Big Habesha Tech
Статистикаበተመሳሳይ ሰምና profile እንደትጭበርበሩ። This is my only username @bighabesha
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 07:59
- Постов за неделю
- 8
- Всего постов
- 95
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 11 606
- 1/48двое суток
- 15 271
- 1/72трое суток
- 16 470
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
ስድስትና ከዚያ በላይ በሚሆኑ የአሜሪካ ግዛቶች የሚገኙ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያዎች በሃከሮች ተጠቁ! በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች (በተለይም በMinnesota፣ Georgia እና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች) የሚገኙ የህዝብ የውሃና የፍሳሽ አገልግሎት ጣቢያዎች በኢራን የሃከር ቡድኖች ከባድ የሳይበር ጥቃት እንደደረሰባቸው ተገለጸ። CISA፣ FBIና EPA ባወጡት የጋራ መግለጫ አብዛኞቹ አነስተኛ የከተማ ውሃ ጣቢያዎች የውሃ ፍሰቱንና ግፊቱን ለመቆጣጠር እንደ PLCs (Programmable Logic Controllers) እና HMIs (Human Machine Interfaces) የመሳሰሉ ኦፕሬሽናል ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመው ጥቃቱን እንዳደረሱ ገልፀዋል። እነዚህ መሳሪያዎች በቀጥታ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ ስለሆኑና ደካማ የይልፍ ቃል የሚጠቀሙ በመሆናቸው ሃከሮቹ በቀላሉ እንዲገቡ አድርጓቸዋል። ሃከሮቹ ሲስተሙ ውስጥ ከገቡ በኋላ የትዕዛዝ መቆጣጠሪያ ፓስወርዶችን በመቀየር የውሃ ግፊት መቆጣጠሪያዎችንና ሴንሰሮችን በማበላሸት አጠቃላይ ሂደቱን አስተጓጉለውታል። ጥቃቱ በደረሰባቸው አካባቢዎች የውሃ ግፊት ቀንሶ ታይቷል። በርካታ የውሃ ጣቢያዎች የኢንተርኔት ሲስተማቸውን አጥፍተው ወደ ድሮው በእጅ የመቆጣጠር (Manual Mode) አሰራር እንዲመለሱ ተገደዋል። የአሜሪካ የደህንነት ተቋማት የጥቃቱን አፈጻጸምና የሃከሮቹን አሰራር (Signature) በማየት ከኢራን መንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደ Handalaና IRGC የተሰኙ ቡድኖች እንደሆኑ ገምተዋል። ኢራን ቀደም ሲል በ2023 በPennsylvania የውሃ ጣቢያዎች ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽማ እንደነበር ይታወሳል። ይህ አጋጣሚ ለዓለም አቀፍ የመሰረተ ልማት (Critical Infrastructure) ዘርፍ ትልቅ ትምህርት የሰጠ ሲሆን በተለይም የኢንዱስትሪ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ከኢንተርኔት ጋር ሲገናኙ ጥብቅ Multi-Factor Authenticationና አስተማማኝ የCybersecurity ጥበቃ ሊኖራቸው እንደሚገባ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች አሳስበዋል።
3ኛ ዙር የContent creating Bootcamp በዚህ የSocial media ዘመን ማንኛውም ሰው Content creator በመሆን ህይወቱን መቀየር ይችላል። በእያንዳዱ ቀን ያልተደጋገሙና ያልተንዛዙ ሃሳቦችን በጥልቀት እንማማራለን። ⚫Social media ከ0 ጀምረን እንዴት እናድጋለን? ⚫ኢትዮጵያ ወስጥ አዋጪ የSocial media Platforms ምን ምን ናቸው? ⚫በSocial media አማካኝነት እንዴት ገንዘብ እንሰራለን? ⚫እንዴት ጠንካራ የማህበራዊ ሚዲያ Community እንፈጥራለን? ⚫ይህንን community እንዴት ወደ ገንዘብ እንቀይራለን? ⚫እንዴት TikTok፣ YouTube፣ Facebookና Telegram channel እናሳድጋለን። ⚫እንዴት content type (niche) ይመርጣል? ⚫የContent Idea እንዴት እናገኛለን? ⚫እንዴት content Type እንመርጣለን? ⚫እንዴት Research እናደርጋለን? ⚫እንዴት Script እንፅፋለን? ⚫እንዴት እንቀርጻለን? ⚫እንዴት በቀላሉ Edit እናደርጋለን? ፕሮግራሙ ካለቀ በኋላ የጋራ Group ይከፈትና እየተጋገዛችሁ ማደግ የምትችሉበት መንገድ ይመቻቻል። 🎁 ልዩ ስጦታ፦ ስልጠናውን ለሚመዘገቡ በሙሉ ከ800 በላይ ጠቃሚ ድረ-ገጾችን የያዘ E-book በነፃ ይሰጣል። ክፍያ: ሙሉ ፕሮግራሙን ለመከታተል 399 ብር ብቻ ለመመዝገብ learn.bighabesha.com ወይም @bighabesha Batch 1ና 2 ላይ ትምህርቱን የተከታተላችሁ ሃሳባችሁን በcomment መግለፅ ትችላላችሁ።
Telegram 13 አመት ሞላው። ተወዳጁ የSocial media platform Telegram በወንድማማቾቹ Pavel Durovና Nikoli Durov ከተመሰረተ ዛሬ 13ኛ ዓመቱን ይዟል። በ2013 ዋና መስርያ ቤቱን ጀርመን በርሊን በማድረግ ስራውን የጀመረው ቴሌግራም ለተወሰኑ አመታት ምንም አይነት ገቢ የማያስገባና በየወሩ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለስራ ማስኬጅ የሚያስወጣ Social media platform ነበር። ከሌሎች የማህበራዊ ሚድያ መተግበሪያዎች በተሻለ የተጠቃሚዎቹን መረጃ ሚስጥራዊነት እንደሚጠብቅ የሚነገርለት ይህ አፕ በአጭር ጊዜ ውስጥ በብዙዎች ዘንድ በመወደድ ስኬት ማስመዝገብ ጀመረ። ከመንግስታዊ ተፅዕኖም ነፃ በመሆኑና ከዋና ተገዳዳሪው Whatsapp የተሻለ ብዙ ፊቸሮች ስለጨመረ በብዙዎች ዘንድ ለመወደድ በቃ። በሚቀጥሉት ጥቂት አመታትም በተጠቃሚ ቁጥር በሜታ ስር ከሚተዳደሩት facebook messenger እና WhatsApp ሊበልጥ እንደሚችል ይጠበቃል። በአሁኑ ሰአት ዋና መስሪያ ቤቱን በዩናይትድ አረብ ኢሚሬት ዱባይ ከተማ በማድረግ ከተራ የመልዕክት መለዋወጫ አፕሊኬሽንነት ከፍ በማለት የክሪፕቶከረንሲ ቢዝነስ አካቶ እየሰራ ይገኛል። በአሁኑ ሰአት እጅግ ትርፋማ ከሆኑት የsocial media ፕላትፎርሞች ውስጥ የሚካተተው ቴሌግራም በአለም ዙሪያ ብዙ ሰራተኞች የሚያስተዳደር ትልቅ ድርጅት ሊሆን ችሏል። የብዙ ሰዎች ህይወትም በዚህ app አማካኝነት እየተቀየረ ይገኛል። የዋና መስራቹ Pavel Durov አጠቃላይ ሀብት $15.5B እንደሚገመት Forbes ዘግቧል። 🎉🎉Happy Birthday Telegram🎉 🎉 ✍እስኪ ቴሌግራም ስትጠቀሙ ስንት አመት ሞላችሁ? አካውንት የከፈተችሁበትን አጋጣሚ ካስታወሳችሁት በcomment አካፍሉን። እኔ 10 ዓመት!! @bighabesha_softwares
🎆በ2019 ገንዘብ ላኩልኝ የለም💰 ከሰሪ ጋር ስሩ የክረምት ቻሌንጅ ምዝገባ ላይ ነን! 🔜በ2️⃣0️⃣1️⃣9️⃣ ከትምርታችሁ ጋር እየሰራችሁ ተከፋይ የምቶኑባቸውን ስኪሎች ✔️Cinematography & Photography ✔️Digital Marketing ✔️Video Editing ✔️Graphics Design ለትክክለኛ ቢዝነሶች እየሰራችሁ በዚህ ክረምት ተማሩ! 📌እስከ 50% ቅናሽ 📌20ሺህ ብር Value ያለው online course በነጻ 📌Upwork, Fiver እና Freelancing websites ላይ ለመስራት የምትማሩበት ፓኬጅ ያካትታል! 🔗ከታች ባለው ሊንክ ተመዝገቡ!👇 አድራሻችን መገናኛ መሰረት ደፋር ህንጻ 10ኛ ፎቅ። ወይም በ0988428842 ይደውሉልን! https://docs.google.com/forms/d/1tRr8bE_UabR4by9DiYBxw7ykgYNpcMRbiGZ-cJnHsFs/edit
የGemini ዕለታዊ የተጠቃሚ ቁጥር 1 Billion መድረሱን የGoogle CEO Sundar Pichai አስታወቀ። ይህም 1B የተጠቃሚ ቁጥር የደረሰ 14ኛው የGoogle product መሆን ችሏል። ✍️እናንተ በብዛት የምትጠቀሙት AI chatbot ምንድን ነው? @bighabesha_softwares
3ኛ ዙር የContent creating Bootcamp Social media ላይ scroll በማድረግ ብቻ ዕድሜአችሁን አታባክኑ።✋ በ5 ቀን ብቻ መሰረታዊ ነገሩን በመማር Professional content creator የመሆን መንገዳችሁን ጀምሩ። ⏲ፕሮግራሙ ለተከታታይ 5 ቀናት ከምሽት 3 ሰአት እስከ 5 ሰዕት ይሆናል። 🎁 ልዩ ስጦታ፦ ስልጠናውን ለሚመዘገቡ በሙሉ ከ800 በላይ ጠቃሚ ድረ-ገጾችን የያዘ E-book በነፃ ይሰጣል። ክፍያ: ሙሉ ፕሮግራሙን ለመከታተል 399 ብር ብቻ ለመመዝገብ learn.bighabesha.com ወይም @bighabesha
ሰበር ዜና!! የYouTube የMonitization መስፈርት ጭማሪ ተደረገበት። YouTube የዩትዩብ ክሬተሮች ከቻናላቸው ገንዘብ ለማግኘት (Monetized) ለመሆን የሚያስፈልገውን የWatch Hours መስፈርት በእጥፍ ማሳደጉን ይፋ አደረገ። ከዚህ ቀደም አንድ ቻናል Monetize ለመሆን ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 4,000 Watch Hoursና 1,000 Subscribers እንዲሁም በshorts በ90 ቀናት ውስጥ 10 Million እይታ ማሟላት ይጠበቅበት ነበር። አሁን በተሻሻለው ህግ መሰረት ግን የMonetization ማመልከቻ ለማስገባት ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 8,000 Watch Hoursና 20 Million የshorts ዕይታ ማሟላት ይኖርባቸዋል። የSubscribers መስፈርት ከ1,000 Subscribers ጭማሪ አልተደረገበትም። ይህም ተግባራዊ የሚሆነው ከFebruary 1 ጀምሮ ነው። ይህ አዲስ መመሪያ በተለይም ገና በማደግ ላይ ላሉ Small Creators ትልቅ መሰናክል የሚፈጥር ሲሆን Monetized ለመሆን የሚወስደውን ጊዜ በእጥፍ ያራዝመዋል። ሆኖም ግን አስቀድመው Monetized የሆኑ ቻናሎች ላይ ተግባራዊ አይደሩግም ተብሏል። ✍️YouTube መስራት የጀመራችሁ ወይም ለመጀመር ያሰባችሁ ምን ተሰማችሁ? @bighabesha_softwares
Engadget "AI የሳይበር ደህንነትን በፍጥነት እና በሚያስፈራ መልኩ እየቀየረው ነው!" Engadget ባወጣው አዲስ ትንተናዊ ዘገባ የGenerative AIና AI Agents እድገት የሳይበር ደህንነትን (Cybersecurity) አለም ሙሉ በሙሉ እየቀየረው መሆኑን አስታወቀ። AI ለደህንነት መጠበቂያነት ወይም Defense አገልግሎት እየዋለ ቢሆንም ለአጥቂዎች (Attackers) ግን ጥቃቶችን በከፍተኛ ፍጥነትና ብልሃት ለመፈጸም አዲስ መሳሪያ ሆኖላቸዋል። AI የሳይበር ጥቃቶችን በሚያስፈራ መልኩ የቀየረባቸው 4 መንገዶች ⚫Hyper-personalized Phishing: ከዚህ ቀደም የPhishing ኢሜይሎች በGrammar ስህተትና በቀላሉ ሊለዩ በሚችሉ ጥቃቅን የማታለያ መንገዶች ይጠቀሙ ነበር። አሁን ግን AI የአንድን ግለሰብ Social Media፣ አጻጻፍና መረጃዎች Analysis በማድረግ ፍጹም አሳማኝ የሆኑ የPhishing ኢሜይሎችን እና Deepfake ድምፆችን በሰከንዶች ውስጥ ያዘጋጃል። ⚫Autonomous Vulnerability Exploitation: አጥቂዎች AI Agentዎችን በመጠቀም በሺዎች በሚቆጠሩ Systemዎች ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን (Vulnerabilities) ያለ ሰው ጣልቃገብነት 24/7 Scan እንዲያደርጉ እና የተገኙ ክፍተቶችን በራሳቸው ጊዜ እንዲያጠቁ (Automated Attack) ማድረግ ጀምረዋል። ⚫Polymorphic Malware: በAI የታገዙ Malwareዎች Antivirusና Security Tools እንዳይይዟቸው ሲሉ የራሳቸውን Code መልክ በየጊዜው ይቀይራሉ። ይህም ባህላዊ የSecurity Controls ጥቃቱን መለየት እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል። ⚫Code Generation for Hackers፦ የኮዲንግ እውቀት የሌላቸው ሰዎች እንኳን AIን በመጠቀም ውስብስብ የሆኑ የHacking Scripts እና Exploit Codes እንዲጽፉ መንገድ ከፍቶላቸዋል። በዘገባው መሰረት የSecurity ተመራማሪዎች ትልቁ ስጋት Asymmetry of Speed ነው። ጥቃት አድራሾች AIን በመጠቀም በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ አዲስ Attack Vector መፍጠር ሲችሉ ጥቃቱን የመከላከያ (Defense) ሲስተሞች ግን አደጋውን ለይተው ለመመለስ ደቂቃዎችን ወይም ሰዓታትን ይወስድባቸዋል። ስለሆነም ድርጅቶች ከእንግዲህ በሰው ሀይል ብቻ ሳይሆን ራሱን በራሱ የሚያስተካክል (Autonomous AI-driven Defense) የደህንነት ስርአትን መገንባት ግዴታ እንደሆነባቸው ተመራማሪዎቹ አሳስበዋል። ለ24 ሰአት የሚቆይ ልዩ ቅናሽ!! ከዚህ በፊት 499 ብር ይሸጥ የነበረው ከ800 በላይ ጠቃሚ ዌብሳይቶችን የያዘው Ebook በ299 ብር ብቻ መግዛት ትችላላችሁ። https://ye-buna.com/bighabesha?ref=product_detail&product=6a01d55e96ce7_bighabesha @bighabesha_softwares
Google messages ስትጠቀሙ RCS On ማድረጋችሁ ምን ይጠቅማችኋል? ⚫Message ስትልኩ ብር አይቆርጥባችሁም። ነገር ግን Data ማብራት ይጠበቅባችኋል። የምትልኩለት ሰው Google messages የሚጠቀምና Online መሆን አለበት። ⚫የGemini AI እዛው Google messages ላይ መጠቀም ትችላላችሁ። ⚫ የድምፅ መለዕክት፣ ፎቶ፣ location፣ GIFና Sticker መላላክ ትችላላችሁ። ⚫End-to-End encrypted ነው። ያ ማለት የምትልኩትን መልዕክት ማንኛውም service provider (ቴሌ ወይም ሳፋሪኮም) የማየት እድል የላቸውም። ግን ሁለታችሁም Google messages ከተጠቀማችሁና E2EE on ከሆነ ብቻ ነው። ⚫Message የላካችሁለት ሰው የላካችሁትን መልዕክት ማየቱና አለማየቱን ማዎቅ ትችላላችሁ። እንዲሁም type በሚያደርግበት ጊዜ Typing....ይላችኋል። እዚ ጋ ጥንቃቄ ማድረግ ያለባችሁ RCS on አድርጋችሁ Message ስትልኩ እናንተ data ካላበራችሁ message error ይላችኋል። የምትልኩለት ሰውም Online ካልሆነ የላካችሁት message አይገባለትም። ይህን ነገር ለማስተካከል የምትልኩለት ሰው profile ላይ ገብታችሁ "Only send SMS and MMS messages" የሚለውን On ማድረግ ይጠበቅባችኋል። RCS Chat እንዴት on እንደሚደረግ ማዎቅ ከፈለጋችሁ https://t.me/bighabesha_softwares/1779 ➡️Gemini Pro መግዛት ከፈለጋችሁ inbox me @bighabesha @bighabesha_softwares
Google Assistant ሊዘጋ ነው! ግዙፉ የቴክኖሎጂ ድርጅት Google በብዙ ሚሊዮን አንድሮይድ ተጠቃሚዎች ለዓመታት ስንጠቀምበት የነበረውን Google Assistant ሙሉ በሙሉ ሊዘጋው መሆኑን ይፋ አድርጓል። በአዲሱ የGenerative AI Gemini እንደሚተካ ተገልጿል። አሁን ላይ በአንድሮይድ ስልኮች እና ስማርት device ላይ ዋናው የድምፅ ረዳት (Default Voice Assistant) ሆኖ የሚሰራው Gemini ነው። የGoogle Assistant ሞዴል አሁን ካለው የGenerative AI ቴክኖሎጂ ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ ወደ Gemini እንዲሸጋገሩ ጉግል ግፊት እያደረገ ይገኛል። ኩባንያው አገልግሎቱን September 2026 ከአገልግሎት ውጪ እንደሚያደርገው 9to5Google ዘግቧል። ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ!! ከዚህ በፊት 499 ብር ይሸጥ የነበረው ከ800 በላይ ጠቃሚ ዌብሳይቶችን የያዘው Ebook በ299 ብር ብቻ መግዛት ትችላላችሁ። https://ye-buna.com/bighabesha?ref=product_detail&product=6a01d55e96ce7_bighabesha 499 ብር 👉 299 ብር @bighabesha_softwares
Telegram ከApp Store ላይ ለጥቂት ጊዜ ከወረደ በኋላ ተመለሰ! Telegram በApple App Store ላይ ለጥቂት ሰዓታት ታግዶ ከቆየ በኋላ ድጋሚ ወደ ቦታው መመለሱን ኩባንያውና አፕል አስታወቁ። እንደ Reutersና Bloomberg ዘገባዎች ከሆነ Apple መተግበሪያውን ከApp store ላይ ለጊዜው ያነሳበት ዋና ምክንያት የContent Moderation እና Guidelines ጥሰት እንደሆነ ተጠቅሷል። Apple ባደረገው Review በTelegram ላይ ከህጻናት ጥቃት ጋር የተያያዙ ተገቢ ያልሆኑ ይዘቶች (Child Sexual Abuse Material) መለቀቃቸውን ተከትሎ የአፕልን ጥብቅ ደንቦች መጣሱን አረጋግጧል። Apple ችግሩን ካሳወቀ በኋላ የTelegram ደቨሎፐሮች ወዲያውኑ ህገ-ወጥ ይዘቱን ከፕላትፎርሙ ላይ በማስወገድና ይዘቱን የለቀቀውን User Account በዘላቂነት Ban በማድረጋቸው መተግበሪያው በድጋሚ በApp Store ላይ ተመልሷል። መተግበሪያው በወረደበት ሰዓት ተጠቃሚዎች በApp Store ላይ ቴሌግራምን ሲፈልጉ "The page you're looking for can't be found" የሚል መልእክት ያሳያቸው ነበር። አጋጣሚው በApple App Store ላይ ብቻ የተከሰተ ሲሆን በGoogle Play Store እና በMac App Store ላይ ምንም አይነት መስተጓጎል አልነበረም። ⚠️አካውንታችሁ ban እንዳይደረግ ቴሌግራም ላይ share የምታደርጉትን ነገር ጥንቃቄ አድርጉ። @bighabesha_softwares
ጠቃሚ ዌብሳይቶች ዝርዝር ⚫ https://web3.university A massive hub of free tutorials about blockchain development ⚫https://medscape.com Primarily for professionals, but offers free, high-level clinical information and drug interaction checkers. ⚫ https://linuxjourney.com Linux learning platform ⚫ https://www.iconfinder.com/ Millions of icons that you can use for your projects ⚫ https://zoom.earth/ Live satellite weather maps that look strangely satisfying ⚫ https://brilliant.org Interactive, visual lessons in math, science, and computer science ⚫https://chess.com learn, play, and watching competitive chess at all skill levels ⚫https://www.edge.org/ Intellectual discussions and debates from leading thinkers and scientists ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ!! ከዚህ በፊት 499 ብር ይሸጥ የነበረው ከ800 በላይ ጠቃሚ ዌብሳይቶችን የያዘው Ebook በ299 ብር ብቻ መግዛት ትችላላችሁ። https://ye-buna.com/bighabesha?ref=product_detail&product=6a01d55e96ce7_bighabesha 499 ብር 👉 299 ብር
ከታች የተዘረዘሩትን ማለትም ⚫Telegram Premium ⚫Telegram Star ⚫TikTok Video Boost & followers ⚫Facebook and Instagram Boost ማግኘት ከፈለጋችሁ Contact me➡️ @bighabesha እንዲሁም በተለያየ category ለoffice ሰራተኞች፣ ለContent creators፣ ለተማሪዎች እንዲሁም አስተማሪዎች የሚሆኑ ከ400ና 800 በላይ አሪፍ አሪፍ ድረገፆችን የያዙ Ebook በ199ና 499 ብር ብቻ ማግኘት ትችላላችሁ። ➡️400+ websites https://ye-buna.com/bighabesha?ref=product_detail&product=6a0227768ab06_bighabesha ➡️800+ Websites https://ye-buna.com/bighabesha?ref=product_detail&product=6a01d55e96ce7_bighabesha ⚠️አስታውሱ እኔ ለማንም ቀድሜ inbox አላደርግም።🙅 @bighabesha_softwares
видео или голосовое, без подписи
ኬንያ ከTether ጋር በመተባበር USDTን ለSettlement የመጠቀም ሙከራ ጀመረች። የኬንያው ግዙፍ የአክሲዮንና የሴኩሪቲስ ገበያ Nairobi Securities Exchange (NSE) በአለም አቀፍ ደረጃ በUSDT Stablecoin የሚታወቀው Tether ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት መፍጠሩን ይፋ አደረገ። ይህ ትብብር 26.4 ቢሊዮን ዶላር ካፒታል ባለው የኬንያ የካፒታል ገበያ ውስጥ ክፍያዎችን (Settlement) በUSDT ለመፈጸም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ነው። ከዚህ ቀደም የኬኒያ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ኢንቨስተሮች በNSE ገበያ ውስጥ Stock፣ Bondና ሌሎች Financial Assets ሲገዙ በFiat Currency ወይም በኬንያ ሽልንግና በአሜሪካን ዶላር ብቻ በኩል የነበረው የSettlement ሂደት ቀናት ይወስድ ነበር። Tether USDTን በመጠቀም ግን አጠቃላይ ሂደቱን በBlockchain ቴክኖሎጂ አማካኝነት በሰከንዶች ውስጥ በዝቅተኛ የTransaction Fee ለማከናወን ያስችላል። ይህ ስምምነት የዶላር እጥረት በሚያጋጥምበት በአፍሪካ ገበያ ውስጥ USDTን እንደ Settlement Currency መጠቀም የውጭ ኢንቨስተሮች በቀላሉ ወደ ኬንያ ገበያ ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ በር ይከፍታል ተብሏል። ይህ ሙከራ የሚካሄደው በኬንያ Capital Markets Authority (CMA) የቁጥጥር ማዕቀፍ ስር ሲሆን የደህንነት እና ህጋዊነት መስፈርቶችን የጠበቀ መሆኑ ይረጋገጣል። NSE ባወጣው መግለጫ "ይህ አጋርነት የኬንያን የካፒታል ገበያ ወደ አዲሱ Digital Economy እና Web3 ማስገቢያ ትልቅ እርምጃ ነው። የTrading እና Settlement ሂደቶችን በማዘመን አጠቃላይ የገበያችንን Liquidity ያሳድጋል።" ብሏል። Tether በበኩሉ "አፍሪካ ለCrypto እና Stablecoin አጠቃቀም በጣም ፈጣን እድገት የምታሳይ አህጉር ናት። ከNSE ጋር መስራታችን USDTን Trading ብቻ ሳይሆን ለሀገር አቀፍ የካፒታል ገበያ infrastructure ደረጃ ለመጠቀም መንገድ ይከፍታል።" ማለቱን CoinMarket ዘግቧል። ጎረቤታችን ኬንያ የDigital finance ህጎና ስርዐቶችን በማውጣት ከቴክኖሎጂው እየተጠቀመች ሲሆን እኛ ሃገር ግን ዜጎች ጭራሽ በቴክኖሎጂው ተጠቅመው ሃብት እንዳያፈሩ የተለያዩ ክልከላዎች እየወጡ ነው። ✍እስኪ በዚ ጉዳይ ያላችሁን ሃሳብ በcomment አስቀምጡ። @bighabesha_softwares
Breaking Google በgemini omni አማካኝነት በነፃ እስከ 10 የሚደርስ video Generate ማድረግ እንደምችሉ አስታውቋል። Gemini ክፍቱና የ+ ምልክቱን ነክታችሁ Video የሚለውን በመምረጥ የፈለጋችሁትን አይነት video create ማድረግ ትችላላችሁ። ይህ ዕድል የሚቆየው እስከ august 4 ድረስ ብቻ ነው። ሞክሩት። @bighabesha_softwares
በቅርቡ ይፋ የሆነውን የሳምሰንግ አዲስ ታጣፊ ስልክ Galaxy Z Fold 8 Review ስልኩ አጠቃላይ rating 8.9 / 10 ከፍተኛ ነጥብ ያገኘ ሲሆን ዘንድሮ ሳምሰንግ የDesign ለውጥ ካደረገባቸው ስልኮች ቀዳሚው ነው። ስልኩን ከቀደሙት የFold ስልኮችና ከUltra series የበለጠ ተመራጭ አድርጎታል ብሏል። ⚫አዲስ Aspect Ratio (Passport Shape): የቀደሙት የFold ስልኮች ረዥምና ጠባብ ነበሩ። Z Fold 8 ግን አጭርና ሰፊ (Wider) ሆኖ ተሰርቷል። ⚫የውጪ ስክሪን (Cover Screen): 5.5-inch AMOLED (10:16 aspect ratio) ሲሆን እንደ ፓስፖርት ሰፋ ያለ በመሆኑ ስልኩን ሳትከፍቱት መልእክት ለመጻፍ እና ካርታ ለማየት በጣም ይመቻል። ⚫የውስጥ ስክሪን (Main Display): 7.6-inch AMOLED (4:3 aspect ratio) አለው። ይህም ቪዲዮዎችን ሲያዩ የሚፈጠረውን ጥቁር ፍሬም (Letterboxing) ይቀርፋል። ለGamingና ለMultitasking በጣም ምቹ ነው። ⚫Flex Titanium & Anti-Glare Coating: በስክሪኑ ስር Titanium alloy የተጨመረበት ሲሆን የስክሪኑ መታጠፊያ መስመር ከበፊቱ በበለጠ እንዳይታይ አድርጎታል። አዲሱ Anti-glare coating ደግሞ የፀሐይ ብርሃን ነጸብራቅን ይከላከላል ተብሏል። ⚫ቀላልና ቀጭን፦ ስልኩ በታሪክ ቀላል የተባለው የFold ስልክ ሲሆን ክብደቱ 201 ግራም ብቻ ነው። ሲታጠፍ 9.7mm ውፍረት አለው። 🚀 ዋና ዋና specificationና Performance ⚫Processor: በቅርቡ የወጣው Snapdragon 8 Elite Gen 5 ቺፕሴት ተገጥሞለታል። ⚫RAM & Storage: እስከ 16GB RAM እና 1TB Storage ⚫Battery: 4,800mAh ⚫Brightness: የሁለቱም ስክሪኖች Peak Brightness እስከ 3,000 nits ይደርሳል። ⚫Durability: IP48 Dust & Water resistance Gorilla Glass Victus 2 እና 3 ተጠቅሟል። ደካማ ጎኖች (Cons): ስልኩ በጣም ውድ የሚባል ሲሆን ዋጋውም ከ1,900 ዶላር ጀምሮ ይሸጣል ተብሏል። ሌላው Dedicated Zoomና Telephoto Camera የለውም። 50MP Main + 50MP Ultra-wide ብቻ ነው ያለው። እንደ MagSafe ያሉ Magnetic accessories ለመጠቀም ተጨማሪ Case ያስፈልገዋል። የ5 ቀን content creating course መማር ከፈለጋችሁ። Learn.bighabesha.com @bighabesha_softwares
Nike የሰራው ዘመናዊ ነጠላ ጫማ ከስፖርትና ከከባድ የሰውነት እንቅስቃሴ በኋላ የእግርን ድካም ለመቅረፍ የሚረዳ አስደናቂ የቴክኖሎጂ ውጤት ይፋ ሆኗል። ታዋቂው የጫማ አምራች ኩባንያ Nike ከቴክኖሎጂ ተቋሙ Hyperice ጋር በመተባበር «Nike Air Zoom Hyperslide» የተሰኘ ሙቀት የሚሰጥና ማሳጅ የሚያደርግ ነጠላ ጫማ ሰርተዋል። በጫማው የላይኛው ማሰሪያ ላይ በማግኔት የሚጣበቁ አነስተኛ መሳሪያዎች አሉት። እነዚህ መሳሪያዎች ለእግር ሙቀትና የVibration ማሳጅ ይሰጣሉ። ጫማው ከ42.8°C እስከ 47.2°C የሚደርስ የሙቀት አማራጭ ሲኖረው እግርን ለማዝናናትና ደም በስርዓት እንዲዘዋወር ለማድረግ 3 የተለያዩ የንቅናቄ ፍጥነት አማራጮች ተካተውበታል። በብሉቱዝ አማካኝነት ከስልክ መተግበሪያ ጋር በማገናኘት ወይም በራሱ በጫማው ላይ ባሉት ቁልፎች የሙቀቱንና የንቅናቄውን መጠን በቀላሉ ማስተካከል ይቻላል ተብሏል። ጫማው በስፖርት ወይም ረጅም መንገድ በመራመድና ቆሞ በመዋል የሚፈጠርን የእግር ህመምና ድካም ያስታግሳል የተባለ ሲሆን በUSB-C አማካኘነት ቻርጅ ይደረጋል። ይህ ጫማ September 29 በ249 ዶላር ለገበያ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። ቴሌግራም አካውንታችሁን Premium ማድረግ ከፈለጋችሁ @bighabesha ላይ ፃፉልኝ። @bighabesha_softwares
Wordን ወደ pdf፣ pdfን ወደ word፣ wordን ወደ ppt፣ pptን ወደ word፣ pdfን ወደ ppt፣ pptን ወደ pdf መቀየር ከፈለጋችሁ እነዚህን ድረገፆች መጠቀም ትችላላችሁ። ⚫ zamzar.com ⚫ smallpdf.com ⚫ ilovepdf.com እነዚህን የመሳሰሉ የተለያዩ ጥቅም ያላቸው ምርጥ ምርጥ ከ800ና ከ400 በላይ ድረገፆችን የያዙ ebook click አድርጋችሁ ማግኘት ትችልላችሁ። ➡️400+ websites, Price: 199 Birr https://ye-buna.com/bighabesha?ref=product_detail&product=6a0227768ab06_bighabesha ➡️800+ Websites, Price: 499 Birr https://ye-buna.com/bighabesha?ref=product_detail&product=6a01d55e96ce7_bighabesha @bighabesha_softwares
የMeta አዲስ Application Meta ለፌስቡክ ማርኬትፕሌስ ሻጮችና ነጋዴዎች ንግዳቸውን በቀላሉ ማስተዳደር የሚያስችላቸውን “Seller” የተሰኘ አዲስ የተለየ አፕሊኬሽን ይፋ አድርጓል። 📌 የአፕሊኬሽኑ ዋና ዋና ባህሪያትና ጥቅሞች፦ ⚫በAI የተደገፈ ዕቃዎችን የመመዝገብ ሂደት፦ የዕቃውን ፎቶ ብቻ በመጫን Meta AI ራሱ ርዕስ፣ መግለጫ (Description)፣ ምድብና ዋጋ በሰከንዶች ውስጥ ያዘጋጃል። በተጨማሪም በርካታ ዕቃዎችን በአንድ ጊዜ መመዝገብ ያስችላል። ⚫Unified Inbox፦ ከገዢዎች የሚመጡ ጥያቄዎችን እና መልዕክቶችን በየዕቃው አይነት ለይቶ በአንድ ቦታ በማደራጀት ቀልጣፋ ምላሽ ለመስጠት ያግዛል። ⚫Inventory Management፦ ያሉትን ዕቃዎች ማየት፣ ማስተካከል፣ ዋጋ መቀየር እና አዳዲስ ዕቃዎችን መቆጣጠር ያስችላል። ⚫Performance Insights፦ የትኞቹ ዕቃዎች ብዙ እይታ (Views) እና መልዕክት እንዳገኙ የሚያሳዩ መረጃዎችን በማቅረብ የተሻለ የንግድ ውሳኔ ለመስወሰን ያግዛል። አፑ ከአሁኑ ጀምሮ በአሜሪካ ለሚገኙ ዕድሜያቸው 18ና ከዚያ በላይ ለሆኑ የiOS (App Store) ተጠቃሚዎች ክፍት ሆኗል። የWeb እና የAndroid አፕሊኬሽኖች በቅርቡ እንደሚለቀቁ ተገልጻል። @bighabesha_softwares