tgindex
Mack Computer Technology 🧑‍💻

Mack Computer Technology 🧑‍💻

Статистика

ይህ ቻናል ስለ ኮምፒውተር እና ቴክኖሎጂ የሚያወራ ሲሆን የ ኮምፒውተር ሳይንስ Tip,ጥያቄዎች video ቱቶር የሚያገኙበት እንዲሆን የተከፈተ ነው። computer tutorial, free downloaded software/set up and different information about application software , security mechanism ... ያገኙበታል። https://t.me/macktech2

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
264
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
75
25 постов
Вовлечённость
28,4%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 25
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
23
1/48двое суток
26
1/72трое суток
28

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 10 авг.331из Addis_Reporter

    ለጥንቃቄ!!!! ትናንት ይሁን ከትናንት ወዲያ ይህንን መረጃ  የሰይፉ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ቀርቦ ብዙዎች ተምረውበታል። ጉዳዩን ላልሰማችሁ ለጥንቃቄ እነሆ ብሎ ዳዊት እርገጤ እንዲህ ከትቦታል። የዕድሜ ልክ ጥረቱን የተበላው የፌድራል ፖሊስ አመራሩ ባለቤት ታማ ፀበል ገባች! በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉት ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት ሽመልስ እና ቤተሰቦቻቸው፣ በዘመናዊ የዲጂታል ቀማኞች ወጥመድ ውስጥ ወድቀው ከ1.3 ሚሊየን ብር በላይ ተዘርፈዋል። ጉዳዩ የተጀመረው "ቤት ቁጭ ብሎ በወር ከ70 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር መሥራት ይቻላል" በሚል ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚወጣ አታላይ ማስታወቂያ ነው። የቤት እመቤት የሆነችው ባለቤታቸው ነገሩን አምና አፕሊኬሽኑን ስትሞክረው፤ ወደ ቴሌግራም እና ዋትስአፕ ግሩፖች በመግባት "አሊባባ ኦንላይን ንግድ" በሚባል አደገኛ መዋቅር ውስጥ ትገባለች። አጭበርባሪዎቹ ሰዎችን ለማጥመድ የተካኑ ስለሆኑ፣ እምነት ለማግኘት ሲሉ በመጀመሪያ 800 ብር ልከው 1,500 ብር ይመልሱላቸዋል። ቤተሰቡም "ነገሩ እውነት ነው" ብሎ እንዲያምን ያደርጉታል።ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ትክክለኛው ሰቆቃ የሚጀምረው። የገንዘቡ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲመጣ፣ የራሳቸውን ቁጠባ ጨምሮ ከውጭ ሀገር ከምትኖር የባለቤታቸው እህት ጭምር 600,000 ብር ተበድረው ገቢ ያደርጋሉ። አጭበርባሪዎቹ ጨካኝነታቸውን አሳይተው "አንደኛ ደረጃ ነጋዴ ስለሆናችሁ ከፍተኛ ግብር መክፈል አለባችሁ" በማለት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስገቡ አድርገው በድምሩ 1.3 ሚሊየን ብር እንዲዘረፉ አድርገዋቸዋል። በሐሰተኛው መተግበሪያ ላይ 3 ሚሊየን ብር አትርፈዋል ተብሎ ይታይባቸውም ነበር፤ ነገር ግን ገንዘቡን ማውጣት ሳይችሉ ቀርተው አካውንታቸው ላይ የቀረው 59 ብር ብቻ ነው! ይህ ሁሉ አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸም ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት በሥራ ስምሪት (ፊልድ) ላይ ነበሩ። የገንዘቡን መበላት ስትሰማ የባለቤታቸው ልብ ድንጋጤን መቋቋም አቅቶት ዛሬ ላይ በጽኑ ታማ በጸበል ቦታ መንፈሳዊ ሕክምና እየተደረገላት ይገኛል። የዕድሜ ልክ ድካማቸው በአንድ ቀን ባዕድ ኃይል መናጋቱ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ከቷቸዋል። Via_ጉርሻ page @Addis_Reporter @Addis_Reporter

  • 3 авг.50из Wcuniversity

    #NGAT_Registration_Extended የተከበራችሁ ዉድ የሁለተኛ ድግሪ አመልካቾች የNGAT መመዝገቢያ ቀን እስከ ራቡዕ መራዘሙንና የመፈተኛ ቦታ/ዩኒቨርሲቲ መቀየር ለምትፈልጉ እስከዛው ቀን የሚቻል መሆኑን ተገልጿል። የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም ተራዝሟል። የመመዝገቢያ ሊንክ 👇 https://ngat.ethernet.edu.et ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ ያስፈልጋል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር ሲሆን፤ በምዝገባ ወቅት በቴሌብር በኩል መክፈል ይጠበቅባችኋል። ምዝገባው በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። የፈተና መስጫ ጊዜው በቀጣይ እንደሚገለፅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

  • ለውድ ደንበኛችን፡ የጥንቃቄ መልዕክት አለን። ‎* ‎ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ እርስዎ በአካል ወደ ባንካችን ቅርንጫፎች ሳይመጡ በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ ምንም አይነት አገልግሎትም ሆነ የአሠራር ሂደት የሌለን መሆኑን እያሳወቅን፤ የይለፍ ቃልዎን ለሌላ ሶስተኛ ወገን ተጋላጭ ባለማድረግ በጥንቃቄ እንዲገለገሉ እናሳውቃለን፡፡ እንዲሁም “ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው” በሚል በስልክ በሚላክ መጠይቅ ምንም አይነት መረጃዎን እንደማንጠይቅዎ በመረዳት እራስዎን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ እናሳስባለን፡፡ ‎በተጨማሪም ፦ ⦁ ከባንክ ነው በሚል የሚደርስዎትን የስልክ ጥሪ ትክክለኛነት ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ወደ 951 በመደወል ሳያረጋግጡ ምንም ዓይነት እርምጃ አይውሰዱ፣ ⦁ የአፕሊኬሽንም ሆነ USSD ‎ተጠቃሚ ከሆኑ የይለፍ ቃልዎን ከአራት እስከ አስር ዲጂት(ቁጥሮች) ይጠቀሙ፤ ⦁ የሞባይል መተግበሪያዎችን (Applications) ወይም ማስፈንጠሪያዎችን (Links) ከማይታወቅና ትክክለኛ ካልሆኑ ምንጮች ስልክዎ ላይ አይጫኑ፤ ⦁ ማንኛውንም አይነት መተግበሪያ ከ-Playstore እና ከAppstore ብቻ አውርደው ይጠቀሙ፤ ⦁ የዲጂታል የባንክ አገልግሎት የሚስጥር ቁጥርዎን ለማንም አያሳውቁ፤ ሞባይል ስልክዎ ላይ ወይም ማንኛውም ነገር ላይ አይፃፉ፣ ጠንካራ የሚስጥር ቁጥር ይጠቀሙ፣ ⦁ ጓደኛ ወይም ዘመድ በመምሰል በማንኛውም አይነት የማህራዊ ሚዲያን በመጠቀም የገንዘብ ዝውውር/ብድር ሲጠየቁ ክፍያውን ከመፈፀምዎ በፊት መልዕክቱ ከትክክለኛ ወገን የተላከልዎት መሆኑን ያረጋግጡ፤ ⦁ በተለያዩ ስልቶች ከሚፈፀሙ ስርቆቶችና ማጭበርበሮች እራስዎን ይጠብቁ፤ ⦁ የአሻራ ደህንነት ማጠናከሪያን ይጠቀሙ፤ ⦁ መረጃ ለማግኘት የባንካችንን ቅርንጫፎች፣ በነጻ የስልክ መስመር ወደ 951 በመደወል እና ትክክለኛ የባንካችንን የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይጠቀሙ፡፡ ⦁ የአካውንት ገቢና ወጪ ሒሳብዎን ሁሌም ይከታተሉ፤ የቀሪ ሒሳብዎን ትክክለኛነት በማረጋገጥ የማያውቁት ተቀናሽ ካለ፣ ስልኮት ከጠፋ/ከተሰረቀ፣ ከሒሳብዎ ጋር የተገናኘ ሲም ካርዶ ከጠፋ ወዲያውኑ 951 በመደወል ወይም በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኘው ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ያሳውቁ፤ ⦁ የ*889# ብቻ ተጠቃሚ ከሆኑ እባክዎ ለደህንነትዎ ይበልጥ አስተማማኝና ቀልጣፋ እንዲሁም ተጨማሪ አገልግሎት ወደሚያስገኝልዎ የሞባይል መተግበሪያ ይዛወሩ፡፡ መተግበሪያውን ለማግኘት፦ ለAndroid፦https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.mobilebanking ለIOS፦https://apps.apple.com/us/app/cbe-mobile-banking-new/id1534203410 * የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!!

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 29 июл.38из ethio_job_vacancy1

    ★ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የስራ ማስታወቂያ 100+ ክፍት ቦታዎች Addis Ababa City Education Bureau would like to invite qualified applicants for the following job positions. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2019 የትምህርት ዘመን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ክፍት የስራ መደቦች ላይ መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ 🔻Required No: 100+ 🌀ሙሉ መረጃውን ለማየት ሊንኩን ይጠቀሙ👇👇👇 https://ethiojobshub.com/addis-ababa-city-education-bureau/ Share to your friends @ethio_job_vacancy1 @ethio_job_vacancy1

  • 26 июл.52из mackcs21

    ለላርጎ ሱቅ ሽያጭ መስራት የምትችል ካለሺ @mackcs21 ...

  • ⚠️🚨 የጥንቃቄ መልእክት ⚠️🚨 ውድ ደንበኛችን፤ በWhatsApp፣ Telegram፣ Facebook፣ Email ወይም በSMS "ገንዘብ ላኩልኝ" የሚል ጥያቄ ሲደርስዎት፤ ጠያቂውን በቀጥታ በስልክ አነጋግረው ማንነቱን ሳያረጋግጡ ፍፁም ገንዘብ አይላኩ። የሒሳብዎን ወይም የዋሌትዎን (Wallet) እንቅስቃሴና ቀሪ ሂሳብም በየጊዜው የመከታተል ልምድ ያሳድጉ። ጥንቃቄዎ የገንዘብዎ ደህንነት ነው! ለሁሉም ባንክ ሒሳብዎ ጥንቃቄ አይለየዎ። ለበለጠ መረጃ https://t.me/awash_bank_official ይጎብኙን። ©አዋሽ ባንክ!

  • https://t.me/MekuYT/s/216

  • 23 июн.971из TikvahUniversity

    ውጤትዎን ይመልከቱ! ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት መታየት ጀምሯል። ውጤትዎን ለማየት 👇 https://result.ethernet.edu.et ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'Exit Examination' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ። @tikvahuniversity

  • የጥንቃቄ መልእክት! ከአጭር መልእክት፣ ከኢሜል ወይም ከማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያገኟቸውን አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን አይክፈቱ፤ እንዲሁም ገንዘብ ነክ መተግበሪያዎችን ከታወቁ የመተግበሪያ አድራሻዎች ወይም ከአገልግሎት አቅራቢው ብቻ ያውርዱ! አጠራጣሪ ሁኔታዎችን በ9090 በነጻ የጽሑፍ መልእክት ያሳውቁ። ኢትዮ ቴሌኮም

  • 18 июн.902из bighabesha_softwares

    Phishing, Smishing እና Vishing ምንድን ናቸው? ልዩነታቸውስ? በዚህ የቴክኖሎጂ አለም ላይ የሳይበር ሌቦች ሰዎችን የሚያታልሉበት ዘዴ በየቀኑ እየተቀያየረ ይገኛል። ከእነዚህ ውስጥ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉትን 3 የማጭበርበሪያ ስልቶች (Social Engineering) እና ልዩነታቸውን እንይ፡ ➡️ፊሺንግ (Phishing) ይህ በብዛት በኢሜይል አማካኝነት የሚፈጸም የማጭበርበር ተግባር ነው። አጭበርባሪዎች እንደ ታዋቂ ባንክ፣ ማህበራዊ ሚዲያ (ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ) ወይም የሥራ ባልደረባ በመምሰል የሐሰት ሊንኮችን የያዙ ኢሜይል ይልካሉ። ዓላማው የይለፍ ቃላችንን ወይም የባንክ አካውንት መረጃችንን ለመስረቅ ነው። ➡️ስሚሺንግ (Smishing) ይህ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ወይም በስልክ SMS የሚመጣ የፊሺንግ አይነት ነው። (SMS + Phishing = Smishing) ለምሳሌ፦ "የባንክ አካውንትዎ ታግዷል፣ እባክዎ በዚህ ሊንክ ገብተው ያስተካክሉ" ወይም "የስጦታ እጣ ደርሶዎታል" የሚሉ መልዕክቶች ይላካሉ። ሊንኩን ስንነካው መረጃችንን ወደሚሰርቅ የሐሰት ገጽ ይወስዳል። ➡️ቪሺንግ (Vishing) ይህ ደግሞ በስልክ ጥሪ (Voice call) የሚደረግ የማጭበርበር ተግባር ነው። (Voice + Phishing = Vishing) አጭበርባሪው በቀጥታ ስልክ በመደወል "የባንክ ሰራተኛ ነኝ" ወይም "ከቴሌኮም ነው የምደውለው" በማለት የማረጋገጫ ኮድ (OTP)፣ የባንክ ሚስጥራዊ ቁጥር (PIN) ወይም ሌላ መረጃ እንድንነግረው በንግግር ለማታለል ይሞክራል። ሶስቱም የማጭበርበርያ ዘዴዎች ሰዎችን በፍርሃት ("አሁኑኑ ካላደረጉ አካውንትዎ ይዘጋል") ወይም በደስታ ("ሽልማት ደርሶዎታል") ስሜት ውስጥ በመክተት፣ ሳናስበው ሚስጥራዊ መረጃችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ማድረግ ነው። 🛡ከአጭበርባሪዎች ራሳችንን እንዴት እንጠብቃለን? ✔️አትቸኩሉ፦ መልዕክቶች ወይም ጥሪዎች "አሁኑኑ" የሚል የጥድፊያ ስሜት የሚፈጥሩ ከሆኑ ቆም ብላችሁ አስቡ። ✔️ሊንኮችን በጥንቃቄ ተመልከቱ፦ ከማይታወቅ አካል የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን በፍጹም መንካት የለባችሁም ወይም ሁለት ጊዜ አረጋግጡ። ✔️ወርቃማው ህግ፦ ባንኮችም ሆኑ የቴሌኮም ድርጅቶች የእናንተን የማረጋገጫ ኮድ (OTP) ወይም የባንክ ሚስጥራዊ ቁጥር (PIN) በስልክ፣ በSMS ወይም በኢሜይል በፍጹም አይጠይቁም! ማንኛውም አካል ይህንን መረጃ ከጠየቃችሁ አጭበርባሪዎች መሆናቸውን እወቁ። ✍️ከነዚህ ከ3ቱ የየትኛው ተጠቂ ነበራችሁ? ሃሳባችሁን comment ላይ አካፍሉን። @bighabesha_softwares

  • 10 июн.981из TikvahUniversity

    #AAU #GAT   በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ለመውሰድ ይመዝገቡ! የ GAT ማመልከቻ ጊዜ 👇 ከግንቦት 29 እስከ ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም   ➫ https://portal.aau.edu.et ይግቡ። ➫ 'Online Exams' የሚለውን ይጫኑ። ➫ Quick Links ከሚለው ስር 'Apply for GAT' የሚለውን ይጫኑ። ➫ 'Test Taker Registration' የሚለውን ቅፅ ይሙሉ። ➫ የፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶ ያስገቡ። ➫ 'Submit' የሚለውን ይጫኑ። ➫ ሲስተሙ የሚሰጥዎን የመለያ ቁጥር ይያዙ። ➫ ቴሌብር በመጠቀም የምዝገባ ክፍያ ይፈፅሙ። ➫ አድሚሽን ቲኬትዎን በማውረድ ፕሪንት ብለው፡፡   የ GAT ፈተና በሁለት ዞሮች ይሰጣል፦ ከሐምሌ 20-24/2018 ዓ.ም እና ከነሐሴ 07-08/2018 ዓ.ም @tikvahuniversity

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

Mack Computer Technology 🧑‍💻 — tgindex