tgindex
Meseret Media

Facts matter! www.meseretmedia.org

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
11
Всего постов
48
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
72 355
+140 за 3 дн.
Сутки
+39
+0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
33,1 тыс
40 постов
Вовлечённость
45,7%
к подписчикам
Постов в день
1,6
всего 48
Упоминаний
3
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
21 316
1/48двое суток
24 428
1/72трое суток
26 346

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14 авг.14,6 тыс628

    #YouTube በሳምንት አንድ ቀን አርብ ዕለት በዩትዩብ የምናቀርበው መረጃ ተለቋል፣ ይከታተሉ https://youtu.be/iOtKSiGnChM?is=n2sn_89vZlNyT8TK

  • 13 авг.21,7 тыс16915

    #የሚድያዳሰሳ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ውስጥ ወደቀ ስለተባለ የጦር ጄት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲሰራጩ የቆዩት መረጃዎች ትክክለኛ መሆናቸውን ኢትዮጵያ ቼክ አረጋገጠ የመረጃው መሰራጨትን ተከተሎ አንዳንዶች የጦር ጄቱ በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች ተመቶ መውደቁን በመጥቀስ ምስሎቹን ያጋሩ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ምስሎቹ እና ቪዲዮዎቹ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም ኤአይ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተሰርተው የቀረቡ ናቸው ሲሉ ተከራክረው ነበር ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/023

  • 13 авг.22,1 тыс754

    የመሠረት ሚድያ መረጃዎችን ካለገደብ ማንበብ ይፈልጋሉ? በቀጥታ በኢሜይል አድራሻዎ አዳዲስ ዜናዎች ልንልክልዎትም እንችላለን። ዛሬውኑ በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉን ⤵️ https://meseretmedia.substack.com/30pcoff

  • 13 авг.24 тыс18023

    #ዜናመሠረት በድሬዳዋ የታይዋን ገበያ አዳራሽ 120 ነጋዴዎች ሱቆቻቸው ተዘግተውባቸው እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ገለጹ “በሰራነው ልክ ተገቢና ገቢያችንን ያማከለ ህጋዊ ግብር ለመክፈል ዝግጁ ነን፤ ነገር ግን ከስራ ውጭ የሚያደርገንና የሚያከሰርን አሰራር ሊጫንብን አይገባም” ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/120

  • 13 авг.22,8 тыс665

    #ዜናመሠረት የኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ዲያስፖራ መሪዎች ከአሜሪካ ኮንግረስ አባል ሳራ ጃኮብስ ጋር በህዝብ ደህንነት እና ሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ተወያዩ በሚቀጥሉት ሳምንታት የዲያስፖራ ልዑኩ በዋሽንግተን ዲሲ ኮንግረስ አባላት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት፣ ከፖሊሲ ጥናት ተቋማት እና ከሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጋር ተከታታይ ከፍተኛ ስብሰባዎችን ለማድረግ ማቀዱ ታውቋል ተጨማሪ ያንብኑ: https://www.meseretmedia.org/p/97e

  • 13 авг.22,4 тыс12412

    #ዜናመሠረት በሀዋሳ ከተማ የሀይቅ ዳርቻ የኮሪደር ልማት መዋጮን ሰበብ ያደረገ በከፊል የመንግስት ሰራተኞች ላይ የደመወዝ እገዳ መደረጉ ተሰማ የከተማዋ የፋይናንስ ቢሮ ሠራተኞች ከደመወዛቸው ከ50 እስከ 100 ፐርሰንት የሚሆነውን ለልማቱ መዋጮ ካልፈቀዱ በስተቀር የክፍያ ፔሮል እንዳይሰራ ትዕዛዝ ማስተላለፉ የዕለት ተዕለት ሕይወታቸውን እንዳወከው ሰራተኞች እየተናገሩ ይገኛሉ ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/ac0

  • 13 авг.25,3 тыс44416

    #ዜናመሠረት በቅርቡ አበሽጌ ወረዳ ውስጥ 'ፋኖ ናቸው' በማለት የተገደሉት ሶስት ወጣቶች ቤተሰቦች ግድያውን አስተባብሉ የሚል ጫና እየደረሰባቸው መሆኑ ታወቀ ለሟች ቤተሰቦች "የሞቱበትን ምክንያት አናውቅም፣ የመንግስት አካላት አልገደሏቸውም በሉ፣ አሊያ ግን እኛ ከታሰርን እናንተው ትጠፋላችሁ" በማለት ቀጥተኛ እና ከባድ ዛቻ እያቀረቡባቸው እንደሆነ ምንጮች ተናግረዋል ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/1c4

  • 12 авг.26,3 тыс33629

    #ዜናመሠረት የፖለቲካ እስረኞችን በአዲሱ አመት ለመፍታት መንግስት ታራሚዎች ይቅርታ እንዲጠይቁ እያግባባ መሆኑ ታወቀ በይቅርታ ከመፈታታቸው በፊት የሦስት ወይም የሁለት ቀን ሥልጠና ለመስጠትና 'አይደገምም!' የሚል ጽሑፍ ያለበት ቲሸርት ለማዘጋጀት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል፣ በቁጥር 30 የሆኑ ታራሚዎች ግን በቀረበው የይቅርታ ሰነድ ላይ 'አንፈርምም' የሚል አቋም ይዘዋል ዝርዝሩን ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/2fa

  • 10 авг.33,8 тыс877116

    #ዜናመሠረት በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ሶስት ወጣቶች 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ከመኪና እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መረሸናቸው ታወቀ ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት የአማራ ክልል ተወላጆች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በግፍ መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/346

  • 10 авг.32,8 тыс634

    #ዜናመሠረት የግራንድ አፍሪካ ራን አዘጋጆች 'ከሩጫም በላይ ነው!' በሚል መርሃ ግብር 10 የበጎ አድራጎት አጋሮችን አስተዋወቁ እነዚህ አጋር ድርጅቶች በካንሰር ግንዛቤና ሕሙማን ድጋፍ፣ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ወገኖች በማገዝ፣ የሕፃናት ትምህርትን በመደገፍ፣ ድህነትን በመቀነስ፣ የነርሶችና የሌሎች ባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት እንዲሁም ንጹሕ የመጠጥ ውኃ በማቅረብ ዘርፍ የተሰማሩ መሆናቸው ተገልጿል ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/10-e22

  • 10 авг.32,5 тыс435111

    #ዜናመሠረት ከአሜሪካ ወደ ሀገር ቤት ለግል ስራ የተመለሰው ዲያስፖራ ከመንገድ ላይ ታፍሶ እስር ላይ እያለ በደረሰበት ድብደባ ህይወቱ ማለፉ ተሰማ በተጨማሪም በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ በሚገኙ አካባቢዎች ወጣቶችን ከመንገድ ላይ ያለፍላጎታቸው ለውትድርና የማፈስ፣ የታሰሩትን የማሰቃየት እና በገንዘብ ክፍያ የመደራደር ድርጊቶች እየተፈፀሙ መሆኑን የሚጠቁሙ አዳዲስ መረጃዎች እና የምስክሮች ቃል እየወጡ ይገኛሉ። ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/28b

  • 7 авг.37 тыс6717

    #YouTube በሳምንት አንድ ቀን አርብ ዕለት በዩትዩብ የምናቀርበው መረጃ ተለቋል፣ ይከታተሉ https://youtu.be/k9dh_eWAm80?is=w9W-B91i8MoM7CpA

  • 6 авг.51,8 тыс356184

    #ዜናመሠረት በፉሪ፣ በኬንቴሪ፣ በሰበታ፣ በአለምገና እና በወለቴ አካባቢዎች በወጣቶች ላይ የግዳጅ ምልመላ እና አፈሳ መጀመሩ ተሰማ - በትግራይ ክልል ከሚያዝያ 2026 ጀምሮ የክልሉ ባለስልጣናት “15 ዓመት የሞላቸውን ህጻናት ጨምሮ ወጣቶችን በግዳጅ እየመለመሉ” እንደሆነ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በሪፖርታቸው መጥቀሳቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ድርጊቱ በመንግስት ሚሊሻዎች አዲስ አበባ እና በዙርያዋ መፈፀም መጀመሩ ታውቋል - በወለቴ አካባቢ ብቻ ብዙ ሺህ ወጣቶች ታፍሰው ሀረር ዳቦ አካባቢ በሚገኘው የወጣት ማእከል ውስጥ ተይዘው እንደሚገኙ ታውቋል Photo: File ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/447

  • 6 авг.44,4 тыс10810

    #ዜናመሠረት የአዲስ ስታንዳርድ አታሚ በዋና አዘጋጁ ላይ እገታ፣ በስቱዲዮው ላይ ወረራ መፈፀሙን ጠቅሶ ከቢሮው እንዲለቅ ትእዛዝ መተላለፉን አስታወቀ እነዚህ ድርጊቶች የተፈፀሙት ተቋሙ የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን የአዲስ ስታንዳርድን የኦንላይን ሚዲያ ምዝገባ ሰርተፊኬት ለመሰረዝ ያሳለፈውን ውሳኔ በሕግ ለመቃወም በሚንቀሳቀስበት ወቅት መሆኑ የታወቀ ሲሆን ተቋሙ የባለስልጣኑ ውሳኔ ሕገ-ወጥ ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/9ea

  • 6 авг.42,4 тыс1297

    #አስተያየት የአዲስ አበቤዎች እውነተኛ አጀንዳ እና መልሶቻቸው በሱራፌል ጌታሁን፣ የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግኑኝነት መምህር እና ተመራማሪ ፣ጋዜጠኛ እና ፖለቲካል ተንታኝ "የአዲስ አብቤዎች ተቃውሞ ከመነሻው ከተማዋ ለምትተዳደርበት የረጅም ጊዜ መዋቅራዊ ችግሮችን ነው፤ ይኸውም ከተማዋ እንደ ራስ ገዝ አካል ሳትታይ የምትተዳደርበት ሥርዓት ነው። ይህንን ቀውስ ለመፍታት የከተማዋ ህጋዊ፣ የበጀት እና አስተዳደራዊ ሁኔታ በመሠረቱ እንደገና መገምገም እና ማስተካከል አለበት" https://www.meseretmedia.org/p/941

  • 6 авг.33,8 тыс19477

    #ዜናመሠረት አሽከርካሪዎች ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከፍተኛ የትራፊክ ቅጣት ውዝፍ ሲያስተናግዱ የቆዩት 'በህግ አተረጓጎም ስህተት' እንደነበር ታወቀ - የቅጣቱ ብዛት እና የህገወጥነት ጥያቄው እየበረታ ሲመጣ ተቋሙ ከሀምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከ6 ወር በላይ የሆናቸው አሽከርካሪዎች ላይ ወለድ መቁጠሩን በሚስጥር እንዲቋረጥ ማድረጉ ታውቋል - የህግ ባለሙያዎች ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የስርዓት ስህተቱን ቢያስተካክልም እስከዛሬ ድረስ በህግ አሰራር ውጭ ከአሽከርካሪዎች የተቀበለውን ገንዘብ ከነወለዱ ተመላሽ የሚያደርግበት አሰራር ሊዘረጋ ይገባል ብለዋል ሙሉ መረጃውን ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/a68

  • 6 авг.36,1 тыс18429

    #ዜናመሠረት በሸገር ከተማ አገራዊ ምርጫው ከተካሄደ ማግስት ጀምሮ ማንኛውንም የመንግስት አገልግሎት ለማግኘት 6,200 ብር ለተለያየ መዋጮ በግድ እየተጠየቀ መሆኑ ተሰማ "ለምርጫው ተብሎ ተቋርጦ የነበረው የ3,500 ብር ክፍያ አሁን የሚሊሻ ደመወዝ፣ የዜግነት አገልግሎት እና ለቡሳ ጎንፋ ማህበር በሚሉ የተለያዩ ስያሜዎች በሲንቄ ባንክ በኩል ወደ 6,200 ብር አድጓል"– ነዋሪዎች ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/6200

  • 6 авг.38,9 тыс1195

    #ዜናመሠረት በመሠረት ሚድያ ህገወጥ ስራቸው የተጋለጠ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ የፀጥታ አካላቱ አመራሮቹን ከያዟቸው በኋላ በቢሯቸው ውስጥ የሚገኙ ሰነዶችንና የመረጃ መያዣዎችን ሲሰበስቡ እንደነበር የደረሰን ዘገባ ያመላክታል ሙሉ ሪፖርቱን ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/af3

  • 3 авг.46,8 тыс17620

    #ዜናመሠረት በኮሪደር ልማት ከካዛንችስ ወደ ቃሊቲ ወርቁ ሰፈር የተወሰዱ ዜጎችን ምን ገጠማቸው? ያሉበትን የከፋ ሁኔታ ለክፍለ ከተማው አመራሮች ያቀረቡት ነዋሪዎች ለችግራቸው አፋጣኝ መፍትሔ ከማግኘት ይልቅ "ለልማት ተባባሪ አይደላችሁም" የሚል ውንጀላ እና "ከንቲባዋ ቤቶቹን ልትመርቅ ስትመጣ ይሰራላችኋል" የሚል የፌዝ ምላሽ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.meseretmedia.org/p/0a3

  • 31 июл.51,7 тыс567

    #YouTube በሳምንት አንድ ቀን አርብ ዕለት በዩትዩብ የምናቀርበው መረጃ ተለቋል፣ ይከታተሉ https://youtu.be/o6X5B7qHEuQ?is=-TPRguL2y-WuJ6dK

Meseret Media — tgindex