ፍትሕ ለአምሓራ!
Статистикаፍትህ ልብን ትጠግናለች! #እኛ፣ የፍትህ አወቅ አበው ልጆች ነን! የፍትህ አደባባዩን በክንዳችን እንፈጥራለን!
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 26
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 157
- 1/48двое суток
- 179
- 1/72трое суток
- 194
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
🔥#ሰበር_ዜና‼️ በምስራቅ ወለጋ እና በሆሩ ጉዱሩ ዞኖች የአንሻ ሰይድ ዕዝ አናብስቶች በጥላት ጥምር ጦር ላይ ድል ተቀዳጁ‼️ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓም በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን ከተማ መውጫ ላይ ጌጤ ግርማ መብረቅ ክ/ጦር፣አንገር ጉትን ክ/ጦር እና አበጀ ጥበቡ ነበልባል ክ/ጦር በደፈጣ ባንድ በመናበብ የክልሉ ገዳይ ኮማንዶ ላይ አንፀባራቂ ድል ተቀዳጁ። ትናት አዝረክርኮት የወጣውን አስክሬን ለማሳት በርካታ የክልሉ ጥምር ጦር በመያዝ ዛሬ ረፋድ 4:00ላይ ከአንገር ጉትን ከተማ በመነሳት ከዚያው ከከተማዋ መውጫ በር #ኢንጅሮ ላይ ተግተልትሎ ሲመጣ ካስክሬኑም ሳይደርስ የአንሻ ሰይድ አናብስቶች ዶግ አመድ አድርገውታል።በመጨረሻም ወደ መሀል ከተማዋ በመሸሽ በፍርኀት ቤት ዘግተው የጠቀመጡ ንፁኋን አማራዎችን ቤቶችን ገጥሎ በመግባት ህፃናትን፣እናቶችንና አዛውንትን ባደባባይ መስመር ላይ አያወጡ እየረሸኑ ይገኛሉ። ለክልሉ ህዝብና ለሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ንፁሃን ላይ እየተደረገ ያለ የዘር ጭፍጨፋ ባስቸኳይ የማይቆም ከሆነ ግጭቱ ወደ ህዝብ ለህዝብ መግባቱ አይቀሬ ነው። በሌላኛው በሆሩ ጉዱሩ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ሎምጫ ቀበሌ ላይ ታፈረ አለሙ ሳተናው ክፍለጦር እና "የሃሳብ ልዩነትን በንግግር ለመፍታት በሂደት ላይ ያለውን ፅናት ክ/ጦር በመናበብ ሎምጫ ቀበሌ የክልሉ ጥምር ጦር ላይ እርምጃ በመውሰድ ከተማዋን መቆጣጠር ተችሏል።የጥላት ጥምር ጦርም የተረፈው ወደ ደንጎሮ ከተማ ፈርጧል። በአንገር ጉትን ከተማ ሶስቱ ክፍለጦሮች በምርኮ ያገኟቸው ቁሳቁሶች፦ 👉ከስልሳ(60)በላይ ይህ ገዳይ ሃይል የተደመሰሰ 👉አንድ(1)ብሬን 👉አርባ ሁለት(42) የነፍስ ወከፍ ክለሽ 👉በርካታ የብሬ እና የክላሺ ተተኳሾች F1 ቦንቦች ከተለያዩ ትጥቆችና ወታደራዊ ሻንጣዎች ገቢ ሲሆኑ ፦ በተጨማሪም በሆሩ ጉዱሩ አቤደንጎሮ ወረዳ ሎምጫ ቀበሌ ላይ በሁለቱ ክፍለጦሮች በምርኮ የተግኙ፦ 👉ከ30 በላይ የጥላት ሃይል ሲደመሰስ 👉14 ክላሾችን መማረክ ተችሏል። ግፍ የወለደን:ግፈኞችን የምቀጣ የአንሻ ሰይድ ወድሞች ነን‼️ ©አፋብን ወለጋ/ቢዛሞ አንሻ ሰይድ ዕዝ ህ/ግንኙነት መምሪ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
አየር መቃዎሚያው ተመታ!/ተኳሾቹ ተገደሉ! በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወሎ ቤተ ዐምሐራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 71ኛ ክ/ጦር ስር የሚገኙት የ1ኛ ሙሐመድ ዳውድ ሬጅመንት አርበኞች ትናንት ሰኔ 21/2018 ዓ.ም በከላላ ግንባር በታላቅ የጦር ብቃት የጠላትን ኃይል በማፍረክረክ አንፀባራቂ ድል አስመዝግበዋል። በአየር መቃዎሚያና በሌሎች የሜካናይዝድ መሣሪያዎች ታጅቦ መነሻውን ከጊምባ ያደረገው የጠላት ኃይል፡ ንፁኋንን ለመጨፍጨፍ፣ ሃብት-ንብረት ለማውደምና ወረራ ለመፈፀም ወደ ሻፊ እና ባከት አከባቢዎች ለመንቀሳቀስ ሙከራ አድርጎ የነበረ ቢሆንም፡ በአርበኞቹ ልዩ የውጊያ ጥበብ ሁለትና ሦስት ቦታዎች ላይ ተቆርጦ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል። ትናንት አመሻሽ ድረስ በወሎ ቤተአማራ ቀጠና ከላላ ግንባር ሻፊና በባከት አከባቢዎች ላይ በተደረገው ተጋድሎ፡ የፋኖ አስደማሚ የፀረ ማጥቃትና የመልሶ ማጥቃት ጥበብ ሲታየ፡ በአንፃሩ የጠላት ብልፅግና ኃይሎች ከወደ ፋኖ የተወሰደባቸውን እርምጃ የሚመክቱበት ፋታ አጥተው ተሽመድምደው የዋሉበት አውደ ውጊያ ተካሂዷል። አርበኞቹ ጠላትን በሁለት አቅጣጫ ማለትም በሻፊ እና በባከት በኩል ቆርጠው ቀጠናውን በመቆለፍ ከባድ እርምጃ ወስደውበታል። በአከባቢው በተለይ ጎራዳ ተብሎ በሚጠራው ቦታ፡ ጠላት በአየር መቃዎሚያ መሣሪያ ታግዞ ከወደ ፋኖ የተከፈተበትን የፀረ ማጥቃት እርምጃን ለመቋቋም ሙከራ ቢያደርግም፡ ነገር ግን ከጥቃቱ መክበድና ከአጥቂዎቹ ፍጥነት ጋር ተዳምሮ ጠላት ሙትና ቁስለኛውን አዝረክርኮ ለመሸሽ ተገድዷል። በዚህ ተጋድሎ ሙትና ቁስለኛ ከተደረጉ የጠላት እግረኛ ወታደሮች በተጨማሪ የአየር መቃዎሚያው አፈሙዝ በፋኖ ዲሽቃ ተመቶ በእሳት ሲጋይ፡ የአየር መቃዎሚያ ተኳሹና ረዳቶቹ ፋኖ ባካሄደው የዲሽቃና የብሬን ስብጥር ተኩስ ተገድለዋል። የ71ኛ አባናደው ክፍለጦር አርበኞች ከወሰዱት ከባድ የሆነ የፀረ ማጥቃትና የመልሶ ማጥቃት ስልትን ከአንዳች አማራዊ ጀግንነትና ወኔ ጋር ያዋሃደ እርምጃ አንፃር የጠላት ከባባድ መሣሪያዎችና የሰው ኃይሉ ትርጉም ባጣበት በዚህ ተጋድሎ፡ 23 የአገዛዙ ወታደሮች ተደምስሰዋል፡ በርካታ ልዩ ልዩ የጦር መሣሪያዎችና ሌሎች ወታደራዊ ቁሣቁሶች በፋኖ ቁጥጥር ስር ውለዋል። አርበኞቹ ከሚያደርጉት የመደበኛ ውጊያ በተጨማሪ፡ የጠላት ኃይልን ስቦ ከመምታት ጀምሮ፡ በከባባድ የጦር መሣሪያዎች ሽፋን ታግዞ በሚንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ የፀረ ማጥቃት እርምጃ በመውሰድ እንዲሁም የቆረጣና የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም የብልፅግናውን አገዛዝ አሽመድምደው በድል ጎዳና እየገሰገሱ ይገኛሉ። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! በአፋብን ወሎ ቤተ- አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ሰኔ 22/ 2018 ዓ/ም
видео или голосовое, без подписи
📌 የዋርካው ጽናት፣ የማይበገሬው ሕዝባዊ መቅረዝ በወታደራዊ ሳይንስ እና በሕዝባዊ አብዮቶች ታሪክ ውስጥ፣ የአንድን ንቅናቄ ዘላቂነት እና ስልታዊ ብስለት የሚወሰነው መሬት ላይ ባለው የጦር መሣሪያ ብዛት ሳይሆን፣ ሰራዊቱን በጥበብ መርቶ አመርቂ ድል የሚያበስር እና በብዙኃኑ ዘንድ ፍጹም ተወዳጅነትና ክብርን ያተረፈ መሪ (Strategic Leadership) ሲኖር ነው። ለአንድ ሕዝብ ነፃነት ደምና አጥንት እየተከሰከሰ፣ በዘመናት የማይተኩ ጀግኖች የሚገበሩበት የሕልውና ትግል፣ በመጨረሻም የጠላትን ስሌት የሚያፈርስ ጽኑ ተቋማዊ መሠረት ይፈጥራል። ዛሬ በአማራ ምድር፣ በተለይም በታሪካዊው የወሎ-ቤተ አማራ ቀጠና፣ ለአምስት ዓመታት በደሙና በአጥንቱ ታሪክ የጻፈውና የሕዝቡ ደማቅ ኩራት የሆነው የአማራ ፋኖ እያስመዘገበ ያለው ወታደራዊ ልዕልና፣ ከዚህ ጥልቅ መሪነትና ሕዝባዊ ደጀንነት የመነጨ ነው። የዚህ ገናና ሕዝባዊ ኃይል ቁልፍ ወታደራዊ አሰባሳቢ ዋርካ፣ አርበኛ ምህረቱ “ምሬ” ወዳጆ—በደጋፊዎቹና በትግል አጋሮቹ ዘንድ “ዋርካው” በሚል የቁልምጫ ስም የሚጠራው ታዋቂ የፋኖ መሪ—የትግል ታሪክና አመጣጥ የዚህን አብዮት Organic Nature ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። ይህ ዋርካው ዋና ዓላማው ትግል ሲጀምር ለአማራ ሕዝብ ሕልውና ጋሻ ለመሆን ነበር። ዋርካው ትግል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶበወሎ ቤተ-አማራ፣ በጎንደር፣ ጎጃምና ሸዋ የፋኖ አደረጃጀቶች ላይም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፣ በሰሜኑ ጦርነት ወቅትም የምስራቅ አማራ ፋኖን በመምራት በግንባር ቀደምትነት የተሰለፈ የጦር ጠበብት ነው። የአሁኑን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) እንደ መዋቅራዊ ምሶሶ በመትከል፣ እርሱ እያደረገ ያለው እያንዳንዱ ወታደራዊና ስልታዊ እንቅስቃሴ በብዙኃኑ ሕዝብ ዘንድ እጅግ የሚወደድ፣ የሚከበርና እንደ ትልቅ ተስፋ የሚታይ ሆኗል። የአራት ኪሎው አገዛዝ የክልል ልዩ ኃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታትና ሕዝቡን መከላከያ-አልባ ለማድረግ የወሰደውን ዕውር ውሳኔ ተከትሎ፣ ምሬ ወዳጆ እና ኃይሎቹ ወደ በረሃ በመግባት የጀመሩት የትጥቅ ትግል፣ ዛሬ ላይ የአገዛዙን መጠነ-ሰፊ መዋቅር ያሽመደመደበት ታላቅ ማዕበል ሆኗል። ጫማ ሳይኖረው በባዶ እግሩ በመጓዝ፣ የረባ ስንቅ ሳይዝ ደረቅ ቆሎ እየቆረጠመ እና በሽርጡ ብቻ ተሸፋፍኖ የታገለው ይህ ሰራዊት፣ ዛሬ ላይ የአገዛዙን በርካታ ዕዞችና የሪፐብሊካን ጋርድ ልዩ ኮማንዶን በክንዱ ተቋቁሞ ድባቅ የመታበት ምስጢር ይህ የማይበገሬ መዋቅራዊ ጽናትና በሕዝብ ዘንድ ያለው ፍጹም መከበር ነው። ጦርነት አንዴ ከተጀመረ በኋላ በተራ ፕሮፓጋንዳ የማይለሰልስ መራር ጭካኔን የሚተካ ቢሆንም፣ የፋኖ ሰራዊት ግን የሞራል ልዕልናው ምን ያህል ከፍ ያለ መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል። አርበኛ ምሬ ወዳጆ በተደጋጋሚ እንደሚያሰምርበት፣ ይህ ትግል የዐማራን ሕዝብ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ፣ ሕልውናውን ለማረጋገጥ የተለኮሰ የአብዮት እሳት ነው። ይህ ግዙፍ ዋርካ ዛፍ ለራሱ የሚተርፍ አንዳችም ነገር ሳያስቀር፤ ጥላውን፣ ፍሬውንና መላ አካሉን ለሰፊው ሕዝብ መጠለያና ህልውና የሰጠ የጀግንነት እና የፍቅር ተምሳሌት ነው። ለዚህ ሁሉን ነገር ለሕዝብ ለሰጠ፣ ስለ ወገኑ ሲል ራሱን ላሳጣ ታላቅ ዋርካ ምንጊዜም የሚላቅ ምስጋና ይገባዋል። የጣለው የራስን ጥቅም የመካድና የመስዋዕትነት መሰረት፣ ለሕዝብ የመኖርን ጥልቅ ሚስጥር ያስተማረን ህያው ተምሳሌታችን ነው። ለከፈለው ወደር የሌለው መስዋዕትነትና ለታላቅ ልግስናው ምስጋናችን የላቀ ነው! ትግላችን ያሸንፋል!
видео или голосовое, без подписи
√ የማጥቃት ስልት (The Attack Strategy) አንድ ሰራዊት እንደ ተኩላ መንጋ (Wolfpack) ውጤታማ እና ገዳይ እንዲሆን፣ የማጥቃት ስልቱ በጭፍን ጉልበት ላይ ሳይሆን በከፍተኛ ብልሃት፣ በትዕግስት እና በጋራ ቅንጅት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። ተኩላዎች የሚያድኑበትን ተፈጥሮአዊ ጥበብ ወደ ወታደራዊ ስልት ስንቀይረው የማጥቃት ስልቶች እናገኛለን፡- 1. የከበባ እና የማግለል ስልት (Isolate and Encircling) ተኩላዎች የአንድን ትልቅ ከብት መንጋ ሙሉ በሙሉ አይጋፈጡም፤ መጀመሪያ መንጋውን በማስፈራራት እንዲበታተን ያደርጋሉ፣ ከዚያም ደካማውን ወይም የተለየውን ክፍል ነጥለው ያጠቁታል። የአፋብን ሰራዊቱ የጠላትን ዋና ምሽግ ከመምታቱ በፊት፣ የጠላትን አቅርቦት መስመር፣ የመገናኛ ዘዴዎችን ወይም የተለዩ ትናንሽ ክፍሎችን በመምታት ከዋናው ጦር ማግለል (Isolate) አለበት። ጠላት ተከፋፍሎ አቅሙ ሲዳከም በተለዩት ክፍሎች ላይ ማተኮር አለበት ። 2. "የመንጋ ማጥቃት" ስልት (The Wolfpack Tactics) ይህ ስልት ጠላትን ከአንድ አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ አቅጣጫዎች በተመሳሳይ ሰዓት በትናንሽና ተንቀሳቃሽ ቡድኖች ማጥቃትን ያካትታል ። የአፋብን ሰራዊቱ በትናንሽ ልዩ ተኳሽ ቡድኖች (Fireteams) ይከፋፈላል ፣ አንደኛው ቡድን ከፊት ለፊት ጠላትን ሲያስቆጣና ትኩረት ሲያስቀይስ፣ ሁለተኛው እና ሶስተኛው ቡድን ከጎንና ከጀርባ (Flanking) ድንገተኛ ጥቃት ይሰነዝራሉ። ጠላት ወዴት መዞር እንዳለበት ግራ እስኪገባው ድረስ የማያቋርጥና ተለዋዋጭ ጥቃት ማድረስ ይቻላል ። 3. የማድከም እና የማፈግፈግ ስልት (Feigned Retreat & Attrition) ተኩላዎች ሰለባቸውን በአንድ ጊዜ ለመጣል አይጣደፉም፤ እየነከሱ በማፈግፈግ ሰለባቸው ደም እስኪፈሰው እና እስኪደክም ድረስ ያባርሩታል። የአፋብን ሰራዊቱ "መታህ መሸሽ" (Hit and Run) ስልትን ይጠቀማል። ጠላትን በድንገት በመምታት ወደ ኋላ ማፈግፈግ፤ ጠላት የተሸነፉ መስሎት ሲያሳድድ አስቀድሞ ወደተዘጋጀ የደፈጣ ቀጠና (Ambush Zone) እንዲገባ ማድረግ እና እዚያ ውስጥ ማጥፋት። ይህ የጠላትን ጥንካሬ እና ስነ-ልቦና ቀስ በቀስ ያደክማል። 4. የስነ-ልቦና ሽብር እና ድንገተኛነት (Psychological Shock & Surprise) ተኩላዎች ከማጥቃታቸው በፊት በሚያሰሙት አስፈሪ ድምፅ የጠላታቸውን (የሰለባቸውን ) ልብ ያሸብራሉ። በጦርነት ላይ ፍርሃት የሽንፈት ግማሽ መንገድ ነው። ጠላት ፍጹም ባልጠበቀው ሰዓት (ለምሳሌ በሌሊት፣ በከባድ አውሎ-ነፋስ ወይም በጭጋግ ውስጥ) እና ባልገመተው አቅጣጫ መብረቃዊ ጥቃት መሰንዘር። ጠላት መከላከያ ሳይዘረጋ እና ሳይደራጅ በፊት በመደናገጥ ውስጥ እያለ መደምሰስ። 5. የመጨረሻው ገዳይ ንክሻ (The Decisive Strike) ተኩላዎች ሰለባቸው ሙሉ በሙሉ መዳከሙን እስኪያረጋግጡ ድረስ ትልቁን ጥቃት አይሰነዝሩም። አንዴ ግን ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ ሁሉም በአንድነት ወሳኙን ጥቃት ያደርሳሉ። ከላይ በተጠቀሰው ስልቶች የጠላት የመከላከል አቅም መፈራረሱን፣ መገናኛው መቆረጡን እና ወታደሮቹ መልፈስፈሳቸውን ሲያረጋግጡ፣ ሁሉንም ጥንካሬ (የጦር መሳሪያ እና የሰው ሃይል) በአንድ ላይ በማስተባበር ጠላት ዳግም እንዳያገግም አድርጎ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መደምሰስ ይቻላል ። እንደ ተኩላ ማጥቃት ማለት "ብልህ መሆን፣ በጥንካሬ ላይ አለመታመን፣ የጠላትን ድክመት መፈለግ፣ በጋራ ማጥቃት እና ማፈግፈግን እንደ ስልት መጠቀም" ማለት ነው። ይህ ስልት በተለይ በቁጥር ለሚያንስ ነገር ግን በስልጠና ለበለፀገ ሰራዊት ፍጹም አውዳሚ መሳሪያ ነው። አፋብን ማጥቃት እንዴ ተኩላ ንቃ አማራ ።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ግባ በለው💪 የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አሃዶች በሰሩት ከፍተኛ የደህንነት ስራ የብልፅግናውን አየር ወለድ ክፍለጦር አመራሮች በሥቦ ማስካዳት ውጤታማ ተግባር መፈፀሙን ኮሩ አስታወቀ። አፋብን ሸዋ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ ከአዲስ አበባ መናገሻ ቤተ-መንግሥቱ ደጅ አፍ ላይ የሚገኘው የከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር የፋኖ ሰራዊት የአገዛዙን ዙፋን አሥጠባቂ 112ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር አመራሮችን ሥቦ በማሥከዳትና ከፍተኛ የውጊያ ሽፋን በመስጠት የአገዛዙን ወታደራዊ ቁልፍ አመራሮች ማስኮብለሉን ኮሩ በምስል አስደግፎ በላከው የግንባር መረጃ አስታወቀ። ጠላት የከዱትን አመራሮቹን ለመያዝ ከንጋቱ 10:00 እስከ 12:00 ድረስ ባደረገው የውጊያ ሙከራ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር አናብስቶች በአገዛዙ ወራሪ ሰራዊት ላይ የአፀፋ እርምጃ በመውሰድና ፋኖን አምነው የመጡ ሁለት ከፍተኛ የ112ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር አመራሮችን ከነሙሉ የደህንነት ጥበቃ ጋር መቀበሉን ዕዙ በመረጃው አረጋግጧል። ጀግናው የአማራ ፋኖን የተቀላቀሉት የአገዛዙ አየር ወለድ ቁልፍ አመራሮች:- 1ኛ. ፻ አለቃ ዋቆ አባድባ ✅ማዕረግ ፻ አለቃ ✅ ኅላፊነት ሻለቃ መሪ ✅(1) መገናኛ ሬዲዎ ✅ (1) ሀዲድ ክላሽ ከ120 በላይ የክላሽ ተተኳሽ ✅(03) ቦምብ በመያዝ ፋኖን ሲቀላቀል 2ኛ. ፶ አለቃ ግርማ አበረ ✅ማዕረግ ፶ አለቃ ✅ ኅላፊነት ጋንታ መሪ ✅ (01)ሀድድ ክላሽ ✅160 የክላሽ ተተኳሽ ✅(03) የክላሽ ካዝና እና ሙሉ የደረት ትጥቅ በመያዝ የኃ/ማርያም ማሞ ክፍለ ጦርን ሲቀላቀሉ በየደረጃው ባሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል ሲል የከሰም ፪ኛ ኮር በላከው የግንባር መረጃ አስታውቋል። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ሬማ ከተማ የመሸገው የብልፀግናው 101ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር አባላት መካከል ትላንት ምሽት በተፈጠረ አለመግባባት በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ጥቂት የማይባሉ የሰራዊቱ አባላት መጎዳታቸውን የውስጥ አርበኞች መረጃውን ያደረሱ ሲሆን በአገዛዙ ሰራዊት መካከል ከፍተኛ አለመተማመን መፈጠሩን ጠቁመዋል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 10/2018ዓ.ም
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
https://youtu.be/2fk3kWpx-4Q?si=flii19th_CVi6HK2
የአደረጃጀት ዜና ከአውደ ውጊያ ጎን ለጎን ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ አደረጃጀትን የማዘመን ስራዎች በወሎ ቤተ-አማራ ተጠናክረው ቀጥሏል! የአማራ ሕዝብ እያደረገ ባለው የሕልውና ተጋድሎ ዘመን አይሽሬ እና አንፀባራቂ ተጋድሎ እያደረገ የሚገኘው የምስራቅ ኮኮቦቹ ስብስብ የሆነው ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር አንድ ሳምንት የፈጀ ጥልቅ የስራ ግምገማ በማድረግ የኮር አደረጃጀቱን በመስራት የአመራር መዋቅሩን ይፋ አደረገ! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ጥልቅ የስራ ግምገማ በማድረግ ለህልውና ትግሉ ስኬታማነት በሚመጥን መልኩ አደረጃጀቱን በመስራት መዋቅሩን ማዘመኑና ይፋ ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞም በስሩ የሚገኙ ኮሮችን ጥልቅ የስራ ግምገማና ተሃድሶ በማድረግ እያደራጀ ይገኛል:: በዚህ መሰረት የምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ 101ኛ ኮር አንድ ሳምንት የፈጀ ጥልቅ የስራ ግምገማና ተሃድሶ በማድረግ የሰራው አዲሱ የአደረጃጀትና የአመራር መዋቅር እንደሚከተለው ይሆናል፦ 1. ሰብሳቢ____አርበኛ ጌታሁን ሲሳይ 2. ወታደራዊ አዛዥ_____አርበኛ ደባሽ መምሬ 2.1 ም/ወታደራዊ አዛዥ__አርበኛ እንድሪስ ጉደሌ 2.2 ዘመቻ መምሪያ__አርበኛ ካሳ አበበ •ም/ዘመቻ መምሪያ_____አርበኛ አድኖ ሲሳይ •መገናኛ ሃላፊ_____አርበኛ** 2.3 ሎጀስቲክስ_____አርበኛ ጋሻው ንጉስ •ስርጭት______አርበኛ ሞሃመድ ትኩ •ኦርድናንስ____አርበኛ መቶ አለቃ ጥበቡ ታከለ 2.4 ስልጠና መምሪያ__አርበኛ አምሳ አለቃ ሲሳይ አሰፋ 3. ወታደራዊ አስተዳደር__አርበኛ ገብረፃዲቅ መሸሻ 3.1 ፋይናንስ_____አርበኛ በላይ ንጋቴ 3.2 ኦዲተር___አርበኛ አብዱ ዘመን 3.3 ህክምና ሃላፊ___አርበኛ ንጉስ እያሱ 3.4 የሰው ሃይል___አርበኛ ጌታሁን ረዳይ 3.5 ሃብት አፈላላጊ___አርበኛ ወንድሙ እንዳሻው 4. ፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ_____አርበኛ ዝናቡ አድኖ 4.1 ህዝብ ግንኙነት __አርበኛ ንጉስ አበራ •ሚዲያና ኮምንኬሽን_____አርበኛ ጥላሁን ገሰሰ 4.2 አደረጃጀት ሃላፊ__አርበኛ አሰፋ መለሰ 4.3 ህዝብ አስተዳደር___አርበኛ ጌታየ ተስፋየ 4.4 ህግ ክፍል____አርበኛ ሰይድ የሱፍ 4.5 መረጃና ደህንነት___አርበኛ * መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ101ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኋላፊ አርበኛ ንጉስ አበራ መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 8/2018 ዓ.ም
видео или голосовое, без подписи
🧨በምርጫ ስም የሚነገድ ደም፦ የሽሮ ሜዳው ግድያና የብልጽግና "ነፃ እርምጃ"! (ሙሉጌታ አንበርብር) አገዛዙ "ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አደርጋለሁ" እያለ በየመድረኩ በሚያላግጥበትና የውሸት ትርክት በሚያመርትበት በዚህ ሰዓት፣ መሐል አዲስ አበባ ላይ ግን ዜጎችን አድኖ የመግደል "ነፃ እርምጃ" በይፋ ተጀምሯል። ዛሬ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት፣ የሥርዓቱን አምባገነንነትና የሕግ አልባነቱን ጥግ ለዓለም ያሳየ ሌላው ጥቁር ጠባሳ ሆኖ ተመዝግቧል። ወጣት ተገኝ ባልቻ (በቅፅል ስሙ ኦሮሮ) የተባለው የሽሮ ሜዳ ነዋሪ፣ በፖሊስ ተይዞ ከተወሰደ በኋላ በሕግ ጥላ ስር ሆኖ ሊጠበቅ ሲገባው፣ እዚያው ጽሕፈት ቤቱ በር ላይ በአራት ጥይት ተደብድቦ እንዲገደል ተደርጓል። ይህ ድርጊት "ሕግ ማስከበር" ሳይሆን በጠራራ ፀሐይ የተፈጸመ የመንግሥት ሽብር ነው። አንድን ዜጋ በቁጥጥር ስር ካዋሉ በኋላ ፍርድ ቤት ከማቅረብ ይልቅ፣ በፖሊስ ጣቢያ ደጃፍ ላይ በጥይት መረሸን፣ አገዛዙ ከሕግ በላይ መሆኑንና ለሰው ልጅ ሕይወት ቅንጣት ታክል ክብር እንደሌለው ማረጋገጫ ነው። የሚገርመው ግን፣ ይህ ግድያ የተፈጸመው ሥርዓቱ "ምርጫ እያካሄድኩ ነው" በሚል ዓለምን ለማታለል በሚሞክርበት ወቅት መሆኑ ነው። በምርጫ ስም የሚነገድ ፖለቲካና በየመንገዱ የሚፈስ የዜጎች ደም አብረው ሊሄዱ አይችሉም። ወጣት ተገኝ ባልቻ የተገደለው በፈጸመው ጥፋት ሳይሆን፣ አገዛዙ በሕዝብ ላይ የጀመረው የማሸማቀቅና የኃይል እርምጃ ሰለባ በመሆኑ ነው። "ነፃ እርምጃ" በሚል ስም በከተማው ወጣቶች ላይ እየተወሰደ ያለው ግድያ፣ የሥርዓቱን የመጨረሻ የውድቀት አፋፍና የጭንቀት መግለጫ መሆኑን ልንረዳ ይገባል። ይህ በሽሮ ሜዳ የፈሰሰው ደም፣ አገዛዙ ስለ ሰላምና ስለ ልማት የሚያወራው ወሬ ሁሉ መሠረት የሌለው መሆኑን ይመሰክራል። መሐል አዲስ አበባ ላይ ዜጎችን በፖሊስ ጣቢያ ደጃፍ የሚረሽን ሥርዓት፣ ነገ ደግሞ ወደ ማንኛው ቤት ገብቶ ጥይት እንደማያዘንብ ምንም ዋስትና የለም። የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህንን በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎችን የመረሸን አደገኛ አካሄድ በጽኑ ሊያወግዘው ይገባል። ወጣት ተገኝ ባልቻ የዛሬው የብልጽግና መሥዋዕት ቢሆንም፣ የፈሰሰው ደሙ ግን የግፈኞችን ዕድሜ የሚያሳጥር እንጂ የሚያራዝም አይሆንም። በምርጫ ስም እያላገጡ ዜጎችን መግደል የታሪክ ተጠያቂነትን ያስከትላል። ለወዳጅ ዘመዶቼ መጽናናትን እመኛለሁ፣ ፍትሕ ለወጣት ተገኝ ባልቻ! ፍትሕ በግፍ ለሚገደሉ የኢትዮጵያ ልጆች!