tgindex
ሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሚዲያ

ሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሚዲያ

Статистика

የብፁዕ አቡነ ኤርምያስ እና የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ እንዲሁም የሌሎች መምህራን ትምህርቶች፣ ስብከቶችና ተግሳጾች በተጨማሪም በሀገረ ስብከቱ የሚከወኑ ዓበይት ክንውኖች የሚተላለፉበት የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የቴሌግራም ቻናል ነው። የቻናሉ ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በመጋበዝ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት ያፋጥኑ።

Последний пост
6 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
6 129
+4 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
822
20 постов
Вовлечённость
13,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
738
1/48двое суток
845
1/72трое суток
912

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.917101

    видео или голосовое, без подписи

  • አድባራት ዘመኑን የዋጁ አገልጋዮችንና ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው ያወቁ ምእመናንን ለማፍራት በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አሳሰቡ፡፡ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ) በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የወልድያ ከተማ ቤተ ክህነት አስተዳደር 45ኛ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም አከናውኗል። ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መሪነት የተካሄደ ሲሆን የተጠናቀቀው ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ቀርቦ ተሳታፊዎች ተወያይተውበታል። ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት የሥራ መመሪያና ቃለምእዳን ባሳለፍነው ዓመት በርካታ ችግሮች ቢገጥሙንም አድባራት ችግሮችን ተቋቁመው ያከናወኗቸው ተግባራትና የተመዘገበው ስኬት የሚያስመሰግንና የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በ2019 ዓ.ም በትኩረት ሊከናወኑ ይገባል ባሏቸው የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ዙሪያ አባታዊ መመሪያ ያስተላለፉ ሲሆን የአብነት ትምህርት ቤቶችን በመከታተል፣ በመደገፍና በማሰልጠን ዘመኑን የዋጁ አገልጋዮችን ማፍራት፤ የሰንበት ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋትና አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት በአግባቡ በመተግበር አውቀው የሚያመልኩ ምእመናንን መፍጠር እንደሚገባ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ ቤተክርስቲያኗ የተገበረችውን የአሥር ዓመት መሪ እቅድ በአድባራት ተግባራዊ ለማድረግ መደበኛ አገልጋዮችን ሊቀጥሩ እንደሚገባ ያሳሰቡት ብፁዕነታቸው ከምእመናን ተሰብስቦ በአድባራት የሚቀረው ገቢ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን መቆጣጠርና መከታተል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የከተማ ቤተክህነት አስተዳደሩ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር የምክክር ጉባኤ በማዘጋጀት በቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ አገልግሎቶች ላይ ውይይት ለማድረግ በእቅድ እንዲይዙ አሳስበዋል፡፡ በጉባኤው የሀገረ ስብከቱ የልዩ ልዩ ክፍል ኀላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት የተሳተፉ ሲሆን በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አድባራት የተዘጋጀላቸውን የዕውቅና ሽልማት በብፁዕነታቸው ቡራኬ ተቀብለዋል። ─── ~ “#ቃሉን_ለማገልገል_እንተጋለን” ~ ~ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ~ ─── የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን #ይወዳጁ_ለሌሎችም_ያጋሩ፦ ቴሌግራም~ https://t.me/NWDnews ዩቲዩብ~ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia ድረገጽ~ https://eotc-nw.org ፌስቡክ~ https://www.facebook.com/EOTCNWD Tiktok~ https://www.tiktok.com/@eotc.north?_t=ZM-8ukkHRXMOYg&_r=1

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • የራያ ቆቦ ወረዳ ቤተክህነት በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዓመት ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ። ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ማዲያ) በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የራያ ቆቦ ወረዳ ቤተክህነት 45ኛ ዓመታዊ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል። ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታዊ መሪነት በቆቦ ከተማ ተካሂዷል። የወረዳ ቤተክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ተስፋሚካኤል ፈለቀ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ሪፖርትና የቀጣይ ዓመት እቅድ አቅርበዋል። ወረዳ ቤተክህነቱ በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዓመት ለገዳማት፣ ለአብነት ትምህርት ቤቶችና ለግለሰቦች 5 ሚሊዮን ሁለት መቶ ሽህ ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ ማደረጉን በሪፖርቱ ገልጿል። ከአፈጻጸም ሪፖርቱ በተጨማሪ በቀጣይ ዓመት ወረዳ ቤተክህነቱ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የሚያከናወናቸው ተግባራት በመሪ እቅዱ 16 ግቦች መሠረት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ ወረዳ ቤተክህነቱ፣ ገዳማትና አድባራት ትኩረት ሰጥተው በሚያከናውኗቸው ተግባራት ዙሪያ አባታዊ የሥራ መመሪያ አስተላልፈዋል። የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ማቋቋምና ማጠናከር፣ የሰበካ ጉባኤያት ምርጫና የአገልግሎት ዘመን፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማጠናከርና የምስጢራተ ቤተክርስቲያን አፈጻጸም፣ የገንዘብ አስተዳደር፣ የበዓላት አከባበርና ሌሎች ትኩረት የሚደረግባቸው ተግባራትን በዝርዝር አስገንዝበዋል። አድባራት የትርጓሜ መጻሕፍት ሊቃውንትንና የነገረ መለኮት ምሩቃንን በመቅጠር ለምእመናን ትምህርተ ሃይማኖትን በእድሜ፣ በጾታና በእውቀት ደረጃቸው እንዲያስተምሩ አሳስበዋል። ለአብነት ትምህርት ቤቶች ግብዓት በማሟላትና ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመስጠት ቤተክርስቲያኗን ሊመሩ የሚችሉ ኹለገብ ሊቃውንትን ማፍራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። በአጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤው የሀገረ ስብከት ልዑካን፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤያት ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አድባራት ወረዳ ቤተክህነቱ ያዘጋጀላቸውን ሽልማት ከብፁዕነታቸው ተረክበዋል። ─── ~ “#ቃሉን_ለማገልገል_እንተጋለን” ~ ~ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ~ ─── የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን #ይወዳጁ_ለሌሎችም_ያጋሩ፦ ቴሌግራም~ https://t.me/NWDnews ዩቲዩብ~ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia ድረገጽ~ https://eotc-nw.org ፌስቡክ~ https://www.facebook.com/EOTCNWD Tiktok~ https://www.tiktok.com/@eotc.north?_t=ZM-8ukkHRXMOYg&_r=1

ሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሚዲያ — tgindex