tgindex
Ethio 251 Media

Ethio 251 Media

Статистика
@ethio251mediaПолитикаанглийский

ETHIO 251 is an independent media offering you News, Political Analysis and Information feeds. መረጃ ለማድረስ :- @Ethio251MediaInfo

Последний пост
16:04
Последнее чтение
16:14
Постов за неделю
41
Всего постов
60
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Политика
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
41 148
−58 за 4 дн.
Сутки
−15
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
6 020
40 постов
Вовлечённость
14,6%
к подписчикам
Постов в день
5,9
всего 60
Упоминаний
4
каналов
Охват размещения
по 4 постам
1/24сутки в ленте
5 401
1/48двое суток
6 189
1/72трое суток
6 675

Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.

Посты

  • 16:041 58182

    ላለፉት ስምንት ዓመታት የሕዝብ አይንና ጆሮ ሆኖ ሲያገለግል የቆየው መረጃ ቲቪ በዘላቂነት ለማስቀጠል የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ተዘጋጅቷል። የበርካታ ሚዲያዎች የስርጭት መድረክ በሆነው መረጃ ቲቪ የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ በመገኘት በሚዲያው ዘርፍ የሚደረገውን ትግል ይደግፉ። August 22&23 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 2:00 ጀምሮ https://mereja.tv/main/

  • 11:593 360531

    ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ የተላለፈ የስልጠና ጥሪ!! ! "እምቢ ለሕልውናዬ! እምቢ ለነፃነቴ"! የአማራ ሕዝብ የሕልውናና የነፃነት ትግል በጀግኖች የአማራ ፋኖ አርበኞች በሚያደርጉት መራራ ተጋድሎ አሁን ላይ የመጨረሻውና ወሳኙ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ፀረ አማራውና ሀገር አውዳሚው የብልፅግና አገዛዝ በየግንባሩ በደረሰበት ከባድ ወታደራዊ ሽንፈት ምክኒያት የመቃብር አፋፍ ላይ ቆሞ የመጨረሻ ጣዕረ ሞቱን እያሰማ ይገኛል። ይህ ተጋድሎ፡ የአማራን ሕዝብ በጅምላ እየጨፈጨፈ፣ በጅምላ እያፈናቀለና እያሳደደ የሚገኘውን ከዚህ አልፎ አገሪቱን በጦርነት እያመሰ ወደ አዘቅት እያምዘገዘጋት የሚገኘውን የብልፅግና አገዛዝ ገርሶ፡  የአማራን ሕዝብ ሕልውና ማስከበርና የፍትሕ ርትዕ ማስፈን፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሰላም ወጥቶ በሰላም የሚገባበትና በየትኛውም የሀገሪቱ አከባቢ በነፃነት ተንቀሳቅሶ ሀብት ንብረት የሚያፈራበትን፣ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በእኩል አይን የሚታዩበትን፣ ተማሪዎች ተምረው ስራ ይዘው ሀገር የሚያገለግሉበትን፣ ድሃ የማይበደልበትን ፍትህ የማይጓደልበትን መንግስት ለመመስረት የሚደረግ ታሪካዊ ትግል ነው። ስለሆነም፦ ➛ ይህ ትግል የጥቂቶች ሳይሆን የመላው የአማራ ሕዝብ የጋራ እጣ ፈንታ በመሆኑ፡ ነገ ነፃ በምትወጣዉ ሀገርና በሚገነባው ፍትሐዊ አገዛዝ ስርዓት ላይ "እኔም ዋጋ ከፍዬበታለሁ፡ የኔም ድል ነው" ብሎ በኩራት ለመቆም ➛ ነፃ በወጡና ወደፊት ነፃ በሚወጡ ቀጠናዎች የሕዝባችንን ሰላም፣ ሕግና ፍትሕ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስከበር ➛ አገዛዙ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኖ ለጉልበት ሥራ፣ ለትምህርትና ለገበያ የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችን አፍኖ ለጦርነት የሚማግድበትን እኩይ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ለመግታትና ወጣቱን ከአጋች ኃይሎች ለመጠበቅ እድሜያችሁ ለትግል የደረሰ የወሎ ቤተ-አማራ ወጣቶችና የመላው አማራ ልጆች በሙሉ፡ በምኒልክ ዕዝ ስር በሚገኙ በሁሉም ቀጠናዎች በፍጥነት በመመዝገብ የታሪክ አሻራችሁን እንድታስቀምጡ የክተት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ መታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑኑን እናሳውቃለን። ꕺ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥሩ ስነምግባር የሚታወቅ/የምትታወቅ ꕺ በክልሉ ውስጥና ውጭ ከሚገኙ ከየትኛውም ቀበሌዎች መታወቂያ ማቅረብ የሚችል/የምትችል ꕺ ከማንኛውም ደባል ሱሶች ነፃ የሆነ/የሆነች ꕺ ሙሉ የአካልና የአዕምሮ ጤነኛ የሆነ/የሆነች ꕺ ከማንኛውም ወንጀል ነፃ የሆነ/የሆነች ꕺ በአማራነቱ የሚኮራና የአማራን ሕልውናና ነፃነት ለማስከበር ሙሉ ቁርጠኝነት ያለው/ያላት ማሳሰቢያ፦ ስትመጡ መታወቂያችሁን በሁለቱም በኩል ኮፒ አስደርጋችሁ መያዝ ይጠበቅባችኋል ::      ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!   የጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ነሃሴ 10/2018ዓ.ም

  • 15 авг.5 0795

    видео или голосовое, без подписи

  • 15 авг.5 046765

    "በአዲስ አበባ ከተማ እና ነዋሪወቿ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋ በድርጅታችን ቁርጠኝነት፣ በህዝባችን ፅናትና በፀረ ብልፅግና ብሔራዊ ኃይሎች ትብብር በሚታጀበው የትግላችን አይቀሬ ድል የሚመመከት ይሆናል" ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ ! ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም ዘረ ፈጁ የብልፅግና አገዛዝ ''አገራዊ ምክክር'' በሚል ስም በኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚያካሂደው የድራማ መድረክ የህዝብ ውክልና የሌለበት፣ ተጨማሪ ቀውስ የሚያዋልድ እና የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም የተነደፈ የአረመኔው አገዛዝ የፖለቲካ አሻጥር መሆኑን ከዚህ በፊት ባወጣነው መግለጫ አቋም መውሰዳችን ይታወቃል። ሆኖም ግን አገዛዙና አጋሮቹ ይህንን ከጥፋት መንገዳቸው እንዲመለሱ ያቀረብንላቸውን ጥሪ በመተው ''በምክክር'' ስም የከተሞችንና አካባቢዎቻቸውን የታሪክ፣ የዴሞግራፊ፣ መልክአምድራዊና የይዞታ ቅርፃቸውን ለማዛባትና በተለይም ነባር የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪዎችንና የአማራን ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የጥፋት መንገድ ላይ መሆናቸውን ተገንዝበናል። አዲስ አበባ ከተማ እንደገና ከመቆርቆሯና ከአሁኑ መጠሪያዋ ቀደም ብሎ ''በራራ'' በመባል የምትታወቅ፣ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን በጦርነት ሳቢያ እስከወደመችበት ጊዜ ድረስ የአማራ ነገስታት መቀመጫና የአማራ ህዝብ ጥንተ-ርስት እንደሆነች የታሪክ መዛግብትና አርኪዮሎጂያዊ ማስረጃዎች በግልፅ ያረጋግጣሉ። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል አዲስ አበባ ከተማን በድጋሚ ሲቆረቁሯት፣ ባዶ መሬት ላይ ሳይሆን የአባቶቻቸውን ታሪካዊ ይዞታ፣ ርስትና ውርስ መነሻ በማድረግ ነው። ይህ ታሪካዊ እውነት ሊሸረሸርም ሆነ ማንም አምባገነናዊ አገዛዝ በጊዜያዊ ስልጣን ህዝብ ባላመነበት ፖለቲካዊ ውሳኔ ሊሰርዘው የማይችለው ፅኑ የታሪካችን አንድ አካል ነው። ከተማዋ የአማራ ጥንተ-ርስት መሆኗ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሂደት የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ መኖሪያ፣ የባህልና የኢኮኖሚ ማዕከል፣ እንዲሁም የአንድነት ተምሳሌት ሆና ተገንብታለች። ከዚህ አኳያ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) አዲስ አበባ የኗዋሪዎቿ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መኖሪያ፣ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ መናገሻና የዓለም አገራት የዲፕሎማሲ ማዕክል መሆኗን ሙሉ በሙሉ ያምናል፤ ይቀበላልም። በዚህ መነሻ፣ ከተማዋ የብዝኃነትና የጋራ እድገት ማዕከል እንጂ የአንድ ዘረ ፈጅ አገዛዝ ብቸኛ መጫወቻ ስፍራ ልትሆን እንደማትችልም ድርጅታችን ያረጋግጣል። የአማራ ህዝብ፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ አገሪቱ በስፋት በሚኖርባቸው አካባቢዎች፤ ፍትሐዊ የስልጣንና የሀብት ተጠቃሚነቱ መረጋገጥ እንዳለበት ድርጅታችን ያምናል። በአሁኑ ወቅት፣ የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ አዲስ አበባን በብቸኝነት የአንድ ወገንና ብሔር በበላይነት እንዲቆጣጠራት ለማስቻል የሚሰራው ሕግን የጣሰ፣ የዴሞግራፊና የጂኦግራፊ ለውጥ በምንም መልኩ ሕጋዊ፣ ሞራላዊ፣ ፖለቲካዊና ታሪካዊ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልፃለን። አገዛዙ ''አገራዊ ምክክር'' በሚል የፖለቲካ ሽፋን በከተማዋ ላይ የሚያካሄደው ሴራና አሻጥር የከተማዋን ነባር ኗዋሪዎች መብት የሚጥስ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ መኖሪያነቷን የሚክድና ታሪካዊ እውነታውን ለማዛባት የተሸረበና የአንድ ቡድን የበላይነትን በህዝባችን ላይ በኃይል ለመጫን ያለመ በመሆኑ፣ የዚህን አምባገነን አገዛዝ ዕድሜ ለማሳጠር መላው የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪዎችን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን እንዲያወግዙት፣ እንዲቃወሙትና እንዲታገሉት በድርጅታችን አፋብን ስም ጥሪ እናቀርባለን። እንዲሁም በከተማዋ ቀደም ብለው ይኖሩ የነበሩትም ይሁን አሁንም የሚኖሩት 80 በመቶ ( በ1999 ዓ.ም በተካሄደው ህዝብና ቤት ቆጠራ መሰረት) የሚሆኑት ነባር ኗዋሪዎች አማራዎች ናቸው። በመሆኑም የህዝብ ስብጥርንም ሆነ ታሪካዊ እውነታን በኃይልና በተሳሳተ ፖለቲካዊ ውሳኔ ለመቀየር የሚደረገውን ማንኛውም የአገዛዙን ሴራ አጥብቀን የምንታገለው መሆኑን እንገልፃለን። የአማራ ህዝብ በገዛ አገሩ ከገጠመው ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ ባሻገር ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የትጥቅ ትግል ውስጥ ለመግባት ካስገደዱት ምክንያቶች መካከል፦ በአዲስ አበባ ከተማ በአገዛዙ የተደቀነው የዴሞግራፊ ለውጥ አደጋ፣ የከተማዋን ቀደምት ባለቤቶችና ነባር ኗዋሪዎች በማፈናቀልና ማንነታቸውን በማጥፋት፣ የአማራ ህዝብ ከከተማዋ ጋር ያለውን ታሪካዊ እና ማህበራዊ ትስስር በመበጣጠስ ከህዝቦች ተፈጥሯዊ መስተጋብር ውጭ በሆነ መልኩ የባህል፣ የቋንቋና የተለያዩ አመለካከቶችን በኃይል ለመጫን የሚደረገው ሩጫ ይገኝበታል። በመሆኑም፣ ድርጅታችን አፋብን ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ውስጣዊ አንድነቱንና አደረጃጀቱን ጠብቆ በመጓዝ፣ አምባገነኑና ከፋፋዩን አገዛዝ በጀመርነው ትግል ከስሩ ነቅለን በመጣል፣ ለአማራ ህዝብ ብሎም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚስማማ፣ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚያከብር ሥርዓተ መንግስት በመገንባት ፍትህ፣ እኩልነትና የሕግ የበላይነትን ከመትከል ባሻገር አዲስ አበባ የኗዋሪዎቿ፤ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ መኖሪያና ዋና ከተማ፤ የአንድነትና የእድገት ማዕከል ሆና እንድትቀጥል ይታገላል። አገሪቱ ከገባችበት ጥልቅ የህልውና፣ የፍትህና የእኩልነት ቀውስ መውጣት የምትችለው የህዝቧን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በኃይል በማፈን፣ አገሪቱን የማያቋርጥ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በማስገባት ወደ ገደል እየመራት ያለውን ዘረ ፈጁን የብልፅግና አገዛዝ፤ በሕዝባዊ ትግል ሙሉ በሙሉ መገርሰስ ሲቻል ብቻ መሆኑን አፋብን በፅኑ ያምናል። በስተመጨረሻ የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ በአዲስ አበባ ከተማና በህዝባችን ላይ በምክክር ስም የጠነሰሰው ዓይን ያወጣ የፖለቲካ አሻጥር የፈጠረው የህልውና በድርጅታችን ቁርጠኝነት፣ በህዝባችን ፅናትና በፀረ ብልፅግና ብሔራዊ ኃይሎች ትብብር በሚታጀበው የትግላችን አይቀሬ ድል የሚመመከት ይሆናል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)

  • 15 авг.5 724561

    የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)--ወታደራዊ የግንባር አውደ-ውሎ እና የህዝብ አደረጃጀት መረጃዎች፦ ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም። ​፩. የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ሰራዊት በጎንደር ግንባር የፈጸመው አመርቂ ድል፦ ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ስር የሚገኙት ዞብል፣ ጃኖ እና በጌምድር ክፍለ ጦሮች ባካሄዱት የተቀናጀ ኦፕሬሽን በጠላት የሰው ኃይል እና ወታደራዊ ቁሳቁስ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አደረሱ። ​መዳረሻውን ጨውድባ አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው እና በህዝብ ላይ በደል ሲፈጽም የቆየው የጠላት ኃይል፤ ይዞታውን ለማስፋት በማሰብ ከምዕራብ ደንቢያ ጫዊት፣ ከደልጊ ጣቁሳ ወረዳ፣ ከጭልጋ ከተማ እና ከጫንድባ ያደረገው እንቅስቃሴ በሁለቱ ክፍለ ጦሮች የተቀናጀ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ “ጫንድባ አምባተራራ” ላይ ከፍተኛ ምት አርፎበታል። ​በጫንድባ አምባተራራ የደረሰበትን የከፋ ምት መቋቋም የተሳነው የጠላት ስብስብ በሌላኛው አውደ ውጊያ በኳክ አቅጣጫ ተጨማሪ የማጥቃት ሙከራ ለማድረግ ቢሞክርም፣ በክፍለ ጦሮቹ በተናበበና በተደራጀ አፀፋዊ ምት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል። ​፪. የፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት አባላት እየፈረሱ ፋኖን እየተቀላቀሉ ነው። ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ጠቅላይ ግዛት ሚኒሊክ ዕዝ 101ኛ ኮርን የጠላት አገዛዝ ሠራዊት አባላት እየፈረሱ በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ። ​በዚህም መሰረት፡- ✔️የ47ኛ ክፍለ ጦር አምስተኛ ሻለቃ አባል አንድ ጥቁር ክላሽ ከ200 የክላሽ ተተኳሽ ጋር፣ ✔️የ45ኛ ክፍለ ጦር አምስተኛ ሻለቃ ሁለት አባላት ሁለት ጥቁር ክላሽ፣ 240 የክላሽ ተተኳሽ እና አምስት F1 ቦንቦች፣ ✔️የ46ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ሻለቃ የሻለቃ አመራሩ አጃቢ 110 የክላሽ ተተኳሽ፣ አንድ ጥቁር ክላሽ እና የሻለቃውን የመገናኛ ሬድዮ በመያዝ 11ኛ እና 15ኛ ክፍለ ጦሮችን ተቀላቅለዋል። ​በአጠቃላይ ከ45ኛ፣ 47ኛ እና 46ኛ ክፍለ ጦሮች አፋብን ወሎ ጠቅላይ ግዛት ሚኒሊክ ዕዝ 101ኛ ኮርን፡- • ​4 ጥቋቁር ክላሾች • ​550 የክላሽ ተተኳሾች • ​5 የF1 ቦንቦች • ​1 የመገናኛ ሬድዮ ይዘው መቀላቀላቸውን የ101ኛ ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል። ​፫. በሰሜን ወሎ ዞን የመቄት ወረዳ ጊዜያዊ ሕዝብ አስተዳደር ተዋቀረ ​የአማራ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እና አስተዳደራዊ ፍትሕ ለማስፈን በሚደረገው ፖለቲካዊ የትጥቅ ትግል መዋቅራዊ ስራዎችን ማጠናከር ተችሏል። በዚህም መሰረት በአፋብን ወሎ ጠቅላይ ግዛት ምኒልክ ዕዝ እና በሰቆጣ/መቄት አደረጃጀት ኃላፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎ የመቄት ወረዳ ጊዜያዊ ሕዝብ አስተዳደር የሚከተለው መዋቅር ተዘርግቷል፦ ~1ኛ. ዋና አስተዳዳሪ፡ 50/አ መንግስቱ ካሳ ~2ኛ. ም/አስተዳዳሪ፡ ምስጋን ዘውዱ ~3ኛ. የፖለቲካ ጉዳዮች መምሪያ፡ ኢ/ር አበባው ተስፋው ~4ኛ. ሰላምና ደህንነት መምሪያ፡ 100/አ በጊዜው ታደሰ ~5ኛ. ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ፡ ሳሙኤል አያሌው ~6ኛ. ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ፡ አንተነህ አምሳሉ ~7ኛ. መረጃና ደህንነት መምሪያ፡ ኮስትር (እሚያምረው) ~8ኛ. ፋይናንስ መምሪያ፡ ውበት እባቡ ~9ኛ. ሎጅስቲክስ መምሪያ፡ አለበል መኩሪያው ~10ኛ. ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ፡ ጌታሁን ቢሰጥ ~11ኛ. ም/ሎጅስቲክስ መምሪያ፡ ንጋት ሙጨ ~12ኛ. ም/ሰላምና ደህንነት መምሪያ፡ ቢራራ ፀጋነው ~13ኛ. ሕግ መምሪያ ዋና ዳኛ፡ መንግስቱ ያለው ~14ኛ. ሕግ ክፍል ጸሐፊ፡ መርሻ መልካም ~15ኛ. ሕግ ክፍል አባል፡ አዳነ መንግስቴ ~16ኛ. ሕግ ክፍል ገንዘብና መዝገብ ያዥ፡ ዮርዳኖስ ጫኔ ~17ኛ. ሴቶች ጉዳይ መምሪያ፡ ማህሌት አስናቀ ​የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል...... ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የወታደራዊ ቃል አቀባይ

  • 15 авг.5 775453

    ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ዞብል ጃኖ እና በጌምድር ክፍለ ጦሮች ባካሄዱት የተቀናጀ ኦፕሬሽን በጠላት የሰው ኃይል እና ወታደራዊ ቁሳቁስ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አደረሱ። መዳረሻውን ጨውድባ አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው እና በህዝብ ላይ በደል ሲፈጽም የቆየው የጠላት ኃይል፣ ይዞታውን ለማስፋት በማሰብ ከምዕራብ ደንቢያ ጫዊት ፣ ከደልጊ ጣቁሳ ወረዳ ፣ ከጭልጋ ከተማ እና ጫንድባ ደረገው እንቅስቃሴ በሁለቱ ክፍለ ጦሮች የተቀናጀ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ “ጫንድባ አምባተራራ” ላይ ከፍተኛ ምት አርፎበታል። ​ በጫንድባ አምባተራራ የደረሰበትን የከፋ ምት መቋቋም የተሳነው የጠላት ስብስብ በሌላኛው አውደ ውጊያ በኳክ አቅጣጫ ተጨማሪ የማጥቃት ሙከራ ለማድረግ ቢሞክርም ፣ በክፍለ ጦሮቹ በተናበበና በተደራጀ አፀፋዊ ምት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

  • 14 авг.6 7163

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.6 4493

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.5 855473

    የአውሮፓ ህብረት (EU) በኢትዮጵያ ያለውን አጠቃላይ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እክል እና የሽግግር ፍትሕ ሁኔታዎችን በጥብቅ እንዳሳሰበው ገለጸ! (ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም — ኢትዮ 251 ሚዲያ) የአውሮፓ ህብረት (EU) እ.ኤ.አ በ2025 በዓለም ዙሪያ የነበረውን የሰብዓዊ መብቶች እና ዲሞክራሲ ሁኔታ አስመልክቶ ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ሪፖርቱ፣ በኢትዮጵያ ያለውን አጠቃላይ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ የእርዳታ አቅርቦት እክል እና የተጠያቂነት ሁኔታዎችን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል። በሪፖርቱ መሠረት፣ እ.ኤ.አ በ2025 በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚካሄዱት ግጭቶች የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ሕግ (IHL) ጥሰቶች እንዲባባሱ ማድረጋቸውንና የሰብዓዊ ሁኔታው አሁንም እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ፣ የተከሰቱት ግጭቶች የተቸገሩ ማኅበረሰቦች ዘንድ ደርሶ አስፈላጊውን እርዳታ ለማቅረብ የሚደረገውን ጥረት አደናቅፈውታል። በዚሁ ዓመት ውስጥ ከ90 በላይ የእርዳታ ሰራተኞች ታግተው የተወሰዱ ሲሆን፣ አብዛኞቹ እገታዎች የተፈጸሙት በአማራ ክልል እንደሆነና ከእነዚህም መካከል ቢያንስ የአንድ እርዳታ ሰራተኛ ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል። የአውሮፓ ህብረት የሀገሪቱን አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እና የጥበቃ ፍላጎቶች ለማሟላት ወደ 80 ሚሊዮን ዩሮ የሚጠጋ በጀት መመደቡንም አስታውቋል። በሌላ በኩል፣ በመስከረም 2025 በተካሄደው 60ኛው የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት (HRC60) ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ህብረት በ42 ሀገራት የተፈረመ የጋራ መግለጫ ያቀረበ ሲሆን፣ በመግለጫውም በኢትዮጵያ ባለው የሰብዓዊ መብቶች እና የሽግግር ፍትሕ ሂደት ላይ ያለውን ጥልቅ ስጋት መግለጹን አስታውሷል። የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኛም በተጠያቂነት እና በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካላት፣ ከቀጠናዊ ድርጅቶች እና ከሲቪል ማኅበራት ጋር ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸው ተጠቅሷል። ኢትዮ 251 ሚዲያ የነጻነት አንደበት!

  • 14 авг.6 472471

    *ኑ አዲስ ዓመትን በልዩ ድምቀት በጋራ እናክብር!* ሰላም ውድ የአማራ ወገኖች፣ የአማራ ደጋፊዎች እና ውድ ኢትዮጵያውያን! አዲሱን ዓመት በፍቅር፣ በአንድነትና በኢትዮጵያዊ ባህላችን ድምቀት አብረን ለማክበር ልዩ የአዲስ ዓመት የባህል ፕሮግራም ተዘጋጅቷል! ቀን 📅 ቅዳሜ፣ 26 September 2026 ሰዓት🕐 1:00 PM – 10:00 PM ቦታ📍 Manner House Station, N4 1QJ በዝግጅቱ ባህላዊ ምግቦች፣ የቡና ሥነ-ሥርዓት፣ ባህላዊ ዳንስና ሙዚቃ በዲጄ እና ለቤተሰብ የተዘጋጁ ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ። 🎟️ መግቢያ: ግለሰብ £25 | ቤተሰብ £40 | VIP £50 ገቢው ለተፈናቀሉና በጦርነት ለተጎዱ ወገኖቻችን ይውላል። ከቤተሰብዎና ከወዳጅዎ ጋር ይምጡ፤ በጋራ ደምቀን ባህላችንን እናክብር፣ ወገናችንን እንደግፍ፣ አንድነታችንን እናጠናክር! 📞 ለተጨማሪ መረጃ፦ +44 7391146910/+447984 109189

  • 14 авг.6 097533

    የአፋብን 1ኛ ዕዝ 14ኛ ኮር ለተከታታይ ቀናት ሲያደርግ የቆየውን ጥልቅ ግምገማ በስኬት በማጠናቀቅ፣ ድርጅታዊና ወታደራዊ ተልኮን ለማስፈፀም ብቁ ናቸው ያላቸውን አመራሮች ያደራጀ ሲሆን በግምገማው የኮሩና በስሩ ያሉ ክ/ጦር አመራሮች በንቃት ተሳትፈዋል። ይህ አደረጃጀት በየደረጃው ያሉ አርበኞችን አፈፃፀምና ብቃት መሠረት በማድረግ የተከናወነ ሲሆን፣ የኮሩን የወደፊት ድርጅታዊና ወታደራዊ ተልዕኮዎች በተሻለ ቁመና ለማስፈጸም ያለመ ነው። በዚህም የግምገማ ፕሮግራም የአፋብን አመራሮች፣የ1ኛ እዝ አመራሮች በመገኘት ጥልቅ ግምገማ በማድረግ የስራን ልምድና የስራ አፈፃፀም ጥንካሬን እንድሁም የአመራር ጥበብና ብቃትን ከግምት ውስጥ በማስገባት የኮሩን አመራር አደረጃጀት ሰርተዋል። ወደ ኮሩ የተመደቡ አመራሮችም ትግሉን የማስቀጠል ታሪካዊ አደራ ከትግሉ ሰምዓት ስላለብና የህዝባችን መከራ ለማሳጠር ቆርጠን ለመታገልና ለማታገል ቃለ-መሀላ በመፈፀም አጠናቀዋል። ​📌 አዲስ የተመደቡ የ14ኛ ኮር አመራሮች ዝርዝር 1, አርበኛ ሰለሞን አሊ.. የ14ኛ ኮር ሰብሳቢ 2, አርበኛ እንዳሻው ጌታሁን ..ወታደራዊ አዛዥ 3, አርበኛ መሀመድ አሊ.. ም/ወታደራዊ አዛዥ 4,አርበኛ ዳኒኤል ዋጋው ..ወ/አስተዳደር ሀላፊ 5 አርበኛ ሱልጣን የሱፍ ..ፓለቲካመምሪያ ሀላፊ 6, አርበኛ ሲሳይ አድሱ ..ሎጀስቲክ መምሪያ 7,አርበኛ ሞላ አባተ ..ዘመቻ መምሪያ 8,አርበኛ ጌታቸው ማሩ ..ም/ዘመቻ መምሪያ 9, አርበኛ አማረ አባተ ..ም/ዘመቻ መምሪያ 10, አርበኛ ጌትነት አለሙ...ስልጠና መምሪያ 11, አርበኛ አበራ ከበደ ም/ስልጠና 12, አርበኛ ኡመር ምሰው...ም/ስልጠና 13, አርበኛ ገረመው አልታሰብ ም/ወታደራዊ አስተዳደር 14, አርበኛ ተስፋየ ገዱ ...መሀንድስ 15, አርበኛ ----------መረጃና ደህንነት 16, አርበኛ-------------ም/መረጃና ደህንነት 17, አርበኛ አስናቀው ገብሬ ...ቃኝ መሪ 18, አርበኛ እድገት አያሌው .... መገናኛ 19, አርበኛ አብርሀም ይሁኔ....ም/መገናኛ 20, አርበኛ ቢያመሽ መኮነን ....የሰው ሀይል 21, አርበኛ --------------.....ም/የሰውሀይል 22, አርበኛ ኑሩ መኮነን .....ፋይናስ 23, አርበኛ አማን አደራው ....ሂሳብ ሹም 24, ህግ አገልግሎት 1,አርበኛ መቶ አለቃ አያሌው አበበ 2,አርበኛ እያሱ ፋንታው 3,አርበኛ ሰለሞን ተገኘ 25, መቶ አለቃ ከተማው ....ወታደራዊ ፖሊስ 26, አርበኛ ሰለሞን አማረ ....ግዥ 27, አርበኛ ኢብራሂም አሊ ....ም/ሎጀስቲክ 28, አርበኛ አሰፋ አባተ....ስንቅና እደላ 29, አርበኛ ሙሀመድ ፋንታው ....ኦርድናስ 30, አርበኛ መካሻው ደምሴ ....ም/ኦርድናስ 31, አርበኛ ደሳለኝ እጅጉ .....ስቶር 32, ዶ/ር ዘላለም አዳነ....ጤና መምሪ 33, ዶር እሸቱ ሀይሌ ......ም/ጤና መምሪያ 34, አርበኛ ገ/መሰቀል ካሳው....ነዘቅ 35, አርበኛ አባተ አለሙ.....ትራንስፖርት 36, አርበኛ ይመር ሀይሌ....ቃል አቀባይ 37, አርበኛ መላኩ መስፍን ...ኢንደክትሪኔሽን(ስርፀት) 38, አርበኛ በለጠ ተፈራ ሚኒ-ሚድያ ክፍል 39, አርበኛ ሰለሞን ሞላ ...ኢንስፔክሽን(ወታደራዊ ተቋም ቁጥጥርና ክትትል 40, አርበኛ -------- ኦድትና ቁጥጥር 41, አርበኛ አስፋው አበበ ....የኮር ፀሀፊ በማድረግ አደረጃጀቱ በተሳካ ሁኔታ ተከናዉኗል!! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !! አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ!! ነሀሴ08/12/2018 ዓ.ም

  • видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.5 49112
  • 14 авг.6 208311

    በደቡብ ወሎ ዞን ጉሽ ሜዳ ቀበሌ ህዝባዊ ዉይይት ተካሄደ! ​ በጉሽ ሜዳ ቀበሌ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በተገኘበት አጠቃላይ ህዝባዊ ስብሰባ በዛሬዉ ዕለት ማለትም ነሃሴ 8/2018 ዓ.ም የምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል። ​በዚህ አበይት ህዝባዊ መድረክ ላይ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ምክትል ኃላፊ፣ የህዝብ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የ11ኛ ኮር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ጨምሮ የሲቪል መዋቅር አመራሮች ተገኝተው ከህዝቡ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በዕለቱ የተደረገውን ስብሰባ በተመለከተ እንደተገለጸው፣ የህዝቡ አቀራረብና ተሳትፎ እጅግ ከፍተኛ እና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቃ ሁኔታ ተሳትፈዋል። ​በውይይቱ ወቅት የህዝቡን ስሜትና አቋም ያንጸባረቁ አንድ የአካባቢው አባት እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል የነበረውን ሁኔታ በማስታወስ «እስካሁን ድረስ በእንደዚህ አይነት መንገድ ግንዛቤ ተፈጥሮልን አናውቅም» በማለት የተጀመረው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ህዝቡ ሁልጊዜም ከፋኖ ጎን እንደሚቆም ገልጸዋል። ቀደም ሲል የነበረው አሰራር የተበታተነ እንደነበር በማስታወስ፣ የአሁኑ የፋኖ መዋቅር፣ የተስተካከለ የመሪነት ቁመና እና ፖለቲካውን በቅጡና በወርዱ የተረዳ አመራር ያለው መሆኑን በመጥቀስ «ድርጅታችን አፋብን መድኃኒታችን እና መዳኛችን ነው» ሲሉ አደንቀዋል። ​ ሰራዊቱ አሁንም ከማህበረሰቡ ጋር ያለዉን ጥሩ ዲሲፕሊን አሁንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል። ​በመጨረሻም ህዝቡ በሎጂስቲክስም ሆነ በሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ከሰራዊቱ ጎን በመቆም አብሮ ለመሰለፍ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ!! ነሀሴ :- 08/ 2018 ዓ/ም

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.6 27366

    ሁለት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት 64ኛ ክ/ጦር ተቀላቀሉ!! 1ኛ.አቡሌ ኩምሳ 4ኛ ክ/ጦር አንድ ጥቁር ክላሽ 150 ጥይት ከወገብ ትጥቅ 2 ቦንብ 2ኛ. ዳመን ቸርነት ፖራ ኮማንዶ እስኬስ መሳሪያ በመያዝ ሸበል በረንታ መረገጭ ንዑስ ከተማ እና እነማይ ወይራ ጠልማ ቀበሌ የአገዛዙን ብልሹ አሰራር ተስፋ በመቁረጥ ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!! ሀምሌ 07/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት

  • 13 авг.6 321521

    ሰበር ዜና! በራያ ግንባር በግዳጅ ላይ የሚገኙት የጠላት ብልፅግና ሰራዊት ከስምሪት ቀጠና በመጥፋት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮርን ተቀላቀሉ። ዛሬ ነሐሴ 07/2018ዓ/ም በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የጠላት የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 1ኛ ኮር 45ኛ ክፍለጦር 4ኛ ሻምበል አዛዥ እና የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 802ኛ ኮር 49ኛ ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ 2ኛ ሻምበል አባል ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ የ102ኛ ኮርን ተቀላቀሉ። ከተቀላቀሉት የጠላት የሰራዊት አባላት ሀምሳ አለቃ ጫላ ተኩ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 1ኛ ኮር 45ኛ ክፍለጦር 1ኛ ሬጅመንት 4ኛ ሻበል አዛዥ እና ሙሉጌታ አሰፋው ጡሩነህ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 802ኛ ኮር 49ኛ ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ 2ኛ ሻምበል አባል ትናንትና አመሻሹን የ102ኛ ኮር ፋኖን ተቀላቀሉ። ወደ ፋኖ ከመጡት የብልፅግና የሰራዊት አባላት መካከል 2 ጥቁር ክላንሽ ኮፍ መመሳሪያ፣ 400 የክላሽ ጥይት 4 ኤፍ ዋን ቦምብ እና 6 የክላሽን ኮፍ ካዝና በመያዝ ተቀላቅለዋል። በተጨማሪም ሌሎች የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 802ኛ ኮር 48ኛ ክፍለጦር የ6ኛ ሻለቃ ሁለት የሰራዊት አባል ሻምበል ታከለ ዋጋው እና ታምራት ዳባ ደበሌ አገዛዙን በመክዳት በጀሌ(ያለመሳሪያ) የ102ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል። ሰሞኑን ከራያ ግንባር እስከ ወልድያ፣ ደሴና ኮምቦልቻ ድረስ ከባድ ውጥረት መንገሱን ተከትሎ በየቀኑ ቢያንስ ከ30 በላይ የሚሆኑ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በራያ ግንባር ከስምሪት ቀጠናቸው እየወጡ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሠራዊቱ "በማን ደም፡ የማን ስልጣን ሊፀና" በሚል ከጥርናፌው በመውጣት እየጠፋ ሲሆን፡ ከፍተኛ አዛዦች እነ ጀኔራል አሰፋ ቸኮልን ጨምሮ የፈረሰውን ጦር እንደገና ለማስተሳሰር እየሞከሩ ቢሆንም ነገር ግን ዛሬ ያስተሳሰሩት ነገ ፈርሶ እያደረባቸው የሚይዙት የሚጨብጡትን እንዳጡ የውስጥ መረጃዎች ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! "ክብር ለትግሉ ሰማዕታት" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ወሎ(ቤተ-አማራ) ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም

  • 13 авг.5 6341

    видео или голосовое, без подписи