Let's Save Orthodoxy and humanity( ሰብእናንና ኦርቶዶክሳዊነትን እንታደግ)!!⁉️
Статистикаሰብእናንና የመንፈስ ልዕልናን ካዳበሩ ቤተሰቦች ጋር በመተባበር በሰብእናና በኦርቶዶክሳዊነት ላይ የሚፈጸምን(የተፈጸመን) ሥርዓታዊ፣መዋቅራዊ፣ሕጋዊ፣መናፍስታዊ፣ስነልቦናዊ ..ጥቃቶችንና አጥቂዎችን እንዲሁም ከጥቃት የመዳኛ መንገዶችን(መፍትሔ) የሚመለከትበት ቻናል ነው::
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 13
- Всего постов
- 67
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 117
- 1/48двое суток
- 134
- 1/72трое суток
- 144
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
❝ ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ ።❞ገላ 6:2 ያልፈረማችሁ ፈርሙ፤የፈረማችሁ አጋሩ 👇 https://c.org/QnvbXPW6LF ❝ In the last three months, more than 144 people have been slaughered, believers massacred in their homes and Churches razed in a surge of ethnic and religious attacks.❞ Hoollie McKay
☝️የሞትከው አንድን ታናሽ ብላቴና ለ መ ግ ደ ል ይህን ያህል ስትደክም ነው! በጥፊ ብቻ የሚሞት ህፃንን እጆቹን የፊጥኝ አስረህ፥ ግንባሩ ላይ አፈ ሙዝ ደቅነህ ፎቶ ስትነሳ በእውነትም ከሰውነት ወጥተህ አረመኔ ጭ ራቅ መሆንህን በግልጽ ታስረዳለህ። ይሄ የሚሆነው በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የኦርቶዶክሳውያን ቄራ በሆነችው 'አርሲ' በተባለች ቦታ ነው!!! እንግዲህ እንዲህ ያለውን ጭካኔ ከየት እንደተማራችሁት እናንተው ንገሩን።👇 Megbaru Asmare
ሦስት የሥጋ ቤተሰብ የሆኑ ደቡብ ኮሪያውያን ተጠምቀው የቅድስት ሥላሴን ልጅነት አገኙ! በሩቅ ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ሥር ባሉ ሁለት ሀገራት አራት ነፍሳት ተጠምቀው የቅድስት ሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል። በጃፓን የቶኪዮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እና በደቡብ ኮሪያ የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩት አራት ሰዎች ማለትም... አንድ ወጣት ኤርትራዊ ወንድም እና የሥጋ ቤተሰብ የሆኑሦስት የደቡብ ኮሪያ ዜጎች መጠመቃቸውን የሩቅ ምሥራቅ ሀገረ ስብከት አስታውቋል። ሀገረ ስብከቱ ነፍሳትን ወደ እውነተኛው መንጋ ለመቀላቀል በየሀገራቱ ቋንቋዎች የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር እና በአገልግሎት ያለመታከት እየሠሩ ያሉትን ካህናትን (ቄሶችን እና ዲያቆናትን)፣ ወንድሞችንና እህቶችን እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮችን አመስግኗል። ይህ አገልግሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ መቅረቡም ተገልጿል። ግዮን ማለዳ
በአሰቦት ገዳም አንድ መነኮስ ጉዳት ደረሰባቸው ተደጋጋሚ ጥቃት በሚያጋጥመው በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አንድ መነኮስ አባት ባልታወቁ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ። የገዳሙ አገልጋይ የሆኑት አባ ተክለ ዮሐንስ ደረሰ በእንጨት ለቀማ ላይ እያሉ ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 አካባቢ አደጋው እንደደረሰ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት ጽ/ቤት ገልጿል። ታጣቂዎቹ አባ ተክለ ዮሐንስን በአሰቃቂ ሁኔታ ጉሮሯቸውን ወግተው ለመግደል ሲሞክሩ ለማምለጥ የቻሉ ሲሆን ገዳሙም በሕይወትና በሞት መካከል ያሉትን አባት ወደ ህክምና የወሰዱ መሆናቸውን ገልጸው እየደረሰባቸው ያለውን ተደጋጋሚ ጥቃት ለመከላከል ለሚመለከታቸው አካላት መረጃውን አድርሱልን በማለት ጥሪ አቅርበዋል። የሀገረ ስብከቱም ጽ/ቤት በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ተደጋጋሚ ጥቃቶችና ችግር እንዲቀረፍና ገዳማውያኑም በተረጋጋ ሁኔታ እንዲኖሩና ለሀገር እንዲፀልዩ የመንግስት የፀጥታ አካላት መፍትሄ እንዲሰጥና ክትትል እንዲያደርግ ለሚመለከተው የዞኑ የፀጥታ አካላት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስና የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ሪፖርት በማድረግ ክትትል እያደረጉ መሆኑን ገልጿል። ዘገባው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ነው። #አሰቦትደብረወገግ #ቤተክርስቲያን #ዜና
በአርሲ ተባብሶ የቀጠለው ጅምላ ፍጅት ፩ ጉና ወረዳ ሬኤ አምባ ቀበሌ 02/12/2018 ዓ.ም ለ 03/12/2018ዓ.ም አዳር የ70ዓመት አዛውንት አቶ ጌታቸው ቶሎበል ከእነ ባለቤታቸው ለቀብር በማይመች ሁኔታ ገድለው ጥለው የሄዱ ሲሆን 17ከብቶቻቸውንም ዘርፈው ወስደዋል በዚህ ወረዳ ያለው ኦርቶዶክሳዊ አብዛኛው በአክራሪዎቹ ከበባ ውስጥ ነው ያለው። ራሳቸውንም እንዳይከላከሉ የወረዳው ባለሥልጣናት ከፍተኛ ጫና እያደረጉ ይገኛሉ። ይኽ ብቻ አይደለም በጸጥታ መዋቅር ውስጥ ያሉ ኦርቶዶክሳውያንን ስልታዊ በሆነ መንገድ እያስመቷቸው ነው።ሰሞኑን በ አለንዴ ባዱ ቀበሌ አራት ኦርቶዶክሳውያን ሚሊሾች ተመርጠው ከአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች ጋር እንዲዋጉ ተልከው ወዲያውኑ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው የታገቱ ሲሆን ሦስቱ ይኑሩ ይሙት አይታወቅም አንደኛውን ደግሞ እያሰቃዩት ነው።እንዲህ ዓይነት ሴራ መከላከያ ውስጥ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ጭምር በተደጋጋሚ ሲሠራ ቆይቷል። ፪ በአሰኮ ወረዳ ካራ አሊባር ቀበሌ ከሳምንት በፊት ማለትም ሐምሌ 25/2018ዓ.ም እድሜው የ37 ዓመት የሆነው ጠግዬ ቃልዬ የተባለ ኦርቶዶክሳዊ በ20 ጥይት ተደብድቦ ተገድሏል።ከወረዳው አመራር ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ አብይ አሕመድ አሊ ድረስ ያሉት " ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ተሰደው የነበሩት ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል"የሚል በሐሰት መረጃ ቢያሠራጩም አንድም ወደ ቤቱ የተመለሰ ኦርቶዶክስ የለም። ሕዝባችን የሰቆቃ ኑሮ እየገፋ ነው በ ቤተ መንግሥቱምበ ቤተ ክህነቱም ክህደት ተፈጽሞበታል። ፫ በሔበን አርሲ ወረዳ ኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ሃይማኖታዊ ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መጥቷል። ሰሞኑን ዘር እየዘሩ ባሉ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በተከፈተ ጥቃት አንድ ሰው እዚያው ማሳ ላይ እያለ በአቃቂ ሁኔታ ተገድሏል አንደኛው ደግሞ ከእነ በሮቹ ታግቶ የተወሰደ ሲሆን በማግስቱም አምስት ኦርቶዶክሳውያን እገታ ተፈጽሞባቸዋል። ይኽ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ወር ጎልጆታ በተባለ ቦታ ላይ አንድ የ19 ዓመት ዲያቆንና 7 ኦርቶዶክሳውያን ገበሬዎች ተገድለዋል።ታግተው ደብዛቸው የጠፋ ይኑሩ ይሙቱ የማይታወቁ ብዙ ኦርቶዶክሳውያን አሉ።ብዙ የወረዳው ቀበሌዎች ከኦርቶዶክሳውያን እየጸዱ ነው አሁንም ርስት ጉልታቸውን እየለቀቁ የሚሸሸ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥራቸው እየጨመረ ነው ይኽ ሁሉ የግፍ ግፍ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ሲፈጸም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባ ኤልሳዕ በከተማና አንጻራዊ ሰላም ያለባቸው አከባቢዎች ላይ እየተመላለሱ ዜና እያሠሩ ግጽታቸውን ከማስገምባት ውጭ ፍጅቱን ለማስቆም አንዳች ያደረጉት እንቅስቃሴ የለም።
ተባብሶ የቀጠለው የኦርቶዶክሳውያን ፍጅት በአርሲ ዞን ጉና ወረዳ ሬኤ አምባ ቀበሌ ልዩ ስሙ መልከምያ መንደር ትናንት 02/12/2018 ዓ.ም ለ 03/12/2018ዓ.ም አዳር የ70ዓመት አዛውንት አቶ ጌታቸው ቶሎበል ከእነ ባለቤታቸው ለቀብር በማይመች ሁኔታ ገድለው ጥለው የሄዱ ሲሆን 17ከብቶቻቸውንም ዘርፈው ወስደዋል
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ይኽ ሁሉ የግፍ ሲፈጸም ዝም ብላችሁ ያያችሁ የሃይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች በምድርም ሆነ በሰማይ ከፍርድ እንደማታመልጡ እንድታውቁ።
ፎቷቸውን ትኩር ብዬ ተመለከትኩት፣ ህይወታቸው ገና ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ወጣቶች እንደሆኑ ያስታውቃሉ። መሀል ላይ ያለው ወጣት ድንጋጤው ይጋባል፣ ሰው ባላጠፋው ጥፋት ሲከሰስ የሚሰማው ስሜት። ሁሉም 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ተረሸኑ፣ አስከሬናቸው እንኳን እንዳይነሳ ለቀናት ተከለከለ። ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው፣ ግዛው ግርማዬ! ነፍስ ይማር! https://www.meseretmedia.org/p/346
❝...የምድር ነገሥታት ሁሉ ፈሩት እጅ መንሻም አገቡለት የእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋራ እንዳለ አውቀዋልና...❞ ነሐሴ አራት በዚህች ቀን ከዳዊት ዘር የሆነ የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ ንጉሥ አረፈ። ከጻድቁ ንጉሥ ከዳዊት በኋላ እንደ ሕዝቅያስ ያለ በእስራኤል ውስጥ አልተሾመም ከዚህ ጻድቅ ንጉሥ በቀር ሁሉም ጣዖትን አምልከዋልና መሠዊያም ሠርተዋልና። እርሱም በነገሠ ጊዜ ጣዖታትን ሰበረ መሠዊያቸውንም አፈረሰ ከነሐስ የተሠራውንም እባብ ቆራረጠ የእስራኤል ልጆች አምልከውት ነበርና እግዚአብሔርም ዘመነ መንግሥቱን እጅግ አሳመረለት በጎ ነገርንም ሁሉ ሰጠው ። ሕዝቅያስም በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዘመን የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ኢየሩሳሌምን ከበባት ይህም ሰናክሬም በዘመኑ እንደርሱ ያለ የሌለ ኃይለኛ ብርቱ የምድር ነገሥታት ሁሉ የፈሩትና የታዘዙለት ነው ። ሕዝቅያስም ከእርሱ ግርማ የተነሣ ፈርቶ አገሩን እንዳያጠፋ ብዙ ወርቅና ብር እጅ መንሻ ላከለት ሰናክሬምም ደስ ብሎት ምንም ምን አልተቀበለም በእርሱ ላይና በልዑል እግዚአብሔር ላይ ተቆጥቶ እግዚአብሔር ከእኔ እጅ ሊያድናችሁ አይችልም በማለት የስድብን ቃል ላከ እንጂ ። ሁለተኛም በልዑል ስም ላይ ስድብና ቍጣ የተጻፈበትን ደብዳቤ ላከ ሕዝቅያስም በሰማ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ አለቀሰ ልብሱንም ቀዶ ማቅ ለበሰ እንዲህም ብሎ ጸለየ ። አቤቱ የእስራኤል አምላክ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ አንተም ብቻህን በዓለም መንግሥታት ላይ ንጉሥ የሆንክ አንተም ሰማይና ምድርን የፈጠርህ ልመናዬን አድምጥ ። ዐይኖችህን ገልጠህ ተመልከት ሕያው እግዚአብሔር አንተን እያቃለለ ሰናክሬም የላከውን ቃሉን ስማ ። ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሕዝቅያስ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬም የተናገውን እንዲነግሩትና ስለርሱና ስለ ሕዝቡ ይጸልይ ዘንድ ወደ ኢሳይያስ መልእክተኞችን ላከ ። ኢሳይያስም ከእግዚአብሔር ቃልን ተቀብሎ እንዲህ ብሎ መለሰለት ልብህን አጽና አትፍራ በዓለሙ ሁሉ እንደርሱ ያለ ያልተሰማ ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሥራ በሰናክሬም ላይ ሊሠራ እግዚአብሔር አለውና ። ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር የላከው መልአክ መጥቶ ከፋርስ ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ የለኪሶም ሰዎች ሲነጋ በተነሡ ጊዜ የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ሁሉ አገኙ የተረፉትም ከንጉሣቸው ጋራ ሸሽተው ነነዌ አገር ገቡ ። ሰናክሬምም ሊጸልይ ወደጣዖቱ ቤት በገባ ጊዜ ልጆቹ አድራማሌክና ሶርሶር በሰይፍ መትተው ገደሉት ። ሕዝቅያስምከሰናክሬም እጅ ድኖ የተመሰገነ እግዚአብሔርን አመሰገነ ። በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ታመመ ለሞትም ደረሰ የአሞፅ ልጅ ኢሳይያስም ወደረሱ መጥቶ እግዚአብሔር እንዲህ አለ ትሞታለህ እንጂ አትድንምና ቤትህን ሥራ አለው። ሕዝቅያስም ፊቱን ወደግድግዳው መልሶ ወደ እግዚአብሔር ለመነ እያመሰገነውም እንዲህ አለ አቤቱ በቀና ልቡና በዕውነት ሥራ በፊትህ ጸንቼ እንደኖርኩ ፈቃድህንም እንደፈጸምሁ አስብ ብሎ ሕዝቅያስ ፈጽሞ ጽኑዕ ልቅሶን አለቀሰ ። ኢሳይያስም ወደ መካከለኛው ዐፀድ ደረሰ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረው ሒደህ ለወገኖቼ ንጉሥ ለሕዝቅያስ ያባትህ የዳዊት ፈጣሪ እግዚአብሔር እንዲህ አለ በለው ። ጸሎትህን ሰማሁ ዕንባህንም አየሁ እነሆ እኔ አድንሃለሁ እስከ ሦስት ቀንም ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ ። በዘመኖችህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨምሬልሃለሁ ከፋርስ ንጉሥ እጅም አድንሃለሁ ይቺንም አገር ስለ እኔና ስለ ባለሟሌ ዳዊት አጽንቼ እጠብቃታለሁ ። ሕዝቅያስም ኢሳይያስን እንዲህ አለው እግዚአብሔር እንደሚያድነኝና እስከ ሦስት ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ለመውጣቴ ምልክቱ ምንድ ነው ። ኢሳይያስም እንዲህ አለው የተናገረውን ቃል ያደርግ ዘንድ ከእግዚአብሔር የተገኘ ምልክቱ ይህ ነው እነሆ ጥላው ወደ ዐሥረኛው እርከን ቢመለስ ምልክቱ ይህ ነው ። ሕዝቅያስም እንዲህ አይደለም የጥላው ወደ ዐሥረኛ እርከን መመለስ ቀላል ነው ። መመለስስ ከሆነ ፀሐይ ወደ ዐሥረኛው እርከን ይመለስ አለ ። ኢሳይያስም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ ፀሐይም ዐሥሩን እርከን ተመለሰ ። ሕዝቅያስንም የምድር ነገሥታት ሁሉ ፈሩት እጅ መንሻም አገቡለት የእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋራ እንዳለ አውቀዋልና ። በመንበረ መንግሥቱም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነግሦ ኖረ ። እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም አረፈ ።
የተስፋ ቅድስናን በምታድለን በእግዚአብሔር እናት በድንግል ማርያም _ ላይ እምነት ይኑራችሁ:: አማላጅነቷ በራሷ ቅድስና የተጠናከረ ስለሆነ ወደ ለእርሷ የምናቀርበው ጸሎት ፈጽሞ ያለ ዋጋ አይቀርም፡፡ በጸሎቷ አማካይነት ለኃጢአቶቻችን ምሕረትና ይቅርታ እናገኛለን፤ድኅነታችንንም እናረጋግጣለን፡፡ የምንባረከውም በጤና፣ በሀብት፣ በጥበቃና በክፉ ቀን ከጥፋት በመጋረድ ነው፡፡ አባ ክሮስታድ
❝ሁሉ የሚቻልህ የሚሳንህ የሌለ የድኆች ፈጣሪ ተስፋ ላጡት ተስፋ የምትሆን አንተን እኛ እንማጸናለን ።❞መጽሐፈ ሰአታት https://c.org/QnvbXPW6LF ❝ In the last three months, more than 144 people have been slaughered, believers massacred in their homes and Churches razed in a surge of ethnic and religious attacks.❞ Hoollie McKay
◈የወንጌል ለምምዳችን በተቃራኒው ሁኗል። በስሁት ልምምድ እነዚህን አፍርተናል👇 ◈1.)የእግዚአብሔርን ቃል እንደተራ ቃል መለማመድ፤ ◈2.)ወንጌልን ሙያና መብያ ማድረግ፤ ◈3.)የማንኖረውን ቃል ለሌላው መስበክ፤ ◈4.)ሳይታወቁ በማስመሰል ሲታወቁ በመቃረን መኖር፤ ◈5.)ሞትንና ትንሣኤ ሙታንን፣ፍትሐ እግዚአብሔርን መርሳት፤ ◈6.)እግዚአብሔር አጎታችን እስኪመስለን ድረስ መዳፈር፤ ◈7.)አምላካዊ አደራን ከቁስ አደራ በታች አድርጎ ማየት፤ ◈8.)ፌዝን ቧልትን እንደ ቁም ነገር ማዘውተር፤ ◈9.)ሲጠቀለል፦ምረረ ገሀነመ እሳትን ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን መዘንጋት ይስተዋልብናል። ◈10.)መፍትሄው ከእነዚህ ጉዳዮች በተቃራኒ መሆን ነው። "ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማል እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል። ይህ ቃል የታመነ ሁሉም እንዲቀበሉት የተገባ ነው ይህን ለማግኘት እንደክማለንና ስለዚህም እንሰደባለን ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።"፩.ጢሞ.፬፥፰-፲
❝ቅድመ ዓለም በነበረ ዓለምን አሳልፎ በሚኖር በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ስም ተነሥቼ አማትባለሁ ፤ የሦስቱን ስም ይዤ እመረኰዛለሁ፤ ብወድቅም እነሣለሁ፤ ወደ ጨለማም ብሄድ እግዚአብሔር ያበራልኛል በእግዚአብሔር አምኛለሁና።❞መጽሐፈ ሰአታት https://c.org/QnvbXPW6LF ❝ In the last three months, more than 144 people have been slaughered, believers massacred in their homes and Churches razed in a surge of ethnic and religious attacks.❞ Hoollie McKay
📌ፍልሰታ ጾም ( ሱባኤ) 📝""አቤቱ የሆነብንን አስብ ተመልከት"" ሰቆቃ ኤር. ፭፥፩ ♣ በሀገራችን ኢትዮጵያ መቼም በማይረሳ የሀዘን ሰቆቃ ፦ ካህናት ሲገደሉ፤ አብያተክርስቲያን ሲቃጠሉ ፤ ወገኔ እየተገደለ ሀብት ንብረቱ ሲዘርፍ አምላክ ሆይ የሆነብንን አስብ በማለት በዚህ ሱባኤ እንዲህ ብለን እንማፀን ኃይላችን እሱ ነውና ፦፦፦፦ ♣"ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣ።" (ሰቆቃው ኤርምያስ ፫: ፵፩) እግዚኦ ማሀረነ እንበል ፦፦ ♣" እግዚአብሔር ከሰማይ እስኪጐበኝና እስኪመለከት ድረስ ዓይኔ ሳታቋርጥ ዝም ሳትል እንባ ታፈስሳለች።" (ሰቆቃው ኤርምያስ ፫: ፵፱-፶) እንዳለ ነብዩ በእንባ እንማፀን ወደ ጌታ፦፦ ♣" ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?" (ሰቆቃው ኤርምያስ ፭:፳) መከራውን ከእኛ እንዲያርቅ እንለምን ፦፦ ♣" አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፤ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።" (መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ ፳፡ ፲፪) በማለት ፍርዱን ለፈጣሪ እንስጥ፦፦ ♣" አቤቱ፥ ማረን አንተን ተማምነናል፤ ጠዋት ጠዋት ክንድ በመከራም ጊዜ ማዳን ሁነን።" (ትንቢተ ኢሳይያስ ፴፫: ፪) መታመኛችን እሱ ነውና ዘወትር የምህረት ክንዱን እንዲዘረጋልን ማረን እንበል ፦፦ ♣" ማረን አቤቱ ማረን" (መዝሙረ ዳዊት ፼፳፫: ፫) ዛሬ ዐይናችን ያየነውን ፣ ጃሮአችን የሰማውን የመረረ ሀዘንና መከራ ከእኛ እንዲያርቅ በሱባኤው ማረን አቤቱ ማረን እንበል ፤ የሞቱትን ነፍስ ይማር ፤ የተጎዱትን ጨርሶ ምህረቱን ይላክልን ፣ ለሕዝቡ መጽናናትን ያድልልን፤ ቤተክርስቲያችንን ከክፉ ይጠብቀልን ፤ ሀገራችንን ኢትዮጵያንን ሰላም ያድርግልን፤ ለዘመናት ተዋዶና ተከባብሮ የኖረውን ክርስቲያኑና ሙስሊሙን ለመለያየት እሳት የሚያፍሙትን ልቦና ይስጥልን!!!! ሱባኤውን በሰላም አስጀምሮ እንዲያስጨርሰን የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁን!!!! 👉የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከት እና ረድኤት በሁላችን ይደርብን ፦ መልካም ሱባዔ🙏 📍ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ
“ሰዎች ሁሉ ጥለውህ በብቸኝነት ጨለማ ውስጥ ስትሆን አታልቅስ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከሰው ጩኸት አውጥቶ በጸጥታ አንተን ብቻህን ሊያነጋግርህ የሚፈልግበት ልዩ ሰዓት ነው። ብቸኝነትህን ወደ ማጉረምረም ሳይሆን ወደ ጸሎትና ወደ ምስጋና ለውጠው፤ ያን ጊዜ ክፍሉ በቅዱሳን መላእክት ሕብረት ይሞላል።’’ ✍️ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን
❝ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ ።ለያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገ፟ባ፟ችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ ፥በጨው እንደ ተቀመመ ፥ በጸጋ ይሁን ።❞ቆላ4:5-6 https://c.org/QnvbXPW6LF ❝ In the last three months, more than 144 people have been slaughered, believers massacred in their homes and Churches razed in a surge of ethnic and religious attacks.❞ Hoollie McKay
«ሞዐ ተዋሕዶ» የማነው? ከወቅታዊ የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ጎልተው ከሚነሱ አጀንዳዎች መካከል አንዱ «ሞዐ ተዋሕዶ» ነው። ስለ ንቅናቄው ግልጽና የጠራ ግንዛቤ ይኖረን ዘንድ በተረዳሁት መጠን የሚከተለውን ምልከታ ማጋራት ወደድሁ። «ሞዐ ተዋሕዶን» በተመለከተ ብዙ ግራ መጋባቶች ይስተዋላሉ። አንዳንዶች ሆን ብለው በሚመስል ሁኔታ ከዐውዱና ከዓላማው ውጭ የሆነ መረጃ በማሰራጨት፣ ንቅናቄው የፖለቲካ ዓላማ እንዳለው አድርገው በመሳል ብዙዎችን ያሳስታሉ። እንዲያውም «ሞዐ ተዋሕዶ» በአንዳንድ የመንግሥት አካላትም ሆነ በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ተቃዋሚዎች በኩል የሚለጠፍበት አሉታዊ ስም፣ በተግባር ከሚሠራው በጎ ሥራ ጋር በፍጹም የሚገናኝ አይደለም። ከዚያም አልፎ ስሙን የመምቻ ዱላ በማድረግ፣ ኦርቶዶክሳውያንን ለማሳቀቅ፣ ለማሰር፣ ለማሳደድና ለማጥቃት እንደ ምክንያት ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። ሆኖም «ሞዐ ተዋሕዶ» ምንም ዓይነት የፖለቲካ ወገንተኝነት የሌለውና ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ሊጋሩት የሚችሉትን ዓላማ ሰንቆ የሚጓዝ ግብረ-ኃይል ነው። ዋና ግቡም ቤተ ክርስቲያንን ከጥቃት፣ ከስደትና ከጥፋት መከላከል ብቻ ነው። አንዳንዶች ሞዐ ተዋሕዶን ከ«ሞአ አንበሳ» ጋር በማመሳሰል ንቅናቄውን ከንጉሣዊ ሥርዓት መመለስ ጋር ለማያያዝ የሚያደርጉት ጥረት ፈጽሞ መሠረት የለውም። የ«ሞዐ ተዋሕዶ» መነሻ ቅዱስ ሲኖዶስ በ በጥቅምት 2013 ዓ.ም. የምልዓተ ጉባኤው ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ያደረገውን ጥሪ መሠረት ያደረገ ነው። ሲኖዶሱ በምእመናንና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በመመልከት፣ ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የካቲት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በይፋ ተመሠረተ። ሞዐ ተዋሕዶ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚሰነዘሩ መዋቅራዊ፣ አስተዳደራዊና ርዕዮተ-ዓለማዊ ጥቃቶችን ለመመከት የሚሠራ የጥብቅና ንቅናቄ (Advocacy Movement) ነው ማለት ይቻላል። ግብረ-ኃይሉ ለዘመናት የነበረውን «የዝምታ ስልት» በመስበር፣ የቤተ ክርስቲያኗን መብትና ድምፅ በግልጽ የሚያሰማበትን ሰላማዊ መንገድ ቀይሷል። ይህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከዝምተኛ ተከታይነት ወደ «ንቁ ተሟጋችነት» የተሸጋገሩበትን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ያመላክታል። «ሞዐ ተዋሕዶ» ከምሥረታው ዕለት ጀምሮ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ለሚመለከታቸው አካላት ያቀረባቸው ሰባት ዋና ዋና ጥያቄዎችን በማስተጋባት ላይ ይገኛል። እነዚህም በትምህርት፣ በሚዲያና በልማት ስም የሚሰራጩ ጸረ-ኦርቶዶክስ ትረካዎች እንዲቆሙ፣ በመንግሥት መዋቅርና በኢኮኖሚ ላይ የሚፈጸም መዋቅራዊ ማግለል እንዲያበቃ፣ ቤተ ክርስቲያንን በብሔርና በቋንቋ የመከፋፈል ፖለቲካዊ ሴራዎች እንዲገቱ፣ በምእመናን ላይ የሚፈጸሙ አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ጥቃቶች እንዲቆሙ፣ በጥፋተኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ተወስዶ ለተጎጂዎች ካሳ እንዲሰጥ፣ የተፈናቀሉ ምእመናን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ፣ እንዲሁም «አዲሲቷን ኢትዮጵያ» በመገንባት ሰበብ የሚካሄዱ ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የማጥፋት ዘመቻዎች እንዲቆሙና መንግሥት ይፋዊ የይቅርታ መግለጫ እንዲሰጥ የሚጠይቁ ናቸው። በአጠቃላይ፣ መገንዘብ እንደቻልሁት ሞዐ ተዋሕዶ በየትኛውም ዓይነት የፖለቲካ አሰላለፍ ያልወገነ፣ ዋና ዓላማውና ትኩረቱ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻና ብቻ የሆነ ንቅናቄ ነው። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የታሪክ እውነታ ሀገርና ቤተ ክርስቲያን ተነጣጥለው ስለማይቆሙ፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አወንታዊ አስተዋጽኦ ከመስጠት ወደ ኋላ አይልም። ሁሉም ኢትዮጵያውያን በፍቅርና በመከባበር የሚኖሩባት፣ ፍትሕ፣ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነባት ሀገር እንድትገነባ እንደቀደምት አያቶቹ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል። እንደ እኔ መረዳት፣ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ እየደረሰ ያለውን ዘርፈ-ብዙ ጥቃት ለመከላከል ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱበት የትብብር መረብ በመሆኑ «ሞዐ ተዋሕዶ» የማንም ሳይሆን የሁሉም ነው። በአሁኑ ወቅት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በህልውና አደጋ ውስጥ የምትገኝ በመሆኗና ይህንን ሰፊና መዋቅራዊ ፈተና ለመመከት ይመጥናል ተብሎ የሚታመን ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት ባለመኖሩ፣ እንደ «ሞዐ ተዋሕዶ» ያሉ ንቅናቄዎችን መደገፍ፣ ማበረታትና ማሳደግ ከመላው ኦርቶዶክሳውያን የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ(ዶ/ር)