TIKVAH-MAGAZINE
Статистикаይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያና የመረጃ መለዋወጫ መድረክ ነው። በ +251913134524 ላይ ያግኙን። ለማስታወቂያ @tikvahmagbot ላይ መረጃ ይጠይቁ።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 27
- Всего постов
- 128
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 15 335
- 1/48двое суток
- 18 600
- 1/72трое суток
- 20 060
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
በኮንጎ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ ከእንስሳት ወደ ሰው በተላለፈ አዲስ ቫይረስ መሆኑ ተገለጸ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ የሚገኘውና የሺዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ባለው የኢቦላ ወረርሽኝ፣ ከዚህ ቀደም በሰዎች መካከል ከነበረ ቫይረስ ሳይሆን ከእንስሳት ወደ ሰው በተላለፈ ቫይረስ (Zoonotic Spillover) የተቀሰቀሰ መሆኑን አዲስ የወጣ ጥናት ይፋ አደረገ። «Nature Medicine» በተሰኘው የሕክምና ሳይንስ መጽሔት ላይ በቅርቡ የታተመው ይህ ጥናት እንደሚያመላክተው፤ ተመራማሪዎች በኮንጎ እና በኡጋንዳ ከሚገኙ 22 ታካሚዎች የተወሰዱ የቫይረስ ናሙናዎችን የጂን መዋቅር መርምረዋል። በምርመራውም አሁን እያጠቃ የሚገኘው የኢቦላ ዝርያ እ.ኤ.አ በ2007 እና በ2012 ታይተው ከነበሩት «Bundibugyo» ከተባሉ የኢቦላ ቫይረስ ዓይነቶች የተለየ የጂን ባህሪ ያለውና አዲስ ከእንስሳት ወደ ሰው የተላለፈ መሆኑ ተረጋገጧል። ነገር ግን ጥናቱ ቫይረሱ በግልጽ ከየትኛው የተወሰነ የእንስሳት ዝርያ ወደ ሰው እንደተሸጋገረ አላመለከተም። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረኢየሱስ፤ ወረርሽኙ አሁን ባለው ፍጥነት የሚቀጥል ከሆነ ከ2014 እስከ 2016 በምዕራብ አፍሪካ ተከስቶ የ11,300 ሰዎችን ሕይወት የበላውን የኢቦላ ወረርሽኝ የሚበልጥና በታሪክ አስከፊው ሆኖ ሊመዘገብ ይችላል ሲሉ ገልጸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአደጋ ጊዜ ምላሽ ዳይሬክተር ዶ/ር አብዲራህማን ማሃሙድ፣ ወረርሽኙ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ከፍተኛው ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል፤ የከፋ ሁኔታ ከተፈጠረ ግን ከ9 እስከ 12 ወራት ሊዘልቅ እንደሚችል አመላክዋል። Credit : Al-Jazeera @tikvahethmagazine
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
+3
ከአፈር ነዳጅ ለማዘጋጀት የተወጠነው ፈጠራ የት ደረሰ? ⚫"ፕሮጀክቱ ሳይቋረጥ አሁንም በላቦራቶሪ ደረጃ ቀጥሏል" - ተመራማሪው በኢትዮጵያ ከአፈር የባዮ-ነዳጅ ለማምረት ለሁለት አስርት ዓመታት ገደማ ሲካሄድ የቆየ የምርምር ፕሮጀክት በፋይናንስ እጥረትና በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ወደ ፋብሪካ ደረጃ እንዳይሸጋገር እንቅፋት እንዳጋጠማቸው ዋና ተመራማሪው ለአሚኮ ገልጸዋል። ከአስር ዓመታት በፊት በነዳጅ እና በሊቲየም ፈጠራ ሥራቸው የብዙዎችን ትኩረት ስበው የነበሩት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ መምህር እና ተመራማሪው አቡሃይ ውብሸት ብዙዎች ግኝቱ የት ደረሰ ብለው ሲጠይቁ ቆይተዋል። ተመራማሪው ፈጠራው ስላለበት ወቅታዊ ሁኔታ ባብራሩበት በዚህ ቃለ-መጠይቅ፦ - አሁን ላይ ከአፈር ነዳጅ የመፍጠር ፕሮጀክት፣ በላቦራቶሪ በሚሊ ሊትር ደረጃ ከነበረበት አልፎ አሁን በሊትር ደረጃ (ከ30 እስከ 40 ሊትር) ማምረት የሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሱን፤ - ለፈጠራው የፓተንት (የባለቤትነት) መብት ማግኘታቸውን፤ - የኢትዮጵያ የጥራት ኤጀንሲ ምርቱ ለተሽከርካሪዎች መዋል እንደሚችል የጥራት ማረጋገጫ መስጠቱን፤ - በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ነዳጁ ተመርቶ የተወሰኑ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መቻሉን፤ - ለምርቱ ግብዓት የሚሆነውን «ዶቤ» የተባለ የአፈር ዓይነት ናሙናዎችን በተለያዩ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ለማጥናትና ወደ ፋብሪካ ደረጃ ለመሸጋገር የጸጥታ ሁኔታው አስቸጋሪ እንደሆነባቸው፤ - የፕሮጀክቱን አዋጭነት እና የጥሬ ዕቃውን ክምችት በሰፊው ለማረጋገጥ የሚረዳ የፋይናንስ እጥረት ማጋጠሙን ገልጸዋል። ተመራማሪው ፕሮጀክቱ ሳይቋረጥ አሁንም በላቦራቶሪ ደረጃ መቀጠሉን ጠቅሰው፥ ከባዮነዳጁ በተጨማሪ ለኤሌክትሪክ መኪናዎች እና ለወደፊት ኢነርጂ ወሳኝ የሆነውን የሊቲየም ማዕድን ማውጣት ሥራ ላይ ትልቅ ውጤት ተገኝቷል ብለዋል። ባለሀብቶች፣ የመንግሥት አካላት እና በጎ አድራጊዎች በጥናት እና በፋይናንስ ከደገፏቸው የጥሬ ዕቃ ክምችቱን አጥንተው ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን ተመራማሪው ገልጸዋል። ዘገባው የአሚኮ ነው። @tikvahethmagazine
አሁን ላይ ማንኛውም መኪና ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ያስፈልጎታል። Electra Auto sales ለዚህ ዋነኛ ምርጫዎ ነው እጃችን ላይ ወቅታዊ የሚሸጡ 00 ሆነ ትንሽ የተነዱ መኪኖች ማግኘት ይችላሉ! ትክክለኛ መኪና ፈላጊ ወይም ሻጭ ከሆኑ ይህን ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/ElectraAutosales 👉https://t.me/ElectraAutosales 👉https://t.me/ElectraAutosales
በማስታወቂያ ዋጋ 30% ልዩ ቅናሽ 🎯ብስራተ ገብርኤል ላፍቶ ሞል ግቢ ውስጥ 🎯ካሳንቺስ ኢንተር ኮንተኔንታል ፊት ለፊት ከዚህ በፊት ካዛንቺስ, በቦሌ ደምበል ጋዜቦ አፓርትመንቶችን እና ቆሬ ላይ ቪላ አስረክበናል :: አሁን ደግሞ በብስራተ ገብርሄል እና በካሳንችስ እስከ 9 ሚሊዮን ብር ቅናሽ ያወጣንበትን ቤት በማስታወቂያ ዋጋ በሺያጭ ላይ ነን ። 👉ከባለ አንድ መኝታ 89 ካሬ እስከ 248 ካሬ ባለ 3 መኝታ እንዲሁም ትላልቅ ካሬዎችን በፈለጉት መጠን እንዲገዙ አመቻችተናል:: 👉በ15% ቅድመ ክፍያ ቀሪውን በ8 ዙር ክፍያ እስኪረከቡ የሚከፍሉት 👉100% ለሚከፍሉ እስከ 30% እውነተኛ ቅናሽ ✨ ልዩ መገልገያዎች፦ 🏊♂️ መዋኛ ገንዳ 🏋️♂️ ዘመናዊ ጂም 🧸 የልጆች መጫወቻ ቦታ ⚡️ 24/7 መብራት (ጀነሬተር) 💧 የከርሰ ምድር ውሃ 🚗 በቂ የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) ⏳ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ ዛሬውኑ ይደውሉ! 🎯ልብ ይበሉ # ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት ነው #ይሄ ቅናሽ የወጣው ለ15 እድለኞች ብቻ ነው ⁉️ ንብረትዎ በአስተማማኝ እጆች! አማን ፕሮፐርቲ #አማንፕሮፐርቲ #አማንፕሮፐርቲ#amanpropertis ለበለጠ መረጃ ይደውሉ 👇👇👇👇👇👇 +251913656955 WhatsApp. https://wa.me/251913656955 Telegram :@housesaller
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በሳዑዲ የድንበር ጠባቂዎች ሀሺሽ እና ጫት የተገኘባቸው 8 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ዋሉ። በሳዑዲ አረቢያ የዓሲር እና የጃዛን ክልሎች የድንበር ጥበቃ ኃይሎች ጫት እና ሀሺሽ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሞከሩ ያሏቸውን 8 የኢትዮጵያ ዜጎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተነግሯል። በሳዑዲ አረቢያ ሕግ መሠረት እንደ ጫት እና ሀሺሽ ያሉ እፆችን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እጅግ ከባድ ወንጀል ሲሆን፣ ጥፋተኞች እስከ ሞት ቅጣት ወይም እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት፣ ከባድ የገንዘብ መቀጮ እና ከሀገር የመባረር እርምጃ ያስቀጣል። ለመሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለምን በተደጋጋሚ በዚህ መልኩ ይያዛሉ ? በየዓመቱ ከ100 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የምሥራቃዊውን የስደት መስመር በመከተል በጂቡቲ እና በየመን አቋርጠው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሲጓዙ፥ አብዛኞቹ ስደተኞች ከሀገር የሚወጡት በድህነት፣ በሥራ እጥረት እና በየአካባቢው በነበሩ ግጭቶች ምክንያት ነው። ታዲያ በጉዞ ወቅት በአዘዋዋሪዎች ታግተውና ተገደው ዕዳቸውን ለመክፈል ወይም ዕቃ እንዲያጓጉዙ በመደረግ ለአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ይዳረጋሉ። አንዳንዶቹም ጫት በኢትዮጵያ ሕጋዊ በመሆኑ በሳዑዲ አረቢያ ያለው ሕግ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ሳይረዱ ለከፍተኛ አደጋ ይጋለጣሉ። ሲኤንኤን በቅርቡ ባወጣው ዘገባ በደቡብ ምዕራብ ሳዑዲ አረቢያ በሚገኘው የኸሚስ ሙሻይት እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አስከፊ ሁኔታ ይፋ አድርጓል። ዘገባው በትግራይ ግጭት ወቅት ከሀገር ወጥቶ በየመን በኩል ወደ ሳዑዲ የገባውን እና “አማኑኤል” የተባለውን ወጣት የሕይወት ታሪክ ያሳያል። ወጣቱ እረኝነት ሲሰራ ከቆየ በኋላ የሳዑዲ ዜጎች መደበኛ ዕቃ እንደሆነ በመንገር የሰጡትን መኪና ሲነዳ ሀሺሽ ተገኝቶበት እንደተያዘ ይናገራል። በምርመራ ወቅት ድብደባ እንደተፈጸመበት፣ በማያውቀው የአረብኛ ቋንቋ በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ እንዲፈርም መደረጉን እና ተርጓሚ እንዲሁም የሕግ ድጋፍ ሳያገኝ በአጭር ጊዜ የሞት ቅጣት እንደተፈረደበት አስረድቷል። በአሁኑ ወቅት በኸሚስ ሙሻይት እስር ቤት ብቻ በዕፅ ተያያዥ ክስ የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸው የምስቀያ ቀናቸውን የሚጠብቁ 60 ገደማ ኢትዮጵያውያን በአንድ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ። የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እንደሚሉት ሳዑዲ አረቢያ በየዓመቱ በዕፅ ወንጀል የተከሰሱ በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎችን የምትገድል ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያውያን ከፍተኛውን ቁጥር አላቸው። በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ በተደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት 1 ሺህ 971 ኢትዮጵያውያን የንጉሣዊ ምሕረት ተጠቃሚ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል። @tikvahethmagazine
ማዳጋስካር በቅኝ ግዛት ዘመን በውጭ ሀገራት ዜጎች ስም የተመዘገቡ መሬቶችን ልትወርስ ነው። በህንድ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘው የአፍሪካ ደሴት ሀገር ማዳጋስካር፣ በቅኝ ግዛት ዘመን በውጭ ሀገራት ዜጎች ስም ተመዝግበው የቆዩ መሬቶችን ወደ መንግሥት ይዞታነት ለማዛወር የሚያስችላትን አዲስ ሕግ አጽድቃለች። ሕጉ ማዳጋስካር ከፈረንሳይ ነፃነቷን ያገኘችበትን ሰኔ 26 ቀን 1960 እ.ኤ.አ. እንደ መነሻ ሲቆጥር፥ ከዚያ ቀን በፊት በውጭ ሀገር ዜጎች ስም የተመዘገቡ እና እስከዛሬ ድረስ ለሀገር ውስጥ ዜጎች ያልተላለፉ መሬቶች ወደ መንግሥት ይዞታነት ይዛወራሉ ተብሏል። ሕጉ፥ በዲፕሎማቲክ እና የቆንስላ ቦታዎች፣ ከነፃነት ቀን በፊት ለሀገር ውስጥ ዜጎች የተላለፉ መሬቶች እንዲሁም የማዳጋስካር ዜግነት አግኝተው በይፋ የተመዘገቡ የውጭ ዜጎች ይዞታዎች ከዚህ ሕግ ነፃ ተደርገዋል። @tikvahethmagazine
በአከባቢው "ወርቅ ተገኘ" የሚል መረጃን ተከተሎ በ10 ሺዎች ወደ ስፍራው እየጎረፉ ነው። በምዕራብ ኬንያ ዌስት ፖኮት ግዛት በሚገኘው ካንያርክዋት አካባቢ የወርቅ ግኝት መኖሩን የሚገልጹ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ አከባቢው በሰዎች ተጨናንቋል። ህጻናት ከብት ሲጠብቁ መሬት ቆፍረው ወርቅ የሚመስሉ የሚያብረቀርቁ ማዕድናት ማግኘታቸው ከተሰማና በማኅበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ በኋላ ሲሆን፣ በሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ10,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ወደ አነስተኛዋ የቼፖሮር መንደር በጅምላ ጎርፈዋል። በተጨማሪም በርካታ የትምህርት እድሜ ላይ የሚገኙ ህጻናት ትምህርታቸውን አቁመው በመቆፈር ስራ ላይ መሳተፋቸውን እና ትንንሽ ህጻናትም ያለ ተንከባካቢ ሜዳ ላይ መተዋቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል። ፍለጋው የሚካሄደው ያለ ምንም ጥንቃቄ እና መደበኛ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በመጠቀም በመሆኑ የመሬት መንሸራተት እና የጉድጓድ መደርመስና የጎርፍ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ተሰግቷል። በአጭር ጊዜ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በትንሽ ቦታ ላይ በመሰብሰባቸው ጭምር በቂ የመጠጥ ውሃ እና ሽንት ቤት ባለመኖሩ ምክንያት ለተላላፊ በሽታዎች እንዳይከሰቱ ስጋት ፈጥሯል። በሌላ በኩል ግን ይህ አጋጣሚ የምግብ፣ የውሃ፣ የማዕድን መቆፈሪያ ቁሳቁሶች እና የሞተር ብስክሌት (ቦዳ ቦዳ) ትራንስፖርት ንግድን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምርና እንዲነቃቃ አስተዋጽኦ አበርክቷል። Source : Kenya News Agency @tikvahethmagazine
видео или голосовое, без подписи
Samsung Galaxy note 3 32 gb 3 gb ram ዋጋ 4500ብር በማከፋፈያ ዋጋ Call me 👇👇👇👇 ☎️ 0909255008 ☎️ 0912739699 የሚፈልጉትን ስልክ ለመምረጥ አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ 👇 ቤተሰብ ይውኑ Join ያድርጉ 👇 👉 https://t.me/used_phone_ethiopia2
በማስታወቂያ ዋጋ 30% ልዩ ቅናሽ 🎯ብስራተ ገብርኤል ላፍቶ ሞል ግቢ ውስጥ 🎯ካሳንቺስ ኢንተር ኮንተኔንታል ፊት ለፊት ከዚህ በፊት ካዛንቺስ, በቦሌ ደምበል ጋዜቦ አፓርትመንቶችን እና ቆሬ ላይ ቪላ አስረክበናል :: አሁን ደግሞ በብስራተ ገብርሄል እና በካሳንችስ እስከ 9 ሚሊዮን ብር ቅናሽ ያወጣንበትን ቤት በማስታወቂያ ዋጋ በሺያጭ ላይ ነን ። 👉ከባለ አንድ መኝታ 89 ካሬ እስከ 248 ካሬ ባለ 3 መኝታ እንዲሁም ትላልቅ ካሬዎችን በፈለጉት መጠን እንዲገዙ አመቻችተናል:: 👉በ15% ቅድመ ክፍያ ቀሪውን በ8 ዙር ክፍያ እስኪረከቡ የሚከፍሉት 👉100% ለሚከፍሉ እስከ 30% እውነተኛ ቅናሽ ✨ ልዩ መገልገያዎች፦ 🏊♂️ መዋኛ ገንዳ 🏋️♂️ ዘመናዊ ጂም 🧸 የልጆች መጫወቻ ቦታ ⚡️ 24/7 መብራት (ጀነሬተር) 💧 የከርሰ ምድር ውሃ 🚗 በቂ የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) ⏳ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ ዛሬውኑ ይደውሉ! 🎯ልብ ይበሉ # ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት ነው #ይሄ ቅናሽ የወጣው ለ15 እድለኞች ብቻ ነው ⁉️ ንብረትዎ በአስተማማኝ እጆች! አማን ፕሮፐርቲ #አማንፕሮፐርቲ #አማንፕሮፐርቲ#amanpropertis ለበለጠ መረጃ ይደውሉ 👇👇👇👇👇👇 +251913656955 WhatsApp. https://wa.me/251913656955 Telegram :@housesaller
አቢ-ዘር የበጎ አድራጎት ሥራውን በ60 ከተሞች ለማዳረስ ማቀዱን ገልጿል አቢ-ዘር ማህበረሰብ አቀፍ የልማት ድርጅት ከነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ የበጎ አድራጎት ሥራውን በስድስት ዙሮች በመላ አገሪቱ ወደሚገኙ 60 ከተሞች ለማስፋፋት ማቀዱን አስታውቋል። ድርጅቱ ከዚህ በፊት በአማራና አፋር ክልሎች በሚገኙ ሦስት ከተሞች ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ አሁን ሥራውን ወደ 60 ከተሞች ለማስፋፋት እየሰራ መሆኑን ነው የገለጸው። የመጀመሪያው ዙር ከነሐሴ 9 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ/ም በ10 ከተሞች 5 ሺህ ሕፃናትን በደብተር፣ ቦርሳ፣ ዩኒፎርምና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶች ይደግፋል። ቀሪዎቹ 50 ከተሞች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በአምስት ዙሮች የንፅህና መጠበቂያ ፣ የምግብ፣ የአልባሳትና ሌሎች መሠረታዊ ድጋፎችን ያገኛሉ ተብሏል። አቢ-ዘር በየከተማው ማህበረሰቡን በማሳተፍ አዳዲስ በጎ አድራጊዎችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑንና ለበጎ አድራጎቱም ለ60 ከተሞቹ 30 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ሀብት ለማሰባሰብ ማቀዱን ነው የገለጸው። ድጋፉ የሚደረግላቸው ሰዎችም በወረዳ አስተዳደርና በሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት የሚመረጡ ሲሆን፣ አቢ-ዘር መረጃቸውን ሁኔታዎችን ከተመለከተ በኋላ ድጋፉን ያደርሳል ተብሏል። ድርጅቱ ከማህበረሰቡ የሚሰበስባቸውን የመማሪያ ቁሳቁስ፣ የንፅህና መጠበቂያ፣ ምግብና ልብስ የመሳሰሉ ድጋፎች 70 በመቶ በተሰበሰቡበት አካባቢ በቀጥታ ተደራሽ እንደሚያደርግ ገልጿል። ድርጅቱ ድጋፉን በአብዛኛው ከማህበረሰቡ በሚሰበሰብ ሀብት የሚያከናውን መሆኑንና ከ10 ሺህ የሀገር ውስጥና 2 ሺህ የውጭ አገር በጎ አድራጊዎች እንዳሉት ገልጿል። ማህበረሰቡም ከ100 ብር ጀምሮ በመደገፍ አባል መሆን ይችላልም ተብሏል። አቢ-ዘር ከዳሽን ባንክ ባለፈውና በዘንድሮ ዓመት በእያንዳንዳቸው 500 ሺህ ብር ድጋፍ ማግኘቱን ሲገልጽ፥ የዘንድሮው ድጋፍ ለሕፃናት የትምህርት መሳሪያ ግዥ እንደሚውልና ከባንኩ ጋር በቀጣይ በጋራ ለመስራት ውይይት መጀመሩም ተነግሯል። አቢ-ዘር ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ለወላጅ አልባ ሕፃናት፣ ለእናቶች፣ ለአረጋውያንና ለተፈናቃዮች ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቶ፣ በአሁኑ ወቅት 234 ሕፃናትንና 1,200 አረጋውያንን እየደገፈ ይገኛል። ቀደም ሲልም 15 ወጣቶችን በ500 ሺህ ብር ወደ ዶሮ እርባታ ሥራ እንዲገቡ ማገዙን፣ ተማሪዎችንና ሴቶችን መደገፉን እንዲሁም ለሕፃናት የጤና መድን፣ የንፅህናና የትምህርት ቁሳቁስ ማቅረቡን ገልጿል። @tikvahethmagazine
አሁን ላይ ማንኛውም መኪና ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ያስፈልጎታል። Electra Auto sales ለዚህ ዋነኛ ምርጫዎ ነው እጃችን ላይ ወቅታዊ የሚሸጡ 00 ሆነ ትንሽ የተነዱ መኪኖች ማግኘት ይችላሉ! ትክክለኛ መኪና ፈላጊ ወይም ሻጭ ከሆኑ ይህን ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/ElectraAutosales 👉https://t.me/ElectraAutosales 👉https://t.me/ElectraAutosales
በካናዳ 'ቀበቶ አላስርም' ባለ ሕፃን ምክንያት በረራ ተሰረዘ። በካናዳ ቀበቶ አላስርም ባለ ሕፃን ምክንያት በረራ ከተሰረዘ በኋላ በአውሮፕላን ከሚጓዙ ሕፃናት ጋር በተያያዘ የሚወሰዱ የደኅንነት እርምጃዎች ውዝግብ አስነሱ። ፖርተር አየር መንገድ እንደገለፀው አውሮፕላኑ ከአምስት ቀናት በፊት ከቪክቶሪያ ወደ ቶሮንቶ ለመብረር ተዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም አንድ ሕፃን ወንበር ላይ ቆሞ ቀበቶ አላስርም በማለቱ በረራው ተስተጓጉሏል። የበረራ ሰዓቱ በመዘግየቱ እና ማኮብኮቢያው ከመዘጋቱ በፊት አውሮፕላኑ መነሳት ባለመቻሉ ተሳፋሪዎች በማግሥቱ ለመብረር መገደዳቸውንም አየር መንገዱ አስረድቷል። ክስተቱ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ወላጆች የአየር መንገዱን ሕግ ለማክበር መውሰድ ስላለባቸው እርምጃ እንዲሁም አየር መንገዶችም መስጠት ያላባቸውን ምላሽ በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እንዲንሸራሸሩ አድርጓል። በርካታ ሰዎች “በአንድ ሕፃን ምክንያት በረራ መስተጓጎል አልነበረበት፤ መውረድ የነበረባቸው ወላጁ እና ልጁ ነበሩ” ብለዋል። ሌሎች ደግሞ ሕፃናት በበረራ ወቅት እንደሚፈሩ እና እንደሚጨነቁ በመግለፅ ትዕግስት እንደሚያስፈልግ መክረዋል። ፖርተር አየር መንገድ በበኩሉ “ችግሩን ለመፍታት የሕፃኑ ወላጅ እና የበረራ ሰራተኞች ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም።” ብሏል። “በዚህ ደኅንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ አውሮፕላኑ መብረር ስላልቻለ ወደ ጣቢያው ተመልሶ ሁለቱ መንገደኞች እንዲወርዱ ተደርጓል።” ሲልም አክሏል። የሕፃናት አቪየሽን ደኅንነት ባለሙያ የሆኑት ሊያ ቱሶ፣ "የፖርተር ሰራተኞች በረራውን በመሰረዛቸው የሕፃኑን እና የበረራ ቡድኑን አባላት ጨምሮ የተሳፋሪዎችን ደኅንነት ጠብቀዋል" ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። “በተገቢ ሁኔታ እንዳልተቀመጠ ዕቃ ሁሉ ሕፃናትም አውሮፕላኑ በሚነሳበት እና በሚያርፍበት ጊዜ ሊወረወሩ ይችላሉ” ሲሉም በራሳቸውም ሆነ በተሳፋሪዎች ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው። @tikvahethmagazine
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት የሟቾች ቁጥር 2,000 አለፈ። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው እና በታሪክ እጅግ ፈጣኑ ተብሎ የተገለጸው የኢቦላ ወረርሽኝ የሟቾች ቁጥር 2,000 ማለፉን የሀገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እስካሁን ድረስ ፦ ⚫ በአጠቃላይ 4,381 የተረጋገጠ የኢቦላ ተጠቂዎች ተመዝግበዋል፤ ⚫ 2,011 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ⚫ 704 ታካሚዎች በተለዩ የህክምና ማዕከላት ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ የመጀመሪያዎቹን 1,000 ሰዎች ለመግደል ዘጠኝ ሳምንታት ያህል የፈጀበት ቢሆንም፣ ሁለተኛውን 1,000 ሰዎች ለመግደል ግን የወሰደበት ጊዜ ሶስት ሳምንታት ብቻ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ ወረርሽኝ እ.ኤ.አ. ከ2014 እስከ 2016 በምዕራብ አፍሪካ ከተከሰተው እና ከ11,000 በላይ ሰዎችን ከገደለው ወረርሽኝ ቀጥሎ በታሪክ ሁለተኛው ትልቁ የኢቦላ ወረርሽኝ ሆኗል። በኢቱሪ ግዛት እና አካባቢው ባለው የታጠቁ አማፂያን ግጭት እንዲሁም የመሰረተ ልማት አለመሟላት ምክንያት የመከላከል ሥራው አስቸጋሪ እንዳደረገው ሲገለጽ የቆየ ሲሆን፥ አሁን ደግሞ የጤና ባለሞያዎች ከክፍያ ጋር በተያያዘ የሚያሰሟቸው ቅሬታዎችና አድማዎች ሌላ ፈተና ደቅነዋል ተብሏል። @tikvahethmagazine
ከ800 በላይ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ከዓለም አቀፉ “Pathways to Space” የስፔስ ሳይንስ ፕሮግራም ተመረቁ። የወደፊቱ የአፍሪካ ስፔስ ተመራማሪዎች STEM አካደሚ (FASESA) ከዓለም አቀፉ የኤሮስፔስ ኩባንያ ቦይንግ ጋር በመተባበር የሚያካሂደው 3ኛው ዓመታዊ "Pathways to Space" መርሃ-ግብር 832 ኢትዮጵያንን ጨምሮ 2,626 አፍሪካውያን ተማሪዎችን አስመርቋል። ለአምስት ወራት በተካሄደው በዚህ የስልጠና መርሃ-ግብር ተማሪዎቹ በኤስትሮኖቲክስ፣ ሲስተምስ ኢንጂነሪንግ፤ በማቴሪያል ሳይንስዐ ላይ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን፣ በከፍተኛ ከፍታ ላይ በሚለቀቁ ባሉኖች አማካኝነት የተግባር ልምድ እና የመረጃ ትንተና ክህሎት አዳብረዋል ተብሏል። ተመራቂ ተማሪዎቹ ፦ 🇿🇦 ከደቡብ አፍሪካ 1,313 ተማሪዎች፣ 🇪🇹 ከኢትዮጵያ 832 ተማሪዎች፣ 🇳🇬 ከናይጄሪያ 431 ተማሪዎች፣ 🇰🇪 ከኬንያ 50 ተማሪዎች የተወጣጡበት ነው። ተማሪዎቹ ከናሳ (NASA) ጆንሰን ስፔስ ሴንተር፣ ከፋይናል ፍሮንቲየር ዲዛይን እና ከተለያዩ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ከተውጣጡ የስፔስ ባለሙያዎች እና የቀድሞ ኤስትሮኖቶች ጋር በቪዲዮ የመገናኘት እድል አግኝተዋል። ፕሮግራሙ እ.ኤ.አ. በ2024 ከተጀመረ ወዲህ በአጠቃላይ ወደ 3,500 ለሚጠጉ አፍሪካውያን ተማሪዎች ተዳራሽ ማድረግ ችሏል። @tikvahethmagazine