трое суток
- 1 376
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ በዓለ ጽንሰታ ለማርያም ድንግል። ቤዛ ኵሉ ሚዲያ https://youtube.com/watch?v=EmUVwksDqWw&si=_c8j_Hx58oCMTHdl ጽንሰታ ለማርያም
በጾማችን ላይ የማይበርድ ኦርቶዶክሳዊ ቁጭትና የማይጠፋ ተስፋ ያስፈልጋል።
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ብትግረኛ wdase maryam tirgum by tigrigna https://youtube.com/watch?v=TZgk3KncN9A&si=8QUF_ti9jkRrnf5d ታላቁ ጉባኤ ቤታችን ከያዛቸው ዋና ዋና እቅዶቹ መካከል በሀገራችን ኢትዮጵያ ያሉ ቋንቋዎችን ሁሉ የሚናገሩ ምእመናን በቋንቋቸው ሃይማኖታቸውን እንዲረዱ ማድረግ ለዚህም ቋንቋ ለሚችሉ ደቀመዛሙርት ቅድሚያ ሰጥቶ መቀበል ነው ። ይህ ትርጓሜም የዚህ ሐሳብ ውጤት ነው። የጉባኤ ቤታችን ቤተሰቦች ማዲያችንን በመከታተል ለሰውም እንዲደርስ በማድረግ ቤተክርስቲያንን እወቁ
◈የወንጌል ለምምዳችን በተቃራኒው ሁኗል። በስሁት ልምምድ እነዚህን አፍርተናል👇 ◈1.)የእግዚአብሔርን ቃል እንደተራ ቃል መለማመድ፤ ◈2.)ወንጌልን ሙያና መብያ ማድረግ፤ ◈3.)የማንኖረውን ቃል ለሌላው መስበክ፤ ◈4.)ሳይታወቁ በማስመሰል ሲታወቁ በመቃረን መኖር፤ ◈5.)ሞትንና ትንሣኤ ሙታንን፣ፍትሐ እግዚአብሔርን መርሳት፤ ◈6.)እግዚአብሔር አጎታችን እስኪመስለን ድረስ መዳፈር፤ ◈7.)አምላካዊ አደራን ከቁስ አደራ በታች አድርጎ ማየት፤ ◈8.)ፌዝን ቧልትን እንደ ቁም ነገር ማዘውተር፤ ◈9.)ሲጠቀለል፦ምረረ ገሀነመ እሳትን ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን መዘንጋት ይስተዋልብናል። ◈10.)መፍትሄው ከእነዚህ ጉዳዮች በተቃራኒ መሆን ነው። "ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማል እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል። ይህ ቃል የታመነ ሁሉም እንዲቀበሉት የተገባ ነው ይህን ለማግኘት እንደክማለንና ስለዚህም እንሰደባለን ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።"፩.ጢሞ.፬፥፰-፲
➪ አንድን ገጽ ስታነብ የሞቱት ይናገራሉ፣ ➪ የራቁት ይቀርባሉ፣ ➪ ያልተፈጠሩት ዓለማት በዓይነ-ሕሊናህ ፊት ይገለጣሉ። 👉 የቃላት ውበት ደግሞ በቀላሉ የማይነጥፍ፣ የአእምሮን ረሃብ የሚያስታግስ፣ የነፍስን ባዶነት የሚሞላ የእውቀት ማዕድ ነው። እናም እላችኋለሁ ወዳጆቼ፦ 🛑➠ለዛሬው ወጣት ግን ይህ ውበት «ያልተገለጠ ውበት» ሆኖ ቀርቷል። በአሁኑ ዘመን ማህበራዊ ሚዲያና አጫጭር ቪዲዮዎች የሰውን ትኩረት በጣጥሰውታል። ይህ ደግሞ ወጣቱ ጥልቅ ወደሆነው የመጽሐፍ ውበት እንዳይደርስ አድርጎታል። 👉 በዲጂታል ጫጫታ፣ በቅጽበታዊ መዝናኛዎች! 👉 በአስቂኝና ቀልዳቀልዶች! 👉 በአነቃቂ ንግግሮች! 👉 በውጫዊ ብልጭልጭ ዓለም ውስጥ የተጠመደው የአሁኑ ትውልድ፣ የቃላትን ጥልቅ ውበትና የመጽሐፍን መንፈሳዊ እርካታ ለመቅመስ ጊዜ አጣ፤ መሰልጠንና መታወቅ ፍለጋ ብቻ ሆነ። ወዳጄ፦ 👉 ስልጣኔ ማለት በማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ በሰከንዶች ውስጥ የሚያልፍ መረጃን ማየት ብቻ አይደለም፤ 👉 ስልጣኔ ማለት ሐሳብን በጥልቀት ማሰላሰል፣ መጠየቅ፣ መመርመርና ነገሮችን ከስራቸው መረዳት ነው—ይህ ደግሞ የሚገኘው ከንባብ ብቻ ነው።አንብብ፣ የተቀበረውን ግለጥ! ➵ የተቀበረ ተስፋ ➵ የተቀበረ አቅም ➵ የተቀበረ መረዳት ➵ የተቀበረ መፍትሔ ለውጥ፣ መረዳት የሚገለጡት በንባብ ነው። በተፈጥሮ ውብ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ፣ በመጽሐፍም ውብ ቃላቶች አሉ። የተፈጥሮን ውበት አይተን እንዳናደንቅ ልዩነት ይገድበናል፤ የመጽሐፍን ውበት አነብበን እንዳናደንቅ ደግሞ ስንፍና እና የተዛባ መረዳት ይጋርደናል። ግን ከስንፍና ወጥተን እናንብብ! 🛑➠ለአንድ ሰው በጎ ሕሊና፣ በጎ መምህር፣ በጎ መጽሐፍ ያስፈልገዋል። በመ/ር ብርሃነ ሕይወት አበራ የተከተበ!
👉<< ያልተገለጠ ውበት!>> <በመጀመሪያ አንድ ጥያቄ ላስቀድም> 🛑➠በሕይወታችሁ ከሰው የመጣላችሁ ውብና ድንቅ ስጦታ ቢኖር፤ ነገር ግን ይህ ስጦታ የመጣው ታሽጎና ተቆልፎ ነው እንበል? ስጦታውም እንደመጣ ታሽጎና ተቆልፎ፣ ማንም ሳያየው ከቤታችሁ ክፍል ውስጥ ቢቀመጥ... ውበቱ ለማን ይበጃል? የስጦታው ጠቃሚነትስ በምን ይለካል? ምን እንደሆነስ እንዴት ይታወቃል? አዎ! ዛሬ ልነግራችሁ የመጣሁት ስለዚሁ ‘ያልተገለጠ ውበት’ ነው። 🛑➠ብዙዎቻችን በየቀኑ አጠገባችን አልፈነው የምንሄደው፣ ነገር ግን ካልከፈትነው በቀር ውበቱ የማይገባን፣ ካላነበብነው በቀር ሕይወታችንን የማያበራ አንድ የተሸፈነ ድንቅ ነገር አለ! ዛሬ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይህንን ያልተገለጠ ውበት አብረን እንገልጣዋለን፤ አብራችሁኝ ዝለቁ። በዚህ ዓለም ብዙ ውብ ነገሮች አሉ! እኔ ግን የማሳያችሁ ውብ ሆኖ ሳለ የማይታይ፣ ጥሩ ሆኖ ሳለ የማይፈለግ፣ ወዳጅ ሆኖ ግን የተጠላ፣ ለውበቱ የውበት መወዳደሪያ መለኪያ የማይገኝለትና በመጨረሻም እፁብ እፁብ ብለን ዝም የምንልበት ብቻ ሳይሆን ደግመን የምናየው፣ አይተነውም ደግሞ ስለማንሰለቸው ውበት ነው። ➠ይሄ ውበት ምንድን ነው? ካላችሁኝ መልሱን እነሆ፡ ታይቶ የማይጠገብ፣ ለውበቱ መለኪያ የሌለው ውበት መጽሐፍ ነው። ወዳጆቼ! በዚህ ዓለም ያሉ ድንቅ ነገሮችን «ውብ ናቸው» የምንለው ባነበብነው ለክተን ነው። ታዲያ መጽሐፍን በምን ለክተን ውበቱን እንናገራለን? መደነቅ ነው እንጂ! የሰው ልጅ ውበት የሚታየው በመልካም ሥራውና፣ በፊቱ ፈገግታና በዓይኖቹ ብርሃን ነው፤ የተፈጥሮ ውበት የሚታየው በፈካው አበባና በተዘረጋው ሰማይ ነው። የመጽሐፍ ውበት ግን የት ነው ያለው? የመጽሐፍ ውበት በሽፋኑ ላይ አይደለም፤ በገጾቹ መካከል በተደበቁት ጥበቦች ውስጥ ነው። አሁን ባለንበት ዘመን፣ አእምሯችን በአጫጭር ምስሎችና በቪዲዮዎች በተጠመደበት ወቅት፣ ድንቅ የሆኑ የአእምሮ ውበቶች በመጽሐፍት መደርደሪያዎች ላይ አቧራ እየጠጡ ተሸፍነው ቀርተዋል። እናም የዛሬ ጽሑፌ እዚህ አጠገባችን ተቀምጦ ሳናየው ያለፈውን፣ ያልተገለጠውን የመጽሐፍና የንባብ ውበት አቧራውን (ስንፍናን) አራግፈን ለማየት ነው...» ወጣቱ ከመጽሐፍ በመራቁ ምክንያት ያ ሁሉ የእውቀትና የሕይወት ውበት ማንም ሳያየውና ሳያደንቀው ተሸፍኖ ቀርቷል። ግን ለእናንተ ውብ ምንድን ነው? 🛑➠የዚህ ዘመን ወጣት የሚያወራው ስለ ሴት ውበት፣ ሴቶችም ስለ ወንድ ውበት ነው። ከዚህ ያለፈውም የቁስ ውበት አድናቂ ነው፤ ወይ ልብስና ጫማ፣ ወይ ስልክ ወይም ቤት፣ ጥሩ መኪና ወዘተ... ስለ መጽሐፍ ማሰብም ሆነ መናገር የሚፈልግ የለም፣ አይማርከውምም። «ያልተገለጠ ውበት» ያልኳችሁም ይህ ነው፤ ተመልካች ያጣ ውበት ማለትም ይህ ነው። በእግዚአብሔር የተፈጠሩ ድንቅና ግሩም ውብ ፍጥረቶች አሉ፤ ሰውን ጨምሮ «ግሩምና ድንቅ አድርገህ ፈጥረኸኛልና አመሰግንሃለሁ» እንዳለ ቅዱስ ዳዊት። ውብ አድርጎ እግዚአብሔር ፍጥረትንም የፈጠረው የሱ ውብነት እንዲገለጥ ነው። «ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ የማይታወቅ እግዚአብሔር በፍጥረቱ ይታወቃል» እንዲል ሮሜ 1፡20 ስለዚህ ለሁሉም የሚስማማና ደስ የሚያሰኝ አድርጎ ውብ የሆነው እግዚአብሔር ተፈጥሮን ገልጦታልና በዓይናችን እናያለን፤ የመጽሐፍን ውበት ግን የምትገልጠው አንተ ነህ! መጽሐፉን ስትከፍተው ውበቱ ይገለጣል፤ ገጹን ስትገልጠው ደግሞ አንተ ትገለጣለህ። የውበቱ መለኪያው አንተ ነህ! አንቺ ነሽ! ስለዚህ ወዳጆቼ፦ 🛑➠«መጽሐፍ የተቆለፈ የጥበብ ሙዚየም ነውና፣ ቁልፉ ደግሞ ንባብ ስለሆነ፣ መጽሐፍትን በመክፈት ያልተገለጠውን ውበት ለዓለማችን እንግለጥ!» ጥያቄ፦ ይህን ውበት መመልከትና መግለጥ አያስፈልግምን? ወዳጆቼ! ሰው ያላያቸውን ድንቅ ፍጥረቶች ፈልገን ከተደበቁበት፣ ከተሸፈኑበት እየገለጥን ነው! የመጽሐፍ ውበትንም አንብበህ ግለጠው። ጥሩ አንባቢ ስትሆን ለስድብ ጊዜ የለህም፣ ሥራህ ላይ ትጠመዳለህ፤ አሁን በማኅበራዊ ሚዲያ ተሳዳቢው የበዛው ሥራ ፈት ስለሆነ ነው። ወንድሜ! ለጉልበትህ ሥራ ባትፈጥርለት ለአእምሮህ ሥራ ፍጥርለት፣ ለዓይንህ ሥራ ፍጥርለት! የአእምሮህና የዓይንህ ሥራ ምንድን ነው? «ምን አነባለሁ? ምንንስ አስባለሁ?» በል፣ ራስህን ጠይቅ! ለንባብ ምክንያት አታብዛ፣ የማንንም ፖስት አትልቀም። በቀልዳቀልድ አትጠመድ፣ የሚጠቅም የእግዚአብሔርን ቃል አንብ! ምክንያት ለትምህርትና ለንባብ ብቻ ሳይሆን ለምንም አይሠራም፤ ግን ለትምህርትና ለንባብ የዘመኑ ወጣት ምክንያቱ ብዛቱን ሳየው ይገርመኛል። አባ ዮሐንስ የሚባሉ ያረፉ ሊቀ ጳጳስ በአንድ ወቅት ለተልዕኮ ሲሄዱ አንድ ወጣት ቁጭ ብሎ አገኙት። ባረኩትና «ልጄ ሕይወት እንዴት ነው? ጤና?» አሉት። «እግዚአብሔር ይመስገን» አለ። አሁንም ጥያቄውን ቀጠሉና «ልጄ ትማራለህ?» አሉት። ልጁም «አልማርም» አላቸው። «ምን ሆነህ?» አሉት፤ «የምበላው የለኝም» አላቸው። እሳቸውም «እረ ልጄ! እና ስትደነቁር ምን እየበላህ ነው?» አሉት ይባላል። ወዳጆቼ! ለመልካምና ለንባብ ሲሆን ሁሉም ነገር የሚጨንቀን፣ ምክንያት የምንደረድር አሁንም አለን! ለማንበብ ጊዜ የለውም፤ ግን ከስልኩ ጋር ነው የሚውለው። ታዲያ በስልኩ ደግሞ ጠቃሚ ሳይሆን ሲጃጃልበት ቀኑ ይመሻል። ✍️ ወዳጆቼ፦ «🛑➠የሚያነብ ሰው አእምሮው ሰፊና የሰከነ ነው፤ ንባብ ለአእምሮ ምግብ፣ ለነፍስ ደግሞ እረፍትና ብርሃን ነው። የማያነብ ሰው ግን በአንድ ቦታ ላይ እንደቆመ ውሃ ይገማል።» «የመንፈሳዊ መጻሕፍት ንባብ ለአእምሮ ትልቅ ጥበቃ ነው፤ ንባብ አእምሮን ወደ ሰማይ ያነሳዋል፣ ሰውንም ከምድር ጭንቀትና ከከንቱ አሳብ ይለያዋል።» ከትንሽ እስከ ትልቅ ሁሉ በሚባል ሁኔታ ጭንቀት የነገሠብን ከንባብም ስለራቅን ጭምር ነው። እንዲያውም ቅዱስ አምብሮስ፡ «መጻሕፍትን አለማንበብ ለብዙ ክፉ ነገሮች መነሻና መንገድ ነው» ይላል። ምክንያቱም ካላነበብን የመፍትሔ ሰዎች አንሆንም፤ ለእያንዳንዱ ነገር መፍትሔ ካልሰጠነው ደግሞ ሲበዛ መፍትሔ የሌለው እየመሰለን እንጨነቃለን። በድንግዝግዝ ጨለማ የሚጓዝ ሰው ቁጥቋጦው ሽፍታና አውሬ እየመሰለው እንደሚጨነቀው፣ ያላነበበ ሰውም የማያስጨንቀው ቀላሉ ነገር መፍትሔ የሌለው እየመሰለው ሁልጊዜ በጭንቅ ይኖራል። ስለዚህ «ሁልጊዜ መጻሕፍትን በማንበብ ላይ ተጠመድ፤ እጅህ መጽሐፍን ከመያዝ አያቋርጥ። ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምትነጋገርበት መንገድ ከሆነ፣ ንባብ ደግሞ እግዚአብሔር ለእኛ የሚናገርበት መንገድ ነውና!» ስታነብም በቃላቱ ውስጥ የተሰወረውን ምስጢር ለማግኘት አእምሮህን ወደ ውስጥ ላከው፤ አእምሮህ በምርምር፣ ዓይንህ በቃላቱ ውበት ይመላለሱ። ✍️ «የመጽሐፍ ቃል እንደ ምንጭ ነው፤ በጠጣኸው ቁጥር ጥማትህን እያራሰ አዲስ እውቀትን ያፈልቅልሃል።» አንድ መጽሐፍ ገጹ ሲገለጥ የሚፈጠረው ድምፅ፣ የህትመቱ ሽታና የቃላቱ ሰልፍ ብቻ አይደለም ውበቱ፤ እውነተኛው ውበት ያለው በዚያ ጥቁርና ነጭ ጽሁፍ ውስጥ በተሰወረው፣ አእምሮን ከምድር ስቦ ወደ ማያውቁት ዓለም በሚወስደው የስልጣኔና የጥበብ መንፈስ ውስጥ ነው። ✍️ መጽሐፍ የሰው ልጅ ሕሊና የተቀረጸበት ምስጢራዊ መስተዋት ነው። የታላላቅ ሊቃውንት (ሐሳቦች)፣ የዘመናት እውቀትና የጥበበኞች ነፍስ ሳይደበዝዝ ለትውልድ የሚሻገርበት የማይጠፋ መብራት ነው።
видео или голосовое, без подписи
"ትምህርት የማያልቅ ምርት" የሕይወት መሠረቱ፦ 1.)ትምህርት፣ 2.)ማገሩ ንባብ፣ 3.)ውበቱ ተግባር፣ 4.)ግቡ ተስፋ ሐዋርያት ነው። ➻ለዚህ ደግሞ ጉባኤ ቤቶች ወደ ኅብረታዊና ሐዋርያዊ የልሕቀት አስተሳስብ መሸጋገሪያዎች ናቸው። ➻ጊዜውን ተረድተው ዘመኑን ዋጅተው ከሚያስተምሩ ጉባኤ ቤቶች አንዱ ፈለገ ጥበብ ጉባኤ ቤት ነው። ➻መማር የምትፈልጉ ደቀ መዛሙርት ሁሉ በዚህ ሦስት ቀናት ውስጥ ተመዝግባችሁ መመዘኛውችን አልፋችሁ መግባት ትችላላችሁ። ➻ፈለገ ጥበብ ጉባኤ ቤት ደብረ ማርቆስ ከተማ ቦሌ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን።
ትምህርት የምትፈልጉ ደቀ መዛሙርት። እስከ ሥስት ቀን ባለው ተወዳድራችሁ መግባት እንደምትችሉ ጉባኤ ቤቱ ጥሪ እያደረገ ነው። (ፈለገ ጥበብ ጉባኤ ቤት ደብረ ማርቆስ)
видео или голосовое, без подписи
ዋና መጻሕፍቶች እነዚህ ናቸው። ከመጻሕፍተ ብሉያት፦ 1.)ዘፍጥረት ዘጸአት ትርጓሜ 2.)ኩፋሌ ትርጎሜ 3.)ዘሌዋውያን፣ዘኁል፣ዘዳ ትርጓሜ 4.)ኢያሱ፣ሩት፣መሳፍንት ትርጓሜ 5.)ብሔረ ነገሥት ትርጓሜ 6.)ኢዮብ ትርጓሜ 7.)ጦቢት፣ዮዲት፣አስተር ትርጓሜ 8.)ዳዊት ትርጓሜ 9.)ዕዝራ ሱቱኤል ትርጓሜ 10.)ሰሎሞን ሲራክ ትርጓሜ 11.)ሄኖክ ትርጓሜ 12.)ኢሳይያስ ትርጓሜ 13.)ኤርምያስ ትርጓሜ 14.)ሕዝቅኤል ትርጓሜ 15.)ዳንኤል ትርጓሜ 16.)ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን የብሉይ ኪዳይ ማብራሪያዎች፦ የሐዲሳት 1.)አርባዕቱ ወንጌላት ትርጓሜ 2.)ጳውሎስ ትርጓሜ 3.)ሠለስቱ ሐዲሳት ትርጓሜ። 4.)ዲድስቅልያ 5.)ቀሌምንጦስ 6.)ሲኖዶስ የሐዲስ ኪዳን ማብራሪያዎች ከሊቃውንት 1.)ፍትሐ ነገሥት 2.)ሃይማኖተ አበው 3.)ቄርሎስ 4.)ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሣን ወተግሣጽ 5.)አስራ አራቱ ቅዳሴ የትምህርተ አበው ማብራሪያዎች ከመነኮሳት 1.)ማር ይስሓቅ 2.)ፊልክስዩስ 3.)አረጋዊ መንፈሳዊ 4.)ዜና አበው የሕይወተ ቅዱሳን ማብራሪያዎች ያስፈልጋሉ። ከእነዚህ ቀጥሎ ማብራሪያዎች በስፋት ያስፈልጋሉ። እንዲሁም የታሪክ፣ የባህል፣የሥነ ልቡና፣የኪነ ጥበብ፣የክህሎት፣.. መጻሕፍቶችም አስፈላጊዎች ናቸው። አርዕስተ አበው ጉባኤ ቤት
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ሕያው አገልጋይ ፧፧፧፧፦ስለ ተአማኙ እግዚአብሔር በተጠራጣሪ አንደበት አይመሠክርም። ፧፧፦ ስለ ኃያሉ እግዚአብሔር ሲናገር በፈሪ አንደበት አይገልጠውም እየፈራ ወንጌልን አይሰብክም። የዋሕና ትጉህ ስለሆነው አምላክ በትቢተኛ አንደበትና በትቢት አነጋግር አይናገርም ፍቅር የሆነው እግዚአብሔርን በጥላቻና በስድብ አያገለግለውም ፠ አምላኩ እንዲመሠገን እንጅ እራሱን ሊወደስበት ከአውደ ምህረቱ አይቆምም ፠ ሌሎች የሚድኑበትን እርሱ የሚጠፋበትን አገልግሎትአያገለግልም ማለት እያገለገለ አይጠፋም የጌታውን ማዕድ አይነፍግም እኔ ብቻ ላስተምር እኔ ልናገር እኔ ብቻ ልኑር አይልም ከወንድሞቹ ጋር ይተባበራል ሌላውን እንደ ኃጥእ ራሱን እንደ ጻድቅ አይቆጥርም ። እግዚአብሔር መቸ ነው በእኔና በሥራየ ውስጥ ተገልጦ የሚታየው? ብሎ ዘወትር ይጨነቃል የቤተ ክርስቲያንን ችግር ይሸከማል እንጅ ራሱ ችግር አይሆንም። ዛሬን በመከራ ነገን በተስፋ ይኖራል በመንፈሳዊነት ሽፋን ሥጋዊና ዓለማዊ ፍላጎቱን አይዘራም።
ንጽሐ ሰብእና ኃጢያትን ከሥራ ማራቅ የመንገሥተ ሰማያት ቁልፍ ነው።የጥፋተኝነት ስሜትም ወደ ፊት እንድንሔድ ማድረግ ካልቻ በራሱ ሌላ ውድቀትን ሊያመጣ ይችላል። ፧፧፧፦ ከስህተት መማር አዳማዊነት ነው አለመማርም ሠይጣናዊነት ነው። ብዙዎች ይስታሉ ትንሾቹ ከስተታቸው ይማራሉ ። ከስተታቸው የሚማሩት ። ጠቢባን ሲሆኑ ከስተታቸው ተምረው የማይለወጡ አብዳን ዝንጉዐን ይባላሉ። ስለ ዚህም ብዙ ሰዎች ይሰሳታሉ ትንሽ ሰዎች ከስተታቸው ይማራሉ ፧፧፧፦ ሕይወት ትርጉም እንዲኖረው ከእግዚአበሔር ጋር ማየያዝ የሰው ልጅ ክብር ፈላጊ ነው ክብር ደግሞ የሚፈልገው ክብር ከጎደላቸውና ክብር ከሌላቸው ነው። ክብር ከሌላቸው ነገረች ክብርን አለመፈለግ ።ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር ካልተየያዘች ትርጉም አልባ ናት ሕይወት ትርጉም የሚኖረው በእግዚአብሔርና በቃሉ ሲመሠረት ነው። ሁሉም ፍጡራን በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን ውሳጣዊ ሕይወታቻን ማርካት አይችሉም ነፍሳችንና ልባችን የሚያረካው ፈጣሪ ነውና። ፧፧፧፦ ስናገኛቸው በሚጠፉ ነገሮች አለጨነቅ ። የማይጠፋውን መውረስ ነው የሚያስጨንቁን ነገሮች ስናገኛቸው የሚጠፉ ነገሮች ናቸው ስለ ዚህዓለም የምናስበው ነገር ሁሉ ከንቱ ነው ከእግዚአብሔር ውጭ ያለ ሕይወት ከንቱ ነው ፧፧፧፧፦ ስነ ፍጥረትን ከተፈጠረለት ዓላማ አንጻር መጠቀም። እግዚአብሔር የፈጠረውን ዓለም ለምን ከንቱ ይለዋል?ሥነ ፍጥረትን ያላግባብና ያለቦታቸው ስለተጠቀመባቸው ከንቱ ተባለ።ስነ ፍጥረት ከንቱ የሚሆነው ያለአግባብ ስንጠቀምበትና ስንረዳው ነውና ። ፧፧፧፧ ከንቱ ሕሊናን ማራቅ ከንቱ ሕሊና መንድን ነው? ከንቱ ሕሊና ማለት በከንቱ ነገረች ላይ ትኩረት ያደረገ ሕልውና ማለት ነው እግዚአብሔር ዓለምን ስለኛ ፈጠረው እንጅ እኛን ስለዓለም አልፈጠረንም ማለት ዓለም የእኛ ባሪያ ሊሆን እንጅ እኛ የዓለም ባሪያ ልንሆን አልተፈጠርንም ማለት ነው ።ከንቱ ሕሊና ማለት የክፉ አሳብ ባርያ ማለት ነውና። መጻሕፍትም የሚነግሩን ተስፋ እንድንቆርጥ ሳይሆን ተስፋ ወደ ሚያስቆርጥ ከንቱ ነገር እንዳንሔድ ነው። በጎ ሕሊናን ማሳደግ ማጽናት በከንቱ ነገሮች ላይ ትኩረት አንዳያደርግ ሕሊናን መጠበቅ ሰው ሕይወትን በምድራዊ ዕሴቶች ዐይንየሚመለከታት ከሆነ የድካሙ ሁሉ ትርፍና ውጤት ምንድን ነው ከንቱ ነገር ፍሬ የለውም ፍሬ የሌለው ነገርም ኃይል የለውም ሰው የዓለሙን ከንቱነት ለመረዳት ከዓለሙ መነጠል አለበት ቅዱስ አብሮስ ።። መዳን የሚፈልግ ሰው ሁሉ ከዓለም በላይ ከፍ ይበል። አሁን የምፈልገው ከእግዚአብሔር የሚያስታርቀኝ እንጅ የሚያጣላኝ የሚያቀርበኝ እንጅ የሚያርቀኝ አልፈልግም ብዙ ጥፋት አጥፍተናል እግዚአብሔር ግን ይወደናል ይፈልገናል። ሠናይ አስረሴ
видео или голосовое, без подписи
ትድረስ ለቲሊሊ ምእመናን፦ 1.)ሰበካ ጉባኤዎች፣ለቲሊሊ ከተማ ማኅበረ ካህናት፣ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ማኅበራት። 2.)ለቲሊሊ ከተማ ኦርቶዶክሳውያን ኑዋሪዎች፤ 3.)በተለያየ ቦታ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ለምትኖሩ የቲሊሊ ተወላጆች ኦርቶዶክሳውያን፤ ➻በቅዱስ ሚካኤል ደብር የተከፈተውን የብሉያትና የሐዲሳት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት ታውቁታላችሁ? ➻ይሄንን ጉባኤ ቤት በበቂ ሁኔታ አስተባብራችሁ የኦርቶዶክሳዊ ልሕቀት፣የስብከተ ወንጌል፣የሊቃውንት ማዕከል ለማድረግ ምን አስባችኋል? ➻ይሄ ጉባኤ ቤቱ ከሁሉም በፊት የእናንተን የአንድነት ተግባር ይፈልጋል። ➻ካሰባችሁበት በእርግጠኝነት በአንድ ሳምንት ውስጥ ከፍ አድርጋችሁ ከቀደምት ጉባኤ ቤቶች ከፍታ ልክ እንደምታደርሱት አምናለሁ። ➻ጉባኤ ቤትን መሥራት የዛሬውን እየጠበቁ የነገውን ትውልድ መሥራት ነው።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи