tgindex
✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

Статистика

በዚህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰንበት ትምህርት ቤት የሚሰጠውን ተከታታይ ትምህርት በጉባኤ ተገኝተው መማር ላልቻሉ በሃገር ውስጥም ከሃገራችንም ውጪ ለሚኖሩ ምዕመናን መማማሪያ የተከፈተ ነው። t.me/betgubae የፌስቡክ ኣድራሻዬንም ይጎብኙ https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
8 022
+21 за 4 дн.
Сутки
+12
+0,15%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 453
21 постов
Вовлечённость
30,6%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
865
1/48двое суток
991
1/72трое суток
1 069

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 12 авг.9762226

    ✥✥✥ ፅንሰታ ለእግዝእትነ ✥✥✥ 👉 ነሐሴ 7 እመቤታችን የተፀነሰችበት ነው። ቤተክርስቲያናችንም ከምታከብራቸው ዓበይት በዓላት መካከልም ነው። 👉  አባ ሕርያቆስ ስለ እመቤታችን የመፀነስዋን ነገር ሲናገር ድንግል ሆይ በልተው ጠጥተው ጾር ሲጸናባቸው በሚያደርጉት ግንኙነት የተፀነሽ ኣይደለሽም ጋብቻ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ነው ብዙ ተባዙ ባለው ፈቃድ በሩካቤ ዘበሕግ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ በማለት ያደንቃል! 👉  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም " የእግዚኣብሔር ልጆች የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ማኅበር እንግዲህ ይህችን ንጽሕት ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናድንቃቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግል የተባረከችይቱም ፍሬ የተፈራችባት የሩካቢያቸው ንጽሕት ቀን እንደምን ያለች ናት፡፡ ከይሁዳ ወገን የምትሆነውን ንጽሕት ርግብ ለመፀነስሽ ለእግዚኣብሔር ፈቃድ የሆነው የመገናኘታቸው ቀን እንደምን ቅድስት ናት፡፡ የንጉሥ አዳራሽ የምትሆን የርሷ መሠረት የተመሠረተባት ዕለት እንደምን ደስ ያለች ናት፡፡ ➛   ነቢዩ ኢሳይያስም እንዲህ አለ " ከዕሤይ ሥር በትር ትወጣለች፡፡ ከግንዱም አበባ ይወጣል በላዩም የእግዚኣብሔር መንፈስ ያርፍበታል፡፡ " (ኢሳ ፲፩፣ ፩፣ ፪) - ይኸውም ትንቢት በጽዮን የተነገረው በኢየሩሳሌም የተሰበከው በነቢያት አንደበት የተሰማው በሌዋውያን እጅ በዕብራይስጥ ልሳን የተጻፈው ሊፈጸም የክህነት በትር በቀለችልን፡፡ የመንግሥትና የኃይል የሕይወትና የመድኃኒት የሃይማኖት የንጽሕና የቅድስና በትር የኃይል የመዊዕ በትር በቀለችልን፡፡ ➛  "ከዕሴይ ዘር በትር ትወጣለች፤ ከግንዱም አበባ ይወጣል የሚለው እንደተጻፈ፤ ያሰበውን ለማድረግ የሚከለክለው የለም፤ ከኢያቄም ኣብራክ ተከፍላ በሐና ማህፀን ከተፀነሰች ከቅድስት ድንግል የትውልድ ዘር በቀር የበትር ከሥሩ መውጣት ምንድነው? የእመቤታችን የማርያም ኣባቷ ኢያቄም ከዕሴይ ዘር ነውና፤ ዳግመኛም ከኢያቄም ሴት ልጁ የመለኮት ሰው መሆን በቀር የአበባ የግንድ መውጣት ምንድነው?" 👉   የልደትዋን ነገር አያይዞ ሲናገርም ፦ በኢያቄም በኣባትሽ ወገን የንጉሥ ልጅ ሆይ አመሰግንሻለሁ፡፡ የዳዊት ልጅ ነሽና የሊቀ ካህናት ልጅ ሆይ ውዳሴሽን አቀርባለሁ፡፡ ከእናትሽ ወገን የኣሮን ልጅ ነሽና፡፡ ገናንነትሽንም አደንቃለሁ፡፡ የነገድሽን ወገን አመሰግናለሁ ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ተገኝተሻልና፡፡ ➛  ስለዚሀም የነጎድጓድ ልጅ ነሽ እልሻለሁ ያዕቆብና ዮሓንስን ኣኔሬጌስ ብሎ እንደጠራቸው ይኸው የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፡፡ ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ናቸውና፡፡ ስለዚህም የነጎድጓድ ልጆች ተባሉ፡፡ ➛  እኔም የነጎድጓድ ልጅ ነሽ ኣልሁሽ፡፡ የመወለድሽ ድምፅ (ወሬ) እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ይሰማልና፡፡  ከሁለቱ ከተቀቡት ነገድ በነቢያት አለቃ በሙሴ እጅ ለክህነት ከተቀባው ከኣሮን ቤት፡፡ በሳሙኤል እጅ ለመንግስት ከተቀባው ከዳዊት ዘር፡፡ (፩ ሳሙ ፲፮፣ ፲፫) (ዘሌዋ ፰፣ ፲፪)   👉  ደግሞም ያንበሶች ልጅ ነሽ እልሻለሁ እንደ አንበሳ ግልገል ጩኸት እንደ ሴትም አንበሳ ድምፅ የልደትሽ ወሬ ይሰማልና፡፡ አባቱ ያዕቆብ ይሁዳን ያንበሳ ግልገል ብሎታልና፡፡ (ዘፍጥ ፵፣ ፱፣ ፱) ➛ ስለዚህም ያንበሶች ልጅ እልሻለሁ፡፡ ሰሎሞን እንደተናገረ እንዲህ ሲል ኣንቺ ሙሽራ ከሊባኖስ ጋራ ነይ ከሊባኖስ ጋራ ነይ፡፡ ከአንበሶችም ጉድጓድ ወጥተሽ ነይ፡፡ (መኃ ፬፣ ፰) ከተመረጠ ነገዱ የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ወሬ እጅግ ግሩም ነው፡፡ በማለት ያደንቃል። ይቆየን ➕ ፍቅርዋን ከልቡናችን ጣዕመ ምስጋናዋንም ከአንደበታችን ታሳድርልን አትለይብን። ➛ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ( አባ ሕርያቆስ ) ➛ መጽሓፈ አርጋኖን ፣ መጽሐፈ ምሥጢር (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ) ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ) https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71 http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ)

  • 8 авг.1 9201517

    #፯ቱ_ዕለታት_ለእመቤታችን_ምሳሌዋ_ናቸው ➕ በዕለተ እሁድ ትመሰላለች - በዕለተ እሁድ አሥራወ ፍጥረታት አራቱ ባሕርያት ተገኝተዋል። ከሷም ዘኮነ ምክንያተ ፍጥረት በህላዌሁ እንዲለው አሥራወ ፍጥረት ጌታ ተገኝቷልና ። ➕ በዕለተ ሠኑይ ትመሰላለች - በዕለተ ሠኑይ ከዚህ ምድር እስከ ብሩህ ሰማይ መልቶ የነበረውን ውሀ ከሶስት ከፍሎታል፣አንዱን እጅ ከላይ ሰቅሎታል ሐኖስ ነው አንዱን እጅ በዙሪያው ወስኖታል አንዱን እጅ አጽንቶ የብርሃን ማኅደር አርጎታል። ዕለቲቱ የሱዋ ጠፈር ከሱዋ የነሣው ሥጋ ብርሃን የጌታ ምሳሌ። ➕ በዕለተ ሠሉስ ትመስላለች - በዕለተ ሠሉስ ለታብቀል ምድር ሐመልማለ ሣዕር ዘይዘራዕ በበዘርዑ ወበበዘመዱ በበአርአያሁ ወበአምሳሊሁ ባለ ጊዜ በእጅ የሚለቀሙ አትክልት በማጭድ የሚታጨዱ አዝርዕት በምሳር የሚቆረጡ ዕፀዋት ለሥጋውያን ምግብ የሚሆኑ ተገኝተዋል። የመንፈሳውያን ምግብ የሚሆን ጌታም ከሱዋ ተገኝቷልና ። ➕ በዕለተ ረቡዕ ትመሰላለች - በዕለተ ረቡዕ በይቁሙ ብርሃናት በገጸ ማይ ካለ ጊዜ ለሥጋውያን ምግብ የሚሆኑ ፀሓይ ጨረቃ ከዋክብት ተገኝተዋል ። ለመንፈሳውያን ምግብ የሚሆን ጌታ ከሱዋ ተገኝቷልና ። ➕ በዕለተ ሐሙስ ትመሰላለች - በዕለተ ሐሙስ ለታውጽዕ ባሕር ዘቦ መንፈሰ ሕይወት ባለ ጊዜ በልባቸው የሚሳው በእግራቸው የሚሽከረከሩ በክንፋቸው የሚበሩ በደመ ነፍስ ሕያዋን ሁነው የሚኖሩ ፍጥረታት ተገኝተዋል። በልባቸው የሚሳቡ የሰብአ ዓለም በእግራቸው የሚሽከረከሩ ከትሩፋት ወደ ትሩፋት የሚሄዱ የባሕታውያን በክንፋቸው የሚበሩ ተመስጦ ያላቸው የሰማዕታት ምሳሌ። ዕለቲቱ የሱዋ ባሕር የጥምቀት ምሳሌ ። - > ደመ ነፍስ ከሌላት ባሕር በደመ ነፍስ ሕያዋን የሚሆኑ ፍጥረታት እንደተገኙ ለምዕመናን የድኅነት ምክንያት የሚሆን ጌታ የሴቶች ልማድ ከሌለባት ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ለመገኘቱ ምሳሌ ነው። ➕ በዕለተ ዓርብ ትመሰላለች ከዕለተ ዓርብ በኵረ ፍጥረት አዳም ተገኝቷል ዳግማይ አዳም ጌታም ከሱዋ ተገኝቷልና ። ➕ በዕለተ ቀዳሚት ትመሰላለች በዕለተ ቀዳሚት ሥጋዊ ዕረፍት ተገኝቷል ወአእረፈ እግዚእነ እምኩሉ ግብሩ ዘአኃዘ ይግበር እንዲል ከሱዋም የመንፈሳውያን ዕረፍት ጌታ ተገኝቷልና ። ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ) https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71 http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ)

  • 6 авг.1 9921322

    ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - 1ኛቆሮ. 5፥11፦ ወይእዜኒ ጸሐፍኩ ለክሙ ከመ ኢትደመሩ፡፡ - 1ኛዮሐ. 2፥14፦ ጸሐፍኩ ለክሙ አበው እስመ አእመርክዎ - ሓዋ.ሥራ 12፥18 ፦ ወጸቢሖ ተሀውኩ ሠገራት፡፡ - ምስባክ መዝ 44፥16-17፦ ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ፡፡ ወትሠይሚዮሙ መላእክተ ለኵሉ ምድር፡፡ ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ - ወንጌል ሉቃስ.6፥20፦ ወውእቱሰ አንሥአ አዕይንቲሁ፡፡ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ➕ ነሐሴ 12 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ቅዱስ ሚካኤል አስተርአዮ ለቈስጠንጢኖስ ወነግሠ ቈስጠንጢኖስ በሮሜ ወ፳፻ ሰማዕታት ማኀበራነ ፋሲለደስ፡፡ - ምስባክ ዘነግህ መዝ 137፥1-2፦ በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ፡፡ ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ፡፡ ወእገኒ ለስምከ፡፡ - ወንጌል ማቴዎስ 25፥31 ወአመ ይመጽእ ወልደ እጓለ እመሕያው፡፡ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - 1ኛቆሮ.9፥17 :- ወአመሰ ዘእምፈቃድየ ገበርክዎ ለዝንቱ፡፡ - ይሁዳ. 1፥8፦ ወከማሁ እሉኒ እለ በሕልሞሙ ይጌምኑ፡፡ - ሓዋ.ሥራ 24፥1 :- ወአመ ኀሙስ ዕለት ወረደ ሐናንያ - ምስባክ መዝ 71፥1-2፦ እግዚኦ ኵነኔከ ሀቦ ለንጉሥ፡፡ ወጽድቀከኒ ለወልደ ንጉሥ፡፡ ከመ ይኰንኖሙ ለሕዝብከ በጽድቅ፡፡ - ወንጌል ማቴዎስ. 22፥1 ፦ ወአውሥአ ኢየሱስ ዳግመ ወነገረ በምሳሌ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ፣ አው (ወይም) ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ፡፡ ➕ ነሐሴ 13 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- በዓለ ደብረ ታቦር ወልደቱ ለሙሴ ወብንያም ወጋልዮን መስተጋድል፡፡ - ምስባክ ዘነግህ መዝ 67፥15-16፦ ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል፡፡ ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉዓን፡፡ ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኀድር ውስቴቱ፡፡ - ወንጌል ማቴዎስ.17፥1፦ ወእምድኀረ ስሱ መዋዕል ነሥኦሙ ኢየሱስ፡፡ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - ዕብራው.11፥23 :- በተአምኖ ተወሊዶ ሙሴ፡፡ - 2ኛጴጥ. 1፥15፦ ወዓዲ እጔጕዕ ከመ ተሀሉ ኀቤክሙ፡፡ - ሓዋ.ሥራ 7፥44፦ ወደብተራ ስምዕ እንተ ነበረት ኀበ አበዊነ - ምስባክ መዝ 88፥12-13፦ ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥ ወይሴብሑ ለስምከ፡፡ መዝራዕትከ ምስለ ኃይል፡፡ - ወንጌል ሉቃስ.9፥28 ፦ ወእምድኀረ ዝንቱ ነገር አመ ሳምንት ነሥኦሙ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ፣ አው (ወይም) ዘዳዮስቆሮስ፡፡ ➕ ነሐሴ 14 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- በዓለ መስቀል ወባስሊቆስ ሰማዕት ወድምጥያ ሰማዕት ገባሬ ተአምር ወዮሐንስ ወስምዖን አኃው ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - 1ኛቆሮ. 1፥10፦ አስተበቍዐክሙ አኃዊነ በስሙ ለእግዚእነ - ያዕቆብ. 1፥12፦ ወብፁዕ ብእሲ ዘይትዔገሣ ለእኪት፡፡ - ሓዋ.ሥራ 10፥30 ፦ ወይቤሎ ቈርኔሌዎስ ረቡዐ ዮም፡፡ - ምስባክ መዝ 43፥4-5 ፦ ዘአዘዝከ መድኃኒቶ ለያዕቆብ፡፡ ብከ ንወግዖሙ ለኵሎሙ ፀርነ፡፡ ወበስመከ ነሐስሮሙ ለእለቆሙ ላዕሌነ - ወንጌል ማቴዎስ.17፥14፦ ወበጺሖሙ ኀበ አሕዛብ ቀርበ ኀቤሁ፡፡ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ፣ አው (ወይም) ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ፡፡ ➕ ነሐሴ 15 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ክርስጢና ሰማዕት ወ፫፻፻፲ወ፪ ማኀበራኒሃ ወዕንባምሬና ቅድስት ሓዋርያት ለግንዘተ እሙ ለእግዚእነ ወለውረንዮስ ሰማዕት፡፡ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - 1ኛቆሮ. 12፥18 ፦ ወይእዜኒ አስተናበሮ እግዚአብሔር፡፡ - ይሁዳ. 1፥17፦ ወአንትሙሰ አኃዊነ ተዘከሩ ቃለ ዘነገሩክሙ - ሓዋ.ሥራ 1፥12፦ ወእምዝ ተሠውጡ ኢየሩሳሌም - ምስባክ መዝ 18፥4-5 ፦ አልቦ ነገር ወልቦ ነቢብ ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ፡፡ ወእስከ አጽናፍ አለም በጻእ ነቢቦ - ወንጌል ማቴዎስ. 10፥1፦ ወጸውዖሙ ለ፲ወ፪ አርዳኢሁ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ፦ ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ) ➕ ነሐሴ 16 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ፍልሰተ ሥጋሃ ለእግዝእትነ ወፍልሰተ ሥጋሁ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወጊጋር መስፍነ ሶርያ፡፡ - ምስባክ ዘነግህ መዝ 44፥9 ፦ ወትቀውም ንግሥት በየማንክ፡፡ በአልባሰ ወርቅ ኡጽፍት ወሑብርት ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ እዝነኪ - ወንጌል ሉቃስ.1፥39 ፦ ወተንሥአት ማርያም ፍጡነ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - ሮሜ. 8፥31፦ ምንተ እንከ ንብል እንበይነዝ - ዮሐንስ.2፥1፦ እምነ ቀሲስ ለኀሪት ወለእግዝእት - ሓዋ.ሥራ 1፥12 ፦ ወእምዝ ተሠውጡ ኢየሩሳሌም - ምስባክ መዝ 45፥4-5፦ ቀደሰ ማደሮ ልዑል፡፡ እግዚአብሔር ውስተ ማዕከላ ኢትትሐወክ ወይረድአ እግዚአብሔር ፍጽመ፡፡ - ዓዲ ምስባክ መዝ 121፥6-7 ፦ ወተዚያነዉ ዳኅናሃ ለኢየሩሳሌም፡፡ ወፍሥሖሆሙ ለእለ ያፈቅሩ ሰመከ፡፡ ይኩን ሰላም በኃይልከ፡፡ - ወንጌል ማቴዎስ.26፥26፦ ወእንዘ ይበልዑ ነሥ ኀብስተ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ፦ ዘእግዚእነ (ነኣኵተከ) 🙏 ጾመን መንፈሳዊ ፍሬያችንን ለማበርከት ታብቃን ሱባኤውንም በሰላም ታስፈጽመን🙏 ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ) https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71 http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ )

  • 6 авг.1 6001025

    ✥✥✥ የጾመ ፍልሰታ ምንባባት ✥✥✥ ➕ ነሐሴ 1 - አመ ዓሚሩ ለነሐሴ አቦሊ ሰማዕት ፣ ወተዝካረ ሐና እመ እግዝእትነ፣ ወዮሴፍ ወኒቆዲሞስ እለ ገነዝዎ ለእግዚእነ፡፡ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - 1ኛጢሞ. 5፥1፦ ሊቃናተ ኢታመጉዕ፡፡ - 1ዮሐ. 5፥1፦ ኵሉ ዘየአምን ከመ ኢየሱስ ውእቱ መሢሕ ሐዋ.ሥራ 5 ፥ 26:- ወእምዝ ሖረ መጋቤ ምኵራብ፡፡ - ምስባክ መዝ 118፥47-48 ፦ ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኀፈር ወኣነብብ ትእዛዘከ ዘኣፍቀርኩ ጥቀ፡፡ ወኣነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘኣፍቀርኩ - ወንጌል ዮሐንስ.19፥38፦ ወእምድኀረዝንቱ ሰአሎ ለጲላጦስ ዮሴፍ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ አው (ወይም) ዘዮሐንስ አፈወርቅ ፡፡ ➕ ነሐሴ 2 - በዚህ ዕለት የሚተሰቡ ፦ ኣትናስያ ቅድስት ወደሚና ሰማዕት ወአኃዊሁ ወኢዮጰራቅስያ ብዕፅት፡፡ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - 1ኛጢሞ 2፥8 :- ወእፈቅድ ለኵሉ ሰብእ ይጸልዩ በኵሉ ገጸ መካን። - ጴጥ 3፥1 :- ወከማሁ አንትንሂ አንስት ተኰነና ለአምታቲከን ። - የሐዋ. ሥራ 16 ፥13፦ ወወፃእነ በዕለተ ሰንበት እምኣንቀጸ ሃገር፡፡ - ምስባክ መዝ 44 ፥14-15፦ ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግለ ድኀሬሃ፡፡ ወቢጻሂ ይወስዱ ለከ፡፡ ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበሐሤት፡፡ - ወንጌል ዮሐንስ.8.1 ወኢየሱስኒ ሖረ ደብረ ዘይት - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ➕ ነሐሴ 3 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ስምዖን ዘዓምድ ወቅድስት ሶፍያ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - 1ኛተሰሎ. 3፥1፦ ወሥዒነነ ተዐግሦ አብደርነ ንንበር አቴና፡፡ - 1ኛጴጥ. 3፥10፦ ወዘሰ ያፈቅራ ለሕይወት ወይፈቱ ይርአይ - ሐዋ.ሥራ 14 ፥20፦ ወበሳኒታ ሖረ ምስለ በርናባስ፡፡ - ምስባክ መዝ 44፥12-13፦ ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ፡፡ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፡፡ ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሥ ሐሴቦን፡፡ ወንጌል ሉቃስ.18፥9 ፦ ወይቤሎሙ ለእለ ያጽድቁ ርእሶሙ፡፡ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ➕ ነሐሴ 4 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ሕዝቅያስ ንጉሥ ወፊልጶስ ወኣኃዊሁ ወማቴዎስ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - ሮሜ. 12፥18፦ ወከመዝ ሐልዩ ምስለ ቢጽክሙ፡፡ - 1ኛጴጥ. 5.6፦ አትሕቱ እንከ ርእሰክሙ - ሓዋ.ሥራ 17፥23:- ወበጺሕየ ዝየ ርኢኩ ጣዖተክሙ - ምስባክ መዝ 20፥1-2፦ እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ፡፡ ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኀኖትከ፡፡ ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ፡፡ - ወንጌል ሉቃስ.14፥31 ወእመኒ ፈቀደ ንጉሥ ይሑር ይጽብአ፡፡ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ፣ አው ( ወይም ) ዘቄርሎስ፡ ➕ ነሐሴ 5 -- በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- አብርሃም ካልእ ወዮሐንስ ሐራ ወአባ ፊሊጶስ ዘደብረ ቢዘን፡፡ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - 2ኛቆሮ.12፥10:- ወበእንተ ዝንቱ ሠመርኩ በሕማምየ፡፡ - 1ኛዮሐ. 5፥14 :- ወዛቲ ይእቲ እንተ ብነ ገጽ በኀቤሁ፡፡ - ሐዋ.ሥራ 15፥1 :- ወቦ እለ ወረዱ እምብሔረ ይሁዳ፡፡ - ምስባክ መዝ 17፥43-44፦ ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ፡፡ ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ፡፡ ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥ ዉኒ፡፡ - ወንጌል ሉቃስ.15.1፦ ወሀለዉ ይቀርብዎ መጸብሐውያን፡፡ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ፣ አው (ወይም) ግሩም፡፡ ➕ ነሐሴ 6 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ኢየሉጣ ወማርያም መግደላዊት ወአባ ዊፃ፡፡ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - 1ኛቆሮ. 3፥10፦ ወበከመ ጸጋሁ ለእግዚአብሔር፡፡ - 1ኛጴጥ. 3፥1፦ ወከማሁ አንትንሂ አንስት ተኰነና፡፡ - ሓዋ.ሥራ 16 ፥13 ፦ ወወፃዕነ በዕለተ ሰንበት እምአንቀጸ ሃገር - ምስባክ መዝ.44፥12-13፦ ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ፡፡ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፡፡ - ወንጌል ማርቆስ.16፥9 ፦ ወተንሢኦ በጽባሕ በእሑድ ሰንበት፡፡ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ፣ አው (ወይም) ግሩም፡፡ ➕ ነሐሴ 7 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ፅንሰታ ለእግዝእትነ ወተስእሎተ ቂሣርያ ወጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት ወልደቱ ለዮሴፍ ወልደ ራሄል ወናዖድ ንጉሠ ኢትዮጵያ፡፡ - ምስባክ ዘነግህ መዝ 86፥1-2 ፦ ምስባክ መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡፡ ያበድሮን እግዚአብሐር ለአናቅጸ ጽዮን እምኵሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ፡፡ - ወንጌል ማቴዎስ.1፥1፦ መጽሐፈ ልደቱ ለእግዚእነ፡፡ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - ዕብራው. 9፥1 ፦ ወለቀዳሚትነ ደብተራ፡፡ - 1ኛጴጥ.2፥6 ፦ እስመ ከመዝ ጽሑፍ ናሁ እሠይም - ሓዋ.ሥራ10፥1፦ ወሀሎ ፩ዱ ብእሲ በሀገረ ቂሣርያ፡፡ - ምስባክ መዝ 93፥12፦ ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ ወዘመሀርኮ ሕገከ ከመይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት - ወንጌል ማቴዎስ.16፥13፦ ወበጺሖ ኢየሱስ ብሔረ ቂሣርያ፡፡ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ➕ ነሐሴ 8 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- አልዓዛር ወሰሎሜ ብእሲቱ ወውሉዱ 7ቱ ወአሞን፡፡ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - ሮሜ.9፥24፦ ወንሕነ እሙንቱ እለ ጸውዐነ ውስተ ክብሩ፡፡ - 1ኛጴጥ. 4፥12፦ አኃዊነ ኢታንክርዋ ልእንተ ትመጽአክሙ - ሓዋ.ሥራ.17፥3፦ ወጸቢሖ ለዐኩ መኳንንት፡፡ - ምስባክ መዝ 57፥8-9፦ ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ፡፡ ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ኅለተ ኮነ፡፡ ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ፡፡ - ወንጌል ማቴዎስ.7፥12 ኵሎኬ ዘትፈቅዱ ይገበሩ ለክሙ ሰብእ፡፡ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ➕ ነሐሴ 9 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- አባ ኦሪ ሰማዕት ወጲላጦስ ሊቀ ጳጳሳት ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - ፊልጵስ.1፥12፦ እፈቅድ አኃዊነ ታእምሩ ዜናየ፡፡ - 2ኛዮሐ. 1.6፦ ወበዛቲ ይእቲ ተፋቅሮትነ፡፡ - ሓዋ.ሥራ.15፥19፦ ወይእዜኒ እብለክሙ ኢታክብዱ፡፡ - ምስባክ መዝ 44፥9 ፦ ወትቀውም ንግሥት በየማንክ፡፡ በአልባሰ ወርቅ ኡጽፍት ወሑብርት ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ እዝነኪ - ወንጌል ዮሐንስ .10፥1 ፦ አማን አማን እብለክሙ፡፡ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ፣ አው (ወይም) ዘባስልዮስ፡፡ ➕ ነሐሴ 10 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ማኀበረ በኵር ወመጥራ ሰማዕት ወሐርስጥፎሮስ ወቢካቦስ ወዮሐንስ፡፡ ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - ዕብራው. 12፥22 :- ወአንትሙሰ በጻሐክሙ ኀበ ጽዮን፡፡ - 1ኛጴጥ. 1፥6፦ወባሕቱ ኀዳጠ ይእዜ ሀለወክሙ፡፡ - ሓዋ.ሥራ 4፥31፦ ወእንዘ ይጼልዩ አድለቅለቀ ውእቱ መካን - ምስባክ መዝ 73፥2፦ ተዘከር ማኀበረከ ዘአቅድምከ ፈጢረ፡፡ ወአድኀንከ በትረ ርስትከ ደብረ ጽዮን ዘኀደርከ ውስቴታ፡፡ - ወንጌል ሉቃስ.16፥9 ፦ ወአነሂ እብለክሙ ግበሩ ለክሙ አዕርክተ፡፡ - በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ ) ➕ ነሐሴ 11 - በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ኮኑ ፫፻ ነፍስ ምስለ ቅዱስ ፋሲለደስ ወአባ ሞይስስ ኤጲስ ቆጶስ ወአብጥልማዎስ

  • 5 авг.1 453117

    የገጠሪቱ ቤተክርስቲያን የጾመ ፍልሰታ ቅዳሴ እንዳይታጎል እርዳታ እናድርግላቸው ! አድራሻው በወረቀቱ ላይ አለ

  • 26 июл.2 480326

    -> በመላእክቱ ዘንድ ጽኑ ብለህ ያጸናኻቸው እኛንም በሃያማኖት በምግባር አጽናን -> ነቢዩ ዳንኤልን ከተራቡ አናብስት ያዳንከው እኛንም ሊውጠን ሽቶ ዘወትር በዙሪያችን ከሚያጋሳ ሰይጣን አድነን -> ሠለስቱ ደቂቅን ከሚነድድ እሳት ፣ ቅድስት ኢየሉጣን እና ቅዱስ ቂርቆስን ከሚፈላ ውኃ የታደካቸው እኛንም ከፍትወት እሳት ታደገን ከጥንት ጀምሮ በጎ ምሥራችን ማብሰር ልማድህ የሆነ መልአክ ሆይ ለእኛም ልቡናችንን የሚያረጋጋ የምሥራችን አሰማን

  • 25 июл.2 5022514

    ➕ የ3 ዓመት ሕፃን የእናቱ የእምነት ጉድለት በጸሎት አራቀላት በእጁም ይዟት ወደ ሕይወት መራት እናቱም “ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ” “ያች የተወለድክባት ዕለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት” አለችው። ➕ ከፍላቱ የተነሣ እንደነጎድጎድ የሚያስፈራ የነበረው እንደ ማለዳ ውርጭ ቀዘቀዘላቸው ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። ➕ በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል ( አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ) ➕ እግዚአብሔር አምላካችን የሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣን የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከታቸውንና ረድኤታቸውን ያድለን አሜን። ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ) https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71 http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ)

  • 24 июл.2 528325

    ዘወትር ልናደርገው የሚገባን ነው ፤ ነገር ግን አድርገነው የማናቅ ከሆነ ከዛሬ ጀምሮ የቤተክርስቲያን ሰላም የሚመለከት ጸሎት እናድርግ ! ብዙዎች በሶሻል ሚዲያ ስለ ቤተክርስቲያን ስደት ድምጻቸውን ያሰማሉ ነገር ግን ቤተክርስቲያን መከራዋን ያርቅላት ዘንድ ምሕላ ስታደርግ አይገኙም በግል ጸሎታቸውም አያስቧትም ..። -> እረኛውን አንድ መንጋውም አንድ ያደርግላት ዘንድ “ እንደ ልቤም በግ ጠባቆችን እሰጣችኋለሁ፥ በእውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል። ” ያለውን ቃል ይፈጽምል ዘንድ (ት.ኤር 3÷ 15 ) -> ጉባዔዋን (ማኅበረ ምዕመናንን) ያሰፋላት ዘንድ -> ቅዱስ ጴጥሮስ በታሰረ ጊዜ በቤተክርስቲያን (በክርስቲያኖች ማኅበር በማርቆስ እናት ቤት) ጸሎት ይደረግለት እንደ ነበረ በዚህም ፈጣሪ ከእስራት እንዲፈታ እንዳደረገው ዛሬም በስደት በመከራ እየተጨነቁ ያሉ ምዕመናን ይታደግልን ዘንድ -> እርሱ ራስ ለሆነላት ቤተክርስቲያን እኛ ሕዋሳቱ እንደመሆናችን ለእርሱ አካል ሕዋስ የሚገባው ንጽሕና ቅድስና እንዲኖረን ፣ ፍሬ አልባ ሆነንም ከእርሱ ግንድነት እንዳንቆረጥ .... ይህን የመሰለውን ጸሎት እናድርግ ።

  • 23 июл.2 2031

    без подписи

  • 23 июл.2 150161

    ቤተክርስቲያን እየደረሰባት ያለውን መከራ በመዋቅርዋ መቃወም ካልቻለች በመንጋው ጩኸት ብቻ መከራውን ማራቅ አይቻልም ! መንጋውን ከጠላት መታደግ የሚቻለው መንጋው በእረኛው ሲመራ ብቻ ነው ! (ዮሐ 10 )

  • 13 июл.3 235257

    #ሐምሌ_7_ልደቱ_ወዕረፍቱ_ለማር_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ አፈ በረከት የጋስጫው ኮከብ የቤተ ክርስቲያን መብራት አባ ጊዮርጊስ የደረሳቸው መጻሕፍት ኆኅተ ብርሃን መጽሐፈ አርጋኖን ወዳሴ መስቀል መጽሐፈ ብርሃን መጽሐፈ ሰዓታት ዘመዓልት ወዘሌሊት የቅዳሴ መጽሐፍ (መዓዛ ቅዳሴ) ጸሎተ ፈትቶ ውዳሴ ሐዋርያትና የሐዋርያት ማኅሌት መልክዓ ቊርባን እና የቍርባን ሥርዓት ፍካሬ ሃይማኖት መጽሐፈ ምሥጢር እንዚራ ስብሐት መሰንቆ መዝሙር ሕይወታ ለማርያም ተአምኆ ቅዱሳን ጸሎት ዘቤት ውስተ ቤት ውዳሴ ስብሐት ወሰላምታ ጸሎተ ማዕድ ቅዳሴ እግዚእ ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ውዳሴ ማርያም ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መዝሙረ ድንግል መልክዐ ውዳሴ ይዌድስዋ መላእክት (የሰዓታት ክፍል) መልክ0 ሥዕል ከበረከታቸው ያሳትፈን🤲 ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ) https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71 http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ)

  • 13 июл.2 23299

    አድርገው ‹‹በሦስት ሰዎች የተመሰሉ ሥላሴን ተቀብሏል›› ይላሉ (ስቡሕ አዳምጤ፣ የሐዋርያው ጳውሎስ መልእክታት፣ ገጽ 450)፡፡ ‹‹ሦስቱ መላእክት /ሰዎች/ የሥላሴ አምሳል ናቸው›› በሚለው የሳውርያኖስ (Typology) አነጋገርና ‹‹ሥላሴ በሦስት ሰዎች ተመሰሉ›› (Theophany) በሚለው የመ/ሐ ስቡሕ ትርጓሜ መካከል ቀጭን መስመር አለች፡፡ የታዩት መላእክት ናቸው እነዚህም መላእክት በሥላሴ ይመሰላሉ የማለትና የታዩት ሥላሴ ናቸው፣ ሲታዩትም በሦስት ሰዎች ተመስለው ነው በማለት መካከል ቀጭን ክር አለች፡፡ ለመጀመሪያው የታዩት መላእክት /ሰዎች/ ናቸው፤ ለሁለተኛው ሥላሴ ናቸው፡፡ ዮሐንስ ደማስቆና አውሳብያዮስ ዘቂሳርያም ሥላሴ በሦስት መላእክት ተመስለው (the Holy Trinity in the guise of the three angels) ተገለጡ ብለው ከተረጐሙ ሊቃውንት መካከል ናቸው (The Meaning of Icon, 1982, p.201)፡፡ -- ምን ይሁን? በኦርቶዶክሳዊ ክበበ ሕሊና ውስጥ እስካለን ድረስ በሊቃውንቱ ዘንድ ልዩ ልዩ የትርጓሜ መንገድ መኖሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ ጥቅሶቹ በየዘመኑ ለተነሣው ኑፋቄ መመከቻ ሲባል አበው በትጥቅነት ይጠቀሟቸዋልና የተጠቀሙበትን ዐውድ ማየት መልካም ነው፡፡ በጉባኤ ቀለም የአተረጓጐም ዘይቤ ልዩነት ያለ ነው፡፡ ሊቃውንቱ በጉባኤ ደረጃ ላይ ቤትና ታች ቤት ሲሉ እንሰማለን፡፡ ስም ጠርተው የቸር ደሞ (ደመ ክርስቶስ) አብነት፣ የኤስድሮስ ትርጓሜ፣ ቂርሎስ ተርጎመ፣ ካልዕ ትርጓሜ፣ ወቦ ዘይቤ   ሲሉም እንሰማለን፡፡ ያለ ነው፡፡ እንደ አማኝ በፀናው እንሄዳለን፡፡ የፀናው ትርጓሜ የመጀመሪያው ነው፡፡ በዘፍ.18 ለአብርሃም የተገለጡለት ሥላሴ ናቸው የሚለው፡፡ የአንድምታ ትርጓሜያት (Commentaries) የቤተ ክርስቲያንን ያልተቋረጠ ትውፊት (ቅብብሎሽ)ና መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበትን ዐውድና ይዘት ለመረዳት አጋዥ ናቸው፡፡ መጽሐፍን በየግላችን እንተረጕማለን ብለን ወደ ምኞታችን እየሳብን ዝርዋን እንዳንሆን ያግዙናል፡፡ ሆኖም አንድምታና ዶግማ ዕሩያን (እኩዮች) አይደሉም፡፡ አንድምታ በዶግማ ልክ አይታይም፤ ከክበበ ሃይማኖት ሳይወጡ መመራመርን ማመሥጠርን ይፈቅዳልና መተርጕማኑ እንደየ ትርጓሜ ስልታቸው የሚለያዩበት ጊዜ አይጠፋም፡፡ ስለዚህ ልዩ ልዩ ትርጓሜ መኖሩ ዶግማን እስካላናጋ ድረስ በተዐግሦ ሲታይ እንታዘባለን፡፡ ከላይ እንዳልነው ጥቅሶች ከተለያዩ ወገኖች ለሚነሡ ሃይማኖታውያን ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትን ማዕከል አድርገው ሲተረጐሙ ልዩነቱ ይከሠታል፡፡ በተርጓሚው ሊቅ የትኩረት ማዕከል ተገብቶ ማየት መልካም ነው፡፡ (1)በሥላሴ የሚተረጕሙት የሥላሴን ሦስትነት  ከማይቀበሉ አይሁድ የተከራከሩና ምሥጢረ ሥላሴ ላይ ያተኮሩ ሊቃውንት ናቸው፡፡ የእኛው ዘርዐ ያዕቆብና አባ ጊዮርጊስ የሥላሴን ሦሰትነት ከማይቀበሉ ቤተ እስራኤላውያን (ፈላሾች) ጋር የነበራቸው ክርክር በመጽሐፈ ሚላድም በገድለ አባ ጊዮርጊስም የተመዘገበ ነው፡፡ (2)ነገረ ክርስቶስን ማዕከል ያደረጉ መተርጕማን ከቃል ዘለዓለማዊ ሕልውና ጋር በተገናኘ ጥያቄ ያነሡ ተጠራጣሪዎችን ለመመከት ነው፡፡ (3) ሥላሴ በመላእክትና በሰው ተመሰሉ የሚሉ ሊቃውንት ደግሞ ‹‹እግዚአብሔር እንደ እኛ የሚዳሰስ ግዘፋዊ አካል አለው›› (Anthropomorphism) የሚል ውጹእ አስተምህሮን ለመመከት ሲሉ በምሳሌነት ተርጕመውታል፡፡ በአስተርእዮው (እግዚአብሔር ለአብርሃም በመገለጡ) ሦስቱም ይስማማሉ። እንዴት ተገለጠ ነው ልዩነቱ። የትርጓሜው ልዩነት ዓለም አቀፋዊ ገጽታ ያለው መሆኑን ማስተዋል ይገባል፡፡ በሚደንቅ መልኩ እዚያ የተነሣው ጥያቄ እዚህም በብሔራውያን ሊቃውንት መነሣቱ ይደንቃል፡፡ ተኀሥሦን ለሚሻ ያኮራልም! አባቶችህ የቀረበውን ሁሉ በቁሙ የሚወስዱ ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ ምሥጢራትን የሚያሥሡ ረቂቃን፣ ስፉሓነ አእምሮ መሆናቸውን ስታነብ ኩራት ይስሰማሀል፡፡ ቤተ ክርስቲያንህ በራሷ በክርስትና ዓለም ውስጥ ያለች የተለየች መንፈሳዊት ዓለም፣ በክርስትና ካርታ ውስጥ ጉሉሕ ቀለምና ዘይቤ ያላት ቤተ ክርስቲያን መሆኗን ትታዘባለህ፡፡ የተኀሥሦ አንደኛው ዐላማ እርሱ ነው፡፡  በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ክበበ ሕሊና ውስጥ ሆነው ማሰላሰል መጠየቅ - ተኀሥሦ - ብርቃቸው ያልነበረ ብሔራውያን ሊቃውንት እንደነበሩን እንዳሉን መጠቆም፡፡ ተኀሥሦ ዝርዝር ሐተታ የላትም፡፡ ዐላማዋ ወደ ራስ ወደ ቀደሙት አበውና እነርሱ በተኀሥሦ ወደ አነሷቸው ልዩ ልዩ ሃይማኖታውያን ጥያቄዎች መመልከትና ማመልከት ነው፡፡ ብንዘረዝርማ አንዱ ጥያቄ ብቻውን መጽሐፍ ይወጣዋል፡፡ ግሩም የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፍ ይወጣዋል፡፡ እርሱ የነገረ መለኮት ምሁራንና የሊቃውንቱ ሥራ ነውና አንገባበትም፡፡ አልፎ አልፎ ሲናከኩን ግን ለንዴት መወጫ ያህል በንባበ ደብተራ ወዲህ ወዲያ እንወራጫለን፡፡ -- ማስታወሻ፡- በመምሬ አድባር ሥር ለአብርሃም የተገለጠው ማን ነው? የሚለው ጥያቄ ላይ ልዩ ልዩ አመለካከት መኖሩን ስንጠቁም የያዘው አቋም የተነካ መስሎት የሚቈጣ አንባቢ እንደሚኖር እገምታለሁ፡፡ ዐላማው ማስቈጣት አይደለም፡፡ ቀደምት ሊቃውንት በዚህ ርእስ ዙሪያ ልዩ ልዩ ትርጓሜን ተርጕመዋል፡፡ የአንተም አባቶች ከእነዚያ ሊቃውንት የሚተካከልና የሚመሳሰል ትርጓሜን ተርጕመዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ነጥሮ የወጣውን ተከትለዋል፡፡ የነጠረውን እምነት ያዝ! ስፍሐ አእምሮአቸውን፣ የተዋሥኦ ዘይቤአቸውን፣ የማመሥጠርና የንባብ አድማሳቸውን አድንቅ! ቈናጽል ለራሳቸው ዐላማ ቈንጽለው፣ ቈርጠው ቀጥለው አንተኑ ለማስተሐቀር ከመጠቀማቸው፣ ለቤትህ እንግዳ ከማድረጋቸው በፊት ንባቡን ከነዐውዱ በራስህ መነጽር አስተውልና በርህን የማይደፈር አድርግባቸው! ቤትህ ምን እንዳለ አውቀህ ጠብቅ! ደግሞ አጥንትም ልመድ! አንባቢውና ሰማዒው ምን ይፈልጋል? ብቻ ብሎ መጻፍና መስበክ አእምሮን ከመገደብም ባለፈ የአንባቢውንና የጸሐፊውን ግንኙነት የሻጭና የሸማች እንዳያደርገው እንሰጋለን፡፡ ምን ያስፈልገናል? ብሎ መነሣትም ሸጋ ነው፡፡ እንደ አንባቢና ሰማዒ የምናውቀውን ብቻ ደጋግመን ለመስማት ራሳችንን መቃኘት ስንፍና ነው፡፡ ስለቤታችን ምንባባትና ትርጓሜያት ከባዕዳን ያውም ከወደረኞቻችን መስማት ያማል፡፡ መቀደም ያማል! ያ እንዳይሆን ያለንን እንወቅ፣ ወደ ውስጣችንም እንይ፤ ያየነውን በቤታችን ንጻሬ እንቃኝ! በራስ ዱላ መመታት ያማል! -- ወስብሐት ለእግዚአብሔር: ኪያነሂ ይምሐረነ በጸሎቱ ለአብርሃም አቡነ - ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ፤ እኛንም በአባታችን አብርሃም ጸሎት ይማረን፤ አሜን።

  • 13 июл.1 46459

    -- 2. ለአብርሃም የታዩት እግዚአብሔር ወልድና ሁለት መላእክት ናቸው! በዳሰሳ እንዳነበብኩት፣ ዳንኤል ክብረትም በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‹‹ፍካሬ ሃይማኖት›› ሐተታ (ገጽ 11፣ ኅዳግ ቁጥር 20) እንዳብራራልን ግብጻውያን ሊቃውንት ዘፍ.18ን በዚህ መልክ ነው የሚተረጕሙት፡፡ በራሳችን ንባብም ከቀሲስ ታድሮስ ማላቲ “ … the Lord and His two angels - እግዚአብሔርና ሁለቱ መላእክቱ …” ከሚለው የዘፍ.18 ትርጓሜያቸው አረጋግጠናል (Father Tadros Y.Malaty, Interpretation of the Book of Genesis, p.174፣ 184.)፡፡ ማስረጃ የሚያደርጉትም በዘፍ.19 ታሪካቸው ሲቀጥል ‹‹ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ›› የሚለውን ነው፡፡ እንደ ግብጻውያኑ ዘፍ.18 ላይ ለአብርሃም የተገለጡት ሰዎችና ወደ ሎጥ ቤት የገቡት መላእክት ታሪክ የተመሳሳይ አስተርእዮ ወጥ ታሪክ ነው፡፡ የእኛ መተርጕማን ትርጓሜ ሁለቱን ምዕራፍ ለየብቻ ያትተዋል፡፡ የዘፍ.18 ታሪክ ለሥላሴ ይነገራል፣ ዘፍ.19 ራሱች ችሎ ስለ ሁለት መላእክት የሚነገር ነው፡፡ ዘፍ.18 ‹‹ሰዎች /እደው/›› ሲል ዘፍ.19 ‹‹መላእክት›› ይላል፤ ከዘፍ. 19 መነሻ ተነሥተን የኋሊት ካልደመደምን በቀር በዘፍ.18 ስለመላእክት ቃል በቃል አልተነገረም፤ ‹‹ሰዎች›› ነው የሚለው፡፡ እዚህ ላይ ግን ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ለየት ብሎ ይቆማል፡፡ ዘፍ.18 እና 19ን ያያይዝና ሎጥ ያያቸው ሁለቱ መላእክት የተባሉት ወልድና መንፈስ ቅዱስ ናቸው ሲል በመጽሐፈ ሚላድ ይከራከራል፡፡ ‹‹ሥላሴ ናቸው›› በማለቱ ከብሔራውያን መተርጕማን ይገጥማል፣ ሁለቱን ምዕራፎች አንድ ላይ በማተት ከግብጻውያን ይስማማል፣ በዘፍ.19 የተጠቀሱትን ሁለት መላእክት ወልድና መንፈስ ቅዱስ በማለቱ ከሁለቱም አካሄድ ለየት ብሏል፡፡ በግብጽ የተማሩት የእኛው መ/ር ዐሥራት ገብረ ማርያም በጻፉት ትምህርተ መለኮት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት እንደሚያደርጉት ዘፍ.18ን ለሥላሴ ሰጥተው አለመተረጐማቸውን ታዝቤያለሁ፡፡ ዘርዐ ያዕቆብ በመጽሐፈ ሚላድ የሚከራከረው ዘገማልያል የተባለ ሊቅ ግብጻውያን በሚተረጕሙት መልኩ መተርጐሙን ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ይነግረናል፡፡ በዚህ ትርጓሜ አንደኛው እግዚአብሔር ወልድ ነው ለማለት ‹‹አቤቱ በፊትህ ሞገስን ካገኘሁ - እግዚኦ እመ ረከብኩ ሞገሰ በቅድመ አዕይንቲከ›› (ዘፍ.18፡3)፣ ‹‹አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት ቆመ›› (ዘፍ.18፡22) የመሰሉ ጥቅሶች ማጠናከሪያ ሆነዋል፡፡ ይኽ የትርጓሜ መንገድ ከሥነ መለኮት አንጻር የእግዚአብሔር ቃልን እምቅድመ ዓለም መኖር (Preexistence of the Incarnate Word) ማዕከል ያደረገ የነገረ ክርስቶስ ትርጓሜ (Christological Interpretation) ይሉታል፡፡ እነ ቅዱስ ሄሬኔዎስ፣ ሊቁ አርጌንስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የመሳሰሉ ሊቃውንት ለአብርሃም የተገለጡት እግዚአብሔርና ሁለት መላእክት ናቸው ካሉት ወገን ናቸው፡፡ ሊቃውንቱ ከምግባረ ሠናይ (virtue) አንጻርም አንቀጸ ተአንግዶ (የእንግዳ አቀባበል - hospitality/On Strangers) ጥቅስ እያደረጉ ያቀርቡታል፡፡ ሦስቱ መስፈሪያ፡- የእምነት፣ የተስፋ፣ የፍቅር ምሳሌያት፤ እንጎቻውን የጋገረችው ሣራ፡- ምሥጢራትን የምትፈጽመው የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ፣ አብርሃም፡- የአማንያንን ነፍስ፣ እሳት፡- በፍቅረ እግዚአብሔር የመናደድ (የመያዝ) ምሳሌ እየሆኑ ይቀርባሉ (Tadros Malaty, p.176, St.John Chrysostom, Homilies of Genesis, Homily 41)፡፡ -- 3. ለአብርሃም የታዩት ሦስት ሰዎች መላእክት ሲሆኑ እነርሱም የሥላሴ ምሳሌዎች ናቸው! ፈረንጆቹ Typologyም Theophanyም ሲሉት አያለሁ፡፡ ምሳሌ እንደ ማለት ነው፤ ማራቀቁን ለነገረ መለኮት ሰዎች ትተን ያገኘነውን እንተርክ፡፡ በአብርሃም የታዩት ሦስት ሰዎች መላእክት ስለመሆናቸውና ሦስት መሆናቸውም የሥላሴን በአካል ሦስት መሆን እንደሚያጠይቅ (እንደሚያስረዳ) በተረፈ ቄርሎስ የምናነበው ሳዊሮስ ዘገብሎን (Severian of Gabalah) ይናገራል፡፡ ንባቡን በጋሽ ዐምዴ (መ/ር ዐምደ ወርቅ እስጢፋኖስ) በኩል እንሂድበት፡- ‹‹አባታችን አብርሃም በወይራ ሥር ባለ ጥላ ወንበር ላይ ሳለ ሦስት መላእክትን አይቶ ለሥላሴ አንዲት ክብርን አንዲት ጌትነትን ሰጥቶ ተናገረ፡፡ ሦስቱ መላእክት፣ የወይራ እንጨት፣ ዳስ፣ አብርሃም ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ሦስቱ መላእክት፡- የሥላሴ ምሳሌ፣ ወይራ፡- የመስቀል ምሳሌ፣ ዳስ፡- የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ፣ አብርሃም፡- የሰው ዘር ምሳሌ ነው፡፡›› (መ/ር እስጢፋኖስ፣ ተረፈ ቄርሎስ፣ ምዕ.19፡33-35፣ ገጽ 107)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ.11፡1-2 ላይ ‹‹አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን በእንግድነት ተቀብለዋል›› የሚለውም ለአብርሃም ተሰጥቶ ሲጠቀስ ይታያል (Tadros Malaty on Hebrews, p.126)፡፡ በሊቀ ሊቃውንት መሐሪ ትርፌ የታተመው የጳውሎስ አንድምታ ዕብ.13:2ን  " እንግዳ መቀበልን አትተዉ። እንግዳ መቀበልን ስለወደዱ ሳያውቁ የመላእክት እንግድነት ይቀበሉ ዘንድ ያደላቸው አሉና (አለ) ፤ እለ ሎጥ እለ አብርሃም" ይላል (የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡና ትርጓሜው ፣ ገጽ 468)። በቁርኝትም ዘፍ.18ንና 19ኝን ወጥ አድርጎ ያገናኛቸዋል። የሊ/ሊ መሐሪ የዕብራውያን ትርጓሜ ለአብርሃም የታዩትን ሰዎች መላእክት ወደማለት አድልቱአል። በመጽሐፈ ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ ዘኑሲስ በሐዳፌ ነፍስ የአንድምታ ትርጓሜ ‹‹ኦ ዘአፍቀርከ ንዴተ ዚአሁ ለአዳም እመዛግብቲሆሙ ለነገደ አብርሃም - አብርሃም በእንግድነት ከተቀበላቸው ከመላእክት ከባሕርያቸው ይልቅ የአዳምን ባሕርይ የወደድህ፤ ቦ እለ ከፈሎሙ ከመ ይትቀበሉ ነግደ መላእክት /የመላእክትን እንግዶች ይቀበሉ ዘንድ ያደላቸው አሉ/ እንዲል (ዕብ.13፡1-2)›› በሚል እንግዶቹ መላእክት መሆናቸው ተጠቁሟል (መጽ.ቅዳ.አንድምታው፣ 1988፣ ገጽ 376)፡፡ ነጠላ ትርጓሜን የያዘው መጽሐፈ ቅዳሴ ግን ‹‹ነግድ - እንግዶች›› ሳይሆን ‹‹ነገድ - ዘር›› በሚል ይዘት ንባቡን አስቀምጦ ‹‹ነገደ አብርሃም›› ሲል ፈትቶታል፡፡ የቅዳሴው ንባብ እግዚአብሔር ወልድ ለተዋሕዶ ከመላእክት ይልቅ የሰውን ዘር መመምረጡን በሚያሳይ ዐውድ የቀረበ ነው፡፡ ‹‹የያዘው የአብርሃምን ዘር እንጂ የመላእክትን አይደለም›› የሚለውን የዕብ.2፡16 ንባብ ያዘክራል፡፡ ስለዚህ ‹‹ነገድ - ዘር›› ብለን በነጠላው ንባብ በቀረበው መልኩ ብንወስደው ከዐውዱ ይወጣል፤ ነጠላው ትርጓሜ ዳግም እይታን ይሻል፡፡ "ከአብርሃም ዘር ይልቅ ... " የሚል አሉታን ያስከትላል። የአንድምታው ግን ከዕብ.2፡16 እና ከቅዳሴው ዐውዳዊ ምንባብ ይስማማል ፤ ንባቡንም  "ነግድ" ሲል አቃንቶታል፡፡ የአንድምታውን አካሄድ አጽድቆ ንባቡ አብርሃም በዘፍ.18 የተቀበላቸው ሰዎች መላእክት ናቸው በሚል የትርጓሜ ዘይቤ የቀረበ መሆኑን መጠቆም ይሻላል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በዘፍጥረት ትርጓሜው አብርሃም የተቀበላቸው እግዚአብሔርና ሁለት መላእክት ናቸው ቢልም በእንግሊዝኛም በግእዝም በደረሰን የዕብራውያን ድርሳኑ (ድርሳን 33) ይኸን የቅዱስ ጳውሎስ ጥቅስ ለማብራራት አብነት ያደረገው ሎጥን ብቻ ነው፤ አብርሃምን አልጠቀሰውም፤ በዕብራውያን ትርጓሜው አብርሃም መላእክትን ተቀበለ አላለም፡፡ አባታችን መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ አዳምጤ ጥቅሱን ለሎጥም ለአብርሃምም ሰጥተው ያብራሩታል፡፡ ለአብርሃም ሲሆን ለየት

  • 13 июл.1 82479

    📌ጽሑፉ በአማን ነጸረ ከ 4 ዐመት በፊት በfacebook ገጻቸው አቅርበውት የነበረ ነው ። ለአብርሃም በመምሬ አድባር ሥር የተገለጠው ማን ነው? -- ‹‹ሥላሴ ናቸዋ!›› ዐይነተኛው የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መልስ ነው፡፡ ጥያቄው ከተኀሥሦ አንባብያን ከመጡ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች አንዱ ነውና እንሂድበት፡፡ መምሬ አድባር በእንግሊዝኛ Oak መባሉን አነበብኩ፡፡ በዘፍጥረት አንድምታ ወይራ፣ ግራር ተብሏል፡፡ በኩፋሌ በአንጻረ ግራር ያለ ወይራ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ መምሬ (በመጽ.ኩፋሌ ማምሪም) የሚለው ቃል በሁሉም ቋንቋ እንደ ወረደ ሰፍሯል፡፡ Mamre/Mambre እየተባለ ተተርጕሟል፡፡  በአፋን ኦሮሞ #ኦዳ_ቂልጡ መባሉን አየሁ፡፡ ግሩም ነው! ከመጽሐፉ አይርቅም፡፡ መምሬ ዛፍ (ዕፀ መምሬ)፡- ዘርፈፍ ያለ ባለትልቅ ግንድና ቅርንጫፍ ዛፍን ያሳያል፤ ወትሮ በገጠር ሰንበቴ/ማኅበር የሚጠጣበትን ትልቅ የቤተ ክርስቲያን ዐፀድ የመሰለ፡፡ ወደ ርእሳችን እንመለስ! ጥቅሱ (ዘፍ.18) በ15ኛው ክፍለ ዘመን እጅጉን አጨቃጭቋል፡፡ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ‹‹ብትገድሉኝ ሰማዕት እሆናለሁ፣ ብገድላችሁም ክህደትን አጠፋለሁ›› ያለው ከላይ ከተቀመጠው የተለየ መልስ የሰጡትን ተከራካሪዎች ነው፡፡ ጉዳዩን በመጽሐፈ ተኀሥሦ የመጀመሪያ ምዕራፍ ነካክተነው ነበረ፡፡ ያዩት ሰዎች አነሰ ብለዋል፡፡ 'ያልዋልንበትን ከየት እናምጣ?!' ብንልም አልሰሙንም፡፡ ንባቡ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ መተርጐሙ ብቻውን ለተቃውሞ የሚያነሣሣቸው ዘመዶቻችንም እንደጎነጡን መልእክት ደርሶናል፡፡ ዘፍ.18፡1 ጀምሮ ያለው ንባብ በትኩረት ያነበቡትን ቀደምት ዓለም አቀፍ ሊቃውንት አነጋግሯል፤ በዚያ እንዳነጋገረ በዚህም ብሔራውያን ሊቃውንትን አነጋግሯል፡፡ ከንግግሩ ሦስት የትርጓሜ ዓይነት እናነባለን፡፡ (1)ለአብርሃም የታዩት ሦስቱ ሰዎች /እደው/ ሥላሴ ናቸው፣ (2)ለአብርሃም የተገለጡለት እግዚአብሔር ወልድና ሁለት መላእክት ናቸው፣ (3) ለአብርሃም የታዩት ሦስት መላእክት ናቸው፡፡  -- 1. ለአብርሃም የታዩት ሦስት ሰዎች ሥላሴ ናቸው! በቤተ ክርስቲያናችን በ‹‹ኦፊሴል›› ሊባል በሚችል ደረጃ የምናምነው እንደዚህ ነው፡፡ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብና አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን ጨምሮ በርካታ ምንጮች ሦስቱ ለአብርሃም የተገለጡለት ሰዎች ሥላሴ መሆናቸውን ደጋግመው ተናግረዋል፡፡ አባ ጊዮርጊስ (በሕማማት ሰላምታ) ‹‹አጋእዝትየ ዘትሤለሱ - ሦስት የምትሆኑ ጌቶቼ›› ይላቸዋል፤ ግጥማዊ ይዘት ያለው ስለሆነ ንባቡ በዜማው ልክ ለምሥጢሩ መጠንቀቁ ያጠራጥራል፤ እግዚእና /ጌትነት/ የሦስቱም የጋራ ገንዘብ ነውና በነጠላ /እግዚእ - Lord ተብሎ/ ቢነገር የቀና ይሆናል፤ አጋእዝት በእንግሊዝኛ ሲሰሙት Lords ይሆናል፤ ያውካል፤ በእናቱ መጽሐፍ በዘፍጥረትም በነጠላ ነው የተቀመጠው - ‹‹አቤቱ (እግዚኦ - My Lord) በፊትህ ባለሟልነትን አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ››፡፡ ዜና ሥላሴም እንዲሁ ይናገራል - ለአብርሃም የታዩት ሦስት ሰዎች ሥላሴ ስለመሆናቸው፡፡ ሊቃውንቱ ዘፍ.18፡2ን ሲተረጕሙ ‹‹በዚያ በተራራው ሥላሴ ወደ እርሱ ሲወርዱ አይቶአቸዋል፤›› ይላሉ፡፡ በዘፍ.18፡6 ያለውን በሦስት መስፈሪያ ተሰፍሮ በአንድ የተጋገረ እንጎቻም ሦስቱ መስፈሪያ የአካል ሦስትነታቸው፣ በአንድ መጋገሩ የአንድነታቸው እያሉ ያስኬዱታል፡፡ ይህ ትርጓሜ ምሥጢረ ሥላሴን የተከተለ ትርጓሜ (Trinitarian Interpretation) ይባላል፡፡ መጽሐፈ ኩፋሌ ግሱንም በብዙ አድርጎ ‹‹አስተርአይናሁ ለአብርሃም በኀበ ድርስ ዘማምሪም - በግራሩ አንጻር ባለ በወይራው ሥር ለአብርሃም ታየነው›› (ኩፋ.12፡49) ሲል ለምሥጢረ ሥላሴ በሚመች ንባብ ያስኬደዋል፡፡ ዘፍ.18 በነጠላ አንቀጽ ‹‹አሰተርአዮ-ተገለጠለት›› ነው የሚለው፡፡ ካቶሊካዊው ሊቅ አውግስጢኖስ ንባቡን ለሥላሴ ሰጥቶ ይተረጕማል፡፡ የምሥራቅ ኦርቶዶክሳውያን ሊቅ የሆነው መክስምያኖስ (Maximus the Confessor)ም ይኸንን ትርጓሜ ይከተላል፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ጁሊያን ለተባለ አረማዊ ንጉሥ በሰጠው መልስ ዘፍ.18ን ለሥላሴ ስለመስጠቱ አንበበናል፡፡ በሃይማኖተ አበው ዘሱኑትዩ ምዕ.110፡15 እንዲህ ተጽፏል፤ ‹‹ልዑል ክቡር የክብር ባለቤት እየረዳን ስለ ቅድስት ሥላሴ ከሚሰማው ከመጻሕፍት አምጥተን በግልጥ ከተናገርን በኋላ ከብዙ ምስክሮች ጥቂቶቹን ከዚሁ እንናገራለን፤ ከሁሉ አስቀድሞ የነቢያት አለቃ  የሙሴ መጽሐፍ ክብር ይግባውና የእግዚአብሔርን ነገር ስትናገር ‹አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ› /ዘፍ.1፡26/ ብላ ኦርቶዶክሳውያን እንደሚያምኑ  የቅድስት ሥላሴን ነገር አስረድታለች፤ ይህም አነጋገር ልዩ ወደሆነች  የሦስትነት ምሥጢር /ምሥጢረ ቅድስት ሥላሴ/ ይመራል፤ ዳግመኛም በአካል ሦስት በመለኮት አንድ እንደሆኑ አስረዳች፤ አብርሃም በቀትር ጊዜ ከፊቱ የቆሙትን ሦስቱን ሰዎች በዓይነ ምሕረት የምታየኝ ከሆንክስ ባሪያህን ቸል አትበለው ብሏል፤ አብርሃም ሦስት ሰዎችን ያይ ነበር፤ ነገሩን ግን ለአንድ ሰጥቶ ተናገረ፡፡›› በዚያው በሃይማኖተ አበው ዮሐንስ ዘእስክንድርያ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ በተናገረበት አንቀጽ ‹‹አብርሃም ርእየ ሠለስተ እደወ በአሐዱ ምልክና - አብርሃም ሦስት ሰዎችን በአንድ ጌትነት አይቶአል›› ሲል ንባቡን በሦስቱ አካላተ ሥላሴና በአንዲት ጌትነታቸው ተርጕሞታል (ሃይ.አበ.ዘዮሐ.ዘእስክ.90፡2፣ ገጽ 388)፡፡ እነዚህ ምስክሮች ባሉበት ትርጓሜውን ዘርዐ ያዕቆብ በግሉ የፈጠረው ማስመሰል አንድም በጭፍን ጥላቻ፣ አንድም በንባብ አድማስ መጥበብ፣ አንድም ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን ሰበብ አድርጎ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በማነወር ልክፍት ያሳማል፡፡ አንድም ትርጓሜ አያስፈልግም የሚሉ፣ አንድም ሁሉም ሰው በተረዳው ልክ መጽሐፍ ቅዱስን መተርጐም እንደሚችል የሚያትቱ ሰዎች ‹‹በእኛ ትርጓሜ ያልሄደ ሁሉ…›› የምትመስል ሸምቀቆ ሊያስሩልን ሲቃጣቸው ፈገግ እንላለን፡፡ ‹‹ደብል ስታንዳርድ›› አይመስጥም! እዚህ ላይ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እንደ አንድ መተርጕም ሊቅ ተወስዶ የትርጓሜ ዘይቤው በራሱ ሊታይ ይገባል፡፡ ንጉሡ ሊቅ ነው! ሀቅ ነው! ዘርዐ ያዕቆብ በጥቅስ ለማጽደቅ የሚከብድ እርምጃ መውሰዱን እናውቃለን፤ እናምንለንም፤ ሊቅነቱን ግን አንክድም! በቤተ ክርስቲያናችን አብርሃም ቤት የገቡት ሥላሴ ናቸው የሚለው በንግሥ ታጅቦ የጸደቀ ነው፡፡ ከእነ አባባሉ ‹‹የአብርሃሙ ሥላሴ›› ይባላል፡፡ ከነገሥታት ዜና መዋዕልም ከቅድስት ሥላሴ ጋር የተለየ ውዴታ ባለው የጎንደር ደብረ ብርሃን አስሠሪ አድያም ሰገድ ኢያሱ ዜና መዋዕል ‹‹ወአመ ሰብኡ ለሐምሌ ገብረ በዓለ ሥላሴ - በሐምሌ ሰባት ቀን የሥላሴን በዓል አከበረ›› ተብሎ ተጽፏል (ዜና.መዋ.ዘአድ.ሰገድ ኢያሱ፣ ገጽ 170)፡፡ የታተመው ስንክሳር በሐምሌ ሰባት ምንባብ ሥላሴ ለአብርሃም መገለጣቸውን አንስቶ ዝርዝሩን ወደ ኦሪት ዘፍጥረት መርቶታል።  የአድያም ሰገድ ኢያሱ ዜና መዋዕል ንባብ ጠቅሰው የሐምሌ ሥላሴ በዓመታዊ ክብረ በዓልነት መከበር የጀመረ ከአድያም ሰገድ ኢያሱ ወዲህ ነው የሚሉ ሰዎችን ሰምቻለሁ፡፡ ታሪክ ነውና ‹ነውም አይደለምም› ለማለት ተጨማሪ ንባብና ማስረጃ ይፈልጋል፡፡

  • 8 июл.2 817305

    #ዝናብ / ም '' ውኃውን በደመና ቋጥሮ ያመጣዋል ዝናሙን ከደመና ያዘንመዋል ለሰው ሁሉ ምግብ ሊሆን መልሶ ያዘንመዋል'' / ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ / ይህን ማለቱ ስለ ምንድን ነው ቢሉ፦ መገብተ ማያት፣ መገብተ ደመናት ፣ መገብተ ነፋሳት መላእክት አሉ። ደመናው እንዳይበት ነፋሱ እንደ ወደል ጋዝ ነው። መገብተ ደመናት ደመናውን ያቀርባሉ፣ መገብተ ማያት ውኃውን በደመና ቋጥረው በነፋስ ጭነው በደመና እያራውጹ ከሁሉ ያደርሱታልና እንዲህ አለ። በመጽሐፍ ቅዱስም " እግዚአብሔር እንደ ወደደ ዝናም የያዘ ነፋስን ይሰጣል ሥርም በምድር ላይ በቅላ ቅጠልን ታወጣለች። " /፩መቃ ፰/ ይላል። የሰው ልጅ በሚበድል ጊዜ ግን መገብተ ነፋሳት ውኃ የቋጠረውን ደመና ወደ ሌላ ቦታ ወስዶ ያዘንሙታል። ጌታ እግዚኣብሔርም እንዲህ ያለጉዳት እንዳይደርስባቸው ሰማይን እንደ ነሐስ አደርጋታለሁ ሰማይ ለምድር ዝናብን አትሰጥም ምድርም ለሰው ልጆች ፍሬዋን አትለግስም እያለ ያስጠነቅቃቸው ነበር " የእግዚኣብሔርም ቍጣ እንዳይነድድባችኹ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ ምድሪቱም ፍሬዋን እንዳትሰጥ ሰማይን እንዳይዘጋባችኹ፤ እግዚአብሔርም ከሚሰጣችኹ ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችኹ እንዳትጠፉ ተጠንቀቁ። " / ዘዳ ፲፩፥ ፲፯/ እንዲል። ለዚህም በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ያህል ዝናም መከልከላቸው በ፩ ነገ ምዕ ፲፯ ምዕ ፲፰ /ሉቃ ፬፥ ፳፬ -፴፯/ ላይ የተመዘገበው ታሪክ ተግባራዊ ማስረጃ ነው። ዛሬ ግን በድለን ሳለ በመሐሪነቱ የሚያዘንምልን በመሆኑ " ጠለ ምህረት " ይባላል። በዳዊት ቃልም "እግዚኣብሔርም በጎ ነገርን ይሰጣል፥ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች። " / መዝ ፹፬፥፲፪ / እያልን እናመሰግነዋለን :: #ዝናብን_ለዘር_ጠልን_ለመኧር_የሚሰጠን_አምላክ_የተመሰገነ_ይሁን🙏 አሜን እክለ በረከቱን ጠለ ምህረቱን አያሳጣን።🙏 ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ) https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71 http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ)

  • 21 июн.3 6153318

    📌 የሥጋን ፈቃድ በምን ይገደላል? «እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ ዕዳ አለብን እንደ ሥጋ ፈቃድ ግን እንኖር ዘንድ ለሥጋ አይደለም። እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ» (ሮሜ 8፥12-13)። ▪️የሥጋ ፈቃድ ለሰይጣን በር የሚከፍት የመንፈሳዊ ጉዞ ጠላት ነው። ከሰይጣን ፈተና ይልቅ የሥጋ ፈቃድ ይከብዳል፤ የሥጋ ፈቃድ መሞት ያለበት ጠላት ነው። እርሱም በእግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በተለያዩ የሥጋ ጥበቦች የሥጋን ፈቃድ መግደል አይቻልም ለመንፈሳዊ ነጻነት አያበቃም። ቅዱስ ጳውሎስ «በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ» ይላልና የሥጋ ፈቃድ የሚሞተው በእግዚአብሔር መንፈስ ነው። 👉 በእግዚአብሔር መንፈስ የሥጋን ፈቃድ እንዴት እንገድላለን? የሚለው ጥያቄ መቅረቡ አይቀርም። ቅዱስ ጳውሎስ በሌላ ቦታ ይህንን ምክር ይሰጠናል፦ «እላለሁም፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ» (ገላትያ 5፥16)። ይህም ማለት ልባችን በመንፈሳዊ ነገር ሲጠመድ ለሥጋ ምኞት የሚሆን ቦታ ያጣል። . የሥጋ ሕይወት ነፍስ ናት የነፍስም ሕይወት መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ነፍስ በመንፈስ ቅዱስ ስትመራ፣ ሥጋን ከክፉ ምኞቱና ፈቃዱ ትገዛዋለች። ሥጋም የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆንን ይለምዳል። ያን ጊዜ የሥጋ ፈቃድ እየደከመና እየሞተ ይሄዳል። . እሳት በዕንጨት ላይ ሰልጥኖ እንደሚበላው ሁሉ፥ የእግዚአብሔርም ፍቅርና የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በሰው ልብ ውስጥ ሲበራ የሥጋን ክፉ ምኞትና ኃጢአትን ፈጽሞ ያጠፋዋል። * የሥጋን ፈቃድ ለመግደል በመንፈስ ፈቃድ መመላስ ማለትም አዘውትሮ መንፈሳዊ ተግባራትን መፈጸም ይገባል። * እሳት ብረትን የሚዋሐደው ብረቱ እሳት ውስጥ በመቆየቱ እንደሆነ ሁሉ፥ እኛም የእግዚአብሔር መንፈስ የሚዋሐደን መንፈሳዊ ተግባራትን በማዘውተር ነው። ስለዚህ ፈጣን ለውጥ ለምን አላገኘሁም ሳንል የመንስፈ ቅዱስ ሙቀት እስከ ሚዋሐደን ድረስ በመንፈሳዊ ግብር በመመላስ "ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ " ያለውን ቃል እንፈጽም (ሮሜ12፥11) ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ) https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71 http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ)

  • 18 июн.3 9333524

    🕊️ ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛው የሹመት ቀን እንኳን ለታላቁና ለኃያሉ ሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ የሹመት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ሰኔ 12 ቀን በቤተክርስቲያናችን ታሪክ እጅግ ከፍተኛና ታላቅ ዕለት ነው። የታሪክ መጽሐፍት ይህንን ዕለት "ሁለተኛው የሹመቱ ቀን" ይሉታል። (የመጀመሪያው የሹመቱ ቀን ኅዳር 12 መሆኑ ይታወቃል።) ሳጥናኤል በትዕቢቱ ከወረደ በኋላ፣ ቅዱስ ሚካኤል በትሕትናውና በየዋህነቱ በፈጣሪ ዘንድ ከፍ ብሎ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመበትን ምስጢር ኅዳር 12 በደመቀ ሁኔታ እናስባለን። ሁለተኛው ሹመቱ በትንሣኤ ላይ ነው አስቀድሞ የጌታን ትንሣኤ ለደቀመዛሙርቱ ያወጀ ፣ በዕርገቱም ጊዜ አዝነው ለነበሩ ሐዋርያት ዳግም የሚመጣ መሆኑን የነገራቸው እርሱ ነው፡፡ በዳግም ምጽአት ጊዜ አስቀድሞ ሙታንን ይቀሰቅስ ዘንድ ሥልጣን የተሰጠው የተሾመበት ሰኔ 12 ነው ። በዕለተ ምጽአትም ልዩ ስፍራ አለው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የሙታን ትንሣኤ በቅዱስ ሚካኤል አዋጅና ድምፅ የሚፈጸም መሆኑን ሲያስረዳ እንዲህ ይላል፦ "ጌታ ራሱ በትእዛዝ በሊቀ መላእክትም ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ" (1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፥16) በማለት ገልጾልናል ። ታላቁ ነቢይ ሄኖክ በመጽሐፈ ሄኖክ [6፥9 / 20፥5] ላይ ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር የተሰጠው ኃላፊነት "በሰው በጎነት ላይና በሕዝቡ ላይ የተሾመው" እንደሆነ በመግለጽ "ለሰው ልጆች ታዛዥ ነው፤ ከደግነቱ ሁሉ በላይ ለሰው ልጅ ያዝናል" ብሎ መስክሮለታል። እሱ ባለበት ስፍራ ሁሉ በጎ ነገር እንጂ ክፉ ነገር የለም! -> የማይቋረጥ የተራዳይነት አገልግሎት (ከብሉይ እስከ ሐዲስ) ለአባቶችን፣ ሐዋርያትን፣ ሰማዕታትንና ጻድቃንን ሲራዳ የኖረ የማይጎድል የጸጋ ምንጭ ነው። -> ተራዳይነቱ ለመላእክትም የሚተርፍ ነው ፦ ቅዱስ ገብርኤል ነቢዩ ዳንኤልን ባነጋገረው ጊዜ የቅዱስ ሚካኤልን ረዳትነት እንዲህ ሲል መስክሯል፦ "የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋናዎቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ... ከደገፈኝ ከገዥአችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የለም።" (ትቢተ ዳንኤል 10፥13 - 21) ሲል መስክሮለታል። -> በተጨማሪም የአፎምያና የባሕራን ታላቅ ተራዳይነት በዚሁ ሰኔ 12 ዕለት ነው ። -> ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ስለ ቅዱስ ሚካኤል መናፍስትን ድል የመንሳት ታላቅ ሥልጣን እንዲህ ሲል ጽፏል፦ "በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልበረታምም፥ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም።" (የዮሐንስ ራእይ 12፥7-8) -> አማኞች "ድርሳነ ሚካኤል" በየቤታቸው እንዲነበብ የሚያደርጉት እንዲሁ በዋዛ አይደለም። በራዕይ ዮሐንስ እንደተገለጸው እና እንደ አፎሚያና እንደ ባሕራን ሁሉ፣ መናፍስትን ድል በነሳበትና የሞትን አዋጅ በሻረበት ሥልጣኑ ቤታቸውን ከክፉ ነገር ሁሉ እንዲጠብቅላቸው፣ ሰማያዊ በረከትን እንዲያሰፍንላቸውና የጨለማውን ሥልጣን እንዲያሳድድላቸው ባላቸው ጽኑ ተስፋና እምነት ነው! ይህ ታላቅ፣ ደግ፣ ብሩህና ሩኅሩኅ መልአክ በየቤታችን ተገኝቶ ሁላችንንም ይባርከን! የአፎሚያንና የባሕራንን በረከት በየቤታችን ያውርድልን! የበረከት በዓል ያድርግልን🤲 ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ) https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71 http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ)

  • 13 июн.3 7362941

    ሰንበተ ሰንበታት በዓመት ውስጥ አራት ሰንበተ ሰንበታት አሉ ። እነዚህ ቀናት የሚሰሉት የዓመቱን 365 ቀናት ለ4 በመክፈል (91 ቀናት በመቁጠር) ነው። - የ2018 ዓ.ም የሰንበተ ሰንበታት ቀናት መስከረም 1 ቀን ሐሙስ ስለዋለ፣ በዚህ ዓመት የሚውሉባቸው ቀናት እንደሚከተለው ይሆናሉ፡ 1ኛው ሰንበተ ሰንበታት መስከረም 4 2ኛው ሰንበተ ሰንበታት ታኅሣሥ 5 3ኛው ሰንበተ ሰንበታት መጋቢት 6 4ኛው ሰንበተ ሰንበታት ሰኔ 7 ይሆናል ። በሌላ ቀላል ዘዴም ማወቅ ይቻላል ይኸውም መስከረም ፣ ታህሳስ ፣ መጋቢት ፣ ሰኔ በእነዚህ 4 ወራት የመጀመሪያው እሁድ ሰንበተ ሰንበታት ይሆናል። የእነዚህ የ4ቱ ዕለታት ማሳረጊያ ደግሞ ጳጕሜን 3 ናት። -> በእነዚህ ዕለታት ርኆተ ሰማይ የሚሆንባቸው በመሆናቸው የዚህ ዓመት 4ኛው ሰንበተ ሰንበታት ሰኔ 7 ስለሆነ ከወትሮው በተለየ መልኩ እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት፣ ምህረትን የምንለምንበት እና ለራሳችንና ለሀገራችን ሰላም የምንጸልይበት ታላቅ ዕለት ነው። ጸሎታችንና ምልጃችን በፊቱ ይድረስ! ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ) https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71 http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ)

  • 13 июн.2 882164

    #ትከሻ_እንጂ_ሸክም_አትሁኑ 📌 የልማቱ መዳረሻ ለጥቂቶች ወይስ ለብዙኃኑ? ቤተክርስቲያን በከተሞች የምታከናውናቸው የሕንጻ ግንባታዎች ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት የተጀመሩ በጎ ጅምሮች መሆናቸውን እንገነዘባለን። ይሁን እንጂ የዚህ ልማት አላማ ከጠባብ ተጠቃሚነት ወጥቶ፣ ብዙኃኑን ምዕመን የሚጠቅም ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ ላይ እንዲያተኩር ማድረግ የዘመኑ የቤት ሥራ ነው። ▪️ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምዕመናንን መንፈሳዊ ህይወት ብቻ ሳይሆን የሥጋዊ ህይወት ፍላጎታቸውንም ይንከባከብ ነበር። በምድረ በዳ የተራቡትን ሰዎች "በለመለመ ቦታ አስቀምጧቸው" ብሎ ካሳረፋቸው በኋላ፣ የሚበሉትን አበርክቶ በመስጠት ሥጋዊ ኑሯቸውን ታድጓል (ማቴ 14፡19)። ይህ መለኮታዊ ምሳሌ፣ ቤተክርስቲያን ለምዕመናን የሥጋዊ ኑሮ አጋዥ መሆን እንዳለባት የሚያሳይ ትልቅ ትምህርት ነው። አስተዳደሩ ሕንጻዎችን ለንግድ በማከራየት ብቻ ከመወሰን ይልቅ፣ ፋብሪካዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን እና ጤና ጣቢያዎችን ቢገነባ ለብዙ ምዕመናን የሥራ ዕድል መፍጠርና ጥራት ያለው አገልግሎት በዝቅተኛ ዋጋ ማቅረብ ይችላል። የቤተክርስቲያኗ ልማት የሕዝቡ የሥጋዊ ህይወት መደገፊያ መሆን አለበት። የከተማው ልማት ውጤት በከተማው ብቻ መቆየት የለበትም። እነዚህ የልማት ሥራዎች የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ችግር ለመፍታት የሚውሉበት ስልታዊ አቅጣጫ ሊኖራቸው ይገባል። የቤተክርስቲያን አንድነት የሚገለጠው የከተማው ልማት የገጠሩን ምዕመን ሲታደግ ነው። የቤተክርስቲያኗ አስተዳደር በዚህ መልኩ የምዕመኑ " ትከሻ መሆን ሲገባው ሸክም መሆኑ ያሳዝናል " ከአምላካችን በነጻ የተሰጠንን " በነጻ የተቀበላችሁትን በነጻ ስጡ" ያለውን የጌታችንን መመሪያ በመጣስ ለተክሊል፣ ለፍትሐት እና ለሌሎች ምስጢራት ምዕመኑን ከአቅሙ በላይ ከፍተኛ ክፍያ መጠየቅ መንፈሳዊውን አገልግሎት እንደ ንግድ ያስቆጥረዋል። አስተዳደሩ ምዕመናንን በሥጋዊ ህይወታቸው መታደግ ሲገባው፣ ይህንን የመሰለ ሸክም መጫን ከክርስቲያናዊ ፍቅር ጋር ፈጽሞ አይጣጣምም። ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ) https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71 http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ)

  • 12 июн.3 5122

    без подписи