የአምሓሮች ድምፅ በወለጋ Committe for the Dignity of Wollegan Amhara Nationalist
Статистикаነፃ ማንነትን ከማስከበር የሚቀድም አላማ የለንም! "አምሓሮች ነን፣ ነባር ህዝቦች"
- Последний пост
- 17 февр. 2025 г.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ከየትኛውም አቅጣጫ ይነሳ…‼️ አላማቸው ከማይታወቅ ድብቅ ኃይሎች እና ከግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነት ተፅዕኖ ያልተላቀቀ ስብስብ፣ አደረጃጀትም ቢሆን፣ ከፋሽስቱ ብልፅግና፣ ከብዐዴንስ በምን ይለያል? በትግላችን ውስጥ፣ ተዋረዳዊ የስልጣን ደረጃን መጣኝ ሸፍጥ በፍረጃ እና በመጠፋፋት ላይ የቆመ በሴራ እና ተንኮል የታጀለ ፋሽስታዊ ግብረ ልምምድ ቀስ በቀስ በእግሩ ሲሄድ እየታየን ነው። የፋሽስቱ ብልፅግና እኩይ ማንነቱ "ስረ ውል" ዋና ችግርኮ የአብይ አህመድ በዘረኝነት የተሳከረ፣ በሸፍጥ እና ሴራ የበለፀገ ለፍቅረ ስልጣን ህሊናው የታወረ ፈላጭ ቆራጭነት ነው። በዚህ ወቅት…ገና ከቁጥቋጦ እና ምሽግ ሳንወጣ፣ ከሞት ጋር የሰዓታት ቀጠሮ ይዘን በምንዋደቅበት መራራ ሰልፍ ላይ ቆመን… ጉዳዬ ዋና ያደረግናቸው አጀንዳዎቻችን የሚያብራሩልን ቁም ነገሮች አስደንጋጭ ናቸው። ሁሉም እንቶፈንቶ መቧቀሻ እና መዳቆሻ አጀንዳዎቻችን… የአሸናፊነታችንን ቅድመ ትንበያ እውንነት አያስረግጡም፣ አያፀድቁምም። #ግለሰቦችን የነብይነት በትር አስጨብጦ የነፃነት መንገድ ተላሚ አድርጎ ተክለ ስብዕናን አጋኖ በመካብ ትይዩ… ሌላኛውን ግለሰብ ደግሞ በተቃርኖ በትግል ደንቃራነት አግዝፎ ማጠልሸት እና የማሰይጠን… "#አርካሽ እና ቀዳሽ" መንገዳችን የሚጠቁመን አንድ መራራ ኃቅ ነው። ገና፣ በአንድ መስመረ አምሓራዊነት የሚራመድ ጠንካራ ድርጅት ማዋለድ እንዳቃተን! በጠንካራ ርዕይ የሚመራ እና በመርህ የተጠረነፉ መሪ እና ተመሪ ያለው ድርጅት ሲወለድ… ቅድመ ወሊድ የነበሩ አሉባልታዊ፣ በፍጭት ትርምስ ውስጥ ላይ ሳለን የሚታይብን ተፈጥሯዊ ውስጣዊ ህመሞች፣ ድህረ ወሊደ !#አምሓራ ድርጅት" ሁሉም በምስራች ተስፋ ቃል ይተካሉ። በድርጅታችን እድገት እና አላማዊ ተልዕኮ ስኬት ላይ ያተኮረ አጀንዳ እና ውይይት አየሩን ይይዛል። ለድርጅታዊ ራዕያችን መሳካት የሚሆኑን ሁነኛ ራዕይ የታጠቁ፣ የነቁ እና የበቁ መሪዎች እና ተመሪዎች በድርጅቱ አላማ እየተጠመቁ ለድርጅቱ ራዕዬ ስኬት በአሳዳጊነት በተዋረድ በየቦታቸው ይሰለፋሉ። ዛሬ ላይ… በአንድ አላማ የምንሰለፍለት አንድ አምሓራዊ ድርጅት ለማዋለድ ያቃታቸው፣ የማይሹም፣ ነፃ ጀርባ የሌላቸው በአባታቸው አፋሪ፣ በምላሳቸው ታፋሪ ድቃይ በቅሎ ዲስኩረኞች… የትግላችንን ዓምደ ማዕከል ይዘው… አምሓራዊ መናኝ ጀግኖቻችንን ተስፋ ቢስ ሽብርክ እያደረጉ ነው። ይህ፣ ያለፉ 2 ዓመታት የተፈተነ ለጠላት ጥቅም ያዘነበለ ጥራት አልባ መንገድ "#በቃ!" ሊባል ይገባል! እንዴት⁉️ ይመለሳለሁ! #Hiruy Amhara #ቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችንን join አድርጉ። #ድል-ለመላው አምሓራ ፋኖ! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 10/06/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ https://t.me/Moamediamor
#አምሓራዊነት - ሆኜ የተወለድኩት ማንነቴ (የማልደራደርበት፣ ሊለወጥ የማይቻል ደማዊ፣ የተፈጥሮ ፀጋዬ ነው) #ኢትዮጵያ/ዊነት- በኃይል የተበጀች ክቡረ ዜግነቴ (ታሪካዊ እና ጆግራፊያዊ መገኛዬን አመልካች ሊለወጥ የሚችል ፖለቲካዊ እጣ ፋንታዬ ነው። ዜግነት ሊለወጥ ሲችል #ማንነት ግን ህያው ነው። #ሐይማኖቴ - በትምህርት እና ስብከት አንዳንዴም በኃይል አበው የተቀበሉት የኋላ ታሪኬ ወይም የኔ ዘመን ግንዛቤ መረዳት ውጤት ነው። በትምህርት ስብከት በኃይልም ጭምር ከዘመናት በፊት አባቶቼ የተቀበሉት ሊቀየርም በዚያው ተለማጅ መንገድ ሊለወጥ የሚችል የማንነቴ አንድ አካል ነው። ከአዲስ መረዳቱ በመነሳት ክርስቲያን ሊሰልም፣ ሙስሊምም ክርስቲያን ሊሆን ይችላል። በልውውጡ ውስጥ ይቀየር ዘንድ የማይቻል ተፈጥሯዊ ማንነት አምሓራዊነትህ ነው። ለዚህ ነው… አምሓርነትህን መጠበቅ፣ ለተፈጥሯዊ ህልውናህ ዘብነት የመጨረሻ ጥግህ ላይ መቆም ነው የምንለው። * ክርስትናህን የጠሉ ጠላቶች፣ ክርስትናህን ስትጥልላቸው አያጠፉህም * እስልምናህን የጠሉ ጠላቶች፣ እስልምናን ስትጥልላቸው ይምሩሓል፣ ይሄም በታሪክ ታይቷል። የእኛ ጠላቶች ግን፣ ጥላቻቸው ልንለውጠው ከማንችለው የተፈጥሮ ፀጋችን #ከአምሓራዊ ማንነታችን ነውና ሳያጠፉን አይተውንም። ከሁሉም በላይ፣ ካለ አንዳች ምርጫ ተፈጥሮ ያጎናፀፈችን፣ ሆነን የተገኘንበት፣ የተወለድንበት አምሓራዊ ማንነታችንን የማያከብር፣ ህልውናውን የሚጠራር ሰብዓዊ ስብስብ ቢኖር… ፊት መሪው የጠላታን ቁንጮ ነው። ቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችንን join አድርጉ። #ድል-ለመላው አምሓራ ፋኖ! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 05/06/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ https://t.me/Moamediamores
#ብዙዎቻችን፦ጥቅመኛ፣ ውሸታም፣ አስመሳይ እና የስሜት ደንባሪ መንጋዎች ነን‼️ ብዙዎቻችን፦ ውሸታም ከሀዲዎች ነን፣ በአሳምነው ቃል እና አላማ የምንማማል፣ በተግባር ግን ለልዩነት፣ የተሳልን፣ በጎጥ ተቧድነን የምንቧቀስ የጠላት ወጥመድ በጥቅም እና ሴራ የተተበተብን አስመሳይ ጉዳዬ-ሆድ የረታን፣ አንካሳ ጭንቅላት ተሸካሚ መንጋዎች ነን! ከዚህ፣ የጠላት ቀንበር መላቀቅ እስካልቻልን፣ በተሸከምነው ነፍጥ እና የፕሮፖጋንዳ ሚዲያ ነፃ አንወጣም። ይልቁንስ፦ የተሸከምነው ሚዲያው፣ የታጠቅነው ነፍጥም ራሳችን ከፋፍሎ እርስበርስ የሚያጫርስ የጠላት መጠቀሚያ የምናደርግበት እድል ሰፊ ነው። ጠላት፣ በአካሉ፣ በመንፈሱ እና አስተሳሰቡ በአሞሌ ደልሎ መልምሎ አሰልፎን በመካከላችን ለፀረ አንድነት ዐላማው በመንጋ እየተናዳ ቢሆንም እናየው ዘንድ እንዳንችል የረቀቀብን ምክንያቱ… በአምሓራዊነት ቅዱስ ሰልፍ በብፅዕና መናኝ ሆነን ያልተሰለፍን፣ ሁሉን ለትግሉ አላማ ያልሰዋን በሁለት እግር ሁለት ዛፍ ለመውጣት የምንውተረተር ምርጫ ቢሶች፣ የአላማ ጥራት ያልጨበጥን መናኛ የብዓዴን ስልብ ስነ ልቦና የተጫነን እሪያዊ ተናጅዎች በመሆናችን ነው። ይህ፣ ውንግርግር ከሀዲድ የወጣ ራስን ጠላፊ ጉዞ፣ ወደ መስመር መመለሻው ቁልፍ አንድ ነው። ከጎጥ ጉረኖ ዋሻ አምልጦ፣ የመፈራረጅ የጠላት ዱላን አስቀምጦ፣ በአምሓራዊ ጨዋነት እና ወንድማማችነት ሰክኖ ፍቅርን ባስቀደመ ጥበብ ለመፍትሄ በጥልቅ መወያየት ነው። ያኔ፣ ሰርጎ ገቡ፣ የጥቁር አምሓራው ጭንብል ይገፈፋል! ለጠራ መረጃ #ቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችንን join አድርጉ #ድል-ለመላው አምሓራ ፋኖ! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 07/06/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ https://t.me/Moamediamores
አስቸኳይ‼️ ከደጀን ወደብቸና ተጨማሪ ሀይል እየገባ ነው 2ታንክ 2 መድፍ 1 ብረት ለብስ 2 ኦራል 2ሲኖ 2 ፓትሮል እየገባ ስለሆነ ለመረጃ ያህል እንዲያደርሱልን Inbox ቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 #ድል-ለመላው አምሓራ ፋኖ! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 04/06/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ https://t.me/Moamediamores
የቅዱስ ቀውሱን እንቆቅልሽ ፍቱ‼️ ቅዱሱን ቀውስ፣ ቅዱስ ሰልፍ፣ ቅዱስ ጉባኤ አድርጉት! #ቅዱስ ቀውስ የተባለ የቃላት ተቃርኖ መንገድ እንቆቅልሽ እስኪፈታ… በፋኖ አንድነት ስም የሚሞከር ውይይት እና ጥረት ምክክር እርባና የላቸውም። ቀውሱ ከቅድስና ጋር ህብረት የለውም። ቀውስ ሽብር ነው። ቅዱስ፣ ሰላም ነው። ሰላም እና ሽብርን አስማምቶ መዝለቅ አይቻልም። ቅዱስ ሰልፍ እንጅ፣ ቅዱስ ቀውስ አምሓራዊ አንድነት አያመጣም። የአምሓራዊ አንድነት፣ የፋኖን ህብረት ለማምጣት የቀውሱን መንገድ አርሙ!! አምሓራዊ ቤተ ዝምድናን እንጅ… የጀርባ ዘዋሪ እጆችን ማዕከል አታድርጉ። በዚያኛው ጎራም ሆነ፣ በዚህኛው ጎራ ታዩ ለተባሉ ክፍተቶች እርስበርስ መተማመን ማጣቶች ዋስትና ሰጭ መፍትሄ እስካልተሰጠ፣ በአንድነት ስም የሚደረጉ ምክክሮች የህዝባችን የመከራ ጊዜ አራዛሚ እንጅ ዘላቂ መፍትሄ አያመጡም። የአማራ #ፋኖ አንድነት ዋና ማነቆ፣ ከኢጎ እና የስልጣን ሽኩቻ ባሻገር ያሉ የፍላጎት ልዩነቶች በጊዜ ሂደት ጠርተው፣ ተለይተው እየወጡ ነው። ይህ፣ ልዩነትና ፍላጎት… ከመሪ ግለሰቦች ጀርባ ያሉ ተኳሽ ያልሆኑ ሰልፈኞች እንጅ፣ ከነፍጠኛው የሚነሳ ልዩነት አለመሆኑንም ጠንቅቀን አውቀናል። በየትኛውም የአማራ ቀዬ የተደራጀ ሰልፈኛ ፋኖ አላማ እና ግብ አንድ ነው። የመሪዎቹ የልዩ አጀንዳ የተሸካሚነት ጉዳይ ግን፣ የአማራ ህዝብ ትግል ትውልዳዊ ወኪል ፋኖ ሰልፈኛን አንድነት አዘግይቷል። በዋናው ተዋጊ ዘንድ፦ • ጎጠኝነት የለም • የስልጣን ሽኩቻ የለም • የጥቅም ሰልፍ የለም • አውራጃዊነት የለም • የዓላማ ልዩነት የለም • የዕምነት ዐጀንዳ የለም • የኢጎ ስካር የለም መላው አምሓራ ፋኖ፣ አምሓራዊ ሰልፈኛ እና የአምሓራ ወታደር ነው። በጥቂት አመራሮች ዘንድ እና ወኪል የሚዲያ እና ሳይበር ሰልፈኛው በኩል ግን፣ ልዩ፣ ልዩ አይነት የጥፋት ውክልና ፍላጎቶች ሰርገው እየገቡ እንዳለ ፍንጭ ታይቷል። ይህ፣ አሸናፊ የማያደርግ አደገኛ ፍላጎታቸውን በፍጥነት ያከስሙ ዘንድ የታችኛው ተዋጊ ፋኖ ከፍተኛ ጫና ማድረግ፣ አሊያም የልዩነት አራጋቢ እና የአንድነት ሳንካ የሆኑ አመራሮችን ገምግሞ ከስልጣን በማንሳት በተሻለ ቆራጥ የለውጥ መሪ ተክቶ ትግሉን ማስቀጠል ምርጫ የሌለው መንገድ ነው። ዛሬ ላይ፣ "#መሪ ነን" የሚሉት ተቧቃሾች ራሳቸውን በኢጎ ከማሳበጣቸው በፊት የነበረው፣ የተዋጊው ሞራል እና የህዝባችን ተሳትፎ ተነሳሽነት ከፍ ያለ ነበር። አሁን ላይ፣ መሪዎች ጎልተው ሚዲያ መቆጣጠር፣ የልዩነት መርዛማ ከፋፋይ ንግግሮች ማሰማት ከጀመሩ በኋላ… በብዙ ሁኔታ ትግሉ ወደ ኋላ መጎተት፣ አቅጣጫ ስቶ መንጋደድ፣ በጎጥ እና መንደር መከፋፈል፣ ግለኝነት፣ ጥቅመኝነት፣ እና የባንዳ ሰርጎ ገብ ክህደት አጋጥሞታል። ስለዚህ፣ አንድነት የማጣታችን ዋና የችግሩ ስር ያለው፣ በተዋጊው ፋኖ ሳይሆን፣ በአመራሩ በኩል ነው ማለት ነው። አመራሮች፣ ከአማካሪ መሳይ የባህር ማዶ ዘዋሪዎቹ በተላቀቀ ግማሽ መንገድ ለአንድነት መቅረብ፣ ለመወያየት፣ ለመቀራረብ መስራት አለበት። #ቅዱስ ቀውስ የተባለን፣ መርህ መር ያልሆነን ጥቁር መስመር ደምስሶ… በቅዱስ ጉባኤ ወደ ቀደመ ምክክር ለመመለስ መወሰን አለበት። ሁሉንም አሳታፊ ውይይቶች እንጅ… ጎራ የለዩ ድርጅቶች መመስረታቸው ነፃ አያወጣንም። አንዱ ጎራ፣ በአንዱ ጎራ ላይ የሚፈፀም ህልውናዊ መካካድ፣ ይበልጥ ስንጥቅ አስፊ እና የልዩነት መንገድን አርዛሚ እንጅ፣ አስተማማኝ አንድነት አያመጣም። ይልቅ፣ እርስ በእርስ እውቅና ተሰጣጡ እና በረጋ እና በሰከነ መንገድ ጣልቃ ገብነት የራቀው ውይይት አድርጉ። ተኳሽ ያልሆኑ እና ከመሬት የራቁ የትግሉ ዋና ባለድርሻዎች ሚና መስመር ይበጅለት። ሰርጎ ገብ የልዩነት ባለሟል፣ የከፋፋይነት አውራ የሆኑ የጠላት ወኪሎችን በጥልቅ ግምገማ አጥሩ። የምናውቃቸው፣ እጅ፣ ጠምዛዥ፣ የጠላት እጆች ይቆረጡ። በጠላት ላይ አኩራፊው የውስጥ፣ ወንበረኛ እና የውጭ ባለ ኢኮኖሚያዊ ኃቅም አርበኛን አደራጅቶ በቀይ መስመር የሚያታግል ልዩ ኮማንድ ይቋቋም እንጅ…ወደ መሃል በሚስጥር ዐወቅነት፣ በአዛዥ ናዛዥነት አይግቡ። ቅዱሱን ቀውስ፣ ቅዱስ ሰልፍ፣ ቅዱስ ጉባኤ አድርጉት! ዋናው፣ የፋኖ አንድነት ሳንካ ፣ የቅዱሱ ቀውስ፣ ማዕበል ያለመርጋት ነው። ቅዱሱን ቀውስ… ቅዱስ ሰልፍ ከማድረግ ወዲህ ያለ… ሌላ መላ አትምቱ! አካሄዳችንን የተቃረነ፣ ወይም አካሄዱን የተቃረንነው ጎራ ላይ፣ ጊዜያዊ፣ የፕሮፖጋንዳ ብልጫ ለማግኘት ስንል፣ የምወስዳቸው የበሬ ወለደ ስም አጥፊነት፣ ዋናው የትግል ምሰሶን ነቅናቂ መሆኑና በህዝባችን ተስፋ ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ዳፋው ይጠና። እርግጥም፣ የህዝባችሁ መከራ ከራሳችሁ እና የጀርባ ባለ ፍላጎቶች አጀንዳ ይልቅ ከገዘፈባችሁ… ከቅዱሱ ቀውስ በፊት ወደነበራችሁበት ወንድማዊ አንድነትን ናፋቂ ምክክር ተመለሱ። @Hiruy Amhara ቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 #ድል-ለመላው አምሓራ ፋኖ! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 26/05/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ https://t.me/Moamediamores
ጥበባችሁ፣ ከምላሳችሁ ሳይሆን፣ ከተግባር እና ህሊናችሁ ይዛነቅ‼️ ከዚህ በኋላ፣ ውብ በሆኑ ንግግሮቹ፣ እና ተስፈኛ ስብከቶቹ አምነን የምንከተለው መሪ የለንም፣ በተግባራዊ እርምጃዎቹ እንጅ… በተግባር አልባ አማላይ ከንዐንን ሰባኪ ንግግር ተሸውደን "ሙሴያችን" ባልነው ጭንብላም መንበርም ባስረከብነው ተኩላ እየተነከስን እንዳለን አንዘነጋም። አንዴ፣ የመታን እንቅፋት ደግሞ ከመታንማ፣ እንቅፋቶቹም ከንቃት እና አስተውህሎት የተኳረፍን እኛ ነን ማለት ነው። በፍፁም፣ አይሆንም፣ አንሸወድም፣ በብልጭልጭ ፕሮፖጋንዳም፣ በመድረክ አሟቂ ንግግር እምነት የምንጥልበት ግለሰብም ቡድንም የለም። ይህ፣ የጊዜ አውድ የተግባር እንጅ… የምላስ ብርቃታ፣ የአማላይ ተስፈኛ ስብከቶች መድረክ ነጋሲነት አይደለም። ወቅቱ በጋ ነው። የደከሙበት ፍሬን ከክምር እያወረዱ የሚወቁበት፣ ግርዱን ከገለባ የሚለይበት። ጠንካራው እንቅልፍ አልባ ገበሬን፣ ከሰነፉ የምንለይበት። የሚከፈለውን ሁሉ በመክፈል፣ መውረድ ባለብን ልክ በመውረድ፣ መውጣትም ባለብን ከፍታም ከፍ ብለን በመውጣት አምሓራዊ አንድነታችንን መገንባት፣ አንድ ባለ ራዕይ የፋኖ መዋቅርን በማምጣት መስራት ላይ ባለን አስተዋፅኦ ብቻ የምንመዘን እንጅ… ለመድረክ ስምሙ ቅሙም ንግግር የምንመዘንበት ጊዜ አክትሟል። በምንናገረው ልክ እና፣ በቃላችን ፅናት ብንታሰር፣ ለህሊናችን ክብር መስራት ብንችል ኖሮ… የ፬ ኪሎ ጉግ ማንጉግ ቡድን በህዝባችን ደም ሻምፓኝ እየተራጨ 6 ዐመታት ባልዘለቀ። የእነሱ ብርታት… የእኛ ድካም ነው። የነሱ ጥንካሬ፣ ከእኛ መልፈስፈስ የሚመነጭ ነው። ይህ፣ ነው መራራው እውነት… በምላስ ወጌሻነት የሚጠገን ስብራት አልገጠመንም፣ በሃቀ ለልፍ ዋጋ በሚያስከፍል ተግባራዊ ስራ እንጅ… ዳይ… ለዐንድነት ከልባችሁ፣ ከጫና ነፃ ሆናችሁ ስሩ… ‼️ የቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 10/05/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ https://t.me/Moamediamoresh https://t.me/Moamediamoresh
አርአያነት❗️ በትኛውም ቦታ ለመስራት ዝግጁ ነኝ። በትግል ውስጥ ከላይ ከታች የሚለው ስሜት አይሰጠኝም ።ዋናው ትግሉን ለማሸነፍ ጠጠር እየጣልሁ ነው ወይ የሚለው ነው።የየትኛውም ታጋይ ህልሙ ትጉሉን ማሸነፉ ብቻ ነው። ወደላይም ወደታችም አይደለም የሄድሁት አሁንም እዚያው ትግል ላይ መሆኔ ብቻ ነው የሚሰማኝ። በክርስትና እምነት ያለውን የሰጠ እንጅ ብዙ የሰጠ አይልም ። በናሳ ታሪክም አንድ የሚነገር ታሪክ አለ '' እኔ የማፀዳው እናንተ ህዋ ላይ ለመታደርጉት ጉዞ አእምሯችሁ እና ጤናችሁ እንዲጠበቅ ነው።'' በማለት ለህዋ ምርምሩ ድርሻ ያላት መሆኑን የፅዳት ሰራተኛይት ገልፃለች። በፋኖ ትግልም የትም ላይ ያለን ታጋዮች ውሃ የሚቀዳም፣ የሚጋግርም ፣ጋንታ የሚመራም ፣ድርጅት የሚመራም እኩል ነው። ሁሉም አላማው ይህን መከረኛ ህዝብ ከሞትና ስቃይ ነፃ አውጥቶ የሀገር ባለቤት አድርጎ ማየት እንጅ የግል ጉዳዩን ለማሳካት አይደለም። ስለዚህ በኔ ሹመት የተደሰታችሁም ይሁን የከፋችሁ እኔ አሁንም የተለየ ቦታ የለኝም ትናንት እንደታገልሁት ዛሬም እየታገልሁ ነው ምንም የተለየ ነገር የለውም። ድርጅቴ አምኖ ባስቀመጠኝ በየትኛውም ቦታ ለመስራት ዝግጁነኝ። መርህ አሰራር ማክበር ከዚህ ይጀምራል። የአማራ ፋኖ በጎጃም አምኖ የሰጠኝን ይህን ከባድ ሃላፊነት ለመወጣት ያቅሜን ሁሉ የማደርግ መሆኑን እገልፃለሁ። ፅናት ፣ ትዕግሥት ፣እምነት ፣ እውነት ። ፅና!!!!! እስቲበል አለሙ ዘሪሁን https://t.me/Beteamharavoice
በማህበራዊ ሚዲያው መድረክ፦ ሁሉም… የየራሱን ጎራ ግለ ንጉስ… ዜና መዋዕል እና ገድልን አግዝፎ ጸኃፊ እና ተራኪ በሆነበት ሁኔታ "#አምሓራዊነት" የቱጋ ያብብ⁉️ የቱጋ⁉️ የራስ ያልነውን ለማንገስ፣ የሌላ ሆነ ያልነውን የራስ ወንድም ማኩሰ ደግሞ… የድንቁርናና የኋላ ቀርነታች መታያ ሆኗል። የስህተታችን መሰረት ደግሞ ክብረ አምሓራዊነት ከፍታችንን የመረዳት ኃቅም ማጣታችን ነው። #አበ ድል - ክብረ መሰረታችንን እናጥብቅ! ከዚያ በታች ያለው ንቃተ አንካሳነት መታያ የሆነው "#ጎረኝነት" የአምሓራዊ አንድነታችን ሳንካ፣ ካንሰርም ነው። እርግጥም ትግሉ የገባው፣ የኃቅ ሰልፈኛ… በግልፅም፣ በህቡም ከሚያራምደው የጎጥ እና ጎራ ኩሸታዊ መወድስም፣ ማኩሰስም ኋላ ቀር መስመሩ ይውጣ እና ትግሉን በምክያታዊ እውቀት እና ፋይናንስ ይደግፍ! https://t.me/Moamediamoresh
ህግ-33 ደካማ ጎናቸውን ፈልገህ አግኝ‼️ እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ደካማ ጎን አለው፣ ስብዕናው ውስጥ ክፍተት አይጠፋውም። ድክመቱም፣ አብዛኛውን ጊዜ በራስ አለመተማመን፣ እንዲሁም መቆጣጠር የማይችለው ስሜት ወይም አንዳች ፍላጎቱ ነው። ምን አልባት አንዳች መደሰቻው ሊሆን ይችላል። በዚህም አለ በዚያ፣ ደካማ ጎኑ አንዴ ከተገኘ፣ ለራስህ ስኬት እና የአላማ መንገድ የምትዘውረው ትልቅ እሴት ይሆንልሃል። ከዛሬ 400 ዓመት ገደማ በፊት፣ አንድ አንድ በሰው ማህበራዊ እና ሞራል ላይ በቅጡ የተመራመረ እና የተፈላሰፈ ስፔናዊ ሊቅ ፈላስፋ ከዚህ በታች ያለውን ምክር ፅፎ ነበር። ------------------------------------ ወዳጄ፣ ግሩም የጥበብ ምክር ልስጥህ፣ የእያንዳንዱን ሰው ደካማ ጎን ፈልገህ አግኝ። ፍላጎታቸውን በምትፈልገው መንገድ የመዘወርን ጥበብ የምታገኘው ከእዚህ ጋር ነው። ይሁን እንጅ፣ ይሄን ማድረጉ ከቆራጥነት የበለጠ ችሎታን ይጠይቃል። ማንኛውንም ሰው በየት በኩል እንደምታጠቃው ማወቅ አለብህ። እያንዳንዱ ጠንካራ ፍላጎት እንደ ጣዕሙ የሚለያይ ልዩ መንስኤ አለው። የሰው ልጆች ሁሉ አምላኪዎች ናቸው። ጥቂቶቹ፣ ዝናን፣ ሌሎቹ የግል ፍላጎታቸውን ሲያመልኩ አብዛኛዎቹ ደስታን ፈላጊ ናቸው። ችሎታ ማለት፣ በአምልኮ ማዕከላቱ መጫወት እንዲቻል፣ እነኝህኑ በሚገባ ማወቅ ነው። የማንኛውንም ሰው የተነሳሽነቱን ስረ-መሰረት ካወቅህ ውስጣዊ መንፈሱን የምትቆጣጠርበትን ቁልፍ እጅህ ውስጥ አስገባህ ማለት ነው። ---------------------------------------------------------- ባልታዛር ግራሽያ (ስፔናዊ ፈላስፋ1601-1658 ዓ.ም) 🗞🗞🗞🗞🗞-🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞🗞 ለንቁ #ሞዐውያን ገፀ ሰበዝ ይመዘዛሉ። የቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 07/05/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ https://t.me/Moamediamoresh
ጀነራሉ ፈረጠጡ‼️ ከውጊያ ባለፈ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ባለቤቶች በሚል ፋሽስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲያሞካሿቸው የነበሩት ህፃን ገዳይ ሴት ደፋሪ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት ከዋጃ ከተማ በፋኖ የተከፈተባቸውን ጥቃት መቋቋም አቅቷቸው ወደ ጥሙጋ መፈርጠጣቸው ተሰምቷል። ትናንት ለዛሬ አጥቢያ ለሊት ጀምሮ እስከ ንጋት ባለው በራያ አላማጣ ዋጃ ከተማ ላይ ከባድ ውጊያ ተከፍቶ የነበረ ሲሆን፡ በዚህም ከ20 በላይ የአየር ወለድ ኮማንዶዎች ተግድለዋል ተብሏል። በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የሀውጃኖ ክ/ጦር ፋኖዎች ትናትና ጥር 4/2017 ዓ/ም ወደ ዋጃ ከተማ በመግባት ከእኩለ ለሊት ጀምሮ እስከ ንጋት የዘለቀ ጥቃት በመክፈት ድል መቀዳጀታቸውን የአማራ ፋኖ በወሎ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል። ከእኩለ ለሊት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ በዘለቀው በዚህ ጥቃት የሪፐብሊካን ጋርድ አባላቱ ከባድ ኪሳራን አስተናግደዋል ተብሏል። በዚህ ጥቃት በዋጃ ከተማ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ብቻ ከ20 በላይ ኮማንዶዎች ሲገደሉ ከ11 በላይ የሚሆኑት ቆስለው ንጋት ላይ ወደ አላማጣ ከተማ መወሰዳቸው ተነግሯል። የትናንት ለሊቱ ኦፕሬሽን እጅግ ስኬታማ ነበር የተባለ ሲሆን በዚህም ሙትና ቁስለኛ ከሆኑት ወታደሮች በተጨማሪ በህይወት የተረፉት ኮማንዶዎች መሣሪያቸውን እያዝረከረኩ ወደ ራያ አላማጣ ጥሙጋ ቀጠና መሸሻቸውን የድርጅቱ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ ጨምሮ ገልጿል። ወደ ጥሙጋ የሸሸው የፀረ አማራው ብልፅግና ፓርቲ አገልጋይ ጦር እንደገና ኃይሉን አደራጅቶ ዛሬ ማርፈጃውን ዙ23ና ሌሎች ከባባድ የጦር መሣሪያዎችን በመጠቀም ዋጃ ከተማንና በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ አከባቢዎችን ሲደበድብ መዋሉ ተሰምቷል። በዚህም በአከባቢው ነዋሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱ ነው የታወቀው። የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/Moamediamoresh https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 05/05/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ https://t.me/Moamediamoresh ተጨማሪ ዝርዝር👉https://www.youtube.com/watch?v=5_-jtTmlaU4&t=47s
በኩረ ሀሳብ‼️ በዚህ ልክ…! ግለሰቦች አጀንዳ ወርውረው፣ የውስጥ ጥብቅ የሚስጥር ጉዳያችሁ ላይ ዘልቀው በመግባት ያሻቸውን ያህል ስንጥቅ እና መጠራጠር ፈጥረው የሚያተራምሱበት ኃቅም ኖሯቸው ከተገኙ… ወይ ገና ተቋም አልገነባንም፣ አሊያም ይሄን ትርምስ መፍጠር የቻሉት እነርሱ ግለሰብ ብቻ አይደሉሞ ማለት ነው። ይህ አጋጣሚ፦ ግለሰቦችንም ተቋሙንም የመፈተሽ፣ የመመርመር፣ የመገምገም እድል የሰጠ ጥሩ ጊዜ ነው። ይህ፣አጋጣሚ፦ ከመርህ ውጭ፣ በተቋም ውስጥ አዝልቀን በማስገባት በሚስጥር አወቅነት የምናስቧችራቸው ገና ነገም የሚገለጡ፣ ያደፈጡ ሌሎች ግለሰቦችንም የነገ አቅጣጫ አመልካች የአደጋ መብራት ነው። ግለሰቦች፦ እጃቸው ላይ ያለው መረጃ እና ድርጅታዊ ሚስጥር… የትግሉ መበተኛ እና መጠበቂያ ዋና ቁልፍ እና መዶሻ ሆኖ እስኪሰማቸው ድረስ ከድርጅት ውጭ ላሉ በመርህ ለማይገሩ፣ በመተዳደሪያ ደንብ ለማንጠረንፋቸው ግለሰቦች፣ ጋዜጠኞች ሚስጥር የሚያጋራ የድርጅት አባል እና አመራር ያሉበት ተቋም… ተቋም አይባልም። *************** ሁሌም፣ በለጋ ተቋም ግንባታ ውስጥ የሚያጋጥሙ ፈተናዎች እና ስር የያዙ ተዕግዳሮቶች ይኖራሉ፣ ነበሩም። የጠላት ተልዕኮ የተሸከሙ ተቋም ጠላፊ ሰርጎ ገቦች፣ እንዲሁም ግላዊ የጥቅም እና ስልጣን ፍላጎት የተጫኗቸው መሪዎች እና አባላት ተዋረዳዊ ችግር ሆነው ሊከሰቱ ይችላሉ። ሆኖም፦ ተቋሙ፣ በጠንካራ መስመራዊ ዐለት ላይ ከቆመ፣ አባላት እና አመራሩን በድርጅታዊ ርዕዬ ዓላማ ያስተሳሰረ፣ በጠንካራ ጓዳዊ የመንፈስ ውህድ አንድነት ያፀና፣ በመሪዎቹ የሚታመን፣ ሲያጠፋ የሚቀጣ አባል፣ በአባላቱ የሚታመን፣ በአባላቱ የሚገመገም የሚቀጣም መሪ… ድርጅታዊ መርሆች በሁሉም ጓድ እኩል የሚከበሩበት፣ በግለሰቦች በትረ ሙሴ ፈላጭ ቆራጭነት ያልተመካ መመሪያዎች የሁሉም የበላይ የሆኑበት ድርጅታዊ ተቋም መስርተን ከሆነ… ይህ ውዥንብርን በአጭር ጊዜ ለማጥራት አይከብደውም። ይህ ያልጠሩ የመረጃ ሰበዞች በግለሰቦች በተመዘዙ ቁጥር… ጭንቅ እና ጥብብ የሚለው… ከድርጅታዊ የውስጥ መገማገም እና ችግሩን ማጥራት ይልቅ… ባህር ተሻግሮ በግለሰብ የስልክ ጆሮ ስር ቀርቦ የመካሰስ፣ የመደራደር ስንፍና ላይ ከተገኘ ግን… ድርጅቱ ስር አልባ፣ በፕሮፖጋንዳ አሸዋ ላይ የቆመ ጥልቅ ተሃድሶ የሚያስፈልገው ደካማ መዋቅር ነው ማለት ይቻላል። ይህ አጋጣሚ ጥሩ ነው። ሁሉም፣ የአምሓራ ትግል ውስጥ ሰልፍ ያደረጉ ቡድኖች ራሳቸውን የሚገመግሙበት፣ መስመረ አቅጣጫቸውን የሚያስተካክሉበት ወቅት ነው። የፋኖ መዋቅር አባል ያልሆኑ ግለሰቦች ከተቋሙ በላይ ገንነው አየሩን የያዙበት አሉኝ የሚሏቸው መረጃዎች እና ችግር ፈጣሪ እርሾ የወጣው… ቀይ መስመር እና ሚስጥር ከሌለው፣ በፕሮፖጋንዳ ብቻ ከገነነ ስመ ተቋም ነው። ስለ ትግል ፅናት፣ ስለ ድርጅት ሚስጥር ጥበቃ እና ጓዳዊ ትስስር ሳስብ… ስለ ኢህአፓ ዘመን ያ! ትውልድ ወጣቶች ቅናት የሚይዘኝ ለምንድን ነው? ጓዶች‼️ #አምሓራዊ አይዲዮሎጅ የጓዳዊነት ትስስር ሚስጥር ቋት መዝጊያ ቁልፍ ሆኖን… ከዚያ መሰረት ላይ የቆመ የትግል ፍኖት ካልያዝን ብንንሸራተት እንጅ… ዳገቱን አንወጣም። ዛሬም… ትላንት ላይ ቆመን ዛሬን እየገደልን… የነገ ተስፋ ቀንን አንቃትት! ትላንት፣ የምንማርበት፣ ዛሬ የምንሰራበት፣ ነገ የተስፋችን ፍኖት ነው። ከትላንት የአካሄድ ስህተታችን እየተማርን፣ በጥልቅ እየተገማገምን፣ አባላት እና መሪዎቻችንን እናጥራ። ውስጣዊ አንድነታችንን በጥብቅ እንስራ፣ ሚስጥር እንጠብቅ! ሚስጥር የሌለው ድርጅት ተቋም አይባልም። የሳይበር አውራ አክቲቪስቶችንና ጋዜጠኞችን የሚስጥር ሳንዱቅና፣ የፕሮፖጋንዳ ጠበቃ ያደረገ ስሁት ተቋማዊ መንገድ መዳረሻው ውድቀት ነው። * በውስጥ የሚቋጩ ግምገማዊ እርምት እርምጃ ይወሰዱ! * አመራሮች ሁሉ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ባይኖሯቸው። ድርጅታዊ አቋሞች በድርጅታዊ ታዋቂ ገፆች ብቻ ቢሰራጩ * ለሚዲያ የሚቀርቡ አባላት እና አመራሮች ከድርጅት አቋም ውጭ የግላቸውን ስሜት መር አተያይ ባያሰራጩ * ስህተትን በስህተት ለመምታት በተያዘ ዘመቻ ድርጅታዊ መርሆች ባይጣሱ * ሁሉም ፕሮፖጋንዳዎች፣ እና የመድረክ ሙቀት ዲስኩሮቻችን ለአምሓራዊ አንድነት ባላቸው ፋይዳ ቢገመገሙ * ሚዲያዎች በተደራሽ ብዛታቸው ሳይሆን ለአምሓራዊ የህልው ትግል፣ ለአምሓራዊ አንድነት ባላቸው የፀና አላማ ላይ የተመረኮዘ መርኻዊ ግንኙነት አድርጉ * የውስጥ እና የውጭ የቀጠና ዲፕሎማሲያዊ ትስስሮች በአምሓራዊ ርዕይ ጥቅም አስጠባቂ ድርጅታዊ አቅጣጫ ይመሩ * የጎጥ እና አውራጃዊ ትርክቶች በአምሓራዊ አንድነት ላይ ባላቸው ፋይዳ ልክ ይመጠኑ፣ በጎጥ እና ወንዜ ድጋፍ ጭንብል የተደበቁ ከፋፋዮች ምሽግ ጎጥ እና አውራጃዊነት ነውና * የትግል ግበ መስመራችን ቅልብጭ ባለ አምሓራዊ ርዕይ ተቃኝቶ የሰልፈኞች ሁሉ ዋናው ትጥቅ ይሁን * የጠላት ኃይል ያለው ኃቅም ትንተና ፕሮፖጋንዳ በታጋዩ፣ በህዝቡ እና ለራሱ ጠላት ባለው ፋይዳ እና ጉዳት ተተንትኖ ተከፋፍሎም ይድረስ * ተዋረዳዊ መመሪያ ትግበራ እና ተጠይቅ… ከላይ ወደ ታች እና ከታች ወደ ላይ ያለ መሰናክል ይንሸራሸር * አምሓራዊ ግዙፍ አንድነት አዋላጅ ሀሳቦች በብስለት አጀንዳ ሆነው በጥልቀት ይመከር ይዘከርበት * * ይቀጥላል… የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/Moamediamoresh https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 05/05/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ https://t.me/Moamediamoresh
መራራው እውነት‼️ ከዐምሓርነት ይልቅ፦ ጎንደሬነት ጎጃሜነት ወሎየነት ሸዋየነት… የሚልቅባቸው የየወንዜ ስርቻ ልኩፍ ባለዛሮች… የሚዲያ እና ትግላችን አጋፋሪነት ውክል ቦታ ይዘዋል። ምላሳቸው ላይ የሚያገላብጧት አማራዊ የፕሮፓጋንዳ ትርክት… አንዳንዴም የሀገረ ኢትዮጵያ ወኪል መሳይነት ድንፋታ… የየስርቻው ቁማር እና ማታለያ ድራማ ናት። #ማይክ ኦፍ አድርገው የሚማማሉት በወንዛቸው ነው። #አምሓርነት ማይክ ሲያበሩ የሚጋባባቸው የመድረክ ድምቀታቸው፣ የኦዲየንስ ተከታይ ማጋበሻ፣ ፖለቲካዊ ጥቅም መልቀሚያ ኩሸታዊ መፈክር ነው። #አምሓርነት… ደመ ስጋቸው ላይ በተግባር እንደ አይዲዮሎጅ የደመ አጥንት ስሪት ስረ ሀረግ ሆኖ አልሰረፀም። #አምሓራዊነት፦ ደማዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ትውፊታዊ እና ፖለቲካዊ እጣፋንታ በአንድ ርዕይ የጠረነፈው ምነ ማንነት እንጅ… ተራ የፕሮፖጋንዳ እና ግላዊ፣ ደጋፊን ማካበቻ፣ ኢኮኖሚን ማዳበሪያ፣ የምላስ ወሬ ማሳመሪያ የእነ እንቶኔ የዲስኩር ሸቀጥ አይደለም። ሆኖም፦ የዛሬው ኃቅ መራራ ነው። የአምሓርነትን መልካም ዘር ያቀጨጨው እንቦጩ አረም በስብዕናችን ገዝፎ ለምልሟል። ይሄን፣ የወል ውለ መሰረታችንን ንዶ… ራስ ወዳድነት ያሰረፀብን ክፉ የመንደር አረም፣ ከስብዕናችን ነቅለን…ነፃ አምሓራዊነት በእኛነታችን ልዕልናው እስኪታይ… የምኩራቦች አጋፋሪ አስመሳዮች… በደማችን ሲታጠቡ፣ በነፍሳችን ሲጫወቱ፣ በመስዋዕታችን ሲነግዱበት ይዘልቃሉ! ይሄው ነው!!! ሀቀኛ አምሓሮች፣ እራሳችንን እንሁን…! ማንነታችንን ተነጥቀን፣ ራስ ወዳድ መረን ግለኛ ሆነናል። የማይክ አጋፋሪዎች ድኩም ቅበ ስሜተ አምሓራነትም… በስሜ ይመጣሉ እንደተባሉት… አይነት… ነፃነትን የማያውቁ ነፃ አውጭዎችን መሳይ ነው። ነፃ- ለማውጣት ጠመንጃም፣ ማይክም ከመታጠቅህ በፊት… በአምሓርነት ትጥቀ ዝናር፣ ስብዕናህን ነፃ አውጣ!! አንተ፣ ያልዳንክበትን መስመረ መድሃኒት…ሌላውን እንዲድንበት አትስበከው። አንተ ያልሆንከውን፣ ሆኖ የሚከተልህ አንዳች የለም። ይሰማል! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 03/05/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ https://t.me/Moamediamoresh https://t.me/Moamediamoresh https://t.me/Moamediamoresh
ሞዐ ሚዲያ፣ በአፋጎ ጉዳይ‼️ ======================== ተቋም፣ በተቋማዊ መርህ እና መመሪያ፣ በጥልቅ የስነ ምግባር ደንብ ግምገማ ውስጡን ማጥራት ይኖርበታል እንጅ… የግለሰቦች የስማ በለው እና ብጥስጣሽ መረጃ ላይ ተመርኩዞ… ግዙፍ የፋኖ እምርታዊ በደም እና አጥንት የተፃፉ፣ በጀብድ የደመቁ ስራዎችን አኮሳሽ፣ አሁናዊ ሰበር የሚቀረፉ ችግሮቹን ማዕከል በማድረግ ውስጣዊ አንድነቱን ሊያናጋ አይገባም። እስከሰራን ስህተቶች ይኖራሉ፣ ይታረማሉም። ከስህተታችን ጋርም፣ ያሳካነው ግብ፣ የፈፀምነው ተግባራዊ በድል የታጀበ ተጋድሎ በችግሮቻችን ሊሸፈን አይገባውም። በመስዋዕትነት የታጀቡ ታላላቅ የጎመሩ የትግል ፍሬዎችን የሚጋርዱ አሉታዊ መርዛማ ፕሮፓጋንዳዎች ጥቅም ለጠላት ካልሆነ፣ ለወዳጅ አይሆኑም። ወዳጅ፣ ገመናን በአደባባይ አያሰጣም። በውስጥ፣ እንድናርም፣ አብሮን ይታገላል እንጂ… ቀድሞ ነገር፣የተቋሙ አባል ያልሆኑ፣ በተቋም ህገ ደንብ የማንጠረንፋቸው፣ ተጠያቂነት የማይፈሩ ግለሰቦች፣ በደም ፍሳሽ፣ በአጥንታችን ምሰሶ ባቆምነው ተቋም ውስጥ አስተዋፅኦ ያልነበራቸው የሌሊት ወፎች ያሰማሩ የመረጃ ነጋዴዎች የሚነዙት ወሬ ለምን ቦታ ተሰጠው? ለምንስ ከነርሱው ጋር በመርህ አልባ የፕሮፖጋንዳ ግልሙትና ውስጥ ተዘፈቅን? ይህ፣ ተቋማዊ ያልሆነ፣ በስነምግባር ደንብ ላይ፣ በትግል መስመረ ቀይ አላማ ላይ ያልተመካ የምላስ ኪራይ እና የጀማ ዋስትና ላይ የቆመ የስሜት አሸሸ ገዳሜ … ችግር ይዞ እንደሚመጣ፣ "ሚስጥረ ነጭ" ትግል የእንቧይ ካብ አካሄድ እንደሆነ… አስቀድመን… ደጋግመን ፣ ደጋግመን አስጠንቅቀናል። የአማራ ትግል ውስጥ፣ ያለ ጠንካራ ገሪ ተቋም የሚደረግ መረናዊ ተሳትፎ መጨረሻው አያምርም ብለናል። በተቋም ውስጥ፦ • የዳያስፖራው ሚና • የአክቲቪስቱ ሚና • የጋዜጠኛው ሚና • የሙህራኑ ሚና ቀይ መስመር ባለው የተቋም መመሪያ ስር… የተሰፈረ እና በልካቸው ስራ ሊሰጣቸው ይገባል እንጅ… ነፍሳት፣ ለመስዋዕትነት… ለህዝባዊ ብርቱ አላማ ሰልፍ ይዞ ዋጋ እየከፈለ ባለ አላማ መር ተቋም ውስጥ፣ ያለ ምጣኔ እና ከልካይ በሚስጥር አወቅ ምስለኔነት እንዳሻቸው እንዲቧችሩበት እድል መስጠት፣ ነጭ ስህተት፣ በጓዶች ደምም መቀለድ ነው። የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ ይህ ሰሞነኛ አክቲቪስት ወለድ ክፍተቱን… በራሱ የውስጥ አሰራር ይፍታው። ይሄን የማድረግ ሃቅም እንዳለውም እንገነዘባለን። ይህ፣ ማለት… አየሩን ከያዙት የየአክቲቪስቱ ተተንታኝ ችግሮች ሁሉ… "ተቋሙ ነፃ ነው፣ ችግሩ ውጫዊ ነው" ለማለት አይደለም። ዛሬ ላይ፣ አየሩን የያዙት፣ በነጭ፣ ነጭ መርህ አልባ አክቲቪስቶች… እየተነተኑ አየሩን የተቆጣጠሩባቸው ጥቂቶቹ ችግሮች… እኛ አስቀድመን በውስጥ ደፍረን ስንታገላቸው የነበሩ እባጭ ህመሞች ናቸው። በፍጥነት፣ ከነዚህ የሳይበሩን አየር ከሞሉት ውስብስብ ችግሮቹ የተላቀቀ አፋጎ፣ በቅርብ ቀን እናያለን የሚል ተስፋ አለኝ። ለጊዜው ግን… "አንድ አምሓራዊ ተቋም እንዲወለድ እሻለሁ፣ የምተጋውም ለዚያ አላማ ነው" ሲል የሚዘበዝበን ዘመዴ… የተፈጠሩ፣ ክፍተቶችን በተቋማዊ አሰራር ችግራቸውን እንዲፈቱ፣ ትልቁን ጉዳይ ለአፋጎ ተቋም… ትልቅ የቤት ስራ አድርጎ እንዲተው ማሳሰብ የሞዐ ሚዲያ አቋም ነው። አክቲቪስት ሆኖ… መረጃን ከማሳዎቅ ባለፈ፣ በተገነባ ተቋም ውስጥ ወፎቼ በሚላቸው ቅልብተኞቹ ጠልቆ እና ሰርጎ ገብቶ፣ ሚስጥረ አዋቂ ተልዕኮ መር ከፋፋይ ፕሮፖጋንዳን ማሳለጥ… የተቋም መገንባት መሻትን ሳይሆን… ከፋፋይ ሚና መጫዎት ነውና! እንደ ማጠቃለያ…! አፋጎ…! በአደባባይ በተሰጡት እና ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ችግሮቹ ላይ ትኩረት አድርጎ ይስራ… • የአንድ ድርጅታዊ መዋቅር አሰራርን ያልተከተለ፣ ለትግሉ ባለው ፋይዳ ባልተተነተነ አኳኋን መረጃ የመሸጥ እና መለወጥ ንግድ ላይ በተሰማሩ • በመዋቅሩ መካከል በመሆን በደብል ኤጀንትነት ለጠላት የሚሰራውን… በውስጥ የፋኖ ኢንተለጀንስ አነፍንፎ በመድረስ መቀጣጫ በማድረግ • ትግላችን፣ የገቢ ማግኛ፣ የሀብት ማደራጃ የሆነለትን ዘራፊ እና ቀማኛ ዋሽቶ አደር የፎቶ አርበኛውን አበጥሮ በመለየት • አንድ አምሓራዊ አንድነትን ገፊ፣ ጎጣዊ አጀንዳ አሳላጭ እና ፀረ አንድነት ሴራ አሳላጭ ቅጥረኛውን ለይቶ በመድረስ • በግላዊ ውሳኔ፣ ዘግናኝ ጭካኔ የተሞላባቸው ፀረ አምሓራ ድርጊቶችን በድርጅቱ ስም፣ በህዝብ ላይ የፈፀሙ እና ያስፈፀሙትን በጥልቅ ግምገማ በማጥራት • ከዋናው ፋሽስት ጠላት ይልቅ፣ በሀሳብ እና አካሄድ የተለየው ተዋጊን ኢላማ በማድረግ ስም አጠልሽነት ራስን ወጊ አካሄድ፣ እንዲሁም የተጋነነ ጎጅ ለሀሰት የቀረበ ፕሮፖጋንዳን በሚያሳልጥ ላይ… • የቀን እና የሌሊት ወፍነት ሚና በመጫወት፣ ተቋሙን ሚስጥር አልባ በማድረግ፣ በ 2 ማልያ በመጫወት ስምሪት ላይ የተገኙ ተዋረዳዊ አባላትን፣ ጥልቅ ግምገማ በማድረግ አስተማሪ ማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ፣ ከአፋጎ በላይ ራዕዬ ፋኖ ለሆነው አምሓራዊ አንድነት መሪ ሚና ተጫዋች በመሆን ተቋሙ የምስራች እንደሚያሰማን ተስፋ እናደርጋለን። ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ #ድል- ለመላው አምሓራ ፋኖ! 26/04/2017 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 https://t.me/Moamediamoresh https://t.me/Moamediamoresh
በማህበራዊ ሚዲያው መድረክ፦ ሁሉም… የየራሱን ጎራ ግለ ንጉስ… ዜና መዋዕል እና ገድልን አግዝፎ ጸኃፊ እና ተራኪ በሆነበት ሁኔታ "#አምሓራዊነት" የቱጋ ያብብ⁉️ የቱጋ⁉️ የራስ ያልነውን ለማንገስ፣ የሌላ ያልነውን የራስ ወንድም በማኩሰስ፣ በስም አጥፊነት መሰለፍ ደግሞ… የድንቁርናና የኋላ ቀርነታችን መታያ ሆኗል። የስህተታችን መሰረት ደግሞ ክብረ አምሓራዊነት ከፍታችንን የመረዳት ኃቅም ማጣታችን ነው። #አበ ድል - ክብረ መሰረታችንን እናጥብቅ! ከዚያ በታች ያለው ንቃተ አንካሳነት መታያ የሆነው "#ጎረኝነት" የአምሓራዊ አንድነታችን ሳንካ፣ ካንሰርም ነው። እርግጥም ትግሉ የገባው፣ የኃቅ ሰልፈኛ… በግልፅም፣ በህቡም ከሚያራምደው የጎጥ እና ጎራ ኩሸታዊ መወድስም፣ ማኩሰስም አሻጥራዊ ኋላ ቀር መስመሩ ይውጣ እና ትግሉን በምክንያታዊ እውቀት እና ፋይናንስ ይደግፍ! https://t.me/Moamediamoresh
በማህበራዊ ሚዲያው መድረክ፦ ሁሉም… የየራሱን ጎራ ግለ ንጉስ… ዜና መዋዕል እና ገድልን አግዝፎ ጸኃፊ እና ተራኪ በሆነበት ሁኔታ "#አምሓራዊነት" የቱጋ ያብብ⁉️ የቱጋ⁉️ የራስ ያልነውን ለማንገስ፣ የሌላ ሆነ ያልነውን የራስ ወንድም ማኩሰ ደግሞ… የድንቁርናና የኋላ ቀርነታች መታያ ሆኗል። የስህተታችን መሰረት ደግሞ ክብረ አምሓራዊነት ከፍታችንን የመረዳት ኃቅም ማጣታችን ነው። #አበ ድል - ክብረ መሰረታችንን እናጥብቅ! ከዚያ በታች ያለው ንቃተ አንካሳነት መታያ የሆነው "#ጎረኝነት" የአምሓራዊ አንድነታችን ሳንካ፣ ካንሰርም ነው። እርግጥም ትግሉ የገባው፣ የኃቅ ሰልፈኛ… በግልፅም፣ በህቡም ከሚያራምደው የጎጥ እና ጎራ ኩሸታዊ መወድስም፣ ማኩሰስም ኋላ ቀር መስመሩ ይውጣ እና ትግሉን በምክያታዊ እውቀት እና ፋይናንስ ይደግፍ! https://t.me/Moamediamoresh
ታች ሰፈር፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ዘምተውበት አየን‼️ እኛ ደግሞ አምሓራዊ ትከሻ፣ ጋሻ መከታው ሆነን ለህልውና ትግሉ በቻለው ሃቅም እንዲያግዝ፣ አምሓራዊ መሰባሰቢያ ማዕከላችን ውስጥ ሚነኛ ቁም ነገር እንዲሰራ እድል ፈጣሪ እና አመቻች ልንሆን ይገባል። አምሓራውያን ሁሉ… የሚሰባሰቡበት፣ የሚመክሩ፣ መፍትሄ የሚቀምሩበት የዛሬ እና ነገ እጣ ፋንታችንን በያኝ አንድ ፖለቲካዊ ማዕከል፣ አንድ ንቁ ማህበረ ፖለቲካዊ ህዝብን ለመገንባት፦ •ገፊነትን • ፈራጅነት • ከሳሽነት • ወንጃይነት • ወቃሽነት • ተችነት • አሸማቃቂነት… ሊቀዛቀዙ… መድረክ ሊያጡ እና በይደር ሊቆዩ ይገባል። ይልቅ፦ እንደ ገዱ አንዳርጋቸው አይነቶች፣ በኢጎ ሳይወጠሩ፣ በትላንታቸው ምስለ ከፍታ ታሪክ ሳይቸበቡ ህዝባቸውን ይቅርታ ጠይቀው፣ ለፍርድ ራሳቸውን ላዘጋጁ…፣ በፓርላማ መድረክ ላይ በይፋ ለአማራ ትግል ወግነው የተሰለፉ፣ የካሳ እድል ሊሰጣቸው ይገባል። በአምሓራውያን መካከልም፦ • ይቅርታ • ውይይት • ምክክር • መመሳጠር • መተጋገዝ • መደራጀት • መተባበር • በትህትና ጓዳዊነት፣ በቀና ልቦና መገሳሰፅ እንጅ… በቂም እና መፈራረጅ፣ በስልጣን ግፊያ እና ኢጎ ኮፍታ መጓተት ማብቃት አለበት። #አንድ አምሓራዊነት… በይቅርታ መድረክ ማበብ፣ መጎምራትም እንዲችን የትግሉ አባቶች የቤት ስራ ነው። ጠላት… የትላንቱን መጎሻሸሙን ትቶ በአንድነት… ወያኔ በTDF፣ ኦነጋውያኑም የገዳ ኃይል ሆነው ከበው እየወጉን ሳለ… እኛ በደማችን ጎርፍ እየታጠብን፣ ለልዩነት እና መካሰስ አድብተናል። ከዚህ በኋላ ይህ፦ መቆም አለበት! ታላቁ! ብሄረ መድህናችን #አምሓራዊ ኃይል ገዝፎ እንዲቆም… ሁሉም የአምሓራ፣ ሁሉም ኃቅም … በየ ጎራው "#ሞረሽ!" ብሎ ተጠራርቶ ሊነጋገር ይዘጋጅ! https://t.me/Moamediamoresh
አሳዛኝ ሰበር ዜና‼️ =================== ኢሰመጉ በብልፅግና ታገደ‼️ አንጋፋው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በመንግስት መታገዱን ተሰማ። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ኢሰመጉን ያገደው፣ ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል በማለት ነው። የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአመራሮቹ፣ ሠራተኞቹ እና አባላቱ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚፈጽሙ ለበርካታ ወራት ሲገልጽ የቆየው ኢሰመጉ፣ ዋና ዳይሬክተሩ ዳን ይርጋ በዚኹ ዛቻና ማስፈራሪያ ሳቢያ ከአገር ለመሰደድ እንደተገደዱ በቅርቡ መግለጡ ይታወሳል። ባለሥልጣኑ በዲሞክራሲና መብቶች ዕድገት ማዕከል እና ጠበቆች ለሰብዓዊ መብቶች በተሰኙት ሲቪል ማኅበራት ላይ ባለፈው ኅዳር ወር በተመሳሳይ ምክንያት ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ፣ ድርጅቶች የተሰጧቸውን የማስተካከያ ርምጃዎቾ ተግባራዊ አላደረጉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ጥፋታቸውን ቀጥለውበታል በማለት በቅርቡ በድጋሚ እንዳገዳቸው አይዘነጋም። https://t.me/Moamediamoresh
እንደ አማራ አንድ ሆነን የቆምን ቀን…ከፊታችን የሚቆም የሚገዳደረን ኃይል አይኖርም‼️ #ታላቁ አምሓራዊ ታጋይ ክርስቲያን ታደለ https://t.me/Moamediamoresh
ጫካ የሸፈናቸው የመሬት ላይ ነብር ንስር ፋኖዎቻችን ዛሬም ጥብቅ መልዕክት አላቸው። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ "የአማራ ፋኖ እና መሪዎቹ፣ በወጉ ቁጭ ተብሎ፣ ጊዜ ተሰጦት፣ መስመረኛ የአማራ ብሔርተኛ ጥበበኞች እና ንስሮች በተበጀ የአማራ የመጨረሻ ደረጃ ብሔርተኝነት የመብቃት ማረጋገጫ ወንፊት ማለፍ አለባቸዉ የሚል ጥብቅ እምነት አለኝ!! ማሸነፍ የሚጀምረዉ ከሀሳብ ሲገፋ ከወረቀት ነዉ። ይህ ማለት ሌላ አይደለም ከአላማ ሽክፍነት፣ ከይሉንታ ከፀዳ አላማ፣ በመጀመሪያም በመጨረሻም ለህዝቤ (ለነገዴ/ለወገኔ) በሚል በፍቅረ ወገናዊ ጓዳዊነት ወጋግራ ከቆመ አላማ ነዉ። ከዚህ ፍሬ ነገር ተነስተን በግርድፉ ብንገምት የቱ ወይስ የቷ የፋኖ መሪ በወንፊቱ በኩል ያልፋል? የትኛዉ የአማራ ተቋምስ አሻጋሪ ዋስትና ሰጭ ራዕዬ መድህን የሆነ ፅኑ አላማ አለዉ? ፍርዱን እንሆ ለእናተ ንቁ አማራዊያን ሁሉ ተዉኩ!! ሆኖም፦ "ገና ስራ አለብን" የሚል መልዕክቴ በአንደኛው እጄ ነፍጥ ይዤ በሌላኛው እጄ ላነሳሁት ብዕር ምክንያት ነው። © ፋኖ ገ/ማሪያም አግማስ የፊታውራሪ ሞትባይኖር ሻለቃ መሪ እና የአተማ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ https://t.me/Moamediamoresh
በጨካኞቹ አውሬዎች የተጨፈጨፉ አማራዎች ሁሉ በየዘመናቸው ፥ በየታሪካቸው የሚመዘገቡበት፣ የሚዘከሩበት ብሔራዊ መታሰቢያ እናቆማለን ‼ በአማራ ልጆች ደምና ላብ የሚቆም እና ደም-መላሽ የፍትሕ ቀናኢነታችንን የምናረጋግጥበት ይሆናል ‼ << መቼምና የትም እንዳይደገም >> የተባለው የቀይ ሽብር ክፋት በሌላኛው የኦሮሞ ኮለኔል አብይ አሕመድ የተባለ Butcher ተደግሟል። ኢትዮጵያ ከአርባጉጉ እስከ መተከል፣ ከጉራ ፈርዳ እስከ ወልቃይት፣ ከወለጋ እስከ መርዓዊ የሆነውን ሁሉ "የአማራ ዘር ማጥፋት መርማሪ ኮሚሽን" በማቋቋም ፍትሕ ታነግሳለች ብለን እንጠብቃለን። የአማራ ትግል ግን ታሪክ ይቀይራል ‼ የምንዘነጋው የአማራ ሰማዕት አይኖርም ‼ -- በአለም ላይ የተፈፀሙ መሠል ግፎች ሁሉ እንዳይመለስ የሚያደርጉ መታሰቢያዎች ቆመውላቸዋል። በፎቶው እንደሚታየው ያለ። https://t.me/Moamediamoresh