- Последний пост
- 7 июн. 2025 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 36
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ቅዱሳን ሐዋርያትም ‹‹ከ #አብ የሠረፀ የሁላችንም መጽናኛ የሚሆን ዓለሙንም ሁሉ ያዳነ ከ #አብና ከ #ወልድ ጋር ህልው የሚሆን #መንፈስ_ቅዱስን ላከልን፡፡ #መንፈስ_ቅዱስ #ጰራቅሊጦስም አንድ ነው›› ብለዋል። በሌላም ነቢዩ ዳዊት ስለ #መንፈስ_ቅዱስ ‹‹መንፈስህን ከእኔ አታርቅ አለ፤ ዳግመኛም በሰውነቴ እውነተኛ መንፈስን አጽናልኝ፣ ከሁሉ በሆነ #መንፈስ_ቅዱስ አጽናኝ አለ›› በማለት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ #መንፈስ_ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አጽናኝ መካሪ መባሉን አስተምሯል። (መዝ. ፶፥ ፲-፲፪፤ መጽሐፈ ምሥጢር) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በበዓለ ኀምሳ ምንባብ ላይ #እግዚአብሔር_መንፈስ_ቅዱስ #ጰራቅሊጦስ ስለተባለበትና ተስፋ በተሰጣቸው በኀምሳኛው ቀን ወርዶ ስለ ሠራው ሥራ እንዲህ በማለት ያብራራል። ‹‹ወ #መንፈስ_ቅዱስኒ ኢተሰምየ #ጰራቅሊጦስሃ ዘእንበለ አመ ይቤሎሙ #እግዚእ_ኢየሱስ ለአርዳኢሁ እፌኑ ለክሙ ካልአ #ጰራቅሊጦስሃ። #ጰራቅሊጦስ ብሂል ናዛዚ ብሂል በነገረ ጽርዕ …… #መንፈስ_ቅዱስም #ጌታ_ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሌላውን አጽናኝ እልክላችኋለሁ›› ከማለቱ በፊት #ጰራቅሊጦስ አልተባለም #ጰራቅሊጦስ ማለት በጽርዕ ቋንቋ አጽናኝ ማለት ነው ስለምን አጽናኝ ተባለ ደቀ መዛሙርቱ #ወልድ ካረገበት ቀን ጀምሮ #ጰራቅሊጦስ እስከ ወረደበት ቀን ድረስ ያለቅሱ ነበረና ስለዚህም #ወልድ #መንፈስ_ቅዱስን_ጰራቅሊጦስ አለው። የስሙ ትርጓሜ ግን አስቀድመን እንደተናገርነው አጽናኝ ማለት ነው። (ዮሐ. ፲፬፥፲፭) #በዓለ_ጰራቅሊጦስ የሚከበረው ርደተ #መንፈስ_ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመሆኑ ምክንያት ጸጋ #መንፈስ_ቅዱስ ለመቀበል ነው፤ በዕለቱም ኢየሩሳሌም በተባለችው #ቤተ_ክርስቲያን ስለመጽናት፤ ከግለኝነት ይልቅ መንፈሳዊ አንድነትን ስለማስቀደም እና ስለመጸለይ እንማራለን፡፡ በዓለ ትንሣኤውን በቸርነቱ በሰላም እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ጠበቀን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ሆነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን #አምላካችን_ልዑል_እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን፤ አሜን፡፡ ➣ምንጮች፤ መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፲፰ ቀን፣ መጽሐፈ ምሥጢር፡፡መጽሐፈ ግጻዌ...፡፡ ወስብሐት ለ #እግዚአብሔር #መልካም_በዓል
#ሰኔ_1 ቀን #በዓለ_ጰራቅሊጦስ #መንፈስ_ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ ጰራቅሊጦስ ናዛዚ መጽንዒ መስተፍሥሒ፤ የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ የሚል ትርጉም አለው፡፡ አጽናኝም የተባለው #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው። ‹‹#አብ በስሜ የሚልከው ግን #መንፈስ_ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋ›› ብሎ ተናግሯል፡፡ በሌላም በኩል ደግሞ ‹‹እኔ ከ #አብ ዘንድ የምልክላችሁ #ጰራቅሊጦስ እርሱም ከ #አብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል›› እንዲል። (ዮሐ.፲፬፥፳፮፤ ፲፭፥፲፮) #ጰራቅሊጦስ የሚለው የ #መንፈስ_ቅዱስ ስም የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ መሆኑም ከማሳየት በላይ፤ ፍጹም አካል ያለው አምላክ እንደሆነ አመልካች ነው። ➣ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #ጰራቅሊጦስ ማለት መሪ፣ አጽናኝ፣ ረጂ ማለት መሆኑን በስፋት ካስተማሩ ሊቃውንት በቀዳሚነት ይነሳል። #ጰራቅሊጦስ የተባለው #መንፈስ_ቅዱስ_እግዚአብሔር ነው። ሐዋርያዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በ #መንፈስ_ቅዱስ ያላትን እምነቷን ስትገልጥ ‹‹ወነአምን በ #መንፈስ_ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ ዘሠረፀ እም #አብ ንሰግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ #አብ #ወወልድ››፤ በ #መንፈስ_ቅዱስ እናምናለን እርሱም #ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከ #አብ የሠረፀ ከ #አብ ከ #ወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን፣ እናመሰግነዋለን፤›› የሚል ነው። #እግዚአብሔር_መንፈስ_ቅዱስ ፤ የቅድስናም ምንጭ ነው። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‹‹ወስመ #መንፈስ_ቅዱስ ነቅዐ ቅድሳትየ፤ የ #መንፈስ_ቅዱስም ስም የቅድስናየ መገኛ ነው›› በማለት ገልጾታል። (መጽሐፈ ምሥጢር) ቅዱስ ባስልዮስም በቅዳሴው ‹‹ሃሌ ሉያ ቅዱስ #መንፈስ_ቅዱስ #ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር #መንፈስ_ቅዱስ ንጹሕ ክቡር ልዩ ነው›› በማለት አምላካዊ ስሙን ጠርቶ አመስግኖታል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ዕለት ዕለት በምታከናውነው ሥርዓተ ቅዳሴ ‹‹መንጽሒ ወመጽንዒ የሚሆን #መንፈስ_ቅዱስ ክቡር ምስጉን ነው›› እያለች የአምላክነት ስሙን ጠርታ ታመሰግነዋለች። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ሊያጸኑ ከሓድያንን ሊለዩ (ሊያወግዙ) ሲሰባሰቡ በመካከላቸው ተገኝቶ ውሳኔ ያስወስናቸው የነበረው #እግዚአብሔር_መንፈስ_ቅዱስ እንደሆነ ሲገልጹ #ጰራቅሊጦስ የተባለ ስሙን ጠርተው እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹ወሀሎ ምስሌሆሙ ኅብረ #መንፈስ_ቅዱስ …. #ጰራቅሊጦስ የሚያነጻና የሚያጸና #መንፈስ_ቅዱስም በጉባኤያቸው ነበረ፡፡›› (መጽሐፈ ምሥጢር) #ጌታችን_አምላካችንና_መድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ሆነው በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ #ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ‹‹እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤›› ሲል ለሐዋርያቱ በሰጣቸው የተስፋ ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን #መንፈስ_ቅዱስን ልኮላቸዋል (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)፡፡ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በሁሉም ላይ አረፉባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁላቸውም #መንፈስ_ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየሀገሩ ቋንቋዎች ሁሉ ተናገሩ፡፡ (ሐዋ.፪፥፩-፬) #ጌታችን_መንፈስ_ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ካህናተ ኦሪት ስለሚቀበሉበት በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ተብሎ ይከበር ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት #መንፈስ_ቅዱስን ስለ ተቀበሉበት በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ #ጰራቅሊጦስ ተብሎ ይከበራል፡፡ የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብጽ፣ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ሆነው ሁሉ፣ ለበዓለ #ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው፡፡ የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በኀምሳኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚሆነውን በዓለ ሠዊት (የእሸት በዓል) ያከብሩ ነበር፡፡ ቅዱሳንጨሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ #መንፈስ_ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ #መንፈስ_ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ሆነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡ ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ቋንቋ በተጨማሪ ፸፩ ቋንቋዎች ተገልጠውላቸው ምሥጢራትን በልዩ ልዩ ቋንቋ መተርጐም ጀምረዋል፡፡ ሐዋርያት በየሀገሩ ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ በዚያ የነበሩ ሰዎችም በሐዋርያት ተገረሙ፡፡ አንዳንድ የአይሁድ ወገኖች ግን በሐዋርያት ላይ ያዩት ክሥተት አዲስ ነገር ስለሆነባቸው ክብር ይግባቸውና ‹‹ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ›› እያሉ ሐዋርያትን ያሟቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ሐሳባቸውን በ #መንፈስ_ቅዱስ አውቆ ‹‹ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትጠራጠሩት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ፣ ሰዓቱም ገና ሦስት ሰዓት ነውና፡፡ ግን በነቢዩ ኢዩኤል ‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ፣ ይህንን ድንቅ ተአምር ያደረገው እናንተ የሰቀላችሁት #ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው፤››በማለት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥቷቸዋል፡፡ (ኢዩ.፪፥፳፰) በትምህርቱም ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት፣ ምሳሌ የመሰሉለት #አምላክ_ወልደ_አምላክ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መሆኑን ሐዋርያት እንደሚመሰክሩ በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡ በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ‹‹ምን እናድርግ?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ከክፋታቸው ተመልሰው፣ንስሓ ገብተው በ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ነገሯቸዋል፡፡ በዚያችም ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በ #ኢየሱስ_ክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል፡፡(ሐዋ.፪፥፩-፵፩) ቅዱሳን ሐዋርያት፤ ‹‹በዚህች ቀን በሦስት ሰዓት #ኢየሱስ _ክርስቶስ #ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና በላያችን ኃይልን ሞላ፡፡ #ኢየሱስ_ክርስቶስ የ #እግዚአብሔር ልጅ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው በአዲስ ቋንቋ ተናገርን፤›› በማለት በዕለቱ ያዩትንና የተደረገላቸውን፣ እንደዚሁም የበዓሉን ታላቅነት ከመሰከሩ በኋላ ይህንን በዓል ማክበር እንደሚገባ አዝዘዋል፤ በዚህ ወቅት መጾምና ማዘን ተገቢ አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡ (ዲድስቅልያ ፴፥፴፰-፴፱፤ ፴፩፥፷፱-፸)
видео или голосовое, без подписи
✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✝✞✞✞ ❖ ✝እንኳን አደረሳችሁ ✝❖ ❖ ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ_ዮሴፍ_ጻድቅ +"+ =>ቤተ_ክርስቲያን በዚህ ስም ብዙ ቅዱሳን አሏት:: በተለይ ደግሞ እስራኤል የተባለ የቅዱስ_ያዕቆብ ልጅ ቅዱስ ዮሴፍ ከሁሉም ቅድሚያውን ይይዛል:: ታላቁ ቅዱስ_መጽሐፍ ላይ በስፋት ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳን አንዱ ነው:: +ስለዚህ ቅዱስ ዝርዝር መረጃን ለማግኘት ኦሪት_ዘፍጥረትን ከምዕራፍ 39 እስከ 50 ድረስ ማንበብ ይኖርብናል:: ከዚህ በተረፈም በዜና ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሱ ብዙ ተብሏል:: +መጽሐፍ ቅዱስ ሲጀምር ስለ ቅዱስ ሰው አዳም ይነግረናል:: ቀጥሎም ስለ ቅዱሳኑ ሴት ሔኖክ ኖኅ ሴም አብርሃም ይስሐቅና ያዕቆብ ነግሮን ቅዱስ_ዮሴፍ ላይ ይደርሳል:: +ቅዱስ ዮሴፍ ያዕቆብ (እስራኤል) ከሚወዳት ሚስቱ ራሔል ከወለዳቸው 2 የስስት ልጆቹ አንዱ ነው:: ቅዱሱ ምንም እናቱ ብትሞተበትም በአባቱና በፈጣሪው ፊት ሞገስ ነበረው:: ምክንያቱም ቅን: ታዛዥና የፍቅር ሰው ነበርና:: +እንዲያ አምርረው ለሚጠሉት ወንድሞቹ እንኳን ክፋትን አያስብም ነበር:: ይልቁኑ ለእነሱ ምሳ (ስንቅ) ይዞ ሊፈልጋቸው በበርሃ ይንከራተት ነበር እንጂ:: +መንገድ ላይ ቢርበው አለቀሰ እንጂ ስንቃቸውን አልበላባቸውም:: የአባቶቹ አምላክ ግን ድንጋዩን ዳቦ አድርጐ መግቦታል:: 10ሩ ወንድሞቹ ግን ስለ በጐነቱ ፈንታ ሊገድሉት ተማከሩ:: ከፈጣሪው አግኝቶ በነገራቸው ሕልም "ሊነግሥብን ነው" ብለው ቀንተውበታልና:: +በፍጻሜው ግን በይሁዳ መካሪነት ለዐረብ ነጋድያን ሸጠውታል:: በዚህም ለምሥጢረ ሥጋዌ (ለጌታ መሸጥና ሕማማት) ምሳሌ ለመሆን በቅቷል:: ወንድሞቹ ለክፋት ቢሸጡትም ቅሉ ውስጡ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበትና በባርነት በተሸጠበት በዺጥፋራ ቤት ፈጣሪው ሞገስ ሆነው:: +ወጣትነቱን በፍቅረ እግዚአብሔር ሸብ አድርጐ አስሮ ነበርና የዺጥፋራ ሚስት የዝሙት ጥያቄ አላንበረከከውም:: "ማንም አያየንም" ስትለውም "እፎ እገብር ኃጢአተ በቅድመ እግዚአብሔር" (ማንም ባያይስ እንዴት በፈጣሪየ ፊት ኃጢአትን አሠራለሁ?) በማለት ከበደል አምልጧል:: ስለዚህ ፈንታም የእሥር ቅጣት አግኝቶታል:: +ጌታ ከእርሱ ጋር ቢሆን በእሥር ቤትም ሞገስን አገኘና አለቅነትን ተሾመ:: "ኢኀደረ ዮሴፍ ዘእንበለ ሲመት" እንዲል መጽሐፍ:: ከዚያም የንጉሡን (የፈርዖንን) ባለሟሎች ሕልም ተረጐመ:: ቀጥሎም ንጉሡን በሕልም ትርጓሜ አስደመመ:: ፈርዖንም ቅዱሱን በግዛቱ (ግብጽ) ላይ ሾመው:: +ቅዱስ ዮሴፍ በምድረ ግብጽ ነግሦ ሕዝቡን ከረሃብ ታደገ:: ለቅዱስ አባቱ ለእሥራኤልና ክፉ ለዋሉበት ወንድሞቹም መጋቢ ሆናቸው:: አስኔት (አሰኔት) የምትባል ሴት አግብቶም ኤፍሬምና ምናሴ የተባሉ ልጆችን አፍርቷል:: +በመንገዱ ሁሉ እግዚአብሔርን አስደስቶ: ከአባቱ ዘንድም ምርቃትና በረከትን ተቀብሎ በ110 ዓመቱ በዚህች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፏል:: ወገኖቹም በክብርና በእንባ ቀብረውታል:: "አጽሜን አፍልሱ" ብሎ በተናገረው ትንቢት መሠረትም ልጆቹ (እነ ቅዱስ ሙሴ) ከግብጽ ባርነት ሲወጡ አጽሙን ወደ ከነዓን አፍልሠዋል:: +" ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት "+ =>ቅዱሱ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት ነገሥታቱን ያገለግል ነበር:: ድንግል: ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው:: +እርሱ ግን ምን ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ ይጸልየው: ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የታሸ ነውና ብዙ ጉዋደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት: ከክፋት ወደ ደግነት መልሷል:: +የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ ጊዜም አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት: ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር:: +በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገቱን ተሰይፏል:: ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና በእምነት እንጥራው:: ቤተ ክርስቲያንም ዛሬ የቅዱሱን ተአምራት ታስባለች:: ቅዳሴ ቤቱም የተከበረው በዚሁ ዕለት ነው:: =>አምላከ ቅዱሳን ወርኀ ሰኔን የፍሬ: የበረከት: የንስሃና የጽድቅ አድርጐ ይስጠን:: ከሰማዕቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: =>ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (የያዕቆብ ልጅ) 2.እናታችን አስኔት (የቅ/ ዮሴፍ ሚስት) 3.ቅዱስ ለውንትዮስ ክቡር ሰማዕት 4.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት 5.ቅዱስ ቆዝሞስ ሰማዕት ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ልደታ ለማርያም 2፡ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 3፡ ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ 4፡ ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት 5፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና =>+"+ እንዲህም አላቸው:- "ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ:: አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትዘኑ:: አትቆርቆሩም:: እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከእናንተ በፊት ሰዶኛልና . . . እግዚአብሔርም በምድር ላይ ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ: በታላቅ መድኃኒትም አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ::" +"+ (ዘፍ. 45:4-8) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
#የግንቦት_30_ግጻዌ ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_30_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 1ኛ ቆሮንቶስ 15 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤ ² በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ። ³ እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ ⁴ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ ⁵ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ፤ ⁶ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነርሱም የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን አንቀላፍተዋል፤ ⁷ ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ፤ ⁸ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ። ⁹ እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ፤ ¹⁰ ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም። ¹¹ እንግዲህስ እኔ ብሆን እነርሱም ቢሆኑ እንዲሁ እንሰብካለን እንዲሁም አመናችሁ። ¹² ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ የሚሰበክ ከሆነ ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ፦ ትንሣኤ ሙታን የለም እንዴት ይላሉ? ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 1ኛ ዮሐንስ 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁷ እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። ²⁸ አሁንም፥ ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ። ²⁹ ጻድቅ እንደ ሆነ ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደ ተወለደ እወቁ። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ሐዋርያት 18 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²³ ጥቂት ቀንም ቆይቶ ወጣ፥ ደቀ መዛሙርትንም ሁሉ እያጸና በገላትያ አገርና በፍርግያ በተራ አለፈ። ²⁴ በወገኑም የእስክንድርያ ሰው የሆነ ነገር አዋቂ የነበረ አጵሎስ የሚሉት አንድ አይሁዳዊ ሰው ወደ ኤፌሶን ወረደ፤ እርሱም በመጻሕፍት እውቀት የበረታ ነበረ። ²⁵ እርሱ የጌታን መንገድ የተማረ ነበረ፥ የዮሐንስንም ጥምቀት ብቻ አውቆ በመንፈስ ሲቃጠል ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር ነበር። ²⁶ እርሱም በምኵራብ ገልጦ ይናገር ጀመር። ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ፥ ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት። ²⁷ እርሱም ወደ አካይያ ማለፍ በፈቀደ ጊዜ፥ ወንድሞቹ አጸናኑት፥ ይቀበሉትም ዘንድ ወደ ደቀ መዛሙርት ጻፉለት፤ በደረሰም ጊዜ አምነው የነበሩትን በጸጋ እጅግ ይጠቅማቸው ነበር፤ ²⁸ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ከመጻሕፍት እየገለጠ ለአይሁድ በሁሉ ፊት በጽኑ ያስረዳቸው ነበርና። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_30_ቀን_የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ "እስመ ጽድቅ ወምጽዋት ያበድር #እግዚአብሔር። #እግዚአብሔር ይሁብ ክብረ ወሞገስ። #እግዚአብሔር ኢያስተፄንሶሙ እምበረከቱ ለእለ የሐውሩ በየዋሃት"። መዝ 83፥11-12 #ትርጉም፦ “ #እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ #እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም።” መዝ 83፥11-12 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_30_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ሉቃስ 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ከዚህም በኋላ ጌታ ሌሎቹን ሰብዓ ሾመ፥ ሁለት ሁለትም አድርጎ እርሱ ሊሄድበት ወዳለው ከተማና ስፍራ ሁሉ በፊቱ ላካቸው። ² አላቸውም፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት። ³ ሂዱ፤ እነሆ፥ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ። ⁴ ኮረጆም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድም ለማንም እጅ አትንሡ። ⁵ ወደምትገቡበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ፦ ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን በሉ። ⁶ በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለዚያም ይመለስላችኋል። ⁷ በዚያም ቤት ከእነርሱ ዘንድ ካለው እየበላችሁና እየጠጣችሁ ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋልና። ከቤት ወደ ቤት አትተላለፉ። ⁸ ወደምትገቡባትም ከተማ ሁሉ ቢቀበሉአችሁ፥ ያቀረቡላችሁን ብሉ፤ ⁹ በእርስዋም ያሉትን ድውዮችን ፈውሱና፦ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ቀረበች በሉአቸው። ¹⁰ ነገር ግን ወደምትገቡባት ከተማ ሁሉ ባይቀበሉአችሁ፥ ወደ አደባባይዋ ወጥታችሁ፦ ¹¹ ከከተማችሁ የተጣበቀብንን ትቢያ እንኳን እናራግፍላችኋለን፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ግን ወደ እናንተ እንደ ቀረበች ይህን እወቁ በሉ። ¹² እላችኋለሁ፥ በዚያን ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶም ይቀልላታል። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱሳን_ሐዋርያት_ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው ቅዱስ ቆሮስ፣ የአባ ሚካኤል፣ የቅድስት ወለተ ማርያም የዕረፍት በዓል፣ የቅድስት ዜና ማርያም የልደትበዐልና የበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ አርዋ ቅድስት +"+ =>እናታችን ቅድስት አርዋ በስነ ገድላቸው ከደመቁ የቀደመው ዘመን ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት:: በሕጻንነቷ የሚገባውን የክርስትና ትምሕርት ተምራለችና ምርጫዋ ሰማያዊው ሙሽርነት ሆነ:: +ለሰዎች ሕይወት እንቅፋት እየሆኑ ከሚያስቸግሩ ነገሮች አንዱ መልክ ነው:: እግዚአብሔር የፈጠረውን ደም ግባት (ቁንጅና) በማይገባ ተጠቅመው የአጋንንት ራት የሆኑ: ሌሎችንም አብረው ያጠፉ ሰዎች ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው:: አርዋ ግን ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ብትሆንም እርሷ ለዚሕ ቦታ አልነበራትም:: በለጋ እድሜዋ በክርስቶስና በድንግል እናቱ ፍቅር ተጠመደች እንጂ:: +ቅድስት አርዋ ሁሉ ያላት ስትሆን ስለ መንግስተ ሰማያት ሁሉን ንቃለች:: በተለይ ደግሞ ሥጋዊ ፍትወትን ትገድል ዘንድ ያሳየችው ተጋድሎ በዜና ቤተ ክርስቲያን የተደነቀ በመሆኑ "መዋኢተ ፍትወት" (የሥጋን ፍላጎት ድል የነሳች) አስብሏታል:: +የሚገርመው የቅድስቷ እናታችን ሕይወት በጾምና በጸሎት ብቻ የተወሰነ አልነበረም:: በሰው ሁሉ ፊት ብርሃን መሆን የቻለ የደግነት: ርሕራሔ: የፍቅርና የምጽዋት ሕይወትም ነበራት እንጂ:: +አንድ ቀን በተንኮለኞች የሐሰት ምስክር ያለ ጥፋቷ ለፍርድ ቀረበች:: ፍርደ ገምድል ዳኛ ሞት ፈረደባት:: በአደባባይ በጭካኔ ቅድስት እናታችንን ገደሏት:: እግዚአብሔር ግን ድንቅ ነውና ከሞት አስነስቷት ገዳዮቿ እንዲጸጸቱ አድርጓል:: ከዚሕ በኋላም በንጹሕ አኗኗሯ ቀጠለች:: +አንድ ቀን ግን ከባድ ፈተና መጣባት:: አንድ በደም ግባቷ ተማርኮ ሲፈልጋት የኖረ ጐልማሳ አሳቻ ሰዓትና ቦታ ላይ አገኛት:: የሥጋ ፈቃዱን ይፈጽም ዘንድ አስገደዳት:: +እርሱን መታገሉ ከአቅሟ በላይ ስለሆነባት እርሱ ልብሱን እያወለቀ እርሷ ከወደቀችበት ሆና ወደ ፈጣሪዋ ለመነች:- "ጌታየ ሆይ! የእኔንም ድንግልና ጠብቅ: እርሱንም ኃጢአት ይሠራ ዘንድ አትተወው:: ስለዚሕም ነፍሴን ተቀበላት" ብላ አለቀሰች:: +እመቤታችን እንደ ዐይን ጥቅሻ ወርዳ ነፍሷን አሳረገች:: ጐልማሳው ወደ ጣላት ቅድስት ዘወር ቢል ሙታ አገኛት:: እርሱም ተጸጸተ:: ወገኖቿ በዝማሬ እናታችን ቅድስት አርዋን ቀብረዋታል:: ✞ ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ ✞ =>ዳግመኛ በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቆሮስ አርፏል:: +ቅዱስ ቆሮስ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ከጌታችን እግር የተማረ: ለስብከተ ወንጌል ብዙ ሃገራትን የዞረ ታላቅ ሐዋርያ ነው:: ባስተማረባቸው ቦታዎች ብዙ ሕማማትን ተቀብሏል:: +ብዙ አሕዛብንም ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሷል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለዓመታት አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስ ሲታሠር መልዕክቶችንም ይወስድለት ነበር:: ❖ወርኀ ግንቦትን በሰላም ላስፈጸመን እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን:: አምላካችን ከወዳጆቹ በረከትን ይክፈለን:: ❖ግንቦት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት አርዋ እናታችን 2.ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ 3.ቅዱስ ዲማዲስ ሰማዕት 4.አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ 2፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ 3፡ አባ ሣሉሲ ክቡር 4፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት 5፡ ቅድስት ሶፍያና ሰማዕታት ልጆቿ ++"+ መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ:: ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው:: እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች:: ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥረዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት:: +"+ (ምሳሌ. 31:29) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
#የግንቦት_29_ግጻዌ ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_29_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ገላትያ 4 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥ ² ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው። ³ እንዲሁ እኛ ደግሞ ሕፃናት ሆነን ሳለን ከዓለም መጀመሪያ ትምህርት በታች ተገዝተን ባሪያዎች ነበርን፤ ⁴ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ ⁵ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። ⁶ ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ። ⁷ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ። ⁸ ነገር ግን በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን ሳታውቁ በባሕርያቸው አማልክት ለማይሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ ተገዛችሁ፤ ⁹ አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን? ¹⁰ ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ። ¹¹ ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ። ¹² ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ሆኜአለሁና፦ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ። አንዳችም አልበደላችሁኝም። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 1ኛ ዮሐንስ 4 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁹ በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና። ¹⁰ ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። ¹¹ ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል። ¹² እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል። ¹³ ከመንፈሱ ስለ ሰጠን፥ በእርሱ እንድንኖር እርሱም በእኛ እንዲኖር በዚህ እናውቃለን። ¹⁴ እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን። ¹⁵ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል። ¹⁶ እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል። ¹⁷ በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና። ¹⁸ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። ¹⁹ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ሐዋርያት 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁷ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና፦ ፈጥነህ ተነሣ አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ። ⁸ መልአኩም፦ ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ። ⁹ ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም። ¹⁰ የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም አንዲት ስላች አለፉ ወዲያውም መልአኩ ከእርሱ ተለየ። ¹¹ ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ፦ ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ። ¹² ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_29_ቀን_የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ "ወተግሣጽከ ውእቱ ዘይሜሕረኒ። ወአርኅብከ መከየድየ በመትሕቴየ። ወኢደክመ ሰኰናየ። መዝ.17÷38-39 #ትርጉም፦ "አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፤ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ"። መዝ.17÷38-39 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_29_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ማቴዎስ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ ² አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ፦ ³ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ⁴ የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና። ⁵ የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና። ⁶ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና። ⁷ የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና። ⁸ ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና። ⁹ የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና። ¹⁰ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ¹¹ ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ¹² ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና። ¹³ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። ¹⁴ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። ¹⁵ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። ¹⁶ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ¹⁷ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ሠለስቱ_ምዕት ወይም የ #ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ_ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የበዓለ ሃምሳ ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ አባ አፍፄ ወአባ ጉባ +"+ =>አባ አፍፄና አባ ጉባ ቁጥራቸው ከተስዓቱ (ዘጠኙ) ቅዱሳን ነው:: +"+ አባ አፍፄ +"+ =>ጻድቁ የተወለዱት እስያ ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ:: ገና በሕጻንነታቸው ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቀው ወደ ግብፅ ወርደዋል:: በዚያም በአባ መቃርስ እጅ መንኩሰዋል:: አባ አፍፄ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በአልዐሜዳ ዘመን ከ8ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ነው:: +ጻድቁ ጸበል እያፈለቁ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል:: ትግራይ ውስጥ የሐ የተባለው ቦታም ማረፊያቸው ነበር:: ❖ለጻድቁ በጥቂቱ እነዚሕን እንጠቅሳለን:- 1.ከ100 ዓመት በላይ አበ ምኔት ሆነው በኖሩበት ገዳማቸው በፍጹም ትጋት: በጾምና በጸሎት አገልግለዋል:: 2.በመጀመሪያ ያስከተሏቸውን 366 ደቀ መዛሙርት ጨምሮ ብዙ መናንያንን አፍርተው በሃገራችን ገዳማዊ ሕይወትን አስፋፍተዋል:: 3.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስትና ከጽርዕ ቋንቋ ወደ ግዕዝ ተርጉመዋል:: 4.በስብከተ ወንጌል ለሃገራችን ብርሃን አብርተዋል:: ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር "አፍፄ (አፈ-ዐፄ)" ብሏቸዋል:: "የዐፄ (የንጉሥ) አንደበት ያለው" ወይም "ንግግር አዋቂ" ማለት ነው:: +ጻድቁ ከ200 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን አገልግለው በዚሕች ቀን በ684 ዓ/ም ተሠውረዋል:: እግዚአብሔርም በስማቸው ለተማጸነ: ገዳማቸውን ለተሳለመ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: +"+ አባ ጉባ +"+ =>ጻድቁ የተወለዱት ታሕሳስ 29 ቀን በ336 ዓ/ም በመንፈቀ ሌሊት ነው:: አባታቸው ጌርሎስ: እናታቸው ቴዎዶክስያ ደጐች ነበሩ:: +አባ ጉባ ("ባ" ጠብቆ ይነበብ) በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር:: ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን ሃሌ ሉያ ብለው አመስግነዋል:: +በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው: ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገብተው መንነዋል:: ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮዽያ ሒድ" ብሏቸው ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሃገራችን መጥተዋል:: በወቅቱ ዕድሜአቸው ከ140 በላይ ነበር:: +ጻድቁ አባ ጉባ እንደመሰሎቻቸው በስብከተ ወንጌል: መጻሕፍትን በመተርጐም: ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ ቆይተዋል:: በተለይ ራማ ኪዳነ ምሕረት የእርሳቸው ናት ይባላል:: +ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ብለው ነበር:: ብዙ ጸበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል:: ሙታንንም አንስተዋል:: እመቤታችንም የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች:: ጻድቁ ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል:: +በዘመኑ ትኩረት ካጡ ታላላቅ ገዳማት አንዱ ይሔው ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የአባ ጉባ ገዳም ነው:: (በነገራችን ላይ "ጉባ" ማለት "አፈ-መዐር: ጥዑመ- ልሳን" ማለት ነው) ❖ቸሩ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የጻድቃኑን በረከት ያድለን:: በጸሎታቸውም በደላችንን ይቅር ይበለን:: ❖ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አባ አፍፄ (ከዘጠኙ ቅዱሳን) 2.አባ ጉባ (ከዘጠኙ ቅዱሳን) 3.አባ ስምዖን ገዳማዊ (በ7 ዓመታቸው መንነው ለ81 ዓመታት በተጋድሎ የኖሩ ሶርያዊ) 4.አባ ይስሐቅ ጻድቅ ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ በዓለ ልደቱ ለክርስቶስ 2፡ ቅድስት አርሴማ ድንግል 3፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት 4፡ ቅዱስ ማርቆስ ዘሮሜ 5፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ 6፡ ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ 7፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሐዋርያ 8፡ ጉባኤ ሰማዕታት ++"+ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም:: +"+ (ማቴ. 10:41) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
#የግንቦት_28_ግጻዌ ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_28_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 1ኛ ቆሮንቶስ 7 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁹ ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ ³⁰ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ ³¹ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። ³² ነገር ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤ ³³ ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአል። ³⁴ ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች። ³⁵ ይህንም ለራሳችሁ ጥቅም እላለሁ፤ በአገባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም በጌታ እንድትጸኑ ነው እንጂ ላጠምዳችሁ ብዬ አይደለም። ³⁶ ዳሩ ግን ማግባት ወደሚገባው ዕድሜ በደረሰ ጊዜ ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር፥ የወደደውን ያድርግ፤ ኃጢአት የለበትም፤ ይጋቡ። ³⁷ ሳይናወጥ በልቡ የጸና ግን ግድ የለበትም፥ የወደደውን እንዲያደርግ ተፈቅዶለታል፤ ድንግልናውንም በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና፥ መልካም አደረገ። ³⁸ እንዲሁም ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ ያላገባም የተሻለ አደረገ። ³⁹ ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት። ⁴⁰ እንደ ምክሬ ግን እንዳለች ብትኖር ደስተኛ ናት፤ እኔም ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ያለ ይመስለኛል። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ያዕቆብ 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁹ እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል። ²⁰ አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን? ²¹ አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? ²² እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን? ²³ መጽሐፍም፦ አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ። ²⁴ ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ። ²⁵ እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን? ²⁶ ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ሐዋርያት 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ሐናንያም የተባለ አንድ ሰው ሰጲራ ከተባለች ከሚስቱ ጋር መሬት ሸጠ፥ ² ሚስቱም ደግሞ ስታውቅ ከሽያጩ አስቀረና እኩሌታውን አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አኖረው። ³ ጴጥሮስም፦ ሐናንያ ሆይ፥ መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ? ⁴ ሳትሸጠው የአንተ አልነበረምን? ከሸጥኸውስ በኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን? ይህን ነገር ስለ ምን በልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም አለው። ⁵ ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ ሞተም፤ በሰሙትም ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ። ⁶ ጐበዞችም ተነሥተው ከፈኑት አውጥተውም ቀበሩት። ⁷ ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላም ሚስቱ የሆነውን ሳታውቅ ገባች። ⁸ ጴጥሮስም መልሶ፦ እስቲ ንገሪኝ፥ መሬታችሁን ይህን ለሚያህል ሸጣችሁትን? አላት። እርስዋም፦ አዎን፥ ይህን ለሚያህል ነው አለች። ⁹ ጴጥሮስም፦ የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለ ምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው አንቺንም ያወጡሻል አላት። ¹⁰ ያን ጊዜም በእግሩ አጠገብ ወደቀች ሞተችም፤ ጐበዞችም ሲገቡ ሞታ አገኙአት አውጥተውም በባልዋ አጠገብ ቀበሩአት። ¹¹ በቤተ ክርስቲያን ሁሉና ይህንም በሰሙ ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ። ¹² በሐዋርያትም እጅ ብዙ ምልክትና ድንቅ በሕዝብ መካከል ይደረግ ነበር፤ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ ነበሩ። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_28_ቀን_የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ "አሌ ሎን ለከናፍረ ጒህሉት። እለ ይነባ ዓመፃ ላዕለ ጽድቅ። በትዕቢት ወበመንኖ"። መዝ.30÷18÷19 #ትርጉም፦ “በድፍረትና በትዕቢት በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።” መዝ.30÷18÷19 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_28_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ሉቃስ 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²² ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ። ²³ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና። ²⁴ ቍራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም፥ ዕቃ ቤትም ወይም ጎተራ የላቸውም፥ እግዚአብሔርም ይመግባቸዋል፤ እናንተስ ከወፎች እንዴት ትበልጣላችሁ? ²⁵ ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? ²⁶ እንግዲህ ትንሹን ነገር ስንኳ የማትችሉ ከሆናችሁ፥ ስለ ምን በሌላ ትጨነቃላችሁ? ²⁷ አበቦችን እንዴት እንዲያድጉ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዲቱ አለበሰም። ²⁸ እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን በሜዳ የሆነውን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት? ²⁹ እናንተም የምትበሉትን የምትጠጡትንም አትፈልጉ፥ አታወላውሉም፤ ³⁰ ይህንስ ሁሉ በዓለም ያሉ አሕዛብ ይፈልጉታልና፤ የእናንተም አባት ይህ እንዲያስፈልጋችሁ ያውቃል። ³¹ ዳሩ ግን መንግሥቱን ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ³² አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ። ³³ ያላችሁን ሽጡ ምጽዋትም ስጡ፤ ሌባ በማይቀርብበት ብልም በማያጠፋበት በሰማያት የማያልቅ መዝገብ የሚሆኑትን የማያረጁትንም ኮረጆዎች ለራሳችሁ አድርጉ፤ ³⁴ መዝገባችሁ ባለበት ልባችሁ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። ³⁵ ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤ ³⁶ እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ፤ ³⁷ ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል። ³⁸ ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፥ እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው። ³⁹ ይህን ግን እወቁ ባለቤት በምን ሰዓት ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ፥ ቤቱም እንዲቆፈር ባልፈቀደም ነበር። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ኤጲፋንዮስ_ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የበዓለ ሃምሳ ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ግንቦት_28_ቅዳሴ_ቤቱ_ለቅዱስ_አማኑኤል የደብረ ገሊላ #ቅዱስ_አማኑኤል ካቴድራል የተተከለው በ1905 ዓ.ም በልጅ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት ነው። የመጀመሪያውን መቃኞ ያሠሩት ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ሲሆኑ ጽላቱም በጎንደር ክፍለ ሀገር የነበረና ከዚያ መጥቶም በ #ቅድስት_ሥላሴ ቤተክርስቲያን የተቀመጠ ነበር። ታድያ ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ያሠሩት የመጀመርያው መቃኞ ለአገልግሎት ምቹ ስላልነበር ሁለተኛ መቃኞ ድጋሚ ተሠርቶ ታቦቱ እንዲገባ ተደርጓል። ንግሥት ዘውዲቱ በግንቦት 28 በ1914 ዓ.ም የ #ቅዱስ_አማኑኤልን በዓል ተገኝተው ሲያስቀድሱ ምርጊቱ ተደርምሶ ሲወድቅ በማየታቸው ሦስተኛ መቃኞ እንዲሠራ አዘዙ። የደብሩ አስተዳዳሪ በጊዜው የተክለ ሃይማኖትን ቤተክርስቲያንም አንድ ላይ ያስተዳድሩ የነበረ በመሆኑ ንግሥቲቷ የቤተ መንግሥታቸውን አጣኝ የመጀመርያው አስተዳዳሪ ሆነው ደብሩን እንዲጠብቁ አደረጉ። አለቃው ሦስተኛ መቃኞ አሠርተው ታቦቱ ወደ ተዘጋጀለት መቃኞ ገባ። በ1920 ሕዝቡ እየበዛ በመምጣቱ አገልግሎቱ እንዲሰፋ ስላስፈለገ በንግሥት ዘውዲቱ አማካኝነት አዲስ ሕንፃ ቤተ መቅደስ ግንባታ ተጀመረ። በ1931 ታኅሣሥ 28 ቀን ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ታቦቱ ወደ መንበሩ ገብቷል። ንግሥት ዘውዲቱ ፍጻሜውን ሳያዩ ያረፉ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ደግሞ ክብ ቅርጽ ነበረው። አሁን ያለው ቤተክርስቲያን በጥር 28 ቀን 1969 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው የተጀመረ ሲሆን የወቅቱ የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ በነበሩት በሊቀ ሊቃውንት ንቡረ ዕድ አባ ተፈራ መልሴ አስተባባሪነት በምእመናን ርብርብና በ #ቅዱስ_አማኑኤል አከናዋኝነት ግንቦት 28 ቀን 1978 ዓ.ም ተጠናቆ ታቦተ ሕጉ ወደ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ገብቷል። #እንኳን_አደረሰን_መልካም_በዓል!
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
✝✞✝ እንኩዋን ለእናታችን "ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ገዳማዊት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝ +*" ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ "*+ =>ቅድስቷ እናታችን በነገድ እሥራኤላዊ ስትሆን የተወለደችው ኢየሩሳሌም ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ወላጆቿ ክርስቲያኖች በመሆናቸው በሚገባው ፈሊጥ አሳድገው ወደ ትምሕርት አስገቧት:: +አስተማሪዋ ገዳማዊ መነኮስ ነበርና ከተማ ውስጥ አያድርም:: አስተምሯት ዕለቱኑ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር እንጂ:: ዓመተ ክርስቶስ ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቃ ተማረች:: +አንድ ቀን እንደ ልማዷ ልትማር ብትጠብቀውም መምሕሯ ሊመጣ አልቻለም:: ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ መነኮሱን ልትጠይቅ : አንድም ልትማር ወደ በዓቱ ሔደች:: +በሩ ላይ ደርሳ ብታንኩዋኩዋም መልስም : የሚከፍትም አልነበረም:: ከውስጥ ግን ምርር ያለ የለቅሶ ድምጽ ተሰማት:: "ጌታ ሆይ! ይቅር በለኝ?" እያለ በተደጋጋሚ ይጮሃል:: ያ ደጉ መነኮስ ነበር:: +ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ በቅጽበት አንድ ሐሳብ መጣላት:: "እርሱ በንጽሕና እየኖረ ስለ ነፍሱ እንዲሕ ከተማጸነ እኔማ እንደምን አይገባኝ!" ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች:: የለበሰችውን ልብስ አልቀየረችም:: ቤተሰቦቿን አልተሰናበተችም:: ከቤቷ አተር በዘንቢል እና ውሃ በትንሽ እቃ ይዛ ወደ ጐልጐታ ገሰገሰች:: +ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ ወድቃ አለቀሰች:: ጸለየችም:- "ጌታ ሆይ! ነፍሴን ወደ ዕረፍት አድርሳት? ከክፉ ጠላትም ጠብቀኝ? ይሕንን አተርና ውሃ ለእድሜ ዘመን ሁሉ ባርክልኝ::" +ይሕን ብላ እየፈጠነች ከኢየሩሳሌም ተነስታ በእግሯ ቃዴስን : ሲናይ በርሃን አቁዋርጣ ግብፅ ደረሰች:: ምርጫዋ ብሕትውና ሆኗልና ልምላሜ ከሌለበት : ፀሐዩ እንደ ረመጥ ከሚፋጅበት በርሃ ገባች:: +በዚያም ከያዘችው አተር ለቁመተ ሥጋ እየበላች : ከውሃውም በጥርኝ እየተጐነጨች : ማንንም ሰው ሳታይ : በፍጹም ተጋድሎ ለ38 ዓመታት ቆየች:: የቀኑ ሐሩር : የሌሊቱ ቁር (ብርድ) ልብሷን ቆራርጦ ቢጨርሰው እግዚአብሔር ፀጉሯን አሳድጐ አካሏን ሸፈነላት:: +ጊዜ ዕረፍቷ ሲደርስ የቅዱሳንን ዜና የሚጽፈው ታላቁ አባ ዳንኤል ወደ እርሷ ደረሰ:: እንዳያት ተከተላት:: እርሷ ግን በተሰነጠቀ አለት ውስጥ ገብታ ተደበቀች:: አባ ዳንኤል በውጪ ሆኖ ተማጸነ:- "እባክህ አባቴ! ውጣና ባርከኝ" አለ:: ሴት መሆኗን አላወቀም ነበርና:: እርሷ ግን "ራቁቴን ነኝና አልወጣም" አለችው:: +ልብሱን አውጥቶ ሰጥቷት ወጥታ ተጨዋወቱ:: በፈቃደ እግዚአብሔር ዜናዋን ሁሉ አወቀ:: ወደ በዓቷ ዘወር ሲል በዘንቢል የሞላ አተር ተመለከተ:: ለ38 ዓመታት ተበልቶ ዛሬም ሙሉ ነው:: አባ ዳንኤል ይፈትነው ዘንድ ከአተሩ በደንብ በላለት:: ከውሃውም ጠጣለት:: ግን ሊጐድል አልቻለም:: +እያደነቀ "እናቴ ሆይ! ልብሴን ውሰጂው" ቢላት "ሌላ አዲስ አምጣልኝ" አለችው:: ይዞላት በመጣ ቀን ግን ተሠውራለችና አላገኛትም:: +አንድ ቀን ግን (ማለትም ግንቦት 28) አረጋውያን መነኮሳት መጥተው የገጠማቸውን ነገር ነገሩት:: እንዲሕ ሲሉ:- "ሰው ተመልክተን ወደ በዓቱ ስንገባ አተር በዘንቢልና ውሃ በመንቀል አገኘን:: ስንበላው ወዲያው አለቀ::" አባ ዳንኤል ነገሩን ገና ሳይጨርሱለት አለቀሰ:: +አተሩ አለቀ ማለት ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ አርፋለች ማለት ነውና:: አረጋውያኑ ግን ቀጠሉ:- "ከበዓቱ ስንወጣ በጸጉሯ አካሏ ተሸፍኖ ወደ ምሥራቅ ሰግዳ አርፋ አግኝተን ከሥጋዋም ተባርከን ቀበርናት" አሉ:: አባ ዳንኤል ዜናዋን ጽፎላት ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ታከብራታለች:: =>አምላካችን በቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን:: ከበረከቷም ያድለን:: =>ግንቦት 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ተጋዳሊት (ገዳማዊት) 2.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ሥጋው ቆዽሮስ የደረሰበት) 3.አባ መርቆሬዎስ ገዳማዊ 4.አባ ጌርሎስ (ጻድቅና ሰማዕት) 5."45" ሰማዕታት (የአባ ጌርሎስ ደቀ መዛሙርት) 6.ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት =>ወርኀዊ በዓላት 1.አማኑኤል ቸር አምላካችን 2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም : ይስሐቅና ያዕቆብ) 3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ 4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት) =>+"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
አርባሃራ መድኃኔዓለም ገዳም ~ ከአድስ አበባ በደብረ ብርሀን ሰሜን ሸዋ ከጣርማ በር ዋሻ 180 ኪ.ሜ አስፍልት ከጣርማ በር በስተ ቀኝ ወይም መንዝ መሀልሜዳ መንገድ በ65 ኪ.ሜ ይገም (ነፍሶ ከተማ) እንደደረሡ በ500ሜ. በእግር ወደ ዉስጥ በመጔዝ አርባሃራ መድኃኔዓለም ይደርሳሉ፤ በቦታው ሠው አይቀበርም ፥ዋሻ ነው፥በየቀኑ ትኩስ እሬሳ በንሥር እየተመሠሉ ይመጣሉ ማረፊያቸውም ዋሻ ውስጥ ነው።አፅሙም አይፈርሥም፤የተገነዙበት እንኳን ሳይቀር ምንም ሳይሆን እንዳለ ነው የሚታየው፤ፀጉር፤ፂማቸው፤የደም ሥራቸው እንኳን እንዳለ ነው የሚታየው።የሚረግፍ ምንም ነገር የለም። በህይወታችን ሽቶ የማያውቅ በዋሻው ውስጥ ግን የሚገርም ሽታ ይሸታል፤በዋሻው ውስጥ ማጠንት ሲጨስ ሲሸት ይታያል ።የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው።የተዋህዶ ልጆች ለማመን የሚያስቸግርም ቢሆንም በማየትም ማመን አለና ወደ እግዚአብሔር ፊታችንን በመመለስ ታምራቱን እንመልከት። መንዝ ማማ ምድር ለዘብር ገብርኤል ጉዞ በሚያስቡበት ወቅት ከእርሡ ብዙም አይርቅም።ከሞላሌ በ8 ኪ.ሜ ርቀትም ላይ ይገኛል።ሀለቱንም በአንድ ቀን በመጎምኘት መንፈሳዊ ደስታዎን መቀበል ይችላሉ። አርባራ ማለት፦ 40 ቅዱሳንና አብነሃራ የሚባሉ ከግብፅ መጥተው በ9ኛው ክፍለ ዘመን የመሠረቱት የግብፃውያን ገዳም ነው። በኢትዮጵያ ሁለት አብነሃራ የሚባሉ የፃድቅ ገዳሞች አሉ። 1ኛ፦ በ 9ኛው ክፍለ ዘመን ግብፃዊ አብነሃራ (መንዝ) 2ኛ፦በ 15ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጰያዊ አብነሃራ (ጎጃም ) የሚገኙ ናቸው። መንዝ የሚገኘው አብነሃራ ገዳም ዋሻ ሲሆን ዋሻው የ6 ሠአት የእግር መንገድ አለው።በውስጡም ትልቅ ባህረ መቅደስ፤ቅኔ ማህሌት፤የነዋይ ቅዱሳት መቀመጫ፤የምግብ ማብሠያ፤ዕቃ ቤት፤የእንግዳ ማረፊያ፤አፅመ ቅዱሳን ምንም ያልፈረሡ ማንነታቸው የሚለይ በውስጡ ይገኛል። ለአብነሃራም ጌታችን መድሀኒታችን እየሡስ ክርስቶስ የሠጣቸው ቃል ኪዳን፦ ~ ++++_ላልምረው ቦታዬን አላስረግጠውም ወንድ ልጅ 40 ቀን ሴት ልጅ 80 ቀን ልጆች አረጋችዋለሁ። +++_ቦታውን የረገጠ ሀጢአት ቢሠራም ይቅር እልዋለሁ ++++_አልወልድ ያለውን ያለችውን ልጅ እሠጣለሁ ++++_እኔን ብለው ይህ አለም በቃኝ ብለው በበርሀ በዱር በገደል በየገዳሙ ያሉ መነኮሳት የማረፊያ ግዞያቸው በደረሠ ሠአት ሲሞቱ አፅማቸው በንሥር መጥቶ ሳይፈርስ ሳይበሠብስ እንዳለ ምንም ሳይሆን አንተና 40 ቅዱሳን በለፈለፍችሁት ዋሻ 40 የሚሠወሩበት እና አንተ አብነ ሃራ በምታርፍበትና አፅምህ በምታርፍበት በዚች ዋሻ የቅዱሳንም አፅም እንዲያርፍ ቃል ገብቼልሀለሁ ብሎአቸዋልብ እግዚአብሔር አምላክ። እኛም የአንተ ቃል ኪዳን በሁላችንም ላይ ይደርብን እንላለን፤ እግዚአብሔር አምላክ ለዚህ ገዳም ለማየትና ቅዱስ ረድኤቱን ለመቀበል ያብቃን፤አሜን https://t.me/Etu_zewdu