Mulugeta Anberber
Статистикаለፈጣን መረጃ እንዲሁም ለዕለታዊ ክንውኖች ወዳጅ ይሁኑ! መረጃ ለመላክ @Mulugetaanberber1
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 9
- Всего постов
- 32
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2 961
- 1/48двое суток
- 3 393
- 1/72трое суток
- 3 659
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
❗️❗️የአብይ አህመድ ጉድ ወጣ❗️❗️ የአብይ ትክክለኛ ማንነት እና አቅዶቹ ለአመታት ጥያቄ ሆነው የቀሩ ማንነቶቹ ይፋ ወጥተዋል ከታች ያለውን ሊንክ ነክታቹ ሙሉ መረጃውን ተከታተሉ። https://t.me/+Rt2tlQ5GeWRjOWI0 https://t.me/+Rt2tlQ5GeWRjOWI0
https://youtu.be/gAiXcVfg5pU?si=1EPWvDbLpjQh9N9J
«የፋኖ መንግሥት» የተሰኘው ምስላዊ ዘገባ፣ ከኦገስት 29 እስከ ሴፕቴምበር 13 ቀን 2026 እ.ኤ.አ በፈረንሳይ ፔርፒኛን በሚካሄደው 38ኛው ዓለም አቀፍ የፎቶ journalism ፌስቲቫል (Visa pour l’Image) ላይ ለዓለም ሕዝብ እንደሚቀርብ ተገለጸ! (ነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓ.ም — ኢትዮ 251 ሚዲያ) የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውንና በፋኖ የሚመራውን የአማራ ህዝባዊ ትግል "በዓለም ላይ ካሉ የተረሱና ድምፅ ያልተሰጣቸው ከባድ ጦርነቶች አንዱ" ሲሉ በሰፊው ዘግበውታል። «የፋኖ መንግሥት» (Fano’s Kingdom) በሚል ርዕስ በቀረበው በዚህ ሰፊ ዘገባ፣ የአማራ ህዝባዊ አርበኞች ከአለታማዎቹና ስልታዊ ጠቀሜታ ካላቸው የላስታ፣ ሰሜን ወሎና ጎንደር ተራሮች ተነስተው ሰፋፊ የገጠር ቀጠናዎችን በቁጥጥራቸው ሥር ማዋላቸው ተመልክቷል። በዘገባው መሠረት፣ የፋኖ አርበኞች አገዛዙ በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለውን ሁለንተናዊ በደል፣ ጭፍጨፋና የኢኮኖሚ ማዕቀብ ለመመከት ወደ ትግሉ መግባታቸው ተገልጻል። ቀደም ሲል በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከአገዛዙ ጎን የቆሙ ቢሆንም፣ በ2015 ዓ.ም የተደረገው የፕሪቶሪያ ስምምነት የአማራን ሕዝብ ሕልውናዊ ጥያቄዎችና ታሪካዊ መሬቶች ወደ ጎን ማለሉ እንዲሁም አገዛዙ የክልሉን ልዩ ኃይል ለማፍረስ የሄደበት መንገድ ለአሁኑ አገር አቀፍ ቁጣና ለትግሉ መስፋፋት ዋና ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል። አገዛዙ የፋኖን ህዝባዊ መሠረት ለመስበር ሲል በንጹሐን ዜጎች ላይ ድሮንን ጨምሮ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እንደሚጠቀም፣ በግፈኛ እስራትና በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ መሰማራቱን የጠቀሰው ዘገባው፤ ይህም ድርጊት ይበልጥ ወጣቶችን፣ ተማሪዎችንና አባወራዎችን ወደ ፋኖ ካምፖች እንዲቀላቀሉ ማድረጉን ያመላክታል። በአሁኑ ወቅት የትግራይን ክልል በሦስት እጥፍ የሚያበልጥና አስቸጋሪ መሬት ባለው ሰፊ ቀጠና የሚካሄደው ይህ የጉሬላ ውጊያ፣ የፌደራል ሰራዊቱን ከፍተኛ ወታደራዊና ስነ-ልቦናዊ ውጥረት ውስጥ ከቶታል ተብሏል። በተጨማሪም፣ የተለያዩ የፋኖ አደረጃጀቶች ትግሉን በተቀናጀ መንገድ ለመምራት ያደረጉት ጥረትና የተፈጠሩት ጥምረቶች የትግሉን አቅም ማሳደጋቸው ተገልጻል። በሌላ በኩል፣ በአካባቢው ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታ የሚፈልግ ቢሆንም፣ አገዛዙ የጋዜጠኞችን እንቅስቃሴ በመግደቡና የእርዳታ ድርጅቶችን መንገድ በመዝጋቱ ሳቢያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀዉሱ የከፋ መሆኑ ተመልክቷል። ይህ በፎቶግራፈር ሮቢን ቱቴንገስ (Robin Tutenges) የተሰነደውና የፋኖ አርበኞችን የትግል ሕይወት የሚያሳየው «የፋኖ መንግሥት» የተሰኘው ምስላዊ ዘገባ፣ ከነሐሴ 23 እስከ ጳጉሜ 08 ቀን 2018 ዓ.ም (ከኦገስት 29 እስከ ሴፕቴምበር 13 ቀን 2026 እ.ኤ.አ) በፈረንሳይ ፔርፒኛን በሚካሄደው 38ኛው ዓለም አቀፍ የፎቶ journalism ፌስቲቫል (Visa pour l’Image) ላይ ለዓለም ሕዝብ እንደሚቀርብ ታውቋል። ኢትዮ 251 ሚዲያ የነጻነት አንደበት!
📌ከሂትለር “ደምና አፈር” (Blood and Soil) እስከ አዲስ አበባ፦ የኦሕዴድ ጽንፈኞች የፋሺዝም አስተሳሰብ! በ20ኛው ክፍለ ዘመን ናዚ ጀርመን አዶልፍ ሂትለርና ተከታዮቹ ዓለምን ወደ ከፋ እልቂትና የዘር ማጥፋት የከተቱበት አንደኛው አደገኛ ጽንሰ-ሐሳብ “ደምና አፈር” (Blut und Boden / Blood and Soil) የሚለው የፋሺዝም አስተሳሰብ ነበር። የዚህ አስተሳሰብ መሠረታዊ ፍልስፍና፦ “አንድ መሬት/አፈር ባለቤት ሊሆን የሚችለው በተወሰነ የደም ሐረግ የተሳሰረ ማኅበረሰብ ብቻ ነው፤ ሌሎች ዜጎች መሬቱ ላይ ምንም ዓይነት አገራዊና ዜግነታዊ መብት የላቸውም” የሚል ጠባብ፣ አግላይና አደገኛ የዘር የበላይነት ተረክ ነው። ዛሬ በኢትዮጵያ የምናየው የኦሕዴድ ጽንፈኛ ባለሥልጣናት አካሄድ፣ በተለይም አዲስ አበባን በተመለከተ የሚያንጸባርቁት አቋም ከዚህ የሂትለር “ደምና አፈር” አስተሳሰብ ጋር ፍጹም አንድ ዓይነትና የቀጥታ ግልባጭ ነው። ጽንፈኞቹ “አዲስ አበባ የእኛ ብቻ ነች”፣ “የተለየ ጥቅም ያስፈልገናል”፣ “የደም አባቶቻችን መሬት ነች” እያሉ የሚረጩት ፕሮፓጋንዳ የዚሁ የናዚዝም አስተሳሰብ አደገኛ መገለጫ ነው። በዘመናዊ የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ የአንድ ከተማ ወይም ሀገር ባለቤትነት የሚወሰነው በዜግነት፣ በሕግ የበላይነትና በጋራ አስተዋጽኦ እንጂ በደም ሐረግ አይደለም። አዲስ አበባ የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ ቤት፣ በሁሉም ብሔረሰቦች ደምና ላብ የተገነባች፣ የሁሉም ዜጎች ሀብትና ዕውቀት ያደገች ዘመናዊ ከተማ ነች። ጽንፈኞቹ ግን ልክ እንደ ሂትለር “የደም መሠረት የሌለው ዜጋ በከተማዋ ላይ ሙሉ መብት ሊኖረው አይችልም” የሚል ግልጽ አቋም በማንጸባረቅ፣ በዜጎች መካከል የበላይና የበታች ደረጃ ለመፍጠር እየሰሩ ይገኛሉ። ሌላኛው የኦሕዴድ ጽንፈኞች “ልዩ ጥቅም” የሚለውን ቃል ሽፋን በማድረግ አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠርና የመዋጥ ፍላጎታቸውን ያሳያሉ። ይህ ሰልቃጭና ዋጭ አካሄድ ከልዩ ጥቅም ይልቅ የከተማዋን የስነ-ሕዝብ (demographics) መዋቅር በኃይል የመቀየር፣ የመሬት ዘረፋ የመፈጸምና የሌሎችን ብሔረሰቦች ውክልና የመግፈፍ ስልታዊ ዘመቻ ነው። ልክ የናዚ ጀርመን ኃይሎች “የሕይወት ቦታ” (Lebensraum) በሚል ሽፋን የሌሎችን መሬት በግፍ እንደወረሩት ሁሉ፣ እነዚህም ጽንፈኞች አዲስ አበባን የእነሱ ብቻ በማድረግ የዜጎችን ሀብትና መሬት በቋንቋና በደም መስፈርት ለመንጠቅ እየሞከሩ ነው። በተጨማሪ እነዚህ የኦሕዴድ ጽንፈኞች አዲስ አበባን “የእኛ ብቻ ነች” ሲሉ፣ ለዘመናት በከተማዋ የኖሩትን፣ ከተማዋን ያቆሙትንና ሀገራዊ ግዴታቸውን ሲወጡ የነበሩትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ታሪክና ህልውና በግልጽ እየካዱ ነው። ልክ ሂትለር በጀርመን የሚኖሩ ማኅበረሰቦችን “እንግዳና ባዕድ” አድርጎ እንደፈረጃቸው ሁሉ፣ እነዚህም ባለሥልጣናት አዲስ አበቤውን “መጤና ሰፋሪ” አድርገው በመሣል የፖለቲካና የኢኮኖሚ መብቱን ለመንጠቅ ባለፉት ስምንት ዓመታት በሰፊው ባጅተዋል፣ ዛሬ እነዚህን ጽንፈኞች ማስቆም ካልተቻለ አዲስ አበባን የደም መሬት ለማድረግ ወደኋላ የማይመለሱ ፍጹም ከሂትለር የባሱ ጨካኞች ናቸው። እንደውም በዘመናዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ የ“ደምና አፈር” የዘር ስሌት ፈጽሞ የማይሰራና አደገኛ ቢሆንም፣ ውይይቱን ወደ ታሪክና መሬት ባለቤትነት መለስ አድርገን ብናየው እንኳ ጽንፈኞቹ የሚያቀርቡት የባለቤትነት ሙግት በመረጃና በታሪክ ፊት ተቀባይነት የሌለውና የሚወድቅ ነው። ታሪክ እንደሚያስተምረን “ደምና አፈር” (Blood and Soil) በሚል የጽንፈኝነትና የፋሺዝም አስተሳሰብ የተመራ የትኛውም ኃይል መጨረሻው ውድቀትና አሳፋሪ ሽንፈት ነው። አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ሀብት፣ የነፃነትና የብዝሃነት ተምሳሌት እንጂ በጽንፈኞች የደም ስሌትና የዘር ገዥነት የምትወደቅ ከተማ አይደለችም። የኦሕዴድ ጽንፈኛ ባለሥልጣናት ይህንን የሂትለር አስተሳሰብ ተሸክመው አዲስ አበባን የሕገ-ወጥ ስግብግብነታቸው ማ ማዕከል ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት፣ በመላው ፍትሕ ፈላጊ ሕዝብና በሕዝባዊው የነፃነት ትግል የሚከሽፍ ይሆናል! ትግላችን ያሸንፋል!
📌መረጃ ቴሌቪዥን በስምንት ዓመታት የትግል ጉዞ፦ ተቋምን ከማፍረስ መገንባት፣ ከጫናዎች ባሻገር ያለው እውነት! ባለፉት ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ እጅግ ፈታኝና ውጣ ውረድ የበዛበት ነበር። በዚህ የትግል ጉዞ ውስጥ፣ በተለይም የፍትሕ፣ የነፃነት እና የህልውና ድምጽን በማስተጋባት ረገድ መረጃ ቴሌቪዥን (Mereja TV) ከፍተኛና የማይተካ አስተዋጽኦ አድርጓል። የብዙዎችን ብሶት አደባባይ በማውጣት፣ የተዳፈኑ እውነታዎችን በማጋለጥና ለሕዝብ ትግል መድረክ በመሆን የተጫወተው ሚና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ሆኖም፣ ይህ የተቋሙ ጉዞ አልጋ ባልጋ አልነበረም፤ በርካታ ፈተናዎችን፣ መንገራገጮችንና የውስጥ ጫናዎችን ያስተናገደበት ረጅም መንገድ ነው። መረጃ ቴሌቪዥን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የሚዲያ ባለሙያዎችና አክቲቪስቶች አብረውት ሠርተዋል። ከእነዚህም መካከል እነ ኢትዮ 360፣ ዘመድኩን በቀለ እና ሌሎችም የተለያዩ ግለሰቦች ይገኙበታል። ይሁን እንጂ፣ ጣቢያው አቅም እየገነባና ተጽዕኖ ፈጣሪነቱ እያደገ ሲመጣ፣ ከተቋማዊ ራዕይ ይልቅ የግል እና የቡድን ፍላጎቶች ማየል ጀመሩ። በተለያዩ ጊዜያት እነዚህ አካላት የየራሳቸውን የፖለቲካ ወይም የቡድን አጀንዳ በጣቢያው ላይ ለመጫን ሞክረዋል። የጣቢያው ዓላማ የሁሉንም ድምጽ ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ማስተናገድ ሆኖ ሳለ፣ "የእኛን ሀሳብ ብቻ አስተጋባ" የሚሉ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጫናዎች ጣቢያውን ሲያናውጡት ቆይተዋል። እነዚህ የፍላጎት ግጭቶች ጣቢያውን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ዋጋ እያስከፈሉት፣ አላስፈላጊ ውጥረቶች ውስጥ እንዲገባ አድርገውታል። ♦️የኢትዮ 251 ሚዲያ እውነተኛ ምስክርነት:- ተቋሙ በሌሎች አካላት "ጫና ያደርግብናል፣ አጀንዳ ይጭንብናል" በሚል ሲወቀስ ቢሰማም፣ ኢትዮ 251 ሚዲያ (Ethio 251) ባለፉት ሦስት ዓመታት ከመረጃ ቴሌቪዥን ጋር በነበረው የሥራ ቆይታ ያየው እውነት ግን ፈጽሞ የተለየ ነው። ኢትዮ 251 ሚዲያ ፕሮግራሞቹን አዘጋጅቶ ለመረጃ ቴሌቪዥን ሲያቀርብ፣ አንድ ቀንም ቢሆን ከመረጃ ቴሌቪዥን አመራሮችም ሆነ አዘጋጆች በኩል፡- "ይህን ፕሮግራም ብቻ አዘጋጁ"፣ "ይህን አስተያየት እንደዚህ አድርጋችሁ ስጡ"፣ "ይህንን አጀንዳ ተዉት" የሚል የኤዲቶሪያል ጣልቃ ገብነት ወይም ጫና ተፈጥሮበት አያውቅም። ይህ የሚያሳየው ተቋሙ ለሚዲያ ባለሙያዎች የሰጠውን የኤዲቶሪያል ነፃነት እና በልዩነት ውስጥ አብሮ የመሥራት ባህልን ነው። ይህ ማለት ግን መረጃ ቴሌቪዥን ፍጹም ነው፣ አሊያም በውስጡ ምንም ዓይነት የአሠራር ስህተቶችና ግድፈቶች አልተሠሩም ወይም አይሠሩም ማለት አይደለም። ተቋሙ ለወራት የተቋረጠ ጊዜ መቋረጡ ልክ አይደለም በሚል ከተቋሙ ባለቤቶች ጋር ተሟግተናል፣ በውስጡ የራሳቸውን ፍላጎት ለማንጠባረቅ የሞከሩ ሁሉ ነነሩ ወደፊትም ይኖራሉ፣ ይህን በተመለከተ ራሱ ተቋሙ ጠንካራ መተዳደሪያ ደንብ በማዘጋጀት የማስተካከል ኃላፊነተረ አለበት። መረጃ ቴሌቪዥን የሚዲያዎች መተላለፊያ አውታር ነው። በመረጃ ቲቪ የሚተላለፉ ዝግጅቶች በዋነኝነት ስህተት ከተሰራ መረጃ ቲቪ ተጠየቅ ቢኖርትበትም አብዛኛው ተጠየቅ የሚቀርበው ግን በአዘጋጆቹ ሚዲያ ነው። ማንም ሰው ወይም ተቋም ስህተት ሊሠራ ይችላል። ዋናው ጥያቄ ግን "ስህተት ሲፈጠር መፍትሔው ምንድን ነው?" የሚለው ነው። የትግል አጋር የሆነን የሚዲያ ተቋም፣ በታዩበት ጥቃቅን ስህተቶች ወይም በግለሰቦች አለመግባባት ምክንያት ለማፍረስ መነሳት የትግሉን ዐቢይ ዓላማ መሳት ነው። ስህተቶች ካሉ በእርጋታ እየታረሙ፣ አሠራሮች እየተስተካከሉ ተቋሙን ይበልጥ ማጠናከር እንጂ፣ ማፍረስ የጠላት አጀንዳ ማስፈጸሚያ ከመሆን አያልፍም። መገንባት ዓመታትን ይፈጃል፤ ማፍረስ ግን የአንድ ቀን ስሜታዊ ውሳኔ ነው። ለአማራ ሕዝብ ትግል የበርካታ ሚዲያዎች አስፈላጊነት ዛሬ ላይ መሬት ላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲታይ፣ የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እጅግ ወሳኝና የሞት ሽረት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ይህን መሰል ግዙፍ አገራዊና ሕዝባዊ ትግል ደግሞ በአንድ የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ ብቻ ሊሸፈንና ሊመራ አይችልም። ♦️የአማራው ትግል፡- አንድ ሳይሆን በርካታ የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ ጠንካራ የዲጂታል ሚዲያ አውታሮች፣ የሠለጠኑና ስትራቴጂካዊ የሚዲያ ባለሙያዎች ያስፈልጉታል። ያሉንን ጥቂት ተቋማት እያፈረስን የትግሉን ድምጽ ማፈን የለብንም። ይልቁንም መረጃ ቴሌቪዥንን ጨምሮ ያሉትን የሚዲያ ተቋማት መጠበቅ፣ ስህተታቸውን እያረሙ ማጠናከር እና ተጨማሪ አዳዲስ የሳተላይት ጣቢያዎችን በመክፈት የሕዝቡን ድምጽ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስተጋባት የዘመኑ ግዴታ ነው። ትግሉ የሚያሸንፈው ተቋማትን በማፍረስ ሳይሆን፣ ያሉትን በማጽናትና አዳዲሶችን በመገንባት ነው! #ማስታወሻ:- ባለፉት ዓመታት በተቋሙ ውስጥ እንደ ኢትዮ 251 ሚዲያ ስንሰራ ከኛ በኩል ጫና አልነበርብንም፣ ለተቋሙም የገቢ ማሰባሰቢያ ሲኖር ተገኝተን እናስተባብራለን እንጂ ክፍያ ተጠይቀን አናውቅም፣ ከመረጃ ቲቪም ምንም አይነት ክፍያ ተቀብለን አናውቅም።
ቀጠሮ ይያዙ!
📌ፀረ-ሀበሻ ክሴኖዶውሊያ የተጠናወተው አብይ አህመድ! (ክፍል ሁለት) “የውጭን አክባሪ፣ የገዛ ቤቱን ቀባሪ” እንደሚባለው፣ የአንድ አገር መሪ የገዛ አገሩን ታሪካዊና ማኅበራዊ መሠረት እያፈረሰ ለባዕዳን አጀንዳና ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ሲንበረከክ፣ ችግሩ የፖለቲካ ስህተት ብቻ ሳይሆን የጠለቀ የሥነ-ልቦና ቀውስ መሆኑን እንረዳለን። የአብይ አህመድን አገዛዝ የፖለቲካ ባሕሪና የጂኦፖለቲካዊ አካሄድ በትክክል ለመረዳት፣ "ፀረ-ሀበሻ" (የገዛ አገርንና የቀጠናውን ታሪካዊ ሥረ-መሠረት መጥላት) እና "ክሴኖዶውሊያ" (ለባዕዳን አገልጋይና ተገዢ መሆን) የሚሉትን ሁለት ገዳይ ደዌዎች አጣምሮ ማየት ግድ ይላል። ይህ አገዛዝ የሀገር ውስጥ የጀርባ አጥንቶችን በመስበር፣ ቀጠናውን ለውጭ ኃይሎች የትርምስና የብዝበዛ ሜዳ እያደረገው ይገኛል። የአብይ አህመድ "ፀረ-ሀበሻነት" በዋናነት ኢላማ ያደረገው የቀጠናውን የረጅም ዘመን ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊና ሥነ-ልቦናዊ መሠረት የሆኑትን አማራን እና ትግራይ ነው። እነዚህ ሁለቱ ተዋናዮች የጋራ ታሪክ፣ ሥልጣኔና አኩሪ የነፃነት ተጋድሎ ያላቸው፣ እንዲሁም የአፍሪካ ቀንድን ከባዕዳን ወረራ ጠብቀው ያቆዩ ታሪካዊ ምሰሶዎች ናቸው። አብይ አህመድ ይህንን ጠንካራ መሠረት ለማፍረስ ሆን ብሎ የተቀናጀ የጥፋት ስትራቴጂ ነድፏል። ለዚህም ግልጽ ማሳያው፣ በትግራይ ሕዝብ ላይ የከፈተው አውዳሚ ጦርነትና ያስከተለው ሰፊ የሰብዓዊ ቀውስ፣ የሰሜኑን ታሪካዊ ምሰሶ ለማፈራረስ የተደረገ የመጀመሪያው ሙከራ መሆኑ ነው። ይህ አልበቃ ብሎት፣ የትግራይን ሕዝብ በረሃብና በእልቂት ከቀጣ በኋላ፣ ዛሬ ደግሞ ትልቁን አገራዊ ደጀን የሆነውን የአማራን ሕዝብ በማንነቱ ፈርጆ በድሮንና በከባድ መሣሪያ እየጨፈጨፈ ይገኛል። ታሪካዊ ቅርሶችን፣ ገዳማትንና የአብሮነት እሴቶችን እያፈረሰ፣ አማራውን ከፖለቲካና ከኢኮኖሚ ተሳትፎ በማግለል የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ ነው። በሌላ በኩል፣ ይህ ፀረ-ሀበሻ አባዜው የሀገር ውስጥ ድንበር ተሻግሮ ኤርትራን ጭምር ያካተተ ነው። መጀመሪያ ላይ የውሸት የሰላም ሽልማት በመቀበልና የኤርትራን መንግሥት በማቀፍ ታማኝ ወዳጅ መስሎ ከቀረበ በኋላ፣ የኤርትራን ሉዓላዊነትና የረጅም ጊዜ የደኅንነት ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ጂኦፖለቲካዊ አሻጥሮችን ሲሠራ ቆይቷል። "ወደብ ያስፈልገኛል" በሚል ሽፋን በአማራ፣ በትግራይና በኤርትራ ሕዝቦች መካከል የቆየ የጥላቻና የጦርነት ትርክት እንዲነሳሳ በማድረግ፣ የኤርትራን ሉዓላዊነት አሳልፎ ለባዕዳን የባህር በር ፍላጎት ለመሸጥ መሞከሩ የዚህ ክህደት ማሳያ ነው። "ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል" እንደሚባለው፣ በውሸት የተገነባው የሰላም ስምምነት ፈርሶ ዛሬ ኤርትራን ለማግለልና አደጋ ላይ ለመጣል የሚሠራው ሴራ የፀረ-ሀበሻነት እቅዱ የመጨረሻው ምዕራፍ ነው። የዚህ ሁሉ የውስጥ ጥፋት ዋናው ገፊ ምክንያት ደግሞ ሌላኛው ደዌው የሆነው "ክሴኖዶውሊያ" (ለባዕድ ማጎብደድ) ነው። አብይ አህመድ ታሪካዊውን የሀበሻ ብሎክ (አማራን፣ ትግራይንና ኤርትራን) እያዳከመና እርስ በርሱ እያጋጨ ያለው፣ የቀንድ አፍሪካን ስትራቴጂካዊ የባህር በሮችና ጂኦፖለቲካዊ አቅም ለውጭ ኃይሎች (በተለይም ለዓረብ ኤምሬትስ) አሳልፎ ለመስጠት ነው። ለገዛ ሕዝቦቹ (ለአማራና ለትግራይ ገበሬዎች) ቦምብና ድሮን ሲያዘንብ፣ ለውጭ ጌቶቹ ግን እጅግ የተለሳለሰ፣ ተገዢና አገልጋይ ነው። የሀገሪቱን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጭ ተቋማት ማስረከቡ፣ የሀገር በቀል ዛፎችን ነቅሎ የውጭ ዘንባባዎችን በቤተ-መንግሥት መትከሉ፣ እንዲሁም የሀገር መከላከያ አቅምን የውጭ ኃይሎች መለማመጃ ማድረጉ የዚህ የክሴኖዶውሊያ ሥነ-ልቦናዊ ክስረት ተጨባጭ ማሳያዎች ናቸው። ፀረ-ሀበሻ ክሴኖዶውሊያ የተጠናወተው የአብይ አህመድ አገዛዝ የኢትዮጵያን ብሎም የቀጠናውን ታሪካዊ ክብርና ሉዓላዊነት ገደል አፋፍ ላይ አድርሶታል። "ገመድ ከየት መጣህ ቢሉት ከዛፉ፣ ዛፉን አስቆረጠው የገመዱ ጫፉ" እንደሚባለው፣ አብይ አህመድ ከዚሁ ማኅበረሰብ አብራክ ወጥቶ ታሪካዊ መሠረቱን ለባዕዳን ጌቶቹ ሲል እየቆረጠው ይገኛል። ዛሬ በአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) እና በፍትሕ ፈላጊው ሕዝብ እየተካሄደ ያለው የህልውና ትግል፣ ይህንን ፀረ-ታሪክ የሆነ የባዕድ አገልጋይነት አዙሪት ሰብሮ፣ ቀጠናዊ ሉዓላዊነትንና ሰላምን የማስመለስ ታላቅ ታሪካዊ ግዴታ ነው። ትግላችን ያሸንፋል!
📌የ‹‹ክሴኖዶውሊያ›› አዙሪት፦ የአብይ አህመድ የባዕድ አገልጋይነትና የሀገር ክህደት ማሳያ! በፖለቲካና በታሪክ ትንተናዎች ውስጥ፣ የአንድን መንግሥት የውድቀት፣ የክህደትና የሞራል ኪሳራ ደረጃ ለመለካት ከሚያገለግሉ ኃይለኛ ጽንሰ-ሀሳቦች መካከል «ክሴኖዶውሊያ» (Xenodoulia) ግንባር ቀደሙ ነው። ይህ ቃል ከሁለት የግሪክ ቃላት (ክሴኖስ/ባዕድ እና ዶውሊያ/ባርነት) የተገነባ ሲሆን፣ ትርጉሙም «ለባዕዳን ወይም ለባዕድ ነገሮች አገልጋይና ተገዢ መሆን» ማለት ነው። በዘመናችን የአብይ አህመድን አገዛዝ ምንነት፣ ፖለቲካዊ ባሕሪና የጂኦፖለቲካዊ አካሄድ ከዚህ የባዕድ አገልጋይነት ጽንሰ-ሀሳብ በተሻለ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አገላለጽ አይገኝም። የአብይ አህመድ ሥርዓት የ«ክሴኖዶውሊያ» ሕያው ማሳያ የሚሆንባቸው ዐቢይ መገለጫዎችና ተጨባጭ እውነታዎች ብዙዎች ናቸው። አንደኛው:- የፖለቲካና የሉዓላዊነት ተገዥነት (የባዕዳን አጀንዳ አስፈጻሚነቱ ነው) አንድ መንግሥት የራሱን ሀገራዊ ጥቅም ትቶ የውጭ ኃይላትን ፍላጎትና አጀንዳ ማስፈጸሚያ ሲሆን፣ ሀገር በ‹‹ክሴኖዶውሊያ›› አዙሪት ውስጥ ወደቀች ይባላል። የአብይ አገዛዝ የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ጥቅም፣ ጂኦፖለቲካዊ አቅምና ብሔራዊ ደኅንነት አሳልፎ በመስጠት የውጭ ኃይሎች (በተለይም የዓረብ ኤምሬትስ) ፍላጎት አስፈጻሚ መሣሪያ ሆኗል። ለዚህም ግልጽ ማሳያው፣ የአገዛዙ የውጭ ግንኙነት በሀገራዊ ጥቅም ላይ ሳይሆን በግለሰብ የበታችነት ስሜት ላይ የተመሠረተ መሆኑ፣ እንዲሁም ቀጠናውን የውጭ ኃይሎች መፈንጫ በማድረግና በጎረቤት ሀገራት መካከል አላስፈላጊ ትርምስ በመፍጠር ሀገርን ለከፍተኛ ጂኦፖለቲካዊ ስጋት አሳልፎ መስጠቱ ነው። ሁለተኛው:- የባህልና የሥነ-ልቦና የበታችነት (የባዕድ አምልኮት ነው) የራስን ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ባህልና እሴት ዝቅ አድርጎ በመመልከት የባዕዳንን አኗኗር በየዋህነት ወይም በበታችነት ስሜት ማምለክ ሌላው የ«ክሴኖዶውሊያ» መገለጫ ነው። የአብይ አገዛዝ የኢትዮጵያን ታሪካዊ መሠረቶች፣ የአብሮነት እሴቶችና ታሪካዊ ቅርሶችን በዶዘር እያፈረሰ፣ ከውጭ የተቀዳና የሀገርን ማኅበራዊ ስነ-ልቦና የማይወክል የውጭ ቅጅ በሆኑ የቤተ-መንግሥት ግንባታዎች (እንደ ጫካ ፕሮጀክት ባሉ) ላይ በሚሊዮን ዶላሮችን ያፈሳል። ሕዝብ በረሃብና በጦርነት እያለቀ፣ ሀገር በቀል እሴቶችን ንቆ በባዕዳን የገንዘብና የባህል ተጽዕኖ ስር መውደቅ ከፍተኛ የሥነ-ልቦና ባርነት ነው። ሶስተኛው:- ለገዛ ዜጎች ‹‹ክሴኖፎቢያ››፣ ለባዕዳን ‹‹ክሴኖዶውሊያ›› ነው። «ክሴኖፎቢያ» ባዕዳንን/እንግዶችን መጥላትና ማገለል ሲሆን፣ «ክሴኖዶውሊያ» ደግሞ የሱ ተቃራኒ ሆኖ ለባዕዳን እጅ መስጠትን ያመለክታል። የአብይ አገዛዝ በውስጥ ላሉ ወንድሞቹና ዜጎቹ (በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ) ‹‹ክሴኖፎቢያዊ›› የሆነ የከፋ ጥላቻን፣ ማግለልንና ጭፍጨፋን እየፈጸመ ይገኛል። ወጣቱን ማሰር፣ ሕዝብን በድሮንና በከባድ መሣሪያ መደብደብ የዕለት ተዕለት ተግባሩ ሆኗል። በአንጻሩ፣ ለውጭ ኃይሎች ግን እጅጉን የተለሳለሰ፣ ተገዢና አገልጋይ ሆኖ እናገኘዋለን። ለገዛ ሕዝቡ እብሪተኛና ጨካኝ ፋሺስት የሆነ አገዛዝ፣ በባዕዳን ፊት ግን ሎሌና ታዛዥ መሆን ትልቁ የሞራል ውድቀትና የ«ክሴኖዶውሊያ» ልክፍት ነው። በአጠቃላይ፣ የአብይ አህመድ አስተዳደር የኢትዮጵያን ነጻነት፣ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ክብር አሳልፎ ለውጭ ኃይሎች የሸጠበት አሳፋሪ መንገድ በዘመናዊው የፖለቲካና የጂኦፖለቲካ ትንተና መነጽር ሲመዘን፣ ከ«ክሴኖዶውሊያ» (ከባዕድ አገልጋይነትና ተገዢነት) ውጭ ሌላ ስም ሊሰጠው አይችልም። ይህ አገዛዝ የሀገር ጠባቂ ሳይሆን፣ የባዕዳን አጀንዳ አስፈጻሚ የጥፋት ኃይል መሆኑን መላው ሕዝብ ተገንዝቦ ትግሉን ከዳር ለማድረስ መነሳት አለበት። ትግላችን ያሸንፋል!
ሰበር መረጃ! የኦህዴድ ነባር አመራሮች ብልፅግናን ከሕወሓት ጋር ለማስታረቅ ሰፊ ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ! የቀድሞው የኦህዴድ የበላይ ጠባቂና የአሁኑ የሥርዓቱ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሽግግር የበላይ ጠባቂ አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራው የኦህዴድ ነባር አመራሮች (Old Guard) ቡድን፣ ብልፅግናን ከሕወሓት ጋር ለማስታረቅና ፀረ-ብልፅግና እንቅስቃሴውን ለማስቆም ከዲፕሎማቲክ ምንጮች በተገኘ መረጃ መሠረት ሰፊ የሽምግልና ጥረት እያደረገ ይገኛል። ሕወሓት ከብልፅግና ጋር የሚያደርገውን ፍጥጫ ትቶ የሚስማማ ከሆነ ለድርጅቱ በርካታ ማማለያዎችና አማራጮች ማቅረባቸው ታውቋል። ከቀረቡት ዋና ዋና ነጥቦች መካከል የወልቃይትና የራያ አካባቢዎች ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት ሁኔታ በሕጉ መሠረት እንዲመለሱና ተፈናቃዮችን መልሶ ለማስፈር የፌደራል ፀጥታ ኃይል ኃላፊነት እንዲወስድ የሚል ይገኝበታል። በተጨማሪም የሕወሓት ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲነት ተመልሶ ዕውቅና እንዲያገኝና በሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የተመረጡ ሥራ አስፈጻሚዎች የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን እየመሩ እንዲቀጥሉ የሚሉ ማማለያዎች ቀርበዋል። አክለውም በፌደራል መንግሥት ውስጥ የትግራይ ክልል የሚገባውን የሥልጣን ድርሻ በአግባቡ ለሕወሓት ለመስጠት፣ የታገደውን የትግራይ ክልል የፌደራል በጀት ለመልቀቅ፣ የኢኮኖሚ ማገገሚያ ድጎማ (Economic Rehabilitation Fund) ለማድረግ እንዲሁም በዲዲአር (DDR) በኩል የሰራዊት መልሶ ማቋቋም ተግባር እንዲከናወን የማሸማገያ ሀሳቦች መቅረባቸው ታውቋል። እስከ አሁን ባለው መረጃ ሕወሓት በቀረበለት ጥያቄ ላይ የሰጠው ምላሽ የሌለ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የአሜሪካው አምባሳደር ወደ መቀሌ ለማድረግ ያሰቡት ጉዞ የተሰረዘው በዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል "...የአምባሳደሩ መምጣት የሚቀይረው ነገር ስለሌለ አስፈላጊ አይደለም" በሚል ውድቅ መደረጉ የሚታወስ ነው ተብሏል። "ከሕወሓት ጋር አብረን ሠርተናል፣ እንተዋወቃለን" በሚል ከብልፅግና ጋር ለማሸማገል አምባሳደር ግርማ ብሩ በሚመሩት ኮሚቴ ውስጥ አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ አቶ ጁነዲን ሳዶ፣ አቶ ሙክታር ከድር፣ አቶ አባዱላ ገመዳ እና ሁለት ማንነታቸው ያልተለየ ባለሀብቶች መካተታቸው ታውቋል።
“ከኦሮማራ ጨዋታ እንውጣ፣ ኢትዮጲያን ወደገደል እየከተቷት ነው።” የመከላክያ የውጭ ጉዳይ እና ትብብር ቃል አቀባይ ሜ/ጄ ተሾመ ገመቹ
https://youtu.be/WReNRvScphI?si=-WvEXXXVe3rArpee
📌“የጦርነት ቀጠና” - የከሸፈው የካድሬዎች ፕሮፓጋንዳ እና የሕልውና ትግሉ እውነታ! በአሁኑ ወቅት የአብይ አህመድ አገዛዝና የጥቅም ተካፋዮቹ፣ “ፋኖ የአማራን ክልል የጦርነት ቀጠና እያደረገው ነው” የሚል እጅግ የረከሰና አሳሳች የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በስፋት አፋፍመዋል። ይህ ተረክ የገዛ ራሳቸውን የፖለቲካና የወታደራዊ ኪሳራ ለመሸፈን የተፈጠረ የጭንቀት ጩኸት እንጂ፣ የረባ ስነ-አመክንዮ ወይም መሬት የረገጠ እውነት የለውም። እውነታው ፍጥጥ ብሎ ሲታይ፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት አብይ አህመድ በአማራ ሕዝብ ላይ ያልተኮሰው የትኛው የጦር መሣሪያ አለ? ዛሬ “አካባቢው የጦርነት ቀጠና ሆነ” ብለው አዞ እንባ የሚያነቡት አስመሳዮች፣ ትላንትና የንጹሐን ደም በድሮን ሲፈስ፣ ከተሞች በከባድ መሣሪያ ሲደበደቡ፣ ንብረት ሲወድምና ሕዝብ በጅምላ ሲጨፈጨፍ የት ነበሩ? የአማራ ክልል የባሩድ ማውረጃ የተደረገው ዛሬ ፋኖ ራሱንና ሕዝቡን ለመከላከል ክንዱን ስላጠነከረ ሳይሆን፣ አገዛዙ ሆን ብሎ ሕዝቡን ለማንበርከክ ይፋዊ የመንግሥት ሽብር (State Terrorism) ስላወጀበት ነው። ታዲያ ዛሬ የተለየ ምን ተገኝቶ ነው “አማራ ክልል የጦርነት ቀጠና ሊሆን ነው” የሚለው የካድሬዎች ጩኸት ከወትሮው በተለየ የተጧጧፈው? መልሱ አጭርና ግልጽ ነው። ከትናንት እስከ ዛሬ በሕዝቡ ላይ ሞትና ውድመት ሲዘንብ ያልተሰማቸው እነዚህ የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች ዛሬ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚጮሁት የአማራ ሕዝብ ስላሳዘናቸው አይደለም። ይልቁንም የፋኖ አንድነት ተጠናክሮ፣ ትግሉ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግሮ የአገዛዙን የኃይል መዋቅር በየግንባሩ እያፈረሰው ስለመጣ ነው። የዛሬው ጩኸት የሰራዊቱ መበታተን፣ የኮማንድ ፖስቱ መዋቅር መፍረስና የሥልጣን ዘመናቸው ማክተም እውን መሆኑን ሲረዱ የተፈጠረ የሞት ጣዕር ነው። አገዛዙ ያለ የሌለ ኃይሉን አሟጦ እየተዋጋ ማሸነፍ ሲያቅተው፣ የራሱን የጦርነት ወንጀል በሕልውና ታጋዮች ትከሻ ላይ ለማላከክ የሚጠቀምበት የሥነ-ልቦና ጦርነት ነው። የአማራ ሕዝብና ታጋዩ ፋኖ ጦርነት ናፋቂዎች አይደሉም፤ የገቡበት ትግልም የሕልውና እንጂ የቅንጦት አይደለም። የጦርነት ቀጠና ያደረገውንና የሕዝብን ሰላም የነሳውን እውነተኛ ጠላት (የአብይ አህመድን ሥርዓት) አቅፎ እያገለገሉ፣ ደረታቸውን ነፍተው ርስቱንና ማንነቱን በሚያስከብረው የነፃነት ታጋይ ላይ ጣት መቀሰር የሞራል ክስረት ነው። ሕዝብን በድሮን እየጨፈጨፉ “ሰላም አስከባሪ”፣ ሕልውናን እየተከላከሉ “ጦርነት ቀስቃሽ” የሚለው የአፈ-ጮሌዎች ተረክ፣ ቆርጦ የተነሳውን የአማራን ሕዝብ ትግል አንድ ስንዝር ወደኋላ አይመልሰውም። ትግላችን ያሸንፋል!
📌አጋርነትና ትብብርን በተመለከተ ልንመለከታቸው የሚገቡ ወሳኝ ጉዳዮች እና ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች! በማንኛውም ሕዝባዊና ወታደራዊ የህልውና ትግል ውስጥ የተበታተነን አቅም ማሰባሰብ፣ ከአጋር ኃይሎች ጋር ጠንካራ ትብብር መፍጠር እና ስልታዊ ጥምረት መመስረት የድል ጊዜን የሚያፋጥኑ ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) አሁን ላይ መሬት ላይ እያስመዘገበ ያለውን አንጸባራቂ ወታደራዊ ድል ወደ ዘላቂ የፖለቲካ ስኬት ለማሸጋገር፣ ከሌሎች አገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ኃይሎች ጋር የሚያደርገው የአጋርነት ጉዞ እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት ሊሆን ግድ ይላል። ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከአጋር ኃይሎች ጋር መተባበር የኃይል ሚዛኑን ወደ ሕዝብ ከማዘንበል ባለፈ፣ የአገዛዙን የመከፋፈል ሴራ በማክሸፍ የጋራ ጠላትን በጥቅል ለመጋፈጥ ያስችላል። ይህ ስትራቴጂካዊም ሆነ ስልታዊ አጋርነት አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ቅቡልነትን ከማሳደጉም በላይ የሎጂስቲክስና የዲፕሎማሲ አቅምን በማስተባበር፣ አምባገነኑ ሥርዓት ሲወድቅ ለሚፈጠረው የሥልጣን ክፍተት ጠንካራ የጋራ መሠረት ለመጣል ወሳኝ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ፋኖ ከሌሎች የነፃነት ኃይሎች ጋር በተግባር ሊተገብራቸው የሚገቡ የትብብር መስኮች ሰፊ ናቸው። የመረጃና የስለላ ልውውጥን ማጠናከር፣ ጠላት ኃይሉን እንዳያከማች በየግንባሩ የተቀናጁ ወታደራዊ ጥቃቶችን መሰንዘር፣ እንዲሁም የአገዛዙን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ የሚያመክን ወጥ የሆነ የሚዲያ ዘመቻ መምራት ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። በተጨማሪም፣ በዓለም አቀፍ መድረክ የጋራ ልዑካንን በመላክ የዲፕሎማሲ ስራዎችን መስራት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በጋራ ማጋለጥና ሀገሪቱ ወደ ባሰ ውጥንቅጥ እንዳትገባ የሽግግር ማዕቀፎችን አስቀድሞ ማዘጋጀት የትብብሩ ማዕከላዊ ምሰሶዎች ሊሆኑ ይገባል። ሆኖም ይህ የጥምረት ጉዞ የትግሉን ዓላማና ደኅንነት አደጋ ላይ እንዳይጥል ብርቱ ጥንቃቄዎችን ይሻል። የአማራን ሕዝብ ህልውና፣ ደኅንነትና ታሪካዊ መብቶች አደጋ ላይ ከሚጥል ማንኛውም ኃይል ጋር ቀይ መስመርን (Red Lines) አሳልፎ የሚሰጥ ድርድርም ሆነ ወይይት በፍጹም ሊደረግ አይገባም። በአጋርነት ስም የአገዛዙ ሰላዮችና የጥፋት መልእክተኞች ወደ ትግሉ መዋቅር እንዳይሰርጉ ጥብቅ የደኅንነት ፍተሻ ማድረግ፣ ከማንኛውም ኃይል ጋር ትብብር ከመጀመሩ በፊት የትግሉን ግብ በግልጽ ማሰር፣ እንዲሁም የውጭ ኃይሎች ጥገኛ ባለመሆን የውሳኔ ሰጪነት ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ ያሻል። ጥምረቱ በስሜት ሳይሆን በፖለቲካዊና ወታደራዊ እንድምታዎች በጥናት ላይ የተመሠረተ ሆኖ፣ ጊዜያዊና ዘላቂ አጋሮችን በጥበብ መለየት ያስፈልጋል። ማንኛውም ግንኙነት በእኩልነትና በመከባበር ላይ ተመስርቶ፣ በሌሎች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ሳይገባ፣ እንዲሁም ግልጽነትን በተላበሰ ተቋማዊ አሰራር የረጅም ጊዜ ሀገራዊ መግባባትን ታላሚ አድርጎ ሊመራ ይገባል። ከዚህ በተጓዳኝ፣ ትግሉን በውጭው ዓለም ስኬታማ ለማድረግ የዓለም አቀፍና የዲያስፖራ አጋርነት ግንባታው ሌላው ወሳኝ የትኩረት አቅጣጫ ነው። የዲያስፖራውን አቅም በአንድ ወጥ መዋቅር በማቀናጀት፣ ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ጋር ጠንካራ የመረጃ መስመር መዘርጋትና የምስራቅ አፍሪካን የጂኦፖለቲካ ሁኔታዎች ለትግሉ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማዋል ያስፈልጋል። የአገዛዙን የሐሰት ዲፕሎማሲ በማጋለጥ፣ ታዋቂ የውጭ ሚዲያዎችንና የዲፕሎማሲ መስመሮችን በብቃት መጠቀም የትግሉን ድምፅ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማድረስ የድል መንገዱን ያሳጥረዋል። የአፋብን ከአጋርነትና ትብብር አኳያ የሚወስዳቸው እርምጃዎች በጥበብ፣ በብስለትና በስልታዊ ጥንቃቄ የታጀቡ መሆን አለባቸው። ትብብር አቅምን ያጎለብታል፤ ነገር ግን ያልተጠናና ጥንቃቄ የጎደለው አጋርነት ለትግሉ መዳከም ምክንያት ሊሆን ስለሚችል፣ ፋኖ የሕዝቡን የህልውናና የፍትሕ ጥያቄ ማዕከል በማድረግ፣ የውስጥ አንድነቱን አጠናክሮ ከእውነተኛ የነፃነት ኃይሎች ጋር የሚያደርገውን የተቀናጀ ትግል ሊገፋበት ይገባል። ትግላችን ያሸንፋል፣ አፋብን ያሻግረናል!
📌 የአማራ ፋኖ ትግል እና ከመስመር አሳች ስብከቶች! በአሁኑ ወቅት የአማራ ሕዝብ የሕልውና ተጋድሎ ወደ ተቋማዊ ልዕልና እና ወደ ማዕከላዊ የፖለቲካ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ባለበት ወሳኝ ወቅት፣ በትግሉ ዙሪያ የሚደመጡ የተሳሳቱ ተረኮች እና የፖለቲካ ድንቁርና ያላበቃቸው መከራከሪያዎች በትግሉ መሥመር ላይ ከፍተኛ ጥላሸት ለመቀባት እየሞከሩ ይገኛሉ። ወዳጅ መስለው በበግ ቁርበት የቀረቡ፣ ነገር ግን በትግሉ መንፈስ ላይ ተስፋ የመቁረጥ እና የጥርጣሬ መርዝ የሚረጩ አካላት፣ የሕዝቡን የደምና የአጥንት መስዋዕትነት ዋጋ ለማሳነስ ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላል። አገዛዙ በከፍተኛ በጀት ድጋፍም እየሰራበት ያለው ጉዳይ ነው። በዚህ ሂደትም አጉል ሚዛናዊ ነኝ ባይ በምሁር ካባ የተጠለሉ በርካታ ሰዎች እየተሳተፉበት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ አሁን ያለውን የሕዝብ ልጅ የሆነውን የአማራ ፋኖን ከ1983ቱ የኢሕዴን (የኋላኛው ብአዴን) የጥገኝነትና የአገልጋይነት ታሪክ ጋር ለማመሳሰል የሚደረገው ጥረት ፍጹም ስህተትና የከሰረ ፖለቲካ ነው። ኢሕዴን የሌሎች ኃይሎችን አጀንዳ ለማስፈጸም የተቃኘ፣ በሰው የፖለቲካ መሪነት የሚነዳና ሕዝቡን ለባርነት አሳልፎ የሰጠ የፖለቲካ ስብስብ ነበር። አሁናዊው የፋኖ ንቅናቄ ግን ከራሱ ከሕዝቡ ብቅ ያለ፣ የታጠቀና የታገለ፣ የራሱን ፖለቲካዊና ወታደራዊ አቅጣጫ በራሱ የሚወስን ሉዓላዊ ሕዝባዊ ኃይል ነው። ፋኖን የሌሎች ኃይሎች "መንገድ አድራሽ" ወይም "መሰላል" አድርጎ የመሳል አመለካከት፣ የትግሉን ውስጣዊ ጥንካሬና የሕዝቡን የነፃነት ፍላጎት ከመደፍጠጥ የሚመጣ ብልጽግና መር ስውር አጀንዳ ነው። በሁለተኛ ደረጃ፣ "የአማራ ኃይል ከሌሎች የፖለቲካና የወታደራዊ ኃይሎች ጋር ጥምረት ወይም ትብብር ከፈጠረ ወልቃይትንና ራያን ያጣል" የሚለው ሰበካ፣ የፖለቲካ ዘገምተኝነት እና የመጨረሻው ድንቁርና ማሳያ ነው። ጥምረትና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማለት የራስን መሠረታዊ ጥያቄና ታሪካዊ ርስት አሳልፎ መስጠት ሳይሆን፣ የጋራ ጠላትን ለመጣልና የራስን ሕልውና በሕጋዊና በኃይል ሚዛን ለማስከበር የሚደረግ ዘመናዊ የፖለቲካ ጥበብ ነው። የጸና የውስጥ አደረጃጀትና ጠንካራ ማዕከላዊ አመራር ያለው ኃይል፣ ጥምረት በፈጠረ ቁጥር መብቱን አያጣም፤ ይልቁንም ይበልጥ ያጠናክራል። ርስትን የሚያስመልሰውና የሚያስጠብቀው በበሩ ስር ተሸጉጦ በሚደረግ ፍርሃት ሳይሆን፣ አገራዊ የፖለቲካ ልዕልናን በመጨበጥና ወታደራዊ ብልጫን በማረጋገጥ ነው። በሦስተኛ ደረጃ፣ "ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ጉዞ አማራ ክልልን የጦርነት ቀጠና ያደርገዋል" በሚል የሚሰራጨው የስጋት ፕሮፓጋንዳም የፍርሃትና የአገዛዙን እድሜ የማራዘም ሴራ አካል ነው። ወደ ማዕከል በሚደረግ ማንኛውም ወታደራዊና ፖለቲካዊ ገስጋሴ ውስጥ አማራ ክልል የመሸጋገሪያና የስትራቴጂክ መነሻ መሆኑ አይቀሬ ነባራዊ ሀቅ ነው። ሌሎች ኃይሎች ጦርነት ጀመሩም አልጀመሩም፣ ባለፈው አምስት አመት የአማራ ክልል የጦርነት ቀጠና ከሆነ ከራርሟል። ነው አሁን እየተደረገ ያለው የቲማቲም ውጊያ ነው? ለማንኛውም የጦርነቱ መነሻና መድረሻ የሚወሰነው በጠላት እግር ተከተል ነው፤ አገዛዙ ከአዲስ አበባ ወጥቶ ወደ ጅማም ሆነ እስከ ኬንያ ወሰን ድረስ ቢሸሽ፣ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ምድር የፍልሚያ አውድማ መሆኑ የማይቀር ሀቅ ነው። ውጊያን በራስ ደጅ አስቀርቶ ሰላም ማምጣት የሚቻለው አምባገነኑን አገዛዝ በማዕከሉ ላይ መትቶ በመጣልና የመንግሥትነት ሥልጣኑን በማክሸፍ፣ አማራው የማይጠቃበት በፍትህና ርትዕ ላይ የተመሠረተ መንግሥት ሲቋቋም ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ያለው አዛኝ መሳይ አንጎች ስብከት ነው። በመጨረሻም፣ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የአማራን ትግል ለሌሎች የመሸጥ ወይም በሌሎች ጥላ ሥር የመጠለል ራስ-ጠል ፖለቲካ ማራመድ ለአራማጁ የተፈቀደ ቢሆንም በአማራው ኃይል ዘንድ ግን በፍጹም ተቀባይነት የለውም። የአማራ ሕዝብና ፋኖ፣ የሌሎች የፖለቲካ አጀንዳ ማስተላለፊያ ወይም መንገድ አድራሽ አይደለም። የአማራ ሕዝብ በታሪኩ እንደነበረው ሁሉ፣ ዛሬም ቢሆን በራሱ እግር ቆሞ፣ ሌሎችን አስተባብሮና መርቶ ሀገርን የማዳንና የማስተዳደር አቅም ያለው ታላቅ ሕዝብ ነው። ይህ ትግል ቀደም ሲል በሕዝባዊ ብሂል እንደሚነገረው ሁሉ፦ አማራ አራሽ፣ ቀዳሽ፣ ተኳሽ፣ ሰጋጅ ብቻ ሳይሆን የመጨረሻው ባለቤትና «ነጋሽ» መሆኑን በተግባር የሚያረጋግጥበት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ትግሉ ከማንኛውም ጥገኝነት የጸዳ፣ የራሱን ዕድል በራሱ የሚወስን እና ሌሎችን አሰባስቦ ወደ ፍትሐዊ ሥርዓት ግንባታ የሚያሸጋግር እንጂ የጥቂት ፖለቲከኞች የገበያ እቃ አይሆንም። ትግላችን ያሸንፋል!
📌የተዋህዶ እና የአማራ ጠልነት ስነ-ልቦናዊ እውርነት! (ሙሉጌታ አንበርብር) ተዋናይ አስቴር በዳኔ “አሁን ላይ ላለው ግጭት መነሻው የሆነ ብሔርና ሃይማኖት ለብዙ ጊዜያት የሀገር ባለቤት ነኝ ብሎ ተቀምጧል…” በማለት የሰነዘረችው ንግግር፣ የአሁኑ አምባገነናዊ አገዛዝ የሚንከባከበውንና የሚያሰራጨውን የአንድ ወገን ጥላቻና የታሪክ መዛባት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አደገኛ ፕሮፓጋንዳ ነው። ይህ ንግግር ለአገራት መፍረስ፣ ለዜጎች ጭፍጨፋ እና ለአገዛዙ ውድቀት መንስኤ የሆኑትን መዋቅራዊ ችግሮችና አምባገነንነት ሸፍኖ፣ ጥቃቱን በአንድ ብሔር (በአማራ) እና በአንድ እምነት (በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን) ላይ ለመለጠፍ የተደረገ የከሰረ የፖለቲካ ቁማር ነው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና የአማራ ሕዝብ ለዘመናት የሀገር ባለቤት ሆነው እንደኖሩ አድርጎ ማቅረቡ የታሪክ መሃይምነት ወይም ሆን ተብሎ የተሸረበ ሴራ ነው። ቤተክርስቲያኗ ለሺህ ዓመታት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት፣ ታሪክ፣ ቅርሶች እና የብሔረሰቦችን አብሮ የመኖር እሴት ጠብቃ ያቆየች የሀገር መሠረት እንጂ የአንድ ወገን የበላይነት መገለጫ ሆና አታውቅም። በአንፃሩ፣ የአማራ ሕዝብ በየታሪክ መጋጠሚያው ሀገርን ለማዳን ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከከሰከሰ በኋላ፣ ራሱ በመሰረታት ሀገር ውስጥ በድህነት፣ በበደል እና በአሁኑ ወቅት ደግሞ በመዋቅራዊ የዘር ፍጅት (Genocide) እና የድሮን ጭፍጨፋ ሰለባ እየሆነ ያለ ሕዝብ ነው። በሁለተኛ ደረጃ፣ “Tolerate የማያደርግ (የማይታገስ) ትውልድ ስለተነሳ ሁሉም የዘራውን እያጨደ ነው” የሚለው ንግግር፣ አረመኔያዊነትን እና የዜጎችን ጭፍጨፋ እንደ ትክክለኛ እርምጃ አድርጎ የሚያቀረብ ጸያፍና ከሥነ-ምግባር ውጪ የሆነ ንግግር ነው። ንጹሃን እናቶችና ሕፃናት በማንነታቸው ምክንያት ሲጨፈጨፉ፣ መኖሪያ ቤታቸው ሲቃጠል እና በድሮን ሲደበደቡ “የዘሩትን ማጨድ ነው” ብሎ ማጸደቅ፣ ከአርቲስትነት ስብዕና ወጥቶ የአምባገነን አገዛዝ ገዳይ ሃይሎችን ደም የመጠማት ፍላጎት ማስተጋባት ነው። በአገዛዙ ከተማረኩና ታጋሽ ካልሆኑ ካድሬዎች የተወለደው ትውልድ “ትዕግሥት ማጣት” ያመጣው ውጤት ሰላምንና እድገትን ሳይሆን፣ ሀገርን ወደ ለየለት ውድቀት፣ ረሃብ እና የእርስ በእርስ እልቅቅት መክተቱን አለማወቅ ታላቅ የፖለቲካና የማኅበራዊ እውርነት ነው። አስቴር በዳኔ እና መሰል የብልፅግና ልሳኖች ሊረዱት የሚገባው መሠረታዊ ሀቅ ቢኖር፣ አሁን በኢትዮጵያ ላለው አጠቃላይ ቀውስና ውድቀት ምክንያቱ አማራ ወይም ቤተክርስቲያኗ ሳይሆን፣ አገዛዙ የዘረጋው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ፣ ስግብግብነት እና የስልጣን ጥም መሆኑን ነው። የሕልውና አደጋ የተደቀነበት ሕዝብ መብቱንና ሕልውናውን ለማስከበር የሚያደርገውን ተጋድሎ “የበላይነት ፍላጎት” አድርጎ መፈረጅ፣ የገዳይን እና የተገዳይን ሚና የመቀየር ከንቱ ጥረት ነው። እንዳጠቃላይ ሕዝብን በብሔርና በሃይማኖት ከፍሎ የሚያጋጭ፣ የንጹሃንን ደም የሚያቃልል እና የታሪክ እውነታን የሚቀይር ንግግር የፖለቲካዊና የሞራል ኪሳራ ማሳያ ነው። የአማራ ሕዝብና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በታሪክ ማዕበል እና በአምባገነኖች ሴራ የማይወድቁ የሀገር መሠረቶች በመሆናቸው፣ እንዲህ ዓይነት የካድሬዎች ተረክና የጥላቻ ስብከት የታሪክ ተጠያቂነትን የሚያስከትል እንጂ የትግሉንና የሕዝቡን እውነተኛ ማንንነት ሊቀይር አይችልም። ትግላችን ያሸንፋል!
📌የክረምቱ ወርቃማ ጊዜ እና የታሪካዊ ኃላፊነት ጥሪ፦ የአማራ ፋኖ ትግል ከድርጅታዊ መበታተን ወደ ተቋማዊ አንድነት የመሸጋገር ግዴታ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከተመሠረተበት ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ጊዜ ጀምሮም ሆነ ቀደም ብሎ በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕልውና ተጋድሎ ውስጥ ከፍተኛ መስዋዕትነት ሲከፍል የቆየ ቢሆንም፣ ሂደቱ ከጊዜና ከሁኔታዎች ዕድገት ጋር የሚመጥን ጠንካራ የፖለቲካ ቢሮ፣ የተማከለ አመራር እና ወጥ ድርጅታዊ መዋቅር መፍጠር ላይ ሰፊ ክፍተቶች ይታዩበታል። በተለይም በጎጃምና በጎንደር ቀጠናዎች ሥር የሚገኙትን እንደ የበላይ ዘለቀ እዝ እና የቴዎድሮስ እዝ ያሉትን ታላላቅ ወታደራዊና ሕዝባዊ ክንፎች በአንድ ማዕከላዊ የፖለቲካና የወታደራዊ መዋቅር ሥር አጣጥሞ ማደራጀት አለመቻሉ ትግሉን ለከፍተኛ ተጋላጭነት ዳርጎታል። ይህንን ተቋማዊ ውቅረት መዘርጋት አለመቻል ከተራ ድርጅታዊ ድክመት አልፎ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰማዕታትን ደምና የመላው ሕዝብን ተስፋ አደጋ ላይ የሚጥል፣ በትግሉ ላይ መጫወትና ታሪካዊ ስህተት መሥራት ሆኖ ተመዝግቧል። በአሁኑ ወቅት ከፊታችን የተደቀነው የክረምት ወርቃማ ጊዜ ለሕልውና ትግሉ እጅግ ከፍተኛ ስልታዊና ወታደራዊ ብልጫን የሚያጎናጽፍ አጋጣሚ ነው። ሆኖም ግን፣ ይህንን ታሪካዊ ዕድል በጥቅም ላይ በማዋል ፈንታ፣ የአመራሩ ክፍሎች በቡድንተኝነት፣ በጥቅም ሽሚያ፣ በጎጠኝነት እና በስሜታዊ አጀንዳዎች ተጠምደው የትግሉን ዋና ዓላማ ሙሉ በሙሉ የረሱት ይመስላል። የተበታተነ አደረጃጀት ይዞ፣ የፖለቲካ መስመር ሳይኖረው እና ማዕከላዊ ዕዝ ሳይገነባ ይህንን የክረምት ወቅት ማሳለፍ፣ ጠላት ራሱን አጠናክሮ እንዲመለስና በበጋው ወቅት ወራሪ ኃይሉ ሰፊ ጥቃት እንዲሰነዝር በር የመክፈት ያህል እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው። አመራሮቹ ከትግሉ መነሻ ዓላማ ወጥተው በግላዊና በቡድናዊ ፍላጎት የታወሩበት ነባራዊ ሁኔታ፣ ትግላችንን ወደ ስጋትና ገደል አፋፍ እየገፋው ይገኛል። በታላቅ መስዋዕትነት የተገነባውን ሕዝባዊ አመኔታ በገዛ እጃቸው እየሸረሸሩት፣ በየመገናኛ ብዙኃኑ የሚደረጉ እርስ በርስ የሚያዋርዱ መግለጫዎች እና የሥልጣን ሽሚያዎች የሕዝቡን ልብ የሚሰብሩና የሰማዕታትን አፅም የሚያስቆጡ ናቸው። ፋኖ ማለት የሕዝብ ልጅ፣ የሕልውና መከታና የፍትህ አለኝታ እንጂ የጥቂት ግለሰቦች መጠቀሚያ ወይም የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ ሊሆን አይገባም። በውጭም ሆነ በውስጥ ያሉ አመራሮች ይኸው አጥፊ አካሄዳቸው ትግሉን ሙሉ በሙሉ አደጋ ላይ እየጣለ መሆኑን ተረድተው ከአሁኑ ካልተታረሙና ድርጅታዊ ቁርጠኝነት ካላሳዩ፣ የታሪክ ተጠያቂነቱ እጅግ ከባድ ይሆናል። ስለሆነም፣ ይህንን የተደቀነ አደጋ ለመቀልበስ እና የሕልውና ትግሉን ወደፊት ለማሻገር አጠቃላይ ደጋፊው፣ የውጭው ዲያስፖራ፣ በግንባር የሚፋለመው ፋኖ እና መላው የአማራ ሕዝብ በአንድ ድምፅ ጥያቄ ሊያነሳና በቃ ሊል ይገባል። ሕዝቡና ድጋፍ ሰጪው ኃይል ዕርዳታና ድጋፍ መስጠቱን ከማዕከላዊ አንድነትና ከጠራ ድርጅታዊ መዋቅር መፈጠር ጋር ማያያዝ ይኖርበታል። አመራሮቹ በበላይ ዘለቀ እዝ፣ በቴዎድሮስ እዝ እና በሌሎችም ቀጠናዎች ያሉትን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ኃይሎች በአንድ የጋራ የፖለቲካ ቢሮ እና ማዕከላዊ ዕዝ ሥር በፍጥነት እንዲያደራጁ፣ ካልሆነ ግን ቦታቸውን ለተተኪና ለበሰሉ የሕዝብ ልጆች እንዲለቁ በጽናት መጠየቅ አለበት። ጊዜው የቃላት ድርደራ ሳይሆን የቁርጠኝነትና የተግባር ወቅት በመሆኑ፣ ትግሉን ከድርጅታዊ መበታተን አውጥቶ ወደ ተቋማዊ ልዕልና ማሸጋገር የመላው ሕዝብ እና የፋኖ አባላት አጣዳፊ ታሪካዊ ግዴታ ነው። ትግላችን ያሸንፋል!