tgindex
ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

Статистика
@Historicalheromediaанглийский

በዩትዩብ ቻናላችን ሰብስክራይብ ያድርጉ 👉https://www.youtube.com/@Historicalheromedia ጥቆማ ለመስጠት 👇👇👇 @ethiotemsaletbot

Последний пост
18 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
34
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 794
−6 за 4 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
999
34 постов
Вовлечённость
26,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 34
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 18 июл.1 07562

    💔💔💔የሰኔ ሰባቱ ጥቁር ጠባሳ💔💔💔 ሰኔ ሰባት ቀን... የቀን ክፉ፣ የዕለታት ጨለማ፣ ደስታዬ ተሰርቆ፣ ጩኸቴ የተሰማ። የሞት ጥላ ወርዶ፣ የቤቴን አጥር ጥሶ፣ እምባዬ ፈሰሰ፣ እንደ ጎርፍ ተቅበዝብዞ። ወንድሞቼ... የደስታዬ ምንጭ፣ የትከሻዬ አጋዥ፣ በድንገት ተነጠቅኩ፣ የዓለምን ግፍ ላዋይሽ? ሰማዩ ተደፋ፣ ምድሪቱም ጨለመች፣ ነፍሴ በዚያች ዕለት፣ ከራሷ ጋር ተጣላች። በረሩ እንደ ወፍ፣ ጥለውኝ በድንገት፣ የልቤን ስብራት፣ ማን ሊጠግነው በትዕግሥት? ዓመታት ቢነጉዱ፣ ቀኑ ቢለዋወጥ፣ ያ የሰኔ ሰባት ጠባሳ፣ ከውስጤ አይለወጥ። ጽናቱን ይስጠኝ፣ የነፍሳቸውን እረፍት፣ በብርሃን ማረፊያ፣ በፈጣሪ ገነት። እስክንገናኝ ድረስ፣ በዚያኛው ዓለም፣ የእናንተ ትዝታ፣ ከልቤ አይጠፋም... መቼም!

  • без подписи

  • 15 июн.1 94010

    ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው አረፈ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አበርክቷል፡፡ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር። ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ነፍስ ይማር

  • 13 июн.1 66832

    እየመጡ ነው በስቦ ማስከዳት የተካነው ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ የብልፅግና ወታደሮች የተደረገላቸውን ጥሪ በመቀበል ፋኖን በሰላም መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል! ሰኔ 06/018ዓ'ም አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን )ወሎ ቤተ -አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ሰባት የአገዛዙ መሰረታዊ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በሰላማዊ መንገድ ተቀላቅለዋል ። መሰረታዊ ወታደሮቹ ከተለያዩ ክፍለ ጦሮች የመጡ መሆናቸውን ሲናገሩ በአለምአቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ(UNISCO) ማህደር በደረጃነት ተመዝግቦ የሚመሰከርለትን አለም የሚደነቅበትን የቅዱስ ላሊበላ ህንፃ ቤተ ክርስቲያንን እንደምሽግ በመጠቀም ታሪክን ለማጥፋት አገዛዙ ካስቀመጣቸው 12ኛ ክፍለ ጦር፣ 61ኛ ክፍለ ጦር እና 65ኛ ክፍለ ጦር ስርዓቱ በአማራ ማህበረሰብ ማንነት ተኮር ስብዓዊ፣ ቁሳዊ እና አካላዊ ጉዳትን እየፈፀመ ላለው ስርዓት አንገዛም በማለት ወደ ወንድሞቻቸው በሰላም ተቀላቅለዋል። መሰረታዊ ወታደሮቹ ሰባት ጥቁር ክላሽ፣ 14 ኤፍ ዋን ቦንብ፣ ሰባት የደረት ትጥቅ እንዲሁም 1470 የክላሽ ተተኳሽ ፍሬ ጥይት በመያዝ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)* ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮርን ተቀላቅለዋል። መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል ። አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሰኔ 06 ቀን 2018 ዓ/ም

  • ፻ አለቃ ክብረት ገረመው የ 6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 32ኛ ክ/ጦር ሁለተኛ ሬጅመንት የሻምበል ሁለት አዛዥ 206ኛ ኮር14ኛ ክ/ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ሻለቃ ተቀላቀለ። ( 206ኛ ኮር) ሰኔ 6/2018 ዓ.ም ================================ የአረመኔው ሰርዊት ምንም አይነት የመዋጋት ብቃትና ፍላጎት ባለመኖሩ ከምመራት ሻምበል 23 አባላት ከድተዋል ያለ ሲሆን ከ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጋር ቆይታ አድርጓል። ሰራዊቱ ሴቶችን አስገድዶ እንዲደፍር ካድሬዎች በአካል ተገኝተው ያበረታታሉ ያለ ሲሆን የአረመኔው ሰራዊት በንፁሐን ላይ በተለይም በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሰውን የአስገድዶ መድፈር ፆታዊ ጥቃት የስናን ወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባወቀ በሰራዊቱ መካከል ተግኝቶ ሲያበረታታ እንደነበር ለአብነት ገልጿል። የወንበዴዎችን ምር*ጫ ተከትሎ ማብራሪ የሰጠው ፻ አለቃ ክብረት ገረመው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ3 በላይ ምር*ጫ ካርድ በመውሰድ ግንቦት 22 እና 23 በተደረገው ማጭበርበር ተሳታፊ ይሁኑ እንጂ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ከደብረ ማርቆስ ከተማ ጀምሮ በሁሉም ቀጠናዎች ከፍተኛ ውጊያ በመደረጉ ምንም አይነት ምር*ጫ አለመደረጉን አስታውቋል ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

  • የድል ዜና ከወደ ደራ ሰኔ 06/2018 ዓ.ም ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ኛ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር የበረሀው ጀግኖች ትናንት ከማለዳ አንድ(1:00) ሰዓት ከ30 ደቂቃ ጀምረው እስከ ምሽቱ አንድ(1:00) ሰዓት ድረስ በተደረገ እልሕ አስጨራሽ ውጊያ በሰረርኩላ እና በቱቲ ከተሞች መሽጎ በነበረው የአገዛዙ ኃይል ላይ እንደ እሳት እያቃጠሉ ጠንካራ ምት አድርገውበታል። ሆኖም የሥርዓቱ ጅምላ ተጋላቢ ኃይል በመሬት ላይ ሊቀበለው የሚገባውን ታሪካዊ ቅጣት ከጀግኖቹ ክንድ ተመግቧል። የበረሀው ትንታግ በፍቃዱ በላይ ክፍለጦር አንዲት እሳት የለበሰች ሻለቃ ወደ ሰረርኩላ ከተማ በረገጠችበት ቅጽበት በአገዛዙ ጥርቅም ኃይል ላይ የወሰደችው ፈጣንና መብረቃዊ የማጥቃት ስልት ጠላትን ሙሉ በሙሉ ግራ አጋብቶታል። ከዚሕም የተነሳ ጭንቅ ውስጥ የገባውና መውጫ ያጣው የአገዛዙ ኃይል ጫካ ውስጥ ያደራጀውን ዘራፊውን የ"ሸኔ" ስብስብ ለአጋዥነትና ለሕይወት ማዳኛ የጋበዘ ሲሆን የአናብስቶቹ ክንድ የማይነካ በመሆኑ ነገሩ እዳሠበው ሳይሳካ ቀርርቶበታል። ​በመጨረሻም ጠላት የሚያስማርከውን አስማርኮ የጓዶቹን አስከሬን እንኳን ሳይሰበስብ ከተማዋን ጥሎ ወደ ጫካ ፈርጥጧል። ጀግኖቹ የሰረርኩላን ከተማ እስከ ምሽቱ ሁለት(2:00) ሰዓት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር አውለዋታል። በሌላ በኩል በቱቲ ከተማ በተደረገው አውደ ውጊያ እጅ በአፍ የሚያስጭን ነበር። የቱቲ ከተማ በተናዳፊዎቹ ሻለቆች የባሩድ ጢስ ስትታጠን፣ ባሩዱም ሲቆላ በዋለበት በዚያ አስፈሪ ሰዓት ጠላት ምሽጉን በመነጠቁ ከተማዋን ጥሎ ለመውጣት ተገዷል። የወገን ኃይል ከተማዋን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ድላቸውን አጣጥመዋል። ​ይሕ በእንዲሕ እንዳለ ጠላት በእውር ድንብርና በፍርሃት ተውጦ ዙ-23 እና ሞርተሮችን እያጮኸ ቢውልም በጀግኖቹ የቦታ ቁጥጥርና በማይበገረው የስነ-ልቦና የበላይነት ግንባሩን ተመትቶ እንደ ቅጠል ሲረግፍ አምሽቶ ፣ በዚህ ደማቅ አውደ ውጊያ የተረጋገጠውና በጀግኖቹ እጅ የገባው የምርኮ ዝርዝር እንደሚከተለው ይፋ ሆኗል፦ ​➾3 ከፋኖ ከድተው ወደ አገዛዙ ገብተው የነበሩ ባንዳዎች ​➾1 የአገዛዙ ካድሬ ​➾3 የሚሊሻ አባላት ​➾የተማረከ ንብረት ዝርዝር ፦ ​➾8 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ​➾4 የወገብ ትጥቅ ​➾1 የደረት ትጥቅ ​➾6 የእጅ ቦንቦች ​እና... በርካታ ተተኳሽ ጥይቶች በጀግኖቹ እጅ ገቢ ተደርገዋል። ​"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!" "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን " ​የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

  • ዋግኸምራ ምድር ሐሙሲት ግምባር 303ኛ ኮር 14ኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጁ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር 14ኛ ክፍለጦር አካል የሆነችው ሁለተኛ ማንኩሽ ሻለቃ በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መቀመጫ ሰቆጣ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ከምትገኘው ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ሐሙሲት ከተማ ላይ በመግባት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል። ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት እስከ ረፋዱ 4:00 ሰዓት በተደረገ የደፈጣና ሽምቅ ውጊያ ዙሪያውን ከበባ በማድረግና በማፈን እንዲሁም መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በአገዛዙ ሚሊሻ አባላትና ራሳቸውን ስምረት ብለው በሚጠሩ በጌታቸው ረዳ የሚመሩ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ በጠላት ላይ ድል ተጎናፅፈዋል። ራሱን ስምረት ብሎ የሚጠራው ኃይልም ሞርታር-82 ወደ ሐሙሲት ከተማ ሁለት ጊዜ በማስወንጨፍ ንፁሃንን የጨፈጨፈ ሲሆን በተወረወረው ቅምቡላ ስድስት ንፁሃን ውድ ህይወታቸውን ሲያጡ ከአስራ አምስት በላይ ንፁሃን ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ወደ ሰቆጣ ሆስፒታል ሪፈር እንደተባሉ የአይን እማኞች መረጃውን አድርሰዋል። በተደረገው አውደ ውጊያ 15 ተደምስሶ፣ ሰድስት ሲቆስል፣ ሁለት ሚሊሻ ተማርኳል ፤ እንዲሁም ሁለት ጂምስሪ(GM-3)፣ አንድ ኤምፎርቲ(M-40) እና ዘጠኝ ክላሽንኮፍ በመማረክ ወደ ክፍለ ጦሩ ካዝና ገቢ መደረጉን የ14ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ ሐብቱ ማሞ (ራስታው) አስታውቋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሰኔ 05/2018 ዓ.ም

  • የአደረጃጀት/የሪፎርም ዜና💪💪💪 ተናዳፊዎቹ ሰኔ 05/2018 በድሮ አጠራሩ ጣና ብርጌድ በሚል ስያሜ ስም የቆየው የፋኖ አደረጃጀት አሁን ላይ አመራሩ በጥልቀት በመወያየት አደረጃጀቱን በአዲስ አፋብን በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር 16ኛ ልባርጋቸው ሙጨ ክ/ር በማለት የክ/ር አመራሮችንም እንደሚከተለው ተሰይመዋል በስሩም ተቋሙ ባወረደው አደረጃጀት 4ሬጅመቶችን አደራጅቷል። 1. የክ/ሩ ዋና ሰብሳቢ..............አርበኛ አጉማስ ታደገኝ 2. የክ/ሩ ም/ሰብሳቢ...............አርበኛ ጌታቸው ጋሻው 3. የክ/ሩ ወታደራዊ አዛዥ.........አርበኛ መቶ አለቃ አወቀ አዳነ 4. የክ/ሩ ም/ወ/ አዛዥ............አርበኛ ሻንበል ሙሌ 5. የክ/ሩ ዘመቻ ......................አርበኛ አስር አለቃ ምስጌ ዘሪሁን 6. የክ/ሩ ም/ዘመቻ...................አርበኛ መንገሻ አዳነ 7. የክ/ሩ ልዩ ኦፕሬሽን................አርበኛ አያናው አቡሃይ 8. የክ/ሩ ዋና ፋይናንስ ................አርበኛ አሌክስ ጥጋቡ 9. የክ/ሩ ም/ ፋይናንስ.................አርበኛ አገሩ አቤ 10. የክ/ሩ ፓለቲካ ዘርፍ ...............አርበኛ ሰለሞን ደግሰው 11. የክ/ሩ የህዝብ ግንኙነት...........አርበኛ አንደበት አበጀ 12. የክ/ሩ ሎጀስቲክ.....................አርበኛ ሰለሞን ገበየ እና አርበኛ በቃሉ ታያቸው 13. የክ/ሩ መረጃና ደንነት...............+++++++++++++++ 14. የክ/ሩ ስልጠና........................አርበኛ ከፍያለው ዘለቀ 15. የክ/ሩ የሰው ኃይል አስተዳደር..........አርበኛ ምትኩ ደግፌ 16. የክ/ሩ የህግ ክፍል..........................አርበኛ አምሳ አለቃ ሀብቴ አለሜ 17. የክ/ሩ ፅ/ቤት.................................አርበኛ ሀ/ማርያም መኳንንት 18. የክ/ሩ ህዝብ አስተዳደር...................አርበኛ ዳኘው ታረቀኝ 19. የክ/ሩ ኦርዲናስ...............................አርበኛ ደሴ መሌ እና አርበኛ አምሳያው ድግሱ 20. የክ/ሩ ቀጠናዊ ትስስር....................አርበኛ መግባሩ ታያቸው 21. የክ/ሩ ጤና ዘርፍ ኃላፊ .................. አርበኛ በላይ ግርማ 22. የክ/ሩ ኦዲተር................................አርበኛ ምስጋናው ደሴ ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብን በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር 16ኛ ልባርጋቸው ሙጨ ክ/ር የህ/ግ ሰኔ 05/2018

  • የነበልባል ክፍለ ጦር የፋኖ ቃኚዎች በጠላት ኃይል ላይ የደፈጣ ጥቃት አደረጉ።         ሰኔ 5/2018 ዓ.ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሠም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለጦር ቃኝዎች በብልፅግናው ጥምር ጦር ላይ መብረቃዊ የደፈጣ ጥቃት አደረገች። የጀግናው ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር  በአረርቲ ከተማ  ዙሪያ ልዩ ስሙ ተክልዬ በተባለ ቦታ፣ ከአረርቲ ከተማ ወጥቶ የደፈጣ ጥቃት  ለማድረስ ሲንቀሳቀስ በነበረ  የብልፅግና ጥምር ጦር ላይ መብረቃዊ ጥቃት ተሰንዝሯል። ​ በዚሕም የነበልባል ክፍለ ጦር  ቃኝ ና መሀንዲስ ሻለቃ ፋኖዎች የጠላትን እንቅስቃሴ አስቀድመው በመረጃ መረብ በፀረ መረጃ በመጥለፍ፣ ቀድመው ቦታ ይዘው በመጠበቅ ለደፈጣ  ሲግተለተል በመጣው የሚሊሻ ኃይል ላይ ጥቃት አድርሰውበታል። ከነበልባል ክፍለ ጦር ከሆነችው ከነብሮ ሻለቃ ሸማቂ ፋኖዎች በተገኘው መረጃ መሰረት፣  በደረሰ የተጠና የደፈጣ ጥቃት- ስማቸው ያልተጣራ 2(ሁለት) የሚሊሻ አባላት ወዲያውኑ የተደመሰሱ ሲሆን  በሌሎች ላይ ደግሞ በቁጥር በውል ያልታወቁ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል ብለዋል። ​የነበልባል ክፍለ ጦር ቃኚና መሀንዲስ ፋኖ ሸማቂዎች  የተጣለባቸውን ወታደራዊ ግዳጅ በስኬት አጠናቀው፣ ያለምንም የሰውና የንብረት ጉዳት ወደ ቀጠናቸው በሰላም ተመልሰዋል። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በየቦታው እየፈራረሰ የሚገኘው የብልፅግናው ጥምር ኃይል ወደ ፋኖ መቀላቀሉን ቀጥሎበታል።የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር በዛሬው ዕለት እንደልማዷ የእቴጌ ጣይቱን ፀጋ የተላበሰችው ክ/ጦር  የጠላትን ኃይል እየፈረካከሰች ጠላትን ያለ አፈሙዝ ገዝግዛ እየጨረሰች ትገኛለች። በዚሕም አንድ የአድማ በተን አባል የሆነውን "ስመኘው ማናለ "የተባለን አልዩአምባ  ከ29ኛ ሻለቃ 1(አንድ) ክላሽኮቭ መሳርያ  ከ120 ተተኳሽ ጋር በመያዝ በትናትናው እለት እቴጌ ጣይቱ ክፍለጦርን በሰላም እዲቀላቀል አድርጋለች። ክብር ለትግሉ ሠማዕታት ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

  • ተስፋ የቆረጠው የአገዛዙ ቅጥረኛ የሚሊሻ ሰራዊት አባላት እርስ በእርሱ ባለመተማመን መጋደል ጀምሯል!! 64ኛ ክ/ጦር ሰኔ 05/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ ወይራ ጠልማ ቀበሌ የሚገኘው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ ሰራዊት አባላት ሰኔ 04/2018 ዓ.ም እርስ በእርሱ ሲጋደል ውሏል። በእርስ በእርሱ ውጊያው #ባንዳ_አስቻለ_አሸብር የተባለ ቀንደኛ ሚሊሻ  ከወይራ ወደ ጠልማ ቀበሌ በተሽከረካሪ በጉዞ ላይ እያሉ በእራሱ ጓድ ሲገደል ሌሎች ቁስለኛ መሆናቸው ተረጋግጦል። ከዚህ ድርጊት ተሳታፊ የነበሩ የአገዛዙ ቅጥረኛ የሚሊሻ ሰራዊት አባላት በወይራ ጠልማ ቀበሌ በሁለት ጎራ ተሰልፈው እርስ በእርስ ሲታኮስ ማምሸታቸው ተረጋግጦል። በሌላ መረጃ አገዛዙ በቢቸና እና የዕዱውኃ ከተማ በሚኖሩ ንፁሃን ኖሪዎች ላይ እያካሄደ ባለው አይን ያወጣ ዝርፊያ፣ ግፎች እና በደሎች ምክንያት በሚፈጠሩ አለመግባባት የአገዛዙ ሰራዊት ተስፋ በመቁረጥ ወደ ህዝባቸው የተቀላቀሉ ነው። ከእነዚህም ውስጥ:- 1ኛ.ይባርቅ በልስቲ ሚሊሻ ከየዕዱውሃ ከተማ 2ኛ.ገብሬ ድረስ እና 3ኛ. አትኩት ገበየው የተባሉ ከደብረወርቅ 14ኛ ክ/ጦር አገዛዙን በመክዳት አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ተቀላቅለዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!               ሰኔ 05/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት

  • የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በተለያዩ ግንባሮች የሰራዊቱን ድርጅታዊ ቁመና በጥልቅ ግምገማዎችና በተሃድሶዎች እያጠናከረ መሆኑንና በመንግሥት የጦር መዋቅር ውስጥ የሚገኙ አባላት ደግሞ መኮብለላቸውን በስፋት መቀጠላቸውን አስታወቀ። የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ላለፉት ስድስት ወራት ሲያከናውናቸው የነበሩትን ወታደራዊና አስተዳደራዊ ተግባራት፣ የኮሩ ቋሚ ኮሚቴ በተገኘበት ለሦስት ቀናት በጥልቀት መገምገሙ ታውቋል። በዚህ ስብሰባ ላይ በኮሩ ስር የሚመሩ ክፍለ ጦሮች፣ ሻለቆች እና የወረዳ ጊዜያዊ መንግሥት አስተዳደሮች አሁናዊ ቁመና በዝርዝር የተፈተሸ ሲሆን፤ የተፈጸሙ ጠንካራ ወታደራዊ ግዳጆች፣ ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ሥልጠናዎች፣ እንዲሁም የሰራዊቱ ግብረ-ገብነትና የአመራሩ ቁርጠኝነት በጥልቀት መገምገማቸው ታውቋል። ኮሩ ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ መሠረት በማድረግ የቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችን ያስቀመጠ ሲሆን፣ አመራሩና ሰራዊቱ የተሰጠውን ማንኛውንም ዓይነት ወታደራዊና ድርጅታዊ ግዳጅ ለመፈጸም ሙሉ ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጡን የ206ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ገልጿል። በሌላ በኩል፣ በዚሁ በቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር የትንቅንቅ ቀጠና በሆነው በምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ ረቡዕ ገበያ ከተማ መሽጎ የሚገኘው የመንግሥት የፀጥታ ኃይል መዋቅር እየፈራረሰ መሆኑ ታውቋል። በከተማዋ መሽጎ የሚገኘው ኃይል በፋኖ ስልታዊ ጥቃቶች ሳቢያ ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ በመውደቁ፣ የአገዛዙ የሰራዊት አባላት እየከዱ የሕዝብን ወገን በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ። የስናን ወረዳ ጊዜያዊ መንግሥት ሚዲያና ግንኙነት ባወጣው ወቅታዊ መረጃ መሠረት፣ ከ75ኛ ክፍለ ጦር፣ 5ኛ ሬጅመንት ዋርዲያ መሸገው ከነበሩት የመከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል ዮሐንስ ሐምብሳ እና ድቻሳ ደሪባ የተባሉና የትውልድ ቦታቸው በኦሮሚያ ክልል ወለጋ እና ኢሉባቡር የሆኑ ሁለት የወታደር አባላት፣ በዋርድያ ላይ በነበሩበት ወቅት ያገኙትን አጋጣሚ በመጠቀም መዋቅሩን በመክዳት መኮብለላቸው ተረጋግጧል። እነዚሁ የሰራዊቱ አባላት ሁለት ጥቁር ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከነሙሉ ትጥቁ በመያዝ፣ የአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር፣ 24ኛ ክፍለ ጦር ስር የሚገኘውን የስናን አባጅሜ ሻለቃን በሰላም መቀላቀላቸው ታውቋል።

  • የአፋብን ወሎ ቤተ አማራ ሚኒልክ ዕዝ 104ኛ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር አምባሰል ላይ አንፀባራቂ ድል ተቀዳጀ! መነሻዉን ከኩታበር ወደ ተለያዬንና ዚሃ እንዲሁም ከደላንታ በቴሬ አድርጎ ወደ ዚሃ  በምድር ሞርተር ፣ዙ23 እና መድፍ ሲጠቀም በሰማይ በሁለት ድሮን ታግዞ  ፋኖን አጠፋለሁ በሚል የተለምዶ ቅዠቱ የመጣ ቢሆንም ጀግኖቹ ምንም ነገር ሳይበግራቸዉ እንደቃሪያ ሲያራግፉት ዉለዋል። ዉጊያዉም  ከንጋቱ 11:00 እስከ 6:00 የተደረገ ሲሆን በዚህ እልህ አስጨራሽ ውጊያ የ104ኛ ኮር 23ኛ ክ/ጦር ተናዳፊወች  ዚሃ የገባውን ሃይል ሙሉ ለሙሉ የደመሰሱት ሲሆን በዚህ የተበሳጨዉ  አገዛዝ በዘፈቀደ ሶስት ጊዜ ድሮን በመጣል ከጦርነቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ንፁሀንን የጥቃቱ ሰለባ አድርጓል። አሁን ላይ በድሮን ሽፋን በመስጠት ሬሳና ቁስለኛ እያነሳ ሲሆን ከግሸን በአባላ ለመቁረጥ ቢቀሳቀስም በንስሮቹ በደፈጣ ተመቶ ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ወደ መጣበት ተመልሷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 104ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሰኔ 04/2018ዓ.ም

  • Ashara Media - አሻራ ሚዲያ: ቀን 02/10/2018 ዓ.ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነዉ ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ፪ኛ ሻለቃ በሰራችው ድንቅ ና ልዩ የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን ካለምንም የተኩስ ልውውጥ የአገዛዙን የሚሊሻ ሻንበል መሪ ከነ ሙሉ ትጥቁ ጋማውን አንጠልጥላ በድል ተመልሳለች። የነጎድጓድ ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ትናንት ሰኔ 01/2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ገደማ ላይ በደብረ ብርሃን ከተማ ዙሪያ በሚገኘው በሲያደብርናዋዩ ወረዳ ስር ልዩ ስሙ አንጨቆረር ከተማ ድረስ ዘልቃ በመግባት በወሰደችው የተጠና ልዩ ኦፕሬሽን የአገዛዙን ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻ ሻምበል መሪ የሆነውን መካሻ አግደው በጋሻው የሚባለውን ባንዳ ሚሊሻ ከነሙሉ ትጥቁ ስታወጣ አቶ መካሻ አግደው በበኩላቸው ይሕንን ብለዋ፡  ፋኖ እደመብረቅ ድንገት ከፊቴ ሲበራብኝ  የእምነታቸውና የታማኝነታቸው ልክ ገብቶኛል ስለሆነም በአገዛዙ እንደኔ የተታለላችሁ አድማ ብተና ና ሚሊሻወች አገዛዙ አያዋጣም እኔ አረጋግጫለሁ ስለዚሕ እናተም ተረዱና ወደ ፋኖ ተቀላቀሉ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የፋኖ አናብስቶቹም ይሕንን ሲሉ መልዕታቸውን አስተላልፈዋል ፡ ከአገዛዙ ጎን የተሠለፋችሁ ሁሉ እኛ ስራችን ነውና ከዚሕ ብትማሩ ይበጃችኋል ብለዋል ። በሌላ ዜና የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ንጉስ ሳህለ ሥላሴ ክፍለጦር የተሀድሶ መርሀግብር አካሒደዋል። በዚሕ መርሃግብር የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ  ሰብሳቢ አርበኛ እንጂነር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ፡ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ፖለቲካ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ዶ/ር ታደሰን እና ሌሎች  የዕዝ፣የኮር እና የክፍለጦር አመራሮችን ጨምሮ የክፍለ ጦሩ ሰራዊት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። እንዲሁም ከክፍለጦር አመራሮች ለተነሱ ጥያቄዎች በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ የተሠጠበት ሲሆን ሠራዊቱም ከዛሬዋ ሰዓት ጀምሮ ለቀጣይ ድርጅታዊ ግዳጆች ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ክብር ለትግሉ ሠማዕታት ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሰኔ 02/2018 ዓ/ም ቀን 04/10/18 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር በተቆጣጠራቸው ቀጠናወች የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል የፈተና ጥያቄወች ያለምንም ስጋት ወደ ፈተና ጣቢያ ደርሰዋል። ♨️♨️♨️➡️➡️➡️♨️♨️♨️ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር በተቆጣጠራቸው በሁሉም ቀጠናወች ከሰኔ 08/10/18 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ6ኛ እና 8ኛ  ክፍል የፈተና ወረቀቶች  በፋኖ እጀባ አድራጊነት የሚፈለገው ቦታ መቀጠዋ ወረዳ ደርሰዋል!! ከዚህ በፊት መንግስት ነኝ የሚለው ቡድን ዘግቶት የነበረውን ትምህርት ከህዝባችን ጋር በመነጋገር ማስጀመራችን የሚታወስ ነው። አሁን ደግሞ  በሁሉም ትምህርት ቤቶች የፈተና ተግባራት እንዲፈጸሙ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር የመንግስትነት ሚናውን በመወጣት አስፈላጊውን ነገር ሁሉ በአማራዊ ስነ ልቦና  እያደረግን እንገኛለን። ህዝባችን ከፋኖ ውጭ ባለቤት እንደሌለው በብዙ መንገድ እያረጋገጠ ነው!! 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር በተቆጣጠራቸው ቀጠናወች ስርዓቱ ሙሉ ለሙሉ መፍረሱ እና በፋኖ እየተዳደረ መሆኑ የሚታወስ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ስርዓቱ እንኳን ፈተና ማስፈተን ይቅርና አንዲት እርምጃ በቀጠናው መንቀሳቀስ አይችልም። ለዚህ ደግሞ መላው ህዝባችን እና 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ሚናቸው ከፍተኛ ነበር። የ204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር  ጋፋት ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ አብራራው ይግለጤ የፈተና ጣቢያ  ቦታው ላይ በመገኘት ደህንነቱን አረጋግጠዋል። ፈተናውን ያለምንም ስጋት ወደ ቀጠናችን በመግባቱ መላው ህዝባችን እና ሰራዊታችን ክብር ይገባችኃል ብለዋል። ሻለቃ አክለውም አጠቃላይ የፈተናውን አደራረስ; ደህንነት እና በቀጣይ በሰላም እንዲጠናቀቅ እና ከብልጽግና ስርዓት አሸባሪወች ፈተናው መስተጓጎል እንዳይገጥመው ለመጠበቅ አስፈላጊውን ዝግጂት አድርገናል ብለዋል!! በቀጣይ ቀናት ፈተናወቹ ወደየ መፈተኛ ትምህርት ቤቶች ያለምንም ችግር እንዲደርሱ እንዲሁም ፈተናው ያለምንም ስጋት እንዲጠናቀቅ አንዱ የትግላችን አካል መሆኑን በመገንዘብ  ከህዝባችን ጋር ሁነን የምንፈጽማቸው ተግባራት ይሆናሉ። መላው ተፈታኝ ተማሪወቻችን መልካም እድል እየተመኘን ፈተናችሁን በተረጋጋ መንፈስ እንድትሰሩ እና ለጥሩ ውጤት እንድትበቁ በዚሁ አጋጣሚ አደራ ማለት እንፈልጋለን!! በህዝባችን ጥቅም አንደራደርም!! ድል ለአማራ ፋኖ !! አፋብን ጎጠግ በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል!!

  • አፋብን በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ ኮር 16ኛ ልባርጋቸው ሙጨ ክ/ር ግዙፍ 2ኛ ዙር ኮማንዶ የፋኖ ሰራዊት አስመረቀ! ትናንት ሰኔ 02/2018 ጣና ብርጌድ በመባል የሚታዎቀው አደረጃጀት አሁን ላይ ከቀጠናው አቀማመጥ ለግዳጅ በሚያመች መንገድ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በዉል በማጤንና በመምከር ታላቁ አርበኛ ልባርጋቸው ሙጨ ያለመውን ትክክለኛ የመታገያ ሀሳብ ከዳር ለማድረስ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የክ/ሩን አደረጃጀት አፋብን በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ ኮር 16ኛ ልባርጋቸው ሙጨ በሚል ስያሜና በስሩ አራት ሬጅመንቶችን በማደራጀት ካጠናቀቀ የሰነባበተ ሲሆን ለወራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ብዙ መሰናክሎችን በማለፍ በተለይ የታላቁ አርበኛ ልባርጋቸው መስዋትነት ሳይበግራቸው እንደ ታጋይ በቁጭት የተሻለ በመስራት አንድ ልቡ ቢሰዋ እሽ ልቡ ይወለዳል በማለት ስልጠናውን በብቃት ማጠናቀቅ ተችሏል። ምንጭ፦ አፋብን በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!

  • ቀን 02/10/2018 ዓ.ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነዉ ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ፪ኛ ሻለቃ በሰራችው ድንቅ ና ልዩ የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን ካለምንም የተኩስ ልውውጥ የአገዛዙን የሚሊሻ ሻንበል መሪ ከነ ሙሉ ትጥቁ ጋማውን አንጠልጥላ በድል ተመልሳለች። የነጎድጓድ ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ትናንት ሰኔ 01/2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ገደማ ላይ በደብረ ብርሃን ከተማ ዙሪያ በሚገኘው በሲያደብርናዋዩ ወረዳ ስር ልዩ ስሙ አንጨቆረር ከተማ ድረስ ዘልቃ በመግባት በወሰደችው የተጠና ልዩ ኦፕሬሽን የአገዛዙን ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻ ሻምበል መሪ የሆነውን መካሻ አግደው በጋሻው የሚባለውን ባንዳ ሚሊሻ ከነሙሉ ትጥቁ ስታወጣ አቶ መካሻ አግደው በበኩላቸው ይሕንን ብለዋ፡  ፋኖ እደመብረቅ ድንገት ከፊቴ ሲበራብኝ  የእምነታቸውና የታማኝነታቸው ልክ ገብቶኛል ስለሆነም በአገዛዙ እንደኔ የተታለላችሁ አድማ ብተና ና ሚሊሻወች አገዛዙ አያዋጣም እኔ አረጋግጫለሁ ስለዚሕ እናተም ተረዱና ወደ ፋኖ ተቀላቀሉ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የፋኖ አናብስቶቹም ይሕንን ሲሉ መልዕታቸውን አስተላልፈዋል ፡ ከአገዛዙ ጎን የተሠለፋችሁ ሁሉ እኛ ስራችን ነውና ከዚሕ ብትማሩ ይበጃችኋል ብለዋል ። በሌላ ዜና የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ንጉስ ሳህለ ሥላሴ ክፍለጦር የተሀድሶ መርሀግብር አካሒደዋል። በዚሕ መርሃግብር የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ  ሰብሳቢ አርበኛ እንጂነር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ፡ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ፖለቲካ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ዶ/ር ታደሰን እና ሌሎች  የዕዝ፣የኮር እና የክፍለጦር አመራሮችን ጨምሮ የክፍለ ጦሩ ሰራዊት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። እንዲሁም ከክፍለጦር አመራሮች ለተነሱ ጥያቄዎች በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ የተሠጠበት ሲሆን ሠራዊቱም ከዛሬዋ ሰዓት ጀምሮ ለቀጣይ ድርጅታዊ ግዳጆች ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ክብር ለትግሉ ሠማዕታት ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሰኔ 02/2018 ዓ/ም

  • በቀን 2/10/2018 ዓ.ም  የ305ኛ ኮር 76ኛ ክፍለ ጦር በወልቃይት ጠገዴ  ቁጥር 1 ቀጠና  እያደረገዉ ያለዉን እንቅስቃሴ ገመገመ   አስተባባሪ የዕዝ ከፍተኛ አመራሮች እና የኮር ከፋተኛ አመራሮች በተገኙበት የህዝባዊ የፓለቲካ ስራዎች ህዝባዊ አደረጃጀቱን እና ወታደራዊ እንቅስቃሰ በተመለከተ ሰፋ ያለ ግምገማ ተካሂዷል።      በነበረዉ ግምገማ  :- 1ኛ/  የተደራጁ ህዝባዊ የቀበሌ አደረጃጀ ወደ ስራ መግባታቸዉን 2ኛ/  ህዝቡ ሰላም ለራሴ አደረጃጀቱ ተጠቅሞ አካባቢዉን በመጠበቅ በኩል 3ኛ/ የፋኖ ሰራራዊት ከህዝብ ጋር በመቀናጀት ሌባን ከማፅዳት አኳያ የመጡ ዉጤቶችን 4ኛ / ከፍትህ አኳያ የተሰሩትን ስራዎች 5ኛ/ 76ኛ ክፍለ ጦር  በተሰጠዉ ቀጠና ጠላት ከማፅዳት ያመጣዉን ዉጤቶች የነበሩ ከፍተቶ ተገምግመዋ     ግብረ ሃይሉ በተሰጠዉ ቀጠና የነበሩ ምቹ ሁኔታዎ ያጋጠሙ ችግሮችን ዘርዘር ያሉ ሪፓርቶችን ካቀረበ በኃለ የቀጠናዉ የዕዝ አመራሮች  ማለትም 1ኛ/ አርበኛ በለጠ አዱኛ _ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ፋይናስ መምሪያ ኃላፊ የቀጠናዉ አስተባባሪ 2ኛ/ አርበኛ ወደጅ አሰፋዉ _ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ም/መካናይዝድ መምሪያ ኃላፊ የቀጠናዉ ም/ አስተባባሪ  አፈፃፀሙን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።               አርበኛ ባንዴራዉ ግርማይ የ305ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ                 ሰኔ 02/10/2018 ዓ.ም                    የ305ኛ ኮር

  • የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር የተሀድሶ ፕሮግራም አካኼደ!! ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ​አንጋፋው አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር የተሰጠውን ድርጅታዊ ግዳጅ በስኬት አጠናቆ ከተመለሰ በኋላ ሰፊ የተሀድሶ መርሀግብር አካሄደ። ​በዚህ የተሀድሶ መርሀግብር ላይ የአምሃራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራር፣የ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አመራሮች ፣ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር አመራሮች እና የዓፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር አመራሮች በተገኙበት ወቅታዊ ዝግጁነትንና ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችን በተመለከተ ግምገማና ውይይት አድርጎል። ​ክፍለ ጦሩ፡ በቅርቡ አገዛዙ ያካሄደውን "የጨረባ ምርጫ" ለማስፈጸም የተሸረቡ ሴራዎችን ለማክሸፍ በተለያዩ ግንባሮች በቆራጥነት በመሰማራት ሕዝባዊና ድርጅታዊ ግዴታውን በላቀ ድል መወጣቱን በውይይቱ ላይ የነሳ ሲሆን ፡ ክፍለጦሩ ከመቼውም በላይ ራሱን በማሻሻል ድርጅታዊ ተልዕኮችን በመቀበልና ግዳጅን በመወጣት ለወጣለት ለአማራ ሕዝብ በቁርጠኝነት የቆመ ና አርአያ መሆን የሚችል ግዙፍና ጠንካራ እዲሁም ልበ ሙሉ ጦር ነው ሲል የክፍለ ጦሩ ዋና መሪ አርበኛ አቡሽ ገልፀዋል። የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዋና ዘመቻ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ አሳልፍ ደስታ(ቀጭን) በበኩላቸው ክፍለ ጦሩ ልክ እንደ አማራ የፅንዓት ምልክት ነው ብለዋል። በሌላ በኩል የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የሃብት አሠባሰብ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ አበበ ፀጋዬ "ክፍለ ጦሩ" ልክ እንደ ዓፄ ይኩኑ አምላክ " ታማኝ" ነው ብለዋል። ​በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ ክፍለ ጦሩ ባደረገው በዚህ የተሀድሶ መድረክ ይበልጥ ተጠናክሮና ተደራጅቶ በመምጣት የአማራ ሕዝብ የጣለበትን አደራ ለመወጣትና የትግሉ ሠማዕታት የሠጡት አደራ ለመወጣት በቀጣዩ ማንኛውም ዓይነት የድርጅት ግዳጆች ለመወጣት ሙሉ ዝግጁነቱን አረጋግጧል። ​✊ "ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!!" ​💪 "ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!" ​ሰኔ 01/2018 ዓ.ም አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግኑኝነት መምሪያ

  • አሁን ላይ ማንኛውም ሰው ከቤቱ ቁጭ ብሎ በመነፋረቅ የሚለውጠው አንዳችም ነገር የለም በልመናና በልምምጥ የምታስከብረው መብትም ሆነ የምታገኘው ነፃነት የለም። መፍትሄው መሰባሰብ ፣ መደራጀት ፣ መሰልጠን ፣ መታጠቅ የኮሎኔል አብይ ብልፅግና መር አገዛዝ እስከመጨረሻው ከመንበረ ስልጣኑ ማስወገድ ነው። ለዚህም ደግሞ ወቅቱን የሚመጥነው አሁናዊ አስቻይ የትግል መንገድ ትጥቅ ያነገበ የጠመንጃ አቢዮት ነው። ይህን ደግሞ የኛ ትውልድ እያደረገው ነው ትውልዱ ከመሰባሰብ አልፎ ሰልጥኖ የታጠቀ ፣ በመዋቅር የተደራጀ ፣ በአውደ ውጊያ እየማረከ ትጥቁን እያዘመነ ብልፅግና መሩን ስርዓት ፍርስርሱን አውጥቶ ወደፊት እየገሰገሰ ነው። አሁናዊ ገዥው ህግ ስትሰባሰብ ፣ ስትደራጅ ፣ ስትሰለጥንና ስትታጠቅ ነፃነትህን በክንድህ ታውጃለህ። እስከምፃት አማራ! ክፋት ለማንም ፣ በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ!

  • የአደረጃጀት ዜና! በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 305ኛ ጎቤ ኮር የ52ኛ ክ/ጦር  አመራሮችን መልምሎ ወታደራዊ ኃላፊነት ሰጠ። ‎ይህንን ተከትሎ አርበኛ ሲሳይ አሸብር በተለይ የአስተዳደራዊና ወታደራዊ ክፍሉ መዋቅር ዘመኑን በዋጀ አለማአቀፋዊ ስታንዳርድ መሠረት መሆኑን በመግለፅ፡ ለመላው 52ኛ ክ/ጦር ሠራዊት የእንኳን ደስያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ‎ በዚህም መሠረ፦ ‎1ኛ፦ አርበኛ ገብረኪዳን ደበብ ዘውዱ፦ወታደራዊ አዛዥ 2ኛ፦አርበኛ ወ/ሰንበት ያሬድ ፦ም/ወታደራዊ አዛዥ 3ኛ፦አርበኛ ኮኬ አባይ ፦ወታደራዊ አስተዳደር 4ኛ፦አርበኛ ናቃ  ጌጡ ፦ሎጀስቲክ ‎ 5ኛ፦አርበኛ ሀብቴ አስታጥቄ፦ዘመቻ መምሪያ 6ኛ፦አርበኛ ፈንታ መንገሻ ፦ ም/ዘመቻ ‎7ኛ፦አርበኛ ቢራራ አስፋው ፦ወታደራዊ ዕቅድና ስትራቴጅ ‎8ኛ፦ አርበኛ መብቱ ብርቄ፦ መገናኛ ኅላፊ ‎9ኛ፦ አርበኛ መልኩ ጀጃው፦ ፖለቲካ መምሪያ ‎10ኛ፦አርበኛ ሙላት የሽወንድም፦ም/ፖለቲካ 11ኛ፦አርበኛ ካሳው ፀሀዩ፦ ህግና ስነምግባር ‎12ኛ፦አርበኛ ዳዊት ቀለም ወርቅ ፦ኦርዲናንስ ‎13ኛ፦አርበኛ አታላይ ታፈረ፦ ወታደራዊ ስልጠና ‎14ኛ፦ አርበኛ ገ/ህይወት ሞላ፦ወታደራዊ ቃል አቀባይ ‎ ‎15ኛ፦አርበኛ ገናዬ አሸቱ ፦ ፋይናንስ ‎16ኛ፦አርበኛ ባብዬው ግዛው፦ግዥ ‎17ኛ፦ **** መረጃና ደህንነት ‎18ኛ፦ አርበኛ አስናቀው ገብያው፦ የሰው ሀይል ‎19ኛ፦ አርበኛ አይሸሽም ጀጃው፦ትጥቅና ስንቅ ሆነው ተመድበዋል። ምንጭ፦ ‎በአፋብን በላይ ዕዝ 305ኛ ጎቤ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!

  • 7 июн.1 0651

    ሰበር ዜና! ሰራዊታችን ለተከታታይ ሁለት ቀናት ባደረገው ልዩ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ጀግናው የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ሁለት ከተሞችን ተቆጣጠረ። አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር አካል የሆነውየራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር ከአርበኞች ጦር ሰራዊት ጋር በቅንጅት በተሰራ ልዩ ኦፕሬሽን በግራርያ (ፍቼ ሰላሌ) አውራጃ የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ዋና ከተማን ጨምሮ ሴት ደብር እና ውሻ ገደል የሚባሉ ሁለት የወረዳ ከተሞችን ዛሬ ረፋዱ ላይ በቁጥጥር ስር ማድረጉን ኮሩ በላከው የግንባር መረጃ አስታውቋል። የደብረ ሊባኖስ ወረዳ የሆኑ በርካታ ነዋሪዎችን "የፋኖ ደጋፊ ናችሁ" በሚል ብዙዎችን ለሞትና ለስደት እንዲሁም ለከፍተኛ እስርና እንግልት የዳረጉ የወረዳው የብልፀሰግና አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲፈፀም የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊውና ሌሎች ቁስለኛ ሆነው ወደ ፍቼ ከተማ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን፣ ለአገዛዙ ቅጥረኛ በመሆን የመረጃ ስራ ላይ ሆነው ሲያገለግሉ በተገኙ ባንዳዎች ላይ ክፍለጦሩ የማያዳጋም ርምጃ በመውሰድ ከተማውን ተቆጣጥሯል። የህዝብ ልጅ የሆነው ጀግናው ሰራዊታችን ትላንት ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ግንቦት 30 ቀን 2018ዓ.ም ዕኩለ ቀን ድረስ በሞርተርና ዙ-23 ታጅቦ ከገጠመው አገዛዝ ጋር ባደረገው ልዩ ተጋድሎ ከተሞቹን ሲቆጣጠር እስከ ጫጋል ከተማ ድረስ አድማሱን ባሰፋው ውጊያ ሽንፈቱን የተከናነበው የብልፅግናው የግለሰቦች ታዛዢ ዘራፊ ሰራዊትና ጥምር ጦር ወደ ፍቼ ከተማ መፈርጠጡን ዕዙ በመረጃው አረጋግጧል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 30/2018ዓ.ም