tgindex
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Статистика

Journalist-at-large

Последний пост
10 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
30
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
132 561
+85 за 3 дн.
Сутки
−52
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
94,9 тыс
30 постов
Вовлечённость
71,6%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 30
Упоминаний
9
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
34 935
1/48двое суток
40 035
1/72трое суток
43 179

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 10 авг.39,4 тыс1 429113

    ፎቷቸውን ትኩር ብዬ ተመለከትኩት፣ ህይወታቸው ገና ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ወጣቶች እንደሆኑ ያስታውቃሉ። መሀል ላይ ያለው ወጣት ድንጋጤው ይጋባል፣ ሰው ባላጠፋው ጥፋት ሲከሰስ የሚሰማው ስሜት። ሁሉም 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ተረሸኑ፣ አስከሬናቸው እንኳን እንዳይነሳ ለቀናት ተከለከለ። ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው፣ ግዛው ግርማዬ! ነፍስ ይማር! https://www.meseretmedia.org/p/346

  • 4 авг.70 тыс1 08816

    መንግስትን መቃወም እና የህዝብ ተቋማትን ማጥቃት ሙሉ በሙሉ የተለያዩ ነገሮች ናቸው! እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ንግድ ባንክ ያሉ የህዝብ ሀብቶች ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች ድንቁርና ካልሆኑ ምን ሊባሉ ይችላሉ? መንግስታት ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ: ተቋማቱ ግን የህዝብ ሆነው ይኖራሉ። የሀገራችንን ሰንደቅ አላማ ይዞ አለምን የሚዞርን ታላቅ አየር መንገድ አርማ መሬት ላይ ጥሎ መርገጥ ከቀውስነት የዘለለ ትርጉም ያለው አይመስለኝም። @EliasMeseret

  • 28 июл.92,9 тыс28810

    ከአሜሪካዋ Maine ግዛት ዋና ገዢ (Governor) ጃኔት ሚልስ ጋር ትናንት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ቃለ-መጠይቅ አርጌ ነበር፣ ዝርዝሩን ከታች ይገኛል ⤵️ https://www.amjamboafrica.com/amjambo-exclusive-gov-mills-vows-to-protect-maines-immigrant-communities-after-fatal-ice-shooting/

  • 27 июл.93,6 тыс45135

    የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ አሁን ላይ ደግሞ በአሜሪካ የግዙፉ Delta Air Lines ስትራቴጂክ አማካሪ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከአየር መንገዳችን ከለቀቁ ወዲህ የመጀመርያውን ሰፊ ቃለ መጠይቅ ከ LTM- Network/Amjambo Africa ሚድያችን ጋር ቆይታ አድርገዋል። ሙሉው ቃለ መጠይቅ ከቀናት በኋላ በድረ-ገፃችን እና ሶሻል ሚድያ ገፆቻችን ላይ ይለቀቃል፣ ይጠብቁን amjamboafrica.com ፌስቡክ: https://www.facebook.com/share/1JeWXnEfkK/ ኤክስ: https://x.com/AmjamboAfrica ዋትሳፕ: Follow the Amjambo Africa channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbCHMDG0AgWGXjzVk03K ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/amjamboafrica?igsh=MWt2eDV1aWx0OHIyYg==

  • 23 июл.89,5 тыс93117

    'ሀገር እየመከረ ነው' በሚባልበት ወቅት ንፁሀን ዜጎች ላይ እንዲህ አይነት የጭካኔ ተግባር መፈፀም ምን ማለት ነው? https://t.me/meseretmedia/1787

  • 17 июл.106 тыс1 21732

    #የግልምልከታ "ጽምዶ" የተባለው ስብስብ በጋራ ጥቅምና በሰላም ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የውስጥ ችግሮችን በኃይል ለመፍታት ከውጭ ኃይል ጋር መጣመርን የመረጠ ሀይል መሆኑን እያሳየ ነው፣ ይህ አካሄድ ደግሞ ታሪካዊ ስህተት እና የሕዝብ እልቂት ምንጭ መሆኑ የማይቀር ነው። የውስጥ የፖለቲካ ልዩነቶችንና ቅራኔዎችን በውይይት፣ በዕርቅና በሰላማዊ መንገድ በሀገር ውስጥ ከመፍታት ይልቅ የውጭ ኃይላትን ጦርና ጋሻ ጋብዞ የገዛ ወገንን ለማስጨፍለቅ ማሰብ እኩይ ተባር ነው። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከኤርትራ ጋር በመጣመር በራሳችን ሕዝብ ላይ ያደረሰውን ሰብአዊ ቀውስና ስቃይ ስንተች የነበረውም ለዚሁ ነው ምክንያቱም እንዲህ ያሉ አሰላለፎች የሕዝብን ሕልውና የሚያጠፉ፣ ሀገርን ለባዕድ ጣልቃ ገብነት አሳልፈው የሚሰጡና ጠባሳቸው ለትውልድ የማይሻር በመሆኑ ነው። በመሆኑም አሁንም ሆነ ወደፊት ማንኛውም አካል በየትኛውም ስም “ጽምዶ” የሚል ስብስብ ፈጥሮ የሕዝብን ስቃይና መከራ የሚያበዛ ከሆነ በምንም ዓይነት መመዘኛ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም። የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት መገበሪያ ማድረግና ሀገርን ማፈራረስ የታሪክ ተጠያቂነትን ያስከትላል። እውነተኛ መፍትሔ ሊመጣ የሚችለው ከውጭ ኃይላት በሚገኝ የጦር ድጋፍ ሳይሆን በሀገር ውስጥ ኃይሎች መካከል በሚደረግ እውነተኛና ሁሉን አቀፍ ውይይት ብቻ እንደሆነ በጽኑ አምናለሁ፣ ሰላም የሚገነባው በጠመንጃ አፈሙዝ ሳይሆን በሰላማዊ ድርድር ነው። @EliasMeseret

  • 9 июл.115 тыс44014

    ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ በ Editor-in-Chief (ዋና አርታዒ) የስራ መደብ የሙሉ ግዜ ስራ የጀመርኩበት LTM-Network የአሜሪካዋ ሜይን ግዛት ውስጥ በሰባት ቋንቋዎች መረጃ የሚያቀርብ ብቸኛው እና በአይነቱ ትልቁ ጋዜጣ የሆነው የ Amjambo Africa አሳታሚ ነው። አሁን የተቋሙ ዋና ትኩረት የዲጂታል አቅሙን ማስፋት እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጠን እየሰራን ነው፣ አንዱ ደግሞ በወር ሁለት ግዜ *በነፃ* በቀጥታ ወደ አንባቢዎች ኢሜይል የምንልካቸው እና እኔ የማዘጋጃቸው Newsletter ናቸው። ዛሬውኑ ተመዝግበው መረጃዎቻችንን በነፃ ያንብቡ: ሊንክ ⤵️ https://www.amjamboafrica.com/newsletter/

  • 4 июл.131 тыс68523

    Happy 250th Birthday, America! 🇺🇸 Most of us are grateful to now call this great nation home. While no country is without its challenges, the United States remains a place where people can pursue opportunity, are treated with dignity, and enjoy freedoms that inspire hope. Here's to the enduring ideals that continue to bring people from around the world together. Happy Independence Day! @EliasMeseret

  • 22 июн.136 тыс1 94714

    Stepping into age 43 with gratitude! Thank you everyone for the warm birthday wishes 🙏🏽 @EliasMeseret

  • 20 июн.124 тыс2057

    Having an incredible time at the Joe Russo's Almost Dead concert at Thompson's Point here in Portland, Maine! So grateful for all the amazing people stopping by to show love for our publication. Portland, you have a beautiful community! #PortME #AmjamboAfrica #Maine https://whatsapp.com/channel/0029VbCHMDG0AgWGXjzVk03K/216

  • 19 июн.103 тыс78242

    ድሬዳዋ ላይ በግሉ ለፓርላማ ሊወዳደር እንቅስቃሴ ጀምሮ የነበረው ዶ/ር ሀብታሙ አለሙ በምስሉ ላይ በሚታየው መልኩ የስም ማጥፋት፣ ዛቻ እንዲሁም ማስፈራርያዎች ከደረሱት በኋላ ራሱን ከምርጫው አገለለ። ለምርጫ ቦርድ በተከታታይ አቤቱታ ቢያስገባም ምንም ሊፈይዱ አልቻሉም፣ አሁን ደግሞ ከምርጫው እንዲወጣ ያስገደዱት የከተማው አመራሮች ለስራ ወደ ድል ጮራ ሆስፒታል ሲያመራ አፍነው ወስደውታል። ​ፖሊሶቹ ምንም አይነት የፍርድ ቤት የፍተሻም ሆነ የመያዣ ማዘዣ ሳይኖራቸው "በስልክ የተሰጠን የበላይ አመራር ትዕዛዝ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።  ከሶስት ቀን በፊት ፍርድ ቤት አቅርበውት ዳኞቹ "አንተን ብሎ ዶክተር..." በማለት ሲያንቋሽሹት ነበር። እንኳን ሰው ምርጫ ተወዳድሮ ሊያሸንፍ ለመወዳደር በማሰቡ ብቻ ስቃይ የሚያይበት የድሬዳዋ አመራር አቶ ከድር ጁሀር ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል። በስምሉ ላይ የሚታዩትን ቅንብሮች በመስራት ሲለቁ የነበሩት ከተማው ያደራጃቸው የቀን እና የለሊት የታክሲ ማህበራት አባላት የሆኑ ካድሬዎች ናቸው። @EliasMeseret

  • 17 июн.91,5 тыс91245

    ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2005፣ 2008፣ 2009፣ 2010፣ 2012 በቀድሞው ጠ/ሚር አቶ መለስ ዜናዊ ዘመን እንዲሁም በ2015 እና በ2017 በቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ዘመን በቡድን ሰባት (G 7) ሀገራት ስብሰባ ላይ ተሳትፋ ነበር። ዘንድሮ በፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ኬንያ በፕሬዝደንቷ ስትወከል ግብፅ ደግሞ በታሪኳ ለሁለተኛ ግዜ በመሪዋ ተወክላ ተገኝታለች። ኢትዮጵያ በዚህ ጉባዔ ላይ አለመሳተፏ እና ሙሉ በሙሉ መቅረቷ በዲፕሎማሲውና በኢኮኖሚው ረገድ ስጋት ይፈጥራል። ይህ ይበልጥ አሳሳቢ የሚሆነው የዓለምን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚወሰኑ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ውሳኔዎች፣ የዕዳ ቅነሳ ስትራቴጂዎችና የልማት አጀንዳዎች በሚቀረጹበት በዚህ ተፅዕኖ ፈጣሪ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ድምፅ ሳይሰማ በመቅረቱ ነው። ጎረቤት አገር ኬንያ በተደጋጋሚ የክብር እንግዳ ሆና ጥሪ እየተደረገላት ባለበት እና ሌላው ቀርቶ ግብፅ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ በፈረንሳዩ የኤቪያን (Évian) የG7 ጉባኤ ላይ እንድትሳተፍ በተጋበዘችበት ወቅት ኢትዮጵያ አለመገኘቷ የዲፕሎማቲክ የቤት ስራ እንደሚጠብቀን አመላካች ነው።  የኢትዮጵያ ከዚህ መድረክ መራቅ አገሪቱ ቀደም ሲል በአፍሪካ ቀንድ የነበራትን የጂኦፖለቲካዊ መሪነት ሚና እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነት ዝቅ ማድረጉ አይቀርም። እንደ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የፋይናንስ ድጋፍ እና የቀጣናው ደህንነት ባሉ ወሳኝ አጀንዳዎች ላይ ያላትን የመሰማት አቅም ይቀንሳል። የኢትዮጵያ ድምፅ ከፍ ብሎ እንዲሰማ የቤት ስራው በደንብ ይሰራ። @EliasMeseret

  • 14 июн.101 тыс1 70317

    ብዙ አትሌቶች የውጭ ሀገር ማናጀሮቻቸውን ይፈራሉ፣ በደል ሲፈፀምባቸው እንኳን ውጠው ያልፋሉ እንጂ መልሰው አይናገሩም። Not Kenenisa Bekele! ከጥቂት አመታት በፊት የቀነኒሳ ማናጀር ጆስ ሔርመንስ ለሚድያ የማይመጥን እና ወደ ሚድያ የማይወጣ ጉዳይ ሚድያ ላይ አወጣ። ቀነኒሳ ይህን አካሄድ ዝም ብሎ መመልከት አልፈለገም፣ እውነትም ከእርሱ ጋር ነበረች። በበርካቶች ዘንድ ግርምትን የፈጠረ እና በአትሌቲክስ ተንታኞች 'ደፋር' ያስባለ ቃለ መጠይቅ አድርጌለት በወቅቱ ትልቅ ዜና ሆነ፣ ጆስ ሔርመንስ ምላሽ አልሰጠም። "With those remarks, Jos Hermens acted like someone who lost a gamble." ቀነኒሳ ኋላ እንደነገረኝ ግንኙነታቸው ከዛ በኋላ ክብሮ (respectful) ሆኖ ቀጠለ (ዜናው: https://www.letsrun.com/news/2017/10/kenenisa-bekele-dismayed-jos-hermens-comments-professionalism-berlin-marathon-vows-break-world-record/) "ብዙ ደሀዎች መንገድ ላይ በበዙበት በዚህች ሀገር ውስጥ በጣም ውድ እና ውብ መኪና ይዞ ከቤት መውጣት እጅግ ከባድ ነው፣ ህሊናህ አይፈቅድም። ያንን መኪና ለማን ነው የማሳየው?። እዚያ መንገድ ላይ ፈስሰው ያሉት አባትህ፣እናትህ፣ወንድም እህትህ ፣ ዘመድ አዝማዶችህ ናቸው" ያለው ንግግሩም የብስለቱን ጥግ ያሳያል። መልካም ልደት አንበሳው! @EliasMeseret

  • 14 июн.88,7 тыс1 15526

    በአንዳንድ ጉዳዮች አስተያየት ስሰጥ 'በወያኔ ግዜ የት ነበርክ?' የሚሉ አስተያየቶችን አልፎ አልፎ አያለሁ። በወያኔ ግዜ አሁን ላይ በድምር 1 ሚልዮን ገደማ ተከታታይ ያላቸው የማህበራዊ ሚድያ ገፆቼ (ፌስቡክ፣ ኤክስ፣ ቴሌግራም እና ዋትሳፕ) አልነበሩኝም፣ ትንሽ ተከታይ ያለው አንድ የፌስቡክ ገፅ ነበረኝ። ታድያ በዛን ግዜ የሀገራችንን መልካም ዜናዎችም ሆነ የሚፈፀሙ ግድያዎችን፣ አፈናዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ወዘተ በአለም ዙርያ ለሚገኙ ቢሊዮኖች የማጋልጠው በሶሻል ሚድያ ሳይሆን በምሰራቸው ዜናዎች ነበር። ያኔ የት ነበርክ ለምትሉ ምላሹ በጥቂቱ ይኸው ⤵️ 1. Several dozen shot dead in weekend protests across Ethiopia https://apnews.com/general-news-6b3ca469c63941ebbfbbd321705aece1 2. Group: Ethiopia's security forces killed over 400 protesters https://www.ksl.com/article/40229325/group-ethiopias-security-forces-killed-over-400-protesters 3. HRW: Media suppression in Ethiopia curbing democratic space https://www.sandiegouniontribune.com/2015/01/22/hrw-media-suppression-in-ethiopia-curbing-democratic-space/ 4. Ethiopia: At least 11 students killed in violence https://www.yahoo.com/news/ethiopia-least-11-students-killed-violence-105243525.html?guccounter=1&guce_referrer=aHR0cHM6Ly93d3cuZ29vZ2xlLmNvbS8&guce_referrer_sig=AQAAAMq2WlBdAf1NcDJCHmtvM0ma-HBF8HXZx5-x9akKLeP6s_XJnAf5eA6Pi7OGlNdTc3lGlEkQKDwKoD--yzudyAu9Es9fGZpLdoxdK2HqO9vQ_nCF8H4TceZT3XOTrnuk2J30NaWZ2JZKxTsrS5XTHl0bOJzFdNsZWv0PkLtr2h6Z 5. Ethiopia targets opposition who met with European lawmakers https://gebremariam3.rssing.com/chan-50763547/article1865.html?nocache=0 6. Ethiopia jails 20 Muslims that it accused of pursuing Sharia state https://apnews.com/general-news-e65d8d01cf6146038b5cf37385111d34 7. New report says Ethiopia blocked social media, news sites https://www.njherald.com/story/news/nation-world/2016/12/13/new-report-says-ethiopia-blocked/3127598007/ 8. Ethiopia detains foreign pilots in a vintage air rally https://www.foxnews.com/world/2016/11/24/ethiopia-detains-foreign-pilots-in-vintage-air-rally.html 9. Ethiopia arrests blogger, academic critical of government https://www.heraldonline.co.zw/ethiopia-arrests-blogger-critical-of-government/ 10. Fifty two confirmed dead in stampede at Ethiopia religious event https://www.timesofisrael.com/52-confirmed-dead-in-stampede-at-ethiopia-religious-event/ 11. Ethiopian marathoner remains in US on visa after protest https://apnews.com/general-news-af404d3dbc4e4ab0b048f4f423c7649e 12. Groups urge UN Human Rights Council over Ethiopia protests https://www.sandiegouniontribune.com/2016/09/08/groups-urge-un-human-rights-council-over-ethiopia-protests/ ... በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች የወቅቱን መንግስት ድርጊት በተመለከተ የተሰሩ ዜናዎችን ማቅረብ ይቻላል። ያኔም፣ ዛሬም እዛው አቋም ላይ ነን። መንግስት ቢቀያየር ለህዝብ እና ሀገር እውነት መቆም የሙያው ግዴታ ነው። @EliasMeseret

  • 14 июн.73,3 тыс83

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 июн.96,7 тыс94821

    100 ፐርሰንት እውነት የሆነ ግሩም አባባል ነው! ቁጭ ብሎ ለመነጋገር መቼም አይረፍድም፣ በንግግር የሚያምን ትውልድ የሰው ልጅ ህይወት እንዳይጠፋ ያደርጋል። ተነጋገሩ፣ የቤት ችግራችሁን በቤት ውስጥ ፍቱ። @EliasMeseret

  • 13 июн.79 тыс1 15648

    2 ቢልየን ብር የሚሸጥ የሆስፒታል መሬት አፈፍ ያረገ ሰው አሸዋ መድፊያ አይቸግረውም እኮ! አፍንጫ ዳበስ፣ ዳበስ አይሰራም። አሁን የጋንዲ ሆስፒታልን መሬት ትመልሳለህ ወይስ አትመልስም? ልጅቷ ግን... "ከንክኖሀል" 😂 @EliasMeseret

  • 12 июн.88,3 тыс1 739202

    ለስራ ወደተዛወርኩበት ስቴት ከጥቂት ሳምንታት በፊት አዲስ ታርጋ አውጥቼ ነበር፣ ስንት ከፈልኩ? 25 ዶላር (4,200 ብር ገደማ)! ታርጋውን ለማተም ስንት ይሆን ብዬ ስጠይቅ "ምናልባት 5 ዶላር ቢሆን ነው፣ ቀሪው ፕሮሰስ ማረጊያ ነው" የሚል ምላሽ አገኘሁ። ከዛ ወደ ቻይና የታርጋ አከፋፋዮች ድረ-ገፅ ገባ ብዬ ስማትር እጅግ ዘመናዊ የፊት እና የኋላ ታርጋ ከአንድ እና ሁለት ዶላር ጀምሮ እስከ 5 ዶላር ይሸጣል። ታድያ ታርጋ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምንድነው 350 ዶላር ወይም 60,000 ብር የሚሸጠው? መንግስት ከአይ ኤም ኤፍ ብድር ጋር በተያያዘ እየተከተለው ያለው አቅጣጫ ብድር ለማግኘት ከየትኛውም ህዝብን ለማገልገል ከተቋቋሙ ተቋማት በመቶዎች እና ሺዎች እጥፍ ዋጋ በማስከፈል ትርፍ ማግኘት ነው። የተሽከርካሪ አገልግሎት፣ የኢሚግሬሽን አገልግሎት፣ የኤሌክትሪክ፣ የውሀ... ወዘተ ዋና አላማቸው ትርፍ ሳይሆን ለህዝብ አገልግሎት መስጠት ነበር፣ እየሆነ ያለው ግን በአመቱ መጨረሻ ህዝብን የሚያሳብድ ክፍያ ጠይቀው የትርፍ ሪፖርት ማቅረብ ሆኗል። በመጪው አመት 1.5 ትሪሊየን ብር ታክስ ይሰበሰባል ተብሏል፣ ይህ ከአምና የመንግስት አጠቃላይ በጀት በላይ ነው። በተያዘው አካሄድ ሊሳካ ይችላል፣ አብዛኛው ህዝብ ግን ከአመት አመት ከድህነት ወደ ድህነት ወለል እየወረደ ይገኛል። @EliasMeseret

  • 12 июн.83,4 тыс1 34545

    የዛሬ ስምንት ወር ገደማ (መሠረት ሚድያ እሰራ በነበረበት ወቅት) አዲሱ ታርጋ እስከ 60 ሺህ ብር ሊያስከፍል እንደሚችል ዜና አቅርቤ ነበር። በወቅቱ አንድ የመንገድ ትራንስፖርት ሀላፊ መረጃውን አስተባብለው ይህን ከታች የሚታየውን መረጃ ሲሰጡ ህዝቤ ዜናውን "fake news" ሲል ነበር፣ መንግስትም የህዝቡ አካሄድ ተመቸው። በል አሁን 59,000 ብርህን ውረድ!  @EliasMeseret

  • 9 июн.98,4 тыс1 84029

    ህዝቡን አትግደሉ፣ አታስገድሉ ማለት ከመቼ ጀምሮ ነው ግጭት መቀስቀስ የሆነው? የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በአንድነት ቆመው 'አትግደሉን፣ አታስገድሉን' ማለታቸው ብዙ ነርቮችን አነቃቅቷል፣ አንቀሳቅሷል። በሌላ በኩል አንድም የሌላ እምነት ስም ባልተጠቀሰበት ሁኔታ 'አትግደሉኝ' ያለን ሰው 'የእኔ እምነት ጠላት ስለሆንክ ነው' ማለት ምን አይነት ግብዝነት ነው? አሁንም ግራ የተጋቡ አንዳንድ ቢሮዎች እርስ በርስ የሚጣረስ መረጃ እያወጡ (የሰላም ሚኒስቴር፣ መብቶች ኮሚሽን etc)። ስራቸውን ላለማሰናከል ስማቸውን የማልጠቅሳቸው ሁለት አለም አቀፍ ድርጅቶች በእውነተኛ ጉዳቱ ዙርያ ምርመራ ጀምረዋል፣ ያኔ በሰው ሞት አሁን የሚሳለቅ ሁሉ ይገባዋል፣ የሚገባው አይነት ፍጥረት ከሆነ። @EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ — tgindex