tgindex
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍

ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍

Статистика

የቤተ-አምሓራ ነፃ ህዝብ፣ የትግል ልሳን ነን፣ ይከተሉን፣ "ነፃ ሀሳብ ለነፃነት" መርኸ መስመራችን ነው!

Последний пост
17:28
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
94
Всего постов
537
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
11 388
−22 за 3 дн.
Сутки
−3
−0,03%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
520
40 постов
Вовлечённость
4,6%
к подписчикам
Постов в день
13,4
всего 537
Упоминаний
4
каналов
Охват размещения
по 13 постам
1/24сутки в ленте
496
1/48двое суток
568
1/72трое суток
612

Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.

Посты

  • 17:281711

    видео или голосовое, без подписи

  • 17:2817131

    видео или голосовое, без подписи

  • 17:202121

    видео или голосовое, без подписи

  • 17:2021211

    видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • የጉራጌ ዞን ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ለዐምሓራ ብሔር ነዋሪዎች ገሀነም ሆነው ቀጥለዋል‼️ በአብሽጌ ወረዳ በተጨማሪም ዋልጋ ከተማ ና ቦረር ቀበሌ የሚባሉ ቦታዎችም በጣም ችግር አለ አብሶ ቦረር ወጣቱ ወጥቶ መግባት አልቻለም ግማሹም መገደልን በመፍራት እርሻውን ትቶ ወደ ጫካ እየገባ ነው ። የወረዳ አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል አስተዳድር ፀፅታ ኃይል ጋር በመቀናጀት በዚህ አካባቢ የሚገኝ አምሓራ እያፀዱ ነው። ነሐሴ 8/2018 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 @Moamediamoresh

  • አንድ በግልጽ መጤን ያለበት እውነታ እንደነበረ ከላይ መገለፁን አስታውሱ፣ ይሐውም ከ1967—70 አም በነበሩት አመታት የወልቃይት ጠገዴ አካባቢ በተለይም መዘጋ፣ ቃፍትያ፣ አዲረመጥ፣ አርማይጭዎና ሌሎች የስሜን ተራራ ኮረብታማ ወረዳዎችና ዋሻዎች የኢህአፓ (የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ) ሰራዊት ምሽጎች እንደነበሩ ይነገር ነበር። በ1970 አም ህወሐት የኢህአፓን ድርጅት ከአሲምባ ምሽጉ በጦር ሃይል አስገድዶ ሲያስወጣና ድርጅቱ ከውስጥ አንጃዎች፣ ከውጭ ደግሞ የህወሀትና የሻእቢያን ዱላ ለመቋቋም ባለመቻሉ ተፍረክርኮ ሲበታተን አብዛኛዎቹ ወደሱዳንና ወደተለያዩ አገሮች ሲሰደዱ የወልቃይት ጠገዴ ምሽጎቹን ለህወሀት ታጋዮች ለቅቆ መውጣት የግዴታው ስለነበር ይህንን እስትራተጂክ የሱዳን መውጫና መግቢያ በር ህወሀቶች ፈጥነው ለመቆጣጠር እንደበቁ ይታወቃል፣ ኢትዮጵያውያን እስከሆኑ ድረስ ጥያቄና ተቃውሞ አልተሰነዘረባቸውም በዚያን ዘመን። ከዚያን ጊዜ አንስቶ የህወሀት ሰራዊት አባላትና ደጋፊዎች የሁመራንና የአካባቢውን ለም የእርሻ መሬቶች ሁሉ ቀስ በቀስ በተወላጆቻቸው ቋሚ ይዞታ ስር ለመጠቅለል በቅተዋል ማለት ነው፣ በዚህም ሳቢያ የወልቃይት ነባር ተወላጆችን (ወልቃይቶችን) በግድያም ሆነ በማፈናቀል ከገዛመሬታቸው ነቅለው እንዲሰደዱ አደረጓቸው ማለት ነው። በዚህም የተነሳ ዛሬ በአንድ ወገን፣ የወልቃይት ጠገዴ አካባቢ የወልቃይቶች (የአማራ ክልል) ነው፣ ጥንትም ዛሬም፣ በሌላ ወገን ደግሞ የለም የትግራይ ነው ጥንትም ሆነ ዛሬ የሚሉ እርስ በእርስ የሚጣረሱ አቋሞች እየተራገቡ ናቸው። አሳዛኝ ትርክት ነው። ይህ በዚህ እንዳለ ቢሆንም፣ የኢህአፓ ርዝራዦች የነበሩት ጓዶች "ኢህዲን" (በሁዋላ "ብአዴን" ተብሎ የክርስትና ስያሜ በህወሀት ተሰጥቶት) የሚል የህወሀት ተቀጥላ ድርጅት መስርተው እስከዛሬ ለመዝለቅ በቅተዋል። ሆኖም በኢፌዴሪ ህገመንግስት ድንጋጌዎች መሰረት የተከናወኑት የክልሎች አከላለል ሂደቶችና አፈፃፀሞች በሰላማዊ መንገድ የተከናወኑ ሣይሆን በተለያዩ ክልሎች ደምአፋሳሽ ሁኔታዎች ተከስተዋል፣ የሰዎች ህይወት ሳይቀጠፍና የንብረት ውድመት ሳይኖር የተከናወነ የክልል አወሳሰንና አወቃቀር ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም ። ይህ በዚህ እንዳለ፣ ዛሬ የወልቃይቶችንም ሆነ የማንኛውንም ዘውግ ማንነት የሚወስኑት ራሳቸው ማህበረሰቦቹ እንጂ ማንም ሌላ አካል የነርሱን የዘውግ ማንነት እንደቦሎ አይለጥፍላቸውም ፣ እንዲሁም ያለፈቃዳቸውና ያለፍላጎታቸው ወደየትኛውም ክልል እንዲካለሉ መወሰን የማንም ስልጣን አይደለም። ይህንን የመወሰን መብት የራሳቸው የወልቃይቶች የማይገሰስ መብት ነውና። በሌላ አንፃር፣ በኢፌዴሪ ሕገመንግሥቱ አንቀጽ 48 መሠረት፣ "የአከላለል ለውጥ ወይም የክልል ወሰን የመደንገግ ወይም የመለወጥ/የማሻሻል ጥያቄ ከተነሳ ደግሞ ጉዳዩ በማህበረሰቡና በሚመለከታቸው ክልሎች ስምምነት መፈጸም ይኖርበታል። እነዚህ ለመስማማት ካልቻሉ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የህዝብ አሰፋፈርንና ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥ"፣ በሕገመንግሥቱ ተደንግጓል ። የኢፌዴሪ ህገመንግስት ራሱ ደርግን የገረሰሱት የአሸናፊዎቹ የህወሃት ትሪክት እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰፊ ጊዜ ወስዶና በበቂ መረጃ ላይ ተመርኩዞ ያሳለፈውን ስምምነትና ውሳኔ እንዳልነበር በጊዜው የነበርን የቅርብ ተሳታፊዎችና ታዛቢዎች በትክክል የምንመሰክረው እውነታ ነው። ልክ እንደቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነመንግስቱ የ1923 እና የ1948 አም ሁለት ህገመንግስቶችና እንደደርጉ የ1979 አም የኢህዲሪ ህገመንግስት የወያኔ/ኢህአዴግ የ1987 አም የኢፌዴሪ ህገመንግስትም "ለሚወዱትና ለሚወዳቸው የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች"፣ ወድደውና ፈቅደው የሰጡት ስጦታ ነው። በዚህም የተነሳ ሰጪዎቹ ባለፉት 27 አመታት ህገመንግስቱን እንዳሻቸው ሲጥሱ በመቀጠላቸው ሰነዱ የወረቀት ላይ ነፃነት ብቻ ሆኖ ቀርቷል። ለማንኛውም የወልቃይት ጠገዴ፣ የጠለምት፣ የሰቲት ሁመራ፣ አላማጣ ራያ ቆቦ የማንነትም ሆነ የአከላለል ጥያቄ በኢፌዴሪ ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎች ምላሽ የሚያገኝ ውስብስብ ጉዳይ አይደለም፣ በዛሬው ዘመን የትግራይ ነፍጠኛ ወራሪዎችና ጉልበተኞች በ1984 ዓም በጠብመንጃ ሃይል በቅኚነት ተይዞ የቆየ የአማራ ክልል ይዞታ ስለሆነ ያለአንዳች ቅድመሁኔታና ማካካሻ ለአማራ ክልል መንግስት በአስቸኳይ መመለስ የግዴታ ይሆናል፣ የሚመለከታቸው የፌደራልና የሁለቱም ክልሎች የመንግሥት አካላት ኃላፊነታቸውን አሁንም በአግባቡ ለመወጣት በአስቸኳይ መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል። ለወልቃይት ጠገዴም ሆነ ከወሎ ጠቅላይ ግዛት ተቆርሰው የተወሰዱትን የአላማጣ፣ የኮረምና የራያ ቆቦ የአማራ ይዞታ የነበሩትን መሬቶችንም በተመለከተ የፌደራል መንግስት ብዙ ጊዜ ሳይወስድ የማያዳግም የመጨረሻ ውሳኔ ሊሰጠውና የአካባቢው ሰላም እንዲከበር ሊያደርገው ይገባል፣ ይቻላልም። በመጨረሻም፣ የፌዴራል አባላት ክልሎችን ወሰን በተመለከተ በየጊዜው መከለስና ለህዝቦች መስተጋብር በሚያመች ሁኔታ ጂዎግራፊን፣ የኢኮኖሚ አዋጪነት፣ የማህበረሰብ አሰፋፈር ፣ የሚመለከታቸው ወገኖች ፍላጎት፣ የክልሎች እኩልነት ወይም ተመጣጣኝነት፣ ወዘተ መስፈርቶች በመጠቀም ማካለል አዲስ ክስተት አይደለም። ከናይጄሪያ እስከ ህንድ፣ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ካናዳ፣ ከስዊትዘርላንድ እስከአውስትራልያ ያሉት የፌዴራል አገሮች በየጊዜው የአባል ክልሎቻቸውን ወሰኖች ይከልሳሉ፣ ያሻሽላሉ፣ ይለውጣሉ። የኢትዮጵያ መንግስትም የወልቃይት ጠገዴ፣ የሰቲት ሁመራ፣ የጠለምትን፣ የአላማጣ ራያ ቆቦንም ሆነ ሌሎች የፌደራል ክልሎችን በተመለከተ በየጊዜው የሚነሱትን ጥያቄዎች እየመረመረና እያስጠና በተመሳሳይ አካሄድ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲቋጩ ማድረግ ይኖርበታል። በነዚህ አይነት የማንነትና የአከላለል ጥያቄዎች የተነሳ አስፈለጊና ተገቢ ያልሆኑ የህዝብ ለህዝብ ግጭቶች ደም—አፋሳሽና ንብረት አውዳሚ ክስተቶችን ማስከተል በፍፁም አይኖርባቸውም። ከዚህ ውጭ በማወቅም ሆነ ከግንዛቤ እጦት በመነጨ አጉል እንቅስቃሴ የሁለቱን ክልሎች ወንድማማች ህዝቦች ወደግጭትና ወደጠላትነት የሚያስገባ እንቅስቃሴ ሁሉ በአስቸኳይ እንዲቋረጥ አጥብቀን እንጠይቃለን። በዚህ ረገድ የሚደረገው አሉታዊ እንቅስቃሴ ወይም ሴራ ሁሉ በፅኑ መወገዝ አለበት፣ የህዝብ እውነት ምንጊዜም አሸናፊ ነው። እግዚአብሄር ሰላማዊ አብሮነታችን፣ የእርስ በእርስ መተጋገዛችንና ወንድማማችነታችንን ለዘለዓለም ይጠብቅልን @Dilbato Digoye ነሐሴ 8/2018 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 @Moamediamoresh

ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍ — tgindex