tgindex
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Статистика

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Последний пост
17:34
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
20
Всего постов
48
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
55 198
+30 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
6 609
40 постов
Вовлечённость
12,0%
к подписчикам
Постов в день
2,9
всего 48
Упоминаний
35
каналов
Охват размещения
по 4 постам
1/24сутки в ленте
4 882
1/48двое суток
5 594
1/72трое суток
6 033

Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.

Посты

  • 17:345271

    видео или голосовое, без подписи

  • 14:381 77612

    видео или голосовое, без подписи

  • 15 авг.2 50817

    видео или голосовое, без подписи

  • 15 авг.2 84411927

    видео или голосовое, без подписи

  • 15 авг.4 10017671

    አንድ ሰው ቢበድላችሁና ብትቆጡ፣ ቁጣችሁ በልባችሁ አድሮ ወደ ጥላቻ እንዳያድግ ተጠንቀቁ። ቁጣ በዓይንህ ውስጥ እንዳለ ትንሽ ጉድፍ ነው፤ ጥላቻ ግን እንደ ትልቅ ምሰሶ ነው። አንተ የራስህን ምሰሶ ተሸክመህ፣ በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለማውጣት አትድከም። ጥላቻ የቆየና ሥር የሰደደ ቁጣ ነው። ቁጣህን ዛሬውኑ ካላስወገድከው፣ ነገ ወደ ጥላቻ ይለወጣል። ጥላቻ ደግሞ ነፍስን ይገድላል። ጠላትህ ይቅርታ እንዲያደርግልህ ባይጠይቅህ እንኳ አንተ በልብህ ይቅር በለው። እርሱ ይቅርታ ባለመጠየቁ የራሱን ዕዳ(በደል) ያበዛል፤ አንተ ግን ይቅር በማለትህ የራስህን ዕዳ ታቀልላለህ። አንተ ይቅር ስትል ራስህን ከታሰርክበት ሰንሰለት እየፈታህ ነው፤ ቂም መያዝ ግን ጠላትህን ሳይሆን አንተን በጨለማ ቤት ውስጥ አስሮ የሚያኖር እስር ቤት ነውና። (ሊቁ አውግስጢኖስ "አባታችን ሆይ"ን ባስተማረበት ስብከቱ)

  • 14 авг.4 494291

    ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን! ​በስሜን ወሎ ሀገረ ስብከት፣ በሐብሩ መርሳ ወረዳ ቤተ ክህነት የሚገኘው የስሪንቃ አንድ አይመትር አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ወጣቶች ቤተክርስቲያኗን በወጪ ራሷን እንድትችል ለማድረግ አበራች የሆኑ የልማት ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛሉ። ​ እስካሁን በወጣቶቹ የተቀናጁ አበይት ተግባራት ​የመብራት ዝርጋታ፡ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ለቤተክርስቲያኑ…

  • 14 авг.5 4904

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.5 5424

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.5 359654

    ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን! ​በስሜን ወሎ ሀገረ ስብከት፣ በሐብሩ መርሳ ወረዳ ቤተ ክህነት የሚገኘው የስሪንቃ አንድ አይመትር አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ወጣቶች ቤተክርስቲያኗን በወጪ ራሷን እንድትችል ለማድረግ አበራች የሆኑ የልማት ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛሉ። ​ እስካሁን በወጣቶቹ የተቀናጁ አበይት ተግባራት ​የመብራት ዝርጋታ፡ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ለቤተክርስቲያኑ የመብራት መስመር አስገብተዋል። ​የወፍጮ ግዢ፡ በጋራ ተሰባስበው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ በማዋጣት ወፍጮ ገዝተዋል። ​አሁን ላይ የተገዛውን ወፍጮ ተክሎ ለአገልግሎት ለማብቃት የወፍጮ ቤት መሥሪያ ከ60 በላይ ቆርቆሮ ያስፈልጋል። ​ስለሆነም የቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቻናል ቤተሰቦችና ደግ አሳቢ ምዕመናን ሁላችሁም እንደ አቅማችሁ መጠን በመደገፍ የዚህ በጎና ታሪካዊ ሥራ ተካፋይ እንድትሆኑ በክርስቶስ ፍቅር ጥሪያችንን እናቀርባለን። (የአንድ ቆርቆሮ ዋጋ 1200 ብር ነው) ለበለጠ መረጃ እና ድጋፍ ለማድረግ በውስጥ መስመር @natansolo ማናገር ይችላል። ​"እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና።" (2ኛ ቆሮንቶስ 9፥7)

  • 14 авг.5 349394

    💥ተወዳጁ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዳሴ በአንድምታ ትርጓሜ ክፍል አንድ! በአርማስ ሚዲያ 👉 https://youtu.be/a51gZcf3ngo?si=uYydhsHpfTD8c3n1

  • 13 авг.5 806352

    💥ተወዳጁ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዕለተ ሐሙስ ውዳሴ በአንድምታ ትርጓሜ ሙሉ ክፍል! በአርማስ ሚዲያ 👉https://youtu.be/LcW2XaWa_T0?si=ifv2YippxOyD-k7h

  • 13 авг.6 58731349

    የምሕረት አዋጅ ሊታወጅ 15 ዓመታት ሲቀሩት፣ በአምላክ ቅዱስ ፈቃድ መካኒቱ ሀና በብሥራተ መልአክ በ5485 ዓ.ዓ ነሐሴ 7 ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጸነሰች። ያች ድንግል የተጸነሰችባት ሰዓትና ዕለት ምንኛ የተባረከችና የተቀደሰች ናት! ​የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከትና አማላጅነት አይለየን፤ አሜን!"

  • 13 авг.6 75116633

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.7 255147104

    ነሐሴ 7 ጽንሰታ ለእግዝትነ ማርያም በዚህች ዕለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተጸነሰች። የእመቤታችን ወላጆችዋ ኢያቄምና ሃና ይባላሉ። እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑዋሉ፡፡ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ፡- ኢያቄም:- "አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ፤ ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች። እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ ሃናም አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ (ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ። ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው። ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፤ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም "7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ" አየሁ አላት፤ ሃናም እኔም አየሁ አለችው ምን አየሽ ቢላት "ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ" አለች። ይህንን ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው፡፡ እነሱም እንዲህ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሃሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች፡፡ ምልጃዋ በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን፡፡

  • 13 авг.5 503243

    ተወዳጁ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የረቡዕ ውዳሴ በአንድምታ ትርጓሜ! https://youtu.be/t15GRwkF-hM?si=bvV2yOQ-sXQFau-2

  • 12 авг.7 29614051

    ካህን የቱንም ያህል የራሱን ሕይወት በሥርዓት የሚመራ ቢኾንም እንኳን፥ ለአንተ (ድኅነት) የማይጨነቅ ከኾነ፣ አዎ፥ ለአንተ ብቻ ሳይኾን በእርሱ ዙሪያ ላሉት ሰዎች ኹሉ የማይጠነቀቅ ከኾነ፥ ዕጣ ፈንታው ጽዋ ተርታው ከክፉዎች ጋር በእሳተ ገሃነም ነው፡፡ እርሱ ራሱ በሠራው ኃጢአት ተጠያቂ ባይኾንም እንኳን ማድረግ የሚገባውን ባያደርግ በአንተ መጥፋት ምክንያት እርሱም ይጠፋል፡፡ ስለዚህ ይህ ታላቅ ጉዳት ሊያገኘው እንደሚችል ዐውቀህ ተረድተህ፥ ለካህናት ከፍ ያለ በጎ ፈቃድህን ስጣቸው (ታዘዛቸው)፡፡ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ፡- “ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ” ብቻ ሳይኾን “ስለ እናንተ በእግዚአብሔር ፊት ምላሽ የሚሰጡ እንደ መኾናቸው” ያለው ይህን ሲያመለክት ነውና (ዕብ.13፡17)፡፡ ስለዚህ ካህናት ከእናንተ ከምእመናን ከፍ ያለ ክብርን [እንደዚሁም ማግኘት ያለባቸውን ኹሉ] ሊቀበሉ ይገባቸዋል፡፡ እነርሱን በመናቅ በማዋረድ ከሌሎች ጋር የምትተባበሩ ከኾነ ግን፥ የእናንተ የገዛ ራሳችሁ ድኅነትም ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ አንድ የመርከብ አለቃ በበጎ ሕሊና ውስጥ ሲኾን፥ የተጓዡ ደኅንነተም እንደዚሁ የተጠበቀ ይኾናል፡፡ በተጓዦቹ ንቀትና መዋረድ የተሰላቸ ከኾነ ግን በአግባቡ ሊጠነቀቅላቸው አይችልም፤ ወይም መርከቢቱን በአግባቡ መምራት አይቻለውም፡፡ ከዚህ የተነሣም ራሱን ጨምሮ ተጓዦቹን ኹሉ እልፍ መከራ ውስጥ ይከትታቸዋል፤ የመርከብ አደጋ እንዲገጥማቸው ያደርጋል፡፡ ልክ እንደዚሁ ካህኑም ከእናንተ ክብርን የሚቀበል ከኾነ፥ የራሱን ብቻ ሳይኾን የእናንተንም ጉዳዮች በአግባቡ መምራት ይቻለዋል፡፡ ካህናቱን ተስፋ ወደ መቁረጥ ስሜት ወደ ኀዘን የምታስገቡዋቸው ከኾናችሁ ግን እጆቻቸው እንዲዝሉ ታደርጓቸዋላችሁ፡፡ ይህን የምታደርጉ ከኾነም የቱንም ያህል ቢተጉ እንኳን እነርሱን ብቻ ሳይኾን ራሳችሁንም እጅግ ከፍ ወዳለ መዋግድ (ወደ ብዙ ማዕበል) ታስገባላችሁ፡፡ በልብ መታሰቡ በሕሊናም መዘከሩ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን ክርስቶስ አይሁድን በተመለከተ ምን እንዳለ አድምጡ፡- “ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል፡፡ ስለዚህ ያዘዙአችሁን ኹሉ አድርጉ ጠብቁትም” (ማቴ.23፡2-3)። አሁን “ካህናተ ሐዲስ በሙሴ ወንበር ተጠቀምጠዋል” ልንል አይገባንም፤ “በክርስቶስ ወንበር” ተቀምጠዋል ልንል ይገባናል እንጂ፡፡ እንደሚገባ ትምህርቱን ተቀብለዋልና፡፡ እንዲህም በመኾኑ ቅዱስ ጳውሎስ ጨምሮ፡-“እግዚአብሔር በእኛ [እናንተን] እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን” ብሏል (2ኛ ቆሮ.5፡20)፡፡ [ስለዚህ ስለ ነፍሳችሁ የሚተጉትን፣ ስለ እናንተ በእግዚአብሔር ፊት ምላሽ የሚሰጡትን ካህናተ ሐዲስን እጅግ ልታከብሯቸው፣ ልትታዘዟቸውም ይገባል፡፡] ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (የዮሐንስ ወንጌልን ሲተረጉም ከድርሳን 86 የተወሰደ )

  • 11 авг.8 593300110

    የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ቤት እግሩን ማራቅ ሲጀምር፣ ፍቅርም ከእርሱ ፈቀቅ ትላለች፤ ያን ጊዜ ከሚያየውና ከሚዳስሰው ሁሉ ጋር መጋጨት ይጀምራል። ግጭቱም ከሰዎች ጋር ብቻ አይደለም ከተፈጥሮ፣ ከአካባቢው፣ ከማኅበረሰቡና ከራሱ የሕሊና ሙግት ጋር እንጂ። ​ፍቅር በሌለበት ምድር ባዶነት ትነግሣለች፤ ፍቅር በሌለበት ልብ የውስጥ ሰላም አይገኝም። ፍቅር ከራቀ ደግሞ ሁሉ ነገር ድቅድቅ ጨለማ ይለብሳል። ​ስለሆነም የሰው ልጅ ሆይ! ሙሉ ፍቅርን ታገኝ ዘንድ ሁልጊዜም እግሮችህ ወደ አምላክህ ቤት ይፋጠኑ። ያኔ ለሕሊናህ ፍጹም ሰላምና ፍቅር ታገኛለህ፤ ያን ጊዜ ባዶነትህ ይሞላል፣ ጨለማህም በብርሃን ይተካል።

  • 11 авг.9 499302100

    ድክመቶቼን ማወቄ ምንድነው የሚጠቅመኝ? ካልን አንድ ሰው ድክመቶቹን ካወቀ እግዚአብሔርን ያውቃል። ''ስደክም ያንጊዜ ኃይለኛ ነኝና'' 2ቆሮ 12፡10። ኃጢአቴ ምን ያህል አስነዋሪ እንደሆነ ሳረጋግጥ የእግዚአብሔርን ፀጋ እሻለሁ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ብሏል ''ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ እና ከእኔ ተለይ'' ሉቃ 5፡8። ቅዱስ ጴጥሮስ ምን አይነት ችግር ውስጥ እንዳለ ተሰምቶታል። ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አለው ''አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ'' ሉቃ 5፡10 ቅዱስ ጴጥሮስ ለታላቅ ተልእኮ እና አገልግሎት የበቃው መቼ ነበር? ይህ የሆነው ራሱን ባወቀ ቅጽበትና "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ" ብሎ በተናገረ ጊዜ ነበር። የሰው ልጅ በእንዲህ ዓይነት ስሜት ውስጥ በሆነ ጊዜ እግዜአብሔር እንዲህ ይላል። "አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ"። ስለዚህ ራሳችንን ማወቅ ማለት እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት ነው። 'ከአቡነ ሺኖዳ የሕይወት መዓዛ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ'

  • 10 авг.9 20730363

    የሰውን ልጅ ትህትናው መሰላል ሆኖ ወደ ሰማይ ያወጣዋል። (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

  • 10 авг.10,1 тыс18262

    "....ሀብታምን ዕድለኛ ድሀን ደግሞ ዕድለ ቢስ ብለን መጥራት እንደሌለብን ከአልዓዛር እንማር፡፡እዉነቱን ለመናገር ግን ባለጸጋዉ ጥቂት ንብረቶችን የሚፈልገው እንጂ ብዙ ንብረቶችን የሰበሰበው አይደለም፡፡ ድሀ የሚባለው ደግሞ ምንም ንብረት ሳይኖረዉ ብዙ ፍላጎቶች ያለዉ ነዉ፡፡ የሀብትና የድህነት መገለጫዉም ይህ እንደሆነ ልናዉቅ ይገባናል፡፡ ለብዙ ነገሮች የሚስገበገብና የሁሉንም ሀብት በእጁ ያስገባዉን ሰዉ ብትመለከቱ እንዲህ ዓይነቱ ሰዉ የመጨረሻው ደሀ ሰዉ መሆኑን እወቁ፡፡ በአንጻሩ ምንም ባያገኝ እንኳ ጥቂት ፍላጎቶች ያሉትን ሰዉ ብትመለከቱ እንዲህ ያለዉን ሰዉ የባለጸጎች ሁሉ ባለጸጋ አድርጋችሁ ቁጠሩት፡፡ ድህነትንና ሀብታምነትን በአንድ ሰዉ ዉጫዊ መገለጫ መጠን ሳይሆን እንደ አዕምሯችን ሚዛናዊነት ማስቀመጥ ልማዳችን አድርገነዋል፡፡ በቅምጥልነት ቢደሰትና በወንዞችና በምንጮች አጠገብ ቢኖር እንኳ ሁልጊዜ የሚጠማን ሰዉ ጤነኛ ነዉ ብለን አንጠራዉም፡፡ በባለጸጎችም ዘንድ ያለዉ ልክ እንደዚህ ነዉ፡፡ የሌሎች ሰዎችን ንብረት ለማግኘት ሁልጊዜ የሚጓጉና የሚጠሙ ሰዎችን ጤነኞች ብለን አንጠራቸዉ፡፡ እንደዚህ ያሉ ሰዎች የተትረፈረፈ ነገር ቢያገኙ እንኳ ይረካሉ ብለን አንዳናስብ፡፡ አንድ ሰዉ የሰዎችን ሁሉ ንብረት ለራሱ አድርጎ እየወሰደ የራሱን ስስት መቆጣጠር ካልቻለ እንዴት ባለጸጋ ሊሆን ይችላል? ነገር ግን ዓይኖቻቸዉን ከሌሎች ንብረት ላይ ሳይጥሉ ባላቸዉ ረክተዉና የራሳቸው በሆነ ንብረት ደስ ተሰኝተዉ የሚኖሩት እነዚህ ሰዎች የድሆች ሁሉ ድሀ ቢሆኑም እንኳ የባለጸጋዎች ሁሉ ባለጸጎች ናቸዉ፡፡ በሌሎች ንብረት ላይ ምንም ዓይነት ፍላጎት የሌለውና ራሱን በመቻሉ ደስተኛ የሆነዉም ሰዉ የባለጸጎች ሁሉ ባለጸጋ ነዉ፡፡" (ሀብታምና ድሀ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገፅ 27-28 ➛ በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ) ልዩ ማስታወሻ፦ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሉቃስ 16፥19 ያለውን የባለጸጋዉ ነዌን እና የደሃዉ አልዓዛርን ታሪክ መነሻ አድርጎ የተሰጠ ድንቅ ስብከትን የያዘ በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ ግሩም መጽሐፍ ነዉ፡፡ ገዝተው ቢያነቡት እመክራለሁ። መጽሐፉን አዲስ አበባ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ ባኮስ መጻሕፍት መደብር ያገኙታል