Adebabay Media
Статистикаበወገንተኝነት፣ በጊዜአዊ ጥቅም እና አጋርነት ብቻ የሚደረግ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ጋዜጠኝነት ጥቅም እንደሌለው በመረዳት ዕውቀትና መረጃ ላይ የተመረኮዘ፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ፣ ሀገርንና ወገንን በመጥቀም ላይ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍ ባለ ብዙ ቋንቋዎች ሚዲያ፤ ቤተሰባችን ስለሆኑ እናመሰግናለን። በFacebook/YouTube (@adebabaymedia) ይመልከቱን። www.adebabay.com
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 526
- 1/48двое суток
- 602
- 1/72трое суток
- 650
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን ! በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
ሕወሓትና ሌላ ዙር ጦርነት የምክክር ኮሚሽን ሂደት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፍ የማሳባሰቢያ የሚዲያ ዘመቻዎች - በአማራ ሚድያ ======= ኢትዮጵያ በሌላ ደም አፋሳሽ ጦርነት ዋዜማ ላይ ናት። የትኛውም ወገን ሰላም ለማስፈን ምንም ዓይነት ፍላጎት የለውም። ከጦርከጦርነቱ ርቆ ያለው ወገን የላይ ፈሪ የታች ፈሪ እያለ የጦርነቱን መጀመር እያፋፋመ ነው። ከዚህ ሰይጣናዊ የደም አበላ ለመገላገል ምንም መፍትሔ አለመገኘቱ እጅጉን ልብ ይሰብራል። https://www.youtube.com/live/EPs_IrFi-SQ?is=q6UJAsmOGgab7dKS
"ትንቢተ ጎርጎርዮስ" በድጋሚ የተለጠፈ ============ ( ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ ) 1982 ዓ.ም የብፁዕነታቸው 3ኛ ዙር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጣን ደቀመዛሙርት በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነበርን። ከእኛ አስቀድም ሁለት ዙር ተማሪዎች ሰልጥነዋል። በ1980 እና በ1981 ዓ.ም። የኛ ዙር ተማሪዎች ብዙ ነበርን። 45 እንሞላለን። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ፣ ከጅማ ጤና ሳይንስ፣ ከጅማ ግብርና ኮሌጅ፣ ከደብረ ዘይት እንስሳት ሕክምና ወዘተ የመጣን ተማሪዎች ነበርን። በነገራችን ላይ በዓመቱ (በ1983 ዓ.ም) ወደ ብላቴ ዘመቻ ስንላክ በቀላሉ ለመገናኘት፣ ለመግባባት እና መንፈሳዊ አገልግሎት ለመጀመር ያስቻለን ትልቁ ምክንያት የዝዋዩ ትውውቃችን ነበር። እናም በዝዋይ የትምህርታችን ወቅት መንፈሳዊ ፍቅር ያቃጠላቸው ወጣቶች በግል ከብፁዕነታቸው ዘንድ እየቀረቡ፣ ንስሐ እየገቡ፣ ምክር እየተቀበሉ፣ የወደፊት ሕልማቸውንና ፍላጎታቸውን ለብፁዕነታቸው እየነገሩ ይመለሱ ነበር። ከተመለሱ በኋላ የነበራቸውን ቆይታ ለእኛ ለወንድሞቻቸው ምንም ሳይደብቁ ይነግሩናል። (ማስታወሻ:- እንዲህ ማድረግ ነበረባቸው አልነበረባቸውም የሚል ሙግት እንዳትገጥሙኝ፣ አደራ 🙂)። ከነዚህ ገጠመኞች አንዱ በጣም የምንወደው አንድ የቅርብ ወዳጃችንን/ ወንድማችንን ይመለከታል። ያ ወንድም እንደ ሌሎቹ ሁሉ ኃጢአቱን ተናዝዞ የሚጣልበትን ቀኖና ተቀብሎ ሊመለስ ይሄዳል። እኛም ምን ዓይነት ቀኖና እንደሚሰጠው ለማወቅ በጉጉት እየጠበቅነው ቆየን። ሲመለስ ግን እዝ...ን ብሎ መጣ። ** እኛ:- " ምነው ምን ሆንክ? ምን አሉህ? ምን ቀኖና ተሰጠህ?" እያልን በጥያቄ አጣደፍነው። ** እርሱ፦ "ምንም አላሉኝም" ብሎ ክፍት አለ። ** "እንዴት ምንም አላሉህም?" ** "በቃ ምንም አላሉኝም።" ** "ዝም ሊሉህማ አይችሉም!!!!" (በጥያቄ አጣዳፍነው።) ** እርሱ:- " አንዲት ነገር ብቻ ነው ያሉኝ" (አለ ሲፈራ ሲቸር) ** "ምን? ምን? ምን?"" (ተረባረብንበት) ** "በቃ፣ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን አገልግል ነው ያሉኝ።" አለና ዝም አለ። እኛም ዝም አልን። "አባታችን ምን ማለታቸው ነው? ለሌሎች ያንን ሁሉ ቀኖና እና ምክር ሲሰጡ እርሱን አንዲት ቀላል ነገር ብቻ የነገሩት ምን ማድረጋቸው ነው?" ብለን ተብሰለስልን። ምኑም አልገባን አለ። አልገባንምም። ምሥጢሩ የገባን ከ1985 ዓ.ም በኋላ ነበር። ++++++ ያ ወንድም ተመርቆ ወደ ሥራ ዓለም ገባ። አገልግሎቱን ቀጠለ። ነገር ግን የብፁዕነታቸው ትንቢታዊ ትዕዛዝ መፈጸሙ ግድ ነበር። "በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን አገልግል" የምትለው። እናም ድንገት ተሰውሮ ጠፋ!! የትሄደ? እንደዚህ ዘመን በሞባይል ወይም በኢንተርኔት አይፈለግ ነገር። ብቻ ሥራውን ትቶ ተሰወረ። ++++++ ከዓመታት በኋላ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን ቢሮ ውስጥ ለሥራ ቁጭ ባልኩበት ሁለት ከሩቅ የገጠር ገዳም የመጡ መነኮሳት አንኳኩተው ገቡ። ያን ጊዜ ቢሮአችን ቤተ ክህነት ግቢ፣ ከሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ በተሰጠን ሥፍራ ላይ ነበር። የተለያዩ ገዳማት አባቶች በተለያየ ጊዜ ይመጡ ነበር። አንዳንዶቹ ገዳማቸው ስላለበት ችግር ይነግሩናል። አንዳንዶች ግን መልዕክት ለማድረስ የመጡ በሚመስል መልክ ትምህርትም ምክርም ለግሰውን ይሄዱ ነበር። እናም የዚያን ዕለት የሁለቱ መነኮሳት መምጣት አዲስ ነገር አልነበረም። ስለመጡበት ገዳም ሲነግሩኝ፣ ስለ ማኅበሩም አገልግሎት ሲጠይቁኝ ቆዩ። አብዛኛውን የሚናገሩት አንደኛው መነኮስ ናቸው። ሌላኛው ግን ወይባ ቢጫ መጎናጸፊያቸውን አፋቸው ላይ ጣል አድርገው አቀርቅረው ከመስማት ውጪ ምንም አይናገሩም። በዓይናቸው ብቻ ሰረቅ አድርገው ያዩኛል። ማን መሆናቸውን ለማወቅ ብዙ ቆይቻለሁ። ድሮ የምንተዋወቅበትን ዓለማዊ ስማቸውን ጠርቼ እስከጮህ ድረስ ማን መሆናቸውን አላወቅሁም ነበር። ፊታቸው ላይ ያለች ምልክታቸውን ባላይ ኖሮ ሳላውቃቸው እቀር ነበር። ከዚያ ተቃቅፈን ተላቅሰን፣ የአባታችን ቃል ትንቢት መሆኑን አውስተን እግዚአብሔርን አመሰገንን። እኒያ አባት በሀገራችን ከባድ ከሚባሉት ገዳማት በአንዱ አሁንም በአገልግሎት ላይ ይገኛሉ። የሆነ ዓመት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያዘጋጀው የመነኮሳት ጉባዔ ላይ ገጻቸውን ስመለከት ያ የልጅነት ትውስታ ተቀሰቀቀሰብኝ። ግርማ ሞገሳቸው፣ ጸጋቸው በገጻቸው ላይ ይነበባል። በብዙ ፍለጋ ለ2 ደቂቃ በስልክ አገኘኋቸው። መገናኘታችንን ለወዳጅ ዘመድ እንዳልናገር በዘወርዋራው ነግረውኝ ተለያየን። ለእኔ የብፁዕ አባታችን ቀኖና "ትንቢት" ሆኖ የታየኝ ለዚህ ነው:: ፍርዱን ለእናንተ። ====== (ሐምሌ 22 ዛሬ፣ አባታችን ወደ አምላካቸው ከተጠሩ 36 ዓመት ሞላ።) የብፁዕነታቸው ቡራኬ ይድረሰን። #ዝክረ_አቡነ_ጎርጎርዮስ_ካልዕ_36ኛ_ዓመት_መታሰቢያ @highlight
https://www.youtube.com/live/sU25u392enE?is=A5GyvhHX35o99x59 ===== ድሮን አስተኳሽ የጦር ኃላፊዎች እየፈጸሙት ያለውን የጦር ወንጀል በቅጡ ለማጤን ለምን ተሣናቸው? ==== ** የድሮን ሰለባ የሆኑ ገዳማት እና የገዳማውያኑ ጉዳይ እንዲሁም ** በአሜሪካ የተቃጠለው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያናችንን በተመለከተ ጥሩ ውይይት አድርገናል። ** የቅዳሜ ጥቂት ደቂቃዎችንሁን ብታውሱን መልካም ሐሳቦች ታገኙበታላችሁ ብለን እናምናለን።
ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች፣ የፖለቲካ ቀውሱና፡ የሰላም መንገዶች ተጋባዥ እንግዶች:- ===== 1 - ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግሥቱ 2- ደራሲ ዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል
#ዕድልም_ሁልጊዜ_አትደገምም ====== በቤተክርስቲያናችን ታሪክ በዕውቀት ማዕድነቱ የሚታወቀው፣ በርካታ ሊቃውንትንና አገልጋዮችን አፍርቶ ለቤተክርስቲያንና ለሀገር ያበረከተው አንጋፋው የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለዘመኑ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ራሳቸውን በጥበብና በዕውቀት ለማደግ ለሚሹ ሁሉ በርካታ የትምህርት መስኮችን ዘርግቶ የእውቀት ማዕዱን አዘጋጅቷል። ለዓመታት በደቀ መዛሙርቱና በኮሌጁ ማኅበረሰብ ልብ ውስጥ ሲንቀለቀል የነበረው መሻት በአባቶቻችን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በዚህ ዘመን ፍሬ አፍርቶ የዲግሪ መርሐግብር ከመጀመሩ ባሻገር በዓለም አቀፍ ዙሪያ የሚገኙ አብያተክርስቲያናት የሚያገለግሉ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምዕመናን ታሳቢ በማድረግ የበይነመረብ ትምህርት በ2018 ዓ.ም አስጀምሮ የመጀመሪያውን መንፈቀ ዓመት መገባደጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን አሁን ደግሞ በክረምት ወቅት የሚማሩ ደቀመዛሙርት በመመዝገብ ላይ ነው። ምዝገባው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018ዓ.ም. ድረስ የሚቀጥል ሆኖ ከሐምሌ 1 ቀን 2018ዓ.ም. ጀምሮ የመግቢያ ፈተና በመስጠት መደበኛውን ትምህርት ያካሂዳል። ልብ በሉ ጊዜው ሳይረፍድ ዕድሉን ይጠቀሙበት! ጥበብ ሰዓት አታከብርም፤ ዕድልም ሁልጊዜ አትደገምም። ለተወሰኑ ቀናት ብቻ ክፍት ተደርጎ የቆየው የዚህ ወርቃማ ዙር ምዝገባ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። በመሆኑም ከመንፈሳዊ ዕውቀት ጥማት የተነሣ በዚህ ታላቅ ተቋም ውስጥ ለመማር የምትሹ፣ መሥፈርቱን የምታሟሉ ዕጩ ተማሪዎች በሙሉ የቀሩትን በጣም ጥቂት ቀናት በመጠቀም ከታች በተቀመጠው ሊንክ መሠረት እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን። ✍🏾 የቴሌግራም ግሩፕ ሊንክ፦ https://t.me/Sewasiwe_Birhan_Kidus_Pawlos 👉ለማመልከት ከየት ልጀምር የሚል ጥያቄ ላላችሁ ? ✍ ይህን የማመልከቻ መሙያ ፎርም ይሙሉ:👇 https://forms.gle/bHGroCYF5a3MDxV19 ለበለጠ መረጃ +251982154150 /+251950069082/+251907752509 👉 https://youtube.com/shorts/E7mM7T6ROTU?si=gbKAAQNUXr3GAYNB 👉 https://www.facebook.com/share/r/1Dqiz91ECp/ 👉 https://vt.tiktok.com/ZSC2kfcoQ/
እሳቱ እንዲጠፋ ወይስ እሳቱ እንዲሰፋ? || የምክክር ኮሚሽኑ ነገር አሁንም ===== ** ለምክክርና ለሽምግልና አስቸጋሪ የሆነው የኢትዮጵያ ነገር ===== https://www.youtube.com/live/wxfc4a_iqUA?is=hhXBxaGUCaBHkHfl #ArsiMassacre #EthiopianOthodoxUnderAttack
የቤተ ክርስቲያን ደኅንነት እና ሰላም || መቀሌ፣ መተከል፣ መንግሥት፣ ማሕበረሰብ ====== የዛሬ ልዩ ቆይታ ከብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ጋራ ይሆናል። https://www.youtube.com/live/iQjDMss961c?is=mnh-sZYVvwTtk6nF #ArsiMassacre
በስምንት ቋንቋዎች አገልግሎት የሚሰጥ የምስባክ መተግበሪያ ( wep app) በበርንገሀም ዩናቲድ ኪንግደም ተመረቀ ======= (አደባባይ ሚዲያ፣ ሰኔ 8/2018 ዓ.ም፤ June 15,2026):- የበርሚንግሃም ደብረ መድኃኒት ቅዱስ አማኑኤል ዐምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት የሕፃናት ክፍል በስምንት ቋንቋዎች ምስባክ.ዶት.ኦርግ የተሰኘ የምስባክ ድረ-ገጽ (www.misbak.org) አዘጋጅቶ በሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ተመርቆ ለአግልግሎት እንዲበቃ አድርጓል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም ቀሲስ ሞላ መርሀ ግብሩን በጸሎት በማስጀመር የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም ደብሩ ተተኪ ትውልድን ለማፍራት ከወትሮው በበለጠ ትኩረት እየሠራ መሆኑን ገልጸው፣ በዚህ ጠቃሚ ፕሮጀክት ላይ የተሳተፉ ሁሉንም አመስግነው መልካሙ ሥራ በቀጣይነት እንዲጠናከር አሳስበዋል። በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት፣ በቅዳሴ እና በሌሎች ሥርዓተ አምልኮ ወቅቶች ምዕመናን ምስባኩን ከዲያቆኑ ጋር አብረው እንዲከታተሉ በየሳምንቱ ፓወር ፖይንት (PowerPoint) በመጻፍ ይዘጋጃል። ይህንን አገልግሎት የሚያከናውኑ አገልጋዮች በየሳምንቱ ጽሑፎችን በማዘጋጀት፣ በማረም እና በሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት የማሳያ ስክሪኖችን በመቆጣጠር ብዙ ጊዜ ያጠፋሉ። በዚህ ሂደት ውስጥም አንዳንድ ጊዜ የፊደልና የቃላት ወይም የትርጉም ስህተቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍና በቴክኖሎጂ አማካይነት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል፣ የበርሚንግሃም ደብረ መድኃኒት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ዐምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ሕፃናት ክፍል አዲስና በስምንት ቋንቋዎች የምስባክ ድረ-ገጽ ማዘጋጀት ችሏል። በዚህ ሥራም በስካንዲቪያ ሀገሮች የሚገኙ ዲያቆናት በትጋት እየሰሩ ነው። ይህ ድረ-ገጽ ምስባኩን በግዕዝ፣ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በዴንሽ፣ በፊንሽ፣ በፈረንሳይኛ፣ በጀርመንኛ፣ በኖርዌይኛ እና በስዊድንኛ ቋንቋዎች ማለትም በስምንት ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል። በዚህም በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ አገልግሎት በሚረዱት ቋንቋ እንዲከታተሉ ያግዛል። በተጨማሪም ተደጋጋሚ የሆነውን ሳምንታዊ የዝግጅት ሥራ በመቀነስ፣ የጽሑፍ ትክክለኛነትን በማረጋገጥ እና አገልጋዮች በቅድሴው ላይ የበለጠ እንዲያተኩሩ ያግዛል። ይህ ፕሮጀክት በወጪው ዓላም ተወልደው ያደጉ ልጆች ያላቸውን ጸጋ፣ ዕውቀትና ችሎታ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላያ እንዲያውሉ እድል የፈጠረላቸው ነው። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ዌብ አፑን ያበለጸጉት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስለ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ የሥራ ሂደትና አጠቃቀም ማብራሪያ ሰጥተዋል። በቀጣይም ዌብ አፑን ለማሻሻል የታቀዱ ዕቅዶችን ለተገኙ ምዕመናን አቅርበዋል። ከእነዚህ ውስጥ ምስባኩን በድምጽ የማቅረብ አገልግሎት እና ለቅዳሴ አገልግሎት የሚያገለግሉ የወንጌል ንባቦችን የመጨመር እቅድ እንዳለ ገልጸዋል። ፕሮጀክቱን በማስተባበርና በመምራት የተሳተፉት ዶ/ር በላቸው ጨከነ በበኩላቸው፣ ዌብ አፑ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ታዳጊ ልጆችን በእንዲህ ያሉ ፕሮጀክቶች ላይ ማሳተፍ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ባላቸው አቅም እያገለገሉ እንዲያድጉ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል። የምስባክ ዌብ አፑን በማረምና በሃሳብ ሲያግዙ የቆዩት ሊቀ ዲያቆን ኃይለ ማርያም በበኩላቸው፣ “አባቶቻችን በብራናና በቀለም ያስተላለፉልንን ቅርስ ዛሬ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በዌብ መልክ እንዲደርስ ተደርጓል” በማለት የፕሮጀክቱን ጠቀሜታ አስረድተዋል። የደብሩ የስብከተ ወንጌል ኃላፊና የሰንበት ትምህርት ቤቱ የበላይ ጠባቂ መጋቢ ሐዲስ ዳንኤልም በፕሮጀክቱ ላይ በማማከርና በማረም ተሳትፈው እንደነበር ገልጸው፣ ልጆች በእንዲህ ያሉ ሥራዎች መሳተፋቸው የቴክኖሎጂና የቋንቋ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ እድል እንደሚፈጥር አስታውቀዋል። ይህ ዌብ አፕ የግጻዌ መጽሐፍን ሁልጊዜ በእጃችን እንዳለ በሚያደርግ መልኩ አገልግሎቱን እንደሚያቀርብም ጠቁመዋል። @topfans #Ethiopia #ethiopianorthodoxtewahedo
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቴክሳስ፣ ኦክላሆማ፣ ሉዊዚያና፣ አርካንሳና ሐዋዪ አካባቢ ሀገረ ስብከት በምሥራቅ አርሲ የጅምላ ፍጅት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግ መመሪያ አስተላልፏል። እንዲሁም ለእሑድ ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም (June 14, 2026) ደግሞ ልዩ ጉባዔ ጠርቷል። ዝርዝሩ ከደብዳቤው ላይ ይገኛል። #EOTCUnderattack #ArsiMassacre
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ለአርሲ ሰማዕታት መታሰቢያ፣ የሐዘን፣ የጸሎተ ፍትሐት እና የጸሎተ ምሕላ መግለጫ ========== በአርሲ ሀገረ ስብከት በኦርቶዶክስ ምእመናን እና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ በደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሊባኖስ፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ እና የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ የሐዘን፣ የጸሎተ ፍትሐት እና የጸሎተ ምሕላ መግለጫ ========= “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ስለ ደማችንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” (ራእይ 6፥10) ========== በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በሃይማኖታቸው ምክንያት በኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ላይ በደረሰው አሰቃቂና አስከፊ የሞት ዜናን በሰማንበት ጊዜ፣ በልባችን ከፍተኛ ሐዘን ተሰምቶናል። “ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የእምነት ነፃነት ተደፍሮ፣ ለመቶ ዓመታት የቆመዉ የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ መቅደስ በእሳት ሲበላ፣ የካራ ኩፍቴና መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያንም ሲዘረፍ፣ ንጹሐን ምእመናን በግፍ ሲሠዉ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀያቸዉ ሲፈናቀሉ፣ ያየንበት ይህ ዘመን የማይረሳ የሐዘን ቁስል በልባችን ላይ አስቀምጧል። ቅዱስ ዳዊት “እንባዬ ቀንና ሌሊት ምግቤ ኾኖኛል” (መዝ.41፥3) እንዳለ ዛሬም የእኛ ዐይኖች በእንባ ተሞልተዋል። በዘመናችን በክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው አሰቃቂ እልቂት ተራ የሚባል የሞት ዜና ሳይኾን የእናቶች ልብ የተሰበረበት፣ ሕፃናት ያለ አሳዳጊ ወላጅ፣ አረጋውያን በእርግና ዘመናቸዉ ያለጧሪ የቀሩበት፣ ቤተ ክርስቲያንም ውድ ልጆቿን በአረመኔዎች እጅ የተነጠቀችበት እጅግ መራራ የሐዘን ጊዜ ነው። ዛሬ በአርሲ ምድር ላይ የፈሰሰዉ ደም የግለሰቦች ደም ብቻ አይደለም፤ የእምነት መገለጫ ደም ነው፤ በክርስትና ሕይወታችን የቀራንዮ ጉዞ ደም ነው፤ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ብቻ ኢላማ ተደርገው በክርስቶስ ስም የተሠዉት የሰማዕታት ደም ነው። ከኹሉም በላይ የሚያሳዝነዉ እነዚኽ ወገኖቻችን የሞቱት በራሳቸዉ ሀገር፣ በራሳቸዉ ምድር፣ በራሳቸዉ ወገን መካከል ያለምንም ርኅራኄ በጭካኔ መኾኑ ነው። ስለዚህ እንደ ነቢዩ ኤርምያስ ቃል “በሕዝቤ … ስብራት እኔም ተሰብሬአለሁ” (ኤር. 8፥21) በማለት የሕዝባችንን ጽኑዕ ሐዘን በአንድ ልብ ኾነን እንካፈላለን፤ እንባቸውንም እንባችን እናደርጋለን። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተመሠረተች፣ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ በመከራ፣ በስደትና በሰማዕታት ደም መንገድ የተጓዘች በመኾኗ የሰማዕታት ደም የእምነት ዘር ሆኖ ብዙ ቅዱሳንን እንደወለደ ታሪክ ይመሰክራል። ጌታችንም እንዲህ ብሎአል፦ “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።” (ዮሐ. 16፥ 33) እንዲሁም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ኃያልነት “… የሲኦል ደጆች አይችሏትም” (ማቴ. 16፥18) በማለት ፈተናውን መሻገር እና ማለፍ እንደምንችል ሕያው በኾነ ቃሉ አስረድቶናል። ኾኖም ግን በዘመናችን የሚታየው የግፍ ግድያ፣ የቤተ ክርስቲያን ቃጠሎና የንጹሐን ሰቆቃ ልብን የሚያቆስል በመኾኑ “እኛ ደክመናል፤ ዕረፍትም የለንም” (ሰቆ.ኤር. 5፥5) ያለው የነቢዩ ጩኸት ዛሬም የእኛ ኦርቶዶክሳውያን የዘወትር ጩኸት ኾኗል። በተለይ ከአንድ ምእተ ዓመት በላይ የቆመው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን መፍረስን የሚያሳይ ብቻ አይደለም፤ የአባቶች ጸሎት፣ የእናቶች እንባ፣ የሕፃናት የቅዳሴ ትዝታ አብሮ መቃጠሉን ያስረዳል እንጂ። ይህ ቁስል በቃል የማይገለጽ፣ በጊዜ የማይሽር፣ በእንባ ብቻ የሚገለጽ ሐዘን ነው። ነገር ግን በሐዘናችን መካከል ተስፋችን አልሞተም። ሰማዕታቱም በከንቱ አልወደቁም። “ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።” (ማቴ. 5፥10) “የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት ክቡር ነው።” (መዝ. 115፥ 6) ተብሎ እንደተጻፈ እናምናለን። የእስልምና እና የክርስትና ሃይማኖት መቶ በመቶ የሀገራቸዉ ብሔራዊ ሃይማኖት በኾነባቸዉ ሀገራት ሳይቀር የእምነት ነጻነት የሰው ልጅ መሠረታዊ መብት ነው ተብሎ በሚጠበቅበት፣ በሕይወት የመኖር መብት ከሰው ልጅ አልፎ ለእንስሳት ዋስትና በተሰጠበት ዘመን በሀገራችን ኢትዮጵያ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና በአማኞቿ ላይ የሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶች፣ የሕይወት መጥፋት፣ የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠል በየትኛውም መልኩ የማይታገሡት እኩይ ተግባር በመኾኑ መንግሥት ለዜጎቹ የሕግ ጥበቃና የደኅንነት ኃላፊነቱን በተግባር እንዲወጣ፣ የክርስቲያኖች በግፍ መሞትና መከራ እንዲቆም፣ ሰላምና ፍትህ በሀገራችን እንዲጸና በአክብሮት እንጠይቃለን። እንዲኹም በሀገረ ስብከታችን የምትገኙ ገዳማትና አድባራት በሙሉ በግፍ ለተሠዉ ሰማዕታት ወገኖቻችን ጸሎተ ፍትሐት እንድታደርሱ፣ ስለ ቤተ ክርስቲያንና ስለ ሀገር ሰላም ጸሎተ ምሕላ እንድትፈጽሙ በአክብሮት እናሳስባለን። በመጨረሻም፣ በግፍ የተሠዉ ሰማዕታት ወገኖቻችንን ነፍሳቸውን እግዚአብሔር በሰማዕታቱ ማኅበር እንዲያሳርፍልን፣ በሕይወተ ሥጋ የተረፉትን እንዲያጽናናልን፣ለቆሰሉትም የምሕረት አምላክ ፈውሱን እንዲልክላቸው የዘወትር ጸሎታችን ነው። ሰላመ እግዚአብሔር ከኹላችን ጋር ይኹን! አባ ድሜጥሮስ- ሊቀ ጳጳስ የሊባኖስ የተባበሩት ዐረብ ኢምሬትስ እና የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ግንቦት 25/2018 ዓ/ም አቡዳቢ #EOTCUnderattack #ArsiMassacre #ethiopianorthodox
ቅድሚያ:- ለሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ወይስ ለሕዝቡ (ለሕንጻ ሥላሴ)? ===== የአርሲ ጉዳይ የመላው ሕዝበ ክርስቲያን ቁጥር 1 አጀንዳ ነው። የቤተ ክህነቱ አመራር አባቶችም በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ያደረጓቸውን ስብሰባዎች እና ጉብኝቶች እያየን ነው:: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አባቶች በቅርቡ ባደረጉት ጉባዔ በምሥራቅ አርሲ የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት መወሰናቸውን አይተናል። ወደ አርሲ ጉዞ ያደረገው የአባቶች ቡድንም ዛሬ ምዕመናኑን ስብስቦ ሕንጻውን ደግመን እንሠራለን ማለቱ ተዘግቧል። ይህ ሁሉ ውሳኔ ግን የችግሩን ማዕከል ያልዳሰሰ፣ ችግሩንም የማይቀርፍ፣ ለዋነኛው የጉዳዩ ባለቤቶች ማለትም ለክርስቲያኖች ደኅንነት መረጋገጥ ዋስትና የማይሰጥ መሆኑን ልብ ይሏል። ዋነኛውን ችግር ለመቅረፍ የማንሠራው ለምንድነው? https://www.youtube.com/live/EYt-WEKllEM?is=xaOn9YomwrgDAcWs #EOTCUnderattack #ArsiMassacre
በተጨማሪም ሕዝቡ በሃይማኖት ስም የሚነግዱ አክራሪዎችንና ለፖለቲካ ትርፍ ሲሉ የንጹሐንን ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖችን ደም የሚያፈሱ ኃይሎችን በጋራ እንዲያወግዝ እና አሳልፎ ለሕግ እንዲሰጥ። ብሎም በየአካባቢው የሚገኙ የሌላ እምነት ተከታዮች የኦርቶዶክስ ወንድሞቻቸውንና አብያተ ክርስቲያናትን እንደ ራሳቸው ንብረትና ወገን በመቁጠር የጥፋት ኃይሎችን በጋራ እንዲከላከሉ፤ የሐሰት ወሬዎችን ባለመቀበል በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ፣ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ የጥላቻ ንግግሮችንና የሐሰት ትረካዎችን በንቃት በመከላከል በጋራ እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን። በውጭ ሀገር በስደት የምንኖር ኦርቶዶክሳውያን በሀገር ውስጥ ስላለው ወገናችን በዝምታ የምንቀመጥበት ጊዜ አይደለም ስለሆነም በጸሎት ወደ እግዚአብሔር አብዝቶ በመጮህ፡ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ለሚደረገው ለተጎጂዎች የሚውል ገንዘብ እና ንብረት በማሰባሰብ ሂደት ላይ በጉልህ በመሳተፍ አስተዋጾ እንድናደርግ፤ ቤተ ክርስቲያን በምታደርገው ማናቸውም መንፈሳዊ ጥሪ ውስጥ በመሳተፍ የድርሻችንን እንድንውጣ እና በምንችለው ሁሉ ይህ ጥቃት እንዲቆም መንፈሳዊ ተግባራትን እንድናከናውን እንጠይቃልን። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላም እና የፍቅር መገኛ ናት። ሆኖም ግን፣ ሰላማዊነቷን እንደ ፍርሃት፣ ትዕግሥቷን እንደ አቅም ማነስ በመቁጠር በንጹሐን አማኞቿ ላይ እየተፈጸመ ያለው የደም መፋሰስ እሲኪቆም እና ፍትሕ እስኪሰፍን ድረስ የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት፣ጉዳዩን በዘለቄታነት እንድሚከታተል እያረጋገጥን በሰሜን አሜሪካ እና በሌሎች አህጉረ ስብከቶች የምንገኝ አገልጋዮች ለዚሁ ተግባራዊነት የብኩላችሁን እንድታደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን። እግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንንና ሀገራችንን ይጠብቅ! የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ዋሽንግተን ዲሲ፣ ሰሜን አሜሪካ ግንቦት ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም (June 7, 2026)
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи