እውነትም ሰሚነሽ ኪዳነ ምሕረት
Статистикаየሰሚነሽ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ትክክለኛ ገጽ ዘወትር እሁድ ከአዲስ አበባ የደርሶ መልስ ጉዞ እናዘጋጃለን ✟ ጉዞ ለመመዝገብ 0921137805 0912162878 ጉዞ ለመመዝገብና ፀሎት ለማስያዝ በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ
- Последний пост
- 19 июн.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
"ኦ ሚካኤል ኦ መተንብል፣ ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል፣ ዘእምርዑሳን ርዑስ ወዘእምልዑላን ልዑል፣ ጊዜ ጸዋዕኩከ ቅረበኒ በምሕረት ወሣህል፡፡" "አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ እኮን። የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ እኮን። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ።" (መልክአ ሚካኤል)
ሰኔ 12 በዚህች ቀን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ከሰይጣን እጅ ያዳነበት ቀን ነው። ዳግመኛም በዚህ ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን የሞቱን ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት ዕለት ነው። ይህ ዕለት ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ላልይበላ ያረፈበትም ቀን ነው። አፎምያን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ የታደጋት ቅዱስ ሚካኤል እኛንም በጥበቃው አይለየን አሜን
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር። የሐዋርያት ሥራ 2:1-4
“ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ” በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 4 የምናገኛት ሳምራይቱ ሴት ውኃ ልትቀዳ ወደ ያዕቆብ ጕድጓድ እንደመጣች እንመለከታለን፡፡ ነገር ግን የክብር ንጉሥ፣ የዓለሙ መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ልቧ ሰተት ብሎ ሲገባ “ማድጋዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደች”፡፡ መጽሐፍ “ሊከተለኝ የሚወድ እርሱ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ” ይላል፡፡ በእውነቱ ሐዋርያት መረባቸውን፣ መንጠቆዋቸውን ትተው የምሥራችን ለዓለም ለመንገር እንደወጡ ይህቺ ሴትም ማድጋዋን ትታ በሐሴት ሠረገላ ተጭና ወንጌሉን ለመንገር ስትሯሯጥ እናያታለን፡፡ “ለሰዎችም ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?” እያለች መላ ከተማውን ጠራርጋ ታመጣቸው ነበር። የሚገርመው ሴቲቱ የምታመጣቸው ሰዎች እንደ እንድርያስ ወይም ደግሞ እንደ ፊሊጶስ አንድ ወይም ሁለት ሰዎች ብቻ አይደሉም፡፡ መላ ከተማውን እንጂ፡፡ ትጋቷም ከኒቆዲሞስ በላይ ነው፡፡ ኒቆዲሞስ በወልደ እግዚአብሔር ቢያምንም እንደ እርሷ ግን በግልጥ ለመመስከር አልወጣም፡፡ ሐሳብዋን ብቻ ይግለጥላት እንጂ እንዴት እንደምትነግራቸው የቃላት ምርጫ አታደርግም፡፡ እናም “ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?” ትላቸዋለች፡፡ ተጠራጥራ አይደለም፤ መጥተው ራሳቸው ለራሳቸው እንዲወስኑ እንጂ፡፡ ስለዚህም “ኑና እዩ፤ አይታችሁም እመኑ” እያለች ከነፍሳቸው እረኛ ጋር እንዲገናኙ ትፈልጋቸው ነበር፡፡ ሰዎቹም የምትነግራቸውን ነገር ለማየት “ከከተማ ወጥተው ወደ ጌታችን ይመጡ ነበር”። ይህች ሴት በጠዋት አዋልደ ሰማርያን ላለማየት ብላ በጠራራ ፀሐይ ውኃን ለመቅዳት የመረጠች ሴት ነበረች፡፡ አሁን ግን እውነተኛው ፀሐይ ሲነካት ሐፍረቷ እንደ በረዶ ተኖ ጠፋ፡፡ ስለዚህም ቀድሞ ወደምታፍራቸው ሰዎች በመሄድ “አንድ ነብይን ትመለከቱ ዘንድ” ሳይሆን “ያደረግሁትን ሁሉ፣ ምሥጢሬን ሁሉ የነገረኝን ሰው ትመለከቱ ዘንድ ኑ” እያለች ሕዝቡን ጠራቻቸው፡፡ እነርሱም መጡ፡፡ ትጋቷ እንዴት ድንቅ ነው? ቅናቷ እንዴት ግሩም ነው? ዛሬ የዚህችን ሴት ዜና መዋዕል ከመናገር በላይ እኛ ምን እንማራለን? ምን ያህል ቀናተኞች እንሆን? የራሳችንን ጨምሮ ምን ያህል ነፍሳት በእጃችን እንዳሉ እናውቅ ይሆን? ወንድሞቼ “ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን፤ ያደረግሁትን ሁሉ የፋቀልኝን፤ በነጻ ሥርየተ ኃጢአት የሰጠኝን፤ በነጻ ልጅነት የሰጠኝን፤ በነጻ የራሱን ሥጋና ደም የሰጠኝን… ትመለከቱ ዘንድ ኑ” ብለን የምንመሰክር ስንቶች እንሆን? መክሊታችንን የቀበርን ስንቶች እንሆን? … መጽሐፍ “ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ?” ይላል… ወንድም እኅቶቼ! የምናውቃትን ያህል ከመመስከር ወደኋላ አንበል፡፡ የታመመን ሰው ሕክምና መውሰድ ያለብንን ያህል እንዲሁ ራሳችንን ጨምሮ ብዙዎችን ከመድኃኒተ ነፍሳቸው ጋር ልናገናኛቸው ያስፈልጋል፡፡ ይህን እንድናደርግ እኛን በመውደድ ሰው የሆነው ክርስቶስ ይርዳን አሜን፡፡ /መቅረዝ ዘተዋህዶ /
ፕሬዝደንቱ " ዩኒቨርሲቲው የግእዝን ትምህርት በስልጠናም ሆነ በመደበኛ ትምህርት ለመስጠት ማጽደቁን ተናግረው ይህም በርካታ ታሪካዊ መዛግብትን ለመመርመር ጉልህ ሚና አለው" ብለዋል። በዚህ ላይ የጉባኤ ቤቱ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። የደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የ፬ቱ ትርጓሜ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት መምህር መምህረ መምህራን በጽሐ ዓለሙ በበኩላቸው " ጉባዔ ቤታችን ጥበብና ዕውቀትን ከአባቶቻችን ለልጆቻችን ለማስተላለፍ ራዕይ አንግቦ እየሰራ ይገኛል ፤ ዘመናዊውን ዕውቀት ከነባሩ ዕውቀት አስተሳስሮ ሀገርን እና ትውልድን በዕውቀትና በሥነ-ምግባር ለማነፅ ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጋር ስምምነት አድርገናል " ብለዋል። መምህረ መምህራን በጽሐ ዓለሙ " እኛም እየሰጠናችሁ እናንተም እየሰጣችሁን " በጋራ እንሠራለን በማለት ጉባኤ ቤቱና ዩኒቨርሲቲው ከ፪፳፲፪ ዓ/ም ጀምሮ በጋራ እየሠራ ያለ ቢሆንም የዛሬው የውል ስምምነት ግን በመደበኛነት ለመሥራት ከማስቻሉም በላይ ከዩኒቨርሲቲው ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል። የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአለቃ ገብረሃና የባህል ጥናትና ልማት ክፍል በማቋቋቋም ማኅበረሰባዊ አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ የተነገረ ሲሆን የዛሬው ስምምነት ዋነኛ ዓላማም የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ማከናወን መሆኑ ተሰምሮበታል። የዩኒቨርሲቲው የአለቃ ገብረሃና የባህል ጥናትና ልማት ዳይሬክተር የሆኑት መምህር መሠረት ወርቁ እነሰደተናገሩት የሁለቱ ተቋማት ስምምነት የግእዝ እና የአማርኛ ቋንቋ ድርሣናትን ወደ ሌሎች ቋንቋዎች በመተርጎም፤ በጥንታዊ የብራና ጽሑፎች ውስጥ የሚገኙ የሕክምና፣ የአስትሮኖሚ፣ የትምህርትና መሰል ጥበቦችን ማውጣትና ጥቅም ላይ ማዋል፤ በመዛግብትና ሙዚየም ማደራጀት፣ በቅርስ ጥበቃ፣ በቱሪዝም፣ በሥነ-ምግባር፣ በታሪክ፣ በግብረ-ገብ እና በሰላም ግንባታ ዙሪያ በጋራ መስራት፤ የንባብ ባህልን ማዳበር፣ በቤተ-መጻሕፍት እና በተለያዩ አቅም ማጠናከሪያ ስልጠናዎች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ዓለማ ያለው ነው ብለዋል ። በፊርማ ሥነስርዓቱ የዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የሥራ ዘርፍ ኃላፊዎችና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተዋል።
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ጉባኤ ቤቱና ዩኒቨርሲቲው በጋራ ለመሥራት ተስማሙ። ማኅበረ ቅዱሳን ግንቦት ፲፮ ፪፳፲፰ ዓ/ም የደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የ፬ቱ መጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመሥራት ግንቦት ፲፭ ፪፳፲፰ ዓ/ም ተፈራረሙ። ፊርማው በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሰሎሞን አበጋዝ እና በደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የ፬ቱ ጉባኤያት መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ጉባኤ ቤት መምህር መምህረ መምህራን በጽሐ ዓለሙ መካከል የተከናወነ ሲሆን ሁለቱ ተቋማት በጋራ የሚያሠራቸውን የሰነድ ርክክብም አድርገዋል። በሁለቱ ተቋማት በኩል የተፈረመው ሰነድ ሳይንስን ከሀገር በቀል እውቀት ጋር ለማስተሳሠር እና ሐገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመሰራት የሚያስችል ታሪካዊ ሰነድ (ስምምነት) ነው ተብሏል። ይህ ታሪካዊ ስምምነት ዩኒቨርሲቲው ሳይንሱን ጉባኤ ቤቱ ደግሞ ሀገር በቀል የሆነውን እውቀት በመስጠት ሳይንሱን ከሐገር በቀል እውቀት ጋር የማስተሳሠር ሥራዎችን በመሥራት ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ በር የከፈተ ትልቅ እድል መሆኑ ተነግሯል። በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ሰለሞን አበጋዝ " ዩኒቨርሲቲው ከሚሰጣቸው የማኅበረሰብ አገልግሎቶች መካከል ከጉባኤ ቤቱ ጋር ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርመናል " ብለዋል። " ዩኒቨርሲቲያችን ስምምነቱን በተግባር ለመተርጎም ሙሉ ቁርጠኛ ነው" ያሉት ዶ/ር ሰሎሞን... " ሀገር በቀል ዕውቀትን መሠረት ያደረጉ ስምምነቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት እየተሰጣቸው የመጡ ሲሆን እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የበለጸገ ባህል፣ ታሪክ እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዕውቀት ባላቸው ሀገራት ዘንድ ሕጋዊ ማዕቀፍ የሚፈጥሩ ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ናቸው" ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
ዝምታ አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ከቃላት ይልቅ ውጤታማ፣ ይበልጥ ተገቢና እጅግ ጠቃሚም ነው። ወይም ደግሞ ቢያንስ - ቢያንስ ተናግሮ ከሚመጣ ጉዳት ይልቅ ሳይናገሩ የሚመጣ ጉዳት ይሻላል። በዝምታ ውስጥ ጥበብና ጥንካሬ ከመኖራቸው በተጨማሪ ክብርና ሞገስም አሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ይናገር ዘንድ እኛ ዝም እንላለን፣እኛ ልንናገር ከምንወደው ከማንኛውም ነገር የበለጠ የእግዚአብሔር ቃል እጅግ ኃያል ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አስመልክቶ የተናገረው ቃል ምንኛ ድንቅ ነው! «እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፤እናንተም ዝም ትላላችሁ. . » ዘጸ 14፥14። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በዝምታ ቆይቷል። በዚያን ጊዜ እርሱ አፉን አልከፈተም ራሱንም አልተከላከለም። ጌታ ዝምታን በመረጠ ጊዜ ጲላጦስ «ይህን ጻድቅ ሰው የምወነጅልበት ምንም ዓይነት ምክንያት አላገኘሁም» በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ ዝምታ ትርፍ አስገኚ ይሁን እንጂ የተወሰነ መመሪያ አይደለም፡፡ ወርቃማው መመሪያ፡- ሰው ሊናገር የሚገባው በትክክለኛው ጊዜ መሆኑና ዝም ማለት የሚገባውም ዝም ማለት በሚገባው ትክክለኛ ጊዜ መሆኑ ነው። ሰው ዝም ሲል ልቡ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲነጋገር ስለሚፈቅድ በእርሱ ፈንታ ጌታው እንዲናገር ይጠይቃል ማለት ነው፡፡ (አቡነ ሽኖዳ ሣልሳዊ - የሕይወት ልምድ ገጽ 14 - በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ)
ሁለት ጓደኛሞች በጫካ ውስጥ ሲጓዙ አንድ ትልቅ ድብ መጣባቸው። አንደኛው ሮጦ ዛፍ ላይ ወጣ። ሁለተኛው ግን መሮጥ ስለማይችል መሬት ላይ እንደ ሞተ ሰው ተኝቶ ትንፋሹን ዋጠ። ድቡም መጥቶ ጆሮው ላይ አሸተተውና ሞቷል ብሎ ትቶት ሄደ። ዛፍ ላይ ያለው ወርዶ "ድቡ ጆሮህ ላይ ምን ብሎህ ነው የሄደው?" አለው። እርሱም "በችግር ጊዜ ጥሎህ የሚሄድን ሰው ጓደኛዬ ነው አትበል አለኝ" ብሎ መለሰለት። ፦ እውነተኛ ጓደኛ በደስታ ጊዜ የሚቆጠር ሳይሆን በችግር ጊዜ የሚገኝ ነው። ✞ @Mikre_haymanot ✞ ✞⌲ ˢʰᵃʳᵉ
"ኃጢአትን ብትሠራ እንኳ አትውደቅ፤ ከወደቅህም ተነሥ እንጂ አትደንግጥ። ዕለት ዕለት ብትበድል ዕለት ዕለት ንስሐ ግባ። እንደ ሰውነታችን ዕለት ዕለት እንበድላለን፡፡ በጥምቀት ያገኘነውን ልጅነት እናቆሽሸዋለን፡፡ አዲሱን ሰውነታችን ብሉይ (አሮጌ) እናደርገዋለን፡፡ ነገር ግን ይህን ዕለት ዕለት ማደስ ይቻላል፡፡ አንድ ቤት እያረጀ ቢሄድ እንደ አዲስ እንሠራዋለን፡፡ ክዳኑን፣ ቀለሙን፣ ምንጣፉን እድሳት እናደርግለታለን፡፡ እኛም በኃጢአት ባረጀው ሰውነታችን ላይ እንዲህ ልናደርግ ይገባናል በንስሐ፡፡ ቤት ሲያረጅ ፈርሶ እንደማይጣል ሁሉ፣ ሰውም በኃጢአት ስለወደቀና ስለቆሸሸ ተስፋ ቆርጦ ሊጠፋ አይገባውም። ባለቤቱ መጥቶ እንደሚያድሰው፣ እኛም በንስሐ ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ እርሱ በቸርነቱ ያድሰናል።" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ኤፌሶን 4 በተረጎመበት ድርሳኑ)
በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው። (ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ -የኤፍራጥስ ወንዝ ገጽ 87)