tgindex
፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

Статистика

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/የሰ/ት/ቤ/ማ/መ/ማኅበረ ቅዱሳን አ.አ ማዕከል የ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ዋና የቴሌግራም ገጽ፤ መርሐ ግብራት ፥ #የቅዱሳን_ታሪክ #መጽሐፍ_ትረካ #መጽሐፍ_ጥቆማ #ብሒላተ_አበው https://t.me/amstkilogbigubae በዩትዩብ ቤተሰብ እንሁን ☟☟☟https://www.youtube.com/@5kilogbigubae የፎቶ ማህደር ☟☟☟ https://t.me/+9PbLapMJu91hZThk

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
17
Всего постов
26
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 063
+4 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
516
26 постов
Вовлечённость
12,7%
к подписчикам
Постов в день
2,4
всего 26
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
463
1/48двое суток
530
1/72трое суток
572

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • የነሐሴ ፯ ምስባክ "​​ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ፤ ወዘመሀርኮ ሕገከ ፤ከመ ይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት።​ "          ​መዝ ፺፫፥፲፪-፲፫ "አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው፤ሕግህንም ያስተማርኸው፤ሰው ብፁዕ ነው።"          መዝ 93 ፥ 12-13 ​ ምንባባት ዕብ ፱ ፥ ፩ - ፲፩ ​፩ኛ ጴጥ ፪ ፥ ፩ - ፲፯ ​ግብ ሐዋ ፲ ፥ ፩ - ፴ ወንጌል ማቴዎስ ፲፮ ፥ ፲፫ -፳፬ ቅዳሴ የእመቤታችን ቅዳሴ እንኳን ለእመቤታችን በዓለ ፅንሰት በሰላም አደረሰን!

  • "ትእምርተ ዋህዱ ረሰየኪ አብ... አብ የልጁ ምልክት አደረገሽ" በቀስትነት ሳለሽ የዕርቅ ምልክት አደረገሽ። ሰው ጠላቱን ያየው እንደሆን ቀስቱን ሊያሥር አውታሩን ወደሱ ድንጉን ወደ ጠላቱ ያደርጋል። ወዳጁን ግን ያየ እንደሆን ድንጉን ወደሱ አውታሩን ወደ ወዳጁ ያደርጋል። እንደዚሁም ሁሉ ከእርሷ የነሣውን ሥጋ በዕሪናው አኑሮ፤ እንግዲህ ወዲህ የልጁን ዘመዶች በንፍር ውሃ አላጠፋችሁም ሲል ድንጉን ወደላይ አውታሩን ወደታች አድርጎ ይታይልናልና፤ በቀስትነት ሳለሽ የዕርቅ ምልክት አደረገሽ አለ። አንድም ትእምርተ ዋህድናሁ ይላል፤ የብቸኝነት ምልክት አደረገሽ አለ። እምቅድመ ዓለም እንበለ እናት (ያለ እናት) ተወልዶ ድኅረ ዓለም (ከዓለም መፈጠር በኋላ) ያለ አባት እንድትወልጂው አደረገሽ ሲል ነው። አንድም "ትእምርተ ዋህዱ ረሰየኪ አብ" ይላል፤ የልጁ ምልክት አደረገሽ አለ ስትወልደው ማኅተመ ድንግልናዋ አለመለወጡ። ሰው ሲሆን አምላክነቱ ባለመለወጡ ድንግል ወእም ስትባል መኖሯ አምላክ ወሰብእ (ሰውም አምላክም) ሲባል ስለመኖሩ ምሳሌ። ከረቡዕ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ የተወሰደ

  • የነሐሴ ፮ ምስባክ ​ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ፤ወለገጽኪ ይትመሐሉ ኩሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ ኩሉ ክብራ ለወለተ ንጉሥ ሐሔቦን፡፡               መዝ ፵፬ ፥ ፲፪-፲፫​  የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻ ይዘው ይሰግዱለታል፤ የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ፊትሽ ይማልላሉ፤ ለሐሔቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው።                    መዝ 44 ፥ 12-13 ​ ምንባባት ​፩ኛ ቆሮ ፫ ፡ ፲ - ፳፫ ፩ኛ ጴጥ ፫ ፡  ፩ - ፯ ግብ ሐዋ ፲፮ ፡ ፲፫ - ፲፱ ወንጌል ማርቆስ  ፩፮፥ ፱-፲፱ ቅዳሴ የእመቤታችን ቅዳሴ

  • "ኮንኪ አፅቀ ንጹሐ..." ሐሩረ ፀሐይ ያልወደቀባት፤ ነፋስ ያልወዘወዛት፤ ከልምላሜ ከጽጌ ከፍሬ የተገኘች አፅቀ ሠሉስ አንቺ ነሽ። አንድም አጽቀ አቤሜሌክ አንቺ ነሽ። ለነብዩ ኤርምያስ አቤሜሌክ ባሮክ የሚባሉ ደቀ መዛሙርት ነበሩት። የምድያም ሰዎች ናቸው። ነብዩ ኤርምያስ ኃጢአታቸው በዝቷል። አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል። የበረሀ ተኩላ ይነጥቃቸዋል፣ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል። ከዚያ የሚያመልጥም ተማርኮ ፋርስ ባቢሎን ይወርዳል። ኢየሩሳሌም ባድማ ትሆናለች። ለሞት የሆነው ወደሞት ለሰይፍም የሆነው ወደ ሰይፍ ለረሃብም የሆነው ወደ ረሃብ ለምርኮም የሆነ ወደምርኮ ይሄዳል እያለ የፄዋዌን ነገር ሲናገር እየሰሙ። ኢታርእየነ ሙስናሃ ለኢየሩሳሌም እያሉ ይጸልዩ ነበር። ጼዋዌ ቢደርስ መልአኩ አቤሜሌክን ለድውያን የምን ቀባው አፅቀ በለስ አምጣ ብለህ ላከው።ባሮክንም መቃብረ ነገሥት አስጠብቀው አለው። እንዳለው አደረገ በዚያ ሌሊት እስራኤል ተማርከው ወረዱ አቤሜሌክ አፅቀ በለስን ቈርጦ በመሶበ ወርቅ አ ድርጎ ይዞ ሲሄድ ከጥላ አረፈ። ወዲያው እንቅልፍ እንቅልፍ አለው ተኛ። ፷፮፣ዘመን ተኝቶ ቢነቃ ጊዜ ገጥሞት ከተኛበት ሰዓት እልፍ ብሎ ኣገኘው ዘግ ይቻለሁ መምሬ ይቆጣኛል ብሎ መንገድ ጀመረ አገሩ ተፈቶ መንገዱ ጠፍቶ ለመሄድ ቸገረው ፤ እንቅልፉ ባይለቀኝ ነዉ አእምሮዬን ተለይቶኛል ብሎ ቁሞ ሲመለከት አንድ ሰው ከተራራ ላይ አየ። ሰውስ አይገኝም በ፰፮ ዘመን መልአክ በአም ሳለ አረጋዊ ታየው ከዚያ ሄዶ ዓይቴ ሀለዉ ኤርምያስ ወአኃውየ አለው። አንተኑ ነግድ ለኢየሩሳሌም፤ለኢየሩሳሌም አንተ እንግዳ ሰው ነህ።እለ ኤርምያስ ያሉ ባቢሎን በስደት ኢየሩሳሌም ከጠፋች ፷፮ አመት አለው። ኦሪት አክብር ገጸ አረጋዊ ብላኛለች እንጂ ይህ ጅጁ ባልሁህ ነበር።ለድውያን የምቀባው አፅቀ በለስ ቆርጠህ አምጣ ብሎ መምሬ ልኮኝ ደሟ ይንጠፈጠፋል ቅጠሏ አልጠወለገም እነሆ አለው እስኪ ክፈታት አለው ቢከፍታት ደሟ ሲንጠፈጠፍ ቅጸሏ ሳይጸወልግ ተገኝታለች አንተን ከመከራው ሠውሮህ ነው እንጂ። ሲልክህ ወራቱ ምን ነበረ አለው ። ወርኃ ጽጌ ቢለው ወርኃ ዘርፅ ሁኖብሃል ይለዋል። ወርኃ ዘርዕ ነው ቢለው ወርኃ ጽጌ ሆኖብሃል ይለዋል። ከዚሀ በኋላ ና ከወንድምህ ላገናኝህ ብሎ ወስዶ አገናኘው። ሁለቱ ተገናኝተው ቀኖና ቢገቡ ለሚጠት አራት ዓመት እንደቀረው ተገልጾላቸው ያን በወረቀት ጽፈው የሚወስድላቸወ አጥተው ሲጨነቁ የታዘዘ ንስር መጣ ወረቀቱን አፅቀ በለሱን አርገው ካንገቱ አሥረው ሰደዱለት። ኤርምያስ ሰው ሙቶበት ከንጉሥ ተሰናብቶ መቃብር ሊያስቀብር ሲሄድ ከፈረሰ ግምብ አጠገብ አስከሬኑን አሳርፎ ሳለ ኤርምያስ ኤርምያስ ብሎ በቃል ሰብአዊ ጠርቶ ጣለለት ወዲያው ነገሩን እንዲረዳለት ወኬዶ በእግሩ ለምውት ይላል። በእግሩ ተረግጦ አስነሥቶታል ። ያም ተነሥቶ በወረቀቱ ያለውን መስክሮ ተመልሶ አርፏል ። ያች ስድሳ ስድስት ዘመን ቅጠሏ ሳይጠወልግ ደሟ ሲንጠፈጠፍ እንደ ተገኘች እመቤታችንም በስሳ ስድስተኛው ትውልድ ንጽሐ ጠባይዕ ሣያድፍባት ተገኝታለችና። ወበከመ ነፋሕኩ ውስተ ገጹ ለአዳም ከማሁ አንቲኒ ሀሎኪ ወኢረሳሕኪ እንዲል አንድም ወለተ ንጽሕተ ሲል ነው ( የልደታ ትርጓሜ)።

  • አሜን እግዚአብሔር ይባርከነ ለአግብርቲሁ በሰላም፤ ሥርየተ ይኩነነ ዘተመጦነ ሥጋከ ወደመከ፤ አብሐነ በመንፈስ ንኪድ ኵሎ ኃይሎ ለጸላዒ፤ በረከተ እዴከ ቅድስት እንተ ምልእተ ምሕረት ኪያሃ ንሴፎ ኲልነ፤ እምኵሉ ምግባረ እኩይ አግኅሠነ ወውስተ ኵሉ ምግባረ ሠናይ ደምረነ፤ ቡሩክ ዘወሀበነ ሥጋሁ ቅዱሰ ወደሞ ክቡረ። አሜን እግዚአብሔር እኛን ባሮቹን በሰላም ይባርከን:: የተቀበልነው ሥጋህና ደምህ ለሥርየት ይሁነን:: የጠላትን ኀይል ሁሉ በመንፈስ እንረግጥ ዘንድ አሠልጥነን∶: ምሕረትን የተመላች ክብርት የምትሆን የእጅህን በረከት ሁላችን ተስፋ እናደርጋለን ከክፉ ሥራ ሁሉ አርቀን በበጎውም ሥራ ሁሉ አንድ አድርገን:: ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙንም የሰጠን ቡሩክ ነው:: ♦️መጽሐፈ ቅዳሴ ✨በሥጋ ወደሙ ከብራችሁ የክርስቶስ ሙሽሮች የሆናችሁ ሁሉ እንኳን ለዚህ አበቃችሁ!!! በሂደት ላይ ያለንንም ለዚህ ክብር ያብቃን🙏 📍ሁለተኛው ዙር የምሥጢር ቀናችን ቀጣይ ሳምንት ረቡዕ ነሐሴ 12 ስለሚሆን እራሳችንን እናዘጋጅ። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን! ንስሐ ንዑስ ክፍል ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

  • የነሐሴ ፭ ምስባክ ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ። ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ። ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተመጥዉኒ። መዝ. 17፥43-44 ምንባባት 2ኛ ቆሮ 12፥10-17 1ኛ ዮሐንስ  5፥14-ፍጻሜ ግብ ሕዋ፡ 15፥ 1-13 ወንጌል ሉቃስ 15፥ 1-11 ቅዳሴ የእመቤታችን ቅዳሴ

  • видео или голосовое, без подписи

  • ክቡር ስጋውን እና ቅዱስ ደሙን 📌 ከመቀበል አስቀድሞ ፥ 📌 ስንቀበል እና 📌 ከተቀበልን በኋላ ምን እንበል ❓

  • видео или голосовое, без подписи

  • ✨ከቁርባን በፊት የሚደረግ ዝግጅት ✨ ♦️ምሥጢረ ቁርባንን ለመሳተፍ ፤ ለመቀበል የሚያስብ ክርስቲያን ሁሉ  ንስሐ መግባት ይኖርበታል። ♦️ተፈጥሯዊ አካላችንን /ሥጋችን/ ለምሥጢር ከመቅረባችን በፊት ልናጸዳውና ንጹሕ ሆነን እንቀርብ ዘንድ ያለንን ልብስ አጥበን ልንለብስ ይገባናል። ♦️ወንድ ዝንየት ካጋጠመው በዚያ ዕለት፣ ሴት የወር አበባ በምታይበት ጊዜ መቁረብ አይገባም። ነገር ግን ሰውነትን አጽድቶ በቀጣዩ ዕለት /ለወንድ/፣ የወር አበባዋ ሲቆም/ለሴት/ ሰውነትን አጽድቶ በቀጣይ ዕለት መቁረብ ይቻላል። ♦️በሚገባ ሳይጾም ማንም ሰው ሥጋውን ደሙን አይቀበል።/ፍት፡ምን፡አን 13 ፥512/ ሥጋውና ደሙን ለመቀበል ባሰቡ ዕለት ለ18 ሰዓታት ያህል ከእህል ከውሃ መጠበቅ/መከልከል/ ይገባል። ምክንያቱም ጌታም ከሌሊቱ 9 ሰዓት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት በድምሩ ለ 18 ሰዓታት ያህል ልዩ ልዩ ጽዋትወ መከራን ከተቀበለ በኋላ መራራ ሐሞትን ቀምሷል፣ እኛም ከተመገብንበት ከ18 ሰዓት በኋላ የበላነው የጠጣነው ከሰውነታችን ስለሚዋሐድ፣ ለአፋችን ምሬት ይሰማናል። በዚህም የጌታ ሕማሙን፣ ሞቱንና የቀመሰውን መራራ ሐሞት እናስባለን። 📍በዚህ መሠረት ማክሰኞ ከሰዓት መቁረብ ብንፈልግ ሰኞ ከማታ 2፡00 ጀምሮ ጾመን በነጋታው ማክሰኞ ከድርገት(ቁርባኑን ካህናቱ ለቆራብያኑ የሚያቀብሉበት ጊዜ) በስምንት ሰዓት ገደማ ወርዶ ቁርባኑን ስለምንቀበል እስከዚህ ሰዓት ያለው ቢሰላ 18 ሰዓት ይሆናል። የክርስቶስ ሙሽሮች የምንሆንበት ነሐሴ 5 ም እነሆ ደረሰ!!! እርስዎ ተዘጋጅተዋል ?

  • "ወሠጠጠ መጽሐፈ ዕዳሆሙ ለአዳም ወለሔዋን" የአዳምንና የሔዋንን የዕዳ ደብዳቤያቸውን አጠፋላቸው። መጽሐፍ ግሥ ነው፤ ፍዳን አጠፋ ሲል ነው። አንድም እንዲህ ይሆናል፦ የሰው ዕዳው በደብዳቤ እንደሚታወቅ፣ ኃጢአትም በፍዳ ይታወቃልና። አንድም ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ፣ ሥቃይ አጽንቶ "ስመ ግብርናት ጽፋችሁ ብትሰጡኝ አቀልላችኋለሁ" አላቸው። አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ (አዳም የዲያብሎስ ባርያ)፣ ሔዋን አመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ባርያ) ብለው ጽፈው ሰጡት። ያንን በዕብነ ሩካም ጽፎ፣ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በገሃነም ጥሎታል። በዮርዳኖስ የጣለውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ፣ እንደ ሰውነቱ ረግጦ አጥፍቶልናል። በገሃነም የጣለውን በዕለተ ዓርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ አጥፍቶላቸው ወጥቷል። አንድም "ወይቀውም እኩይ ፊልስጣ ጸሐፊ ወተመያን" እንዲል፤ ዕለት ዕለት የምንሠራውን ኃጢአታችንን እየጻፈ የሚያዘክር ሰይጣን አለ፤ ካህኑ "እግዚአብሔር ይፍታ" ሲለን ይፋቅልናልና። "ወረሰዮሙ አግዓዝያነ ዘተወልደ ለነ በሀገረ ዳዊት መድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ።" በዳዊት ሀገር ከዳዊት ባሕርይ የተወለደ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምና ሔዋንን ነፃ አደረጋቸው። ዳዊትን "እስመ እምፍሬ ከርሥከ አነብር ዲበ መንበርከ" (ዘርህን በዙፋኔ ላይ አኖራለሁ) ያለው ነገር እንደ ተፈጸመ ለማጠየቅ ያነሣዋል። ሰአሊ ለነ ቅድስት። አዳምና ሔዋንን ነፃ ያደረጋቸው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ጸጋውንና ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን። ከሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ የተወሰደ።

  • "የምሥጢር ቀን" — 1 ቀን ብቻ ቀረው! ⏳✨ "ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።" ማቴ 26፤26 ለመጀመሪያው ዙር የምሥጢር ቀን 1 ቀን ብቻ ቀርቶታል! 📅 ማክሰኞ ነሐሴ 5 #የምሥጢር_ቀን #5_ኪሎ_ግቢ_ጉባኤ

  • የነሐሴ ፬ ምስባክ እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ መዝ. 20፥ 1-2 ምንባባት ሮሜ 12፥16-ፍጻሜ 1ኛ ጴጥ 5፥6-12 ግብ ሕዋ፡ 17፥ 23-28 ወንጌል ሉቃስ 14፥ 31-ፍጻሜ ቅዳሴ የእመቤታችን ቅዳሴ

  • "በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ዘእንበለ ተክል።ወኢሰቀይዋ ማየከማሃ አንቲኒ አ ወላዲተ ክርስቶስ አምላክነ ዘበአማን - ሳይተክሏት የበቀለች፤ ውሃ ሳያጠጧት የለመለመች፣ ያበበች፣ ያፈራች የአሮን በትር ነበረች። አምላካችንን የወለድሽልን አንቺም እንደርሷ ነሽ፤ " እንዴት የአንድ ሰው ልጆች ክህነት ከምስፍና ተሾመው ሲገዙ ይኖራሉን ብለው መሳፍንቱ ደቂቀ ሮቤል በሙሴ ላይ ካህናቱ ደቂቀ ቀዓት በአሮን ላይ ተነሱ ። እኛስ የበኩር የሮቤል ልጆች አይደለንም ፤ እኛስ የሌዊ ልጆች አይደለንም ብለው በጠላትነት ተነሥተዋል። ከዚህ በኋላ ሁላችን በአንድነት ስንይዝ ጊዜ የምቀኝነት እንደሆነ ሕዝቡ ያውቁብናል፤ አስቀድመን እኛ በሙሴ ዳኝነት አሮንን ይዘን ክህነቱን በእኛ እጅ ካደረግነው፤ በኃላ በኛ ዳኝነት ይዛችሁ ምስፍናውን እጅ ታደርጋላችሁ አሏቸው። ከዚህ በኋላ ሄደው ሙሴን ሹመት በተርታ ሥጋ በገበታ ነው፤ እኛስ ከሌዊ ተወልደን የለምን፤ እኛንም ሹሙን አሉት። እርሱም አሮን ከእግዚአብሔር አግኝቶ ተሾሟል፤ እናንተም ከእግዚአብሔር አግኝታችሁ ተሾሙ አላቸዉ፤ ይህም ለወንድሙ ማደላቱ አይደለም ብለው ከሁለት መቶ የሚበዙ ካህናት ማዕጠንተ ብረታቸውን አሰርተው ልብሰ ተክህኖ ለብሰው ሊያጥኑ ገቡ፤ ሲገቡ ሙሴና አሮን ከደብተራ ኦሪት ቆመው ቢያዩአቸው ገረመሟቸው። ከዚህ በኋላ ገብተው ሲያጥኑ ጢሰ ቅታሬው ቢነካቸው ልብሳቸውን ሳይነካ ሰውነታቸውን እንደ ተለበለበ ግንድ አድርጓቸዋል፤ ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት በልብሳቸው እያጎናጸፍህ አውጥተህ አፍስሳቸው ብሎታል፤ ያንን ግን ወተቀደሳ ማዕጠንታቲሆሙ በነፍሳቲሆሙ እንዲል፤ ለቤተ መቅደስ ዕቃ አድርገው ብሎታል። ዳታንና አቤሮንን ከነ ቤተሰባቸው ከነ ከብታቸው ከነ ድንኳናቸው ምድር ተከፍታ አስጥማቸዋለች፤ ቆሬም ምክር ሊያጸና ሄዶ በአንድ ሰጥሞ ቀርቷል። ከዚህ በኋላ ይህ ሁሉ ኃጢአታችንን እያዘከሩ የሚያስፈጁን እነዚህ አይደሉምን ብለው ሊወግሯቸው ድንጋይ ድንጋያቸውን አንስተው ቢሄዱባቸው ሸሽተው ከደብተራ ኦሪት ገቡ። ዓምደ ብርሃን ተተከለ ጌታቸው ወጣ ብለው ተመልሰዋል። ከዚህ በኋላ አሮን እስከ መቼ ድረስ እንዲህ እያልህ ትኖራለህ፤ ክህነት ከቤትህ እንደሚወጣ ምልክት አሳይሃለሁና፤ ወንድምህ ሙሴ የአሥራሁለቱን ነገድ በትራቸውን ሰብስቦ በቀዳማይ ሰዓት ሌሊት አግብቶ ከቤተ መቅደስ በቀዳማይ ሰዓት መዓልት ያውጣው፤ አለው። የአሥራሁለቱን ነገድ በትር ሰብስቦ አሮንም የአባቱ የሌዊ በትር ነበረች፤ ያችን አምጥቷል። በቀዳማይ ሰዓት ሌሊት አግብቶ በቀዳማይ ሰዓት መዓልት ቢያወጣው የአሮን በትር ሳይተክሏት ውኃ ሳይጠጧት ለምልማ አብባ አፍርታ ተገኝታለች፤ አሥራሁለት በኵረ ሎሚ አፍርታ ተገኝታለች። እንደዚህም ሁሉ እመቤታችን ከቤተ መቅደስ አሥራሁለት ዓመት ኖራ፣ ጌታን ፀንሳ ተገኝታለችና።   ከእሑድ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ የተወሰደ

  • видео или голосовое, без подписи

  • 9 авг.682619

    ውድ ተመራቂዎች “በለሱን የጠበቀ ፍሬውን ይበላል” እንዳለ ጠቢቡ ሰሎሞን በተግሣጹ (ተግሣ. 3፥18) ከብዙ የልፋት ዓመታት በኋላ የድካማችሁን ፍሬ የሰበሰባችሁበትን ዕለት ማስታወሻ መጽሔት እነሆ! ያለፉት አራት አምስት ዓመታት በሰው አቅም ለማለፍ የማይታሰቡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በቅዱሳኑ ምልጃ እና ጸሎት ያለፍናቸው እንደሆኑ የመረጣችኋቸው የመጽሔት ቃላትም ይገልጻሉ፤ ጽንዕት በድንግልና ፥ ስርጉት በቅድስና እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ቸር ሰውን ወዳጅ ከሆነ ከልጇ ዘንድ ዘወትር እየለመነች ሕይወታችንን ታስምርልን!!! እንኳን አደረሳችሁ፤ ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!! ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ — tgindex