Mesganaw k Endalk
Статистикаለፈጣን መረጃ እንዲሁም ለዕለታዊ ክንውኖች ወዳጅ ይሁኑ❗️መረጃዎችን ለማድረስ @mesgan27
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 800
- 1/48двое суток
- 916
- 1/72трое суток
- 988
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
📌 የአሻራ ሚዲያ አቋም፦ ከመረጃ ቴሌቪዥን ጋር የነበረን እውነተኛ የትግል ጉዞ! አሻራ ሚዲያ ከተመሠረተች እነሆ 8 ዓመታት ሆናት። ዋና መቀመጫዋን በኢትዮጵያ አድርጋ፣ አጠቃላይ የሀገሪቱን የፖለቲካ ውጣ ውረዶችና ፈተናዎች በቅርበት እየተጋፈጠች በሚዲያው ግንባር በቁርጠኝነት እየታገለች የምትገኝ፣ በአማራ ብሔርተኞች የተመሠረተች ሚዲያ ነች። መረጃ የሕዝብን ንቃተ-ሕሊና የሚገነባ፣ ድምፅ አልባ ለሆኑት ድምፅ የሚሆን እና የሕዝባችንን የፍትሕና የነፃነት ትግል አቅጣጫ የሚያሳይ ዋነኛ መሣሪያ ነው። ይሁን እንጂ ይህ የትግል ጉዟችን ቀላል አልነበረም። አሻራ ሚዲያ እውነቱን ስላወጣችና የሕዝብ ድምፅ ስለሆነች ብቻ በአገዛዙ በተቀነባበረና በታቀደ መልኩ የዩቲዩብ ቻናላችን ከ60 ጊዜ በላይ እንዲዘጋና ከዩቲዩብ እንዲወርድ ተደርጓል። ይህንን የአገዛዙን አስከፊ የሚዲያ አፈና እና የዲጂታል ሴራ ሰብረን ለመውጣትና ድምፃችንን ለማስተጋባት የቻልነው ግን በመረጃ ቴሌቪዥን (Mereja TV) በኩል ነው። በዚህ የመረጃና የህልውና ትግል ጉዞ ውስጥ፣ በተለይም የሕዝባችንን ብሶት አደባባይ በማውጣትና ለሕዝባዊ ትግሉ ሰፊ መድረክ በመሆን ረገድ መረጃ ቴሌቪዥን ያበረከተው አስተዋጽኦ የጎላና የማይተካ ነው። 🔷 የአሻራ ሚዲያ እውነተኛ ምስክርነትና ተሞክሮ ባለፉት አራት ዓመታት የመረጃ ቲቪ ቆይታችን፣ የምንፈልገውንና ለሕዝባችን ይጠቅማል ያልነውን ማንኛውንም ፕሮግራም ያለ ማንም አካል ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖ በነፃነት ስናስተላልፍ ቆይተናል። አንድ ቀንም ቢሆን ከመረጃ ቴሌቪዥን አመራሮችም ሆነ አዘጋጆች በኩል፦ • ❌ "ይህን ፕሮግራም ብቻ አዘጋጁ" • ❌ "ይህን አስተያየት በዚህ መልክ ስጡ" • ❌ "ይህንን አጀንዳ ይለፋችሁ" የሚል የኤዲቶሪያል ጣልቃ ገብነት ወይም ጫና ፈጽሞ ተፈጥሮብን አያውቅም። በተለይም ደግሞ የሶሻል ሚዲያ (የማኅበራዊ ሚዲያ) አማራጭ የሌለውንና የማይጠቀመውን ሰፊውን የማኅበረሰባችንን ክፍል ተደራሽ ለማድረግ፣ ዝግጅቶቻችንን ያለ ምንም የሰዓት ገደብ በሳተላይት እያስተላለፍን እንገኛለን። ተቋሙ ለተወሰነ ጊዜ ስርጭት ማቆሙን ከመረጃ ቲቪ አመራሮች ጋር ውይይቶችን አድርገናል። ስህተቶች ሲኖሩ በቅርበት እየተነጋገሩ አማራዊ ተቋማት እንዲጠናከሩ ማድረግ የሁሉም አማራ ኃላፊነት ነው።
📌መረጃ ቴሌቪዥን በስምንት ዓመታት የትግል ጉዞ፦ ተቋምን ከማፍረስ መገንባት፣ ከጫናዎች ባሻገር ያለው እውነት! ባለፉት ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ እጅግ ፈታኝና ውጣ ውረድ የበዛበት ነበር። በዚህ የትግል ጉዞ ውስጥ፣ በተለይም የፍትሕ፣ የነፃነት እና የህልውና ድምጽን በማስተጋባት ረገድ መረጃ ቴሌቪዥን (Mereja TV) ከፍተኛና የማይተካ አስተዋጽኦ አድርጓል። የብዙዎችን ብሶት አደባባይ በማውጣት፣ የተዳፈኑ እውነታዎችን በማጋለጥና ለሕዝብ ትግል መድረክ በመሆን የተጫወተው ሚና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ሆኖም፣ ይህ የተቋሙ ጉዞ አልጋ ባልጋ አልነበረም፤ በርካታ ፈተናዎችን፣ መንገራገጮችንና የውስጥ ጫናዎችን ያስተናገደበት ረጅም መንገድ ነው። መረጃ ቴሌቪዥን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የሚዲያ ባለሙያዎችና አክቲቪስቶች አብረውት ሠርተዋል። ከእነዚህም መካከል እነ ኢትዮ 360፣ ዘመድኩን በቀለ እና ሌሎችም የተለያዩ ግለሰቦች ይገኙበታል። ይሁን እንጂ፣ ጣቢያው አቅም እየገነባና ተጽዕኖ ፈጣሪነቱ እያደገ ሲመጣ፣ ከተቋማዊ ራዕይ ይልቅ የግል እና የቡድን ፍላጎቶች ማየል ጀመሩ። በተለያዩ ጊዜያት እነዚህ አካላት የየራሳቸውን የፖለቲካ ወይም የቡድን አጀንዳ በጣቢያው ላይ ለመጫን ሞክረዋል። የጣቢያው ዓላማ የሁሉንም ድምጽ ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ማስተናገድ ሆኖ ሳለ፣ "የእኛን ሀሳብ ብቻ አስተጋባ" የሚሉ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጫናዎች ጣቢያውን ሲያናውጡት ቆይተዋል። እነዚህ የፍላጎት ግጭቶች ጣቢያውን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ዋጋ እያስከፈሉት፣ አላስፈላጊ ውጥረቶች ውስጥ እንዲገባ አድርገውታል። ♦️የኢትዮ 251 ሚዲያ እውነተኛ ምስክርነት:- ተቋሙ በሌሎች አካላት "ጫና ያደርግብናል፣ አጀንዳ ይጭንብናል" በሚል ሲወቀስ ቢሰማም፣ ኢትዮ 251 ሚዲያ (Ethio 251) ባለፉት ሦስት ዓመታት ከመረጃ ቴሌቪዥን ጋር በነበረው የሥራ ቆይታ ያየው እውነት ግን ፈጽሞ የተለየ ነው። ኢትዮ 251 ሚዲያ ፕሮግራሞቹን አዘጋጅቶ ለመረጃ ቴሌቪዥን ሲያቀርብ፣ አንድ ቀንም ቢሆን ከመረጃ ቴሌቪዥን አመራሮችም ሆነ አዘጋጆች በኩል፡- "ይህን ፕሮግራም ብቻ አዘጋጁ"፣ "ይህን አስተያየት እንደዚህ አድርጋችሁ ስጡ"፣ "ይህንን አጀንዳ ተዉት" የሚል የኤዲቶሪያል ጣልቃ ገብነት ወይም ጫና ተፈጥሮበት አያውቅም። ይህ የሚያሳየው ተቋሙ ለሚዲያ ባለሙያዎች የሰጠውን የኤዲቶሪያል ነፃነት እና በልዩነት ውስጥ አብሮ የመሥራት ባህልን ነው። ይህ ማለት ግን መረጃ ቴሌቪዥን ፍጹም ነው፣ አሊያም በውስጡ ምንም ዓይነት የአሠራር ስህተቶችና ግድፈቶች አልተሠሩም ወይም አይሠሩም ማለት አይደለም። ተቋሙ ለወራት የተቋረጠ ጊዜ መቋረጡ ልክ አይደለም በሚል ከተቋሙ ባለቤቶች ጋር ተሟግተናል፣ በውስጡ የራሳቸውን ፍላጎት ለማንጠባረቅ የሞከሩ ሁሉ ነነሩ ወደፊትም ይኖራሉ፣ ይህን በተመለከተ ራሱ ተቋሙ ጠንካራ መተዳደሪያ ደንብ በማዘጋጀት የማስተካከል ኃላፊነተረ አለበት። መረጃ ቴሌቪዥን የሚዲያዎች መተላለፊያ አውታር ነው። በመረጃ ቲቪ የሚተላለፉ ዝግጅቶች በዋነኝነት ስህተት ከተሰራ መረጃ ቲቪ ተጠየቅ ቢኖርትበትም አብዛኛው ተጠየቅ የሚቀርበው ግን በአዘጋጆቹ ሚዲያ ነው። ማንም ሰው ወይም ተቋም ስህተት ሊሠራ ይችላል። ዋናው ጥያቄ ግን "ስህተት ሲፈጠር መፍትሔው ምንድን ነው?" የሚለው ነው። የትግል አጋር የሆነን የሚዲያ ተቋም፣ በታዩበት ጥቃቅን ስህተቶች ወይም በግለሰቦች አለመግባባት ምክንያት ለማፍረስ መነሳት የትግሉን ዐቢይ ዓላማ መሳት ነው። ስህተቶች ካሉ በእርጋታ እየታረሙ፣ አሠራሮች እየተስተካከሉ ተቋሙን ይበልጥ ማጠናከር እንጂ፣ ማፍረስ የጠላት አጀንዳ ማስፈጸሚያ ከመሆን አያልፍም። መገንባት ዓመታትን ይፈጃል፤ ማፍረስ ግን የአንድ ቀን ስሜታዊ ውሳኔ ነው። ለአማራ ሕዝብ ትግል የበርካታ ሚዲያዎች አስፈላጊነት ዛሬ ላይ መሬት ላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲታይ፣ የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እጅግ ወሳኝና የሞት ሽረት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ይህን መሰል ግዙፍ አገራዊና ሕዝባዊ ትግል ደግሞ በአንድ የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ ብቻ ሊሸፈንና ሊመራ አይችልም። ♦️የአማራው ትግል፡- አንድ ሳይሆን በርካታ የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ ጠንካራ የዲጂታል ሚዲያ አውታሮች፣ የሠለጠኑና ስትራቴጂካዊ የሚዲያ ባለሙያዎች ያስፈልጉታል። ያሉንን ጥቂት ተቋማት እያፈረስን የትግሉን ድምጽ ማፈን የለብንም። ይልቁንም መረጃ ቴሌቪዥንን ጨምሮ ያሉትን የሚዲያ ተቋማት መጠበቅ፣ ስህተታቸውን እያረሙ ማጠናከር እና ተጨማሪ አዳዲስ የሳተላይት ጣቢያዎችን በመክፈት የሕዝቡን ድምጽ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስተጋባት የዘመኑ ግዴታ ነው። ትግሉ የሚያሸንፈው ተቋማትን በማፍረስ ሳይሆን፣ ያሉትን በማጽናትና አዳዲሶችን በመገንባት ነው! #ማስታወሻ:- ባለፉት ዓመታት በተቋሙ ውስጥ እንደ ኢትዮ 251 ሚዲያ ስንሰራ ከኛ በኩል ጫና አልነበርብንም፣ ለተቋሙም የገቢ ማሰባሰቢያ ሲኖር ተገኝተን እናስተባብራለን እንጂ ክፍያ ተጠይቀን አናውቅም፣ ከመረጃ ቲቪም ምንም አይነት ክፍያ ተቀብለን አናውቅም።
ላለፉት ስምንት ዓመታት የሕዝብ አይንና ጆሮ ሆኖ ሲያገለግል የቆየው መረጃ ቲቪ በዘላቂነት ለማስቀጠል የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ተዘጋጅቷል። የበርካታ ሚዲያዎች የስርጭት መድረክ በሆነው መረጃ ቲቪ የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ በመገኘት በሚዲያው ዘርፍ የሚደረገውን ትግል ይደግፉ። Qr ኮዱን ስካን በማድረግ የመረጃ ቲቪ ቤተሰብ ይሁኑ!
ይህ በአፋብን ወታደራዊ ቃል አቀባይ በአርበኛ አበበ ሙላቱ ገጽ ነው። ይወዳጁት https://t.me/abeamoraw
የዘመናዊት ኢትዮጵያ መሠረት፣ የጥበብ እና የሉዓላዊነት አርማ፡ ጃንሆይ! ዛሬ፣ የዕድሜ፣ የጥበብ እና የሀገር ግንባታ ታላቅ ምሳሌ የሆኑት፣ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ 134ኛ የልደት በዓል ነው። «በጭንጫና በጠነከረ መሠረት ላይ የታነጸን ቤት፣ ዝናብ ቢዘንብ፣ ጐርፍም ቢጐርፍ፣ ነፋስም ቢነፍስ ገፍተው ሊጥሉት አይችሉም» እያሉ በታሪካቸው እንደገለጹት, እሳቸውም በዘመናቸው የሰሯቸው በርካታ የሀገር ግንባታ መሠረቶች እስከዛሬ ድረስ በታሪክ ማኅደር ውስጥ በታላቅ ክብር የሚታወሱ ናቸው። ኢትዮጵያን በአለም መድረክ ያስተዋወቁ፣ ዘመናዊ ትምህርት፣ ሕገ-መንግስት እና ተቋማትን በመዘርጋት ረገድ የማይተካ አሻራ ያሳረፉ ታላቅ ንጉስ። በንግሥናቸው ሀገሪቱን ከዘመናዊነት ጋር ለማስተሳሰር እና ተቋማዊ መሠረት ለመጣል በርካታ እርምጃዎችን ወስደዋል። «አሁን ግን ሕገ መንግሥት አቁመን፡ ለሚኒስቴር ቤቱ ሁሉ ደንብ ሰጥተን ሚኒስትሮች ለየሥራቸው ሁሉ አላፊ ሆነው እንዲሠሩ ስለ አደረገን፡ ከመንግሥት ሥራ በሚተርፈው ጊዜያችን ከሊቃውንቱና ከመምህራኑ ጋር እየተገናኘን የቤተ ክህነቱና የሀገሪቱ ሥራ ጥቂት በጥቂት እየተሻሻለ እንዲሔድ አደረግን» በማለት ሐገራዊ አስተዳደርን በሕግና በሥርዓት እንዲመራ አድርገዋል። በክልሎችና በግዛቶች የነበረውን የዘፈቀደ አገዛዝ አስቀርተው፣ የተበደለ የሚጮህበትን ፍትሕ በማስፈን፣ እንዲሁም የግብርና የገቢ አሰባሰብ ሥርዓትን በማቀለል ዜጎች ሰላማዊ ሥራቸውን እንዲሠሩ አድርገዋል። ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያቸውን በማጠናከር በወቅቱ ከነበሩት ሱፐር ፓወሮች ጋር ጠንካራ ግንኙነት የነበራቸው መሪ ነበሩ። በተለይም በፈረንጆቹ 1954 ዓ.ም. አሜሪካን በይፋ በመጎብኘት ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከድዋይት ዲ. አይዘንሃወር ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገራት የትብብርና የልማት ግንኙነት አጠናክረዋል። ይህም ጉብኝት ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ያላት ክብር የተገለፀበት ነው። የንጉሥ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መወለድ ለሀገራችን ይዘውልን የመጡት በረከቶች በፖለቲካው ዘርፍ ብቻ አይደለም። የአማርኛ ሥነ-ጽሑፍን ታሪክ ከተመለከትን በርካታ የሥነ-ጽሑፍ ሰዎች በጃንሆይ ዘመን ታይተዋል፤ ዛሬም ድረስ ሳይደበዝዙ እንደደመቁ የዘለቁ ሥራዎቻቸውን አድርሰውናል። ከእነዚህም መካከል አክሊሉ ሀብተወልድ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ፣ ዮፍታሔ ንጉሤ፣ ተሰማ ኃ/ሚካኤል፣ ደስታ ተክለወልድ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ዮሐንስ፣ ማህተመ ሥላሴ ወ/መስቀል፣ ግርማቸው ተክለሃዋሪያት፣ ከበደ ሚካኤል፣ ታደሰ ሊበን ነጋሽ ገ/ማርያም፣ መንግሥቱ ለማ፣ አቤ ጉበኛ፣ ብርሃኑ ዘርይሁን፣ ፀጋዬ ገብረመድኅን ዳኛቸው ወርቁ፣ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር፣ አበራ ለማ፣ ኃይሉ ገብረዮሐንስ እና ሌሎችም ታላላቅ አበርክቶዎችን ያበረከቱ የብዕር አባቶች ይገኙበታል። ለሀገር እድገት፣ ለዘመናዊ አስተዳደር፣ ለትምህርትና ለሥነ-ጽሑፍ ዕድገት የነበራቸውን ጽኑ አቋም እየዘከርን፤ የኢትዮጵያን ታሪክ እና የከበሩ እሴቶች አብረን እናስብ። ግርማዊነትዎ መልካም የልደት በዓል!
ግራዝማች ተሾመ ግን "ሞትን ቁጭ ብሎ ከመጠበቅ፣ ተታኩሶ መሞት ይሻላል!" በማለት 267 ፈቃደኛ አርበኞችን አስከትሎ በሌሊት እየተታኮሰ ከዋሻው አፋፍ እየተንከባለለ ወጣ። ከዋሻው ከወጡት ውስጥ የተረፉት 7 ሰዎች ብቻ ነበሩ! እሳቸውም በብዙ ቦታ ቆስለውና የመርዝ ጢሱ ዓይናቸውን ጋርዶት እንኳ አልተማረኩም፤ ከወንድማቸው ከአበበ ጦር ጋር ተቀላቅለው ትግሉን ቀጠሉ። 💥 ኮላሽ ምሽግእና የታዋቂው ስንኝ መነሻ ልጅ አበበ ሸንቁጥ የመሩት ሰራዊት ለጠላት ብርቱ የነበረውን "ኮላሽ ምሽግን" በኃይል ሰብረው ሲቆጣጠሩት አካባቢው በጀግንነታቸው ተደንቆ የሸንቁጣውያንን ስንኝ በድጋሚ እንዲህ አሻሽሎ አወጣላቸው፦ "መውዜሩን ነዳፊ የበረሃ ጊንጥ፤ ኮላሽ ላይ ብቅ አለ አበበ ሸንቁጥ፤ መከራ አረገዘ ጣሊያን ያዘው ምጥ፤ በየምሽጉ ሥር ዋለ ሲራወጥ፡፡" የነፃነት ዋጋ ሁሉንምም ቤተሰባቸውን በጦርነትና በመርዝ ጢስ አጥተው፣ ሰውነታቸው በጠላት ጥይት እንደ ወንፊት ተበሳስቶ ደማቸውን የኢትዮጵያ ምድር ላይ ያፈሰሱት ሁለቱ ወንድማማቾች ግራዝማች ተሾመ እና ልጅ አበበ ለጉድ ተረፉ፤ የነፃነትንም ትንሳኤ በዓይናቸው አዩ። በኋላም የደጃዝማችነት ማዕረግ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተሰጣቸው። ዛሬም ታሪክ ራሱን እየደገመ ነው። የቅድመ አያቶችን የአርበኝነት ታሪክና የቆራጥነት መንፈስ በመውረስ፣ ዛሬም የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች የአብይን አገዛዝ በቆራጥነት እየታገሉት ይገኛሉ። የጀግናው የሸንቁጥ የልጅ ልጆችም ትናንት አባቶቻቸው ታሪክ በሰሩባት በዚያችው ታሪካዊት ስፍራ በይደመቆ በድጋሚ ተገናኝተው መምከራቸውን ሰምተናል። የሸንቁጥ ዘር አይሸጥ፤ አይመነዘር! 💪🦅
በትላንቱ ዜና ስለ ሸንቁጣውያን ታሪክ ከተነሳ በኋላ፣ በርካታ ወንድሞች "እነማን ናቸው? ዝርዝር ታሪካቸው ምን ይመስላል?" በማለት ጠይቃችኾል። እነሆ እጅን በአፍ የሚያስጭን የአምስት ወንድማማቾች ለአንድ ዓላማ አምስት ዓመት ሙሉ ለነፃነት የተከፈለ አስደናቂ የሸንቁጥ ልጆች ታሪክ (ምስጋናው ከፈለኝ) 🦅 ከአስኳላ ሊቅነት እስከ መርሃቤቴ ዱር ፧ የትግሉ አጀማመር የፋሺስት ጣሊያን ጦር አገራችንን ወደ መናገሻ ከተማዋ አዲስ አበባ ሲገሰግስ ንጉሠ ነገሥቱም ወደ ስደት አመሩ። በዚህ ግራ የተጋባ ወቅት፣ ቆራጥ የኢትዮጵያ ልጆች የየራሳቸውን የጎበዝ አለቃ እየመረጡ “ዱሩ ቤቴ” ማለት ጀመሩ። ከእነዚህ መካከል በከተማው ምቾት ውስጥ የነበሩት የጀግናው ቀኛዝማች ሸንቁጥ ደራጅ ልጆች ይገኙበታል። ይህ የሸንቁጥ ማህፀን ያፈራቸው ጀግኖች በ1888 ዓ.ም. በዓድዋ ጦርነት ላይ ጣሊያንን የገረፉት የጀግናው ቀኛዝማች ሸንቁጥ ደራጅ እና የነፃነት አርበኛዋ ወይዘሮ ማሚቴ ሙሉነህ ፍሬዎች ናቸው፦ እነ ተሾመ ሸንቁጥ፣ ኃይሌ ሸንቁጥ፣ አበበ ሸንቁጥ፣ ይነሱ ሸንቁጥና ጥላሁን ሸንቁጥ። ከእነዚህ መካከል በከተማ የነበሩት ሦስቱ ወንድማማቾች ወታደራዊና የቀለም ሊቃውንት ነበሩ፦ ሻለቃ ተሾመ ሸንቁጥ እና ልጅ ኃይሌ ሸንቁጥ፦ የአጼ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት ጠባቂዎች ነበሩ። ልጅ አበበ ሸንቁጥ፦ በፖስታ ሚኒስቴር የኮድ ክፍል ኃላፊ የነበሩ፣ በግብፅ ሀገር ድረስ ሄደው የተማሩና በቀለም ትምህርት የረቀቁ ስልጡን ሊቅ ነበሩ። ከተማዋ በጠላት እጅ ከመውደቋ በፊት፣ ሦስቱ ወንድማማቾች በአንድነት ተማክረው አባታቸው ወደሚኖሩበት ወደ መርሃቤቴ ለመሄድ ወሰኑ። ቤተሰቦቻቸውንና ጥቂት ጉዛቸውን ይዘው ሚያዝያ 28 ቀን 1928 ዓ.ም. መርሃቤቴ በሰላም ደረሱ። እዚያም በእርሻ ከሚተዳደሩት ሁለቱ ወጣት ወንድሞቻቸው ልጅ ይነሱ እና ልጅ ጥላሁን ሸንቁጥ ጋር ተገናኝተው አምስቱ ወንድማማቾች የአንድነት ክንድ ፈጠሩ። እነዚህ ከአንድ እናት ከአንድ አባት የተወለዱ ልጆች ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም. ድረስ በመርሐቤቴ አውራጃና በሌሎች ቀጠናዎች ሁሉ ፋሺስት ጣሊያንን ሲያራውጡ የኖሩ እውነተኛ ጀግኖች ሆኑ! 📣 ህዝብን መቀስቀስና ግንባር መፍጠር! ወንድማማቾቹ አገር ተወራ ሰላም አለመኖሩን ተገንዝበው ወዲያውኑ ወደ ስራ ገቡ። የታናናሾቹን ጉልበትና የከተማዎቹን ወንድሞች ወታደራዊና ስልታዊ እውቀት አቀናጁ። ታላቅ ወንድማቸውን ግራዝማች ተሾመ (በኋላ ደጃዝማች) መሪ አድርገው በመምረጥ፣ በአካባቢው እየተዘዋወሩ አገሬውን የመቀስቀስ ስራ ላይ ሙሉ ኃይላቸውን ተጠቀሙበት። ይህ ቅስቀሳቸው ሰፊ ተቀባይነትን አግኝቶ ጦራቸው እየገዘፈ ሲሄድ፣ ታዋቂ ከነበሩት አርበኞች ከደጃዝማች አበራ ካሣ እና ከሻለቃ መስፍነ ስለሺ (በኋላ ራስ) ጋር የፋሺስትን ኃይል በጋራ ለመመከት በመስከረም ወር 1929 ዓ.ም ወደ ፍቼ በመጓዝ ስትራቴጂካዊ ውይይት አደረጉ። ከባላምባራስ አበበ አረጋይ (በኋላ ራስ) ጋር ለመረዳዳትና ስልት ለመቀየስም ከአንድም ሁለት ጊዜ ወደ "ጅሩ አፋፍ" በመሄድ በአካል ተገናኝተው መክረዋል። ከልጅ ከፈለው ወልደ ጻዲቅ (በኋላ ደጃዝማች) ጦር ጋር በመቀናጀትም የጠላትን ጦር ገጥመው ዝርክርኩን አውጥተውታል። ከ1930 ዓ.ም. ጀምሮ እያንዳንዳቸው የየራሳቸውን ጦር በማደራጀት ጠላትን ፊት ለፊት መግጠም ጀመሩ። የወንድማማቾቹ ጦር ድል እየተጎናጸፈ በመሄዱ ጠላት ከመጨነቁ የተነሳ፣ በሰላማዊው ሕዝብና በእህል ማሳ ላይ የአውሮፕላን መርዝ ጢስ ማርከፍከፍ የጀመረው፣ ሰዎችን አካለ ስንኩላን ያደረገውና ማሳዎችን ያመከነው ያኔ ነበር። በኪነጥበብ ሥራዎች ላይ በአባቶች ሲወጋ፣ ሲፎከርና ታሪክ ሲዘከር እንደሚሰማው ሁሉ፤ መርሃቤቴ ላይ ብቅ ሲሉ ጠላትን ያነቀው ያ ሕያው ስንኝ እንዲህ ተቀነቀነላቸው፦ "መውዜራቸው ነዳፊ የበረሃ ጊንጥ፤ መርሐቤቴ ላይ ብቅ አሉ ሸንቁጣውያን፤ መከራ አረገዘ ጣሊያን ያዘው ምጥ፤ በየምሽጉ ሥር ዋለ ሲራወጥ፡፡" 🩸 የሦስቱ ወንድማማቾች ሰማዕትነት በአምስቱ ዓመታት የወረራ ወቅት፣ ከአምስቱ የሸንቁጥ ልጆች መካከል ሦስቱ ለአገራቸው ሲሉ አካላቸው ተቆራርጦ ሕይወታቸውን ሰጥተዋል። ጣሊያናዊው ጸሐፊ ጁሴፒ ማረሊዮ "Fratelli Shenkut /The Shenkut Brothers" በተባለው ጽሑፉ ስለ ሸንቁጣውያን ቃል በቃል እንዲህ ሲል በመጽሐፉ ላይ መሥክሮላቸዋል፦ "የሸንቁጥ ልጆች በዚያ አስቸጋሪ ቦታ በጠላቶቻቸው ላይ የፈጸሙት አደጋ ምንጊዜም የሚረሳ አይደለም፡፡ በመትረየስ፣ በመድፍ፣ በአይሮፕላንና በመርዝ ጢስ ብንደበድባቸውም ሊጠፋ አልቻሉም፡፡ የመንዝና የመርሃቤቴ ህዝብ ከንጉሡ የበለጠ ስላመነባቸው በምድር ላይ ያለውን መከራ ሁሉ ብናወርድባቸውም ከመርሃቤቴ ምድር ዱካቸውን ጨርሶ ልንደመስሰው አልቻልንም፡፡ የሸንቁጥ ልጆች ኃይለኛ የጦር ሰዎች ናቸው፡፡" 1.ልጅ ይነሡ ሸንቁጥ (የመጀመሪያው ተጎጂ)፦ከጠላት ጋር በተደረገ ውጊያ በጥይት ተመቶ እንደወደቀ፣ ጨካኙ የጠላት ጦር ፈጥኖ ደረሰበትና ሰውነቱን በመተልተል ሜዳ ላይ ጣሉት። ታላቅ ወንድሙ ግራዝማች ተሾመ ሬሳውን በጫካ ውስጥ አፈላልጎ በማግኘት፣ በመሪር ሐዘን የተረፈውን አካሉን እዚያው ዱር ውስጥ ቀበረው። 2.ልጅ ኃይሌ ሸንቁጥ መስዋዕትነት፦ "ታሞ" በተባለ ቦታ በተደረገ እጅግ የተፋፋመ ከባድ ውጊያ ላይ፣ ወንድማቸው ልጅ አበበ በግራ በኩል፣ ልጅ ኃይሌ በቀኝ በኩል ሆነው ጠላትን እንደ ጎርፍ መከቱት። ልጅ አበበ ክፉኛ ቆስለው በቃሬዛ ገለል ሲደረጉ፣ ልጅ ኃይሌ የጠላትን ኃይል እየተከላከሉ ብቻቸውን ማፈግፈግ ጀመሩ። እሳቸውም ክፉኛ ቆስለው ቢወድቁም፣ ሊማርኳቸው በቅርብ የመጡትን የጠላት ወታደሮች በተኙበት ሆነው በመሳሪያ አንድ በአንድ እየመረጡ ረፈረፏቸው። የጠላት ጦር ሊቀርባቸው ስላልቻለ ፍርሃት ስለያዘው፣ ከሩቅ ሆነው ቦምብ በመወርወር ገደሏቸው። ከዚያም አንገታቸውን ቆርጠው፣ ጭንቅላታቸውን ለአለቆቻቸው ወደ አዲስ አበባ ላኩት። 3.ልጅ ጥላሁን ሸንቁጥ (የሌሊቱ ጥቃት)፦ በ1933 ዓ.ም. መግቢያ ላይ አርበኞች የንጉሠ ነገሥቱን ወደ አገር መግባት በጉጉት እየተጠባበቁ ሳለ፣ ጠላት በሌሊት ተሸሎክልኮ አርበኞች ሰፈር በመድረስ ድንገተኛ ተኩስ ከፈተ። እዚያው ላይ ልጅ ጥላሁንን ገድለው፣ እንደ ወንድማቸው ሁሉ አንገታቸውን ቆርጠው ይዘው በመሸሽ አመለጡ። 💨 የአመጸኛ ዋሻ ሰቆቃ እና የጦር ሜዳዎቹ የሸንቁጥ ልጆች በ5 ዓመታት ውስጥ በዕርግብዮት ፣በቅመጠት ገብርኤል፣ በጀማ ወንዝ፣ በጃማ፣ በሚዳ፣ በታሞ፣ በሸራፊት፣ በአመጸኛ ዋሻ፣ በሳድን፣ በደራ፣ በአደሬ፣ በሠባጌ፣ በወርቅ አምባ፣ በሽማ ጅሩ እና በእንሳሮ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ተፋልመዋል። ከታሪኮቻቸው ሁሉ እጅግ ዘግናኙ ግን የ"አመጸኛ ዋሻ" ገድል ነው። ግራዝማች ተሾመ ሸንቁጥ ጦራቸውን ይዘው አመጸኛ ዋሻ በመግባት ጠላትን ሊያጠቁ ሲሉ፣ ፋሺስት ጣሊያን በመጋቢት ወር 1931 ዓ.ም በዋሻው መግቢያ ላይ የመርዝ ጢስ በርሚሎችን ሰቅሎ አፈነዳቸው። ዋሻ ውስጥ የነበሩትን አርበኞች ለእብደት፣ ለዓይነ ስውርነትና ለሞት መዳረግ ጀመሩ። እዚያው ዋሻ ውስጥ የጀግኖቹ እህት ወይዘሮ ፋንታዬ ሸንቁጥ ፣ እንዲሁም አባታቸው ቀኛዝማች ሸንቁጥ እና እናታቸው ወይዘሮ ማሚት በዚህ አረመኔያዊ መርዝ ህይወታቸውን አጡ።
ለኢትዮ 251 ሚዲያ ተከታታዮችና ቤተሰቦች ተወዳጁ “ኢትዮ 251 ዛሬ” ዝግጅታችን በአዲስ መልክ በመረጃ ቴሌቪዥን በኩል በቀጥታ ወደ እናንተ መድረስ መጀመሩን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን! ዕለታዊና ወቅታዊ ይዘቶችንና ልዩ ልዩ አጀንዳዎች የሚቀርቡበት “251 ዛሬ” ፕሮግራማችን፣ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ምሽት 2:00 ጀምሮ በመረጃ ቴሌቪዥንና በኢትዮ 251 ሚዲያ ሶሻል ሚዲያ አማራጮች ወደ እናንተ ይደርሳል። በመረጃ ቴሌቪዥን 📡 የሳተላይት ስርጭት መረጃ (Nilesat)፦ 🛰️ ሳተላይት (Satellite): Nilesat / Eutelsat 8 West B (8°W) 📡 ፍሪኩዌንሲ (Frequency): 11636 MHz (ወይም 11637) ↕️ ፖላራይዜሽን (Polarization): Vertical (V) / ቨርቲካል 🔄 ሲምቦል ሬት (Symbol Rate): 27500 🔢 FEC: 5/6 እንዲሁም በቴሌግራም:- https://t.me/ethio251media በዋትስአፕ:- https://whatsapp.com/channel/0029Vb6SADMFy72J1pBscv40 በX (ትዊተር) ፡- https://x.com/251Media ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ወደ እናንተ እንደርሳለን። @ethio251media
https://youtu.be/sl8j6hj4Fzg?si=79ePIcRoamj0HwJQ
ሚዲያ እና የሕልውና ትግል በትጥቅ ትግል ውስጥ ድል የሚቀዳጀው በጦር ሜዳ የጠላትን ምሽግ ሰብሮ በመግባት ብቻ አይደለም፤ የሕዝብን ንቃተ-ህሊና በመገንባት፣ የጠላትን የሥነ-ልቦና የበላይነት በማፍረስና እውነትን በዓለም አቀፍ መድረክ በመንገር ጭምር እንጂ። ለዚህ ነው በትግል ውስጥ ሚዲያ ከተራ ዜና አቅራቢነት አልፎ፣ እንደ አንድ ራሱን የቻለ "ዋና የትግል ግንባር" ተደርጎ የሚወሰደው። የቴሌቪዥን መስኮትና የጋዜጠኛው ብዕር ከጠመንጃው ባልተናነሰ ኃይል የትግሉ ግንባር ቀደም መሣሪያዎች ናቸው። ጠመንጃ አካልን ሲቆጣጠር፣ ሚዲያ ግን አእምሮንና ልብን ይገዛል። ሚዲያ በትግል ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወትባቸው ዋና ተግባሮች፦ - የሀሰት ወሬዎችን ማፍረስ፦ አምባገነኖች ትግሉን ለማዳከም የሀሰት ወሬዎችን ይረጫሉ። ሚዲያው ይህንን የጠላት የውሸት ጋሻ በመስበር እውነቱን ለሕዝብ ያደርሳል። - ምክንያታዊ የትግል ማኅበረሰብ መፍጠር፦ ትግል በስሜት ብቻ አይዘልቅም። ሚዲያ ሕዝቡ የትግሉን ስልታዊ አቅጣጫዎች፣ ታሪካዊ መነሻዎችና ግቦችን ተረድቶ በዕውቀትና በጽናት እንዲቆም ያደርጋል። - ውስጣዊ አንድነትን መጠበቅ፦ ጠላት በትግሉ መሪዎችና ክፍሎች መካከል ክፍፍል ለመፍጠር የሚያሴራቸውን ሴራዎች በማጋለጥ፣ ትኩረትን ወደ ማዕከላዊ ግብ በማሰባሰብ የውስጥ አንድነትን ያጠነክራል። -የዓለምን ትኩረት መሳብ፦ በትግል ሜዳው የሚደረገውን መስዋዕትነት፣ የሰብአዊ መብት ረገጣዎችንና የሕዝብን የነፃነት ጥሪ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማስተጋባት የዲፕሎማሲ ድጋፍ ይፈጥራል። የአማራ የሕልውና ትግል አሁን የደረሰበትን ወሳኝ ምዕራፍ ለማጠናቀቅ፣ ይህ የሚዲያ ግንባር ከመቼውም ጊዜ በላይ በላቀ ስልታዊ አቅምና በቁርጠኝነት መሥራት ይኖርበታል። ጠመንጃው በሜዳው የጠላትን ኃይል ሲደቁስ፣ ሚዲያው ደግሞ በትክክለኛው አቅጣጫ ሕዝባዊ ማዕበሉን ይመራል።
የመረጃ ቲቪ ቦርድ መልዕክት ላለፉት 8 ዓመታት የሚዲያ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው መረጃ ቲቪ ከስድስት ወራት የጽሞና ጊዜ በኋላ ዛሬ ወደአየር ተመልሷል መረጃ ቲቪ ወራት የፈጀ የጽሞና ጊዜ ለማሳለፍ የወሰነው በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ 1) ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና የፍትህ መጓደል ትኩረት ለመስጠት፣ እና 2) የኤዲቶሪያል ፖሊሲ፣ የአስተዳደርና የፕሮግራም ማሻሻያዎች አድግሮ በተጠናከረና በአዲስ ሁኔታ አገልግሎት መስጠት ለመቀጠል ነበር፡፡ የጽሞና ጊዜው እነዚህ ሁለት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ የመረጃ ቲቪ ቦርድ ትኩረት ሰጥቶ ለማሰብ፣ ለመወያየትና እንዲሁም ከመረጃ ቲቪ አባላት፣ ደጋፊዎችና የፕሮግራም ተከታታዮች የተሰጡ ገንቢ አስተያየቶች በማዳመጥና ይጠቅማሉ ተብለው የታመነባቸውን ለውጦች ለማድረግ እድል ፈጥሯል፡፡ የተሻሻለው የመረጃ ቲቪ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ለፍትህና የሰብዓዊ መብቶች መከበር ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ በዚህ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በመረጃ ቲቪ ላይ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች በሙሉ የሕዝብ አገልጋይ መሆናቸውን አጠናክረው በመቀጠል ለፍትህና ሰብዓዊ መብቶች ይሟገታሉ፡፡ በተለይም በወቅቱ የብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ በዐማራ ሕዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ጦርነት በተመለከተ መረጃ ቲቪ የዐማራ ሕዝብ ድምጽ መሆኑን ይቀጥላል፡፡ ተቋሙን ወደሚቀጥለው ምዕራፍ በማሸጋገር፣ አቶ ምስጋናው ከፈለኝን የመረጃ ቲቪ ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ መረጃ ቲቪ በሳተላይት ስርጭት አገር ውስጥ ኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እስከ መካከለኛው ምስራቅ Nile/Eutel sat 8B, frequencey 11.636 Poleraization Vertical, SR 27.500, FEC: ⅚ ላይ፣ በአሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውሮጳ እና እሲያ በ www.merejatv.com, Roku, Amazon Fire TV ላይ ይተላለፋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የመረጃ ቲቪ ቦርድ ለደጋፊዎቹ በሙሉ ምስጋናውን ይገልጻል፡፡ በተለይም የሸዋ ኅብረተሰብ ማህበር ምኒሊክ ዩኒት አባላት ለቴሌቭዥን ጣብያው እያደረጉ ላሉት ሁለገብ ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋናውን ይገልጻል፡፡ የመረጃ ቲቪ ቦርድ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ/ም
ላለፉት ስምንት ዓመታት የሕዝባችን እውነተኛ ዓይንና ጆሮ ሆኖ ያገለገለውን መረጃ ቴሌቪዥን በዋና ሥራ አስኪያጅነት ለመምራት ኃላፊነቱን ተረክቤያለሁ። ተቋማችን ስርጭቱን በአዲስ መልክ በሚጀምርበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ ፋኖ መሩን የአማራ ትግል ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ፣ ውስጣዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ስልታዊ ይዘቶችና ገንቢ አቀራረቦችን ይዘን እንቀርባለን። ምክንያታዊ የሆነ የትግል ማኅበረሰብ ለመፍጠርም በሙሉ አቅማችን የምንሠራ ይሆናል። ተቋሙ ትግሉ የሚፈልገውን የሚዲያና የመረጃ ግብዓት ሁሉ በጥራት ይሰጥ ዘንድ ከሙሉ ቡድናችን ጋር በቁርጠኝነት እንሠራለን!
ዲላን ፔጅን (Dylan Page) በአግባቡ እንጠቀምበት! አገዛዙ አዶናይን በመጠቀም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ19 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ታዋቂውን የቲክቶክ ዜና አቅራቢ ዲላን ፔጅ (Dylan Page) ወደ ኢትዮጵያ አምጥቷል። አገዛዙ በጦርነትና እየታመሰች ያለችውን ሀገር በብልጭልጭ መብራቶቹ በመሸፈን "ሰላም ነች" የሚል ትርክት ለመስራት ነው ደፋ ቀና እያለ የሚገኙው። አማራው ደግሞ ይህንን እድል በመጠቀም እየተካሔደበት ያለውን መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋት፣ የድሮን ጥቃት፣ የሴቶች መደፈር ማሳወቅ አለበት። አዶናይ ከዲላን ፔጅ ጋር ለመገናኘት የቻለው በዲላን ቪዲዮዎች ስር ተከታዮቹን በሰፊው አስተባብሮ "ኮሜንት" በማስደረግ እንደነበር ይታወቃል። ስለዚህ እኛም ይኸው ስልት በመጠቀም አጀንዳችንን ለመሸጥ እንጠቀምበት። ዲላን በሚለቃቸው ቪዲዮዎች ስር ሁሉ በነቂስ በመግባት፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮቹም ጭምር እንዲጠይቁ እና እሱ ራሱ ጉዳዩን እንዲመረምር ግፊት ማድረግ ይገባናል። በአማራ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን መጠነ-ሰፊ የዘር ማጥፋት (Genocide) እና የድሮን ጥቃት ለዓለም ለማሳወቅ ይህ ትልቅ መድረክ ነው። Millions of Amharas are facing drone strikes and ethnically motivated genocide right now. Please investigate and report! 🇪🇹❌ #AmharaGenocide እንደዚህ አይነት ኮመንቶችን በፌስቡክም በቲክቶክም በሚለቃቸው ቪዲዎች ስር ኮመንት እናድርግ። 📌 አሁኑኑ ወደ ተግባር! ሼር በማድረግ ተደራሽ አድርጉ
ከመረጃ ቲቪ የተሰጠ መግለጫ የእናንተው አይንና ጆሮ መረጃ ቲቪ በተጠናከረ አቅምና የተሻሻለ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ወደ ስርጭት ለመመለስ ዝግጅቱን አጠናቋል ላለፉት ስምንት ዓመታት የዐማራ ሕዝብና የመላው ኢትዮጵያውያን እውነተኛ ዓይንና ጆሮ በመሆን፣ በተለይም ደግሞ የዐማራ ፋኖ የህልውና ትግል ወደ ለየለት የትጥቅ ትግል ምዕራፍ ከተሻገረበት ጊዜ ጀምሮ የዐማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ፋኖዎችና የሕዝባችን ቁርጠኛ ልሳን ሆኖ ሲያገልግል የቆየው መረጃ ቲቪ ከግንቦት 17 ጀምሮ ወደ ስርጭት እንደሚመለስ ለክቡራን ተከታታዮቹ እና ለሰፊው ሕዝባችን በታላቅ ደስታና ኩራት ያበስራል። ቴሌቪዥን ጣቢያው ላለፉት ወራት ስርጭቱን በጊዜያዊነት አቋርጦ የቆየው፣ ወደፊት በዝርዝር በሚገለጹ ስልታዊና ተቋማዊ ሁኔታዎች ምክንያት፣ እንዲሁም ይበልጥ የተደራጀ፣ ዘመኑን የዋጀና የሕዝባችንን የትግል ምዕራፍ የሚመጥን ስልታዊ ዝግጅት ለማድረግ ሲባል እንደነበረ እንገልጻለን። በዚህ የስርጭት መቋረጥ ወቅትም ቢሆን፣ ተቋሙ ከአምባገነናዊው ሥርዓት የሚሰነዘርበትን የሚዲያ አፈና እና ዘመቻዎች በጽናት በመቋቋም፣ የሕዝባችን የነፃነት አምድ ሆኖ ለመቀጠል የውስጥ መሰረቱን ሲያጠናክር ቆይቷል። ላሳያችሁት ትዕግሥትና ድጋፍ እያመሰገንን የእናንተው አይንና ጆሮ የሆነው መረጃ ቲቪ በላቀ የስትራቴጂ አቅም፣ ፍትህና ሰብዓዊ መብቶችን መሰረት ባደረገ የኤዲቶሪያል ፖሊሲ፣ እንዲሁም በአዲስ ማኔጅመንት ከግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ስርጭት እንደሚመለስ እናበስራለን። የመረጃ ቲቪ አስተዳደር ቦርድ 10/10/2018 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፦ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ (1920 - 1991 ዓ.ም) አጭር ግለ-ታሪክ (ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም — ኢትዮ 251 ሚዲያ) ዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፣ የሀገር አንድነትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ 27ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ነው። ፕሮፌሰር አስራት በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ በሙያቸው እጅግ የተከበሩ፣ በሀገር ፍቅራቸው ደግሞ ፅኑ የነበሩ ብርቅዬ ግለሰብ ናቸው። 1. የልጅነት ዘመንና የትምህርት ዝግጅት ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሰኔ 12 ቀን 1920 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ። ገና በሦስት ዓመታቸው እናታቸውን ያጡ ሲሆን፣ በሰባት ዓመታቸው ደግሞ አባታቸው አቶ ወልደየስ አልታየ በፋሺስት ጣሊያን ወራሪ ኃይል ተረሽነዋል። ይህ በለጋ ዕድሜያቸው ያጋጠማቸው የቤተሰብ መከራ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ያላቸውን ፍቅር ይበልጥ እንዲጠነክር አድርጎታል። ትምህርታቸውን በተመለከተ፦ • በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ጀምረው፣ በግብፅ የእንግሊዝ ቪክቶሪያ ኮሌጅ ቀጥለዋል። • ከፍተኛ የሕክምና ትምህርታቸውን በታዋቂው የኤድንበራ ዩኒቨርሲቲ (ዩናይትድ ኪንግደም) በመከታተል፣ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት በመሆን ታሪክ ሰርተዋል። 2. የሕክምና ሙያና ልዩ አገልግሎት ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ ሕይወታቸውን ሙሉ ለሕዝባቸው አገልግሎት የሰጡት ፕሮፌሰሩ፣ የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት አከናውነዋል፦ • የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ምሰሶ፦ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋኩልቲ መስራችና ዲን በመሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞችን አፍርተዋል። • የደሃው ሐኪም፦ ምንም እንኳን የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የግል ሐኪም ቢሆኑም፣ አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ተራውንና ድሃውን ሕዝብ ያለምንም ክፍያ በማከም ነበር። • ክብርና ሜዳሊያ፦ ለሀገራቸው ባበረከቱት አስተዋጽኦ የቅዱስ ጊዮርጊስ የጀብደኝነት ሜዳይ፣ የአርበኝነት ሜዳይ፣ የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ እና የድል ኮከብ ሜዳሊያዎችን ተሸልመዋል። 3. የፖለቲካ ተሳትፎና የሕልውና ትግል በ1983 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ ከመጣ በኋላ ሀገሪቱ በዘርና በጎሳ ስትከፋፈል በማየታቸው ድምፃቸውን ለማሰማት የተገደዱት ፕሮፌሰር አስራት፦ • በ1984 ዓ.ም. የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) መስራችና መሪ በመሆን ስለ ኢትዮጵያ አንድነትና ስለ አማራ ሕዝብ መበደል በፅናት ተከራክረዋል። • በወቅቱ የነበረውን የሽግግር መንግሥት ስህተቶች በድፍረት በመንቀፋቸውና "ኢትዮጵያ አትፈርስም" ብለው በመቆማቸው የሥርዓቱ ዋነኛ ተቃዋሚ ተደርገው ተፈርጀዋል። 4. የእስራት ዘመንና ህልፈት ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው ባላቸው ፅኑ አቋም ምክንያት በ1986 ዓ.ም. በፈጠራ ክስ ታስረው ለአምስት ዓመታት ያህል በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቆይተዋል። በእስር ቤት ውስጥ የጤና ሁኔታቸው እጅግ እየተባባሰ ቢሄድም፣ አገዛዙ አስፈላጊውን ሕክምና እንዳያገኙ በማዘግየቱ ለከፋ ስቃይ ተዳርገዋል። ፕሮፌሰር አስራት በደረሰባቸው ሕመም ምክንያት በዓለም አቀፍ ጫና ወደ አሜሪካ ለሕክምና ቢሄዱም፣ ግንቦት 6 ቀን 1991 ዓ.ም. በ71 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። "ሀገር የምሰጠው የለኝም፤ የምሰጠው ነፍሴን ብቻ ነው!" በማለት የታገሉለት የእኩልነትና የአንድነት ራዕይ ዛሬም ለትውልድ እንደ ብርሃን ያበራል። ለኢትዮጵያ ታላቅ ባለውለታ ለሆኑት ለፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ዘላለማዊ ክብር ይሁን! ኢትዮ 251 ሚዲያ የነጻነት አንደበት!
አውቀን እንታረም...! በዓለም ታሪክ የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ቆይተው፣ በመጨረሻ በድል ሳይሆን በውርደት የጠፉ ወይም የተዳከሙ ቡድኖች ጥቂት አይደሉም። ለእነዚህ ኃይሎች መፈራረስ ዋነኛው ምክንያት የጠላት ጥንካሬ ሳይሆን፤ የራሳቸው የውስጥ መከፋፈል፣ እርስ በርስ መበላላት፣ በአንድ ልብ ባለመታገል እና በመጨረሻም ዕጣ ፈንታቸው ከባህሩ እንደወጣ አሳ በሕዝብ መተፋት ይሆናል። በትጥቅ ትግል ውስጥ ሕዝብ እንደባህር ታጋዩ ደግሞ እንደ አሳ ናቸው። እንደ አንጎላው የዩኒታ አማጺ ቡድን፤ እንደ ሲሪላንካው ታሚል፤ እንደ ኡጋንዳው ሎርድ ርዚስሰታንስ አርሚ፤ እንደ ኮሎምቢያው ፋርክ፤ በውድቀት የታጀበ ፍፃሜ እንዲኖረን አንፈልግም። እኛ ስማችን ጭምር የሚዋጋ፣ የአሸናፊዎቹ የዓድዋ ድል ፊትአውራሪ ልጆች ነን። ሆኖም ታሪክ ስንቃችን እንጅ የዛሬ ዕጣችን አያወጣውም። የትግል ወኔውን ከአባቶቻችን፣ አሁናዊ ፈታዎችን ደግሞ ወደ ውስጣችን በመመልከት ራሳችንን ለመማር ዝግጁ አድርገን መነሳት አለብን። ይህ ካልሆነ ግን የፋኖ ትግል ዕጣ ፈንታ ከላይ ከጠቀስኳቸው ከታሚልም፣ ከፋክርም፣ ሎርድ ርዚስሰታንስ አርሚም፣ … ከሁሉም የከፋ ይሆናል።
Dear friends and colleagues, please consider sharing the GoFundMe below to support former prisoner of conscience Ermias Mekuria. The link provides background info in English and Amharic. 🙏🏾 https://gofund.me/c8b76ccc2
ተማሪ ካለ አስተማሪ በየቦታው አለ! በዓለም ታሪክ የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ቆይተው፣ በመጨረሻ በድል ሳይሆን በውርደት የጠፉ ወይም የተዳከሙ ቡድኖች ጥቂት አይደሉም። ለእነዚህ ኃይሎች መፈራረስ ዋነኛው ምክንያት የጠላት ጥንካሬ ሳይሆን፤ የራሳቸው የውስጥ መከፋፈል፣ እርስ በእርስ መበላላት፣ በአንድ ልብ ባለመታገል እና በመጨረሻም በሕዝብ መገፋት ናቸው። ለዚህ ትልቅ ማሳያ የሚሆነው በአንድ ወቅት (ከ1987 እስከ 1989 እ.ኤ.አ.) ሀያል የነበረው የሲሪላንካው ጃናታ ቪሙክቲ ፔራሙና (JVP) ታሪክ ነው። ይህ ታጣቂ ኃይል በውስጡ በፈጠረው ክፍፍልና በሥልጣን ሽኩቻ ምክንያት የገዛ አባላቱን መብላት ጀመረ። ከመጠላላትና ከመጠራጠር የተነሳ የትግል አጋሮች እርስ በእርሳቸው መባላታቸው ለውድቀታቸው የመጀመሪያው እርምጃ ነበር። ለማንኛውም ታጣቂ ኃይል "ጫካው ሕዝቡ ነው!" ለJVP ደግሞ ሕዝቡ ምሽጉም፣ ጋሻውም ነበር። ነገር ግን ቡድኑ በትዕቢት ተወጥሮ ራሱ የተሸሸገበትን "ጫካ" (ሕዝቡን) ማማረርና በመጀመሩ ከመሠረቱ ተነቀለ። ትግሉ በመራዘሙና የሕዝቡን ነፃነት መገደብ፣ ሕዝቡ ትግሉን ትግሉን በመሸከም ትከሻው በመጉበጡ፤ በመጀመሪያ የቆሰለውን ታጋይ ደብቆ የሚያስታምመው ሕዝብ ፊቱን እንዲያዞር አደረገው። ሕዝቡ ሲማረር ደብቆ ያቆየውን ታጋይ እየጠቆመ ማስያዝ በመጀመሩ፣ ያ ሀያል የነበረው ቡድን እንደ አሸዋ ተበተነ። የዚህ የታሪክ ፍፃሜ ይበልጥ አሳዛኝና አስተማሪ የሚያደርገው የቡድኑ መሪ ሮሃና ዊጄዊራ አሟሟት ነው። በሻይ እርሻ ውስጥ ተደብቆ የነበረው መሪ፣ ሕዝቡ በሰጠው ጥቆማ በመንግሥት ኃይሎች ተያዘ። በመጨረሻም በምርመራ ወቅት በተረሸነበትና አስከሬኑ በድብቅ በቃጠሎ በጠፋበት አሳዛኝ ሁኔታ ትግሉ አበቃ። ተማሪ ካለ አስተማሪ በየቦታው አለ!
ትግልን መተቸት ለትግሉ ዋስትና ነው! "መሪዎችን መጠበቅ" ማለት ስህተታቸውን እያዩ በዝምታ ማለፍ ማለት አይደለም። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአማራ ፋኖ ትግል ውስጥ የሚታዩ ግድፈቶችን "ለትግሉ ስንል" በማለት በዝምታ ለማለፍ ሞክረናል። ነገር ግን ዝምታን የመረጥነው ለትግሉ አስበን ቢሆንም፣ ያልታረሙ ስህተቶች ግን ውሎ አድሮ ትግሉን ዋጋ ማስከፈላቸው አይቀሬ ነው። ትግሉ ሊተቸባቸው ከሚገባ በርካታ ምክንያቶች ጥቂቶቹ:- - በእንቁላሉ ጊዜ እንደሚባለው የተተቸ ይስተካከላል ዛሬ በዝምታ የምናልፋቸው ትናንሽ ጥፋቶች ነገ የማይታረሙ ትላልቅ አደጋዎች ሆነው ይመለሱብናል። - ትግሉን ከውድቀት የምንታደገው ጉድለቶችን በድፍረት አውጥተን ስንወያይ እና ገንቢ ትችቶችን ስናቀርብ ብቻ ነው። - ግልጽነት ባለበት ቦታ ጥንካሬ ይኖራል። መሪዎችም ሆኑ ታጋዮች ለሚሰሩት ስህተት ተጠያቂ መሆናቸውን ሲያውቁ ትግሉ ይበልጥ ለድል ይበቃል። የመሪነት ልክ ትችትን የመቀበል አንዱ አቅም ነው! አመራሮች ለገንቢ ትችት ራሳቸውን ክፍት ማድረግ አለባቸው። መሪነት ማለት መስማት እንጂ መናገር ብቻ አይደለም። ሀቀኛ መሪ የትግሉን ጉብጠት ለማረም የሚመጣን ገንቢ ትችትና ሀሳብ በአይነ ቁራኛ ሳይሆን በመልካም ሊቀበል ይገባል። ትግሉ የሁላችንም ነው፤ ስለሆነም በዝምታ መታለፍ የሌለባቸው ጉዳዮች ላይ በሀቀኝነት እና በግልጽነት መነጋገር አለብን። ገንቢ ትችት የጠላት መሳሪያ ሳይሆን የትግሉ ዋስትና ነው! እንቀጥላለን...
"በፍቅር ተጠርተው ከዳር እስከ ዳር፤ መሀል ገቡና አቆሙን ከዳር" ይህ ስንኝ የቴዲ አፍሮ የግጥም ስራዎች ሁሉ ማዕከል እና የአዲስ አበባን ወቅታዊ የጥቃት ስሜት በሁለት መስመር ብቻ የጨመቀ የመርዶ ድምፅ ነው። "መሀል ገቡና አቆሙን ከዳር" የሚለው ሀረግ የከተማዋን ነባር ማህበረሰብ ስነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መፈናቀል የሚገልጽበት መንገድ "በፍቅር ተጠርተው ከዳር እስከ ዳር..." አዲስ አበባ በታሪኳ "የሁሉ" በመሆኗ የምትታወቅ፣ እንግዳ ተቀባይ እና የኢትዮጵያዊነት ማቅለጫ ነች። ስንኙ እንደሚለው፣ ከተማዋ ከየአቅጣጫው (ከዳር እስከ ዳር) የመጡትን ሁሉ በፍቅር ተቀብላ አስተናግዳለች። ሆኖም ግን፣ ያ በፍቅር የመጣው ኃይል "መሀል" ላይ እንደደረሰ፣ መሀል የነበረውን እና ከተማዋን የገነባውን ነባር ማህበረሰብ ወደ "ዳር" (ወደ መገለል) ገፍቶታል። ይህ "ከዳር" መቆም በጂኦግራፊ ብቻ ሳይሆን በባለቤትነት ስሜትም ጭምር ነው። የማህበራዊ ትስስር መበጠስ (ነባር ሰፈሮችና መፈራረስ) የአዲስ አበባ ጥንካሬ የነበሩት እንደ ፒያሳ፣ ካዛንቺስ፣ አራት ኪሎ እና መገናኛ ያሉ ነባር ሰፈሮች መፍረስ የህንጻ መፍረስ ብቻ አይደለም፤ የማህበራዊ ካፒታል መፍረስ ነው። የእድር እና የጽዋ ትስስር፡ ነባር ሰፈሮች ሲፈርሱ፣ ለትውልድ የዘለቁ የሰፈር ትስስሮች፣ እድሮች እና የጎረቤት ፍቅሮች አብረው ይበተናሉ። ከመሀል ወደ ዳር (ኮንዶሚኒየም)፡ ነባር የአዲስ አበባ ልጆች ከመሀል ከተማ ተነቅለው ከተማዋ በማታውቃቸው ዳርቻዎች (ለምሳሌ ኮዬ ፈጬ፣ ቱሉ ዲምቱ) እንዲሰፍሩ መደረጋቸው፣ "አቆሙን ከዳር" የሚለውን ስንኝ ፍጹም እውነት ያደርገዋል። ይህ ሆን ተብሎ የአዲስ አበቤን የጋራ ድምፅ እና አንድነት ለመበተን የሚደረግ "ማህበራዊ ምህንድስና" (Social Engineering) ይመስላል። "ባይተዋር" የመሆን ህመም "ባሳደገኝ ቀየ ባደኩበት መንደር፣ ባይተዋር ሰው ሆኜ እንደሌለው ሀገር" አዲስ አበቤው በራሱ ሰፈር ላይ እንደ እንግዳ የሚቆጠርበት፣ ቋንቋው እና ባህሉ እንደ ስጋት የሚታይበት ሁኔታ ተፈጥሯል። "መሀል" የገቡት ኃይሎች የከተማዋን ውበት ሳይሆን ባለቤትነቷን ለመቀየር ሲሰሩ፣ ነባሩ ነዋሪ ግን "ባንዲራዬን ላንሳት ወይስ ላውርድ?" በሚል ስቅቅ ውስጥ ይወድቃል። ይህ ስንኝ በተለይ ደግሞ በከተማዋ "የኮሪደር ልማት" ስም የሚፈጸሙ መፈናቀሎችን እና የማንነት መገፋትን በሚገባ ይገልጻል። ኢኮኖሚያዊ መገለል "መሀል ገቡና" የሚለው ሀረግ የከተማዋን የኢኮኖሚ ማዕከል መቆጣጠርንም ያሳያል። ነባሩ ነጋዴ እና ሰራተኛ ከመሀል ከተማ የንግድ ስፍራዎች ሲፈናቀል፣ "መሀል" የመጡት ግን በፖለቲካዊ ድጋፍ ስፍራውን ይይዛሉ። በዚህ ጊዜ የአዲስ አበባ ልጅ በራሱ ከተማ ላይ የኢኮኖሚ ተመልካች ብቻ ሆኖ "ከዳር" ይቆማል። ባጠቃላይ ቴዲ አፍሮ በዚህ ስንኝ ውስጥ የከተማዋን "መታረድ" ነው በዜማ የገለፀው ። አዲስ አበባ "አዶ ሸገሩ" መሆኗ ቀርቶ የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ ስትሆን፣ ነባር ሰፈሮቿ ሲፈርሱና ልጆቿ ሲበተኑ የሚሰማውን የቁጭት ለቅሶ ነው። ይሰማል ወይ አዲስ አበቤ!