tgindex
YeneTube

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Последний пост
14:42
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
24
Всего постов
114
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
157 519
−642 за 3 дн.
Сутки
−221
−0,14%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
13,6 тыс
40 постов
Вовлечённость
8,7%
к подписчикам
Постов в день
3,4
всего 114
Упоминаний
3
каналов
Охват размещения
по 8 постам
1/24сутки в ленте
11 524
1/48двое суток
12 830
1/72трое суток
13 837

Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.

Посты

  • 14:424 943143

    видео или голосовое, без подписи

  • 15 авг.9 1641

    видео или голосовое, без подписи

  • 15 авг.9 127451

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.12,2 тыс464

    የመንግሥት «ሥልጣንን የማዕከላዊ ማድረግ» ጥረት በ2025 የኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ ተቋማትና ሰብአዊ መብቶች አዳክሟል — የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያ መንግሥት በብሔር ውጥረቶች እና በትጥቅ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ መካከል ሥልጣንን የማዕከላዊ ለማድረግ ያደረገው ጥረት በ2025 «ዲሞክራሲያዊ ተቋማትን ይበልጥ ያዳከመ እና የሰብአዊ መብቶች መከበርን የሸረሸረ» እንደነበር የአውሮፓ ሕብረት የ2025 ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የዲሞክራሲ ሪፖርት ይፋ አደረገ። ሪፖርቱ፤ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት እና የዲሞክራሲ ሁኔታ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ለሁለት ዓመታት በተካሄደው አውዳሚ ጦርነት ያልተፈቱ መዘዞች፣ የትጥቅ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ተጽዕኖ ስር መቆየቱን ጠቁሟል። በአፋር እና በአማራ ክልሎች ሰፊ ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎችም የፀጥታ ችግር መቀጠሉን ገልጿል። በተጠቀሰው ዓመት ትጥቅ በመፍታት፣ በሽግግር ፍትሕ እና በተጠያቂነት እርምጃዎች ላይ የተፈጠሩ መዘገየቶች እንደነበሩና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚደረጉ ሰፊ ጥረቶችን ማስተጎጎላቸው በሪፖርቱ ተጠቅሷል። https://addisstandard.com/Amharic/?p=13768

  • 14 авг.13,6 тыс4811

    የሱዳኑ ፈጣን ድጋፍ ኃይል በኢትዮጵያ ደንበር አቅራቢያ የምትገኘውን ቁልፍ ከተማ መቆጣጠሩን አስታወቀ! የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) እና አጋር ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ ጋር በሚዋስነው ብሉ ናይል ግዛት ውስጥ የምትገኘውን እና ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላትን አል ኩርሙክ ከተማን መቆጣጠራቸውን አልጃዚራ እና ዘ ናሽናል ዘገቡ። የወታደራዊ እና የመንግሥት ምንጮች ሐሙስ ዕለት ለአልጃዚራ እንደገለጹት፣ የሱዳን መከላከያ ሠራዊት (SAF) አባላት ለቀው በመውጣት በኩርሙክ ክወጭ መክተማቸውን ተከትሎ የአር ኤስ ኤፍ ታጣቂዎች እና የሱዳን ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) አባላት ወደ ከተማዋ ገብተዋል። ታጣቂ ቡድኑ በበኩሉ በሰራዊቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን እና በርካታ መሳሪያዎችንና ጥይቶችን መማረኩን ገልጿል። Via AS @YeneTube @FikerAssefa

  • 13 авг.15,1 тыс7910

    አዲስ አበባ-የምክር ሒደቱ ሥጋት እንዳሳደረባቸዉ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ። አዲስ አበባ ዉስጥ በተያዘዉ አገራዊ ምክር ላይ የሚሳተፉ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክር ሒደቱ ቅሬታ፣ ጥርጣሬና ሥጋት እንደተሰማቸዉ አስታወቁ።እናት ፓርቲ (እፓ) ፣የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በየፊናቸዉ ባወጧቸዉ መግለጫዎችና ደብዳቤ እንዳሉት ምክክሩ እንዲሳካ ሒደቱ ሊታረም ይገባል። እናት ፓርቲና የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ቅሬታና ማሳሰቢያቸዉን በየፊናቸዉ ባወጡት መግለጫ ሲያስታዉቁ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በምክክር ሒደቱ ላይ ያለዉን ቅሬታ ለምክክር ኮሚሽን ለሶስተኛ ጊዜ በፃፈዉ ደብዳቤ መግለፁን አስታዉቋል። እናት ፓርቲ በመግለጫዉ የምንመካከረው "አዲስ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማዋለድ አይደለም" ሲል ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ሥጋት እንዳለው ገልጿል።በምክር ሒደቱ የአዲስ አበባ ከተማን ለአንድ ቡድን ለማስረከብ እና "አዲስ የፀብ ግንባር ለመቀስቀስ" ጥረት እንዳለ መታዘባቸውን የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሠይፈ ሥላሴ አያሌው ገልፀዋል።ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ባወጣዉ መግለጫ ደግሞ ሐገራዊ ምክክሩ እንዲሳካ «ሁሉም የበኩሉን ያበርክት" የሚል ጥሪ አድርጓል። የፓርቲው መግለጫ አክሎም "የምክክር ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ የአንድ ወገንን ፍላጎትን በሌሎች ላይ ለመጫን ከሚደረግ ሙከራ መራቅ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በምክክር ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ከሚያደርጉ አፍራሽ ተግባራት መቆጠብ ያስፈልጋል።" በማለት አሳስቧል። @YeneTube @FikerAssefa

  • 13 авг.15,5 тыс20

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.15,4 тыс20

    видео или голосовое, без подписи

  • +2
    13 авг.13,9 тыс5520

    የቱፓክ ሻኩር ግድያ የፍርድ ሂደት ከ30 ዓመታት በኋላ በይፋ ተጀመረ በአሜሪካ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስም ያለው የሂፕ-ሆፕ ኮከብ ቱፓክ ሻኩር ከተገደለ ከ30 ዓመታት በኋላ የግድያው ዋና ጠንሳሽ ነው የተባለው ግለሰብ የፍርድ ሂደት በይፋ እንደተጀመረ ኤኤፍፒ በዘገባው አስነብቧል። የቀድሞ የወሮበሎች (ጋንግ) መሪ የሆነው የ63 ዓመቱ ዱዌን "ኬፌ ዲ" ዴቪስ በግሪጎርያኑ ሴፕቴምበር 1996 ቱፓክን ለመግደል ትዕዛዝ በመስጠትና ለግድያው የተጠቀሙበትን ሽጉጥ በማቅረብ ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡም ታውቋል። የፍርድ ሂደቱ የዳኞች ምርጫ በማድረግ የተጀመረ ሲሆን ግለሰቡ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ያለምንም የይቅርታ ዕድል የዕድሜ ልክ እስራት ይጠብቀዋል ተብሏል። ለአስርት ዓመታት እንቆቅልሽ ሆኖ የቆየው ይህ ታሪካዊ የፍርድ ሂደት ዳግም ሊያንሰራራ የቻለው ተከሳሹ እንደ ግሪጎርያኑ አቆጣጠር በ2019 ባሳተመው የህይወት ታሪክ መጽሐፉ ላይ በግድያው ወቅት አብሮ እንደነበረ በማመኑ ነው። ምንም እንኳን ዴቪስ አሁን ላይ "ንፁህ ነኝ ማንንም አልገደልኩም" በማለት ክሱን ቢያስተባብልም የቱፓክ ቤተሰቦች እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድናቂዎቹ ይህ የ30 ዓመታት የፍትህ ጥያቄ ምላሽ ያገኛል በሚል የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በጉጉት እየተጠባበቁ እንደሚገኝ ዘገባው አመልክቷል። @Yenetube @Fikerassefa

  • 12 авг.15,5 тыс7252

    ከዩቲዩብ ገቢ ለማግኘት የሚጠየቀው መስፈርት በሁለት እጥፍ አደገ ዩቲዩብ አዲስ ይዘት የሚፈጥሩ አካላት ከማስታወቂያ እና ከዩቲዩብ ፕሪሚየም ገቢ ማግኘት የሚጀምሩበትን የዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም መስፈርት በሁለት እጥፍ ማሳደጉን አስታወቀ። እ.ኤ.አ Feb 1, 2027 ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው በዚህ አዲስ መመሪያ መሠረት፣ አዳዲስ ፈጣሪዎች በዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም ተቀብለው ገቢ ማግኘት ለመጀመር ፦ በመደበኛ/ ረጃጅም ቪዲዮዎች ላለፉት 12 ወራት 8,000 የታዩ ሰዓታት /Watch Hours/ ማሟላት አለባቸው። ይህም ቀደም ሲል ከነበረው 4,000 ሰዓታት በሁለት እጥፍ ያደገ ነው። በአጭር ቪዲዮዎች /Shorts / በኩል ማመልከት የሚፈልጉ ደግሞ ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ 20 ሚሊየን የታዩ ዕይታዎች ማሳካት ይኖርባቸዋል። ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው 10 ሚሊየን እይታ በሁለት እጥፍ ጨምሯል። የ1,000 ተከታዮች መስፈርት አልተለወጠም። ይህ ለውጥ ከፈረንጆች 2018 ወዲህ በዩቲዩብ የገቢ አስተዳደር ደንብ ላይ የተደረገ ትልቁ ማሻሻያ ነው ተብሏል። በተጨማሪም ቀደም ሲል በፕሮግራሙ ውስጥ ያሉ የአጭር ይዘት ፈጣሪዎች የገቢ ክፍያቸውን ለማስቀጠል በየ90 ቀናት ውስጥ 10 ሚሊየን እይታዎችን ጠብቀው መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል። @Yenetube @Fikerassefa

  • 12 авг.14,7 тыс304

    “ኢራን የኒውክሌር ቦምብ ለመሥራት ረዥም ጊዜ ያስፈልጋታል” የሞሳድ የቀድሞ አዛዥ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ የቀድሞው አዛዥ ዮሲ ኮኽን ኢራን በተፈጸመባት ተከታታይ ጥቃት ምክንያት የኒውክሌር ቦምብ የመሥራቅ አቅሟ መዳከሙን ተናገሩ። ባለሥልጣኑ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ፎርዶ የተባለው የኢራን ከመሬት በታች የሚገኝ የኒውክሌር ተቋም ላይ በቅርበት ባደረገው ክትትል ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰበት መልሶ ለመገንባት ረዥም ጊዜ ያስፈልጋታል ብለዋል። አሜሪካ በተቋሙ ላይ ያደረሰችውን ጉዳት ሲያልሙት የነበረው “ሕልም ስኬት ነው” ሲሉ የገለጹት ቢሆንም፤ ይህንን ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ግን ማብራሪያ አልሰጡም። የቀድሞው የሞሳድ አዛዥ ተቋማቸው ኢራን ለዓመታት ከመሬት በታች ስትገነባው የቆየውን ፎርዶ የኒውክሌር ተቋምን በቅርበት እና በዝርዝር ሲከታተለው እንደቆየ ማክሰኞ ዕለት በተደረገ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ጨምረውም ኢራን 60 በመቶ የዳበረ ዩራኒየም አዘጋጅታለች በማለት ምንም እንኳን ንጥረ ነገሩ በከፍተኛ ደረጃ የዳበረ ቢሆንም የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲኖራት ያስችላል ማለት አይደለም ብለዋል። “60 በመቶ ዩራኒየም ማዳበር ማለት ቦምቡን ለማሥራት ገና ብዙ ርቀት መጓዝ የሚሰስፈልገው ነው” ብለዋል። አሜሪካ ፎርዶ የተባለውን ከተራሮች በታች የሚገኝ የኒውክሌር ተቋምን በልዩ እና ከባድ ቦምብ የደበደበችው ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በፈጸመችው ጥቃት ነበር። Via:- BBC @Yenetube @Fikerassefa

  • 12 авг.14,5 тыс9910

    ሴት የመስተንግዶ ሰራተኞችን አለባበስ እና ጌጣጌጥ የሚወስነው ደንብ በአዲስ አበባ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መደረጉ ተነገረ በከ5 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮን ጨምሮ ሌሎች ቅጣቶችን የሚያስከትለው ሴት መስተንግዶ ሰራተኞች አለባበስ እና ጌጣጌጥ የሚወስነው ደንብ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሆነ የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር ለአሐዱ ሬድዮ አስታውቋል። በ2017 ዓ.ም. ህዳር ወር ላይ በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ የወጣው ደንብ ቁጥር 178/2017፤ የደረት ክፍልን ያልሸፈነ ሸሚዝ፣ ከጉልበት በላይ የሆነ ጉርድ ቀሚስ እና ከጋብቻ ቀለበት ውጪ በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ጌጣጌጥ ማድረግን ይከለክላል። የማኅበሩ መስራች እና ስራ አስፈጻሚ አባል ናፍቆት ጌታሁን፤ "በአንዳንድ ተቋማት የመስተንግዶ ሰራተኞች እንዲለብሱ የሚገደዱት መለያ ልብስ (ዩኒፎርም) ከባህል ያፈነገጡ ነበሩ" ብለዋል። ይህንን ለማስተካከልም ማኅበሩ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመሆን ደንቡ እንዲጸድቅ ግፊት አድርጓል። አሁን ላይ ደንቡ ጸድቆ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አንስተው፤ ተግባራዊ ያልተደረባቸው ቦታዎች ካሉ ከመንግስት ክትትል በተጨማሪ ማኅበሩም አፈጻጸሙን እንደሚከታተል ተናግረዋል። መመሪያው ያልተገበሩ የማኅበሩ አባላት ሲገኙ ለአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ሪፖርት እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ እስካሁን የቀረበ ሪፖርት እንደሌለ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት በባር፣ በሬስቶራንት እና በሆቴሎች የሚለበሱ መለያ ልብሶች ጨዋነትን በጠበቀ መልኩ እንዲዘጋጁ እየተደረገ ነው ተብሏል። Via:- አሐዱ ሬዲዮ @Yenetube @Fikerassefa

  • 12 авг.13,1 тыс5412

    ከ4 ሺህ በላይ ሴቶች ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት ማግኘታቸዉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ። ህጉ በሚፈቅድባቸዉ ሁኔታዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት በጤና ተቋማት ደረጃ በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች በመስጠት የእናቶችን ህመምና ሞት ለመቀነስ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገልጿል ። በክልሉ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥና የድህረ ፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት እንክብካቤ ያገኙ ሴቶች 13 ሺህ 621 ሲሆኑ ከእነዚህም ዉስጥ 4 ሺህ 968 የሚሆኑት ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት አግኝተዋል ። የተቀሩት 8ሺህ 653 ሴቶች የድህረ ፅንስ ማቋረጥ ድንገተኛ አገልግሎት ፣ 6 ሺህ 846ቱ ደግሞ የድህረ ፅንስ ማቋረጥ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ማግኘታቸዉን  የቢሮው የቤተሰብ ዕቅድ ፣የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች የጤና ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አብረሀም ወንድሙ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። የፅንስ ማቋረጥ ዋነኛዉ ምክኒያት ያልታቀደ እርግዝና በመሆኑ ቢሮዉ ይህንን ለመከላከል የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት እየሰራ መሆኑን ገልጿል ። በተጨማሪም ፅንስ በማቋረጥ ምክኒያት የሚከሰት ሞትን ለመከላከል ህጉ በሚፈቅድባቸዉ ሁኔታዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ ይገባል ሲሉ አቶ አብረሀም ጨምረዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል ። @Yenetube @Fikerassefa

  • 12 авг.11,8 тыс315

    በኮሎምቢያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ200 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣የነብስ አድን ሰራተኞች እስካሁን ወደ መንቀጥቀጡ ማዕከል መድረስ አልቻሉም። በምዕራብ ኮሎምቢያ በኃይል መጠኑ 7.4 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከተከሰተ በኋላ፣ የአደጋ ጊዜ ደራሾች በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት በውድድር ላይ ይገኛሉ። ይፋዊ መግለጫዎችን መሰረት በማድረግ ሲኤንኤን (CNN) ባዘጋጀው ቁጥር መሰረት አደጋው ከ200 በላይ ሰዎችን ገድሏል። መንግሥት ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ ያወጀ ሲሆን፣ የዓለም መሪዎችም ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። አንድ ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባልደረባ በቀጣዮቹ ቀናት የምግብ ስርጭት በጣም ወሳኝ እንደሚሆን ያሳሰቡ ሲሆን፣ በመንቀጥቀጡ ማዕከል አቅራቢያ የሚኖሩ አንድ የነባር (ኢንዲጂነስ) ማህበረሰብ መሪ እስካሁን ምንም ዓይነት እርዳታ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል።   ሌሎች በሕይወት የተረፉ ሰዎችም የገጠማቸውን አስፈሪ ሁኔታ በማስታወስ በመናገር ላይ ናቸው። ሲኤንኤን (CNN) በፔሬራ ከተማ ፍርስራሽ ውስጥ የተያዙ ሰዎችን ለማዳን የሕይወት አድናኞች እና በጎ ፈቃደኞች የሰው ሰንሰለት ሲሠሩ ተመልክቷል።   ከካሊ ከተማ የተገኘ አስደናቂ ቪዲዮ ደግሞ አንድ ሕፃን ከፍርስራሽ ሥር ሲወጣ ያሳያል። @Yenetube @Fikerassefa

  • 12 авг.13,1 тыс262

    የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በምህጻሩ (RSF) የሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱምን ጨምሮ የሱዳን ጦር በሚቆጣጠራቸው የተለያዩ ከተሞች ላይ ዛሬ በሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ጥቃት አደረሰ። የዓይን ምስክሮችና የጦር ምንጮች እንዳሉት የዛሬው ጥቃት ለወራት ከተፈጸሙት ጥቃቶች በከፍተኛ ደረጃ የተቀነባበረ ነው። ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ኻርቱምን ፣ በኮርዶፋን የምትገኘው ኤል ኦቤይድ እና የሰሜን ሱዳን ከተሞችን አትባራን እና ኤል ዳመርን ብዛት ባለቸው ድሮኖች መደብደቡን የሱዳን ጦር ምንጭ ተናግረዋል። የሱዳን ጦር የፈጥኖ ደራሹን ኃይል አስወጥቶ መልሶ የያዛት እና ከዚህ ቀደምም የድሮን ጥቃቶች ዒላማ የሆነችው ኻርቱም ለወራት አንጻራዊ መረጋጋት ሰፍኖባት ነበር።በኻርቱም ጥቃቱ የደረሰው ከማለዳው 11 ሰዓት ላይ እንደነበር በወቅቱም ከኦምዱርማን በስተሰሜን በሚገኘው ዋዲ ሴይዲና ከተባለው የሱዳን ጦር ሰፈር በኩል ደግሞ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳይሎች ድምጽ መሰማቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የዓይን ምስክሮች እንደተናገሩት ሰሜን ኻርቱም ከናይል ወንዝ ባሻገር በኤል ድሮሽባ አካባቢ ሁለት ድሮኖች አንድ መስጊድና የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር መተዋል።ድሮኖቹ በአየር መቃወሚያ ይመቱ አይመቱ ወዲያውኑ የተባለ ነገር የለም።በሲቭሎች ላይ የደረሰ ጥቃት ይኑር አይኑርም የተሰማ ነገር የለም። በሱዳኑ ጦርነት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ በላይ ይገመታል። Via DW @YeneTube @FikerAssefa

  • 12 авг.5 5459из yenetube

    For sell🔊🔊 Coffee roasting machine -5kg roasting capacity -Fully electric Single phase -Food graded made with stainless steel -Locally made -Price 165,000 ETB Negotiable Miller for salt,coffee and other grains - 7 quintal/hour output - Single-phase - Fully food graded made with stainless steel -Locally made -Price 170,000 ETB negotiable Continuous band sealer Brand new -Price 55,000 Portable Radiation Detector Detects X-ray, beta-ray, gamma ray -Price 58,000 Contact @milcom69

  • 12 авг.14,3 тыс17219

    መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር አዲስ ማለዳ የደረሳት ሲሆን በዚህ መዘርዝር ውስጥ በዋናነት የቀድሞው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለው፣ ዶ/ር ወንደወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ ገነት አስማማው ይገኙበታል፡፡ ሙሉ ዝርዝራቸው ተከታዩ ነው፡- 1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው 2. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም 3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው 4. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ 5. ዶ/ር መሠረት ቀለመወርቅ 6. ዶ/ር ዘሪሁን ባህሪው 7. ጋዜጠኛ መስከረም አበራ 8. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው 9. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው 10. ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ 11. ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ 12. አቶ አለልኝ ምህረት 13. አቶ መንበር አለሙ 14. አቶ ማይክ መላክ 15. አቶ አሳምነው ታደሠ 16. አቶ ደሳለኝ እጅጉ 17. አቶ እሱባለው በለጠ 18. አቶ እስክንድር ሽፈራው 19. አቶ መሰለ ቸሩ 20. ኢ/ር ፍርዱ ተፈራ 21. አቶ ጫኔ ዘየደ 22. ወ/ት ሃሊማ አህመድ 23. ወ/ት ህይወት አለማየሁ 24. አቶ ሲሳይ መልካሙ 25. አቶ ታደሰ ወዳይነው 26. አቶ በላይ ሲሳይ 27. አቶ ያሬድ ግርማ 28. አቶ ማረው ስለሺ 29. አቶ ሠለሞን ተፈሪ 30. አቶ ሙሉቀን ተስፋዬ ለአዲስ ማለዳ የደረሳት ደብዳቤ እንደሚያመላክተው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ከመንግስት ጋር በጀመረው ውይይት በመጨረሻ ፈርሙ የተባሉት ተከታዮቹን ጉዳዮች ያካትታል፡- “በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት ውሰዱ፤ በአማራ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ለሞቱ ሰዎች፣ ለቆሰሉ  ሰዎች (በየመዝገብ ቁጥሩ ይለያያል) ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ለወደመው በበሊዮን የሚገመት ንብረት ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤  ሀገሪቱ በአማራ ትውፊቶችና እና እሳቤ ካልተመራች ማለታችሁን ወንጀል ነው በሉ፤ ያለ አግባብ የተወሰዱ የአማራ ርስቶች መመለስ አለባቸው ስለማለታቸው እና ይህም ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ”  በቅድመ ሁኔታ እንደቀረበላቸው አዲስ ማለዳ የተመለከተችው  ያመላክታል፡፡ ይህንን ተከትሎ ተከሳሾቹ በሰጡት ምላሽ “እኛ ወንጀለኛ ነን ብለን አንፈርምም፤ በህግም፣ በሞራልም፣ በታሪክም ተቀባይነት የለውም ብለን አንፈርምም” ብለዋል፡፡  አክለውም፤ “የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችም ህጋዊ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ በመግለጽ የ60 ሚሊዮን ህዝብን መልካም እሴት ወንጀል ነው ብለን አውቀን አንሰጥም ወንጀልም አይደለም፤ በህገመንግስት እና በዓለምአቀፍ ህጎች ነፃ ሆኖ የመኖር መብታችንን ፈቅደን አንተውም፤ በህግ የተከለከለውን ራስን መከላከል እና ራሳችንን ወንጀለኛ አናደርግም” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን መመልከት ተችሏል፡፡ Via Addis Maleda @YeneTube @FikerAssefa

  • 11 авг.16,6 тыс19718

    ሶስት አሠልጣኞችና አራት አትሌቶች አሜሪካ ፖርትላንድ ላይ ኮበለሉ! 🔴 ቡድኑ በቺካጎ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ 7 የቡድኑ አባላት ከልዑካን ቡድኑ ጋር የሉም 🔴 የአሜሪካኗ ዩጂን ኦሪገን ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብባት ከተማ ብቻ ሳትሆን በርካቶች የሚኮበልሉባት ታሪካዊ ከተማም ሆና ተመዝግባለች ✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት) በአሜሪካ ኦሪገን ዩጂን ሲካሄድ የነበረው ከ20 ዓመት በታች 21ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጠናቀቁ ይታወሳል። ወደ ውድድሩ ስፍራ የተጓዘችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 ወርቅ፣3 ብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 6 ሜዳሊያ ማግኘቷም ይታወቃል። ከወደ ኦሪገን ከደቂቃዎች በፊት የደረሠን አስደንጓጭ ዜና ለሻምፒዮናው ከተጓዙት የልዑኳን ቡድን አባላት መካከል ሰባቱ ፖሬትላንድ ላይ መኮብለላቸው ተረጋግጧል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የልዑካን ቡድን በአሁን ሠዓት ከፖርትላንድ ተነስቶ ወደ ቺካጎ አየር ማረፊያ እየተጓዘ ሲሆን እነዚሁ ሰባቱ የቡድኑ አባላት ከልዑኳን ቡድኑ ተለይተው መቅረታቸውን ነው ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ያረጋገጠችው። እንደ ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ከሄዱት አራት አሠልጣኞች ሶስቱ ከቡድኑ ጋር ባለመመለሳቸው በአሁን ሠዓት ወደ ኢትዮጵያ በመገስገስ ላይ በሚገኘው አውሮፕላን ውስጥ አንድ አሠልጣኝ ማለትም አሠልጣኝ መሠረት ብቻ እንደሚገኝ ነው ምንጮቻችን የገለፁልን። አትሌቶቻችን በተመለከተ አራት አትሌቶች እንደኮበለሉ የገለፁልን የመረጃ ምንጮቻችን በወኪንግ፣በ800፣በ5ሺ እና በ3ሺ መሠናክል ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ከቡድኑ ጋር አብረው እንዳልተመለሱና እንደኮበለሉ ነው የመረጃ ምንጮቻችን ጨምረው የገለፁልን። የአትሌቶቹና የአሠልጣኞቹ ሙሉ ስም የደረሳት ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ለቤተሠቦቻቸውና ለደህንነታቸው ስትል የሁሉንም ስም ይፋ ከማድረግ ተቆጥባለች። የአሜሪካኗ ዩጂን ኦሪገን ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብባት ከተማ ቤቻ ሳትሆን በርካታ አትሌቶች፣አሠልጣኞችና አመራሮች የሚኮበልሉባት ታሪካዊ ከተማ ሆና ተመዝግባለች። @YeneTube @FikerAssefa

  • 11 авг.15,4 тыс24

    видео или голосовое, без подписи

  • 11 авг.17,2 тыс715

    በራያ አላማጣ ወረዳ "የትግራይ ኃይሎችን ዒላማ ያደረገ" የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ምንጮች ተናገሩ! በትግራይ ክልል ራያ አላማጣ ወረዳ "መረዋ" የተባለ ቀበሌ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ባለሥልጣን እና የትግራይ ኃይሎች ምንጮች ተናገሩ። "ትምህርት ቤት" ላይ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት "ሦስት የትግራይ ኃይሎች አባላት ሲገደሉ፤ ሰባቱ መጎዳታቸውን" ምንጮቹ ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሦስት ምንጮች እንደሚስረዱት፣ የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው ትናንት ሰኞ ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም. ጠዋት 2፡30 ገደማ ነው። ከአላማጣ ከተማ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በዚህ ስፍራ ሦስት ጊዜ ጥቃት እንደደረሰ ተገልጿል።በጥቃቱ ዒላማ የተደረገው "አርሚ 26" የተባለው የትግራይ ኃይሎች አባላት እንደሆኑ ቢቢሲ ትግርኛ ከወታደራዊ አዛዦች እና ከደቡብ ትግራይ ዞን ጽሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ አመልክቷል። የፌደራል መንግሥት ተፈጽሟል ስለተባለው የድሮን ጥቃት አስካሁን በይፋ አስተያየት አልሰጠም። ቢቢሲ ስለ ጥቃቱ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ኮሎኔል ቢረሳው ሽፈራው ያቀረበው ጥያቄ ወዲያው ምላሽ አላገኘም። ሁለት ጊዜ ጥቃት የተፈጸመው በመረዋ ቀበሌ በሚገኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የትግራይ ኃይሎች አባል፣ "ጥቃቱ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ነው የተፈጸመው።ክረምት በመሆኑ፣ ትምህርትም ስለሌለ የአርሚ 26 [አባላት] በዚያ ተጠልለው ነበር" ሲሉ "ጉዳት የደረሰባቸው የትግራይ ኃይሎች አባላት" መሆናቸውን አስረድተዋል። በዚህ ጥቃት ሦስት የትግራይ ኃይሎች አባላት ወዲያውኑ እንደተገደሉ እና ሰባቱ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሲቪል እንዲሁም ወታደራዊ ምንጮች ተናግረዋል።ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውም አክለዋል። ሦስተኛው ጥቃት የደረሰው ወንዝ የሚገኝበት አካባቢ እንደሆነ ተገልጿል።በትግራይ ክልል የራያ አላማጣ ወረዳ አስተዳዳሪ ዳንኤል ታምራት በበኩላቸው ጥቃቱ "ሲቪሊያን ሰዎች" ላይ ማነጣጠሩን እና ትምህርት ቤት ላይ ጉዳት ማድረሱን በማንሳት ከስሰዋል።"ድሮኗ ጉዳት ያደረሰችው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው። ጥቃት ያደረሰችው አንደኛ በትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደግሞ ነዋሪዎች ውሃ በሚቀዱበት ስፍራ ላይ ነው። በርካቶች ቆስለዋል፤ አንድ ደግሞ ወዲያውኑ ሞቷል" ብለዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ብዛት አራት መሆኑንም ተናግረዋል።እንደ ፌደራል መንግሥት ሁሉ፣ የክልሉን ሥልጣን የተቆጣጠረው በዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራው አስተዳደርም ስለ ጥቃቱ በይፋ አስተያየት አልሰጠም።ቢቢሲ ትግርኛ ያነጋገራቸው አንድ የትግራይ ኃይሎች ምንጭ ግን ጥቃቶቹ የተፈጸሙት "ከባሕር ዳር እና ቢሾፍቱ ከተሞች በተነሱ ድሮኖች ነው" የሚል ክስ አቅርበዋል።"አንዲት ድሮን ጠዋት ከባሕር ዳር ተነስታ እንደሄደች አውቀናል፤ ሳትዞር በቀጥታ ነው የደበደበችው" ብለዋል። ቢቢሲ እነዚህ ክሶች በገለልተኝነት አላረጋገጠም። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa

YeneTube — tgindex