እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo Media
Статистикаእሔ የቴሌግራም መንፈሳዊ ቻናላችን ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖታችን ምንማማርበት መንፈሳዊ መድረክ ነው። ለሌሎች ያጋሩ፣ አዳዲሶችም ተቀላቀሉ(join) አድርጉ።
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 31
- Всего постов
- 72
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 153
- 1/48двое суток
- 175
- 1/72трое суток
- 189
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ህይወታችንን ለወጠክው ከደስታ ወደ መከራ ብለው በሚያለቅሱ የትግራይ የአማራ እና የኦሮሞ እናቶች አንተ በደስታ ታለቅሳለህ?
☝️የሞትከው አንድን ታናሽ ብላቴና ለ መ ግ ደ ል ይህን ያህል ስትደክም ነው! በጥፊ ብቻ የሚሞት ህፃንን እጆቹን የፊጥኝ አስረህ፥ ግንባሩ ላይ አፈ ሙዝ ደቅነህ ፎቶ ስትነሳ በእውነትም ከሰውነት ወጥተህ አረመኔ ጭ ራቅ መሆንህን በግልጽ ታስረዳለህ። ይሄ የሚሆነው በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የኦርቶዶክሳውያን ቄራ በሆነችው 'አርሲ' በተባለች ቦታ ነው!!! እንግዲህ እንዲህ ያለውን ጭካኔ ከየት እንደተማራችሁት እናንተው ንገሩን።👇 Megbaru Asmare
በአሰቦት ገዳም አንድ መነኮስ ጉዳት ደረሰባቸው ተደጋጋሚ ጥቃት በሚያጋጥመው በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አንድ መነኮስ አባት ባልታወቁ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ። የገዳሙ አገልጋይ የሆኑት አባ ተክለ ዮሐንስ ደረሰ በእንጨት ለቀማ ላይ እያሉ ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 አካባቢ አደጋው እንደደረሰ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት ጽ/ቤት ገልጿል። ታጣቂዎቹ አባ ተክለ ዮሐንስን በአሰቃቂ ሁኔታ ጉሮሯቸውን ወግተው ለመግደል ሲሞክሩ ለማምለጥ የቻሉ ሲሆን ገዳሙም በሕይወትና በሞት መካከል ያሉትን አባት ወደ ህክምና የወሰዱ መሆናቸውን ገልጸው እየደረሰባቸው ያለውን ተደጋጋሚ ጥቃት ለመከላከል ለሚመለከታቸው አካላት መረጃውን አድርሱልን በማለት ጥሪ አቅርበዋል። የሀገረ ስብከቱም ጽ/ቤት በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ተደጋጋሚ ጥቃቶችና ችግር እንዲቀረፍና ገዳማውያኑም በተረጋጋ ሁኔታ እንዲኖሩና ለሀገር እንዲፀልዩ የመንግስት የፀጥታ አካላት መፍትሄ እንዲሰጥና ክትትል እንዲያደርግ ለሚመለከተው የዞኑ የፀጥታ አካላት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስና የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ሪፖርት በማድረግ ክትትል እያደረጉ መሆኑን ገልጿል። ዘገባው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ነው። #አሰቦትደብረወገግ #ቤተክርስቲያን #ዜና
በአርሲ ተባብሶ የቀጠለው ጅምላ ፍጅት ፩ ጉና ወረዳ ሬኤ አምባ ቀበሌ 02/12/2018 ዓ.ም ለ 03/12/2018ዓ.ም አዳር የ70ዓመት አዛውንት አቶ ጌታቸው ቶሎበል ከእነ ባለቤታቸው ለቀብር በማይመች ሁኔታ ገድለው ጥለው የሄዱ ሲሆን 17ከብቶቻቸውንም ዘርፈው ወስደዋል በዚህ ወረዳ ያለው ኦርቶዶክሳዊ አብዛኛው በአክራሪዎቹ ከበባ ውስጥ ነው ያለው። ራሳቸውንም እንዳይከላከሉ የወረዳው ባለሥልጣናት ከፍተኛ ጫና እያደረጉ ይገኛሉ። ይኽ ብቻ አይደለም በጸጥታ መዋቅር ውስጥ ያሉ ኦርቶዶክሳውያንን ስልታዊ በሆነ መንገድ እያስመቷቸው ነው።ሰሞኑን በ አለንዴ ባዱ ቀበሌ አራት ኦርቶዶክሳውያን ሚሊሾች ተመርጠው ከአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች ጋር እንዲዋጉ ተልከው ወዲያውኑ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው የታገቱ ሲሆን ሦስቱ ይኑሩ ይሙት አይታወቅም አንደኛውን ደግሞ እያሰቃዩት ነው።እንዲህ ዓይነት ሴራ መከላከያ ውስጥ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ጭምር በተደጋጋሚ ሲሠራ ቆይቷል። ፪ በአሰኮ ወረዳ ካራ አሊባር ቀበሌ ከሳምንት በፊት ማለትም ሐምሌ 25/2018ዓ.ም እድሜው የ37 ዓመት የሆነው ጠግዬ ቃልዬ የተባለ ኦርቶዶክሳዊ በ20 ጥይት ተደብድቦ ተገድሏል።ከወረዳው አመራር ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ አብይ አሕመድ አሊ ድረስ ያሉት " ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ተሰደው የነበሩት ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል"የሚል በሐሰት መረጃ ቢያሠራጩም አንድም ወደ ቤቱ የተመለሰ ኦርቶዶክስ የለም። ሕዝባችን የሰቆቃ ኑሮ እየገፋ ነው በ ቤተ መንግሥቱምበ ቤተ ክህነቱም ክህደት ተፈጽሞበታል። ፫ በሔበን አርሲ ወረዳ ኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ሃይማኖታዊ ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መጥቷል። ሰሞኑን ዘር እየዘሩ ባሉ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በተከፈተ ጥቃት አንድ ሰው እዚያው ማሳ ላይ እያለ በአቃቂ ሁኔታ ተገድሏል አንደኛው ደግሞ ከእነ በሮቹ ታግቶ የተወሰደ ሲሆን በማግስቱም አምስት ኦርቶዶክሳውያን እገታ ተፈጽሞባቸዋል። ይኽ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ወር ጎልጆታ በተባለ ቦታ ላይ አንድ የ19 ዓመት ዲያቆንና 7 ኦርቶዶክሳውያን ገበሬዎች ተገድለዋል።ታግተው ደብዛቸው የጠፋ ይኑሩ ይሙቱ የማይታወቁ ብዙ ኦርቶዶክሳውያን አሉ።ብዙ የወረዳው ቀበሌዎች ከኦርቶዶክሳውያን እየጸዱ ነው አሁንም ርስት ጉልታቸውን እየለቀቁ የሚሸሸ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥራቸው እየጨመረ ነው ይኽ ሁሉ የግፍ ግፍ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ሲፈጸም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባ ኤልሳዕ በከተማና አንጻራዊ ሰላም ያለባቸው አከባቢዎች ላይ እየተመላለሱ ዜና እያሠሩ ግጽታቸውን ከማስገምባት ውጭ ፍጅቱን ለማስቆም አንዳች ያደረጉት እንቅስቃሴ የለም።
ከብሔራዊ ምክክሩ ጀርባ በኦሮሚያ ብልጽግና ካድሬዎችና በብሔራዊ ደህንነት ቢሮ አባላት እየተፈጸሙ ያሉ ደባዎች፤ ከደረሱኛና አፈትልከው ከወጡ ቁልፍ መረጃዎች በጥቂቱ፤ ++++++ የቆዩና ታሪካዊ የሆኑ ስብራቶችን፣ ፖለቲካዊ ቁርሾዎችን፣ የተፈጸሙ በደሎችን፣ ግፎችንና የመብት ጥሰቶችን፣ በማህበረሰቡ መካከል የተፈጠሩ ኢ-ፍትሐዊ የሆኑ ነገሮችን ለማከምና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት በሚል ለአራት አመት የተደከመበት የብሔራዊ ምክክር አዳዲስ ቁርሾዎችንና የፖለቲካ ሽኩቻዎችን መፍጠሪያ መድረክ ሆኗል። ከሁለት ቀን በፊት እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ላይ ተሳተታፊ የሆኑ አምስት ሰዎችን በተናጠል ሰፋ ያለ ጊዜ ወስጄ ማውራት ችዬ ነበር። ከአምስቱ ሁለቱ የቆዩ የብልጽግና አባላት ሲሆኑ በመንግስት ሽፋን የኦሮሚያ ብልጽግና አባላት በምክክሩ ላይ እየፈጸሙት ባለው ፍጹም ሕገወጥ፣ መረን የለቀቀና አይን ያወጣ የአጀንዳ ነጠቃ ሥራ አንጀታቸው ያረሩ ካድሬዎች ሲሆኑ አንዱ ለብልጽግና ካለው ስስ ልብና ጭፍን ድጋፍ የተነሳ ዲያስፖራውን ወክለዋል በሚል ከውጭ የገባ ሰው ነው። ለማንኛውም በነበረኝ ሰፊ ውይይት ከዚህ የሚአተሉት መረጃዎች ደርሰውኛል። 1ኛ/ በዚህ ምክክር ላይ ሁሉም የብልጽግና አባላት ለብቻቸው ተጠርተው በመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና በተለይም በደህንነት ሰዎች በተሰጣቸው ጥብቅ ማሳሰቢያ ብልጽግና ከሚፈልጋቸው አጀንዳዎች ውጪ የመንግስትን ገጽታ የሚጎዱ ምንም አይነት አጀንዳዎች እንዳይጸድቁ እንዲረባረቡ፣ 2ኛ/ ከኦሮሚያ ክልል ያጡ የብልጽግና አባላት ደግሞ ለብቻቸው በየቀኑ ከምክክሩ በኋላ በየአጀንዳው ላይ ከደህንነትና ከክልሉ ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩና ትዕዛዝ እየተቀበሉ ሌሎች ተሳታፊዎችን (ኦሮሞ ያልሆኑ የብልጽግና አባላትን ጨምሮ) በተናጠል እንዲያስፈራሩና በስብሰባዎቹም ላይ ቁጣቸውን እንዲገልጹ፣ 3ኛ/ በተወሰኑና እጅግ አወዛጋቢ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ፤ በተለይም የአዲስ አበባና የድሬደዋ ከተሞች እጣፈንታ፣ በኦሮሚያ ክልል በተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች፣ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ስለሚደርሰው ተደጋጋሚ ጥቃት፣ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በተነሱ የድንበር ይገባኛል ጥያቄ ውዝግቦችና ሌሎች ከኦሮሚያ ክልል ጋር በተያያዙ በተነሱ ጉዳዬች ላይ በተደረጉ ውይይቶች ላይ ጠንካራ አቋም ይዘው እውነቱንና ትክክለኛ ያሉትን ነገር የተናገሩ ሰዎች በስም ተለይተው በተናጠል በደህንነት አባላትና በካድሬዎቹ በኩል ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ የደረሰባቸው መሆኑን። 4ኛ/ ካናገርኳቸው የብልጽግና አባላት አንደኛው በሦስት የኦሮሚያ ብልጽግና አባል 'አርፈህ ተሸመጥ፣ በመንግስት ደህንነቶች አይን ውስጥ ገብተሃል፣ እያንዳንዱ ንግግርህ ተቀርጿል፣ እንደ በጥባጭ ነው የተቆጠርከው፣ ትላንት ማታ የኦሮሚያ ብልጽግና አባላት ከደህንነት ሰዎች ጋር በነበረን ውይይት ያንተም ስም ከበርካታ ሌሎች ተቀናቃኝ ሰዎች ጋር ተካቶ ስም ሲነሳ ነበር፣ እርምጃ ሊወሰድብህ ይችላል፣ አርፈህ ልጆችህን አሳድግ' የሚሉ ምክር የመሰሉ ማስጠንቀቂያዎች ከኦሮሚያ ክልል በመጡ ተሳታፊዎች የተሰጠው መሆኑን ገልጾልኛል። 5ኛ/ ሁሉም የምክክሩ ውይይቶች በቪዲዬ የሚቀዱ ሲሆን ኮሚሽኑ ለታሪካዊ ሰነድነት የሚቀመጥ ነው ቢልም ውይይቶቹ በሚካሄዱባቸው ሰዓት እዛው ሕንጻው ውስጥ የተለየ ክፍል ተዘጋጅቶላቸው ወሩን ሙሉ የእያንዳንዱን ስብሰባ ሂደት በእስክሪን እንዲከታተሉ የተመደቡ የብሔራዊ ደህንነት አባላተት ማን ምን ተናገረ የሚለውን እየመረመሩ ግለሰቦቹ ላይ ክትትል እንደሚያደርጉና አስፈላጊም ሲሆን ግለሰቡ የያዘውን አቋም እንዲቀይር ውስጥ ባሉ ተሳታፊዎች መልዕክት እንደሚላክበት፣ ግለሰቡ አቋሜን አልቀይርም ካለም ደህንነቶቹ በቀጥታ እንደሚያናግሩትና እንደሚያስፈራረት በደሉ የደረሰበት ተሳታፊ አጫውቶኛል። 6ኛ/ እጅግ አሳፋሪ የሆነው ጉዳይ ደግሞ ከላይ በጠቀስኳቸው የኦሮሚያ ክልልን የሚመለከቱ ጉዳዬች ላይ ውይይት ተደርጎ በአብላጫው ድምጽ የጸደቁና በቃለ ጉባኤ የሰፈሩ የውይይት ሃሳቦች ለፊርማ ተዘጋጅተው ሲመጡ በደህንነትና በኦሮሚያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ውሳኔ ተቀይረውና ከስምምነቱ ውጪ ተዘጋጅተው ለፊርማ እንደሚቀርቡ፣ አንፈርምም ባሉ ሰዎች ላይም የግድያ ዛቻ፣ ማስፈራሪያና እንደሁኔታው መደለያዎችም እንደሚቀርቡ፤ 7ኛ/ ውይይት ተደርጎባቸው በተሰብሳቢው የጸደቁ ነገር ግን የኦሮሚያ ክልልን የሚመለከቱ ጉዳዬች ሁነው የክልሉን ካድሬዎች የማያስደስቱ ጉዳዮች ውይይቱ ካለቀም በኋላ ከሰነዶቹ ላይ ተለይተው እንዳይካተቱ መደረጉን እና ይሄንንም የተቃወሙ ግለሰቦች ላይ ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ እየተሰነዘረ መሆኑን፣ 8ኛ/ በእያንዳንዱ ውይይት በሚካሄድበት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ለውይይት ከተመደቡት ሰዎች ውጭ አስተባባሪ፣ አስተናባሪ መስለው እያንዳንዱን ተወያይ የሚቆጣጠሩ ሲቪል የለበሱ የደህንነት ሰዎች መኖራቸውና በተወያዬቹ መካከል እርስ በርስ የሚደረጉ ምክክሮችን ጭምሮ ለመስማትና ለመቆጣጠር የሚጥሩ መሆኑን። በአጠቃላይ ይህ የምክክር ሂደት ከምክክር ኮሚሽኑ እጅና ቁጥጥር ሙሉ በሙሉ መውጣቱንና ምክክሩን ከጀርባ ሆኑ አቅጣጫ እያሲያዘ ያለው የኦሮሚያ ብልጽግና ካድሬዎችና የብሔራዊ ደህንነት ቢሮ መሆናቸውን ያነጋገርኳቸው የብልጽግና አባላት ብዙ ማሳያዎችን እያቀረቡ አረጋግጠውልኛል። ያሬድ ኃይለማርያም የሰባዊ መብት ተሟጋች
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
♦ይህም ይመዝገብ፦ ይህን ግፍ ሁሉም ይወቀው! የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ፦ «ሽፍቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል» ብለዋል! ይህ ንግግር የትዕቢት፣ የማን አለብኝነት እና «ምን ታመጣላችሁ?» ባይነት ግልጽ ማሳያ ነው። የአገዛዙ ሥርዓት ምን ያህል ጨካኝና የዜጎች ህይወት የማይገደው መሆኑን ይህ መራር መስክርነት ነው ። እጃቸው ወደ ኋላ በገመድ ታስሮ፣ ከፍተኛ እንግልትና ስቃይ ከተፈጸመባቸው በኋላ ጭንቅላታቸውን በጥይት በመምታት በግፍ ተረሽነዋል። የግፉ አፈጻጸም በዚህ ብቻ አላበቃም፤ ከግድያው በኋላ አስከሬናቸው በሜዳ ላይ ተጥሎ ማንም እንዳያነሳና እንዳይቀብር ጥብቅ ክልከላ ተደረገበት። በዚህም ምክንያት እጃቸው እንኳን ሳይፈታ ለሶስት ሙሉ ቀናት ተጥለው የዱር እንስሳት ሲሳይ እንዲሆኑ ተደርጓል፤ የጥይቱ ምት በፈጠረው ከባድ ጉዳት ምክንያትም የአስከሬኖቹ ገጽታ ሙሉ በሙሉ በመበላሸቱ ማንነታቸውን ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ ነበር። አቶ ተመስገን ካሳ ግን ይህን እጅግ አረመኔያዊና ዘግናኝ ድርጊት ትልቅ ጀብዱ እንደፈጸሙ ያህል «በሽፍቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ» ሲሉ በኩራት ተናግረዋታል። እንግዲህ ልብ በሉ! ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ተገድደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ እጅና እግራቸውን የፊጢኝ አስሮ በግፍ መረሸን ይቅርና ፤ እልም ባለ የጦርነት አውድማ ላይ እንኳን የተማረከ የጦር ምርኮኛ አይገደልም፤ አይረሸንም! እነዚህ የግፍ ሰላባዎች ሲዋጉ ወይም ሲዘርፉ እጅ ከፍንጅ አልተያዙም፤ በህግ ፊት ቀርበው ወንጀለኛነታቸው በፍርድ ቤት አልተረጋገጠም። ነገር ግን ያለ ምንም ፍርድ በግፍ ተረሸኑ! ይህ ህሊናን የሚፈታተን ግፍና በደል የታሪክ ማህደር ላይ በጥቁር ቀለም ይመዝገብ! የእውነትና የፍትህ ቀን እሩቅ አይደለምና! ይድነቃቸው ከበደ
የፋሽስታዊ ሥርዐት መገለጫ
видео или голосовое, без подписи
በ ነሐሴ 2/2018ዓ.ም ሌሊት በአርሲ ዞን ጉና ወረዳ ሬኤ አምባ ቀበሌ "ዓረባዊት ኢትዮጵያን" ለመፍጠር ታጥቀው ጫካ በገቡ በአክራሪ የ ኦሮሞ እስላም ታጣቂዎች ከእነ ባለቤታቸው የተገደሉ አቶ ጌታቸው ቶሎበል። ከኦርቶዶክሳውያን የጸዳች አዲስ ሀገር የመፍጠር ፕሮጀክት የሥርዐቱ ዋና ዓላማ ሲሆን ለፍትፍትና ለመኪና በጳጰሱ እረኛ ነን ባዮች ደግሞ ተባባሪዎች ናቸው።በአጭሩ ቤተ መንግሥትና ቤተ ክህነቱን የሞሉ ይሁዳዎችና ዴማሶች በጋራ ተቀናጅተው እየፈጁን ነው።
አሳዛኝ ዜና የታላቁ የየኔታ ይትባረክ የሥጋ ልጃቸው እና ተተኪ ይሆናል ብለው የደከሙለት ደቀ መዝሙራቸው አርፏል። ደቀ መዝሙር አማኑኤል ይትባረክ ከአባቱ ርቆ በደራ ወረዳ በአንበሳሜ ከተማ የአቋቋም ትምህርቱን እየተከታተለ ባለበት ወቅት በድንገት ተገ'd'ሏል። በእንተ ስማ ለማርያም ብሎ በረሀብ እና በስቃይ ለቤተ ክርስቲያን ተተኪ ለመሆን እየደከመ በነበረው ወጣት ሊቅ ላይ የተፈጸመው ጥ'ka'ት እጅግ አስደንጋጭም አሳዛኝም ነው። በእስቴ ማቢ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በርካታ የአቋቋም መምህራንን ላፈሩት ለየኔታ ይትባረክ እና ቤተሰባቸው መሪር ሐዘን፣ ለቤተ ክርስቲያንም ኪሳራ ነው። አረጋዊው አባት የኔታ ይትባረክ ያለ ደመወዝ ረጅም ዓመታትን ያገለገሉና እያገለገሉ ያሉ ሊቅ ናቸው። ደመወዝ ለሌለው የገጠር የአብነት መምህር ልጅ ማሳደግ ምንኛ ፈታኝ እንደሆነ ሁሉም ያውቀዋል። ሳይበሉ እያበሉ፣ ሳይለብሱ እያለበሱ ያሳደጉት ልጃቸው ሲያርፍ ለየኔታ ሐዘኑ ከባድ ነውና በቅርብ ያላችሁ ከጎናቸው አትለዩ። ለየኔታ ይትባረክና ለመላ ቤተሰቡ መጽናናትን፣ ለሟች ወንድማችን ዕረፍተ ነፍስን እንመኛለን። (በማን እና እንዴት ሞተ የሚለውን ትክክለኛ መረጃ ሳገኝ አቀርባለሁ) ዲ/ን ታደለ
видео или голосовое, без подписи
እየሆነ ያለው ይኽ ነው።በእንግድነት የተቀበልናቸው ሰዎች ኦርቶዶክስ ጠሉን ሥርዐት ተደግፈው ኢትዮጵያን " ዐረብ ካላደረግናት"እያሉ ነው።
የምንመካከረው በብሔራዊ መግባባት አገርን ለማጽናት እንጂ የቡድን የበላይነትን ለማንበርና ሌላ አዲስ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማዋለድ አይደለም! በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ዙሪያ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ የአቋም መግለጫ ኢትዮጵያ ሀገራችን እያለፈችበት ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት በምክክር ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር አገር ልትጸና ይገባል በሚል ጽኑ እምነት ፓርቲያችን የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል። በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምሥረታው፣ በኮሚሽነሮች አመራረጥና በኮሚሽኑ የአሠራር ሂደት፣ የአካታችነት ችግሮች፣ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች በሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽዕኖና መሰል አስቻይ ባልሆኑ ሁኔታዎች ላይ ጠንካራ ሀሳቦችንና የመፍትሔ ጥቆማዎችን ፓርቲያችን ሲያቀርብ መቆየቱም ይታወቃል። ፓርቲያችን በምክክሩ ሂደት እና ከምክክሩ አስቀድሞ ስኬታማ ምክክር ለማካሄድ ሊተገበሩ ይገባቸዋል ብሎ የሚያምንባቸውን ሃሳቦችና ቅድመ ሁኔታዎች በግልጽ አስቀምጦ ያለመታከት ሲያሳስብ የቆየ ቢሆንም ሰሚ ጆሮ በመጥፋቱ አገር ባለችበት ሁኔታ ወደ ምክክር እንድትገባ ተደርጓል። እናት ፓርቲ ይህን በትክክለኛው ጎዳና ተጉዞ በስኬታማ መልኩ ሊጠናቀቅ ቢችል የአገራችን መፃኢ ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ ሊከፍት የሚችልን ሂደት ቅድመ ሁኔታዎች ስላልተሟሉ በማለት በቸልታ ሊመለከተው ያልፈለገ ሲሆን ይልቁን ሂደቱ ውስጥ በማሳተፍ ትክክለኛነቱን ካረጋገጠ ለአገር የሚበጁ ሀሳቦችን በማንሳት ለመሞገት ብሎም በተመካካሪዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማድረግ በጎ ተጽዕኖ መፍጠርን በማሰብ በምክክሩ እየተሳተፈ ይገኛል። አገር የገባችበት ችግር ከምንጊዜውም ይልቅ በተወሳሰበበት ሁኔታ ውስጥ የምክክሩ ሂደት ከነችግሮቹ እያነከሰ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየተሸጋገረ ያለ ቢሆንም በሂደቱ የጎሉ ችግሮች እየተስተዋሉበት ይገኛል። ለአብነትም በወረዳ ደረጃ ተደረጉ ከተባሉ ምክክሮች ጀምሮ የምክክር ተሳታፊዎች የገዥው ፓርቲ አባላት እና የሥርዓቱ ደጋፊዎች መሆናቸው ሲገለጽ የነበረ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ባለው በዚህ ምክክርም አብላጫውን ቁጥር የሚይዙ ተሳታፊዎች የገዥው ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች መሆናቸውን መረዳት ችለናል። በምክክሩ ሂደት ድምጾች እንዳይሰሙ መገደብ፣ የአካታችነት ችግሮች፣ የተሳታፊዎች ምርጫና ምደባ፣ የፍትሓዊነት፣ የገለልተኝነት፣ የግልጽነት ማነስ፣ በጸጥታ አካላት ታጅቦ መወያየት፣ የውይይት ተሳትፎውን ለማጥበብ ከውስጥና ከውጭ የሚደረጉ ጫናና ወከባዎች፣ የምክክሩ አጠቃላይ ወለል ወይም ቀይ መሥመር ያለመኖር እና የመሳሰሉ ጉልህ ችግሮች የተስተዋሉበትን እውነታ ታዝበናል። ምክክሩ ኢትዮጵያን ለማጽናት ሳይሆን እንዳለፈው ጊዜ ስሑት ትርክትና ሕገ መንግሥታዊ መሠረት ያለው የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት ብሎም ሁሉ ለእኔ ብቻ ፍላጎት በአጠቃላይ ኢትዮጵያን አንደ ሀገር እና ዋና መገለጫ ጌጦቿን ኹሉ ለድርድር ያቀረበ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በዚኽም የምክክሩን ፍትሓዊነትና ቅቡልነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ አግኝተነዋል። ይኽ ደግሞ ፓርቲያችንና ሌሎች ተሳታፊዎች ከሂደቱ ራሳቸውን እንዲያገሉ እያስገደደ ይገኛል። ምክክር የቅንጦት ጊዜ ኹነት ሳይኾን የቀውስ ጊዜ መፍትሔ ማመንጫ ውጥን ነው። ቀዳሚው ዘርና ጎሳ ላይ የተመሠረተው ፌዴራሊዝም ሀገራችንን ሊያጠፋት ከጫፍ ደርሶ እያለ ይህን ያፈጠጠ አደጋ ሊያስቀር ወይም ሊያለዝብ የሚችል መፍትሔ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ምልክቱ እንኳ አለመታየቱ እጅግ የሚያስቆጭ ነው። እንዲያውም ገና ምክክሩ ሳይጠናቀቅ አንዳንድ ክልሎችን በስም ተጠርተው ሌላ ክልል ለማዋለድ ምክረ ሀሳብ ሲነሳ ብቻ በደስታ ይጨበጨባል፤ ሌላው ደግሞ ማን ነክቶን እያለ በማን አለብኝነት መግለጫ ይሰጣል። ይህም በዘርና በጎሳ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ለሀገር አንድነትና ሕልውና ሥጋት መሆኑን አንዱ ማሳያ ነበር። በሌላ በኩል ይህ ምክክር እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ቢያንስ ሦስት ክልሎች ላይ ጦርነቶች እየተካሄዱ ነው፤ ሌላውም መጣሁ እያለ ነው። የርስ በርስ ጦርነቱን ጉዳይ ብልጽግናን ጨምሮ ሁሉም ተዋጊ ኃይሎች ወደ ድርድር እንዲመጡ እውነተኛ፣ ጥልቅ ውይይትና ደፋር ምክረ ሀሳብ ይፈልግ የነበረ ቢሆንም ሂደቱ ግን እከከኝ ልከክህ ሆኖ የአንድን ወገን ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ ቀድሞ የተወሰነን ውሳኔ በሀገራዊ ምክክር ስም ቅቡልነት እንዲኖረው ለማድረግ እየተከናወነ ነው። የታሪክና የትርክት መፋለሶች በናኙበት በዚህ ዘመን ቢያንስ እውነት አፈላላጊ ቡድኖችን አዋቅሮ ግማሽ መንገድ እንኳን ማቀራረብ ይገባ ነበር። እነዚኽንና መሰል አንኳር ጉዳዮች እንጂ የኢትዮጵያ መሪ (ከፕሮቶኮል አንጻር ነው አመክንዮው) ጠቅላይ ሚንስትር ሳይሆን ፕሬዝዳንት መኾን ነው ያለበት ላይ አልነበረም የችግሮቹ ቋጠሮ ያለው። ዙሪያ ዙሪያዋን ሲሏት የነበረችውን አዲስ አበባ በወከባ ብዛት ለአንድ ቡድን ሆ ብሎ ለማሳቀፍና አዲስ የፀብ ግንባር ለመቀስቀስም አልነበረም ለምክክር የተቀመጥነው፡፡ ድሬዳዋ ከየት ወገን ትሑን የሚለው ሀገር ሊያፈርስ ደርሶም አልነበረም በሚሊዮን የሚቆጠር የሀገር ሀብት አባክነን ለምክክር የተቀመጥነው፡፡ በዓለም በልዩነት የምንታወቅበት ዘመን አቆጣጠር አሥሮ ይዞንም አልነበረም ምክክር ያስፈለገን፡፡ በአጠቃላይ የተጠቀሱና መሰል የተስተዋሉ ሳንካዎች ምክክሩ ከታለመለት ዓላማና በሀገሪቱ ያለውን ችግር ከሥሩ ከመፍታት ይልቅ ጠግኖ ለማስቀጠል፣ ለይምሰል የተደረገ፣ የአገዛዝ እና ቡድን(ኖች) ጠባብ ጊዜያዊ ፍላጎት ለማሳካት በሚመስል ሁኔታ እየተከናወነ እንዳለ ይሰማናል። በዚህም በመሠረታዊ የሀገር ሕልውና ጉዳዮች በዋናነት የርስ በርስ ጦርነትን በማስቆም፣ የዘርና ጎሳ ፌዴራሊዝምን ማስቀረት/ማለዘብ እንደ ዋና ግብ መያዝና መሰል የተጋረጡ ፈተናዎች በአግባቡ ተረድቶ እልባት የሚበጅበትን አቅጣጫ ሊያስቀምጥ ያልቻለ ሀገራዊ ምክክር ከመነሻው እንደከሸፈ ለመረዳት ነቢይ መሆን አይጠይቅም። እናት ፓርቲ ከዚህ በመለስ ባሉ የምክክር አጀንዳዎች እና በምክክር ስም ተላለፉ በሚባሉ ስምምነቶች ላይ ፊርማውን የማያሰፍር መሆኑን ሕዝባችን እንዲያውቅ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ በዚህም፤ 1. ገዥው ፓርቲ በሀገራዊ ምክክሩ ስም ለማሳካት ከሚፈለግ ማንኛውም ፍላጎትና ሀገርን አስይዞ ከሚደረግ የፖለቲካ ቁማር እንዲታቀብ እናሳስባለን። 2. ተመካካሪዎች ለጊዜያዊ ጥቅምና የፖለቲካ ውሳኔዎች ሽፋን ከመስጠት እና በታሪክ ተወቃሽ ከሚያደርጉ ድርጊቶች በመቆጠብ ለሀገርና ለሕዝብ መቆምን በቀረችው አጭር ጊዜም ቢሆን በድፍረት እንዲያሳዩ በአክብሮት እንጠይቃለን። 3. ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገራዊ ምክክሩ የጥቂት አካላትን ፍላጎት ማስፈጸሚያና ለአዲስ ቁርሾ የሚያዘጋጅ እንዳይሆን ሂደቱን በንቃትና በትኩረት እንዲከታተል እናሳስባለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! እናት ፓርቲ ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በአማራ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ለተከሰሱት ከሦስት መቶ በላይ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ግለሰቦች በይቅርታ እንዲለቀቁ ሂደት ላይ ይገኛሉ። ለሽብር ተከሳሾች የቀረበው የይቅርታ ሰነድ በክልሉ ለተፈፀሙ ግድያዎች እና ጉዳቶች ተከሳሾቹ ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚጠይቅ መሆኑን ቢቢሲ የተመለከተው ሰነድ ያሳያል። ቢቢሲ
የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል‼️ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ዛሬ ጠዋት በተሰነዘረ ጥቃት የ18 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ‼️ በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ዛሬ ጠዋት 12፡00 ላይ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተሰነዘረ ድንገተኛ የከባድ መሳሪያ ጥቃት የ18 ሰዎች ህይወት ማለፉ እና በርካቶች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና የዓይን እማኞች ለአዩዘሀበሻ ገለጹ። እንደ እማኞቹ ገለጻ ዛሬ ማለዳ ላይ የተፈጸመው ይሄው ጥቃት የጉሙዝ እና የፋኖ ሀይሎች በጋራ ወደ ከተማዋ ለመግባት ከፍተኛ ተኩስ በነበረበት ሰዓት ድንገት መናኸሪያ ውስጥ ያረፈ ከባድ መሳሪያ መናኸሪያ ውስጥ ተሰብስበው በነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። በጥቃቱ ሳቢያ የደረሰው የጉዳት መጠን የከፋ መሆኑንና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ዜጎች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። ተጎጂዎቹ በአሁኑ ሰዓት በፓዊ ሆስፒታል ገብተው የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ቢሆንም የታካሚዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በሆስፒታሉ ውስጥ የሕክምና መሣሪያዎችና መድኃኒቶች (የዕቃ) እጥረት ማጋጠሙን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s