ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
Статистикаበዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 17:59
- Постов за неделю
- 48
- Всего постов
- 123
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2 680
- 1/48двое суток
- 3 071
- 1/72трое суток
- 3 312
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
✝እንኳን አደረሳችሁ ! ☞ወርኀ ነሐሴ ቡሩክ፤ ወአመ ፱፦ ✝ቅድስት ጾመ ፍልሠታ/ዕርገታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል፥ ወላዲተ አምላክ (ዘአበዊነ ሐዋርያት ንጹሐን) ✝ተዝካረ በዓሎሙ ለአበዊነ ቅዱሳን ወክቡራን፥ ፫፻ ፲ወ፰ቱ ጳጳሳት፥ ርቱዓነ ሃይማኖት (ተዝካረ ተጋብኦቶሙ፥ ዘ፲ወ፯፻) ✝ወተዝካረ በዓሎሙ ለቅዱሳን፦ ጻድቃን ዘብሔረ ብጹዓን፥ ወአባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ፥ አባ ዞሲማስ ቀሲስ፥ ወሳሙኤል ነቢይ፥ አባ በአሚን ተአማኒ፥ ወአባ በርሱማ አበ መነኮሳት፥ አባ እስትንፋሰ ክርስቶስ ዘደብረ አስጋጅ ❖ ወበዓለ ቅዱሳን አበው፦ ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ኃያል ወመስተጋድል ግብጻዊ፥ ማር አባ ኦሪ ሰማዕት፥ ወካህን ቡሩክ፥ ወብእሲ ትሩፍ፥ ዘሀገረ ስጥኑፍ፥ ዘአስተርአዮ እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ዘሎቱ ስብሐት ወአኮቴት (ወዘገነዞ ማር ዮልዮስ ሰማዕት) ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ወመነኮስ ሐዋርያዊ፥ ማር እስትንፋሰ ክርስቶስ ገዳማዊ፥ ዘደብረ አስጋጅ፥ መምህረ ሃይማኖት፥ ወሰባኬ ወንጌል፥ ብእሲ ትሩፍ፥ ኢትዮጵያዊ (እስመ በዛቲ ዕለት፥ መሠጥዎ መላእክት ውስተ ሰማይ) °ቅድስት ገዳሙ ደብረ አስጋጅ/አስቄ ቀርሜሎስ፥ ወቅዱሳን ውሉዱ መነኮሳት ጻድቃን ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ማር አባ ጲላጦስ ሊቀ ጳጳሳት ❖ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ። ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡ https://t.me/zikirekdusn
https://youtu.be/HciPK6RVxEs?si=4eR86QlcGRGwzEJd
"" የጾመ ፍልሠታ ትምህርት "" ፳፻፲፰/2018 (ክፍል ፯/7) 🌼በዓለ ጽንሰታ ለእመ ብርሃን ወላዲተ አምላክ - በትንቢተ ኢሳይያስ °መልክዐ ውዳሴ - ትርጉም (ነሐሴ 7 - 2018) 🌷ማርያም ድንግል እመ ረከብኩኪ: ሐዘነ ልብየ እነግረኪ: በገዳምኑ ወበዓት ኀበ ኀሠሥኩኪ: እግዝእትየ ማርያም እጼውእ ስመኪ: ቀዊምየ ኀበ ሀሎኩ አስተርእይኒ ገጸኪ ወኀበ ስእለትየ ካዕበ ጽልዊ እዝነኪ። 🌷አፉየ አስተንፈሰ ወልሳንየ አልሆሰሰ ለክብረ ፍልሰትኪ ድንግል እንዘ አቄርብ ተውዳሰ ማርያም ዘኮንኪ ቅድስተ ቅዱሳን መቅደሰ በቅድሜኪ እግዝእትየ እመ ረከብኩ ሞገሰ በየማንኪ ባርክኒ ሥልሰ።
✝እንኳን አደረሳችሁ✝ 💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠 /ማቴ ፫:፫/ 🔶ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!! ✨እናስተውል!!✨ 🔸1,ጥሩ ክርስትና ፈጥኖ የሚገኝ አይደለም፡፡ ትእግስትን ይጠይቃል፡፡ 🔸2,ሰይጣን እኛን ኃጢአት በማሠራት አይረካም፡፡ የሚፈልገው ተስፋ ማስቆረጥ ነው፡፡ 🔸3, በእምነት የሚደረግ የትኛውም ጸሎት መፍትሔ አለው፡፡ 🔸4,የበጎ ለውጥ እናት ዓላማና ቁርጥ ውሳኔ ናቸው ✝ 5 ነገሮችን በደንብ እንያዝ!!! 🔻1,ዓላማ 🔻2, እምነት 🔻3,ጥረት 🔻4,ጥንቃቄ 🔻5ጽናት ✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር 🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል) 🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር) 🔗https://t.me/zikirekdusn ▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan °🛑ወገኖቼ፦ ⛅️ ንስሓ እንግባ ! 🌥 ንስሓ እንግባ !! 🌧 ንስሓ እንግባ !!! 🛑የአድርሽኝ ገንዘብ ለማስገባት አካውንት የጠየቃችሁ ✅አዋሽ ባንክ ZIKIRE KIDUSAN MAHIBERE KIDUS DAWIT! ✅Account No 01320670435200
видео или голосовое, без подписи
The cup of blessing which we bless, is it not the communion of the blood of Christ? The bread which we break, is it not the communion of the body of Christ? For we being many are one bread, and one body: for we are all partakers of that one bread.”✞✞✞ 1Cor. 10:14-17 ✞✞✞ Salutation to God ✞✞✞ (Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe)
Feasts of Nehasse 9 ✞✞✞On this day we commemorate the Priest-Martyr Abba Ari (Ori)✞✞✞ ✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞ ✞✞✞ Saint Abba Ari (Ori) the Priest✞✞✞ =>This Holy Father was the fruit of the Era of Persecution. During that period (in the 3rd Century), being a Christian was counted as a crime that would get one killed. And it was more dangerous to be a shepherd, a priest, than to be just a layperson. ✞From the beginning, unlike today where we see requests of “Appoint me” having commonplace, ordination to the priesthood was given to a person elected by the people and the archbishop. The faithful chose not by bribes nor by kinship. Rather, they elected the one who being strong would strengthen them, and who would give himself for the sake of the flock. ✞And if an unfitting person is chosen, he might become a heretic and lead others to renounce or he would become an obstacle. The task of the priests of the Era of Persecution was not only to teach but they were also expected to give their necks to the sword before /in front of/ the faithful. ✞And one of the fathers who did this was Abba Ari (Ori) the Priest. The Saint was a kind man who was well versed in the Scriptures and who was loved in Shatanouf (a region in Egypt) where he was born and raised. ✞Abba Ari’s (Ori’s) inclination, starting from his youth, was asceticism. And the faithful, who were delighted by his purity, said to him, “Be ordained a priest. Then lead and teach us.” However, as the fathers do not want vainglory, he said, “No”. ✞Nonetheless, because it was the will of God, Abba Ari (Ori) was ordained a priest and started serving. He labored much in teaching, counseling and strengthening the weak. ✞And because of his holiness, when he entered to celebrate the liturgy, our Lord used to appear vividly before him. And hosts of angels used to surround and converse with him. ✞Many years went by as he diligently ministered the Holy Body and Blood to the faithful. Nevertheless, later on, the persecution, which the people used to hear as news, reached their doors. And at that time, many people became martyrs. Abba Ari (Ori), on the other hand, entered the Church, beseeched for himself and the people steadfastness and salvation, and then went out of the Church. ✞Afterwards, he directly went to the witnessing arena. Then he went before the governor, and boldly said, “Christ is God, Creator and Lord of all. But your idol is perishable, crumbling, gold, silver, wood and stone.” ✞And the governor angered by the Saint’s speech, placed him under much torture. The soldiers tried all kinds of torments that they found suitable on Abba Ari (Ori). And later, they threw him in a dark prison. There, he healed the sick and performed miracles. ✞And the gentiles, who heard the matter, gathered and came with many of the sick. Then, the Saint with his prayers healed all. And because of this, many of the heathens came to Christianity and believing in Christ they received honor. ✞The soldiers then took out the Saint from prison and afflicted him much, on this day, and they killed him. Thus, he received martyrdom. And upon the crown of righteousness, he added the crown of the priesthood and on top of that he put on the crown of martyrdom. ✞✞✞ May the God of the Saintly Fathers give us perseverance. And may He grant us from their grace and blessings. ✞✞✞ Annual feasts celebrated on the 9th of Nehasse 1. St. Abba Ari/Ori (Martyr) 2. Abba Pilate the Archbishop ✞✞✞ Monthly Feasts 1. Abba Barsauma the Syrian (Father to all Syrian Monks) 2. Abune Estenfase Kirstos (Ethiopian) 3. The “318” Holy Scholars (Fathers assembled at the Council of Nicaea) 4. Saints of the Realm of the Blessed 5. Abba Melchizedek of Mida (Ethiopian) 6. St. Zosimus (Zocima), Righteous (A father who saw the Realm of the Blessed)✞✞✞ “Wherefore, my dearly beloved, flee from idolatry. I speak as to wise men; judge ye what I say.
††† እንኳን ለካህኑ ሰማዕት አባ ኦሪ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ ††† ††† ይህ ቅዱስ አባት የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ነው:: በዘመኑ (በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ክርስቲያን መሆን ብቻውን ለሞት እንደሚያበቃ ወንጀል ይቆጠር ነበር:: በጊዜው ክርስቲያን ከመሆን በባሰ መንገድ እረኛ ካህን ሆኖ መገኘት በጣም ከባድ ነበር:: ከመነሻውም ያን ጊዜ ክህነት የሚሰጠው በሕዝቡና በሊቀ ጳጳሱ ምርጫ ነበር እንጂ እንደ ዘንድሮ "እኔን ሹሙኝ" ማለት ልማድ አልነበረም:: ምዕመናንም እረኛቸውን ሲመርጡ በጉቦ: በዝምድና አይደለም:: በርትቶ የሚያበረታቸውን: ለመንጋው ራሱን አሳልፎ የሚሰጠውን ይመርጣሉ እንጂ:: ያልሆነ ሰው ለክህነት ቢመረጥ አንድም ክዶ ያስክዳል: ሲቀጥልም ለሕዝቡ መሰናክል መሆኑ አይቀርም:: በጊዜው (በዘመነ ሰማዕታት) የነበሩ ካህናት የቤት ሥራቸውም ማስተማር ብቻ አልነበረም:: በድፍረት በምዕመናን ፊት አንገታቸውን ለሰይፍ መስጠት ይጠበቅባቸው ነበር እንጂ:: ይህንን በገሃድ መፈጸም ከቻሉ አበው አንዱ ደግሞ አባ ኦሪ ቀሲስ ናቸው:: ቅዱሱ ተወልደው ባደጉባት ሃገረ ስጥኑፍ (የግብፅ አውራጃ ናት) መጻሕፍትን የተማሩ: ተወዳጅ እና ደግ ሰው ነበሩ:: አባ ኦሪ ገና ከወጣትነት ቀዳሚ ግብራቸው መንኖ ጥሪት (ምናኔ) ነበር:: በንጽሕናቸው ደስ የተሰኙ ምዕመናንም "ቅስና ተሹመህ ምራን: አስተምረን::" ቢሏቸው አበው ውዳሴ ከንቱን አይፈልጉምና "አይሆንም" አሉ:: ነገሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረና አባ ኦሪ ቅስናን ተሹመው ያገለግሉ ገቡ:: ሕዝቡን በማስተማር: በመምከር: ደካማውን በማጽናት ብዙ ደክመዋል:: ከቅድስናቸው የተነሳ ቅዳሴ ሊቀድሱ ሲገቡ ጌታችን በገሃድ ይገለጥላቸው ነበር:: ሠራዊተ መላእክትም ከበው ይነጋገሯቸው ነበር:: ሥጋውን ደሙን በማቀበልም ተግተው ዘመናት አለፉ:: ቆይቶ ግን ያ በዜና ይሰሙት የነበረ መከራ (ሰማዕትነት) በደጃቸው ደረሰ:: በጊዜው ብዙ ሰው በሰማዕትነት አለፈ:: አባ ኦሪም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ገብተው ስለ ራሳቸውና ሕዝቡ ጽናትን: ደኅንነትን ለመኑና ከቤተ ክርስቲያን ወጡ:: በቀጥታ የሔዱትም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምሥክርነት አደባባይ) ነበር:: በመኮንኑ ፊት ቀርበው "ክርስቶስ አምላክ: ፈጣሪ: የሁሉ ጌታ ነው:: የእናንተ ጣዖት ግን ጠፊ: ረጋፊ: ወርቅ: ብር: እንጨትና ድንጋይ ነው::" ሲሉ በድፍረት ተናገሩ:: መኮንኑም ከአነጋገራቸው የተነሳ ተቆጥቶ ሥቃይን አዘዘባቸው:: ወታደሮቹ ይሆናል ያሉትን ማሰቃያ ሁሉ አባ ኦሪ ላይ ሞከሩ:: በኋላም ወደ ጨለማ እሥር ቤት ወስደው ጣሏቸው:: በእሥር ቤት ውስጥም ድውያንን ፈወሱ: ተአምራትን ሠሩ:: ይሕንን ዜና የሰሙ አሕዛብ ብዙ ድውያንን ሰብስበው መጡ:: ቅዱሱም ሁሉን በጸሎታቸው ፈወሱ:: በዚህ ምክንያትም ብዙ አሕዛብ ወደ ክርስትና መጥተዋል:: በክርስቶስ አምነውም ለክብር በቅተዋል:: ቅዱሱንም ከእሥር ቤት አውጥተው ብዙ ካሰቃዩዋቸው በኋላ በዚህች ቀን ገድለዋቸው ሰማዕትነትን አግኝተዋል:: በአክሊለ ጽድቅ ላይ አክሊለ ካህናትን: በአክሊለ ካህናትም ላይ አክሊለ ሰማዕታትን ደርበዋል:: ††† አምላከ ቅዱሳን በአባቶቻችን ጽናት ያጽናን:: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን:: ††† ነሐሴ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ (ሰማዕት) 2.አባ ጲላጦስ ሊቀ ጳጳሳት ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ) 3.ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) ††† "ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" ††† (፩ቆሮ. ፲፥፲፬-፲፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
°የጾመ ፍልሠታ ትምህርት (፳፻፲፰/2018) °ክፍል 7 °በምስል (Video) ለምትሹ፦ https://youtu.be/OMheJxPfCmw?si=RzX6NtHhaiRCFVlt
✝እንኳን አደረሳችሁ ! ☞ወርኀ ነሐሴ ቡሩክ፤ ወአመ ፰፦ ✝ቅድስት ጾመ ፍልሠታ/ዕርገታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል፥ ወላዲተ አምላክ (ዘአበዊነ ሐዋርያት ንጹሐን) ✝ተዝካረ በዓሎሙ ለቅዱሳን ወክቡራን፥ ፬ቱ እንስሳ ኪሩቤል (ጸወርተ መንበሩ ለልዑል) ✝ወተዝካረ በዓሉ ለመልአክ ክቡር፥ አፍኒን ሊቅ፥ ሊቀ መላእክት ✝ወተዝካረ በዓሎሙ ለቅዱሳን፦ ሙሴ ሊቀ ነቢያት ወማር ማትያስ ሐዋርያ፥ አባ ብሶይ ወአባ ኪሮስ ጻድቃን፥ ደናግል በርባራ ወዮልያና፥ ወአባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን ❖ ወበዓለ ቅዱሳን አበው፦ ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ አረጋዊ፥ ወነቢየ እግዚአብሔር ልዑል፥ ማር አልዓዛር ሰማዕት፥ መስፍን ወሊቀ ካህናት፥ ወመምህሮሙ ለመቃብያን፥ ዘተቀትለ በእደ አንጥያኮስ አላዊ ✝ቅድስት ወቡርክት፥ ስብሕት ወብጽዕት፥ ክብርት ወልዕልት፥ ሰሎሜ/መብክዩ ሰማዕት፥ ብእሲተ አልዓዛር ካህን፥ ዘአርሰንዋ በእሳት ✝ክቡራን ወዐቢያን፥ ጻድቃን ንጹሐን፥ ፯ቱ እደው ሰማዕታት፥ ውሉደ አልዓዛር ካህን፥ እለ አሥመርዎ ለእግዚአብሔር (እሉ እሙንቱ፦ አንኤም ወአንጦኒኃስ፥ ወዖዝያ ወአልዓዛር፥ አስዮና ወስሙና ወመርካሎስ) ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ጽሙድ ወመስተጋድል ኢትዮጵያዊ፥ ማር አባ ኂሩተ አምላክ ገዳማዊ፥ መነኮስ ቡሩክ፥ ወብእሲ ትሩፍ፥ ዘገዳመ ጻና፥ ረድኡ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዐ፥ ወእኁሁ ለሐፄ ይኩኖ አምላክ °ቅድስት ገዳሙ ደብረ ዳጋ፥ ወቅዱሳን ውሉዱ መነኮሳት ጻድቃን ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ማር አባ ዮሐንስ ሥውር፥ መምህር ዘደብረ ሊባኖስ፥ ዘአንደየ ርዕሶ፥ ወዘሐወጸቶ እግዝእትነ ማርያም ድንግል °ቅድስት ገዳሙ ደብረ ሊባኖስ፥ ወቅዱሳን ውሉዱ መነኮሳት ጻድቃን ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ማር አባ አሞን ሰማዕት ❖ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ። ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡ https://t.me/zikirekdusn
https://youtu.be/jTL-67y_f5Q?si=Kt4dBKBMY3BVAc6y
"" የጾመ ፍልሠታ ትምህርት "" ፳፻፲፰/2018 (ክፍል ፮/6) °ወላዲተ አምላክ - በትንቢተ ኢሳይያስ °መልክዐ ውዳሴ - ትርጉም (ነሐሴ 6 - 2018) አፉየ አስተንፈሰ ወልሳንየ አልሆሰሰ ለክብረ ፍልሰትኪ ድንግል እንዘ አቄርብ ተውዳሰ ማርያም ዘኮንኪ ቅድስተ ቅዱሳን መቅደሰ በቅድሜኪ እግዝእትየ እመ ረከብኩ ሞገሰ በየማንኪ ባርክኒ ሥልሰ።
✝አቡነ ኂሩተ አምላክ✝ ✨ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱ። ✨ የአጼ ይኩኖአምላክ ዘመድ። ✨የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ወዳጅ። ✨የአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደቀ መዝሙር ። ✨ውሃ ላይ ድንጋይ ጥለው በዛ ላይ የሚሄዱ ድንቅ ተአምር ሰሪ ደግ አባት። ✨ግማደ መስቀሉ ከግብፅ ሲመጣ ተሸክመው ከአመጡ ቅዱሳን መካከል አንዱ ናቸው። ✨✨የገነት ነፋስ እንዲነፍስ ከጌታ ቃል ኪዳን የተቀበሉ። 🌿ዕረፍታቸው ነሐሴ 8 ነው በረከታቸው ይደርብን። 🌷እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤ እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን። ማርያም ድንግል እመ ረከብኩኪ: ሐዘነ ልብየ እነግረኪ: በገዳምኑ ወበዓት ኀበ ኀሠሥኩኪ: እግዝእትየ ማርያም እጼውእ ስመኪ: #ቀዊምየ ኀበ ሀሎኩ አስተርእይኒ ገጸኪ ወኀበ ስእለትየ ካዕበ #ጽልዊ እዝነኪ። ✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት 🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል) 🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር) 🔗https://t.me/zikirekdusn ▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
✝እንኳን አደረሳችሁ✝ 💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠 /ማቴ ፫:፫/ 🔶ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!! ✨እናስተውል!!✨ 🔸1,ጥሩ ክርስትና ፈጥኖ የሚገኝ አይደለም፡፡ ትእግስትን ይጠይቃል፡፡ 🔸2,ሰይጣን እኛን ኃጢአት በማሠራት አይረካም፡፡ የሚፈልገው ተስፋ ማስቆረጥ ነው፡፡ 🔸3, በእምነት የሚደረግ የትኛውም ጸሎት መፍትሔ አለው፡፡ 🔸4,የበጎ ለውጥ እናት ዓላማና ቁርጥ ውሳኔ ናቸው ✝ 5 ነገሮችን በደንብ እንያዝ!!! 🔻1,ዓላማ 🔻2, እምነት 🔻3,ጥረት 🔻4,ጥንቃቄ 🔻5ጽናት ✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር 🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል) 🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር) 🔗https://t.me/zikirekdusn ▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan °🛑ወገኖቼ፦ ⛅️ ንስሓ እንግባ ! 🌥 ንስሓ እንግባ !! 🌧 ንስሓ እንግባ !!! 🛑የአድርሽኝ ገንዘብ ለማስገባት አካውንት የጠየቃችሁ ✅አዋሽ ባንክ ZIKIRE KIDUSAN MAHIBERE KIDUS DAWIT! ✅Account No 01320670435200
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи