Natnael Mekonnen
Статистикаበቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21
- Последний пост
- 17:19
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 62
- Всего постов
- 90
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 22 537
- 1/48двое суток
- 25 827
- 1/72трое суток
- 27 855
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ወቅታዊ መልዕክት ለመላ ኢትዮጵያውያን - ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራችን ኢትዮጵያ አዲስ ታሪክና ባህል ሆኖ እየተከናወነ ያለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መካሄድ ከጀመረ እነሆ ዛሬ ነሐሴ 8/2018 ዓ.ም አንድ ወር አስቆጠረ። ሂደቱ በሀገራችን ሲከናወን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደመሆኑ፣ ለምክክር የቀረቡ አጀንዳዎች እጅግ መሰረታዊና ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ እንደመሆናቸው እንዲሁም የሀገራችንን ብዙኃነት መሰረት ያደረጉ ፍላጎቶች በርካታ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ጉባኤው የብዙዎች መነጋጋሪያ መሆኑ ለኮሚሽኑ አስገራሚ ነገር ሆኖ አልተገኘም። በዚህ ሂደት ኢትዮጵያዊያን የጋራ በሚያደርጓቸው ጉዳዮቻቸው ላይ ለመምከር ያሳዩት ቁርጠኝነት፣ በምክክሩ ሂደት እያሳዩት ያለው መከባበር፣ መደማመጥ እንዲሁም እያካበቱት ያለው ማህበራዊ ግንኙነት እጅጉን አመርቂ እና ተስፋ ሰጪም ነው። ይህ በሀገራችን አዲስ የሆነው የምክክር መድረክ ብዙዎች እንዲተዋወቁ፣ ‘የአንተ ችግር የእኔ ነው’ እንዲባባሉ፣ ለነገ ሀገራቸው የሚጠቅም የጋራ ሃሳብ በመግባባት እንዲያፈልቁ እያስቻለ ይገኛል። ሂደቱ በኮሚሽኑ የአሰራር ሥነ-ዘዴ መሰረት አንዱን ምዕራፍ እየጨረሰ ወደ ሌላው ምዕራፍ ሲሸጋገር ቆይቶ አሁን ላይ ወደ ወሳኙ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። በኮሚሽኑ ግምገማ መሰረት ያለፈው አንድ ወር የምክክር ሂደት ስኬታማ ሥራዎች የተሰሩበት፣ ምክክር ባህል እንዲሆን መሰረት የሚጥሉ አዳዲስ ጉዳዮች የታዩበት ነው። ይህ ማለት ግን ሂደቱ ሙሉ በሙሉ አልጋ በአልጋ ነበረ ማለት አይደለም። አለመግባባት የሚመስሉ ነገሮች ተስተውለዋል። እነዚህ ነገሮች አለመግባባት አለ ብለን ለተቀመጥን ወገኖች እንግዳ መሆን እንደሌለባቸው የኮሚሽኑ እምነት ነው። ኮሚሽኑ ካለው አሰራርና ልምድ በመነሳት እንደዚህ ዓይነት ነገሮች ሊያግጥሙ እንደሚችሉ ምክክሩን ከማስጀመሩ በፊት በውል የተረዳው ጉዳይ ነው።ጉዳዩ እንግዳ የመሰለው ለተመካካሪዎችና ወክለው ለመጡት አካል ነው። ይህ በእንዲህ እያለ በዚህ ስጋት ላይ ኃላፊነት የማይሰማቸው ግለሰቦች እና ቡድኖች እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች የሚያሰራጩት ሀሰተኛ መረጃ ሲጨመርበት ደግሞ ነገሩን ምን ያክል ውስብስብ እንደሚያደርገው ኮሚሽኑ ይረዳል። ለዚህ ነበር ኮሚሽኑ ህብረተሰቡን በኮሚሽኑ ከሚወጡ መረጃዎች እንዲሁም በስፍራው የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ከሚያወጡት መረጃ ውጪ ካሉ መረጃዎች ራሱን በማቀብ ከሀሰተኛ መረጃዎች እንዲጠበቅ ሲያሳስብ የቆየው። አሁንም ምክክሩ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑን ተከትሎ የተዛቡ መረጃዎች በስፋት መውጣታቸውን ስለሚቀጥሉ በድጋሚ መላው ኢትዮጵያዊያን ኮሚሽኑ ከሚያወጣቸው መረጃዎች እንዲሁም በስፍራው የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ከሚያወጡት መረጃ ውጪ ያሉ መረጃዎችን ባለመከታተል ራሱን ከሀሰተኛ መረጃ እንዲጠብቅ ኮሚሽኑ በድጋሚ ያሳስባል። በዚህ አጋጣሚ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችም ጫፍ ያልደረሰ መረጃ በማጋራት በህዝብ ላይ ያልተገባ ብዥታና መደናገርን ከመፍጠር እንድትቆጠቡ ኮሚሽኑ በጥብቅ ያሳስባል። መሰል ተግባራትን ኮሚሽኑ ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ሙያዊና ሥነ-ምግባራዊ ጥሰት እየፈፀሙ ያሉ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎችን ተጠያቂ የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑንም ማሳወቅ ይወዳል። ይህ ክትትልና እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ማሳሰብ ይወዳል። ሀገራዊ ምክክር ለሀገራዊ መግባባት!
በዚህ ቪዲዮ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የለውጥ አመራር እና “መደመር” የተሰኘውን ፍልስፍና—የጋራ ኃይልና ትብብር የሚፈጥረውን ጥንካሬ—በጥልቀት እንመለከታለን። ከኢትዮጵያ የግብርና ለውጥ እና ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) ጀምሮ፣ እስከ ከተማ ልማት፣ አረንጓዴ አሻራ፣ ዲጂታል ፈጠራ፣ የወጣቶች አቅም ማጎልበትና የስፖርት መሠረተ ልማት ድረስ፣ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ አዲስ ትርክት እየፈጠሩ ያሉ ራዕዮችንና ተነሳሽነቶችን እንዳስሳለን። ቪዲዮውን እስከመጨረሻው ይመልከቱ፤ ዐቢይ አሕመድ ለምን የፓን-አፍሪካ ተምሳሌት እና የኢትዮጵያን የወደፊት ጉዞ በአዲስ መልክ እየቀረጹ ያሉ መሪ ተደርገው እንደሚቀርቡ እንመለከታለን። https://youtu.be/YC3BXGBMFNg?si=aUNeRY-VvZRWHVwz
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
+5
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በድሬዳዋ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራን አስጀመረ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ረሻድ ከማል በድሬዳዋ ከተማ በያዝነው ክረምት በኮርፖሬሽኑ የሚከናወኑ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን ከድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከክቡር አቶ ከድር ጀዋር ጋር በጋራ በመሆን አስጀምረዋል። ኮርፖሬሽኑ በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብሩ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያና የንግድ ቤት ግንባታ፣ የችግኝ ተከላ፣ የጤና መድህን ሽፋን እንዲሁም የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ሥራውን በይፋ አስጀምሯል። የአቅመ ደካማ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርገውና በከተማ አስተዳደሩ ወረዳ 6 አካባቢ የሚገነባው የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ግንባታ በይፋ የተጀመረ ሲሆን፣ ቤቶቹ አስፈላጊውን መሠረታዊ አገልግሎት አሟልተው በጥራትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች እንደሚተላለፉ ተገልጿል። ከግንባታው ማስጀመር ጎን ለጎን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ለአንድ መቶ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች የሚሆን የዓመታዊ ጤና መድህን ዋስትና ሽፋን የገንዘብ ድጋፍ እና ለተማሪዎች የሚሆን የትምህርት ቁሳቁሶችን ለድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ለክቡር አቶ ከድር ጀዋር አስረክበዋል። በስነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ረሻድ ከማል፣ በአገራዊ ለውጡ ወዲህ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አነሳሽነት የተጀመሩት የአረንጓዴ አሻራ እና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብሮች እንደ አገር ባህል እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል። አረንጓዴ አሻራ ከድህነት መውጫ ቁልፍ መንገድ መሆኑን ያመላከቱት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ የክረምት በጎ አድራጎት ተግባራት ደግሞ የኢኮኖሚ ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ አኳያ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው አብራርተዋል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው በድሬዳዋ ቆይታቸው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ያከናወኗቸውን የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል። #የፌዴራል_ቤቶች_ኮርፖሬሽን #ድሬዳዋ #የክረምት_በጎ_ፈቃድ #አረንጓዴ_አሻራ #FHC
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
+4
የሁለተኛ ትውልድ ዳያስፖራ ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ አቀና በቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮከብ ተጫዋች አቶ አሸናፊ ግርማ አስተባባሪነት፣ ወደ 120 የሚጠጉ የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያንንና ቤተሰቦቻቸውን ያካተተ ልዑክ ዛሬ ከካናዳ ወደ ኢትዮጵያ አቅንቷል። ልዑኩ ከቶሮንቶ ፒርሰን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲነሳም በካናዳ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ቴዎድሮስ ግርማ አሸኛኘት ያደረጉ ሲሆኑ፣ ይህ ዓይነቱ ጅማሮ የዳያስፖራውን ትውልድ ከኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ማንነት ጋር በማቀራረብ የሚኖረውን ፋይዳ ተናግረዋል። ልዑኩ በኢትዮጵያ የአንድ ወር ቆይታ የሚያደርግ ሲሆን፣ በቆይታውም ከባህል ልውውጥና ከአገራዊ ትውውቅ ባሻገር በክረምት በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ለማህበረሰቡ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት እንዳደረገ ማወቅ ተችሏል። ይህ ጅምር በተለይ የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከአገራቸው ታሪክ፣ ባህልና ማንነት ጋር ያላቸውን ትስስር እንዲያጠናክሩ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተደጋጋሚ ጥሪ መደረጉን ያስታወሱት አምባሳደር ቴዎድሮስ ይህ ጉዞም በኢትዮጵያና በዳያስፖራው መካከል የጋራ መግባባት፣ ወዳጅነትና ትብብርን የሚያጎለብቱ የህዝብ-ለህዝብ ዲፕሎማሲ ድልድዮችን ለመገንባት የሚያግዝ መሆኑ አንስተዋል። አምባሳደር ቴዎድሮስ አክለውም እንዲህ ያሉ ጅምሮች የዳያስፖራው ትውልድ ከአገሩ ጋር ያለውን ትስስር ከማጠናከር ባሻገር በአገር ግንባታና በማህበራዊ ተሳትፎ ያለውን ሚና ለማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል። የልዑኩ አስተባባሪ አቶ አሸናፊ ግርማና የልዑኩ አባላት በበኩላቸው፣ ይህ ጉዞ ለተሳታፊዎቹ የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ በቀጥታ ለመለማመድ፣ ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር ለማጠናከርና በበጎ ተግባራት በመሳተፍ ለማህበረሰቡ አስተዋጽኦ ለማድረግ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸው ይህ ተግባር በቀጣይነትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ይህ እድል እንዳያመልጦ ! የማስታወቂያ ዋጋ! ብስራት ገብርኤል ላይ በ 7.2 ሚሊየን ብር ዘመናዊ አፓርትመት! ብስራተ ገብርኤል ከ ላፍቶ ሞል አጠገብ : እጅግ ዘመናዊ እፓርትመንት በውስጡ መዋኛ ገንዳ : የልጆች መጫወቻ : ሌሎች አገልግሎቶችን ያሟላ : እነሆ አማን ሪልስቴት ይዞ ብቅ ብሏል: ባለ 1 መኝታ በሙሉ ክፍያ በ 7.2 ሚሊየን ብር ባለ 2 መኝታ በሙሉ ክፍያ በ 8.4 ሚሊየን ብር ባለ 3 መኝታ 173 ካሬ በሙሉ ክፍያ በ 13.9 ሚሊየን ብር ለየት የሚያደርገን በዶላርም ይሁን በኮንስትራክሽን ዕቃ ግሽበት የዋጋ ማስተካከያ አይደረግባችሁም ለ 10 ቤቶች ብቻ የወጣ ቅናሽ ስለሆነ ፈጥነው : በ 0974141898/ 0974147898 ይደውሉ! አማን ፕሮፐርቲስ!
እስከ 50 ሺህ ብር ቅጣት፤ በአዲስ አበባ የመስተንግዶ ሰራተኞች አለባበስ ላይ የወጣው አዲሱ ደንብ ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ ገባ! በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ባሮች፣ ሬስቶራንቶች እና ሆቴሎች ውስጥ የሚያገለግሉ ሴት የመስተንግዶ ሰራተኞችን አለባበስና ጌጣጌጥ አጠቃቀም የሚደነግገው ሕግ በሙሉ አቅሙ እየተተገበረ እንደሚገኝ ተነገረ። ደንቡን በማያከብሩ የመስተንግዶ ተቋማት ላይ እስከ 50 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እና ተጨማሪ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተመልሷል። አዲሱ ደንብ ቁጥር 178/2017 በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ጥብቅ ክልከላ ጥሏል፡ 1. ከጉልበት በላይ የሆኑ አጫጭር ቀሚሶችን መልበስ፣ 2. የደረት ክፍልን ክፍት የሚያደርጉ አልባሳትን መጠቀም፣ 3. ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ባሉ በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚደረጉ ማናቸውንም ጌጣጌጦች ማድረግ። የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር መስራችና ሥራ አስፈጻሚ አባል ናፍቆት ጌታሁን ከአሐዱ ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል በዘርፉ ይስተዋሉ የነበሩ የተወሰኑ መለያ ልብሶች (ዩኒፎርሞች) ከማህበረሰቡ ባህልና እሴት ያፈነገጡ ነበሩ። ይህንን አሰራር ለማስተካከል ማኅበሩ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ደንቡ እንዲጸድቅና ወደ ትግበራ እንዲገባ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት በመስተንግዶ ተቋማት የሚለበሱ መለያ ልብሶች ጨዋነትንና ሙያዊ ብቃትን ያማከሉ እንዲሆኑ እየተደረገ ይገኛል። ማኅበሩም የመንግስትን ክትትል በመደገፍ የአፈጻጸም ቁጥጥር እያደረገ እንደሆነና፣ ደንቡን በማያከብሩ አካላት ላይ ለቱሪዝም ኮሚሽኑ ሪፖርት የሚያደርግ ቢሆንም እስካሁን የቀረበ ጥሰት አለመኖሩ ተገልጻል።