tgindex
ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media – FEM

ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media – FEM

Статистика
@Fikureegzi4Видеоитальянский

በደ/ነ/ቅ/ዮሐንስ እና መ/ጎ/ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው https://www.facebook.com/Fikureegzi4 √ ዌብሳይታችን www.fikureegzi.com √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/channel/UCXceln4wpQhIVS42O02kAWg ለሀሳብ አስተያየት ይህንን ይጠቀሙ!! @FikureEgzi04

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
15
Всего постов
30
Тип
открытый
Язык
итальянский
Категория
Видео
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
9 895
+1 за 4 дн.
Сутки
+4
+0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 430
30 постов
Вовлечённость
14,5%
к подписчикам
Постов в день
2,1
всего 30
Упоминаний
3
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 101
1/48двое суток
1 261
1/72трое суток
1 360

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ጾመ ፍልሰታ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም 🟢 በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ ምንባባት 🟢 ቅድመ ወንጌል የሚባል ምስባክ እና 🟢 የእለቱ ወንጌል

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 14 авг.1 00112

    አዲስ ለተመደቡት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ አቀባበል ተደረገላቸው። በመርሐ ግብሩ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክልት ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ሰላም ዶ/ር አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ሐላፊ፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣ የሀገረ ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሠራተኞች ተገኝተዋል። © የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት

  • 14 авг.1 242131

    ጾመ ፍልሰታ ነሐሴ 8ቀን 2018 ዓ.ም 🟢 በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ ምንባባት 🟢 ቅድመ ወንጌል የሚባል ምስባክ እና 🟢 የእለቱ ወንጌል

  • 13 авг.1 38811

    без подписи

  • 13 авг.1 3913111

    የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው እንዲያገለግሉ መደበ። መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ የቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ሲሆን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ዋና ሥራ አስኪያጅነት እንዲያገለግሉ ተመድበዋል ። መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱ አደራሽ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ይጠበቃል ።

  • 13 авг.1 432222

    ጾመ ፍልሰታ ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጽንሰታ ለማርያም 🟢 በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ ምንባባት 🟢 ቅድመ ወንጌል የሚባል ምስባክ እና 🟢 የእለቱ ወንጌል

  • 12 авг.1 503224

    без подписи

  • 12 авг.1 483156

    ነሐሴ 7 ጽንሰታ ለማርያም " አሁንም የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆችና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማህበሮች ሆይ ይኽቺን የተባረከችና የተመረጠች ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናመስግናቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግልን የተባረከችዋን ፍሬ ያፈራችበትን ንጽሕት የምትኾን የሩካቤያቸው ዕለት እንደምን ያለች ዕለት ናት? ከይሁዳ ወገን ለኾነችው ንጽሕት ርግብ መፀነስ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ የጾታዊ ተዋሕዷቸው ቀን ይኽቺ እንዴት ያለች የተመረጠች ቀን ናት፤ ለንጉሥ ማደሪያ አዳራሽ መመሥረት የተደረገባት የደስታ ቀን እንዴት ያላች ቀን ናት "          አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/መጽሐፈ አርጋኖን ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው። ይህ ጻድቅም ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር የእስራኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና ። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር ። ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ። የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷ የሚበራላችውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች። በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ወለደቻት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ኢያቄምና ሐና ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

  • 12 авг.1 469262

    ጾመ ፍልሰታ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ ምንባባት ፣ ቅድመ ወንጌል የሚባል ምስባክ እና የእለቱ ወንጌል

  • 11 авг.1 925253

    ጾመ ፍልሰታ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ ምንባባት ፣ ቅድመ ወንጌል የሚባል ምስባክ እና የእለቱ ወንጌል

  • 10 авг.1 891651

    " ወንጌልን ለመጻፍ ለበረታው ክንድህና የአርያምን ኃይል ለተቀበለው ክርንህ ሰላም እላለው ዮሐንስ ሆይ ለከንቱው የዓለም እንጀራ ስሽቀዳደም መንፈሳዊውን መብል አላገኘሁምና የተሰውረውን መብልና የብርሃን መጽሐፍ ስጠኝ "               መልክአ ቅዱስ ዮሐንስ

  • 10 авг.1 901171

    ጾመ ፍልሰታ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ ምንባባት ፣ ቅድመ ወንጌል የሚባል ምስባክ እና የእለቱ ወንጌል

  • 9 авг.2 123199

    " ተላዌ ጴጥሮስ (የጴጥሮስ ተከታይ)  "     የሙሉ ሰዓት ተውኔት   📆 ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም          ⌚️ ከቀኑ 11:00 ሰዓት                 ⛪️ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ                                       💵 መግቢያ :– 100 ብር                                  👉   ትኬቱን ባሉበት ቦታ በቴሌ ብር 09 01 04 44 44 👉 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  1000658449633  መቁረጥ ይችላሉ‼   ✨  "አቡነ ሚካኤል ከአፈረ ዋናት እስከ ጎሬ"✨

  • 8 авг.1 958207

    ቀድሞስ የክብር ባለቤት የጌታችን የመኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ኾነው እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ተሠውራባቸው እንዴት ዝም ብለው ይቀመጣሉ? ሁለት ሱባዔ ካደረሱ በኋላም የነገሩትን የማይረሳ፣ የለመኑትን የማይነሳ እግዚአብሔር አምላካችን ጸሎታቸውን ሰምቶ ነሐሴ ፲፭ ቀን የእመቤታችንን ሥጋ ሰጥቷቸው በክብር ገንዘው በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል፡፡ በሦስተኛው ቀንም እንደ ልጇ እንደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይታ ተነሥታለች፡፡ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ፤ እንደ ልጇ ትንሣኤ” ያሰኘውም ይህ ታሪክ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ሲሰብክ ቆይቶ ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ እመቤታችን ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ወደ ሰማይ ስታርግ አገኛት፡፡ በዚህ ጊዜ “ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ፤ ዛሬ ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁን?” ብሎ ትንሣኤዋን ባለማየቱ ሀዘን ስለ ተሰማው 140 ከደመናው ይወድቅ ዘንድ ወደደ፡፡ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” እንዲል፡፡ እመቤታችንም “አይዞህ አትዘን፤ ባልንጀሮችህ ሐዋርያት ያላዩትን ትንሣኤዬን አንተ አይተሃል” ብላ ከሙታን ተለይታ መነሣቷንና እንዲነግራቸው አዝዛ የያዘቸውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው፡፡ እርሱም ትዕዛዟን ተቀብሎ በክብር ከተሰናበታት በኋላ ወደ ሐዋርያት ሔዶ እንዳልሰማ እንዳላየ መስሎ “የእመቤታችን ነገር እንደምን ኾነ?” አላቸው፡፡ እነርሱም “አግኝተን ቀበርናት” ሲሉት “ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴት ይኾናል?” አላቸው፡ ፡ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ከዚህ በፊት የክርስቶስን ትንሣኤ መጠራጠሩን ጠቅሶ እየገሠጸ ስለ እመቤታችን መቀበር እነርሱ የሚነግሩትን ኹሉ መቀበል እንደሚገባው ለቅዱስ ቶማስ አስረዳው፡፡ ቅዱስ ቶማስም የያዘውን ያውቃልና ጸጥ ብሎ ሲሰማው ቆየ፡፡ ቅዱስ ቶማስም “አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ስታርግ አግኝቻታለሁ” ብሎ የሰጠችውን ሰበን ለሐዋርያት ሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም በእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት እየተደሰቱ ሰበኑን ለበረከት ተካፍለውታል፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስተምሩን በቅዳሴ ጊዜ ሠራዒ ዲያቆኑ በሚይዘው መስቀል ላይ የሚታሠረው መቀነት መሰል ልብስ፤ እንደዚሁም አባቶች ካህናት በመስቀላቸው ላይ የሚያደርጉት ቀጭን ልብስና በራሳቸው የሚጠመጥሙት ነጭ ሻሽ የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው፡፡ በዓመቱ ቅዱሳን ሐዋርያት “ቶማስ የእመቤታችን ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አይቶ እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን?” ብለው ከየሀገረ ስብከታቸው ተሰባስበው ጌታችን ሥጋዋን እንዲሰጣቸው በጠየቁበት በዚሁ ወቅት ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምረው ሱባዔ ቢይዙ ጌታችን ልመናቸውን ተቀብሎ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችንን መንበር፤ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፤ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ እመቤታችንንም ሐዋርያትንም አቍርቧቸዋል፡፡ እነርሱም እመቤታችንን በዓይናቸው ከማየት ባሻገር አብረው ሥጋውን ደሙን ተቀብለዋል /ትርጓሜ ውዳሴ ማርያም/፡፡ ይህንን ትምህርት መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከነሐሴ ፩-፲፭ ያለው ሁለት ሱባዔ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ኾኖ በምእመናን ዘንድ መጾም እንደሚገባው ሥርዓት ሠርተውልናል /ፍት.ነገ.አን.፲፭/፡፡ ይህ ጾምም “ጾመ ማርያም (የማርያም ጾም)” ወይም “ጾመ ፍልሰታ ለማርያም (የማርያም የፍልሰቷ ጾም)” እየተባለ ይጠራል፡፡ ‹ፍልሰት› የሚለው ቃልም “ፈለሰ ሔደ፤ ተሰደደ” ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ትርጕሙም ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ አገር መሔድን ያመለክታል፡ ፡ ‹ፍልሰታ ለማርያም› ሲልም እመቤታችን 141 ቅድስት ድንግል ማርያም ካረፈች በኋላ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መወሰዷን የሚያስረዳ መልእክት አለው፡፡ በጾመ ፍልሰታ በቤተ ክርስቲያናችን በየቀኑ በማኅሌቱ፣ በሰዓታቱና በቅዳሴው በሚደርሰው ቃለ እግዚአብሔር ነገረ ማርያም ማለትም የእመቤታችን ከመጸነሷ ጀምሮ እስከ ዕርገቷ ድረስ ያለው ታሪኳ፣ ለአምላክ ማደሪያነት መመረጧ፣ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ክብሯ፣ ርኅርራኄዋ፣ ደግነቷ፣ አማላጅነቷ፣ ሰውን ወዳድነቷ በስፋት ይነገራል፡፡ እመቤታችንን ከሚያወድሱ ድርሳናት መካከልም በተለይ ምሥጢረ ሥላሴን፣ ምሥጢረ ሥጋዌንና ነገረ ድኅነትን ከነገረ ማርያም ጋር በማዛመድ የሚያትተው ቅዳሴ ማርያም፤ እንደዚሁም ነገረ ድኅነትን ከምሥጢረ ሥጋዌ (ከነገረ ክርስቶስ) እና ከነገረ ማርያም ጋር በማመሣጠር የሚያትተው ውዳሴ ማርያምም በስፋት ይጸለያል፤ ይቀደሳል፤ ይተረጐማል፡፡ በሰንበታት የሚዘመሩ መዝሙራት፤ በየዕለቱ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለተዋሕዶ በእግዚአብሔር መመረጧን፣ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን፣ ክብሯን፣ ቅድስናዋን፣ ንጽሕናዋን የሚያወሱ ናቸው፡፡ በጾመ ፍልሰታ ባሕታውያን ብቻ ሳይኾኑ ዓለማውያንም በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእመቤታችን አማላጅነት የሰይጣንን ፈተና ድል ለማድረግ እንዲቻላቸው ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በየገዳማቱና በየአብያተ ክርስቲያናቱ በዓት አዘጋጅተው፣ ሱባዔ ገብተው፣ ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው አስገዝተው ይጾማሉ፤ ይጸልያሉ፡ ፡ እንደዚሁም ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበላሉ፡፡ እኛም የእመቤታችንን ዕረፍትና ትንሣኤ በማሰብ ከልጇ ከወዳጇ የሚገኘውን ጸጋና በረከት ተስፋ በማድረግ የአባቶቻችንንና የእናቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በየዓመቱ ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን፤ የምንችል ደግሞ አስቀድሰን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንቀበላለን፡፡ በተጨማሪም ይህ ጾም ለእመቤታችን ያለንን ፍቅርም የምንገልጽበት ወቅት ነው፡፡ በተለይ ኦርቶዶክሳውያን ሕፃናት በአብዛኛው ትምህርተ ወንጌል የሚማሩት፤ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የሚቀበሉት በዚህ በጾመ ፍልሰታ ነው፡፡ ኹላችንም ጌታችን በስሙ ሁለትም ሦስትም ኾነን ለጸሎትና ለመልካም ሥራ ብንሰባሰብ እርሱ በመካከላችን እንደሚገኝ የገባልንን ቃል ኪዳን መሠረት በማድረግ /ማቴ.፲፰፥፳/ በጾመ ፍልሰታ ሳምንታት በጌታችን፣ በእመቤታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት ስም በቤተ ክርስቲያን ተሰባስበን ቅዱሳት መጻሕፍትን ከመማር ባሻገር ብንጾም፣ ብንጸልይ፣ ብናስቀድስ፤ እንደዚሁም ሥጋውን ደሙን ብንቀበል በበረከት ላይ በረከትን፤ በጸጋ ላይ ጸጋን እናገኛለን፡፡ በኋላም ሰማያዊውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ እንችላለን፡፡ ነገር ግን በሕግ የተከለከለ እስኪመስል ድረስ በዚህ ወቅትም ኾነ በሌላ ጊዜ ሥጋውን ደሙን የሚቀበሉ ወጣቶች ጥቂቶች ናቸው፡፡ ስለዚህም አረጋውያንና ሕጻናት ብቻ ሳይኾኑ ወጣቶችም ጭምር የመቍረብና የመዳን ክርስቲያናዊ መብት እንዳለን በመረዳት ራሳችንን ገዝተን፣ ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይገባናል፡፡ አምላካችን በማይታበል ቃሉ “ሥጋዬን የሚበላ፤ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው” በማለት ተናግሯልና /ዮሐ.፮፥፶፬/፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና በረከት አይለየን።

  • 8 авг.1 9345

    без подписи