ZEMEN TECH💻|ethiopia®
Статистикаዘመኑ ስለደረሰበት አዳዲስ ቴክኖሎጂ ማወቅ እና መማር ከፈለጉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ። Dm for promotion ፦ @Ceo123kk
- Последний пост
- 3 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Android secret codes 💡ጠቃሚ 5 የስልክ ሚስጥራዊ ኮዶች:- ✅ 1. ስልካችሁ forward ተደርጎ ይሆን? (Call Forwarding Check)፦ የእናንተ ስልክ ጥሪ ወይም ሜሴጅ ወደ ሌላ ሰው እየሄደ መሆኑን ለማወቅ፦ *#61# ወይም *#62# ብላችሁ ደውሉ። "Not Forwarded" የሚል ከመጣ ሰላም ናችሁ። ቁጥር ካሳያችሁ ግን forward ተደርጓል ማለት ነው! ✅ 2. forward ከተደረገ ለማጥፋት (Deactivate All)፦ የሆነ ሰው ስልካችሁን Forward አድርጎ ከሆነ ወዲያውኑ ለማጥፋት፦ ##002# ብላችሁ ደውሉ። ማንኛውም አይነት የጥሪ ወይም የሜሴጅ Forward ወዲያውኑ ይቆማል። ✅ 3. የስልካችሁን ዝርዝር መረጃ ለማወቅ (Testing Menu)፦ ስልካችሁ ስለ ዋይፋይ፣ ስለ ባትሪ እና ስለ ኔትወርክ ያለውን ጥልቅ መረጃ ለማየት፦ *#*#4636#*#* ብላችሁ ይጫኑ። (ይህ በሁሉም ስልኮች ላይ ላይሰራ ይችላል)። ✅4. wifi fix secret code :- ችግሩ ከስልካችሁ ሆኖ wifi መቆራረጥ ዋይፋዩ አልከፍት ካላችሁ *#2663# ብላችሁ በመደወል refresh wifi version የሚለውም በመጫን ስልካችሁን restart በማድረግ refresh አድርጎ fix ያደርግላችኋል ✅5. Call waiting ለማስጀመር:- ከሰው ጋር ስልክ እያወራችሁ በመሀል ሌላ ሰው ሲደውልላችሁ waiting እንዲያሳይ ከፈለጋችሁ *43# ብላችሁ በመደወል call waiting service activate ማድረግ ትችላላችሁ። ይህ Post ምን ያህል ጠቃሚ ነዉ? REACT እያደረጋችሁ😍🔥👍
Telegram ላይ መጠቀም የምንችላቸው ብዙ አይነት Inline ቦቶች አሉ። Inline bot ማለት chat ስናደርግ የሆነ ነገር search ለማድረግ የምንጠቀምባቸው ቦቶች ማለት ነው። ለምሳሌ ፎቶ search አድርጎ ለመላክ በቀላሉ @pic ብላችሁ search ካደረጋችሁ በኋላ search ማድረግ የምትፈልጉትን ነገር ፅፋችሁ search ማድረግ ትችላላችሁ። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው። @gif Search and send GIFs @vid Search/send YouTube videos @youtube Search/send YouTube videos @pic Search/send pictures @bing Search/send Bing images @wiki Search/send Wikipedia articles @imdb Search/send movie/series info @bold Format text: bold, italic, monospace @music Search/send music/MP3s @sticker Search stickers using emoji @foursquare Search restaurants/places nearby @gamee Send/play games @gamebot Send/play Telegram games ቦቶችን የምትጠቀሙበት ምሳሌ @gif dog dancing @youtube MrBeast @wiki Ethiopia @imdb Inception Source : #bighabesha_softwares @netrotechamharic
በ2026 አለም ዋንጫ ተግባራዊ የሚደረጉ ቴክኖሎጂዎች 1. የሮቦት ውሾች የሜክሲኮ ፖሊስ የሮቦት ውሻዎችን ይጠቀማል። የGuadalupe ከተማ ፖሊስ ሰዉ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች እነዚህን ባለ4 እግር የሮቦት ውሾች በማሰማራት አካባቢውን በመቃኘት video ቀርፀው በonline ለፖሊስ ጣቢያ ይልካሉ። መሳሪያ አይታጠቁም። ይልቁንም ፀብና ብጥብጥ በሚመለከቱበት ጊዜ በተገጠመላቸው የድምፅ ማጉያ በመጠቀም ብጥብጡ እንዲቆም ትዕዛዝ ያስተላልፋሉ ተብሏል። 2. Referee Body camera ሁሉንም 104 ጨዋታዎችን የሚገኙ ዳኞች ሰውነታቸው ላይ ካሜራ ይገጠማል። ስለዚህ ከዳኞች perspective ጨዋታውን በመመልከት ሜዳ ውስጥ እንዳለን እንዲሰማን ያደርጋል። 3. Sensor የተገጠመላት የመጫዎች ኳስ Trionda የተሰኘችው Adidas የሰራት ይህቺ ኳስ በውስጧ IMU Sensor ተገጥሞላታል። በዚህ Sensor አማካኝነት በ1 ሰከንድ 500 ጊዜ አጠቃላይ የኳሷ እንቅስቃሴና ፍጥነት ወደ VAR room ይላካል። ስለዚህ የVAR ዳኞች ማንኛውንም ውሳኔ በቀላሉ ለመወሰን ያስችላቸዋል። 4. የተጫዋቾች 3D model እየነዳንዱ ተጫዋች የራሱ 3D ሞዴል ተሰርቶለታል። ስለዚህ የሁሉም ተጫዋች እያንዳንዱ እንቅስቃሴ Realtime track ይደረጋል። ይህም ለsemi Automated offside technology ግብአት ይሆናል። እንደዚህ አይነት technology በእግር ኳስ ተግባራዊ መደረጉ የእግር ኳስን ውበት ያጠፋዋል ብላችሁ ታስባላችሁ? @bighabesha_softwares
🤖 በአፍሪካ ለመጀመሪያ ገዜ ሰው-መሳይ ሮቦት በማራቶን ውድድር ላይ ተሳተፈ። 👉 ‘ጄይ ትሮን’ የተሰኘው ሮቦት በናይሮቢ ሲቲ ማራቶን የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ላይ ተሳትፎ ነው ታሪክ የሠራው፡፡ የሮቦቱ በስፍራው መገኘት በናይሮቢ የንግድ ማዕከል ከፍተኛ ደስታን ፈጥሮ በርካቶች ማሽኑን በቅርብ ለመመልከት ጉጉት አድሮባቸው ታይተዋል። Source: #Sputnik_ethiopia @bighabesha_softwares
💾 SD Card ወይም በተለምዶ ሚሞሪ ካርድ ተፈላጊነቱ ለምን ቀነሰ? ከገበያ ለምን ወጣ? ያኔ.. ቪዲዮና ዘፈን ለማስጫን ቪዲዮ ቤት ሄደን ባለ 2GB ሚሞሪ ሙሉልኝ የምንልበትን ጊዜ ታስታውሳላችሁ? በድንገት Corrupt እንዳይሆንብን የምናደርገው ጥንቃቄ፣ ስልካችን ካርዱን ሳያነበው ሲቀር የነበረን ጭንቀት ሁላችን ቤት የነበረ ታሪክ ነው። ግን አስተውላችኋል? አሁን አሁን አዳዲስ ስልኮችን ስንገዛ የSD Card መሰኪያ (SD Card Slot) የላቸውም። ያ ስንት ትዝታ ያስቀመጥንበት የድሮ ጓደኛችን SD Card ቀስ በቀስ ከገበያ እየወጣ ነው። ለመሆኑ ለምን? 1. Cloud Storage መምጣት አሁን ላይ ፎቶ፣ ቪዲዮ እና ፋይሎቻችንን በስልካችን ውስጥ ከምናስቀምጥ ይልቅ በGoogle Drive፣ iCloud እና ቴሌግራም ላይ Saved Messages ውስጥ ማስቀመጥ እየተለመደ ነው። አብዛኛዎቹ የስልክ አምራች ድርጅቶችም ከእነዚህ የcloude storage አፕሊኬሽኖች ወርሀዊ subscription ስለሚያስከፍሉ በተዘዋዋሪ የገንዘብ ማግኛ አማራጭ ይፈጥርላቸዋል። 2. የስልኮች Internal Storage ማደግ የቀድሞ ስልኮች የነበራቸው ማከማቻ ቢበዛ 8GB ወይም 16GB ስለነበር ሚሞሪ ካርድ የግድ ያስፈልግ ነበር። አሁን ግን አነስተኛ የሚባሉት ስልኮች እንኳ 128GB፣ 256GB አልፎ ተርፎም 1TB ይዘው እየመጡ ነው። ታዲያ ተጨማሪ ካርድ ማን ይፈልጋል? 3. የፍጥነት ጉዳይ (Performance) አዲሶቹ ስልኮች የሚጠቀሙት internal storage በጣም ፈጣን ነው። በአንጻሩ SD ካርዶች data ለማንበብ ረጅም ጊዜ ይፈልጋሉ። ስለዚህ ስልኩ ቀርፋፋ እንዲሆን እንዲሞቅ እና አፕሊኬሽኖች ለመክፈት እንዲዘገዩ ያደርጋቸዋል። ኩባንያዎች የስልካቸውን ስም ለማስጠበቅ ሲሉ ካርዱን አስቀሩት። 4. የስልኮች ዲዛይን እና ውበት ቀጫጭን፣ ውብ እና ውሃ የማይገባቸው (Waterproof) ስልኮችን ለመስራት የስልክ አምራቾች እያንዳንዷ ሚሊሜትር ቦታ ታስፈልጋቸዋለች። ስለዚህ የSD card ማስገቢያን ማስቀረት ለባትሪ እና ለሌሎች ጠቃሚ ነገሮች ቦታ ያስገኛል። ባጭሩ... ቴክኖሎጂው ተቀየረና የኛ ዘመን ታማኝ ጓደኛ የነበረው ሚሞሪ ካርድ ልክ እንደ ካሴት እና CD ታሪክ እየሆነ ነው። እናንተስ የመጨረሻ ጊዜ ሚሞሪ ካርድ የተጠቀማችሁት መቼ ነው? በሚሞሪ ካርድ ምክንያት የጠፋባችሁ ትዝታ ካለ ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ👇 @bighabesha_softwares
መቼም የማይረሳ እጅግ ጣፋጭ ምሽት ለመድፈኞቹ !!! አርሰናል የሊጉ ሻምፒዮን ሁኗል 🏆 በሚኬል አርቴታ የሚመራው የመድፈኞቹ ሰራዊት አርሰናል ፣ ከ 22ዓመታት በኋላ የ2025/26 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን በይፋ አረጋግጧል ። ከዚህ ቀደም አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ፣ ለሁለት ተከታታይ የውድድር ዓመታት የሊግ ዋንጫውን ሳያሳካ ቀርቶ አያውቅም ። #ዳጉ_ጆርናል
YouTube ስልክ ላይ PIP (picture in picture) mode ጀምሯል። ያ ማለት ስልካችሁ ላይ በapplication YouTube ብትከፍቱና home button ብትጫኑ ቪዲዮው አይዘጋም። ስክሪናችሁ ላይ በpicture mode ይጫወታል። ይህን ለማድረግ YouTube ላይ ግቡና የProfile ምልክታችሁን ንኩ። ከዛ Settings -- Playback -- Picture in picture On አድርጉት። በዚህ መሰረት አስተካክላችሁ ስልካችሁ ላይ YouTube እያያችሁ የፈለጋችሁትን ስራ መስራት ትችላላችሁ። ካልሰራላችሁ update አድርጋችሁ ሞክሩት። @bighabesha_softwares
ፔንታጎን ለበርካታ ዓመታት ሳይፈቱ የቆዩ የUFO ፋይሎችን ይፋ ማድረግ ጀመረ። የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ በምስጢር ተይዘው የነበሩና "ያልተፈቱ" ተብለው የተመደቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ያልታወቁ በራሪ አካላት (UFOs/UAPs) መዝገቦችን ለሕዝብ ግልጽ ማድረግ ጀምሯል። ይፋ የተደረጉት ሰነዶች ከ1940ዎቹ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የታዩ፣ ነገር ግን በወቅቱ በሳይንሳዊ መንገድ ሊብራሩ ያልቻሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ክስተቶችን ያካትታሉ። እነዚህም የአብራሪዎች ምስክርነትን፣ የራዳር መረጃዎችን እና የቪዲዮ ምስሎችን የያዙ ናቸው። መረጃዎቹን የማጣራት እና የማሰራጨት AARO (All-domain Anomaly Resolution Office) የተሰኘው ልዩ ቢሮ ተቋቁሟል። ቢሮው እነዚህን ፋይሎች በዲጂታል መልክ በማዘጋጀት በድረ-ገጹ ላይ ለሕዝብ ክፍት እያደረገ ይገኛል። ፔንታጎን እንደገለጸው፣ አብዛኛዎቹ ሪፖርቶች እንደ ሰው ሰራሽ ድሮኖች፣ የአየር ሁኔታ ፊኛዎች ወይም የተፈጥሮ ክስተቶች ተብለው ሊፈረጁ ቢችሉም፣ ጥቂት የማይባሉ ክስተቶች ግን አሁንም ድረስ በምን ዓይነት ቴክኖሎጂ እንደሚንቀሳቀሱ ለማወቅ አልተቻለም። ይህ ውሳኔ የተላለፈው ከአሜሪካ ኮንግረስ አባላት እና ከሕዝብ ዘንድ "መንግሥት የደበቃቸው የውጭ ዜጋ (Alien) ቴክኖሎጂዎች አሉ" የሚሉ ወቀሳዎችና ግፊቶች በረታበት ወቅት ነው። ይህ የፔንታጎን እርምጃ መንግሥት ስለ UFOs ያለውን አመለካከት ሙሉ በሙሉ መቀየሩን ያሳያል። ቀደም ሲል እንደ ተራ ተረት ይታዩ የነበሩ ጉዳዮች አሁን ላይ እንደ ብሔራዊ የደህንነት ስጋት ተቆጥረው ጥልቅ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ያረጋግጣል። እነዚህ ፋይሎች ይፋ ሲደረጉ ተከታትለን እናሳውቃችኋለን። ✔️Official website https://www.aaro.mil/ @bighabesha_softwares
#Hantavirus 🦠 አዲሱ የአለም ስጋት‼️ ሰሞኑን የኔዘርላንድ ባለቤትነት የሆነ ፣ ከአርጀንቲና ወደ ኬፕቨርድ (ደቡብ አፍሪካ) በአትላንቲክ ውቅያኖስ የሽርሽር መርከብ (Cruise Ship 🛳) ላይ ተከስቶ 3 የመርከቧ መንገደኞችን የገደለው ሀንታ ቫይረስ አዲስ የአለም ክስተት ሆኗል። ከሞቱት 3 ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች 3 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተገልፆ ነበር። በአይጥ ዝርያዎች መነሻነት ገዳይ የሆነው የሀንታ ቫይረስ ስጋቱ ከተከሰተበት የአትላንቲክ ውቅያኖስ በተጨማሪ በሌሎች ሀገራት እየተዛመተ ይገኛል። አሁን ላይ ቫይረሱ በስድስት የአለማችን ሀገራት እንደተገኘ CNN ዘግቧል። እስራኤል በዛሬው ዕለት በዚሁ ቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያ ኬዝ ይፋ አድርጋለች።
ቃሉ ፑቲክ በኢንስታግራም (Instagram) ታሪክ አዲስ ሪከርድ ሰበረ! ኢትዮጵያዊው ቃሉ ፑቲክ (Kalu Putic) በኢንተርኔት ዓለም ላይ አስገራሚና ታሪካዊ የተባለለትን ስኬት አስመዝግቧል። ቃሉ በኢንስታግራም ገጹ 1 ሚሊዮን ተከታዮችን (1M Followers) ለማግኘትና ከደጋፊዎቹ ጋር ደስታውን ለማክበር በዝግጅት ላይ ሳለ፣ ነገሮች ግን ከእሱ እቅድና ግምት በላይ ሆነዋል። ባሳለፍነው አንድ ለሊት ብቻ በለቀቃት አንዲት "Viral" የሆነች ቪድዮ ምክንያት፣ የገጹ ተከታዮች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት በመጨመር ከ1 ሚሊዮን ተነስቶ 2.5 ሚሊዮን ላይ አልፏል። በአሁኑ ሰዓትም ተከታዮቹ ቁጥር 2.8 ሚሊዮን ላይ ደርሷል። እሱ ለ1 ሚሊዮን ተከታዮች የደስታ መግለጫ ዝግጅት ላይ እያለ፣ አድናቂዎቹ ግን በድንቅ የፈጠራ ጥበቡ ተማርከው ከ3 ሚሊዮን በላይ አድርሰውታል። ይህ ስኬት ቃሉን በኢንስታግራም ገጽ ላይ ከ3 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን በማግኘት የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ያደርገዋል። በፈጠራ ስራዎቹ ዓለምን እያነጋገረ የሚገኘው ይህ ወጣት፣ የኢትዮጵያን ስም በዓለም አቀፍ የዲጂታል መድረክ ላይ በጉልህ እያስጠራ ይገኛል። 👏ለቃሉ ፑቲክ እና ለጥበብ አድናቂዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ❤️
OpenAI ስልክ ማምረት ሊጀምር ነው። የchatGPT ባለቤት የሆነው OpenAI የራሱን ስልክ በማምረት የስማርት ስልክ ገበያውን ሊቀላቀል እንደሆነ ተገልጿል። ግዙፉ የቴክኖሎጂ ድርጅት በስማርት ስልክ ገበያ ውስጥ ያለውን የመተግበሪያዎች የበላይነት ለመቀየር እና ስልኮች የሚሰሩበትን መንገድ ሙሉ በሙሉ ለማሻሻል እየሰራ ነው። አዲሱ ስልክ የሚሰራው አሁን በለመድነው መልኩ የተለያዩ መተግበሪያዎችን (እንደ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም ወይም ባንክ አፖች) በመጫን ሳይሆን በAI Agent ላይ የተመሰረተ ይሆናል። ተጠቃሚው አንድን ስራ ለመስራት (ለምሳሌ ምግብ ለማዘዝ ወይም ታክሲ ለመጥራት) የተለየ አፕ ከመክፈት ይልቅ በስልኩ ውስጥ ያለውን የAI agent ያዛል። ኤጀንቱ የተጠቃሚውን ፍላጎት ተረድቶ ስራውን በራሱ የሚያከናውን ይሆናል። OpenAI ለስልኩ የሚሆን ልዩ ቺፕ ለማምረት ከMediaTek እና Qualcomm ጋር በትብብር እንደሚሰራ ተገልጿል። የዲዛይንና የማምረት ስራውን Luxshare የተባለው ኩባንያ ተረክቦታል። የስልኩ ዝርዝር መረጃዎች እስከ 2027 መጀመሪያ ድረስ ተጠናቅቀው በ2028 በከፍተኛ መጠን መመረት እንደሚጀምር ይጠበቃል። የOpenAI የረጅም ጊዜ እቅድ መተግበሪያዎች ሙሉ በሙሉ የሚጠፉበትና በAI ኤጀንቶች የሚተኩበት ጊዜ ማምጣት እንደሆነ ተገልጿል። ይህም የ"Nothing" ኩባንያ መሪ ካርል ፔይን ጨምሮ በርካታ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የሚስማሙበት የወደፊት አቅጣጫ ሆኗል። #openai @bighabesha_softwares
ሜታ የማርክ ዙከርበርግን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ክሎን እየሰራ መሆኑ ተዘገበ። እስኪ አስቡት በሜታ ኩባንያ ውስጥ ሰራተኛ ሆናችሁ ከዋና ሥራ አስፈጻሚው ማርክ ዙከርበርግን የሆነ የስራ ጉዳይ ማነጋገር ፈለጋችሁ ነገር ግን ምላሽ የምታገኙት ከእውነተኛው ማርክ ዙከርበርግ ሳይሆን ከዙከርበርግ AI ገጸ-ባህሪ ነው ብትባሉ። ይህ ምንም እንኳ የማይመስል ቢመስልም በቅርቡ እውን ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል። ፋይናንሻል ታይምስ እንደዘገበው ሜታ በዙከርበርግ የአነጋገር ዘይቤ፣ የድምፅ ቃና እና በይፋዊ ንግግሮቹ ላይ የሰለጠነ እንዲህ ያለ የAI ገጸ-ባህሪ እያዘጋጀ ነው። ይህ ገጸ-ባህሪ ስለ ኩባንያው የቅርብ ጊዜ ስትራቴጂዎች የሥራ አስፈጻሚውን ሃሳብ እየተማረ ሲሆን፣ ዓላማውም ዋና ሥራ አስፈጻሚው በማይኖርበት ወይም በማይፈልግበት ጊዜ ለሠራተኞች ምክርና ትዕዛዝ ይሰጣል። ኩባንያው ለተወሰነ ጊዜ ያህል ግንኙነቶችን ማስተዳደር የሚችሉ እውነተኛ የሚመስሉ የ3D አኒሜሽን AI ገጸ-ባህሪያትን ለመፍጠር ሲሰራ ቆይቷል። አሁን ግን ትኩረቱን በዚህ የዙከርበርግ AI ላይ ያደረገ ይመስላል። @bighabesha_softwares
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ! 🕊️✝️ በዓሉ የሰላም 🕊️፣ የፍቅር ❤️፣ የአንድነት እና የበረከት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን 🙏✨ መልካም የትንሣኤ በዓል
መልካም የስቅለት በዓል
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#Telegram_update ቴሌግራም ሰሞኑን ባስተዋወቀው update አንዳንድ features ያካተተ ሲሆን ከነዚህም መካከል፦ AI Text Editor ይህ feature telegram ላይ ረዘም ያለ መልእክት በምንፅፍበት ጊዜ Translate ማድረግ፣ በተለያዩ Style መፃፍ እና Grammer fix ማድረግ ያስችላል የተባለም ሲሆን የፃፍነውንም text እንደ formal, Short,Tribal,Corp በመሳሰሉ ስታይሎች style ማድረግ እንደሚያስችልም ተገልጿል። ይህንንም feature ለመጠቀም የቴሌግራም መተግበሪያን Update ካደረግን በኋላ 3 እና ከዚያ በላይ መስመር message bar ላይ ስንፅፍ የሚመጣውን የAi ምልክት መንካት። New Features for Polls Pools ላይ እንደ ፎቶ እና ቪድዮ ያሉ medias ወይም location Attach ማድረግ/ማያያዝ፣ Active በሆኑ polls ላይ ምርጫዎችን ሰዎች suggest እንዲያደርጉ ማስቻል፣ምርጫዎቹ ለየሰው random እደምተከተል እንዲኖራቸው ማድረግ የመሳሰሉ features ተካተዋል። Document Scanner on iOS የiOS ቴሌግራም ላይ document scan ማድረግ የሚያስችል feature ሲሆን ይህንንም ለማድረግ attachment menu በመክፈት File የሚለውን መንካት ከዚያም Scan Document የሚለውን መንካት።
✈️ከቴሌግራም ፊልም ወይም ፋይሎች⬇️እያወረዳቹ ሌላ App ስትከፍቱ ፍጥነቱ ቀንሶባቹ ወይም ጭራሹንም ቆሞባቹ የቃል? ⬇️ይህ የሚሆነው በAndroid Battery Optimization System ምክንያት ነው። የስልካቹን ባትሪ ለመቆጠብ ሲል አሁን ላይ ማትጠቀሟቸውን አፖች (Background ላይ ያሉት አፖች) የኢንተርኔት እና የባትሪ አጠቃቀማቸውን እንዲቀንሱ ያደርጋል፤ ይህም ፋይሎች እንዳይወርዱ ወይም እንዲዘገዩ ያደርጋል። ⚙ይህንን ለማስተካከል ለቴሌግራም ብቻ የBattery Optimization Setting ማጥፋት ይቻላል፦ ወደ Settings → Apps → Telegram → Battery -> ከዛን "Unrestricted" የሚለው ላይ አድርጉት። ✅አሁን ቴሌግራም ያለምንም የባትሪ እና የኔትወርክ ገደብ ፋይሎችን ማውረድ ይችላል። ➕በተጨማሪ እዛው ላይ እንዳላቹ አንዴ ወደኃላ ተመልሱና Mobile data -> Allow background data usage ሚለው መብራቱን አረጋግጡ።