tgindex
Addisu Derebe

ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉኝ "ዘጠኙንም ግባ በሉት" የምል ኩሩ አማራ ነኝ!

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
8 721
+5 за 2 дн.
Сутки
+1
+0,01%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
3 531
24 постов
Вовлечённость
40,5%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 24
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 322
1/48двое суток
1 515
1/72трое суток
1 633

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14 авг.1 491815

    ጉዳችን ፈላ¡ ዲና ከዘመተማ አንተርፍም😂😂😂

  • 8 авг.3 007361

    መረጃ ቴሌቪዥንን ይደግፉ ፤ ቀጠሮ ይያዙ!

  • 22 июл.4 707774

    🎯 ፍትሐዊው ባለ ሚዛን! ​(አዲሱ ደረበ) ​የአማራ ሕዝብ ሁሌም ቢሆን ፍትሐዊ፣ ባለሚዛንና ሥርዓት አዋቂ ሕዝብ ነው። ለመንግሥት፣ ለሕግና ለመንግሥታዊ አሠራር ያለው ቀናኢነትና አክብሮት ለዘመናት የጸና ቢሆንም፣ ይህ በጎ እሴቱ ግን ግፍና ጭቆና በእርሱና በወገኖቹ ላይ ሲጫኑ እጁን አጣጥፎ እንዲቀመጥ አድርጎት አያውቅም። ዛሬማ ይልቁን በአማራዊ ማንነቱ ላይ የህልውና አደጋና የዘር ማጥፋት ጥቃት ተደቅኖበት እንዴት ዝም ይላል? ወትሮም ቢሆን ኢ-ፍትሐዊነትንና ጥቃትን እምቢ ለማለትና ለመፋለም ቦዝኖ የሚያውቅ ሕዝብ አይደለም! ​እውነቱ አሁን እንደሚታየው ነው፤ እንኳን አሁን መላው አማራ በየአቅጣጫው አለሁ ብሎ በአንድነት ተሰልፎ ይቅርና፣ ወትሮም ቢሆን በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በአጥቢያው ተደራጅቶ ግፈኞችንና ወራሪዎችን ለመታገል አንዲት ሰከንድ የማያመነታ ብርቱና ኩሩ ሕዝብ ነው። የታሪክ መዝገብ ለዚህ ሕያው ምስክር ነው፤ የፋሽስት ጣሊያንን እብሪትና ወረራ፤ ዘመናዊ የጦር መሣሪያና የመርዝ ጋዝ ሳይበግረው ዱር ቤቴ ብሎ ተፋልሟቸዋል። በቀደሙት ስርአቶች ሁሉ የመሬት ግብር ጭቆና በበረታበት ወቅትም፣ የማይከሰሱና የማይጠየቁ የሚመስሉትን መሳፍንቶች አልገብርም ብሎ በመሬት ግብር እምቢተኝነት አንቀጥቅጧቸዋል። በአህጉር ደረጃ ገናና ስምና ግዙፍ የጦር ግንባር የነበረውን የደርግን መራር ግፍና ቀይ ሽብር የመታገልና የመቋቋም ታሪካዊ ውርስ ያለው ነው፤ ለዚህም የጀግኖች ምድር አቸፈር፣ በለሳና ሰቆጣ ሕያው ምስክሮች ናቸው። እንዲሁም የወያኔ ኢሕአዴግን ዘረኛ አገዛዝ ከዘረኝነት፣ ከጠባብነትና ከመድሎ እንዲወጣ ያለ ምንም ፍርሃትና ተሸማቃቂነት በአደባባይ የተጋፈጠውና የታገለው ይኸው ሕዝብ ነው። ​ዛሬማ መደራጀት፣ መቀራረብና በጋራ የአማራነት ጉዳይ ላይ በጋራ መሰለፍን ዘመኑም፣ የታሪክ አጋጣሚውም ፈቅዶለታል! ትናንት የፋሽስት ጣሊያን የመርዝ ጋዝ ያልበተነውና ያላበረከከው ሕዝብ፣ ዛሬ በፋሽስቱ አብይ አሕመድ ድሮን በፍጹም አይንበረከክም። የደርግን አሰቃቂ ቀይ ሽብር በጽናት የተሻገረው አቅሙ፣ በዛሬው ገዢ ቡድን የዘር ማጥ*ፋት ዘመቻ አይፈታም። የወያኔ የትጥቅ ማስፈታት አዋጅና በሐውልት ማቆም አንገት አስደፊነት ተግባር ያልተሰበረው ወኔ፣ በዛሬው የብአዴንና የአገዛዙ ሱሪ የማስፈታት ዘመቻ ከቶ ድል አይደረግም። ​ጥቅሙን፣ ጉዳቱንና ክብሩን አሳምሮ የሚያውቅ፣ ፍትሐዊ ባለሚዛን የሆነው የአማራ ሕዝብ—ትናንት ጅራፍ እያጮኸ ያልተሰማውን አጠቃላይ ብሶቱን፣ ዛሬ በእውነተኛው የፋኖ ክንድና በጥይት አረር እየታገለ፣ መብቱንና ሕልውናውን እያስከበረ ይገኛል። ከትናንት እስከ ዛሬ ባልተለወጠው የገዢዎች ክፋት፣ ሴራና የወገናችን መራር አኗኗር ውስጥ አንድ ቋሚና የማይናወጥ ትልቅ እሴት አለ፤ እርሱም የአማራ ሕዝብ እምቢ ባይነትና የማይበገር ወኔ ነው! ​ድል ለአማራ የህልውና ትግል! 🎯

  • 22 июл.3 5631192

    መሐል አዲስ አበባ ሆኜ ከአገዛዙ ጋር እንዲህ ስተናነቅ የብአዴን ከዳሚ የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ ላይ አማራነትን ሊያስተምሩኝ ሲዳዱ እንደማየት ያለ ነውር የለም! ብቻችንን ነበርን ፤ አሁን እልፍ ሆነናል! ይኸው ነው!

  • 21 июл.3 417801

    🎯 የአማራነት ጽኑ አለት አርበኛ ስለሺ ከበደ! ​(አዲሱ ደረበ) ​በትግል አውድማ ላይ ከሁሉ በላይ የሚያስደንቀኝና ልቤን የሚነካው፣ ስማቸው በየሚዲያው በጉልህ ሳይጻፍ ነገር ግን በላብ፣ በደምና በአጥንታቸው ትልቅ ታሪክ የሚሠሩ ጥንቅቅ ያሉ እውነተኛ ጀግኖች መኖራቸው ነው። አርበኛ ስለሺ ከበደ ለእኔ ተራ የትግል አጋር አይደለም፤ አብሬው መራራውን የትግል ጽዋ የተቀበልኩት፣ በርካታ ዋጋዎችን የከፈልንበትና ወንድምነቱን በተግባር ያረጋገጠልኝ የቁርጥ ቀን ጀግናዬ ነው። ​የስለሺ የአማራነት ተጋድሎ የትናንት እና የዛሬ ትኩስ ታሪክ አይደለም። በወያኔ የጨለማ ዘመን አማራነትን ቀና ለማድረግና የሕዝባችንን ክብር ለማስጠበቅ ሲታገል፣ በአስፓልት ላይ እስከመጎተትና እስከ ከባድ ግርፋት ድረስ አሰቃቂ እንግልቶችን አስተናግዷል። ወጣትነቱን ሙሉ በሙሉ ለአማራነት ለመገበር ወደ ኤርትራ በረሃ ወርዶ፣ በአዴሃን ውስጥ ከአባልነት እስከ አመራርነት ድረስ በጽናት ታግሏል። ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰ በኋላም ቢሆን፣ እንደ አንዳንዶቹ አጋጣሚ ጠባቂዎች በብአዴን የጥቅም ድርጎ ሳይደለልና ሳይሸጥ፣ ስለ አማራነት መራራውን መንገድ መርጦ ተንከራቷል፤ በሰኔ 15ቱ አሰቃቂ ሁነትም በእስር መማቀቁ የታወቀ ነው። ​ከእስር በኋላ ከእኔ ጋር በአካል ተገናኝተን፣ ከብዙ ጥልቅ ምክክሮች በኋላ በጋራ በፈጠርነው የህቡዕ አደረጃጀት የጠላትንና የብአዴንን ጉሮሮ ያነቀ፣ በርካታ አስደናቂ ጀብዱዎች የተፈጸሙበት ትልቅ ምዕራፍ ነበር። የእርሱ እምቅ አቅምና የአማራነት ቁጭት በእውነት ልዩ ነው። ወታደራዊና ፖለቲካዊ እውቀቱን ከቁጭት ጋር አዋህዶ የያዘ ጀግና ጠበብት ነው ስለሺ። ክንዱ አይዝልም፤ እኔ ራሱ አንዳንዴ በብዙ ውጣ ውረድ ደከም ያልኩ ሲመስለው፣ ያለመሰልቸት በሞራልና በትግል ወኔ በመወትወትና በማነቃቃት ወንድምነቱን በተግባር አሳይቶኛል። ያቀደውን ነገር መሬት ላይ አውርዶ በተግባር ሳይፈጽም እረፍት የሚባል ነገር አያውቅም። ​የጎጃምን ምድር ብትመለከቱ፣ እርሱ ያልረገጠው አንድም የገጠር ቀበሌ የለም። ከአባይ ሸለቆ እስከ ሶማ፣ ከየጁቤ ኮርክ እስከ ቡሬ ቁጭ፣ ከሞጣ እስከ ደንበጫ፣ ከዳንግላ እስከ መተከልና አቸፈር ድረስ በእግሩ አዳርሶ በርካቶችን አሰልጥኗል፣ አስታጥቋል፣ ለአብዮት አብቅቷል። በግል ጥረቱ ብቻ ከ85 በላይ ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎችን በገንዘቡ እየገዛ ወገኖቹን ታጣቂ ያደረገ ልባም ነው። በሕዳር 2016 ዓ.ም በዳንግላ ወረዳ፣ ጫራ ላይ ከ1170 በላይ ብቃት ያላቸውን ፋኖዎች አሰልጥኖ፣ ከተከታታይ ንቅናቄዎች በኋላ ዛሬ የምንኮራበት የሰከነና የጸና መደበኛ የፋኖ ጦር እንዲኖረን ያደረገው ይኸው አርበኛ ነው። የታዋቂው የቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ዋና አዋላጅም እርሱ ነው። ​ከሁሉም በላይ ደግሞ በጠላት ሴራና በእነ ሰማ ጥሩነህ ይቀነቀን የነበረውን እኩይ የአገው ሸንጎ አጀንዳ የበጣጠሰበትና ያከሸፈበት ጀግንነቱ ሁሌም ያስደምመኛል። የጎጃም አገው ምድርንና ጃዊ መተከልን ከብአዴን እኩይ ሴራ አላቆ፣ ወደ አማራነት ትግል ማዕበል አዋህዶ ያስገባቸው የቁርጥ ቀን አርበኛ ነው። ከአዲስ አበባ እስከ ደብረ ማርቆስና ባሕር ዳር ድረስ የባንዳዎችን አንገት የሚያስደፋ፣ የቴዎድሮስ ዕዝን አንድነት ለመገንባት ሌት ተቀን የደከመና ለዛሬው ሕዝባዊ ተጋድሎም በፊተኝነት የቆመ የሕዝብ አለት ነው። ​እውነት ለመናገር፣ የነዚህን መሰል ጀግኖች ተጋድሎ ስመለከት አሁንም እጅግ ይደንቀኛል። ጀግናን መፍጠር ብቻ ሳይሆን፣ የተፈጠሩ ጀግኖችን መጠበቅና መንከባከብም ልምዳችን ሊሆን ይገባል፤ ምክንያቱም ያለ መሪና ያለ መስዋዕትነት የሚመጣ ድል የለምና! አርበኛ ስለሺ ከበደ በርታልኝ አንበሳው! ድል ለአማራ የህልውና ትግል! 🎯

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 21 июл.2 3506

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 июл.4 2782

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 июл.4 4542

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 июл.4 3112

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 июл.4 110342

    እናንተ የዐማራ ህያው ጀግናቻቸን ሆይ ፦ የተሰዋችሁለትን አላማ ከግብ እናደርሳለን! ደመቀ የተባለው ገረድ ደማችሁን ረግጦ ለዘረ-ፈጁ ስርአት በመገበር የተሰዋችሁለትን ህዝብ እየፈጀ መሆኑን ብታዩ ምን ይሰማችሁ ይሆን? በአማራ ልብ ውስጥ ለዘለአለም ታትማችሁ ትኖራላችሁ!

  • 11 июл.3 779314

    🎯 በሰማዕታት አርበኞቻችን ስም የነገደው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ክህደት! ​(አዲሱ ደረበ) ​በትግል ውስጥ ከሁሉ በላይ የሚያስጠላውና ታሪክን የሚያቆሽሸው፣ የጀግኖች መስዋዕትነት የፈጠረውን ወርቃማ የታሪክ እጥፋት ጥቂት ግለሰቦች በመንጋ ጩኸትና በማስመስል ነጥቀው ለግል ዝናቸውና ለሥልጣን ማቆያነት ሲጠቀሙበት ማየት ነው። ዛሬ በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ላይ ትልቁን ክህደትና ውርደት እየፈጸሙ ያሉ አግበስባሾች መሸሸጊያቸው ሲናጋ፣ የሰማዕታትን ደም አርክሰው ራሳቸውን ነቢይና ሙሴ አድርገው ለመሳል በአደባባይ ሲያቅራሩ መስማት ነውርም፣ ክህደትም ነው። ከነዚህ መካከል በቅርቡ በአንድ ማኅበራዊ ድህረ-ገጽ ላይ የሐምሌ 5ን ዝክረ-ሁነት አስመልክቶ የሰጠው ቃለ-ምልልስ በሚያነጋግሩና በሚያጸይፉ ጉዳዮች የታጨቀው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ዋነኛው ማሳያ ነው። ​የታሪክን እውነት ፍንትው አድርገን እንናገር ከተባለ፣ ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም በጎንደር ከተማ የተነሳውና ሕወሓትን ያንቀጠቀጠው ያ ታሪካዊ ተጋድሎ የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የግል ትግል ፈጽሞ አልነበረም! ያ ተጋድሎ ከወገራ፣ ከዳባት፣ ከአርማጭሆ፣ ከጠገዴ፣ ከሰሜን ጃንአሞራና ከተለያዩ የጎንደር አጎራባች ወረዳዎች የመጡ አንበሶችና የጎንደር ወጣቶች ክንድ የወለደው ሕዝባዊ አብዮት ነበር። ከጎንደርም አልፎ ተጋድሎው በባሕር ዳር፣ በደብረ ታቦር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በወልድያ፣ በደሴ፣ በአምባ ጊዮርጊስ፣ በዳንሻ፣ በሽንፋ ቋራ፣ በወልቃይት ሑመራና በሁሉም የአማራ ከተሞች የተቀጣጠለ ሁለንተናዊ የአማራነት ቁጣ ነበር። ​ይህንን ሕዝባዊ ማዕበል መሬት ላይ ሆነው በዋናነት የመሩትና ደማቸውን ያፈሰሱት እነ ዋዋ ጎቤ፣ አርበኛ መሣፍንት፣ አርበኛ ሙሃቤ፣ አርበኛ ቃቁ፣ አርበኛ ሞላጃው፣ አርበኛ ሰጠኝ ባብል፣ አርበኛ ሲሳይ፣ አርበኛ ሙላው፣ አርበኛ ዘውዱ፣ መቶ አለቃ ደጀኔ፣ አርበኛ ታጠቅ ጆርኒ፣ አርበኛ አበበ፣ አርበኛ አራጋው፣ አርበኛ አበራ ጎባው፣ አርበኛ ዘርአይ አዝመራው፣ አርበኛ ታያቸው፣ አርበኛ ስለሺ፣ አርበኚት ያየሽ፣ አርበኛ ሕርያቆስ እና ስማቸውን ያልዘረዘርኋቸው እልፍ አእላፍ የቁርጥ ቀን ጀግኖች ሆነው እያለ፣ ያንን አጋጣሚ ተጠቅሞ በማኅበራዊ ሚዲያና በመንጋ ጩኸት የገነነው ደመቀ ዘውዱ ዛሬ የጀግኖችን ትግል ነጥቆ “እኔ እግዚአብሔር የመረጠኝ የአማራ ሙሴና ዳዊት ነኝ” ለማለት ደፍሯል። ለመሆኑ የአማራን ሕዝብና የፋኖን ትግል በአደባባይ የካደ፣ ራሱን ለአገዛዙ የገበረ ካድሬ እንዴት የአማራ ሙሴ ሊሆን ይችላል? ይህ ፍጹም የታሪክ ስርቆትና ነውር ነው! ​ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ተብዬው ልፍድድ በአሁኑ ሰዓት በወልቃይት ጉያ ተወሽቆ የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ ትግል ሰርክ ሲያንቋሽሽና ሲያረክስ የሚውል የአገዛዙ አገልጋይ ነው። “የደራን ጉዳይ ማንሳት ከኦሮሚያ ጋር ያጋጨናል” ብሎ በአደባባይ የተናገረው፣ የኦሮሙማው ሥርዓት እንዳይቀየምበት ያጎበደደው እኮ ይኸው ደመቀ ነው። “ፋኖ መከላከያን መውጋቱ ክህደት ነው” ብሎ የደሰኮረው፣ ዕለት ተዕለት በድሮንና በከባድ መሣሪያ ሕዝባችንን የሚጨ*ፈጭ*ፈውን የፋሽስቱን አብይ አሕመድን ጦር ያንቆለጳጰሰው ይኸው ኮሎኔል ነው። “ፋኖ የራሱ ዓላማ የለውም፤ የውጭ ኃይሎች ተላላኪ ነው” ብሎ የፋኖን ክቡር ስም ያቆሸሸውና ያቀረሸው ይኸው የብልፅግና ሎሌ ነው። እነ ዋዋ ጎቤና ሰጠኝ ባብል ወድቀው ያመጡትን ድል፣ ዛሬ ላይ ቆሞ “ብልፅግናን ዋጋ ከፍለን ያቆምነው እኛ ነን፣ ድርጅታችን ነው” ብሎ የጀግኖቻችንን ሰማዕትነት ያረከሰ የእንግዴ ልጅ ነው ደመቀ! ​ደመቀና መሠሎቹ የቆሞ-ቀር ፖለቲካ አራማጆች በመሆናቸው፣ ለእነሱ የሚያሳስባቸው የሟች አማራ ማንነት ሳይሆን የገዳዩ ማንነት ነው። አብይ አሕመድና መዋቅሩ በምድር ኃይልና በአየር ኃይል አማራን በገሃድ በዘር ማጥ*ፋት ወንጀል እየፈጁት፣ በዓይናቸው እያዩ ለሥርዓቱ ድጋፍ የሚሰጡት ገዳዩ ሕወሓት ስላልሆነ ብቻ ነው። ሕወሓት አይሁን እንጂ፣ ማንም መጥቶ አማራን ቢያ*ር*ድና ቢያ*ጠፋ ቅንጣት ታህል የማይገዳቸው፣ የደም ነጋዴዎችና እንግዴዎች ማለት ደመቀና መሠሎቹ ናቸው። ​በአማራ ምድር ወልቃይት በደመቀ ዘውዱ የተመለሰና በእሱ ሚሊሻ ብቻ ተጠብቆ የኖረ የሚመስለው ድውይና አላዋቂ ካለ፣ እስኪነስረው ድረስ እንነግረዋለን። ወልቃይትም ሆነ ሌላው የማንነታችን መለያ የሆነው የአማራ አፅመ-ርስት በዘላቂነት ተከብሮ የሚኖረው፣ ዛሬ በየጫካውና በየተራራው እየተዋደቀ ባለው በጀግናው የፋኖ ክንድ እንጂ፣ ዕድሜ ልኩን ለወያኔ ሲገረድ ኖሮ እስከ ኮሎኔልነት ማዕረግ ደርሶ፣ ዛሬ ደግሞ ለዘረ-ፈጁ የአብይ አሕመድ ሥርዓት በሚያጎበድድ ወስላታና እርሱ በሚመራው የነተበ ሚሊሻ አይደለም። ​ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ የሰማዕታት ጀግኖቻችን እውነተኛ ደም አለበት። ዋጋ የተከፈለበትን የአማራን ሕዝብ ትግልና አደራ በአደባባይ ክዷል። ነገር ግን ጊዜው ሲደርስና የአማራ ሕዝብ ነፃነቱን በተግባር ሲያረጋግጥ፣ ደመቀ ዘውዱ እንደማንኛውም የአገዛዙ ባንዳና ካድሬ የሕዝብን የፍትሕ ጽዋ ይቀምሳል። ከታሪክ ፍርድ አያመልጥም፤ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው! ​ድል ለአማራ የህልውና ትግል! 🎯

  • 11 июл.2 729161

    видео или голосовое, без подписи

  • 9 июл.3 999801

    🎯 የትውልዱ መልክና ግርማ! ​(አዲሱ ደረበ) ​በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሳይንስ እሳቤ ውስጥ፣ የታሪክን አቅጣጫ የሚቀይሩና የሕዝቦችን የህልውና መስመር አድሰው የሚጽፉ ትውልድ አሻጋሪ መሪዎች በዘፈቀደ አይፈጠሩም። እሳቤያቸው ከዘመኑ የቀደመ፣ ፅናታቸው ከብረት የጠነከረና ልባቸው እንደ ውቅያኖስ የሰፋ መሪዎች የክፍለ-ዘመናት እምቅ የጭቆና ብሶትና የሕዝብ መቅበዝበዝ የወለዳቸው የታሪክ ስጦታዎች ናቸው። እነዚህ መሪዎች የሕዝባቸውን የትግል ሰንሰለት አስተሳስረው ወደ ድል ማማ የሚያሻግሩ፣ በፖለቲካዊ ብስለት፣ በወታደራዊ ሳይንስ፣ በጂኦ-ስትራቴጂካዊ ግንዛቤና በጥልቅ ታሪካዊ መረዳት የተገነቡ ሁለንተናዊ መሐንዲሶች ናቸው። በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ውስጥ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሊቀመንበር የሆነው ራስ-አርበኛ ዘመነ ካሴ የዚህ ሳይንሳዊ ሀቅ ሕያው ማሳያ ነው። ​ራስ-አርበኛ ዘመነ ካሴ ተራ የትግል አጋጣሚ የፈጠረው መሪ አይደለም። ሙሉ ወጣትነቱን፣ ዕድሜውን፣ አቅሙንና መላው ቤተሰቡን ለአማራነት እውነት ያሰለፈ፣ በትግል እቶን እሳት ውስጥ ተፈትኖ የወጣ ጥንቅቅ ያለ ምሁርና አብዮተኛ ነው። አማራነት እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ሕዝባችን በአገር በቀል ፋሽስቶች የታሪክ ፍርደኛ ተደርጎ ከተፈረጀበት አስከፊ ዘመን መባቻ ጀምሮ፣ ራስ ዘመነ ካሴ ከኤርትራ በረሃዎች አንስቶ እስከ አሁኑ አብዮታዊ ትግል ድረስ አማራነትን ሰብኳል። እልፍ የተኛንና የተሸማቀቀን ሕዝብ በጥልቅ የፖለቲካ ንቃተ-ህሊና ቀስቅሶ አነቃቅቷል። የእሱ አስተዋይና ስልታዊ የአብዮት ጥሪዎች፣ አያሌ የቁርጥ ቀን ወጣቶችን የነፃነት ትጥቅና ሞራል አስታጥቀው የትግሉ ግንባር ቀደም ተሰላፊ አድርገዋቸዋል። ​በአብዮታዊ ትግል ውስጥ የላቁ መሪዎች የሚለኩባቸው መሠረታዊ መለኪያዎች አሉ፤ እነሱም ጽናት፣ ቻይነት፣ ስልታዊ ምሁርነትና ተራማጅ አመራርነት ናቸው። ዘመነ ካሴ በዙሪያው ባሉ ታጋዮችና ሕዝቡ ዘንድ “አባ መቻል” የሚባለው ዝም ብሎ አይደለም፣ አእምሮው፣ ልቡና ትክሻው በእጅጉ ሰፊ በመሆኑ ነው። መከራን፣ እንግልትን፣ ክህደትን፣ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችንና የትግል ስንክሳሮችን ሁሉ ያለ ምንም ድካም ተሸክሞ ያሻግራል። እርሱ ያችን አይነ-ግቡ ሳቅ እየሳቀ፣ የጠላትን ሰይፍና የውስጥ ደካሞችን ሴራ ሁሉ በትዕግሥት አክሽፎ ያልፋል። የከፋው አይመስል፤ የደከመው አይመስል፤ የራበው አይመስል! ሊጥሉት፣ ሊያወርዱትና ስሙን ሊያጠፉ የሞከሩ የውስጥና የውጭ አተሎች ሁሉ ወርደው ተፈጠፈጡ እንጂ፣ ራስ-አርበኛ ዘመነ ካሴን የነቀነቀውና ከዓላማው ያናወጠው አንድም ኃይል የለም። በእሱ ቦታ ብሆን ብዬ አሰብኩት እኮ! እውነት ለመናገር፣ ለአንድ ወር እንኳ በዚህ ከፍታ መታገልና፣ ያንን ሁሉ ማዕበል ተቋቁሞ ሕዝብን ማታገል አይቻልም፤ ኧረ ፍጹም አይታሰብም! ​በዓለም ታሪክ ውስጥ የሕዝባቸውን ሕልውና ያስጠበቁና ከጥፋት የታደጉ ታላላቅ አብዮተኞች በሙሉ የዘመነ ካሴን ዓይነት መዋቅራዊና ስነ-ልቦናዊ ግርማ ነበራቸው። ዘሜን በታሪክ መድረክ ከታዩት እንደነ ጆርጅ ዋሽንግተን፣ ጋሪባልዲ፣ ፊደል ካስትሮ እና ማኦ ዜዱንግ ካሉ ግዙፍ የአብዮት መሪዎች ጎን አሰልፈን ስንመለከተው የትግላችንን መዳረሻ እናውቃለን። ሀገራቸው ልትበታተን ስትቃረብ ወታደራዊና ጂኦ-ፖለቲካዊ ስልትን በመጠቀም የቱርክን ሕልውና እንደታደገው እንደ ሙስጠፋ ከማል አታቱርክ፣ ወይንም የአፓርታይድን ስቃይና እሥራት በትዕግሥትና በቻይነት አሸንፎ ሕዝቡን ወደ አንድነት እንደመራው እንደ ኔልሰን ማንዴላ ሁሉ፣ ዘሜም በጥልቅ ስልታዊ ምሁርነቱ የውስጥ ቁስሎችን እያከመ ትግሉን ወደፊት ያስኬዳል። ሙሉ ሕይወታቸውንና ወጣትነታቸውን ለሕዝባቸው ነፃነት እንደገበሩት እንደነ ሆ ቺ ሚን እና ቼ ጉቬራ ሁሉ፣ የዘሜም የኤርትራ በረሃዎችና የአማራ ተራሮች ስንክሳር ይህንኑ አብዮታዊ ታማኝነትና የትውልድ መሪነት በተግባር ያሳያል። ​እንደ ዘመነ ካሴ ዓይነት ትውልድ አሻጋሪ መሪዎች በአመቺ ሕይወት ውስጥ አይበቅሉም፤ በትግል እቶን፣ በከፋ መከራ፣ በሕዝብ ዕንባና በጠላት የጭካኔ ቀንበር ውስጥ ተፈትነውና ተቅንብበው ነው የሚወጡት። እንዲህ ዓይነት መሪዎች አንዴ ከተፈጠሩ በኋላ፣ ሕዝቡ እንደ ዓይን ብሌኑ ሊጠብቃቸውና ሊንከባከባቸው ይገባል። ምክንያቱም የጠላት ዋነኛ ስትራቴጂ የሕዝብን ኮምፓስና መሪ ማጥፋት በመሆኑ ነው። የእንዲህ ዓይነት መሪዎች መኖር የትግሉን ዕድሜ ያሳጥራል፣ መስዋዕትነትን ይቀንሳል፣ ድልን ያረጋግጣል። ​ራስ-አርበኛ ዘመነ ካሴ ሆይ! አንተ ስላለኸንና ትግሉን በሳይንሳዊ፣ በተራማጅና በበሰለ አመራርነትህ ስለምትመራው የታደልን ነን። ያቺን የአሸናፊነት ሳቅህን እየሳቅህ፣ መከራውን ሁሉ በትከሻህ ተሸክመህ፣ የአማራን ሕዝብ ዘላለማዊ ህልውና እና ነፃነት በተግባር እንደምታረጋግጥ ሙሉ እምነት አለኝ። ታሪክ ያከበረህ መሪ ነህ፤ ትውልድም በአክብሮት ይጠብቅሃል! ​ድል ለአማራ የህልውና ትግል! 🎯

  • 9 июл.3 09513

    видео или голосовое, без подписи

  • 28 июн.5 216593

    አንዳንድ ነገሮች‼️ አርበኛ ዘመነ ካሴ! አለም ፊቱን ዞሮበት፥ ወይንም እንደፍጥርጥሩ ለእጣፋንታው ትቶት "ረስቶት" እያለ "መተን ቀብረነዋል" የተባለው የአማራ ህዝብ "መቃብር" ፈንቅሎ ብድግ አለ። ያለ አንዳች መካሪና ተቆርቋሪ፥ ያለ አንድ ሰው ሃሳብ አበዳሪ ከመከራው ተምሮ፥ ከራሱ መክሮ አማራ የራሱን አቢዮት ራሱ ፈጠረ።ሲነሳ በደነገጡት ጠላቶቹ ፊት ራሱን በፍጥነት አደራጅቶ የህልውና ትግሉን ጀመረ።እፍኝ የማትሞላ ተተኳሽ በመቶ ሽዎች ብር እየገዛ፥ ታጣቂም አስታጣቂም ራሱ ሆኖ ወደ ራሱ ግብ መገስገስ ቀጠለ። እነሆ ሶስት አመት አለፈው። ትልቁ ብሄራዊ ሃብት ሰው ነው። የሁሉም ነገር... የፖለቲካውም፥ የታንኩም፥የዲፕሎማሲውም ፥ የርእዮተ አለሙም ግርግር ማእከሉ፥ መቋጫው ሰው ነው። ለሰው ልጆች የተሻለ ነገር ለማምጣት የሚደረግ ነው። የራሱን ህዝብ በሰማይም በምድርም እሳት አሰማርቶ የሚያነድ ዘረፈጅ ሥርዐት ስለ ብሄራዊ ክብርና ሉአላዊነት የት ያውቃል? ስለ ሃገር ለማውራት ሞራሉስ ከየት ይገኛል?አንገቷ ላይ ቆሞ እያነደዳት ያለችን ሃገር እወዳታለሁ ሊለን ይሞክራል። የጥፋት ተልእኮ ይዞ ሃገር እያቃጠለ ሳያፍር ሌላውን ሃይል በተላላኪነት ሊከስ ይዳዳዋል። ለግብፅ መላላክን፥ ለፕሬዝዝዳንት ኢሳያስ መሽቆጥቆጥን፥ ለህወሃት መንበርከክን አብይና ቡድኑ እንጅ ፋኖ አያውቀውም። በኛ በኩል የአለም ጥቅሞች ሁሉ ተሰልፈው ቢመጡ፥ መዳፋችን ላይ ቢቀመጡ አንዲት ግራም የአማራን ህዝብ ጥቅም አሳልፈን አንሰጥም። የአማራ ህዝብ ህልውና፥ ጥቅሙና ምኞቱ ለድርድር አይቀርቡም፥ "ቅዱስ" ናቸው። ቅዱሱን የሚነካም የሚያስነካም ማንም የለም።ነገር ግን ካለፉት ረጅም አመታትም ፥ከራሱ ከብልፅግና ስህተትና ውደቅትም ተምረን ከቀጠናዊና አለምአቀፋዊ ልውጥውጡ የማንም ወኪል ሳይሆኑ መጠቀምን እናውቅበታለን።በሊማሊሞ ገደል አናት በተወጠረ ገመድ ላይ አይናችን ታስረን እንኳን አመጣጥነን መራመድ እና ወደ ነገ መሻገር እንችላለን። ይህ መከራ ከእድሜው በላይ ያስተማረው ትግል ነው። ስለሆነም በፍፁም አንሳሳትም። ከኢትዮጲያውያን ሃይሎች ጋር በጋራ መርፌ የመግዛት ተልእኮ እንኳን ቢኖረን የአማራ ህዝብ በይፋ ሳያውቀው የምንጓዘው አንድም እንኳን ስውር እርምጃ የለም። ጠላት ግን ይጮሃል። "ይህን ውሃ ምን ያስጮኸዋል ቢሉት፥ በውስጡ ያለው ድንጋይ" ብሎ መለሰለት አሉ። በዚህ ወቅት ብልፅግና የተባለ የኩሬ ቦይን የሚያስጮሁት "ድንጋዮች" ሁለት ናቸው፦ 1) ፍርሃት። አብይ የቀጠናውና የሃገር ውስጥ ሃይሎች ከተባበሩ እድሜዬ በአንድ እጄ እጣቶች ልክ የተቆጠሩ ናቼው ብሎ ስለሚያምን ደንግጧል። እናም ድንገት ጥቂቶችን አደናግሬ የማምሻ እድሜ ባገኝ ብሎ ሌት ተቀን ይጮሃል።ከሞት የማያድን ጩኸት። 2) ጦርነት። በአብይ አህመድ ስሌት የአማራ፥ የትግራይ፥ የአፋርና ሌሎች ህዝቦች ገና በበቂ አልደቀቁም። ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መድቀቅና መጥፋት አለባቼው። ይህ ይሆን ዘንድ ግን "ሰበብ " ያስፈልጋል። ስለሆነም አቅም አግኝቶ ነገ ወደ አንድ ተረኛ ህዝብ ቢተኩስ ለአለሙ የሚነግረው ሰበብ "ተባብረው ሊያጠፉኝ ሲሉ ራሴን ለመከላከል ጦርነት ከፈትሁ" ይሆናል ማለት ነው። ይኸው ነው። ይህ ትግል የአማራንና የሃገራችን ህልውናን የማረጋገጥ ትንቅንቅ ብቻ አይደለም፥ ቢያንስ ለሚቀጥሉት አምስት መቶ አመታት የጥይት ድምፅ የማይሰማ ትውልድ የመፍጠር ተልእኮም ነው። ብልፅግና ይወገዳል፥የአማራ ህልውና ይረጋገጣል። ኢትዮጲያ ለኢትዮጲያውያን የፍቅርና የደስታ ምድር ትሆናለች፥ ሰላም ትሆናለች። ክፋት ለማንም፥ በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ ፥አዲስ አስተሳሰብ፥አዲስ ተስፋ! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ሰኔ-21/2018 ዓ. ም! አርበኛ ዘመነ ካሴ!

  • 28 июн.3 5153

    видео или голосовое, без подписи

  • 28 июн.3 8963

    видео или голосовое, без подписи