- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 39
- Всего постов
- 42
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 881
- 1/48двое суток
- 2 155
- 1/72трое суток
- 2 324
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ህፃኗ ቦታ የቀየረችው ድምፁ ይቀንስ እንደሆነ ብላ በማሰብ በሚጢጢዬ ክብደቷ 'ባላንስ' ለማደረግ መጣሯን(Though futile😂) ከተረዳችሁላት እናንተ ሚዲያ ሞኒተሪንግን ተክናችኋታል !
// ዛሬ ሸራሮ ከተማ ውስጥ በያንዳንዱ ቤት እየዞሩ ለቃሬዛ 100 ብር አዋጡ እያሉ ህዝቡን ሲያስገድዱ ውለዋል // ደብረፂዮን ...ቃሬዛ ፊት ! 😂😂 -- እስኪ Goodnight !!
ወያኔ ራሱ በለኮሰው ጦርነት ሳቢያ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ብቻ ወደ 3 የሚጠጉ አርሚዎቹን አጥቷል።ይኼንን ተከትሎ ወያኔ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ከከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ጋር ባደረገው ምስጢራዊ ውይይት መሠረት የተፈጠረውን ክፍተት በከፊል ለመሙላት በሚል አንድ አዲስ አርሚ ለማቋቋም ወስኗል።ታዲያማ ይህ አዲሰ አርሚ በፖሊሶች እንዲዋቀር ነው የተወሰነው።ምን ማለት ነው ?የትግራይ ፖሉስ አባላት በሙሉ በTDF…
አንድ በግልጽ መጤን ያለበት እውነታ እንደነበረ ከላይ መገለፁን አስታውሱ፣ ይሐውም ከ1967—70 አም በነበሩት አመታት የወልቃይት ጠገዴ አካባቢ በተለይም መዘጋ፣ ቃፍትያ፣ አዲረመጥ፣ አርማይጭዎና ሌሎች የስሜን ተራራ ኮረብታማ ወረዳዎችና ዋሻዎች የኢህአፓ (የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ) ሰራዊት ምሽጎች እንደነበሩ ይነገር ነበር። በ1970 አም ህወሐት የኢህአፓን ድርጅት ከአሲምባ ምሽጉ በጦር ሃይል አስገድዶ ሲያስወጣና ድርጅቱ ከውስጥ አንጃዎች፣ ከውጭ ደግሞ የህወሀትና የሻእቢያን ዱላ ለመቋቋም ባለመቻሉ ተፍረክርኮ ሲበታተን አብዛኛዎቹ ወደሱዳንና ወደተለያዩ አገሮች ሲሰደዱ የወልቃይት ጠገዴ ምሽጎቹን ለህወሀት ታጋዮች ለቅቆ መውጣት የግዴታው ስለነበር ይህንን እስትራተጂክ የሱዳን መውጫና መግቢያ በር ህወሀቶች ፈጥነው ለመቆጣጠር እንደበቁ ይታወቃል፣ ኢትዮጵያውያን እስከሆኑ ድረስ ጥያቄና ተቃውሞ አልተሰነዘረባቸውም በዚያን ዘመን። ከዚያን ጊዜ አንስቶ የህወሀት ሰራዊት አባላትና ደጋፊዎች የሁመራንና የአካባቢውን ለም የእርሻ መሬቶች ሁሉ ቀስ በቀስ በተወላጆቻቸው ቋሚ ይዞታ ስር ለመጠቅለል በቅተዋል ማለት ነው፣ በዚህም ሳቢያ የወልቃይት ነባር ተወላጆችን (ወልቃይቶችን) በግድያም ሆነ በማፈናቀል ከገዛመሬታቸው ነቅለው እንዲሰደዱ አደረጓቸው ማለት ነው። በዚህም የተነሳ ዛሬ በአንድ ወገን፣ የወልቃይት ጠገዴ አካባቢ የወልቃይቶች (የአማራ ክልል) ነው፣ ጥንትም ዛሬም፣ በሌላ ወገን ደግሞ የለም የትግራይ ነው ጥንትም ሆነ ዛሬ የሚሉ እርስ በእርስ የሚጣረሱ አቋሞች እየተራገቡ ናቸው። አሳዛኝ ትርክት ነው። ይህ በዚህ እንዳለ ቢሆንም፣ የኢህአፓ ርዝራዦች የነበሩት ጓዶች "ኢህዲን" (በሁዋላ "ብአዴን" ተብሎ የክርስትና ስያሜ በህወሀት ተሰጥቶት) የሚል የህወሀት ተቀጥላ ድርጅት መስርተው እስከዛሬ ለመዝለቅ በቅተዋል። ሆኖም በኢፌዴሪ ህገመንግስት ድንጋጌዎች መሰረት የተከናወኑት የክልሎች አከላለል ሂደቶችና አፈፃፀሞች በሰላማዊ መንገድ የተከናወኑ ሣይሆን በተለያዩ ክልሎች ደምአፋሳሽ ሁኔታዎች ተከስተዋል፣ የሰዎች ህይወት ሳይቀጠፍና የንብረት ውድመት ሳይኖር የተከናወነ የክልል አወሳሰንና አወቃቀር ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም ። ይህ በዚህ እንዳለ፣ ዛሬ የወልቃይቶችንም ሆነ የማንኛውንም ዘውግ ማንነት የሚወስኑት ራሳቸው ማህበረሰቦቹ እንጂ ማንም ሌላ አካል የነርሱን የዘውግ ማንነት እንደቦሎ አይለጥፍላቸውም ፣ እንዲሁም ያለፈቃዳቸውና ያለፍላጎታቸው ወደየትኛውም ክልል እንዲካለሉ መወሰን የማንም ስልጣን አይደለም። ይህንን የመወሰን መብት የራሳቸው የወልቃይቶች የማይገሰስ መብት ነውና። በሌላ አንፃር፣ በኢፌዴሪ ሕገመንግሥቱ አንቀጽ 48 መሠረት፣ "የአከላለል ለውጥ ወይም የክልል ወሰን የመደንገግ ወይም የመለወጥ/የማሻሻል ጥያቄ ከተነሳ ደግሞ ጉዳዩ በማህበረሰቡና በሚመለከታቸው ክልሎች ስምምነት መፈጸም ይኖርበታል። እነዚህ ለመስማማት ካልቻሉ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የህዝብ አሰፋፈርንና ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥ"፣ በሕገመንግሥቱ ተደንግጓል ። የኢፌዴሪ ህገመንግስት ራሱ ደርግን የገረሰሱት የአሸናፊዎቹ የህወሃት ትሪክት እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰፊ ጊዜ ወስዶና በበቂ መረጃ ላይ ተመርኩዞ ያሳለፈውን ስምምነትና ውሳኔ እንዳልነበር በጊዜው የነበርን የቅርብ ተሳታፊዎችና ታዛቢዎች በትክክል የምንመሰክረው እውነታ ነው። ልክ እንደቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነመንግስቱ የ1923 እና የ1948 አም ሁለት ህገመንግስቶችና እንደደርጉ የ1979 አም የኢህዲሪ ህገመንግስት የወያኔ/ኢህአዴግ የ1987 አም የኢፌዴሪ ህገመንግስትም "ለሚወዱትና ለሚወዳቸው የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች"፣ ወድደውና ፈቅደው የሰጡት ስጦታ ነው። በዚህም የተነሳ ሰጪዎቹ ባለፉት 27 አመታት ህገመንግስቱን እንዳሻቸው ሲጥሱ በመቀጠላቸው ሰነዱ የወረቀት ላይ ነፃነት ብቻ ሆኖ ቀርቷል። ለማንኛውም የወልቃይት ጠገዴ፣ የጠለምት፣ የሰቲት ሁመራ፣ አላማጣ ራያ ቆቦ የማንነትም ሆነ የአከላለል ጥያቄ በኢፌዴሪ ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎች ምላሽ የሚያገኝ ውስብስብ ጉዳይ አይደለም፣ በዛሬው ዘመን የትግራይ ነፍጠኛ ወራሪዎችና ጉልበተኞች በ1984 ዓም በጠብመንጃ ሃይል በቅኚነት ተይዞ የቆየ የአማራ ክልል ይዞታ ስለሆነ ያለአንዳች ቅድመሁኔታና ማካካሻ ለአማራ ክልል መንግስት በአስቸኳይ መመለስ የግዴታ ይሆናል፣ የሚመለከታቸው የፌደራልና የሁለቱም ክልሎች የመንግሥት አካላት ኃላፊነታቸውን አሁንም በአግባቡ ለመወጣት በአስቸኳይ መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል። ለወልቃይት ጠገዴም ሆነ ከወሎ ጠቅላይ ግዛት ተቆርሰው የተወሰዱትን የአላማጣ፣ የኮረምና የራያ ቆቦ የአማራ ይዞታ የነበሩትን መሬቶችንም በተመለከተ የፌደራል መንግስት ብዙ ጊዜ ሳይወስድ የማያዳግም የመጨረሻ ውሳኔ ሊሰጠውና የአካባቢው ሰላም እንዲከበር ሊያደርገው ይገባል፣ ይቻላልም። በመጨረሻም፣ የፌዴራል አባላት ክልሎችን ወሰን በተመለከተ በየጊዜው መከለስና ለህዝቦች መስተጋብር በሚያመች ሁኔታ ጂዎግራፊን፣ የኢኮኖሚ አዋጪነት፣ የማህበረሰብ አሰፋፈር ፣ የሚመለከታቸው ወገኖች ፍላጎት፣ የክልሎች እኩልነት ወይም ተመጣጣኝነት፣ ወዘተ መስፈርቶች በመጠቀም ማካለል አዲስ ክስተት አይደለም። ከናይጄሪያ እስከ ህንድ፣ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ካናዳ፣ ከስዊትዘርላንድ እስከአውስትራልያ ያሉት የፌዴራል አገሮች በየጊዜው የአባል ክልሎቻቸውን ወሰኖች ይከልሳሉ፣ ያሻሽላሉ፣ ይለውጣሉ። የኢትዮጵያ መንግስትም የወልቃይት ጠገዴ፣ የሰቲት ሁመራ፣ የጠለምትን፣ የአላማጣ ራያ ቆቦንም ሆነ ሌሎች የፌደራል ክልሎችን በተመለከተ በየጊዜው የሚነሱትን ጥያቄዎች እየመረመረና እያስጠና በተመሳሳይ አካሄድ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲቋጩ ማድረግ ይኖርበታል። በነዚህ አይነት የማንነትና የአከላለል ጥያቄዎች የተነሳ አስፈለጊና ተገቢ ያልሆኑ የህዝብ ለህዝብ ግጭቶች ደም—አፋሳሽና ንብረት አውዳሚ ክስተቶችን ማስከተል በፍፁም አይኖርባቸውም። ከዚህ ውጭ በማወቅም ሆነ ከግንዛቤ እጦት በመነጨ አጉል እንቅስቃሴ የሁለቱን ክልሎች ወንድማማች ህዝቦች ወደግጭትና ወደጠላትነት የሚያስገባ እንቅስቃሴ ሁሉ በአስቸኳይ እንዲቋረጥ አጥብቀን እንጠይቃለን። በዚህ ረገድ የሚደረገው አሉታዊ እንቅስቃሴ ወይም ሴራ ሁሉ በፅኑ መወገዝ አለበት፣ የህዝብ እውነት ምንጊዜም አሸናፊ ነው። እግዚአብሄር ሰላማዊ አብሮነታችን፣ የእርስ በእርስ መተጋገዛችንና ወንድማማችነታችንን ለዘለዓለም ይጠብቅልን ! (Dilbato Degoye በፌስቡክ ገፁ ላይ እንደፃፈው )
የወልቃይት ጠገዴ፣ የጠለምት፣ የሰቲት ሁመራና የአላማጣ ራያ ቆቦ ይዞታዎች የBegemedir and Simien (አማራ ክልል) ይዞታዎች ነበሩ፣ የትግራይ አልነበሩም!! DILBATO DEGOYE WAQO 15/05 /1995 እኔ የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጅ ስሆን በ1962 አም ከቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቅሁ በዃላ በመንግሥት ሠራተኛነት የተቀጠርኩት በትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር ስር ይተዳደር በነበረው የመንገድ ማመላለሻ አስተዳደር መሥሪያ ቤት ነበር። በ1963/64 አም የተለያዩ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶችን በመላ አገሪቱ ስናቋቋም ለሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያ የሚያገለግል ቅርንጫፍ መ/ቤት የተቋቋመው በጎንደር ከተማ፣ ለትግራይ በመቀሌ ፣ ለኤርትራ ደግሞ በአስመራ ከተማ እንደነበር አስታውሳለሁ። ያንጊዜ የጠቅላይ ግዛቱ ስያሜ የቤጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ተብሎ ሲጠራ የንጉሠነገስቱ እንደራሴና ጠቅላይ ገዥ የነበሩት ኮሎኔል ታምራት ይገዙ ነበሩ፣ የትግራይ ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ ልኡል ራስ መንገሻ ሥዩም፣ የኤርትራ ደግሞ ልኡል ራስ አስራተ ካሳ ነበሩ። በ1963 አም በወልቃይት ጠገዴ በሚገኘው የሁመራ መሬት ጥጥ፣ ሰሊጥና ማሽላ በሰፊው የሚያመርት "የወልቃይት ጠገዴ ሁለገብ የገበሬዎች ማህበር" ነበር፣ በማህበሩ ውስጥ አባል ሆነው ለመሰማራት የሚሹ ሁሉ ከኮሎኔል ታምራት ይገዙ ከጎንደር የድጋፍ ደብዳቤ እየተፃፈላቸው ነበር የሚመዘገቡት፣ አያሌ ሀብታም ባለትራክተር ግለሰቦችን ያፈራ የልማት ማህበር ነበር። የማህበሩ የቀን ሰራተኞች በአብዛኛው የትግራይ ተወላጆች እንደነበሩ ሳስታውስ (ልክ የወንጂና መተሃራ የስኳር ፋብሪካዎች የቀን ሰራተኞች በአብዛኛው የከምባታና የሀዲያ ተወላጆች እንደነበሩ ሁሉ) የሁመራ ከተማ ባለሆቴሎችም አብዛኛዎቹ ኤርትራውያን እንደነበሩ አስታውሳለሁ። ወደሁመራ ከተማ የሱዳን ዜጎች ያለአንዳች ገደብ እየገቡና እየተዝናኑ እንደሚመለሱና ኢትዮጵያውያንም በነፃነት ወደሱዳን እየገቡ ይነግዱ፣ ይመላለሱ እንደነበር አስታውሳለሁ። የወልቃይት ጠገዴ ሁለገብ የገበሬዎች ማህበር በወቅቱ በኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ ከዓለም ባንክ ብድርና እርዳታ የሚያገኝ እጅግ የዳበረ ጠንካራ የእርሻ ልማት ማህበር ነበር። ምርታቸውን በተመለከተ ማሽላውን ወደከረንና አስመራ የሚያስጭኑ ሲሆን ጥጡንና ሰሊጡን በምጽዋ ወደብ በኩል ወደውጭ አገሮች ነበር ኤክስፖርት የሚያደርጉት። እነዚህን ምርቶች ወደምፅዋ የሚጭኑት የቀይባህር ኤርትራ የጭነት ማመላለሻ ማህበር እንደነበር አስታውሳለሁ። እኛም የመንገድ ማመላለሻ አስተዳደር (ዛሬ የትራንስፖርት ባለሥልጣን) ቡድን በ1963 አም ወደሁመራ የሄድነው ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ማህበራት በጭነት ታሪፍ የተነሳ ስላልተስማሙ ለማስታረቅ ነበር፣ ባጭሩ ለመግለፅ፣ የሁለቱን ማህበራት መሪዎች በማወያየትና በማደራደር በኩንታል 3 ብር የነበረው የጭነት ታሪፍ ወደ4 ብር በኩንታል ከፍ እንዲል በማስማማት ወደጎንደር እንደተመለስን አስታውሳለሁ። ያንጊዜ ማለትም የዛሬ 46 አመት ወልቃይት ጠገዴ ምንም በማያሻማና በማያወዛግብ ጂዎግራፊያዊ አቀማመጥና ፖለቲካዊ የግዛት ይዞታ የቤጌምድርና ስሜን አካል ሲሆን ከዚያ ወዲህ በዘመናዊ የትግራይ ነፍጠኛ አቅኚዎች በሃይል ካልተያዘ በስተቀር ከዛሬው የአማራ ክልል ይዞታ ውጭ የሚሆንበት ታሪክ ሊከሰት አይችልም። በወሎ በኩል ደግሞ ከአላማጣና ከራያ ቆቦ አካባቢዎች ተቦጭቀው በጊዜው ወራሪዎች የተነጠቁትን ወረዳዎች ጨምሮ ("መሬት የሁሉም ናት ባለቤት የላትም፣ ሃይለኛው ያስገብራል እየሄደ የትም"፣ ሲል የኢጣልያ ተወላጅ ቹሊ የተባለ ሰው በትእቢት የተናገረውን ያስታውሷል!) የወሎ ጠቅላይ ግዛት አካል ነበሩ። ያንጊዜም ሆነ አሁን የቤገምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛትና የትግራይ ጠቅላይ ግዛት የድንበር ወሰን ደግሞ የማያሻማና ግልፅ የሆነ የተፈጥሮ ወሰን የተከዜ ወንዝ እንደነበርና ዛሬም እንደሆነ ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከሁመራ የሚጫነውም ምርት ተከዜ ሰቲትን ተሻግሮ ከኦምሀጀር (ኤርትራ) ወደምፅዋ ወደብ ድረስ የሚጓጓዝ ነበር። ከዚያን ጊዜ አንስቶ እስከደርግ ውድቀት ድረስ ሰቲት ሁመራ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት ጠገዴ በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነመንግስት (1923—1966 አም) የቤገምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ክልል፣ በደርግ ዘመነአገዛዝ ደግሞ (1966—83 አም) የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ክልል አካል ነበሩ። በነዚያ የአገዛዝ ዘመናት አማራ የሚባል ክልል አልነበረም ። ብዙዎች እንደሚያውቁት፣ ከ1965—70 አም ከአርማጮ አንስቶ እስከቃፍትያ፣ መዘጋ፣ ጠለምት ጠገዴ፣ ወዘተ ባሉት አካባቢዎች የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ሰራዊት በትግራይ ክልል በኢሮብ ምድር ከነበረው የአሲምባ ዋና ማእከል ወይም ቤዝ (base) በተጨማሪ እንደመከላከያ ምሽጎች የሚገለገልባቸው ስፍራዎች እንደነበሩ ይታወቃል። ነገር ግን በ1970 አም የኢህአፓ ሰራዊት ከሻእቢያ የፖለቲካ ጫና እንዲሁም ከህወሃትና ከኢዲህ የተቃጡበትን የጦር መሳሪያ ወራራ እና በውስጡ የተከሰቱትን የአንጃዎች ግጭትና ጫና መቋቋም ተስኖት ሲፈረካክስና ሲበታተን ከሰቲት ሁመራ፣ ከጠለምትና ከወልቃይት ጠገዴም በህወሃቶች የጠብመንጃ ሃይል ተገፍቶ እንዲወጣ ተገደደ። ከዚያም ብዙዎች አባላቱ በሱዳን ለተወሰኑ ወራትና አመታት ቆይታ አድርገው በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን አጋዥነት ወደተለያዩ የውጭ አገሮች ሲሰደዱ፣ ጥቂቶች ደግሞ ኢህዴን የሚባል የፖለቲካ ቡድን መስርተው ወደህወሃት የፀረ—ደርግ ትግል ወድደውና ፈቅደው በአጋርነት ተቀላቀሉ። ሌሎች ደግሞ ለደርግ እጃቸውን ሰጥተው የኢህአፓን ህልውና በወሳኝ መልኩ እንዲያከትም አደረጉት፣ ዛሬ በአሜሪካና በአውሮጳ አገሮች ኢህአፓ አሁንም ትግሉን አላበቃም የሚሉ ግለሰቦች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ። በሌላ አንፃር፣ አማራ የሚባል ክልል ቀድሞ ያልነበረ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ‘የጥምቀት‘ ስያሜ ተሰጥቶት የተዋቀረው ከ25 አመታት በዃላ በ1987 አም የኢፌዴሪ ህገመንግስት ከፀደቀ በሁዋላ ከሌሎች ተጨማሪ 8 ስምንት ክልሎች ጋር እንደነበር የሚታወስ ጉዳይ ነው። ክልሎቹም የተዋቀሩት በሕገመንግሥቱ አንቀፅ 46 መሠረት "በህዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት" ስለነበር ከ46 አመታት በዃላ በመሬት ላይ የተከሰቱትን አስገራሚና ሊታመኑ የማይችሉ የቋንቋ፣ የማንነት፣ የስነልቦናዊና ማህበረሰባዊ ጥንቅር (demographic) ለውጦች እንዴት እውን ሊሆኑ እንደቻሉ በግምት ካልሆነ በስተቀር በበቂ ምክንያት ለማስረዳት አይቻለኝም፣ እነዚያ በብዙ መቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኩሩና ጀግና ወልቃይቶች ወዴት ተሰወሩ? በሙሴ መሪነት እስራኤሎች ከግብፆች ባርነት ተላቅቀው ወደከነአን ምድር ሲጓዙና የቀይ ባህርን በተአምር የባህሩ ውሃ በሙሴ ትእዛዝ ለሁለት ተከፍሎ ለመሻገር ሲችሉ ከባርነት በመለቃቀቸው የተቆጨው የግብፁ ፈርኦን ወታደሮቹን አሳድደው እንዲመልሷቸው ቢያዝም እነዚህ ወታደሮች ተከታትለው በመሄድ እንደእስራኤሎቹ ለመሻገር የሚቻላቸው መስሏቸው ወደባህሩ ሲገቡ እዚያው ተውጠው እንደቀሩ ሁሉ ወልቃይቶችም ባህር ካጠገባቸው ባይኖርም ምናልባት ወደተከዜ ወንዝ ተወርውረውና ተበልተው አልቀው ይሆን? ግራ የሚያጋባ እንቆቅልሽ ነው፣ አሳዛኝ የህዝብ ወገን ታሪክ ነው ።
Ayalew Menber ይሄንን ቪዲዮ ለጥፎ ."#ፅምዶ (ዘመነ ካሴና አስረስ ማረ) በአማርኛ ሲናገሩ ይህንን ይመስላሉ" ሲል ሃቁን አዋዝቶ ነግሮናል። ------ My take ልጁ ይሄንን በመናገሩ አልገረመኝም።ይልቅስ በስጭቶኛል።የበሰጨሁትም በልጁ አይደለም።እንደውም ልጁ አሳዝኖኛል .. ድምፁ አንጀት ይበላል😂 😂 እኔ በእነ"ሴኩ" ነው የበሰጨሁት ! ልጁ ደረቱን ነፍቶ እንዲህ እንዲናገር ድፍረቱንና የሞራል መሠረቱን በገነቡለት እንደ ዘመነና አስረስ ባሉ የወቅቱ "ሴኩቱሬዎች" ላይ ነው መበስጨቴ ! ልጁ ሃሳቡን ለመሸጥ የገበያ ችግር እንደሌለበት ከእነ ሴኩ መተማመኛ ቢሰጠውም አይደል እንዲህ በ "condescending tone" የፎለለው? አዎ ! እነ"ሴኩ" ባለንብረቶች ናቸው ፤ በርካታ "petrified audience" አሏቸው ¡¡
Sudan Founding Alliance (TASIS) forces have advanced near Amora, close to Damazin in Sudan’s Blue Nile region, after clashes with SAF troops. TASIS declared hundreds of fighters were killed or captured and says it seized weapons and military equipment. ምንጭ - The Sudan Times
እፍ እፍ እፍ እፍ ..... የሸረሪናን አንፀባራቂ ድል በዚህች ምርኮኛ ታዳጊ አንደበት ሲገለፅ..... //የሞቱት ሞተዋል።እኛን የቆሰልነውን ግን ማን ያንሳን ? ዞር ብሎ ያየን የለም።ሁሉም ነኩት ..እፍ. እፍ እፍ እፍ - ሩጫ በሩጫ .....// 😂😂
እ....ህ.....እ ወያኔ ትስረ*ር
የሂመቲ ወታደሮች ትናንት ኩርሙክን ሲቆጣጠሩ አንድ የወያኔን ህፃን ታጣቂ ማርከው የሚነጋገሩትን ስሙ.... 👇 "ሚን ኒል አል አዝረግ ከሸና አል ኩርሙክ" ( ዛሬ ከጥቁር አባይ ተነስተን ኩርሙክ ገብተናል)። አሁን ይሄንን ሙቀጫ የሚያክል ወንድ ይሁን ሴት የማይታወቅ ህፃን ልጅ ለውጊያ ሰታሰልፉ ወታደሮቻችሁ እያለቁ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።ይህ የዛሬ 13/8/2026 ነው"
قوات تأسيس تؤمن "قيسان" وتستعرض معدات عسكرية بعد فرار الجيش من المنطقة The Founding Alliance Forces secure “Qeisan” and display seized military equipment after the SAF fled the region #معركة_الديمقراطية #حراس_الثورة_المجيدة
የወያኔ አፈሳ በአይነቱ አንድ ደረጃ ከፍ ብሏል። ወጣቱ አፈሳን በመፍራት ራሱን ከጎዳናዎችና ከመዝናኛ ስፍራዎች አርቆ ከፊሉ እግሩ ወደመራው እየሄደ ሲሰወር ፣ መሄጃ የሌለው ከፊሉ ደግሞ ከቤት ባለመውጣት ህይወቱን ለመታደግ ይጥራል። እቤት የተደበቁቱ ወጣቶች ለጊዜው ካልሆነ በስተቀረ የሚሳካላቸው አልነበረም።የማታ ማታ የሞንጆሪኖ ግዳይ መሆናቸው የማይቀር ነበር። ይሄውና መጡባቸው ....... ሴቷ ... ጠቋሚ ፣ መዝጋቢ እና አስፈራሚ (ልምዓት ጉጅሌ ናት ) ወንዱ ...በር አንኳኪ ነው - በሩ ከውስጥ ካልተከፈተም በር ሰባሪ (የአካባቢ ሚሊሻ ነው )
እህእ
በሂመቲ የሚመራው ጥምረት (TASIS) የኩርሙክ ከተማን ከአልቡርሃን ሃይሎች (SAF) ቁጥጥር ነፃ አድርጌያለሁ እያለ ነው ... ተቆፃፂሩ 😂
ለደቡብ ጎንደር እና ለደብረ ታቦር ከተማ ወዳጆቼና አንባቢያን በሙሉ! 📚✨ በደቡብ ጎንደር ዞንና በደብረ ታቦር ከተማ የምትገኙ ወዳጆቼ እና አንባቢያን፤ የመጽሐፉ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት የሚካሄድበትን ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ስገልጽላችሁ በታላቅ ደስታ ነው! 📅 የምረቃ ቀን፦ ነሐሴ 10 / 2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ከቀኑ 7:00 ጀምሮ 📍 ቦታ፦ ደብረ ታቦር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ በዞኑ እና በከተማዋ የምትገኙ ሁሉም ወዳጆቼና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች በዕለቱ ተገኝታችሁ የደስታችን ተካፋይ እንድትሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችኋል። 🚚 መጽሐፉን ስለማግኘት፦ መጽሐፉን ከነገ ጀምሮ በየቦታው የምናደርስ መሆኑን እንገልጻለን። 💡 አንድ ወንድማዊ ጥቆማ፦ በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ወቅት ጠንካራ ጥያቄዎችን እና ሀሳቦችን በማንሳት ፍሬያማ ውይይት እንድናደርግ፤ መጽሐፉን አስቀድማችሁ አግኝታችሁ እና አንብባችሁ እንድትመጡ በታላቅ አክብሮት እጋብዛለሁ። "የተከዜ ፖለቲካ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ቁልፍ ነው።" መልካም ንባብ! #ደብረታቦር #ደቡብጎንደር #የተከዜፖለቲካ #የመጽሐፍምረቃ #አዲስመጽሐፍ #ንባብለሕይወት ( Chuchu Alebachew )
ወይኔ ወጋቸው 😂😂 //.... ህንፃዎቹ በፊልም እንደሚታዩት የ1950ዎቹ ከተሞች ውስጥ ከነበሩት ጋር ይመሳሰላሉ። በ1950ዎቹ አካባቢ ያለሁ እስኪመስለኝ ድረስ ተመስጫለሁ...//
....ህዝቡ ግን ህግ አክባሪ ነው።ምንም እንኳን መንገዱ ባዶና የመኪና ፍሰት(traffic) ባይኖረውም ህዝቡ ግን ዜብራ ላይ ቆሞ አረንጓዴዋ እስክትበራ በትዕግሥት ይጠብቃል.... 😂
ይህ Davud Akhundzada የተባለ አዘርባጃናዊ አለምን እየዞረ ቪዲዮ ይሰራል። ይህ ቪዲዮ ኤርትራ ሄዶ የሰራው ነው።እዚህ ቪዲዮ ላይ ሰው እያናገረ በነበረበት ሰዓት አንድ ወጣት መጥቶ የሚጠይቀውን ስሙ ... " እባክህን አንድ ዳቦ የምገዛበትን ገንዘብ ስጠኝ " ነው የሚለው።ይህ ወጣት የሻዕቢያ ወታደር የነበረ መሆኑን ቪዲዮውን ያዩት ጓደኞቹ መስክረዋል። ያው ለጠቅላላ እውቀት ነው ¡¡
ሱዳን የሚገኘው የወያኔ ትርፍራፊ ታጣቂ ማምሻውን የRSF (የሂመቲ) ድሮን እራት ሆኗል ‼️ - Goodnight !